tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527057

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

" የጥገኝንነት ጥያቄ ያቀረቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ይታወቃሉ ነገር ግን እነዚህ ተመላሽ ናቸው ለማለት አያስችልም "-የህግ ባለሞያ

የትራምፕ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ በርካታ ውሳኔዎችን እያስተላለፈ የሚገኝ ሲሆን አብዛኞቹ ውሳኔዎች በተለይም በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ የተለያዩ ሃገራት ዜጎችን በተለየ ስጋት ላይ የጣለ ሆኗል።

ህጎቹን ተከትሎ በተወሰዱ እርምጃዎችም በህገ ወጥ መንገድ የገቡ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ወደ መጡበት የመመለስ ስራዎች ተሰርተዋል።

በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ፦
- በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ መግባት፣
- ቪዛ ለማግኘት መዋሸት፣
- ያለ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ስራ መስራት
- የቪዛ ጊዜ ካበቃ በኋላ በአሜሪካ መቆየት ከባድ ቅጣት ያስከትላል ብሏል።

አምባሳደር ኤሪቪን ማሲንጋ ቅጣቶቹ እስርን፣ ወደ ሃገር መመለስን እና ዳግም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መከልከልን እንደሚያካትት የተናገሩ ሲሆን " በህገ ወጥ መልኩ በአሜሪካ የሚኖር ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ካላችሁ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የምትነግሩበት ጊዜ አሁን ነው " ብለዋል።

ከትራምፕ አስተዳደር በኋላ የወጡ አዳዲስ ህጎች ሳቢያ በርካታ የህጋዊነት ጥያቄዎች እና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት ሂደቶች አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸው እየተነገረ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እነዚህ አሰራሮች በስራቹ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው ስንል ኑሮዋቸውን በአሜሪካ ያደረጉት የህግ ባለሞያውን አቶ ሙሉአለም ጌታቸውን አነጋግሯል።

አቶ ሙሉአለም ጌታቸው በዝርዝር ምን አሉ ?

" የትራምፕ አስተዳደር የሚያወጣቸው የተለያዩ Executive ኦርደሮች ወይም ህጎች አሉ።

እነዚህ ህጎች የኢሚግሬሽን ላንድ ስኬፑን የሚያጠቡ ናቸው ማለትም ከዚህ ቀደም ብዙ ኦፖርቹኒቲዎች (እድሎች) ካሉ እነዛ ኦፖርቹኒቲዎች ጠበዋል።

ከባድ የሆነ ስክሪኒንግ (ምርመራ) የሚደረግበት ወቅት ነው ፋይሎች ይመረመራሉ።

ስራችን ላይ በጣም ከፍተኛ የሆነ ጫናን አሳድረዋል ደንበኞቻችንም ብዙዎቹ ተጨንቀዋል።

ምን ሊፈጠር እንደሚችል እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም።

የኢትዮጵያ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሚመለከት ከሌሎች ሃገሮች አንጻር ትልቅ የሚባል የጥገኝነት ጥያቄ የለም በጣም ትልልቅ የጥገኝነት ጠያቂ ሃገሮች ኢኳዶር ፣ጓቲማላ፣ ኤልሳልቫዶር እና ሜክሲኮ ናቸው።

ከአለም ደግሞ ከቻይናና ህንድ የሚመጡ ስደተኞች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ።

ከአፍሪካም የምዕራብ አፍሪካውያን ቁጥር ከምሥራቅ አፍሪካውያን ቁጥር ይበልጣል።

የኢትዮጵያ ቁጥር ከሌሎች ሃገራት ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የማይባል ቢሆንም ካለፉት ሦስት አመታት ወዲህ ግን በኢትዮጵያ ካሉ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

ትልልቅ አቅም ያላቸው ሰዎች እንኳን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ አደጋ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ እዚህ ጥገኝነት የመጠየቅ ሂደት ውስጥ ነው ያሉት።

በማንኛውም ሰዓት ብዙ ነገሮች ሊቀየሩ ይችላሉ ከአንድ ወይም ሁለት ዓመት በኋላ ምናልባትም ለጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ አሁን ከምንጠብቀው በላይ እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ አሁን ያለው ሲስተምም ሊቆም ይችላል።

እቅድ እና ፖሊሲያቸው ለህዝብ ይፋ ሆኖ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል የሚባልበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው።

የግሪን ካርድ (ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ) ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ አካላት ሁልጊዜ ህጋዊ በሆነ መንገድ አሜሪካን ውስጥ መቆየት፣ ከወንጀል መራቅ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ ቀደም የግሪን ካርድ ጥያቄ ያቀረበ ሰው ጠጥቶ መንዳት ጥፋት ቢገኝበት ወደ ዲፖርቴሽን አያመራም ነበር አሁን ግን በቀጥታ ወደ ዲፖርቴሽን ሊወስዱት ይችላሉ።

እነዚህን ጉዳዮች በብዛት የምንመለከተው ተማሪዎች ላይ ነው በትምህርት ቪዛ የመጡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ዴይ ፓርቲዎች ስላሉ እነዚህ ላይ አሳልፈው ወደ መንዳት ውስጥ እንዳይገቡ በጣም መጠንቀቅ ይጠበቅባቸዋል።

ሌላው የአሜሪካን ብሔራዊ ጥቅም የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ አቋም አለመውሰድ ወሳኝ ናቸው።

አሜሪካዊ ሚስት ያገባ ኮሎምቢያዊ ዜጋ በቅርቡ ሃማስን በመደገፉ ምክንያት ወደ ዲቴንሽን ማዕከል እንዲገባ ተደርጓል።

የጥገኝንነት ጥያቄ ያቀረቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ይታወቃሉ ነገር ግን እነዚህ ተመላሽ ናቸው ለማለት አያስችልም አብዛኞቹም ፕሮሰሳቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው ያላቸውን እድል በሙሉ አሟጠው እስከሚጠቀሙ ድረስ ይህን ያህሉ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ብሎ መናገር አይቻልም " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሌሎች ፕሮጀክቶች የካሳ ክፍያ እና የስራ ልምድ ሰጥተው ነው ያሰናበቱት እኛን ግን ዞሮ ብሎ የሚያየንም አጥተናል "- ቅሬታ አቅራቢዎች

➡️ " አስፈላጊው ጥቅማ ጥቅማቸው እንዲከበር ጥያቄ አቅርበናል ገንዘብ ለጋሹ አካል ይህንን የሚፈቅድ ከሆነ እንሰጣቸዋለን "- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት (USAID/Ethiopia) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሀገሪቱ ያለውን የአደጋ መከላከል ፣አመራርና፣ ባለሙያ የሰው ኃይል አቅም ለማሳደግ " የአደጋ ምላሽ ሥራ አመራር ሀገር አቀፍ የአቅም ግንባታ መርሃ ግብር " የተሰኘ ፕሮግራም ከአጋር ዩኒቨርሲቲዎች እና ተቋማት ጋር ሲተገብር ቆይቷል።

በዩኤስ ኤይድ ስር የነበሩ 83 በመቶ ፕሮጀክቶች እንዲቋረጡ መታዘዙን ተከትሎ ፕሮጀክቱ ከየካቲት 21/2017 ዓ/ም ጀምሮ የተቋረጠ ሲሆን በስሩ የነበሩ የኮንትራት ውል ሰራተኞች የስራ ቅጥር ውላቸው የተቋረጠ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ በማግስቱ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

ፕሮጀክቱ በሦስት ዙር መርሃ ግብር መልምሎ በተለያየ ጊዜ በኮንትራት ከቀጠራቸው አጠቃላይ 450 ሰራተኞች ውስጥ የሁለት ዓመት ውላቸውን ያገባደዱት በመጀመሪያ ዙር የተቀጠሩት 120 ሰራተኞች ብቻ ነበሩ።

ፕሮጀክቱ የተቋረጠው በመጀመሪያ ዙር የተቀጠሩት ሰራተኞች የሁለት ዓመት ውላቸው ሊያበቃ አንድ ወር ሲቀራቸው፣ በሁለተኛው ዙር የተቀጠሩት 10 ወር ሲቀራቸው ፣በ ሦስተኛ ዙር የተቀጠሩት ደግሞ አንድ ወር ብቻ እንዳገለገሉ ነው።

በፕሮጀክቱ ታቅፈው ሲያገለግሉ የነበሩ ሰራተኞች የውል ማቋረጫ ክፍያ እና የስራ ልምድ ሳይጻፍልን ስራችን በመቋረጡ ለችግር ተዳርገናል ያሉ ተቀጣሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

በዝርዝር ባቀረቡት ቅሬታ ምን አሉ?

" ፕሮጀክቱ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የአደጋ ስጋት አመራር ፅፈት ቤት ባሉ፥ከወረዳ እስከ ፈደራል ደረጃ ፥ እንዲሁም በእንዲስትርያል ፓርኮችን(IPDC) ጨምሮ 450 ሰራተኞችን እያሰራ ነበር።

የዩኤስ ኤይድ ፕሮጀክቶች መቋረጣቸውን ተከትሎ ውላችን እንደተቋረጠ የሚገልፅ ደብዳቤ ደረሰን።

አንድ ፕሮጀክት ከሰራተኞቹ ጋር ያለውን ውል ሲያቋርጥ የካሳ ክፍያ፣ የትራንስፖርት፣ የስራ ልምድ ይሰጣል።

አብዛኛው ከዩኤስኤአይዲ ድጋፍ ያገኙ የነበሩ እና የተቋረጡ በእኛ አካባቢ የነበሩ ፕሮጀክቶች ለሰራተኞቻቸው የካሳ ክፍያ እና የስራ ልምድ ሰጥተዋል። 

የእኛ ፕሮጀክት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስር የነበረ በመሆኑ የአንድ ወር ደሞዝ እና የስራ ልምድ ብቻ ስጡን ብለን ነበር ነገር ግን እኛን ዞር ብሎ የሚያየን ሰው አጣን።

ፕሮጀክቱን ወክሎ ውላችን እንደተቋረጠ ለኛ ደብዳቤ የፃፉ ሰውን ደውለን ስንጠይቃቸው እኛም ተባርረናል ነው የሚሉን።

ሌሎች ፕሮጀክቶች የካሳ ክፍያ እና የስራ ልምድ ሰጥተው ነው ያሰናበቱት እኛን ግን ዞሮ ብሎ የሚያየንም አጥተናል።

እኛ እንደተመረቅን ነው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ወደ ፕሮጀክቱ የተቀላቀልነው ሌላ ቦታ ምንም ልምድ የለንም እየጠየቅን ያለነው የስራ ልምድ እንዲጻፍልን እና የኮንትራት ማፍረሻ ክፍያ እንዲጠየቅልን ነው " ብለዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አየነው አዲጎ ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ፕሮጀክቱ ተቋርጧል የፕሮጀክቱ አባላት ያሉት እዚህ ዋናው ቢሮ ብቻ ነው እነሱ የፕሮግራሙ አካል ናቸው።

ተቀጣሪ ሳይሆኑ በየወሩ ስራ እንዲለምዱ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር አታች አድርገው የሚቆዩ ነበሩ ለሁለት ዓመት እኛም ለፕሮጀክቱ እንከፍል ነበር።

ፕሮጀክቱ ሲቆም ምንም ማድረግ ስለማንችል የስራ ውላቸው መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ ጻፍንላቸው።

እነሱም ወደ ቤት መሄጃ ገንዘብ ሳይሰጣቸው ፣የየካቲት ወር የኪስ ገንዘብም ሳይከፈላቸው ነው የተበተኑት።

ልትከፍሏቸው ይገባል ብለን እየተከራከርን ነው ከፈቀዱልን እንሰጣለን ምንም ጥያቄ የለውም እንደ ተቋም ግን ጥያቄ ልናቀርብ እየተዘጋጀን ነው።

የእኛንም ሁኔታ ያለ መገንዘብ ነገር ያለ ይመስለኛል የተወሰነ ፕሮጀክቱን በፕር ታይም ቢሆን ወርክ አውት የሚያደርግ ሰው ክፈሉና ፕሮጀክቱን እንዝጋ ብለን እያልን ነው።

አስፈላጊው ጥቅማ ጥቅማቸው እንዲከበር ጥያቄ አቅርበናል ገንዘብ ለጋሹ አካል ይህንን የሚፈቅድ ከሆነ እንሰጣቸዋለን እኛ የመንግስት መስሪያ ቤት ነን በእነሱ ስም ጠይቀን ገንዘብ አናስቀርም።

ሰርተፍኬትን በሚመለከት ግን የስራ ልምድ አንጽፍም ብለን አልተናገርንም በፍጹም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#USA #China

ቻይና በአሜሪካ ላይ አፀፋዊ የሆነ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች።

ቻይና ከዚህ በፊት ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84% ታሪፍ ጥላ የነበረ ሲሆን ዛሬ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች።

የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ84% ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቀዋል።

የትራምፕ አስተዳደር  በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለፀ ሲሆን የሃገራቱ የንግድ ጦርነት ውስጥ መግባት ትልቅ ስጋትን እየፈጠረ ይገኛል።

የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር አሜሪካ ተጨማሪ ታሪፍ መጣሏን ከቀጠለች በአለም የኢኮኖሚ ታሪክ አስቂኙ ነገር ይሆናል ያሉ ሲሆን ከዚህ በኋላ አሜሪካ ታሪፍ ከጣለች ቻይና ምላሽ አትሰጥም ብለዋል።

የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሜሪካ ጤነኛ ያልሆነ እና አለም አቀፍ የንግድ ህጎችን የጣሰ ውሳኔ እየወሰነች ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም አሁን ባለው የታሪፍ ምጣኔ ከአሜሪካ ወደ ቻይና የሚገቡ ዕቃዎች ገበያ አይኖራቸውም ያሉ ሲሆን የቻይና የንግድ ሚኒስትር ቃለ አቀባይ ደግሞ ቻይና ከአሜሪካ ጋር በእኩል ተቀምጣ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ  የታሪፍ ጦርነት ማንንም አሸናፊ አያደርግም ያሉ ሲሆን ከአለም በተቃራኒ መጓዝ እራስን ከአለም ማግለል ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅትም የአውሮፓ ህብረት ከቻይና ጎን በመቆም አሜሪካ የምታደርገውን ትንኮሳ እንዲቃወም ጠይቀዋል።

ቻይና ለአሜሪካ የምትልካቸው ዕቃዎች የሃገሪቱን ጥቅል ምርት 3% እንደሚይዙ የተገለፀ ሲሆን በቻይና ከ10-20 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች ወደ አሜሪካ ከሚላኩ ዕቃዎች ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን እንደሚመሩ ተገልጿል።

ቻይና አዲሱን ታሪፍ የጣለችው አሜሪካ ከቻይና የሚገቡ ዕቃዎች አጠቃላይ 145% ታሪፍ እንደሚጠብቃቸው ካሳወቀች በኋላ ነው።

ቻይና በአሜሪካ ላይ የጣለችው አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባም ተዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ CNBC እና Reutersን እንደ መረጃ ምንጭነት ተጠቅሟል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እቅዴ ለትግራይ ሕዝብ ኑሮ መሻሻል አስተዋጽኦ ማድረግ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት አቶ ጌታቸው ረዳ በትላንትናው ዕለት ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ስለ ቀጣይ የፖለቲካ ተሳትፏቸው ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " አንዴ እዚህ ጉዳይ ውስጥ ከገባንና አንዴ ለትግራይ ሕዝብ አዲስ መንገድ መጠቆም ከጀመርን ፤ ብዙ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ። እንዲሁ ተነስቼ እንቅስቃሴውን መተው አልችልም " ሲሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደማያቆሙ ገልጸዋል።

" የትኛውም ቦታ ብሆን በእርግጠኝነት በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ እሳተፋለሁ " ያሉት አማካሪ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ " እቅዴ በዚህ ሁኔታ መቆየት እና ለትግራይ ሕዝብ ኑሮ መሻሻል አስተዋጽኦ ማድረግ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሹመት : የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የቀድሞውን የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን እስከ ምሽት 4:00 በማይሰጡ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር የትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ከምሽቱ 4፡00 በፊት ፦
- የትራንስፖርት አገልግሎትን ማቋረጥ፣
- ከስምሪት መስመር ውጪ አገልግሎት መስጠት፣
- አቆራርጦ መጫንና
- ቢሮው ካወጣው ህጋዊ ታሪፍ ውጪ ህብረተሰቡን ማስከፈል እንደማይቻል በጥብቅ አሳስቧል።

ከዚህ አሰራርና መመሪያ ውጪ በሚንቀሳቀሱ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ #ባለንብረቶች እና #አሽከርካሪዎች ላይ የ5000 ብር (አምስት ሺህ ብር) ቅጣት እንደሚጣልበት አሳውቋል።

#TransportBureau

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የአካባቢው ባለስልጣናትም ስለ ዋጋ ጭማሬው መረጃ እየሰጡን አይደለም። ... በመንግስት እየቀረበ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ ደግሞ አርሶ አደሩ እንዳይገዛ  ታጣቂዎቹ እየከለከሉ ነው " - አርሶ አደሮች

በአማራ ክልል መንግስት በሚያስተዳድራቸው አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የማዳበሪያ ዋጋ በእጥፍ መጨመሩ እንዳሳሰባቸው ሲገልፁ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ደግሞ መንግስት ያስወደደውን ማዳበሪያ እስኪቀንስ እንዳይገዙ በታጣቂዎች መከልከላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አርሶአደሮቹ ፥ " የአካባቢው ባለስልጣናት ስለ ዋጋ ጭማሬው መረጃ እየሰጡን አይደለም ፤ በዋጋ ጭማሬው ዙሪያ እና ለሌሎች ጥያቄዎቻችን ማብራሪያ የሚሰጠን አካል አላገኘንም " ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።

በሁለት ሳምንት በአፈር ማዳበሪያ ዙሪያ ለምክር ቤት እንደራሴዎች ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር ) መንግስት በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ 3 ሺህ 700 ብር ድጎማ አያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አርሶአደሮች በዝርዝር ምን አሉ ?

በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦከምክም ወረዳ ነዋሪ መሆናቸውን የሚናገሩት አርሶ አደር አይጠገብ መንግስቱ በዘንድሮው ዓመት የአፈር ማዳበሪያ በመንግስት በስፋት መቅረቡን ይናገራሉ።

ይህ አሰራር ደግሞ ከዚህ ቀደም በጥቁር ገበያ በኩል በውድ ዋጋ አርሶ አደር የሚደርስበትን እንግልትና ምዝበራ ያስቆመ ነው ብለዋል። አርሶ አደሩ አክለውም በመንግስት እየቀረበ ያለው ማዳበሪያ ግን በእጅጉ መወደዱን ይናገራሉ።

ከዚህ ቀድም ኩንታሉን 4 ሺ ብር ይገዙት የነበረው የአፈር ማዳበሪያ ዘንድሮ ግን 8 ሺህ 3 መቶ ብር ሁኗል ብለዋል።

አርሶ አደሩ በአካባቢው ያሉ የመንግስት ባለስልጣናትን የዋጋ ጭማሪውን በተመለከተ ምክንያቱን እንዲነግሩን ስንጠይቅ መልስ አይሰጡንም ሲሉ ገልጸዋል።

ለአርሶ አደሩ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡን የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበጀ ስንሻውን የእጅ ስልካቸው ላይ ደጋግመን ብንደውልም ስልኩ ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

በሰሜን ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ይነሳ ሶስቱ በተባለ ቀበሌ ነዋሪ መሆናቸውን የገለፁልናና ስማቸውን በዘገባው እንዳንጠቅስ የጠየቁን ግለሰብ እርሳቸው የሚኖሩበት አካባቢ በታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መሆኑን ገልፀው በመንግስት እየቀረበ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ አርሶ አደሩ እንዳይገዛ  ታጣቂዎቹ እየከለከሉ ነው ብለዋል።

ምክንያታቸው ደግሞ " መንግስት ዋጋውን ያስወደደው አውቆ ነው የሚገዛው ሲያጣ  ዋጋ ይቀንሳል በማለት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

እኝሁ ግለሰብ አክለውም የታጣቂዎችን ማስጠንቀቂያ ችላ ብሎ ማዳብሪያ የገዛን አርሶ አደር በገንዘብ እየተቀጣ እንደሆነ ተናግረዋል።

" የታጣቂዎችን ማስጠንቀቂያ ያለፈ የማዳበሪያውን ዋጋ 8000 ብር አስከፍለዋል " ብለዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በአፈር ማዳበሪያ ዙሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር ) የማዳበሪያ ዋጋ አምራቹ ተምኖ ለገበያ በማቅረቡ ዋጋ መጨመሩን ገልፀው መንግስት ለአርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርሰው ድጎማ ያደርጋል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ መንግስት በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ 3 ሺህ 700 ብር ድጎማ አያደረገ መሆኑንና በዚህ ዓመትም 84 ቢልየን ብር መንግስት መደጎሙን በዚሁ ወቅት ገልጸው ነበር።

የግብርና ሚንስቴር በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ 24 ሚሊየን ኩንታል ገደማ የአፈር ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግ ገልፆ ከዚህ ውስጥ ለ13.4 ሚልየን ኩንታሉ ግዥ መፈፀሙን እስካሁንም ከ4ሚልየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ  ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ከሳምንታት በፊት መግለፁ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyBDR

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የትራምፕ የታሪፍ ጦርነት ወዴት ያመራ ይሁን ?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራት ላይ የሚጣል አዲስ ታሪፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ በተለይም ከቻይና ጋር ተፋጠዋል።

ትራምፕ ከዚህ በፊት ሌሎች ሀገራት የአሜሪካ ምርቶች ላይ ከሚገባው በላይ ታሪፍ ጥለዋል ብለው እንደሚያምኑ እና ይህንን የሚስተካከል ታሪፍ እንደሚጥሉ ከተናገሩ በኋላ ነው አዲሱን ታሪፍ ያስተዋወቁት።

በመጀመሪያው ዙር ፕረዚዳንት ትራምፕ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ 104 % ቀረጥ ጥለው የነበረ ሲሆን ቻይና በምላሿ (Reciprocal Tariff በተለምዶ አንድ ሃገር የሆነ ሃገር ላይ ታሪፍ ስትጥል በምላሹ ሌላኛዋ ሃገር የምትጥለው ታሪፍ) 84% ከአሜሪካ በሚገቡ እቃዎች ላይ ቀረጥ መጣሏን ገልጻለች።

አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችው ቀረጥ ዝርዝር ምን ይመስላል ?

➡️ 10% አዲስ ቤዝ ታሪፍ (ይህ በኢትዮጵያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የተጣለ ትንሹ ቀረጥ ነው)

➡️ 20% ነባር ታሪፍ

➡️ 34% ተመጣጣኝ / reciprocal ታሪፍ (በፊት ቻይና በአሜሪካ ላይ ጥላው የነበረችውን ታሪፍ መጠን ያክል)

➡️ 50% ለቻይና ያለፉት ድርጊቶች ቅጣት የተጣለ ታሪፍ ያካተተ ነው።

አሜሪካ ይህንን የታሪፍ ዝርዝር ይፋ ካደረገች በኋላ በርካታ ሀገራት ግብረ መልስ ቢሰጡም ዛሬ ከአሜሪካ በኩል የተሰማው መረጃ ተደራራቢ ታሪፍ የተጣለባቸው ሀገራት (ከ10 በመቶ በላይ) ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለመነጋገር መጠየቃቸውን ይገልጻል።

በዚህም ምክንያት የአሜሪካ አስተዳደር ለ75 ሀገራት ከፍተኛ ሽኩቻ ውስጥ ገብታ የነበረችው ካናዳን ጨምሮ ሜክሲኮ፣ ጃፖን ፣ደቡብ ኮሪያ እና ለአውሮፖ አባል ሀገራት የ90 ቀን የታሪፍ እቀባ (አዲሱ ታሪፍ እንዳይፈጸም የተቀመጠ #የእፎይታ_ጊዜ) ሰጥቷል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ እነዚህ 75 ሀገራት ከአሜሪካ መንግስት ጋር ድርድር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተቃራኒው ግን የቻይና መንግስት ለአሜሪካ አዲስ ታሪፍ ተመጣጣኝ ያለውን የ84 በመቶ ታሪፍ መጣሉን ባስታወቀ በሰዓታት ውስጥ አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችውን የታሪፍ መጠን ወደ 125 ከፍ አድርገዋለች።

ቻይና ከዚህ በተጨማሪ 18 የአሜሪካ ተቋማትን በተለይም ከወታደራዊ ምርት ጋር የተያያዙ ተቋማትን ዝርዝር በማውጣት እገዳ ጥላለች።

እንደ አማራጭም የቻይና የመገበያያ ገንዘብ የሆነው ይዋን (yuan) የመግዛት አቅምን ከዶላር አንጻር በማዳከም ምርቶቿ ይበልጥ በገቢያው ተወዳዳሪ እንዲሆኑም እየሰራች ነው።

ለምሳሌ ፦ አሜሪካ በቻይና ላይ የምትጥለው ታሪፍ የቻይናን ምርቶች የሚያስወድዱት ከሆነ የይዋን መዳከም ምርቶቹን ርካሽ ያደርጋቸዋል።

የዓለም ንግድ ድርጅት ይህ በዚህ ከቀጠለ የአሜሪካ-ቻይናን ንግድ እስከ 80% ሊቀንስ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ዓለምአቀፍ
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እሳቱ 3 ሰዓት በፈጀ ርብርብ በጣቢያው ሰራተኞች እና በአካባቢው ማህበረሰብ እንዲጠፋ ተደርጓል " - የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ

በዛሬው ዕለት ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ ከጅቡቲ ወደ ሞጆ የባቡር ጣቢያ ኮንቴነሮችን ጭኖ ሲያቀና የነበረ ባቡር ላይ የኮንቴነር ቃጠሎ መከሰቱን ለማወቅ ተችሏል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የሰጠየቃቸው የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክሲዮን ማህበር የኮምዩኒኬሽን ባለሞያ ወ/ሮ እስራኤል ወልደ መስቀል በቃጠሎው የሞተር ዘይት የጫነ ኮንቴነር ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።

ወ/ሮ እስራኤል " ሰባት ሰዓት ላይ 26 ፉርጎዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ባቡር ለጊዜው ምንነቱ ባልታወቀ ምክንያት የመጨረሻው ፉርጎ ከጫናቸው ሁለት ኮንቴይነሮች ላይ በአንዱ የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል " ብለዋል።

ቃጠሎው ባጋጠመበት ወቅት ባቡሩ በሱማሌ ክልል ወደ ሚገኘው ቢኬ ባቡር ጣቢያ ገብቶ መቆሙን እና እሳቱም 3 ሰዓት በፈጀ ርብርብ በጣቢያው ሰራተኞች እና በአካባቢው ማህበረሰብ እንዲጠፋ መደረጉን አክለዋል።

እሳቱ በተነሳበት ወቅት የመጨረሻው ፉርጎ ከጫናቸው ሁለት ኮንቴይነሮች ውስጥ አንዱ የጫነውን እቃ በማውጣት ከእሳቱ ማትረፍ ቢቻልም የሞተር ዘይት የጫነው አንደኛው ኮንቴይነር ሙሉ በሙሉ ወድሟል ነው ያሉት።

ለሦስት ሰዓታት የቆየው እሳቱ በኮንቴይነሩ ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በቃጠሎው ወቅት ኮንቴነሩ በመቅለጡ የባቡር መስመሩ እና የኤሌክትሪክ መስመሩ ላይ ጉዳት መድረሱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔈 #የሠራተኞችድምጽ

ማንነትን መሰረት ባደረገ ግጭት ምክንያት ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለው የነበሩ የጭልጋ ማረሚያ ቤት ሰራተኞች በክልሉ ምክር ቤት ወደ ሥራ ገበታቸው አንዲመለሱ ትዕዛዝ ቢተላለፍም ተፈፃሚ አልሆነም ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል።

ቁጥራቸው 18 የሚሆኑ የፖሊስ አባላትና ሲቪል ሰራተኞች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አንደገለጹት፥ በ2013 ዓ.ም መጨረሻ ላይ በምዕራብ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አካባቢ በነበረው ማንነትን መሰረት ያደረገ ግጭት ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለው የነበሩ የመንግስት ሰራተኞች ወደ ቦታቸው ይመለሱ የሚል ትዕዛዝ ከመጋቢት 1 / 2017 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ምክር ቤት ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልፀዋል።

ደብዳቤው ለክልል፤ ለዞንና ለወረዳ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተሰራጨ ሲሆን በደብዳቤው መሰረት በወረዳው ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች እየተመደቡ ነው ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ።

ሆኖም " የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት የነበርን ሰራተኞች ግን ልንመደብ አልቻልንም " ብለዋል።

ምክንያቱን ለማወቅ ከወረዳ እስከ ክልል በደብዳቤ ቅሬታችንን ብናሳውቅም አጥጋቢ መልስ አላገኘንም ነው ያሉት ሠራተኞቹ።

ቲክቫህ ኢትዮጽያ የወረዳውን ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ኮማንደር አዱኛ ጌታሁን በስልክ ጠይቆ ከሰራተኞች ጋር እየተነጋገሩ እንደሆኑ ጠቅሰው ተጨማሪ መረጃ ግን ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው ፤ " የክልሉ መንግስት ያስተላለፈው ውሳኔ ተፈፃሚ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም እስካሁንም ደብዳቤው ስላልደረሰን ነው። የሰራተኞች ቅሬታ በቅርቡ ይፈታል " ብለዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት የካቲት 25/2017 ዓ.ም በሳለፈው ውሳኔ በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በነበረው ግጭት ምክንያት ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለው የነበሩ የመንግስት ሰራተኞች ከመጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲሱ በተሻሻለው የደሞዝ ስኬል መሰረት እየተከፈላቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔ ማስተላለፍን ለተቋማት በተፃፈ ደብዳቤ  ለማወቅ ተችሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#CBE

🔴 “ መንግስት ከንግድ ባንክ የተበደረው አንድ ትሪሊዮን ብር ዕዳ አለበት ” - የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ

➡️ “ አንድም ብር ለመንግስት በቀጥታ የሰጠሁት ብድር የለም ” - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

⚫️ “ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች የተሰጠ ብድር የመንግስት ዕዳ አይደለም ” - የኢኮኖሚ ባለሙያ


ሪፖርተር ጋዜጣ በዕሁድ ዕለት እትሙ፣ መንግስት ከንግድ ባንክ የተበደረው አንድ ትሪሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ 2017 በጀት አመት የ8 ወራት ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርብ፣ “ባንኩ ካለበት አጠቃላይ የብድር ክምችት፣ አንድ ትሪሊዮን ብር ዕዳ የመንግስት” መሆኑን እንደገለፀ የጋዜጣው ዘገባ አመልክቷል፡፡  

የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፣ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ስህተት ነው ካለ በኋላ፣ “በዚህ በጀት ዓመትም ሆነ ከዚያ በፊት ለመንግስት አንድም ብር በቀጥታ አበድሮ” እንደማያውቅ አስታውቋል፡፡

እንደ ባንኩ መግለጫ፣ መንግስት ከሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች በቀጥታ የመበደር አሰራርም ሆነ ልምድ የለውም፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ብድር መስጡቱን ጠቅሶ ይህ ግን መንግስት በቀጥታ የተበደረው ሳይሆን፣ የልማት ድርጅቶች የተበደሩት ዕዳ ነው ብሏል።

“ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከአስፈፃሚው መንግስት የተለዩና የራሳቸው ካፒታል ያላቸው፣ እንደ ማንኛውም ድርጅት የንግድ ፍቃድ አውጥተው የሚነግዱ፣ በድርጅታቸው ስም ገንዘብ የሚበደሩ፣ ሊያተርፉም ሆነ ሊከስሩ የሚችሉ፣ ለትርፍ የተቋቋሙ የልማት ድርጅቶች ሲሆኑ ብድሮቹንም የወሰዱት ለራሳቸው ፕሮጀክቶች በመሆኑ ለእነዚህ ተቋማት የተሰጠውን ብድር የመንግስት ብድር ተደርጎ መወሰዱ ስህተት ነው ” በማለት ገልፆዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለዚህ ጉዳይ ከአንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ ማብራሪያ ጠይቋል፡፡

ለመሆኑ መንግስት ከንግድ ባንኮች የሚበደረው መቼ ነው፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች (እንደ ቴሌኮሚኒኬሽን፣ ኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስኳር ኮርፖሬሽን እና የመሳሰሉት) ከንግድ ባንኮች የወሰዱት ብድር፣ የመንግስት ብድር ሊባል ይችላል ? የሚል ጥያቄ ያነሳንላቸው፣ የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ሑሴን ዓሊ፣ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ሑሴን ዓሊ ምን አሉ ?

“ መንግስት የሚባለው አካል በሁለት ይከፈላል፡፡ አንደኛው ዘርፍ ስራ አስፈፃሚው መንግስት (የፌደራሉና የክልሎች) ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የመንግስት የልማት ድርጅቶች (ፐብሊክ ኮርፖሬሽንስ) የሚባለው ነው፡፡ ይህ አገላለፅ ግን በሁሉም ሀገራት ላይ ላይሰራ ይችላል፡፡ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ያላቸው ሀገራት አሉ፣ የሌላቸው አሉ፡፡ ሙሉ በሙሉ ሊበራል የሆኑ ሀገራት የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሉዋቸውም፡፡ ለምሳሌ ፦ በአሜሪካ እንዲህ ዓይነት ድርጅቶች የሉም፡፡

ስራ አስፈፃሚው መንግስት ለአስተዳደራዊና ለልማት ስራዎቹ የሚሆን ገንዘብ የሚያገኘው ከግብር ከፋዮች፣ ግብር ነክ ካልሆኑ ምንጮች ለምሳሌ በራሱ ከሚያከናውናቸው የኢንቨስትመንት ስራዎች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከሚያመነጩት ገቢ/ትርፍ ነው፡፡

ወጪውንም ከግብር ከሚሰበስበው እና በብድር ከሚያገኘው ገንዘብ ይሸፍናል፡፡ ብድር ስንል የውጭ ብድር አለ፣ የሀገር ውስጥ ብድር አለ፡፡ የሀገር ውስጥ ብድር፣ ከግል ባንኮችና ከመንግስት ባንኮች የሚበደረው ገንዘብ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ እንግዲህ መንግስት የምንለው አካል፣ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፌደራል ያለው ስራ አስፈፃሚ አካል የሚበደረው ነው፡፡

መንግስት ለአስተዳደራዊና ለካፒታል ወጭዎቹ ሊበደር ይችላል፡፡ የበጀት ጉድለት ሲገጥመው ሊበደር ይችላል፣ የካፒታል ወጭዎቹንም ለመሸፈን ሊበደር ይችላል፡፡ ግን አሁን ላይ መበደር ያቆመ ይመስለኛል፡፡ ለማንኛውም ይህ ብድር በአጠቃላይ ዝቅተኛ ነው፡፡

አሁን የቅድሙ አገላለፅ እዚህ ጋር ይመጣል፡፡ መንግስት ተበደረ ስንል ምን ማለታችን ነው ? ይህ ብድር፣ ከፌደራል እስከ ክልል ያሉት ስራ አስፈፃሚ መንግስታት የወሰዱት ነው ወይስ፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ? ዝም ተብሎ መንግስት ተበደረ ማለት አንችልም፣ ይህ ስህተት ነው፡፡

መንግስት የሚወስደውና የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚወስዱት ብድር ይለያያል። የልማት ድርጅቶች የተበደሩት ብድር የመንግስት ብድር ሊባል አይችልም፡፡ እናም፣ በንግድ ባንክ ሀሳብ እስማማለሁ፡፡

እነዚህ ድርጅቶች የራሳቸው የማቋቋሚያ ስርዓት፣ ህጋዊ ቁመና፣ የራሳቸው ካፒታል፣ የአሰራር ስርዓት ያላቸውና ዋስትና አሲይዘው የሚበደሩ ናቸው፡፡ የፕሮጀክት ስራዎቻቸውን ለማስፈፀም ሊበደሩ ይችላሉ፡፡ ዕዳቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለባንኩ መክፈል ሲያቅታቸው ግን መንግስት ሐላፊነት አለበት፣ ምክንያቱም ተቋማቱ የመንግስት ናቸው፡፡

ያለባቸውን ዕዳ ሳይሰርዝ አሰራሮቻቸውን እንዲያሻሽሉና ትርፋማ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ዕዳቸውን በሒደት እንዲከፍሉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ከእነሱ ገቢ እየሰበሰበ የባንክ ዕዳቸውን በረዥም ጊዜ እንዲከፍሉ ያደርጋቸዋል፡፡ በአስር አመትም፣ በሀያ አመትም እያመረቱ ገቢ እያስገኙ ለመንግስት ይከፍሉታል፣ መንግስት ደግሞ ያንን ገቢያቸውን ሰብስቦ፣ ለተበደሩበት ባንክ ዕዳቸውን ይከፍላል፡፡ እንደዛ ስለሆነ ግን ዕዳው የመንግስት ነው ሊባል አይችልም፡፡ 

መንግስት የተበደረው ብድር ከሆነ ገንዘብ በማተም ሊከፍለው ይችላል፣ ወይም ከሚሰበስበው ግብር ዕዳውን ሊከፍለው ይችላል፡፡ መንግስት የሚበደረው በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ነው (የመንግስትን የፋይናንስ ገቢና ወጪ የሚያስተዳድረው እሱ ስለሆነ)፡፡ የብድር አከፋፈሉ ራሱ የተለያየ ነው፣ ዓላማውም የተለየ፡፡

ብሔራዊ ባንክም በአመታዊ ሪፖርቱ ሲያቀርበው የፐብሊክ ሴክተር ብድር (የመንግስት የልማት ድርጅቶች ብድር) እና የመንግስት ብድር ብሎ ነው በሁለት ከፍሎ የሚያቀርበው ” ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ አርዕስት ዙርያ ሌሎች ሀሳቦች የሚያቀርቡ አካላትን ወይም የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነው፡፡ 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
 
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ምን አለ ?

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ሚያዝያ 1 ቀን 2017 ባደረገው ስብሰባ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለማዊ ሁኔታዎችን መገምገሙን አሳውቋል።

ከስብሰባው በኃላ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ፤ ምክር ቤቱ ትኩረት የሚሹ ብሎ በግምገማው የተለያዩ ጉዳዮች ማንሳቱን አመልክቷል።

የመጀመሪያው ፤ " ፍላጎትን በኃይል የማስፈጸም ኋላ ቀር አማራጭ የሚከተሉ አካላትን የተመለከተ ነው " ያለው ም/ቤቱ " እነዚህ አካላት መልካቸው ይለያይ እንጂ በተለያዩ አካባቢዎችና በውጭ ይገኛሉ " ብሏል።

- የራሳቸውን አካባቢ ከሌላው የበለጠና የተጎዳ አድርገው ያያሉ፤
- መነጋገርና መወያየት አይፈልጉም፤
- ሤራ፣ ወጥመድ፣ ዝርፊያ፣ እገታ፣ ጭካኔ፣ ሕገ ወጥ ንግድ እና ፍላጎት በኃይል ብቻ ማስፈጸም መለያቸው ነው ሲል ገልጿል።

" አልፎ አልፎም ጥፋት የጋራ ዓላማቸው በመሆኑ ተቀናጅተው ለማጥፋት ይሞክራሉ " ብሏል።

" ሕጋዊ የፓርቲ ሽፋኖችን ለሕገ ወጥ ተግባራት ይጠቀማሉ፤ ከኃላፊነት የተነሡ አኩራፊ ፖለቲከኞችን በመጠቀም ሕገ ወጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፤ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለሑከት ተግባር ለመጠቀም ይሠራሉ " ሲል ገልጿል።

" ሁለተኛዎቹ አካላት በተለያዩ ቦታዎች ተቀምጠው፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በመተባበር፣ የመንግሥትን ሥራዎች በማደናቀፍ፣ የሕዝብን ምሬት በመጨመርና የሐሰት ወሬዎችን በማዛመት የተጠመዱ ናቸው " ብሏቸዋል።

- በማኅበራዊ ቦታዎች፣ በቤተ እምነቶች፣ በመሥሪያ ቤቶች እና በንግድ ቦታዎች ተሠግሥገው እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ይሞክራሉ፤
- ሸቀጥ ይደብቃሉ፤
- የአቅርቦት እጥረት ይፈጥራሉ፤
- የውጭ ምንዛሬ ሥርጭትን ይገድባሉ፤
- ኮንትሮባንድ ያካሂዳሉ፤
- በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችንና መሣሪያዎችን ያዘዋውራሉ፡፡
- በሙስና፣ በዘመድ አዝማድ እና በብልሹ አሠራር ሕዝብ እንዲማረር ሆን ብለው ይሠራሉ ብሏል።

" ሦስተኛዎቹ የሐሰት ፕሮፓጋንዳውን የሚመሩ ክንፎች ናቸው " ያለው ምክር ቤቱ ፦
- መደበኛውንና ማኅበራዊውን ሚዲያ በመጠቀም የሕዝቡን ሰላም ይረብሻሉ፤
- በጦር ሜዳ ሲሸነፉ፤ ሤራዎቻቸው ሲከሽፉባቸው፤ በሰልፍና በዐመጽ የሚወድቅ መንግሥት ሲያጡ፤ የመጨረሻ አማራጫቸውን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፤
- የሐሰት ታሪክ ይፈጥራሉ፤
- የሐሰት መረጃ ይቀምራሉ፤
- የሽብር ወሬ ያደራሉ፤
- የሑከት ዜና ይፈበርካሉ " ብሏል።

ምክር ቤቱ ፤ " የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የጸጥታ ተቋማት ከሕዝቡ ጋር ተቀናጅተው በሚሠሩት ሥራ የጥፋት ኃይሎች ዓላማ እንዳይሳካ፣ ዐቅማቸው፣ ምኞታቸውም ከንቱ ሆኖ እንዲቀር ለማድረግ ተችሏል " ሲል አሳውቋል።

(የምክር ቤቱ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba #EV_Charging

ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን እጅግ ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አገልግሎት በአዲስ አበባ አስጀምሯል።

ስራ የጀመረው ሁለተኛው ጣቢያ ከመገናኛ ቦሌ መንገድ አንበሳ ጋራጅ ፊት ነው የሚገኘው።

ይህ ጣቢያ የአውሮፓ ስሪት የሆኑ መኪኖችን የኤሌክትሪክ ኃይል መሙላት የሚያስችል እጅግ ፈጣን አቅም ያለው ተብሏል።

የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎቹ በ1 ሰከንድ 1 ኪሎሜትር ለመጓዝ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል በመሙላት በ15 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ (100%) የኤሌክትሪክ ኃይል የመሙላት አቅም እንዳላቸው ኩባንያው አሳውቋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ የባትሪ መስፈርቶች እና የደንበኛን ትዕዛዝ በመተንተን የባትሪውን ደህንነት እየፈተሸ የተሽከርካሪው ባትሪ በሚችለው ፍጥነት ቻርጅ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

ኩባንያው ቀደም ሲል 16 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል ጣቢያ ወደስራ ያስገባ ሲሆን ከየካቲት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ14,280 የኤሌክትሪክ መኪኖች፣ በ376,574.72 ኪሎዋት/ሰዓት ኃይል ቻርጅ ማድረግ እንደቻለ አመልክቷል።

አዲሱ የመሙያ ጣቢያ 4 እጅግ በጣም ፈጣን እና 12 በጣም ፈጣን መሙያዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም ያሉንን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች የማስተናገድ አቅም ወደ 32 ለማድረስ አስችሏል፡፡

#EthioTelecom #EcoFriendly #EV_Charging

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ችሎት

⚫️ “ እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ ” - አቶ ክርስቲያን ታደለ

🔴 “
ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሸው ተቀቷል። ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው ” - አቶ ዮሐንስ ቧያለው

የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያሌውን ጉዳይ የሚከታተሉ የቅርብ ሰዎች፣ “የመንግስት አክቲቪስት” ሲሉ የጠሯቸውና “እነ ክርስቲያን ወንጀለኛ ናቸው” ያሉትን ግለሰብ ፌደራል ፓሊስ ማግኘት እንዳልቻለ ለፍርድ ቤት መግለጹን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

በዚህም፣ አቶ ስዩም ተሾመ የተባሉት ግለሰብ በቻናላቸው እነ አቶ ዮሐንስን ወንጀለኞች እንደሆኑ በመናገራቸው፣ እነ አቶ ዮሐንስም ክሰዋቸው ስለነበር ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዞ የነበረ ቢሆንም፣ ፌደራል ፓሊስ አቶ ስዩም ተሾመን ማግኘት አለመቻሉን ለፍርድ ቤት መግለጹን ነው ያስረዱት። 

የእነ አቶ ዮሐንስ እና አቶ ክርስቲያን የቅርብ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

“ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው እና ክርስቲያን ታደለ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሰው ጉዳያቸው በመታዬት እያለ አቶ ስዩም ተሾመ መጋቢት 11/2017 ዓ/ም ባስተላለፉት ፕሮግራም ከተከሰሱበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ‘የአማራን ወጣት አስፈጅተዋል፣ ድሽቃ መሣሪያ መግዣ ጠይቀዋል’ ብለው እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም፣ “በፍትህ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር፣ ሕግን የተላለፈ ፕሮግራም ስላቀረቡ፣ የፌደራል ፖሊስ ለዛሬ መጥሪያ አድርሶት ችሎት እንዲያቀርበው ቢታዘዝም፣  ‘የስዩም ተሾመ አድራሻው ስላልተገለጸልኝ ላቀርበው አልቻልኩም’ ብሎ ምላሽ ሰጥቷል ” ብለዋል።

አቶ ዮሐንስ ቧያሌው በዚሁ ጉዳይ ዛሬ ምን አሉ ?

“ ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሸው ተቀቷል። ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው። ትምህርት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው አሁንም ተመሳሳይ ድርጊት የፈጸመው።

መንግስት ቤት የሰጣቸው፣ ደሞዝ የሚከፍላቸው እና መኪና የተሰጣቸው የመንግስት አክቲቪስት ናቸው። አማራ ሲሆን የትም ይገኛል። ደብል ስታንዳርድ ነው። የፌደራል ፖሊስ የሰጠው መልስ ለእኛ አሳማኝ አይደለም ” ብለዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ በዚሁ ጉዳይ ምን አሉ ?

“ ይሄ ‘ወስፌ ሲለግም ቂቤ አይወጋም’ የሚለው አባባል እውነት መሆኑን ያሳየ ነው። አቶ ስዩም ማለት የኢትዮጵያ መንግስት ጠባቂ ፖሊስ የመደበለት የመንግስት ተከፋይ ሃሜተኛ ነው። 

እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ። የመንግስት ሹመኛን የሚጠብቀው የፌደራል ፖሊስ አካል ነው።

እኛን የህዝብ እንደራሴዎችን ከቤተሰባችን ፊት ደብድቦና አዋርዶ ለማምጣት ያልተቸገረው ፌዴራል ፖሊስ፣ ላገኛቸው አልቻልኩም ማለቱ ስላቅ ነው። እውነቱን ንገረኝ ካላችሁኝ አቶ ስዩም ያልታሰረው አማራ ነኝ ስላላለ ነው ” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ተብሏል።
 
በመጨረሻም፣ “ የተከሳሾች ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የተላለፈው ፕሮግራም ሕግን የተላለፈ በመሆኑ ፖሊስ ያለምንም ምክንያት አቶ ስዩምን እንዲያቀርብ ይደረግልን ” ማለታቸውን የቅርብ ሰዎቻቸው ተናግረዋል።

“ ፍርድ ቤቱም በድጋሚ የፌደራል ፖሊስ ስዩም ተሾመን እንዲያቀርባቸው ለሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል ” ብለዋል።

N.B፦ ፌደራል ፓሊስ ፍርድ ቤት እንዲያቀርባቸው ተብለው ነበር የተባሉት አቶ ስዩም ተሾመ፣ ከሳምንት በፊት ባሳራጩት ዩቱዩብ ቻነል ስለነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው ሲናገሩ፣ “ቧያሌው ተንኮለኛ ነው። ከኔ በላይ ማን ምስክር አለ ያረገውን፤ እሰይ ቧያሌው ታሰረ ብዬ ስላልፎከርኩ ነው? መከራዬን አይደል ያበላኝ እሱ ምን ብዬ ስላልኩት ፋኖ ትጥቅ ይፍታ ' አይፈታም' ሲል የአማራን ህዝብ ታስበላላችሁ ሆን ብላችሁ ይሄ ሴራ ነው ስላልኳቸው ነው ይሄ ችግር የተፈጠረው ፤ የተለየ ወንጀል ሰርቼ አይደለም ፤ ገዱም እሱም ጠምደው መከራዬን ሲያበሉኝ የነበረው ፋኖ ትጥቅ አይፈታም ሲሉ ይሄ የድንቁርና ሃሳብ የአማራን ህዝብ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያጋጫል ፣ የማይሆን ቅርቃር ውስጥ ያስገባዋል፣ የአማራን ህዝብ ታስበላላችሁ፣ ወጣቱን ታስፈጃላችሁ እንዳልኩ ወጣት አስፈጅተዋል። እነዚህ ሰዎች ከዛ አልፈው ታጥቀው ' መንግሥት እንግለብጣልን ' ሲሉ መንግሥት ገልብጦ እስር ቤት ከቷቸዋል ስራቸው ያውጣቸው ” ሲሉ ተደምጠዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የተሰጠኝ ኃላፊነት ከባድ የሆነ ፈተና ነው ፤ ጥሩ ከተሰራ ግን እድል ነው " - ጄነራል ታደሰ ወረደ

አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ አስተዳደራቸው የካቢኔ መዋቅር ማስተካከያ እንደሚያደረግ ገልጸዋል።

ጄነራል ታደሰ የተሰጣቸው ኃላፊነት  ከባድ ፈተና እንደሆነ ተናግረዋል። " የምትመኘው ነገር አይደለም "  ያሉት ፕሬዝዳንቱ " ጥሩ ከተሰራ ግን እድል ነው " ብለዋል።

"ፈተና" ያሏቸውን እንደኖሩባቸውና እንደሚያውቋቸውም ጠቁመዋል።

ባለፉት ጊዜ ያልተሰሩት ስራዎች ከፕሪቶሪያ ስምምነት ጋር የተያያዙ ብቻ እንዳልሆኑ ጠቁመው " በራሳችን በውስጣች የተፈጠሩ ከፍተኛ የፀጥታ ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ቀውሶች አሉ " ብለዋል።

እነዚህን በርካታ ችግሮች ለመቅረፍ ትግራይ ማዕከላዊ ስልጣን አጥታ ነበር አሁን ግን ማዕከሉን በማጠናከር ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል።

የሰላም ስራዎች ላይ ፣ የፕሪቶሪያ ስምምነት መተግበር ላይ፣ የህዝቡ ጥያቄን መፍታት ላይ ጠንክረው እንደሚሰሩ የተናገሩት ጄነራል " አሁን  ያለው ውጥረት ረግቦ ሁሉም የፖለቲካ አካሄድ ለውጥ የሚመጣበት ፤ የወጣቶችም የለውጥ ፍላጎት የሚሳካበት ሁኔታ ይፈጠራል " ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል።

በሳቸው አስተዳደር የካቢኔ ማስተካከያ እንደሚኖርም ይፋ አድርገዋል።

በፕሬዜዳንትነት ጊዜያቸው ዋናው #የትግራይ_ህዝብ ድጋፍ እንደማይለያቸው ፤ የፌዴራሉም መንግሥት እንዲሁም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍም እንዲሁ እንደማይለያቸው እምነታቸው ገልጸዋል።

" ትልቁ ነገር ደግሞ አቶ ጌታቸው ረዳ የስራ ለውጥ ቢያደርጉም ክልሉን ያውቁታል ያላቸውን እና በቀጣይ የሚኖራቸውን ሚና በደምብ እገነዘባለሁና የእሳቸው ድጋፍም እንደማይለየኛ ተስፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EOTC : የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ፈጽመዋል " ያለቻቸው አቶ ጽጌ ስጦታው እና አቶ ምስጢረ መዝገቡ የተባሉ ግለሰቦች ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቀች።

የቤተክርስቲያኗ የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ፥ " እራሳቸውን ' መሪጌታ ' ጽጌ ስጦታው እና ' መሪጌታ ' ምስጢረ መዝገቡ ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ እምነት ላይ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ፈጽመዋል  በሚል  ተጠርጥረው የወንጀል አቤቱታ ቀርቦባቸዋል " ሲል አሳውቋል።

በዚህም የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በዛሬው ቀን ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ሥር በማዋል የወንጀል ምርመራውን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

" ከግለሰቦቹ በተጨማሪ እንዳልካቸው ዘነበ  የተባለ ግለሰብ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያኗ ላይ ፈጽሞታል ተብሎ በተጠረጠረበት ስም ማጥፋት በቅርቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ቃሉን ሰጥቶ   በዋስትና መለቀቁንና በአቃቤ ሕግ በኩልም የወንጀል አቤቱታ ክስ ቀርቦ በሒደት ላይ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።

መረጃው የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኅን አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Apply

አነስተኛ መሬት ይዞታ ያላቸዉ ገበሬዎች ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች (MSEs) የሚያጋጥሟቸውን የኑሮ ተግዳሮቶች ለመፍታት የተነደፈ ☀️በፀሃይ ኃይል የሚሰራ ፈጠራ (solar) /መፍትሄ አለዎት? እንግዲያዉስ ፈጠራዎን (Prototype) የመተግበር እድል እነሆ!

⚡️የኢንኩቤሽን ፕሮግራማችን ለፈጠራ ትግበራ (Prototype Implementation) እስከ 700,000 ብር  የገንዘብ ድጋፍ ፣የአቅም ግንባታ ድጋፍ እና የባለሙያ ድጋፍ  ያቀርባል።

💡ፈጠራ ሲባል ፣ በኢትዮጵያ ሁኔታ ገና ያልተተገበረ ምርታማነትን የሚጨምር የታዳሽ ኃይል መፍትሔ (productive use of energy) ወይም የኢትዮጵያ  ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ መፍትሔ ሊሆን ይችላል።

🗓የማመልከቻ ቀን፡ እስከ ሚያዚያ 22 2017 ዓ/ም

👉🏽ለማመልከት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ :-  https://docs.google.com/forms/d/1XYfQEhIHHkDRCiTKyi7hCenUz8SJ3LFt5C3DS1_VShI/edit

👉🏽 የማመልከቻዉ መመሪያ :- https://drive.google.com/file/d/1A72sq23stvNEcC6wwm9DCJW4cmmU7Q5L/view

#Innovationchallenge #Solar

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የተፈጠረውን የፖለቲካ ልዩነት በማጥበብ የትግራይን ህዝብ ቀጣይ እጣ ፈንታ ማቃናት ይገባል " - ጄነራል ታደሰ ወረደ

➡️ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ነፃነቱን ጠብቆ ስራውን አንዲሰራ የበኩሌን አስተዋፅኦ እወጣለሁ " - ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት


በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት  ፤ " የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተቋማዊ ነፃነቱን ጠብቆ ስራውን አንዲሰራ የበኩሌን አስተዋፅኦ እወጣለሁ " አለ።

የአዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በይፋ ስራቸውን የጀመሩ ሲሆን ከነባሩ ካቢኔና ከደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ጋር ተገናኝተዋል።

ካቤኔያቸው መልሰው እንደሚያደራጁ የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ጎን ለጎን የሦስት ወር እቅድ እንዲዘጋጅ አዘዋል። 

የስራቸው ዋና ማጠንጠኛ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ መተግበር መሆኑ ገልጸዋል።

- የህዝብ ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝነት መጠበቅ
- የክልሉ ኢኮኖሚ ማነቃቃት
- የአስተዳደር መዋቅሩን ማስተካከል የትኩረት አቅጣዎች መሆናቸው ተናግረዋል።

የተፈጠረውን የፓለቲካ ልዩነት በማጥበብ የትግራይ ህዝብ ቀጣይ እጣ ፈንታ ማቃናት እንደሚገባ ያሳሰቡት ጄነራል ታደሰ " አሸናፊና ተሸናፊ ከሚል መገፋፋት በመውጣት በአብሮነት በመደጋገፍ በጋራ መስራት አለብን " ብለዋል። 

" ህወሓትና ጊዚያዊ አስተዳደር " የሚል ልዩነት የሚያሰፋ አጀንዳ እንዲፈታና እንዲዘጋ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በቅርብ ጊዜ የህዝብ ኮንፈረንስ በማካሄድ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንዳቀዱና እቅዳቸው እውን እንዲሆን የሁሉም ፓለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ እንደሚሹ ጠይቀዋል።

በተያያዘ ፕሬዜዳንቱ ትላንት ማምሻውን ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)  የሚመሩት ህወሓት በፅህፈት ቤቱ ይፋዊ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ለፕሬዜዳንቱ ያላቸው መልካም ምኞት በማስቀደም ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተልእኮዎቹ ለመፈፀም በሚያደርገው ጥረትና እንቅስቃሴ የህወሓት ድጋፍ አይለየውም ብለዋል።

" የክልሉና የህዝቡ ችግሮች መፍታት የጋራ አጀንዳ ነው " ያሉት ጄነራል ታደሰ የፓርቲው አመራሮች ላደረጉላቸው አቀባበልና ለገለፁላቸው መልካም ምኞች አመስግነዋል።

" የትግራይና ህዝቡን መልካም ገፅታ ለመመለስ በጋራ ከመስራት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም " ሲሉም ተናግረዋል።

መረጃው ከክልሉ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት እና ከህወሓት የማህበራዊ የትስስር ገፅ የተወሰደ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ፎቶ፦ TPLF

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

https://ethiocoders.et/

በነፃ በመማር የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ !

ለአምስት ሚልዮን ኢትዮጵያዉያን
ነፃ የትምህርት ዕድል!!!
እጅዎ ላይ ባለ ስልክና ታብሌት ጊዜና ቦታ ሳይገድቦት ተመዝግበዉ በመማር ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሠርተፊኬት ያግኙ።
ነፃ የኦንላይን ሥልጠናዎቹ ፦
- በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ
- በዳታ ሳይንስ
- በዌብ ፕሮግራሚንግ እና
- በአንድሮይድ ማበልፀግ ናቸው
እርሶም በመረጡት የትምህርት ዘርፍ  በአጭር ጊዜ ተምረዉ ህይወትዎንና ሙያዎን ያዘምኑ።
ከመገረም ወጥተን እናስገርም!!!

ኢትዮ ኮደርስን ለመቀላቀል
ከታች ባለዉ ሊንክ ተጭነዉ ይመዝገቡ
https://ethiocoders.et/

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ግለሰቡ ስነምግባር የጎደለው በአሽከርካሪው ላይም ሲያደርግ የነበረው አጸያፊ ተግባር ነው ፤ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ ነው " - ፖሊስ

የድሬዳዋ ፖሊስ በአንድ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌር ላይ " አጸያፊ " ሲል የጠራውን ተግባር የፈጸመ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።

ሰሞኑን በአንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ ቪድዮ አለ። ይኸው ቪድዮ አንድ ግለሰብ የከባድ መኪና አሽከርካሪን ተንጠልጥሎ ሲደበድብ የሚያሳይ ነው።

ድርጊቱ የተፈጸመው ድሬ ላይ ነው።

የድሬዳዋ ፖሊስም የድርጊቱን ፈጻሚ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አመልክቷል።

የግለሰቡ ስም ሙክታር መሃመድ እንደሚባል እና መጋዘን አካባቢ ላይ እንደ አጋዥ ሆነው ከሚሰሩ ወጣቶች አንዱ ነው ያለው ፖሊስ " ስነምግባር የጎደለው በአሽከርካሪው ላይም ሲያደርግ የነበረው አጸያፊ ተግባር ነው " ብሏል።

ፖሊስ " ድርጊቱ በተፈጸመ በሁለት ቀን ነው ግለሰቡን የያዝኩት " ያለ ሲሆን " ድርጊቱን የፈጸመው የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ አይደለም ፣ የትራፊክ ፖሊስ አባልም አይደለም ፣ መደበኛ የፖሊስ ኃይልም አይደለም አንድ አጋዥ ኃይል ነው " ሲል አስረድቷል።

አጋዥ ኃይል የሚባለው በከባድ መኪና ላይ የሚጫን እና የሚወርድ ንብረት የሚጭን እና የሚያወርድ ነው ሲል ገልጿል።

ግለሰቡ በተጠረጠረበት ወንጀል ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሆነ የገለጸው የድሬዳዋ ፖሊስ ከሹፌሩ አቤቱታ እንዳልቀረበና ግለሰቡ የተያዘው በማህበራዊ ሚዲያ ጥቆማ እንደሆነ አመልክቷል።

ተበደልኩኝ የሚለው ሹፌር ግለሰቡ ወደተያዘበት ሃሎሌ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ በአስቸኳይ አቤቱታ እንዲያቀርብ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

የድሬ ፖሊስ ማንኛውም ኃይል ወይም ወንጀል ፈጻሚ ወንጀል ፈጽሞ ድሬዳዋ ውስጥ የትኛውም ቦታ መደበቅ አይችልም ብሏል።

#DirePolice

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ታፍሰው የተወሰዱ አሉ። 20 ተማሪዎች በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል ፤ የት እንዳደረሷቸው አናውቅም " - የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች

የመውጫ ፈተና ተፈትነው አልፈው ቴምፖራሪ ሲጠባበቁ እንደነበሩ የገለጹ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች፣ በድጋሚ ገና በሰኔ ላይ 'ትፈተናላችሁ' በመባላቸው ዛሬም መብታቸውን ሊጠይቁ በተዘጋጁበት በጸጥታ አካላት ድብደባና አፈሳ እንደደረሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬስ ምን አሉ ?

አንዱ ምሩቅ በሰጡን ቃል፣ " ተማሪ ሲያልፍ እንዴት እንዲህ ተብሎ ይጠየቃል ? ብለን ሀሳብ ልናቀርብ በተሰለፍንበት ወቅት (50 እናሆናለን)፤  20 ተማሪዎች በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል፤ የት እንዳደረሷቸው አናውቅም። ስልካቸው አይሰራም። የቀሩትም ተደብድበው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሉ " ሲል ተናግሯል።

ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ ተመራቂ፣ " ፈተናችን ታግዶ ከቆዬ ሰነባብቷል። በዚህም የግቢው አስተዳደር አካላትን ምላሽ ለመጠየቅ እየሞከርን ነበር። ሊያናግሩን ፈቃደኞች አይደሉም። ትላንት ልንጠይቅ ስሄድ አባረሩን፤ ዛሬ ልጠይቅ ስንሄድ ደግሞ በርካታ የጸጥታ አካላት ተጭነው መጥተው ተማሪዎች ተደብድበዋል። ሌሎችም በፓትሮል ተጭነው ወደ ማረሚያ ቤት ሂደዋል " ብሏል።

ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ፣ " የመወጫ ፈተና በድጋሜ ከጥር 25 እስከ 30 2017 ዓ/ም እንደወሰድን ይታወቃል። እንዳለፍን፣ ውጤት እንደመጣ ተልኮልናል። ፎቶ ተነሱ ተብለን ዶክሜት ልንሰጥ ፎቶ ተነስተን አስገብተን ክሊራስ የመውጫ ሞልተን ጨርሰን በሳምንቱ ውጤታችሁ ታግዷል ተባልን " ሲል ገልጿል።

" ምንድነው ? አልን ' ትምህርት ሚኒስቴር ነው ያገደው ' ተባልን ስንጠብቅ ቆየን ነገር ግን እስከዛሬ የተሰማ ነገር የለም። የድሀ ልጆች ነን። ቤት ተከራይተን ለምግብ እያስላክን ነው። እኔ 25 ሺሕ ብር ወጪ አድርጌያለሁ። ዩኒቨርሲቲው ከግቢው አሶጥቶናል የሚሰጠን ሰርቪስ የለም ” ሲል ገልጿል።

ሌላኛዋ ተመራቂ ተማሪ፣ “ ተሰብስበን ጥያቄ ልንጠይቅ ነበር። እዚሁ እኛ ፊት ነው የደበደቧቸው። ወደ 20 ሴቶችም ወንዶችም የታሰሩ አሉ። የጸጥታ አካላት ሙሉ ግቢውን አጥለቅልቆት ነበረ ገና ማውራትና መጠየቅ ሳንጀምር " ብላለች።

" ምንም ብጥብጥ አልፈጠርንም፤ ያወክነው ነገርም የለም፤ መብታችን እንዲከበርልን እሱም ኢ - ፍትሃዊ የሆነ ነገር ተደርጎብናል ፍትህ እንፈልጋለን ባልንበት ሁኔታ ነው " ይህ ሁሉ የተደረገው ብላለች።

" ገና እየተሰባሰብን ባለበት መሳሪያ ታጥቀው ዱላ ይዘው የመጡ የጸጥታ ኃይሎች ሰበሰቡንና ተማሪዎቹን በግፍ እየደበደቡ ነበረ። አወላላ ሜዳ ላይ ታፍሰው የተወሰዱ አሉ ወደ 20። ስንደውልም ስልካቸው አያነሱም የት እዳሉ አናቅም። አይተናል እዛነበርን በመኪና ጭነው ነው የወሰዷቸው ” ስትል ተናግራለች።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በመጨረሻም፣ ለጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ያሳሰቡ ሲሆን፣ ለቅሬታቸው ምላሽ ለማግኘት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ዩኒቨርሲቲውና ትምህርት ሚኒስቴር ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው ስልክ አልተነሳም።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር)፣ የተማሪዎቹን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ትላንት በጠየቅናቸው ወቅት ስለጉዳዩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።

ፕሬዜዳንቱ በወቅቱ ሁነቱን ሲያስረዱም፣ "ጉዳዩ ‘ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘
#ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር ሆልድ ስላደረገ ነው/" ነበር ያሉት።

(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

እያንዳንዱ ጎል፣ ሁሉንም ጨዋታዎች በቀጥታ💥📺

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው #EuropaLeague

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoH

" ቃል በገቡልን መሰረት ስንሄድ ከሎጂስቲክስ እና ከጊዜ ጥበት አንጻር ልንመዘግባቹ አንችልም አሉን " - ቅሬታ አቅራቢዎች

➡️ " ' ይህን ፈተና ካጠናቀቅን በኃላ በሳምንታት ውስጥ ለሌላ ፈተና ምዝገባ እንጀምራለን ' ብለው ቃል ገብተዋል " -ዩኒቨርሲቲው


የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና (COC) ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

የአመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 24/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 07/2017 ዓ.ም ድረስ ሲከናወን ነበር የቆየው።

አንዳንድ ተመራቂዎች የቴምፖራሪ ዲግሪ ያልደረሰላቸው መሆኑንና (ቴምፖራሪ ዲግሪ መያዝ ግዴታ በመሆኑ) ምዝገባው እንዲራዘምላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ፤ ምዝገባው ለተጨማሪ ሦስት ቀናት ማለትም እስከ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ተራዝሞ ነበር።

ይሁን እንጂ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ በቁጥር 100 የሚሆኑ የህክምና ተማሪዎች ለምዝገባው የሚያስፈልገው ቴምፖራሪ ዲግሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የብቃት ምዘና የምዝገባ ቀናት ሳይደርስላቸው በመቅረቱ የአሁኑ የብቃት ፈተና እንዲያልፈን ሆኗል ሲሉ ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

የጤና ሚኒስቴር የምዝገባውን ቀን ይፋ ባደረገበት ቀን ለምዝገባ አስገዳጅ የሆነው የቴምፖራሪ ዲግሪ የማይደርስልን መሆኑን በመግለጽ ትብብር ጠይቀን ነበር ያሉት ተማሪዎች ሚኒስቴሩም ዲግሪያቸውን እንዳገኙ እንደሚመዘግባቸው ቃል ቢገባላቸውም በቃሉ አልተገኘም ሲሉ ተችተዋል።

እጩ ተመራቂዎቹ በዝርዝር ባቀረቡት ቅሬታ ምን አሉ ?

" ቴምፖራሪ ዲግሪ በጊዜው ሊዘጋጅልን አልቻለም ነበር ያኔ ተወካዮቻችን ጉዳዩን ሊያስረዱ ጤና ሚኒስቴር በሄዱ ጊዜ ቃል ገብተውልን ነበር።

ምዝገባው ቢያልቅም ፈተናው ለመፈተን ሦስት ቀን እስኪቀረው ድረስ ቴምፖራሪ ዲግሪያቹን ካመጣቹ እንቀበላቹሃለን አሉን።

እኛም በመጋቢት 22 ቴምፖራሪ ዲግሪው እጃችን ገባ ቃል በገቡልን መሰረት ስንሄድ ' ከሎጂስቲክስ እና ከጊዜ ጥበት አንጻር ልንመዘግባቹ አንችልም ' አሉን።

ይህንን ለምንማርበት ዩኒቨርሲቲ ስናሳውቅ ' ለመፈተን የሚያስፈልጉትን ኮምፒውተር ብዙ አለን መፈተኛ ጣቢያ እኛ እናዘጋጅላቹሃለን በሎጅስቲክስ በኩል አትቸገሩም ' አሉን።

የዩኒቨርሲቲያችንን ምላሽ ይዘን በሎጅስቲክስ በኩል ምንም እጥረት እንደማይገጥመን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳወቅን።

በዝግጅት በኩል ሙሉ ዝግጅት አድርገናል እንድትመዘግቡን ብቻ ነው የምንፈልገው በማለት አርሲ ዩኒቨርሲቲ ካሉት ሦስት ካምፓሶች በአንዱ ብቻ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ በመግለጽ ሁለት የመፈተኛ ጣቢያዎች ክፍት መሆናቸውን አስረዳን።

እነሱ ምዝገባው ኦንላይን ስለነበር መክፈት አንችልም አሉን።

ለመመዝገብ የግድ ቴምፖራሪ ዲግሪ ያስፈልጋል የተባለው ዘንድሮ ነው ህጉም አዲስ ነው ቴምፖውን እስክንቀበል ምዝገባው ያበቃው በአንድ ሳምንት ልዩነት ነው የአንድ ሳምንት ልዩነት ወራቶችን ሊያባክንብን አይገባም።

መመዝገቢያውን አልከፍትም ያሉን ከፈተና ደህንነት ከማረጋገጥ አንጻር ነው ነገር ግን በኦንላይን ቀርቶ ማንዋሊም መዝግቡን ስንልም እምቢ ተብለናል።

የዩኒቨርስቲው ማኔጅመንት ብንፈተን መሉ ድጋፍ የሚሰጡ መሆኑን ደውለው አስረድተዋቸዋል " ብለውናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን በመያዝ የጤና ሚኒስቴር አመራሮችን ያነጋገረ ሲሆን ውሳኔ ያልነውን ነገር ለዩኒቨርሲቲው አሳውቀናል የሚል አጭር ምላሽ አግኝቷል።

የጤና ሚኒስቴርን ምላሽ በመያዝ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲንን ምን ምላሽ አገኛቹ ስንል ጠይቀናል።

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር መለሰ ገዛኸኝ ምን መለሱ ?

" በጉዳዩ ላይ በስልክ ከጤና ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያይተናል።

በውይይታችን መሰረት የአሁኑ ፈተና ስኪዩርድ ስለሆነ ፣ሎጂሲትኪስ እና ፈታኞችን እያንዳንዱ የመፈተኛ ጣቢያዎች ላይ መድበው ስለጨረሱ እንደገና ለምዝገባ መክፈት የፈተናውን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው።

በዚህ ዙር መመዝገቢያውን መክፈት ስላልቻልን ይህንን ዙር ፈትነን እንደጨረስን በመሃል ሰፊ ጊዜ ሳንሰጥ እንከፍታለን ብለዋል።

ይህንንም ለልጆቹ በተወካዮቻቸው በኩል በመንገር አረጋግተናቸዋል።

ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ የመመዝገቢያ ጊዜ ያለፈባቸው በርካታ እጩ ተመራቂዎች አሉ የእኛ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በአካል ሄደው ስለጠየቁ ቃል የተገባላቸው ነገር ነበር የእኛ እና ሌሎች ያመለጣቸውን በማካተት ቀደም ብሎ ለመፈተን ዝግጁ መሆናቸውን ነግረውኛል።

ለእኛ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ ሲስተሙን እንዲመዘገቡበት ቢከፍቱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆነም ሊመዘገብ ይችላል ይህ ደሞ ሙሉ ሲስተሙን ይረብሻል።

ጤና ሚኒስቴር የተማሪዎቹን መፈተን እንደሚያምንበት በመግለጽ ' ይህን ፈተና ካጠናቀቅን በኃላ በሳምንታት ውስጥ ለሌላ ፈተና ምዝገባ እንጀምራለን ' ብለው ቃል ገብተዋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ዛሬ አስከሬን ከሆስፒታል ወጥቶ በጆሃንስበርግ ከተማ አሸኛኘት ተደርጓል ፤ ነገ ማለዳ አዲስ አበባ ይደርሳል " - በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራር የነበሩት አቶ ዳኛ ግርማ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በገዛ ቤታቸዉ በር ላይ በመኪናቸዉ ዉስጥ እንዳሉ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ጥቃት አድራሾች በጥይት ተመተዉ መገዳላቸዉንና አስከሬናቸዉም ፒተርስ ማሪትስበርግ ሆስፒታል ለምርመራ መግባቱ መገለጹ ይታወሳል።

የደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ ሀብቢ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት አስከሬኑ ከሆስታል ወጥቶ ጆሃንስበርግ ከተማ አምባሳደሩን ጨምሮ እጅግ በርካታ ሰዎች በተገኙበት የሽኝት መርሃግብር መከናወኑን ተናግረዋል።

በነገዉ ዕለትም አስከሬኑ ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክና ከቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያን ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግ አስታዉቀዋል።

በተለይም በሆሳዕና አብዮ ኤርሳሞ ስታዲየም እና በኮለኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ አቀባበል እንደሚደረግለትና ሥርዓተ ቀብሩም በማግስቱ ዐርብ ዕለት እንደሚፈፀም ገልፀዋል።

አቶ ዳኛ ግርማ ፊጦ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራርና አስታራቂ ሽማግሌ እንደነበሩ ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

ፎቶ ፦ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማሰባሰብ ሕብረት

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

የየእለቱን ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *779# በመደወል የቲክቫህ መረጃዎችን እናግኝ! በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የትግራይ ማእከላይ ዞን ፍርድ ቤት የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከነሂጃባቸው እንዲማሩ ወሰነ።

የወረዳ ፍርድ ቤት በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ላይ ያስቀመጠው የገንዘብ መቀጮም እንዲቀር ወስኗል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 30/2017 ዓ.ም በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ፤ ከአሁን በፊት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የተደረገው የሂጃብ ክልከላ ወድቅ ተደርጓል።   

ፍርድ ቤቱ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት የአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች ጥር 6 / 2017 ዓ.ም የወረዳው ፍርድ ሴት ተማሪዎቹ ሂጃባቸው ለብሰው እንዲማሩ የሰጠው ትእዛዝ እንዳልተከበረ ጠቅሶ ትእዛዙ እንዲተገበር ወስኗል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት " የተሰጠው ውሳኔ አልተተገበረም " በሚል የክስ መዝገቡ ከወረዳው በማንሳት ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እወስደዋለሁ በማለቱ የተጣለበት 12,500 ብር መቀጮም እንዲነሳ መወሰኑ ምክር ቤቱ ገልፀዋል። 

የአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች የማእከላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደ ወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ በማድረግ በአቋማቸው ይፀናሉ ? ወይስ ውሳኔወው ተቀብለው በመተግባር ሙስሊም ሴት ተማሪዎቹ ሂጃባቸው ለብሰው እንዲማሩ ይፈቅዳሉ ? እስከ አሁን  የታወቀ ነገር የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዋሪት !

ክቡራን ደንበኞቻችን! መጪው በዓል የሰላም፤የፍቅር እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እየተመኘን፡ ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን  የጠበቁ ምርቶቻችንን በሁሉም  የማሳያ ቅርንጫፎቻችን ከልዩ ቅናሽ ጋር አዘጋጅተን እንጠብቅዎታልን!

ወደ ማሳያ ክፍሎቻችንን በመምጣት ይጎብኙን !
* 22 - ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* አዳማ - ሶረቲ ሞል * ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት * ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
*ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ግጭቱ ቆሞ የሕዝብ ወይይት እየተደረገ ባለበት የ18 ዓመት ወጣትን ጨምሮ ሁለት ሰዎች በማሳቸዉ ላይ ተገድለዋል " - የሟች ቤተሰቦችና የአከባቢው ነዋሪዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ኦኖታና ቄየማ በሚባሉ ቀበሌያት መካከል መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተከሰተ በተባለዉ ግጭት እስካሁን ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ሰዎች ሞተዋል።

ባሳለፍነዉ አርብ በአከባቢው የመከላከያ ሠራዊት  በመግባቱ ግጭት መቆሙና የሕብረተሰብ ውይይት መካሄድ መጀመሩን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረው ነበር።

ዛሬ የአከባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " ወደ ልማት ስራችሁ ተመለሱ የተባልነዉን ተቀብለን ትናንት ሰኞ በማሳ ስራ ላይ የነበሩ አንድ የ18 ዓመት ታዳጊና ሌላ የ3 ልጆች አባት ተገድለዋል " ብለዋል።

የሟች ቤተሰቦች ከዐይን እማኞች ሰማን እንዳሉት ግድያው የተፈጸመው " በአካባቢው የፀጥታ ሰዎች (ፖሊሶች) " እንደሆነ ጠቁመዋል።

" ቅዳሜና እሁድን ብቻ ነዉ ሰላም የዋልነዉ " ያለን አንድ የአከባቢው ነዋሪ " ሰኞ ገና በጠዋቱ ነበር ሁለቱ ሰዎች በገዛ ማሳቸዉ እጅና እግራቸው ታስሮ በጥይት ተረሽነዉ የተገደሉት " ሲሉ ተናግረዋል።

" ጥቃቱ አሳዛኝና የአከባቢውን ነዋሪዎች እጅግ ያስቆጣ ተግባር ነዉ " ያለን ሌላኛው የሀይ'ቤና ቀበሌ ነዋሪ " የፀጥታ መዋቅሩ አከባቢዉን በተቆጣጠረበት ይህን ጥቃት የፈፀሙ አካላትን ለህብረተሰቡ በፍጥነት ግልፅ አለማድረጋቸው ሕዝቡን ቅር አሰኝቷል "ብለዋል።

በጥቃቱ ልጃቸውን ያጡ አባት ፥ " ሰባት ሴት ልጆችና አንድ ወንድ ልጅ ብቻ የወለድኩ ሲሆን አንዱ ወንድ ልጄን ነዉ አይቼ ሳልጠግበዉ ገና በለጋነቱ  የተነጠኩት " ሲሉ በሀዘን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጥቃቱን የአከባቢዉ ፖሊሶች መፈጸማቸውን ከዐይን እማኞች ስምቻለሁ ሲሉም አክለዋል።

በወረዳዉ የአይ'ቤና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑና በደቦ የማሳ ስራ ላይ የነበሩ 17 የሚሆኑ ወጣቶችም ትላንት ረፋድ በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ በርግገው ወደ ሌሎች ዞኖች መግባታቸዉን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ ወጣቶቹ በሕይወት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ አላገኘንም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በአከባቢው ተገኝተዉ ሕብረተሰቡን ሲያወያዩ የነበሩትን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህን አግኝቶ ለማነጋገር ቢሞክርም ፈቃደኛ ባለመሆን ስልካቸውን ዘግተዋል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስከመጨረሻው የሚከታተል ይሆናል)


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

" ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር ለማድረግ የቀረበው ጥናት ፀድቋል " - የአዲስ አበባ ካቢኔ

በዛሬዉ እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከነዚህም አንዱ ፥ በፕላንና ልማት ቢሮ እና በት/ት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበውን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር የማድረግ ነው።

ካቢኔው " በአካባቢው ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት ፣ የምርምር ፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ ፀድቋል " ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ካቢኔው ፦

- የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና ፤የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል።

- በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶም ዉሳኔ አስተላልፏል።

- የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይም ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

"  ጋዜጠኞችን ወይም የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብ ሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት  አልተሰጠውም  " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ማምሻውን በላከልን መግለጫ  ፤ " የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ፤ ለጋዜጠኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት እና የጋዜጠኞች ምዝገባ ለማከናወን ውይይት እና እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ፤ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ፣ ጋዜጠኞች እና የሙያ ማህበራት ጉዳዩን በተመለከተ የሕጋዊነት ጥያቄ እና ስጋቶቻቸውን እያቀረቡልኝ ይገኛሉ " ብሏል።

የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤቱ ጋዜጠኞችን ወይም የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብም ሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንዳልተሰጠው አስገንዝቧል።

ለዚህ ተግባር እውቅና የማይሰጥ መሆኑንም አሳውቋል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት ፤ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ምዝገባ፣ የሙያ ማረጋገጫ እና የብሔራዊ ሚዲያ ሽልማት እውቅና የማረጋገጫ አውደ ጥናት ማካሄዱ ይታወሳል።

ምክር ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቶ በነበረው ቃል ፤ የሚዲያ ባለሙያዎችን እንደ እውቀታቸው እና አስተዋጾ በመለየት ጋዜጠኞችን፣ አዘጋጆችን፣ ከፍተኛ የሚዲያ ተንታኞችን፣ አርታኢያንን፣ እና የሚዲያ ባለሙያዎችን የሚለይ አሰራር እንደሚዘረጋ ጠቆሞ ነበር።

ለጋዜጠኞች እና ለሚዲያ ባለሞያዎች ሙያዊ እውቅና ይሰጣል የተባለም ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተመዘገቡና እውቅና ለሚሰጣቸው ጋዜጠኞች ወጥ የሆነ
#መታወቂያ እንዲኖር እንደሚደረግ ይህም አሁን ለሚታየው የአክቲቪዝም እና ጋዜጠኝነት መደበላለቅ መፍትሄ እንደሚሰጥ ገልጾም ነበር።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ግን ምክር ቤቱ በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንዲህ ያለውን ተግባርና ኃላፊነት እንዲፈጽም እንዳልተሰጠው አስገንዝቧል። ምንም እውቅናም እንደማይሰጥ ከወዲሁ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Подписаться на канал