#Afar #Somali🚨
" የግጭቱ ማገርሸት ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱ ገልጿል።
ኮሚሽሙ ግጭቱ እንዳሳሰበውም አመልክቷል።
ኢሰመኮ በቅርቡ በሚያዚያ ወር የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በሶማሊ ክልል ሽንሌ ዞን እና አፋር ክልል አዋሳኝ ያገረሸው ግጭት አሳሳቢ ነው ብሏል።
ግጭቱ ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት እንዳሆነ ገልጿል።
በኮሚሽኑ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰኢድ ደመቀ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃል ፤ " የአሁኑ ግጭት የተጀመረው ከግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም 2024 ወዲህ ነው " ብለዋል።
" በግጭቱ የተወሰኑ ሰዎች ሞት፤ መፈናቀል እና የአካል ጉዳት፤ የንብረት መውደም እንደደረሰ ነው ያለው መረጃ በእኛ በኩል ግጭቱ እንዳገረሸ። በትክልል ስንት ሰው ሞተ፤ ቆሰለ የሚለውን ገና በምርመራ የምናጣራው ነው " ብለዋል።
" በአሁኑ ወቅት ግን ጠቅለል ባለ መልኩ የሰው መፈናቀል፤ ሞት እና ጉዳት እንዳለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ኢሰመኮ ከሁለቱ ክልሎች የመንግስት አስተዳዳሪዎች ተረዳሁት ባለው መሠረት ፥ በሁለቱም ክልሎች በኩል የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀሎች ተፈጽሟል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተገኘው አዎንታዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ሁለቱ ክልሎች ያሰጡትን አዎንታዊ ምላሽ ያደነቀው ኢሰመኮ፤ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲቀጥል የፌዴራልም ሆነ የሁለቱ ክልሎች መንግስታት የቀጠለውን ግጭት እንዲያስቆሙት ጥሪውን አቅርቧል።
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የግጭት ማስቆም ጥረት እንዲያስደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የሁለቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በቀጣይ ሕዝበ ሙስሊሙ ከሚያከብረው የኢድ አል-አደሃ በዓል አስቀድሞ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
#DWAmharic #EHRC
@tikvahethiopia
Rosewood furniture
For any inquiry :
Call us 📲 0905848586
Text us 💬 @Rosew0od
ኣድራሻ : 📍4ኪሎ ኣምባሳደር ሞል
📍 እንቁላል ፋብሪካ ሩፋኤል
📍 አያት አደባባይ ወደ ጣፎ መስመር
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇
/channel/R0seWood
/channel/R0seWood
/channel/R0seWood
#Tigray
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።
እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።
ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።
በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።
እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።
ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።
መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።
እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
° “ መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን ” - ማኀበራት
° “ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” - የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር
በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት በማኀበር ተደራጅተው ከቱሉዲምቱ እስከ ዓለም ባንክ ድረስ ቤት እየገነቡ የየበሩ ማኀበራት፣ “መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በሰጡት ቃል፣ “እንደ ማኀበር በጋራ ሆነን ጥያቄ አቅርበን እየተከታተልን ነው ከ3 ዓመታት በላይ የቆየነው። ‘ያኔ ለጊዜው ይቁም፣ በፍጥነት ምላሽ ይሰጣል’ ተብሎ ቆሞ ነበር አሁን ስንሄድ ነው የሚያናግረን ሰው ያጣነው” ብለዋል።
ቦታዎቹ #ከቱሉዲምቱ እስከ #ዓለምባንክ እንደሚገኙ አመልክተው፣ “ አጠቃላይ 960 ማኀበራት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 217ቱን ‘ መስተንግዶ ያግኙ ’ ብለው ለቀውላቸዋል። የቀረነው ግን ‘ ይለቀቃል ’ ተብሎ ለረጅም ጊዜ እየታሸን ነው ” ሲሉ አማረዋል።
➡️ ቤት ለመገንባት ከባንክ ገንዘብ የተበደሩ እንዳሉ፣
➡️ የባንክ እዳቸውን ከፍለው ባለመጨረሳቸው መሬታቸው ለጨረታ የቀረበ እንዳሉ፣
➡️ ቤታቸውን ለመሸጥ የፈለጉ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።
ይህ የሆነው ፣ “ ሕገ ወጥ #የመሬት_ወረራ በመኖሩ ኦዲት ይደረግ ” በሚል ሰበብ እንደሆነ፣ እነርሱ ግን መሬታቸው ሕገ ወጥ እንዳልሆነ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ከተማ አስተዳደሩ ኦዲቱን በፍጥነት አጣርቶና አጠናቆ እግዱን እንዲያነሳ ጠይቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የቅሬታ አቅራቢዎቹ ሰነድ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቱ ውል ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ የተገባ መሆኑን ፣ ከባንክ #በ100_ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደተበደሩ ያስረዳል።
ማኀበራቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ኃላፊዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
በከተማ አስተዳደሩ የቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይነህ አመርቆ ቅሬታውን በተመለከተ ለመናኸሪያ ሬዲዮ በሰጡት ቃል ግን፣ “ግለሰቦች በሌላ ማኀበር የከተማዋን ሀብት ለግል ጥቅም ለማዋል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይደረጉ እንደነበር ይታወቃል” ብለዋል።
“ ይህንምን መነሻ አድርጎም የተወሰኑ የታገዱ አሉ ፣ Specific የሚታወቁ ማለት ነው ” ብለው ፣ የእኚሁ አካላት ጉዳይ “ትክክለኛ ነው? ትክክል አይደለም ? የሚለው ነገር ተጣርቶ ውሳኔ የሚሰጣቸው ” እንደሆኑ አስረድተዋል።
“ ከዛ ውጪ ግን ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” ነው ያሉት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
በአቢሲንያ አሚን አገልግሎት ውስጥ “መሸ” የሚል ቃል አይታወቅም - ፀሐይም አትጠልቅም! በቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን 24 ሰዓት እርስዎን በሐቅ ለማገልገል ዝግጁ ነን!
አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
#ደባርቅ
° “ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ተበራክተዋል ” - የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች
° “ ከጥር ወዲህ ወደ 13 ሰዎች ራሳቸውን #መርዘው ሞተዋል ” - ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል
በአማራ ክልል ባደባርቅ ከተማ ፣ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች እየተበራከቱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
ነዋሪዎቹ በሰጡት ቃል፣ “ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ተበራክተዋል። የሟቾች ቁጥር በተለይ ከፋሲካ በዓል ወዲህ እየጨመረ ነው ” ብለዋል።
አንድ ሁነቱን በቅርበት የሚከታተሉ ታማኝ ምንጭ ፤ በቤተክርስቲያን አንድ የሃይማኖት አባት “ የሟች ቁጥር 63 መድረሱን ” ሲገልጹ መስማታቸውን ተናግረዋል።
እውነትም ሰዎች ራሳቸውን እያጠፉ ነው ወይ ? ተብሎ የተጠየቀው የከተማው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት፣ “ ራስን የማጥፋት አደጋዎች አሉ ፤ በተደጋጋሚ እየታዬ ያሉ። ኬዙ ግን ወደ ሆስፒታል ነው እየሄደ ያለው ” ብሏል።
ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የከተማው አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አለአምላክ ተስፋ በበኩላቸው፣ “ አዎ ችግሩ አለ። በጣም ብዙ ራሳቸውን ለማጥፋት የሚሞክሩ አሉ ” ሲሉ አረጋግጠዋል።
“ ከ13 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን መርዘው እኛ ማገዝ በማንችለው ስለመጡ የሞቱ አሉ ” ብለው፣ ሟቾቹም ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ በማድረጋቸው ምክር ሲሰጣቸው ከነበሩ 59 ሰዎች መካከል መሆናቸውን አስረድተዋል።
“ ከጥር ወዲህ ወደ 13 ሰዎች ራሳቸውን መርዘው ሞተዋል ” ያሉት ኃላፊው፣ ሰዎቹ ለድርጊቱ የሚገፋቸው የኢኮኖሚ መቃወስ ፣ ቤተሰብ #እንደሞተባቸው ሲሰሙ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዋናነት ግን ምክንያቱ #በጥናት መረጋገጥ አለበት ብለዋል።
ይህን መጥፎ ውሳኔ እየፈጸሙ ያሉት በተለይ ወጣቶች እንደሆኑ አስረድተው፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
⚽️ በላቀ ጥራት በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ እየተዝናኑ በጉጉት የሚጠበቀው የአውሮፓ ዋንጫ የልዩ ስሜት ተካፋይ ይሁኑ!
በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር 350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/4bVJ8Df
#Euro2024DStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#ትግራይ #ኢሮብ
ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነቱ በኃላም ቢሆን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የኢትዮጵያ፣ ትግራይ ኢሮብ ወረዳ 23 ት/ ቤቶች በኤርትራ ወታደሮች ስር ይገኛሉ።
በትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ ተነፃፃሪ የሆነ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ባለባቸው አከባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በቀጣዩ ሃምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመዘጋጀት ይገኛሉ።
ለፈተናው እየተዘጋጁ ያሉት ተማሪዎች በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ፤ ትግራይ ክልል በጊዜያዊ አስተዳደር ስር ያሉ ናቸው።
በወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ስር የሚታወቁ እና ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩት አንድ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙባቸው 23 ትምህርት ቤቶች ከ3 ዓመት በላይ #በኤርትራ_ወታደሮች_ቁጥጥር_ስር እንደሚገኙ በኢሮብ ወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤት ተገልጿል።
የትምህርት ቤቶቹ መምህራን እና ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል።
ቃላቸውን የሰጡ ተማሪዎች ፦
- ጦርነቱ ብዙ ነገሮች እንዳሳጣቸው
- አሁን በወረዳቸው ትምህርት ቤት የኢንተርኔት አቅርቦት ጨርሶ እንደሌለ
- ውሃ ፣ መብራት ፣ ትራንስፓርት የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እንደሌለ ጠቁመዋል።
ተማሪዎቹ በቴክኖሎጂ ታግዞ ከሚፈተኑ ተማሪዎች ጋር ተፈኳኳሪ ለመሆን እንደሚከብድም ገልጸዋል።
ያም ሆኖ ግን አሁን ላይ የተገኘው ዕድል እንዳያመልጥ ለመፈተን ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
መምህራን በበኩላቸው ፥ በወረዳው ያሉት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የክልሉና የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር እገዛ እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ነፃ ወጥተው የዘወትር አገልግሎት እንዲሰጡ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።
በወረዳው በጦርነት ምክንያት የትምህርት ሴክተር ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የወደመ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ምንም የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት በሌለበት ለመፈተን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ግምት ውስጥ በማስገባት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የእገዛ እጃቸው እንዲዘረጉ የወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።
ይህንን መረጃ የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማደረግ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
2 ዓመት ?
የህጻን ልጅ ፊት በጋለ ብረት ያበላሸው ወንጀለኛ ላይ የተወሰነው የ2 አመት ፍርድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነሳ።
አንድ ግለሰብ በጌዴኦ ዞን ፤ በይርጋጨፌ ከተማ የሚያሳድጋትን ልጅ " ጥፋት አጠፋሽ " በሚል በጋለ ብረት ፊቷን እጇንና እግሯን በማቃጠል ጉዳት አድርሶባታል።
በወቅቱ የህጻኗን ጉዳት የተመለከተውን መረጃ በአካባቢው ከነበሩ ነዋሪዎች የደረሰው ፖሊስ ህጻኗን ወደ ህክምና በመዉሰድ የተበላሸ ፊትና ሰውነቷ እርዳታ እንዲያገኝ በማድረግ ወንጀለኛውን በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
ጉዳዩን የያዘዉ የይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የሰውና የህክምና ማስረጃ ከተመለከተ በኋላ ግለሰቡ በ2 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ሰጥቷል።
ይሁንና በህጻኗ ላይ ከደረሰዉ አሰቃቂ ጥቃት አንጻር የተሰጠው ፍርድ አግባብ አይደለም ያሉ አካላት በተለይ ዜናውን የሰሙ ግለሰቦች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ይህን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጌዴኦ ዞን ፍትህ መምሪያን አነጋግሯል።
የመምሪያው ሀላፊ የሆኑት አቶ ብዙአየሁ ዘዉዴ ፥ የይርጋጨፌ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ 2 ዓመት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም በውሣኔ ላይ ዐቃቤ ህግ ቅሬታ ያለው በመሆኑ ይግባኝ ለጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ውሣኔውን ለሰጠዉ ፍ/ቤት መዝገብ ተገልብጦ እንዲሰጥ መጠየቁን ገልጸዋል።
ጉዳዩ በሂደት ላይ መሆኑን የገለጹት ሀላፊው ቅሬታዉ ህጋዊ መሰረት መያዙን ገልጸዉ ወደፊት ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጡን ቃል ገብተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቀጣይ የሚኖረዉን የፍትህ ሂደት ተከታትሎ የሚዘግብ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#SamiTech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ
አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ።
የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114
https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
#ረቂቅ_አዋጅ ፦ " በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ "
#የሕዝብተወካዮችምክርቤት #ኢትዮጵያ
#AntiMoneyLaunderingLaw
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#NationalBankofEthiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት የባንክ ስራን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ 5 መመሪያዎችን እንዳሻሻለ አሳውቋል።
እነዚህ መመሪያዎች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የተመደቡ ናቸው።
በመጀመሪያው ምድብ የሚካተቱት ፦
- “ የብድር ተጋላጭነት ጣሪያ ስለመወሰን”፤
- “ከባንኩ ጋር ዝምድና/ግንኙነት ባላቸው ወገኖች አማካኝነት ስለሚኖር የብድር ተጋላጭነት”
- “ስለንብረት ምደባ እና ለተዛማጅ ስጋቶች ስለሚያዝ የመጠባበቂያ ፕሮቪዥን ” የተመለከቱ መመሪያዎች ናቸው።
በ2ኛው ምድብ የሚካተቱት መመሪያዎች በባንክ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አካላት ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ መስፈርቶች እና የኩባንያ አስተዳደርን የሚመለከቱ ናቸው።
ከተደረጉ ማሻሻያዎች አንዱ ...
በከፍተኛ የብድር ተጋላጭነት ገደብ መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።
የመመሪያው ዓላማ አንድ ተበዳሪ (ተያያዥነት ያላቸው ወገኖችን ጨምሮ ) ከባንኩ ጋር በገባው ውል መሠረት ግዴታውን መወጣት ባለመቻሉ ምክንያት በባንኩ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ለመቀነስ እና የባንኮች የተጋላጭነት መጠንን በወቅቱ ለመቆጣጠር የሚያስችል በቂ ፖሊሲ እና አሠራር እንዲኖራቸው ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።
መመሪያው በባዝል መርህ መሠረት ማንኛውም ባንክ ለአንድ ወይም ተያያዥነት ላላቸው ደንበኞች የሚኖረው አጠቃላይ የብድር ተጋላጭነት ከባንኩ ጠቅላላ ካፒታል ከሀያ አምስት በመቶ (25%) እንዳይበልጥ ገድቧል፡፡
ይህ መመሪያ ተያያዥነት ያላቸው አካላት እንደ አንድ የባንክ ተበዳሪ ሆነው እንዲቆጠሩ ይደነግጋል።
(ተጨማሪ ማሻሻያዎችን ከላይ በተያያዘው ምስል ያንብቡ)
#NBE #TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Tigray
ህዝቡ በህብረት ስራ ማህበራት ስም ከሚፈፀሙ #የማደናገር እና #የማጭበርበር ተግባራት ራሱ እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ።
ይህን የማስጠንቅያ ጥሪ ያቀረቡት የትግራይ ፍትህ ቢሮና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ ሆነው ነው።
መንግስታዊ ተቋማቱ " አቦ " በሚል ስያሜ በቤቶች ግንባታና ልማት " ተሰማርቻለሁ ... ተመዝገቡ የቤት ባለቤት ሁኑ " በሚል እንቅስቃሴ በማካሄድ የሚገኘው የህብረት ስራ ማህበር እውግዘዋል ፤ እግድም ጥለዋል።
መንግስታዊ ተቋማቱ ባወጡት መግለጫ ፥ " አቦ " በሚል ስም የሚታወቀው የህብረት ስራ ማህበር ፥ " ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ በጋራ በትግራይ 5 ከተሞች ቤቶች ገንብቼ አስረክባሎህ " ብሎ ከሰነ 3/2016 ዓ.ም ያስጀመረው የምዝገባ እንቅስቃሴ ህጋዊ አይደለም ብለዋል።
" አቦ " የተባለ የህብረት ስራ ማህበር በ5 የትግራይ ከተሞች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ የተሰጠው መሬት የለም ያለው የትግራይ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ድርጅቱ ከድርጊቱ እንዲታቀብ አስጠንቅቋል።
የመኖሪያ የቤቶች ግንባታ በህብረት ስራ ማህበር የማደራጀት ስልጣን የተሰጠው ለፍትህ ቢሮ ነው ያለው የክልሉ ፍትህ ቢሮ ፥ " አቦ የቤቶች ግንባታ ህብረት ስራ ማህበር " በህግ ባልተፈቀደለት የስራ ዘርፍ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ እግድ እንደጣለበት አስገንዝቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
በአቢሲንያ አሚን አገልግሎት ውስጥ “መሸ” የሚል ቃል አይታወቅም - ፀሐይም አትጠልቅም! በቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን 24 ሰዓት እርስዎን በሐቅ ለማገልገል ዝግጁ ነን!
አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
#ብር #ዶላር
የፌዴራል መንግሥት #የ2017_በጀት ሲዘጋጅ ብርን ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሬ ተመን #የሚያዳክም ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል በሚል ታሳቢነት እንዳልሆነ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ለተወካዮች ም/ ቤት ተናግረዋል።
በኢ-መደበኛው እና በባንኮች በሚደረግ ይፋዊ ምንዛሬ (official exchange) መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ እርምጃን አስመልክቶ " ምንም የቀረበ ነገር የለም " ብለዋል።
አቶ አህመድ ፥ የፌዴራል መንግሥት በጀት የተዘጋጀው " የነበረው አካሄድ #እንደሚቀጥል ታሳቢ ተደርጎ " ሲሉ ገልጸዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ " ዘንድሮ የነበረውን ይፋዊ የውጭ ምንዛሬ መጠን (official exchnage rate) ታሳቢ አድርጎ ነው በጀቱ የቀረበው " ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህን ማብራሪያ የሰጡት በም/ቤቱ የኢዜማ ተወካይ ዶ/ር አብርሃም በርታ ፥ " ህጋዊውን እና ኢ-መደበኛውን የውጭ ምንዛሬ ገበያ እኩል ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች እንዳሉ ከአንዳንድ ወገኖች እየሰማን ነው ፤ ... የውጭ መንግስታት #በብድር_ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ ጫና በመፍጠር ይህንኑ ለማስፈጸም እንደሚንቀሳቀሱ የሚገልጹ መረጃዎችም አሉ ፤ እንዲህ አይነቱ እርምጃ የማንወጣው ችግር ውስጥ ይከተናል የሚል የባለሙያዎች ትንታኔ አለ " በማለት ላነሱት ሀሳብ ነው።
#EthiopianInsider #HoPR #TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን /የትምህርት ካላንደር/ ይፋ አደረገ።
የትምህርት ካላንደሩ በከተማው አስተዳደር ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ወጥነት ባለው መልኩ ይተገበራል ተብሏል።
ይፋ በተደረገው በዚህ የትምህርት ሰሌዳ መሰረት ፥ ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ከነሃሴ 21-30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የ7ተኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ እንደሚከቅናወን ፤ ከጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው የሚመጡ አዲስ የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚከናወን ተመላክቷል።
በከተማው መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ/ም መደበኛ ትምህርት እንደሚጀምር የትምህርት ሰሌዳው ያሳያል።
ከጥር 19 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የ2ኛ ወሰነ ትምህርት እንደሚጀምር ተመላክቷል።
የ2017 ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።
የትምህርት ካላንደሩ (ሰሌዳው) ከሰኔ 9 እስከ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ይገልጻል።
(ሙሉውን ከላይ ይመልከቱ)
@tikvahethiopia
በፍቅር እና መተሳሰብ በሚከበረው የኢድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል ልዩ ድምቀት የሆኑትን የሞባይል ጥቅሎች እስከ 25% በሚደርስ ቅናሽ ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው!
በቴሌብር ሱፐርአፕ ከ10% ስጦታ ጋር፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም *999# ለራስዎም ይግዙ፤ በበዓል ስጦታ ወዳጅ ዘመድ ይዘይሩ።
ቴሌብር ሱፐርአፕ ለማውረድ http://onelink.to/fpgu4m ይጠቀሙ!
ኢድ ሙባረክ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Info
ዋትስአፕ በድምጽ እና በምስል ጥሪ ላይ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል።
የቪዲዮ ጥሪ ተሞክሮን ለማሻሻል በሚደረገው እንቅስቃሴ ዋትስአፕ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል።
እነዚህ ማሻሻያዎች ዓላማቸው የዋትስአፕ ቪዲዮ ጥሪን የበለጠ ሁለገብ እና ምቹ ለማድረግ ነው ፣ በተለይ ለትላልቅ ቡድኖች።
ዋትስአፕ አዲስ ይዞ የመጣው አዲስ ነገር ምንድነው ?
▪️የቪድዮ ጥሪ ላይ የሚሳተፍ ሰው ብዛት ጨምሯል።
ዋትስአፕ በሁሉም መሳሪያዎች ማለትም ሞባይል፣ ዊንዶውስ እና ማክ-ኦኤስ ላይ በቪዲዮ ጥሪ ላይ መሳተፍ የሚችሉትን ሰዎች ብዛት ወደ 32 አሳድጎታል። ይህም ትላልቅ የቡድን ስብሰባዎችን ዋትስአፕ ላይ ማድረግን ያስችላል።
▪️ስክሪንን ከድምጽ ጋር ማጋራት እንዲቻል አድርጓል።
ይህ ማሻሻያ በቪዲዮ ጥሪ ጊዜ ስክሪን ላይ የሚታየውን ነገር ከማንኛውም ኦዲዮ ጋር ማጋራትን ያስችላል። ይህ በቀጥታ በዋትስአፕ ውስጥ አብሮ ቪዲዮ ማየትን፣ ወይም አብሮ መስራትን ያስችላል።
▪️ቨዲዮ ጥሪ ላይ ተናጋሪው ሰው ላይ ምልክት ማድረግ እንዲቻል አድርጓል።
በቡድን የቪዲዮ ጥሪ ውስጥ የሚናገረውን ሰው ላይ የተለየ ምልክት መስጠት ጀምሯል። ይህም በቡድን ውስጥ ያሉ ንግግሮችን ለመከታተል ቀላል ያደርገዋል።
የደውል ጥሪን የበለጠ ለማሻሻል በተለይም ደካማ ኔትወርክ ወይም ቆየት ያሉ ስልኮች ላላቸው ተጠቃሚዎች የዋትስአፕ እናት ኩባንያ ሜታ (Meta) የሜታ ሎው ቢትሬት (MLow) አስተዋውቋል።
ይህ ስርአት የተነደፈው ከተገቢው ባነሰ ኔትወርክ ሁኔታ ውስጥ እንኳን የተሻለ ጥራት ለማቅረብ ነው።
#TikvahTechTeam
@tikvahethmagazine
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
20% ቅናሽ ከሰኔ 01-21/2016 ዓ.ም ለሁሉም ተመዝጋቢዎች ። የግራፊክስ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ?
ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር።
በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።
በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል።
" በእርግጥም ፤ የBRICS አባል መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ፊዳን " ስለዚህ በዚህ አመት እንዴት እንደሚሄድ እናያለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ነገር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።
አናዱሉ እንደዘገበው ደግሞ ቱርክ የBRICS አባላት ሀገራትን ትብብር እየተመለከተች ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊትም ወደ ሩስያ አቅንተው ከBRICS አባሏ ሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በBRICS አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።
ፑቲን ከሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ቱርክ ስብስቡን ለመቀላቀል (አብሮ ለመስራት) ያሳየችውን ፍላጎት በደስታ ተቀብለው ፤ ወደ ስብስቡ እንድትቀላቀል ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
የቱርክ መንግሥት BRICS'ን ለመቀላቀል ርምጃ ይወስድ እንደሆነ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በይፋ ስብሰቡን ለመቀላቀል ያለውን ፍላጎት በይፋ አሳውቆ አያውቅም።
ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።
#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።
#BRICS
#Turkey
#China
#Russia
@tikvahethiopia
#NewTariff📈
" የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በሚቀጥሉት ሳምንታት ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ይቀርባል " - የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያዘጋጁትን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በመገምገም በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ እንደሚያቀርበው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሽያጭ ታሪፍን በማሻሻል ላይ ያተኮረ ስብሰባ ዛሬ ተደርጎ ነበር።
በዚህም ስብሰባ ላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት መከለስ የነበረበት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ያለ ማሻሻያ በመቆየቱ ተቋማቱን ለኪሳራ እንደዳረገ እና የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጫና ማሳደሩ ተነግሯል።
" ለዚህም የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ተብሏል።
ሁለቱ ተቋማት በተናጥል እና በጋራ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ላይ ጥናት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በሌላ አማካሪ ድርጅት ተገምግሞ ማሻሻያው ወደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መቅረቡ ተጠቁሟል።
ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ኃይል ለማመንጨትና ለማሰራጨት የተሰጣቸው ባለፍቃድ መስሪያ ቤቶች ያቀረቡትን የታሪፍ ማሻሻያ ፕሮፖዛል ገምግሞ የውሳኔ ሃሳቡን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ የማጸደቅ ኃላፊነት አለበት።
በነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አህመድ ሰኢድ ሁለቱ ተቋማት ጥናት በማድረግ ያቀረቡትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አህመድ ሰኢድ ምን አሉ ?
" መንግስት በሰጠን ስልጣን መሰረት መመሪያ አለን። እነዛን መመሪያዎች ተከትለው ነው ወይ ታሪፉን ያወጡት ? ለምሳሌ ታሪፍ ከጨመረ ገቢ ይጨምራል። ያን ታሳቢ በማድረግ አላስፈላጊ ወጪዎችን ጨምረው ከሆነ እኛ ነን የምንቆጣጠራቸው " ብለዋል።
በተጨማሪ ሁሉቱ ተቋማት ያስጠኑትን የታሪፍ ተመን በባለስልጣኑ መመሪያ መሰረት እንደተሰራ እንደሚገመገም ገልጸው " በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክርቤት ለውሳኔ ይቀርባል ሲሉ " ተናግረዋል።
የታሪፍ ማሻሻያው አሁን ያለውን ታሪፍ በምን ያህል ይጨምራል ? የሚለውን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አንዱአለም ሲአ " አሁን ላይ እዚህ ላይ ይደርሳል ለማለት አይቻልም " ብለዋል።
" ባለስልጣኑ ነው ቁጥሩን መጨረሻ ላይ አይቶ መርምሮ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አስገብቶ የሚያፀድቀው " ሲሉ አክለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ኢሠማኮ
አቶ ካሳሁንን በተመለከተ እውነታው ምንድነው ?
በቅርቡ 112ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) ጉባኤ ተካሂዶ ነበር።
በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በከፍተኛ ድምጽ የዓለም ሥራ ድርጅት አስተዳደር አካል (Governing Body) አባል ሆነው ተመርጠዋል።
ነገር ግን በማኅበራዊ ሚዲያዎች እና በሌሎች ሚዲያዎች መረጃዎች በተጨባጭ ካለው እውነታ በራቀና #በተዛባ መልኩ መዘገቡን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ዛሬ በላከልን ደብዳቤ አሳውቋል።
እውነታው ምንድነው ?
➡ አቶ ካሳሁን የዓለም ሥራ ድርጅት የአስተዳደር አካል ምክትል አባል (Deputy member of the Governing Body) ሆነው ተመርጠዋል።
ከዓለም ሠራተኞች 14 መደበኛ ( Regular) እና 19 ምክትል (Deputy) በአጠቃላይ 33 የሠራተኛ ተወካዮች ባላቸው ብቃት እና ልምድ በድምፅ ይመረጣሉ።
ከአሠሪም በተመሳሳይ ይመረጠሉ፡፡
የመንግሥት ከአሠሪና ሠራተኛ /ቁጥራቸው ከፍ ይላል።
ስብሰባቸውም በዓመት 3 ጊዜ በጥቅምት እና በመጋቢት ወራቶች ለአንዳንድ ሳምንት ሲሆን በሰኔ ወር ላይ ከሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በኃላ ለ1 ቀን ይሰበሰባሉ።
በቋሚነትም አይሠሩም። #ሹመትም_አይደለም።
➡ ይህ የአስተዳደር አካል (Governing Body) ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞችን የሚያፀድቅ ነው።
በየዓመቱ በእኤአ አቆጣጣር ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለሚካሄደው የዓለም ሥራ ድርጅት ጉባዔም (International Labour Conference) አጀንዳ ያዘጋጃል ፤ የበጀት ረቂቅ ያዘጋጃል ፤ እንዲሁም የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ይመርጣል።
እንዲሁም በዓለም ላይ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍንና በመንግሥት፤ በአሠሪ እና ሠራተኛ መካከል ማኅበራዊ ምክክር እንዲጠናከር ይሰራል።
አቶ ካሣሁን ፎሎ የተመረጡት የዓለም ሠራተኞች በመወከል የአስተዳደሩ አካል (Governing Body) ምክትል አባል ( Deputy member of Governing Body) ነው እንጂ ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር በመሆን የዓለም ሥራ ድርጅትን እንዲመሩ በማንኛውም የሥራ አስፈፃሚ ደረጃ #አልተሾሙም።
#ኢሠማኮ
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ
እናት ፓርቲ የሚያካሂደው ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል መሆኑን በመግላጽ መንግሥት በአባላቱ ላይ የሚያደርገውን ማሳደድ እና እስር እንዲያቆም አሳሰበ።
ፓርቲው ፤ የቅዱስ ላልይበላና አካባቢው ቅርንጫፍ አባሉ አቶ ሰብስብ ገናነው ከቤታቸው ተወስደው እንደታሰሩበት አሳውቋል።
አቶ ሰብስብ ሰኔ 4/2016 ዓ/ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው በመንግስት የታጠቁ ኃይሎች መወሰዳቸውን ፓርቲው ገልጿል።
ቤተሰቦቻቸው " መጠየቅ አትችሉም " በመባላቸው ምክንያት እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለ አመልክቷል።
እናት ፓርቲ ፥ " የአባላቶቼ አፈናና እስር የፖለቲካችን ስብራት አንድ ማሳያ ነው " ሲል ገልጾ " ትግላችን ሰላማዊ በመሆኑ መንግሥት አባላቶቻችንን እያሳደደ ማሰሩን ሊያቆም ይገባል " ሲል አሳስቧል።
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
20% ቅናሽ ከሰኔ 01-21/2016 ዓ.ም ለሁሉም ተመዝጋቢዎች። የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ ኮምፒውተርና ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ ገጾችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
#ይነበብ🚨
" በወንጀል የተገኘን ንብረት #ህጋዊ_ማስመሰልና #ሽብርተኝነትን_በገንዘብ_የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር " የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል።
በዚሁ ረቂቅ ላይ በክፍል 5 ' ስለ ምርመራ ' ሰፍሯል።
ረቂቁ ስለ #ምርመራ ምን ይላል ?
- በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት #የዳኝነት_አካላት ለተወሰነ ጊዜ፦
➡ በባንክ ሂሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ #ክትትል_ለማድረግ፤
➡ የኮምፒዉተር ሥርዓቶችን፣ መረቦችንና ሰርቨሮችን ለመለየት፣
➡ መገናኛዎችን #በክትትል ሥር ለማዋል ወይም #ለመጥለፍ፣
➡ ድርጊቶችን፣ ባህሪዎችንና ንግግሮችን በድምፅ እና በምስል #ለመቅረፅ እና #ፎቶግራፍ_ለማንሳት፣
➡ የደብዳቤ ልዉዉጦችን #ለመጥለፍ እና #ለመያዝ፤
➡ በሽፋን ሥር ስለሚደረግ ምርመራና በቁጥጥር ስር የሚደረግ ማስተላለፍ ለመጠቀም፣
የሚያስችል ትዕዛዝ #ለወንጀል_መርማሪ_አካላት መስጠት ይችላሉ።
- የመርማሪ አካል የተደነገጉትን የማስረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚችለዉ ፍርድ ቤት አስተማማኝ ምክንያት መኖሩን በማረጋገጥ #ሲፈቅድ_ብቻ ነዉ።
- መርማሪው አካል #አስቸኳይ_ሁኔታ_ካጋጠመው በአካባቢው ያለውንና የሚመለከተውን የዓቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ማስረጃዎችን ሊሰበስብ ይችላል፡፡
- መርማሪ አካል #ያለፍርድ_ቤት_ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ማስረጃ ለመሰብሰብ በጀመረ በ፵፰ ሰዓት ውስጥ ምክንያቶቹንና በዓቃቤ ሕግ የተሰጠውን ጊዜያዊ ፈቃድ ጨምሮ ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል። ፍርድ ቤቱ የጥያቄውን አግባብነት መርምሮ ለመቀበል ወይም ደግሞ ውድቅ ለማድረግ ይችላል፡፡
- ፍርድ ቤት የምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበስብ ለመርማሪ አካል ፈቃድ ሲሰጥ፡-
ሀ. ማስረጃ ስለሚሰበሰብበት ዘዴ እና ስለሚከናወንበት አግባብ፤
ለ. የሚከናወንበት ጊዜ በተመለከተ ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡
- የማስረጃ ማሰባሰቢያው ዘዴ ጠለፋ ወይም ክትትል እንደሆነ #ጠለፋዉ ወይም #ክትትሉ የሚደረግበትን የስልክ ፣ የፋክስ ፣ የሬዲዮ ፣ የኢንተርኔት ፣ የኤሌክትሮኒክስ ፣ የፓስታና የመሳሰሉትን የግንኙነት መስመሮች አድራሻ ወይም መለያ መጥቀስ አለበት፡፡
- ማንኛውም የመገናኛ አገልግሎት አቅራቢ በመርማሪ አካል ጠለፋውን ለማካሄድ ሲጠየቅ ጠለፋው በፍ/ቤት ወይም በአቃቤ ሕግ የበላይ ሃላፊ የተፈቀደ መሆኑን በማረጋገጥ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ አለበት፡፡
- በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሕግ አስከባሪ አካላት በጠለፋ የተገኘ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ #በጠለፋ_በተገኘበት_መልክ_በቀጥታ ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም፡፡
ሙሉ ረቂቅ አዋጁን በዚህ ያንብቡ 👇 /channel/tikvahethiopia/88222
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#NBE #Ethiopia
የብሔራዊ ባንክ የሕግ ማሻሻያ ፦
ከባንክ ጋር #ተዛማጅነት_ላላቸው_አካላት የሚሰጥ የብድር ተጋላጭነት ገደብ መመሪያ ላይ የሕግ ማሻሻያ ተደርጓል።
የዚህ መመሪያ ዓላማ አንድ ባንክ ተዛማጅነት ካላቸው አካላት ጋር በሚያደርገው ግንኑነት ብድር አግባብነት በሌለው መንገድ እንዳይሰጥ ለማድረግ ፣ የጥቅም ግጭት ለመቀነስ እንዲሁም ደግሞ ተዛማጅነት ካላቸው አካላት ጋር ባንኮች የሚያደርጉትን ማንኛውም ግብይት በተመለከተ በቂ የሆነ ክትትል ለማድረግ እና ያለ አድልዎ በተገቢው መንገድ የተሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።
ይህ መመሪያ በዋነኛነት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን #ገደቦች_ጥሏል።
ሀ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከባንክ ጋር ተዛማጅነት ላላቸው አካላት በማንኛውም ጊዜ የሚኖረው አጠቃላይ የብድር ተጋላጭነት ከባንኩ ጠቅላላ ከፒታል ከ15% እንዳይበልጥ፤
ለ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከባንክ ጋር ተዛማጅነት ላላቸው አካላት በሙሉ በማንኛውም ጊዜ የሚኖር አጠቃላይ የብድር ተጋላጭነት ከባንክ ጠቅላላ ካፒታል ከ35% እንዳይበልጥ፤
ሐ) አንድ ባንክ ተዛማጅ ከሆኑ ወገኖች ጋር ግብይት ሲፈጽም ከማናቸውም ተዛማጅ ካልሆኑ ወገኖች ጋር ግብይት ሲፈጽም ተግባራዊ በሚደረግ ሁኔታዎች ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልክ እንዲሆን እና ከዚህ በተለየ ሁኔታ እንዳይፈጸም ይደነግጋል።
/channel/tikvahethiopia/88218?single
#የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ባንክ
@tikvahethiopia
#ቴፒ #አሽከርካሪዎች
° “ ከቴፒ ቡና ጭነን ለመውጣት ተከልክለን ከቆምን ወር ሊሞላን ነው ” - አሽከርካሪዎች
° “ ክልል ኮሚቴ አቋቁቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ”- ቡናና ሻይ ባለስልጣን
የጫኑትን ቡና ይዘው እንዳይንቀሳቀሱ በመከልላቸው ያለምንም መፍትሄ ከሦስት ሳምንታት በላይ ለመቆም እንደተገደዱ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።
“ ለሥራ የምንወጣው ቤተሰቦቻችንንም ለማስተዳደር ነው ” ያሉት አሽከርካሪዎቹ፣ “ ሥራ ፈትተን የቆምንበት ጊዜ ቀላል አይደለም። እንኳን ቤተሰብ ልናስተዳድር ለእኛም ለእለት ለምግብ ገንዘብ ተቸግረናል ” ብለዋል።
“ የተከለከልንበትን ምክንያት እንኳን #አላወቅንም። መንግስት ግን አሽከርካሪዎች እያስተናገዱት ላለው ተደራራቢ ችግር መፈትሄ የማይሰጠው እስከመቼ ነው? ” ሲሉ ጠይቀዋል።
አንዳንዶቹ በወባ ተይዘው መተኛታቸውንም ለመስማት ችለናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሽከርካሪዎቹ ጉዳዩን በተመለከተ ይጠየቅልን ያሉት ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ችግር ለምን ተፈጠረ? ችግሩን ለመቅረፍስ ምን እየተሰራ ነው? ሲል ተይቋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፋ ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር፣ “ ቡና በአገር ኢኮኖሚ፣ የአገር ሀብት ነው። ይቺ ቡና ከሌለች አገርም የለችም ማለት ይቻላል። 40 በመቶ ገደማ ቡና ነው ይዞ ያለው ” የሚል ቃል ሰጥተዋል።
“ ግን ቴፒ ላይ እያደረጉ ያሉት የExport ቡናን በአፈር እያሹ፣ በውሃ እያሹ ወደ Local መልሰው ቡናው ለExport እንዳይሆን እያደረጉ ነው፤ አቅራቢዎቹ ” ብለዋል።
“ ጅምላ ነጋዴዎቹ ይሄ ቡና በውሃና በአፈር ታሸ እንጂ ንጹህ ስለሆነ ጥሩ ያወጣላቸዋል። ለመሸጥ ነው የሚፈልጉት ” ያሉት አቶ ሻፊ፣ “ ለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ መመሪያ አውጥተን ችግሩ እንዲቆም ብዙ ጊዜ ተናግረን ሳይፈታ ቀረ ” ሲሉ አስታውሰዋል።
አክለው፣ “ ይህ ብቻ ሳይሆን በአፈር የታሸ ቡናም መጋዚን ውስጥ አከማችተዋል። ይህ አገር ማጥፋት፤ አገርን ገቢ ማሻጣት ነው ” ብለዋል።
“ ላለፉት ስድስት (6) ወራት ቴፒ ብቻ ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ድረስ 34 በመቶ ንጹህ ቡና Local ነው የወጣው። ስለዚህ ምንም Local የማውጣት መብት የላቸውም። የሚያወጣው ማዘጋጃና ማከማቻም በአካባቢው የለም ” ነው ያሉት።
መፍትሄውን በተመለከተ ፤ “ አሁን ላይ ጉዳዩን ለክልል ሰጥተናል። ክልል ኮሚቴ አቋቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስለዚህም አሽከርካሪዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ የተደረጉት የExport ቡናን ወደ Local በሚለውጡ አቅራቢዎች መሆኑን ያስረዱት አቶ ሻፊ፣ “ እንደዚያ በሚያደርጉት ላይ ባለሙያዎች አጣርተው እርምጃ እንዲወሰድ ኮሚቴ ተቋቁሟል ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#SamiTech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ
አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ።
የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114
https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
#Ethiopia
የደቡብ ክልል ፈርሶ እንደ አዲስ የተዋቀሩት #ሁሉም አዳዲስ ክልሎች በጀት የሚደለደልላቸው በነበረው የድሮ ቀመር እንደሆነ ተገልጿል።
ገንዘብ ሚኒስቴር #አዲስ_ቀመር የማዘጋጀት ምንም ስልጣን እንደሌለው ይህ ስልጣን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሆነ አመልክቷል።
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ2017 በጀት ረቂቅን ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባብራሩበት ወቅት ስለ አዳዲሶቹ ክልሎች የበጀት ድልድል ቀመር ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
" ከደቡብ አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ #የትኛው_ቀመር ነው ? የሚለው የምክር ቤቱ ስልጣን እንጂ የገንዘብ ሚኒስቴር ስልጣን አይደላም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
" አዲስ ቀመር በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጠንቶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የነበረው ቀመርና በፌዴሬሽን ም/ቤት በፀደቀው መሰረት ነው ገንዘብ ሚኒስቴር ድልድል የሚያደርገው " ብለዋል።
ሚኒስትሩ ፥ ሁሌም የፌዴራል መንግሥት #ለክልሎች አጠቃላይ ምን ያህል በጀት ይመደብ ? በሚል ካለው አቅም አንጻር እንደሚያስቀምጥ አስረድተዋል።
አሁን የተበተኑት ክልሎች በደቡብ ክልል ስር አንድ ላይ በነበሩበት ጊዜ የወጣ ቀመር እንዳለ አስታውሰዋል።
አሁን እየተሰራበት ያለው ያ የቀድሞው ቀመር እንደሆነ ጠቁመዋል።
ቀመሩ ምንድነው ?
አሁን እየተገበረ ያለው ቀመር የቀድሞው ደቡብ ክልል የነበረው በጀት ለአራቱ ክልሎች #ይከፋፈላል።
መጀመሪያ ሲዳማ ሲወጣ ratio ተሰርቶ በዛ መንገድ ነው የተሰራው።
ደቡብ ምዕራብ ሲወጣም ratio ተሰርቷል።
ሌሎቹ ሁለቱም ሲወጡ ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ratio ተሰርቶ በዛ መንገድ ነው ድልድል የሚደረገው።
ይህ ደግሞ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት ነው የተካሄደው።
የነበረው ቀመር ማለት በአጭሩ ደቡብ ክልል በአንድ ላይ በነበረበት ወቅት ይመደብለት የነበረው በጀት በ ratio ለአዳዲሶቹ እንዲከፋፈል ይደረጋል።
አቶ አመህድ ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ቀመር ተገዛጅቶ ተግባር ላይ እስካልዋለ ይህኑን ተፈጻሚ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
" በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ህዝብ ቆጠራ አልቆ ፣ አጠቃላይ የeconomic census እና survey በሚገባ ተጠናቆ ፤ አዲስ ቀመር በሚዘጋጅበት ጊዜ እና የተሟላ ቀመር ሲኖር አዲሱን ቀመር መሰረት በማድረግ ተግባራዊ ይደረጋል (የበጀት ድልድሉ) " ብለዋል።
አዲስ ቀመር #የማዘጋጀት_ስልጣን ደግሞ የገንዘብ ሚኒስቴር ሳይሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣን እንደሆነ ተናግረዋል።
በአዳዲሶቹ ክልሎች ከበጀት ጋር በተያያዘ ፤ " የበጀት እጥረት " የሚሉ ጥያቄዎች እንደሚነሱ ይታወቃል።
የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ መዘግየትና በአግባቡ አለመክፈልም በስፋትም ከአዳዲሶቹ ክልሎች የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Ethiopia
የፌዴራሉ መንግሥት የ2017 ጠቅላላ የወጪ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።
ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበው 236.7 ቢሊዮን ብር ነው።
አጠቃላይ የ2017 በጀት (971.2 ቢሊዮን) በ2016 በጀት ዓመት ከጸደቀው የወጪ በጀት አንጻር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው ተገልጿል።
ዛሬ ከሰዓት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ምክር ቤት ቀርበው በረቂቅ በጀቱ ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም ወቅት ሚኒስትሩ ከ971.2 ቢሊዮን የወጪ በጀት ፦
➡ 451.3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ
➡ 283.2 ቢሊዮን ብር ለካፒታል
➡ 236.7 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበ እንደሆነ አሳውቀዋል።
ለክልል መንግሥታት ከተመደበው ጠቅላላ የበጀት ድጋፍ ውስጥ 14 ቢሊዮን ብሩ የዘላቂ የልማት ግቦችን ለማስፈጸሚያ የሚውል ነው።
ከጠቅላላው የፌዴራል መንግሥት በጀት ከፍተኛውን ድርሻ (የጠቅላላውን 46.5 በመቶ) የያዘው ለመደበኛ በጀት የተመደው እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ለመደበኛ ወጪ የተያዘው የበጀት ድልድል ሲታይ 127.2 ቢሊዮን ብሩ (28.2 በመቶ) ፦
° #ለደመወዝ
° #ለአበል እና ለልዩ ልዩ ክፍያዎች ተመደበ እንደሆነ ተናግረዋል።
ቀሪው 321.4 ቢሊዮን ብር ለስራ ማስኬጅ የተመደበ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለመደበኛው ወጪ ከተደለደለው በጀት ለእዳ ክፍያ የተያዘው 139.3 ቢሊዮን እንደሆነም አመልክተዋል።
ለእዳ ክፍያ ከተያዘው ውስጥ 54.8 በመቶ ለሀገር ውስጥ እዳ ክፍያ ፤ ቀሪው 45.2 በመቶ ለውጭ ሀገር እዳ ክፍያ እንደሚውል ገልጸዋል።
ለፌዴራል መንግሥት ካፒታል በጀት የተመደበው 283.2 ቢሊዮን ብር ሲሆን የወጪ አሸፋፈኑ ሽፋን ሲታይም ፦
° 216.5 ቢሊዮን ብር ከትሬዠሪና ከመስሪያ ቤቶች የውስጥ ገቢ ፤
° 39.8 ቢሊዮን ብር ከፕሮጀክት እርዳታ
° 26.9 ቢሊዮን ብር ከፕሮጀክት ብድር ለመሸፈን የተያዘ እንደሆነ አብራርተዋል።
ከጠቅላላይ የካፒታል በጀት ውስጥ 187.1 ቢሊዮን ብር ቅድሚያ ትኩረት ለተሰጣቸው ፦
☑ ለመንገድ
☑ ለትምህርት
☑ ለግብርና እና መስኖ
☑ ለመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን
☑ ለጤና
☑ ለገጠር እና ከተማ ልማት ሴፍቲኔት ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው ብለዋል።
በጦርነት ምክንያት የወደመውን ንብረት እና አገልግሎት ማስጪያ ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስ እና ለማቋቋም ለተጀመረ ፕሮጀክት ከመንግሥት ትሬዠሪ ብድር 20 ቢሊዮን ተደግፎ መቅረቡን አሳውቀዋል።
የቀረበው ረቂቅ በጀት ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia