tikvahethiopia | Неотсортированное

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1531512

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Подписаться на канал

TIKVAH-ETHIOPIA

“ አስቸጋሪ ነው። በጣም ብዙ ናቸው እናንተ አንድ ብቻ ስላያችሁ ነው እንጂ ! ” - ኢሰመኮ

የጸጥታ ኃይል ልብስ የለበሰና መሳሪያ የታጠቀ አካል እጁን ወደ ኋላ የፊጢኝ የታሰረን ወጣት ከወደጀርባው በመሆን ጭንቅላቱ ላይ ሲተኩስበት የሚያሳይ ቪዲዮ ከሰሞኑን በማኀበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ድርጊቱ ብዙዎችን ያስለቀሰና ያስቆጣ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ “ እንዲያው እንደዚህ ያጨካከነን ምን ይሆን? ” ሲሉ በሀዘን ስሜት ተውጠው ሲጠይቁ ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበከሉ፣ ድርጊቱ ደርሶት በሰብዓዊ መብት ጥሰት አኳያ ጉዳዩን ዳሶት እንደሆን በሚል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል።

ኮሚሽኑ ይህንን ግፍ የተሞላት ድርጊት ተመልክቶት ይሆን ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ “ ጉዳዩ ደርሶናል። እኛ የራሳችንን ኢንቨስቲጌሽን ስለምንሰራ በቪዲዮው ላይ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል ” የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።

ድርጊቱ የት ? መቼ ? በማን ተፈጸመ ? ለሚለው እካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የሌለ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ “ መቼ ነው የተፈጸመው ? ማነው የሞተውስ ? የሚለውን ዝርዝሩን በሙሉ እያጣራን ነው የምንገኘው ” ሲል ጠቁሟል።

“ ዲጂታሊ ሰርተን ስናበቃም እዚያው የነበሩ የአካባቢው ሰዎችን ደግሞ ማነጋገር ይኖርብናል” ነው ያለው።

ድርጊቱ የተፈጸመበት አካባቢ ታውቋል ? ለሚለው ጥያቄ ኮሚሽኑ በምላሹ፣ “ ፍንጭ አለን ግን አሁን ለሚዲያ መግለጽ አንችልም። ምክንያቱም እርግጠኛ አይደለንም። እሱን እርግጠኛ ስንሆን እንነግራችኋለን ” ብላል።

ስለዚህ አሁን ምርመራው ተጀምሯል ማለት ይቻላል? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ፣ “ ቪዲዮው ደርሶናል። ኢንቨስቲጌት እያደረግን ነው ” ሲል መልሷል ኮሚሽኑ።

እንዲህ አይነት ግልጽ የወጡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶትን በተመለከተ አስተያዬት እንዲሰጥ ጠይቀነው ባስረዳበት አውድ ደግሞ፣ “ አሁን ባለው ሁኔታ እንዲህ አይነት ቪዲዮዎች በብዛት እየወጡ ናቸው ሚዲያ ላይ። እኛ ጋም የሚደርሱ አሉ ” ሲል የድርጊቱን ሁኔታ አስረድቷል።

“ አስቸጋሪ ነው። በጣም ብዙ ናቸው እናንተ አንድ ብቻ ስላያችሁ ነው እንጂ። ስለዚህ ይሄ ቪዲዮ ላይ ብቻ አሁን ላይ ኮመንት ማድረግ አልችልም ” ነው ያለው።

“ በአጠቃላይ አገሪቱ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ለሚለው በየጊዜው የምናወጣቸው ሪፓርቶች አጠቃላይ የሚያሳዩት ገጽታ አለ እሱን መያዝ ነው ” ብሏል።

የሰሞንኛውን ቪዲዮ ምርመራ ሲያልቅ ሙሉ አስተያዬትና ማብራሪያ እንደሚሰጥ ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል የገባ ሲሆን፣ ሁነቱን ተከታትለን በቀጣይ ተጨማሪ መረጃ የምናደረሳችሁ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የብርሃን ቤተሰቦች በመሸለም ላይ  ናቸው!
እርሶም የብርሃን ቤተሰብ በመሆን፤ ውድድሩን ይቀላቀሉ  ተሸላሚ ይሁኑ፡፡

አርብ 4፡00 ሰዓት በቴሌግራም ገፃችን ይጠብቁን
                                      👇👇👇
Telegram Link: /channel/berhanbanksc

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Weeklyquiz #questionandanswer #stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመውጫ ፈተና ከጥር 26 እስከ ጥር 30 ይሰጣል።

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ለአዲስ እና በድጋሜ ለመፈተን ላመለከቱ በሙሉ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

Via @tikvahuniversity

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🚨#Alert

ከደቂቃዎች በፊት ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል።

ንዝሩት በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ተሰምቷል።

ቃላቸውን የላኩልን የቤተሰባች አባላት " ዛሬ በጣም የሚያስፈራ ነበር። ሰሞኑን ድግግሞሹ ቀንሶ ነበር። ዛሬ በድንገት በሚያስፈራ ሁኔታ ነው የተሰማን " ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በፓኪስታን ሀገር " እስልምና ላይ ተሳልቀዋል " በሚል የተከሰሱ 4 ሰዎች የሞት ፍርድ ተላለፈባቸው።

4ቱ ሰዎች " ቅዱስ ቁርዓንን ጨምሮ የእስልምናን ዕምነት እሴቶችን ጎድተዋል " በሚል ነው የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው።

ተከሳሾቹ " የእስልምና እምነትን የሚያንቋሽሹ ይዘቶችን በማህበራዊ የትስስር ገጾች አሰራጭተዋል " በሚል ክስ ተመስርቶባቸው ክርክሩ ሲካሄድ ቆይቷል።

ከሰሞኑ በራዋልፒንዲ ከተማ በተካሄደ ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል በሚል 4ቱም ተከሳሾች የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋል ተብሏል።

ግለሰቦቹ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እሴቶችን፣ ቅዱስ ቁርዓንን፣ እምነትን እና ሌሎች ተያያዥ እሴቶችን አንቋሸዋል ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ላይ ከሞት ፍርድ በተጨማሪ 16 ሺህ 500 ዶላር እንዲከፍሉ ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።

የተከሳሾቹ ጠበቃ ፤ በደንበኞቹ ላይ የተላለፈው ፍርድ ተመጣጣኝ አይደለም በመቃወም ፤ የተላለፈውን ፍርድ ለማስቀየር ይግባኝ ለማለት በዝግጅት ላይ እንደሆነም አሳውቋል።

መረጃው የአል አይን ኒውስ / አል አረቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ከፍርድ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ !

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሩብ ዓመት ሪፖርት በኢትዮጵያ በግጭት ዐውድ ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

' ልጄን ትተህ እኔን ብላኝ ! '

🙏" ከእግዚአብሔር በታች እኔና ልጄን የታደገችን ጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ ናት " - መምህርት ደንበሌ አስራት

➡️" እናትና ልጅን ለማዳን ከ10 ደቂቃ በላይ ከጅቡ ጋር ታግለናል" - ወ/ሮ መቅደስ ተካ


ከሰሞኑ መምህርት ደንበሌ አስራት የተባሉ እናት በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ 'ጃሎ ናራሞ ' ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ የ12 ዓመት ልጃቸዉን ሊበላ ከያዘ ጅብ ጋር በመታገል ልጇን ማዳኗን ሲዘገብ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ወደ መምህርት ደንበሌ አስራት የእጅ ስልክ በመደወል ስለጉዳዩ ጠይቋቸዋል።

መምህርት ደንበሌ ስለ ጉዳዩ ሲያስረዱ" ጥር 11/2017 ዓ/ም ረፋድ 3 ሠዓት አከባቢ ዉሃ ለመቅዳት ከልጄ ጋር ሽላንሻ ወደተባለው ምንጭ በወረድንበት አጋጣሚ ነበር አፉ በደም የተለወሰ አንድ ጅብ ወደ እኛ በመምጣት በእኔና በጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ መሃል የነበረዉን የ12 ዓመት ሕፃን እግር ነክሶ በመያዝ ወደ ጫካ ዉስጥ መጎተት ሲጀምር ዐይኔ እያዬ ልጄን አይበላብኝም በማለት ቀኝ እጄን የጅቡ አፍ ዉስጥ በመክተት 'ኤ ሲቴ' ኤ ሲቴ'በሀዲየኛ (ልጄን ትተህ እኔን ብላኝ) እያልኩ መጮህ ጀመርኩ " ብለዋል።

" ጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ ተካ በጄርካንና በመዘፍዘፊያ ጅቡን እየመቱ መጯጯህ ቀጠልን ፤ በመሃል ትግልና ጩኸታችን ስለበዛ ጅቡ እኔንም ልጄንም ትቶ ወደ ወ/ሮ መቅደስ ሲዞር አፉ ደም በደም ሆኖ ነበር " ሲሉ አስረድተዋል።

መምህርት ደንበሌ አስራት " እየጮህን ስንታገል የሰሙ ሰዎች ደርሰዉ ጅቡን በመግደላቸዉ እኛ ወደ ሆስፒታል ተወሰድን " ብለዋል።

" ከፈጣሪ በታች እኔንና ልጄን የታደገችን ጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ ናቸዉ " የሚሉት መምህርት ደንበሌ አስራት ለተደረገላቸው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል።

ወ/ሮ መቅደስ ተካ በበኩላቸው " ልጅና እናቱን ከጅቡ አፍ ለማስጣል ከ10 ደቂቃ በላይ ታግለናል " ያሉ ሲሆን " የናቲቱ ወ/ሮ ደንበሌ ለልጇ መስዋዕት ለመሆን መዘጋጀት እኔም እናት ነኝና ሆዴን አባብቶ ጅቡን በጋራ ታግለን የከፋ አደጋ እንዳይደርስ አድርገናል" ብለዋል።

ከዚህ ቀደም አንዲት እናት ተመሳሳይ አደጋ በራሳቸዉ ላይ መድረሱን የሚያስታውሱት ሁለቱ እናቶች ከአደጋዉ ባሻገር በሀዲያ ዞን ዋና ከተማ ሆሳዕና ዉስጥ ሆነን " ከጅቦች ጋር ታግለን የምንጠቀመዉ የዉሃ ችግር እልባት ሊሰጠዉ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ወደ ግርግር እና ረብሻ የሚመሩ የተዛቡ ሁከት ቀስቃሽ መልዕክቶች እየተሰራጩ ነው " - የትግራይ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ

የህዝቡ ሰላም እና ፀጥታ በሚያውኩ አካላትም ይሁን ግለሰቦችላይ  የማያዳግም አርምጃ እንደሚወሰድ የትግራይ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ በጥብቅ አስጠነቀቀ።

ቢሮው " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች " ጥር 14
/2017 ዓ.ም ያወጡትን መግለጫ ተከትሎ " የማያሻማ የመግለጫውን ትርጉም ወደ ጎን በመተው ለራሳቸው የፓለቲካ ማራመጃ በማለም  ጉዳዩን እያወሳሰቡት ይገኛሉ ብሏል።

" የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች " ጥር 14 / 2017 ዓ.ም ያወጡት መግለጫ የድጋፍ እና ተቃውሞ ሰልፍ የሚያስፈልገው እንዳልሆነ የጠቀሰው ቢሮው " መግለጫውን የተለያዩ ትርጉሞች በመሰጠት ወደ ግርግር እና ረብሻ የሚመሩ የተዛቡ ሁከት ቀስቃሽ መልዕክቶች እየተሰራጩ እየተመለከትን ነው " ሲል ገልጿል።

በተለያዩ አደረጃጀቶች ስም ተሸፍኖ በአንዳንድ ግለሰቦች እየተሰጠ እና እየተሰራጨ ያለውንና  " የበላይ ወታደራዊ  ኃይል አመራሮች " የሰጡት መግለጫ አቋም የማይወክሉ መልእክቶች በአስቸኳይ መታረም አለባቸው ብለዋል ቢሮው።

በተሳሳቱ ቅስቀሳዎች ህዝቡን ወደ ሁከት እና ብጥብጥ የሚመሩ ብሎም ስርአት አለበኝነት እንዲነገስ የሚሯሯጡ አካላት ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ እና ከማንኛውም ህገ-ወጥ ተግባር እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

" ያለውን ሁኔታ የሌለውን መልክ በማስያዝ ፦
- ሰልፍ ማደራጀት ፣
- የመንግስት አገልግሎት ማስተጓጎል እና ማቋረጥ ፣
- መንገድ በመዝጋት እንቅስቃሴ ማወክ እና ማደናቀፍ፣
- ሃይል በመጠቀም የግል ፍላጎት ለማሳካት የሚደረግ እንቅስቃሴ ፍፁም የማይፈቅድ መሆኑ አጥብቆ አሳስቧል።

ህዝቡ ከዚህ መሰል ተግባር እንዲርቅ ወደ ህገ-ወጥ ተግባሩ የሚቀላቀሉ እንዲመክር እና እንዲገስፅ ፤ምክር እና ተግሳፁን በመጣስ ወደ ሁከት እና ግርግር የሚገቡት ደግሞ እንዲኮንን ጥሪ አቅርቧል።

ቢሮው የሚያቀርበው ምክር እና መረጃ ወደ ጎን በመተው በድጋፍ እና ተቃውሞ ስም ወደ ጥፍት በሚገቡትንና በአስተባባሪዎቻቸው ላይ ስርአት የማስከበር ስራ ይሰራል ብሏል።

የህዝቡን ሰላም እና ፀጥታ በሚያውኩ አካላትም ይሁን ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ በጥብቅ አስጠንቅቀዋል።


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል የተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ እንዳልሆነ ለኢትዮጵያ መንግስት  እናሳውቃለን "  - የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ 

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው (null and void እንዲሆን) ወስኗል። 

" በሰራዊቱ የኮር አመራር የሚል አደረጃጀት እውቅና የለውም " ሲል የወሰነው ካቢነኔው  " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የተሰጠውን መግለጫ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።

ካቢኔው ዛሬ ቅዳሜ ጥር 17/2017 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ፤ "የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ፦
- ለአንድ ቡድን የወገነ
- መንግስት የሚፈርስ
- ሰራዊት የሚበትን
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ እና መሰረታዊ ችግር ያለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲታረም እና ታች ወርዶ እንዳይተገበር ወስኗል። 

" የተሰጠው መግለጫ ከሰራዊት ተልእኮ ያፈነገጠ ፣ ተቋማዊ አሰራር የጣሰ " ነው "ሲል የገለፀው ካቢኔው ፥ " ' አመራር ነኝ ' በሚል በዚህ ሁኔታ ተሰብስቦ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል ስልጣን የለውም " ብሏል።

" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ መንግስታዊ ማስተካከያ እንዲደረግ አስመልክቶ የቀረበው አቋም የአንዱ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት ሲባል የፕሪቶሪያ ውል የሚያፈርስ ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው " አደገኛ ነው ' ሲል ገልጾ በአስቸኳይ የሚታረምበት አቅጣጫ ማስቀመጡን አሳውቋል።
  
ካቢኔው ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ለኢትዮጵያ መንግስት ባስተላለፈው መልእክት " ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ አይደለም በመሆኑም ወድቅ አድርጎታል ፤ ሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር  አሁንም ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተገዢ በመሆን ጅምር ሰላሙ እንዲጎለብት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል " ብሏል።

" የትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍላጎት ሰላም ነው " ሲል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ መልእክት ያስተላለፈው ካቢኔው ፤ " የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በአፈፃፀም ብዙ ችግሮች ቢኖሩትም በስምምነቱ አፈፃፀም የሚነሱ ችግሮች በሰላማዊ እና ፓለቲካዊ ትግል እንዲመለሱ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የተሟላ ድጋፍ እንዲያደርግ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ንጉስማልት
አፍ ላይ ቀለል ብሎ የሚጠጣ ፣ ልብን በደስታ የሚሞላ ፣ ልዩ ጣዕም!

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ /channel/Negus_Malt

#ደስደስበንጉስ #nonalcoholic #ከአልኮልነፃ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴 " ዩኒቨርሲቲያችን እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

➡️ " ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " - ሙስሊም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ


የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት የእስልምና እምነት ተከታይ / ሙስሊም ተማሪዎች " በሃይማኖታዊ አለባበሳችን ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን አድርሰዋል።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ተማሪዎቹ መካከል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ እና ሰመራ ካምፓስ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " አትግቡ መባል ከጀመርን አንድ ወር ገደማ ሆኗል " ያሉን ሲሆን " በሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኮሚቴ አማካኝነት በፅሑፍ ቅሬታ አቅርበን ስንጠባበቅ ከሰኞ ጥር 12/2017 ዓ/ም  ጀምሮ ' ንቃብ ማድረግ አትችሉም ' ተብለን ግቢ እንዳንገባ በመከልከላችን በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለን እንገኛለን " ብለዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኑሬዲን አብደላህ ፤ " ችግሩ ከተማሪዎች ባሻገር አንዲት የዩኒቨርስቲው መምህርትም ጭምር ያካተተ ስለነበር ለዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮች ቅሬታ በፅሑፍ አቅርበን በቂ ምላሽ ስላልተሰጠን ተማሪዎች በዚህ የፈተና ወቅት በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለዉ ይገኛሉ " ብሏል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ከማል ሀሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ በደቡብ ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኩል 150 ተማሪዎች ከእስላማዊ አለባበሱ ጋር በተያያዘ ክልከላ እንደተደረገባቸውና አብዛኞቹ  የፈተና ወቅት በመሆኑ ኒቃብ አዉልቀዉ ማስክ እየተጠቀሙ ወደ ግቢ እንደገቡ ገልጸዋል።

ስራ አስኪያጁ ፥ 22 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች አሁንም በመስጊዶች ተጠልለው እንደሚገኙ መረጃዉ በጽሑፍ እንደደረሳቸው ገልፀዉ ጉዳዩን ለትምህርት ሚንስትር በፅሑፍ ማቅረባቸውንና " ባለድርሻ አካላት የቆዩ መመሪያዎችን ዳግም ማየት ይጠበቅባቸዋል " ብለዋል።

" ከሁለት ዓመታት በፊት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ችግር ተነስቶ እንዲረግብ ተደርጎ የነበረ ሲሆን አሁንም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ችግሩ ላለመነሳቱ ዋስተና የሌለ በመሆኑ እነዚህን አጋጣሚዎች ለሌሎች ፍላጎቶች በሚጠቀሙ አካላት ጉዳዩ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ዘላቂ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል " ብለዋል።

ቲክቫህ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)ን ስለ ጉዳዩ አነጋግሯቸዋል።

ዶክተር ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፥ " የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " ብለዋል።

" በዩኒቨርሲቲው ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ አልተከለከለም ኒቃብ ደግሞ አስቀድሞም በዩኒቨርሲቲ አይደረግም ነበር " ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለዉም " በተለያዩ ማህበራዊ  ሚዲያዎች ዩኒቨርሲቲዉ ' ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ሂጃብ መልበስ ከልክሏል ' በሚል የሚሰራጨዉ መረጃ ትክክል ያልሆነ ሀሰተኛ መረጃ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህ ምክንያት ወጪ አሉ ስለተባሉ ተማሪዎች እና ስላመለጣቸዉ ፈተናዎች እንዲሁም ስለዩኒቨርስቲው ቀጣይ አቋም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበዉ ጥያቄ የተለየ ዉሳኔ አለመኖሩን ዩኒቨርስቲው አስታዉቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia

ግምሩክ ኮሚሽን አምራቾች ወደ አገር ዉስጥ እቃዎችን ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ ብቻ እንዲስተናገዱ ፈቅዷል።

ኮሚሽኑ በአምራቾች ወደ አገር ዉስጥ የሚገቡ ዕቃዎች የዋጋ አተማመን ስርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

158/2011 የተደነገገውን በጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ አተማመን መመሪያ እንዲከለስ ማድረጉን ነዉ የተገለጸው።

ይህ መመሪያ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ በሚወስንበት ወቅት የሚወስደው ጊዜ ከአምራቾች ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ ይገኛል።

ይሄን ተከትሎ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ አተማመን ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን ተነግሯል።

መመሪያ ቁጥር
158/2011 እስኪሻሻል ድረስ በክሊራንስ ጊዜ የዋጋ ማጣራት ሃደቱ የሚወስደውን ጊዜ ለማስቀረት በሚል አምራቾች እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ እንዲስተናገዱ ኮሚሽኑ በላከው ሰርኩላር ፈቅዷል።

ይህ ሰርኩላር ፦
- አምራቾች
- ልዩ መብት የተሰጣቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ፕሮግራም ተጠቃሚ ድርጅቶች፥
- ለኢንቨስትመንት ሥራ ዕቃዎችን በቀረጥ ነፃ የሚያስገቡ ድርጅቶች፤
- የመንግስት ፕሮጀክትን ለመስራት በግል ድርጅቶች የሚገቡ ዕቃዎች፣
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የፌዴራልና የክልል መንግስታት ተቋማትን ይመለከታል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካቲፓል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ባለቤቱ ላይ ለመስማት የሚከብድ እጅግ ዘግናኝ የወንጀል ድርጊት የፈጸመው ግለሰብ በሞት ተቀጣ።

(ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ)

" የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት " ይላል ይህ የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ።

ተከሳሽ ግለሰቡ ፀሃዬ ቦጋለ በየነ ይባላል።

ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን እንድትስት ያደርጋል።

በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት ያስገባታል።

ከዛም አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ ይጨምራል።

የቆረጠውን እግሯም ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ይቆያል።

በኋላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ይጣራል።

ግለሰቡም በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል አልቻለም።

በዚህም ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ይወስናል።

ግን ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ተረጋግተን በጥንቃቄ ብናሽከረክር ምናለበት ?

" በአደጋው ከሞቱት ሦሥቱ የግብርና ባለሙያዎች የተቀሩት ነዋሪዎች ናቸው " - የስልጤ ዞን አስተዳደር

ትላንትና #ሀሙስ ጥዋት በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።

አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ወደ አርባ ምንጭ ሲጓዝ የነበረ ሀገር አቋራጭ አውቶቢስ ከቢለዋንጃ ወደ ሁልባራግ ኬራቴ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ/ባጃጅ በመጋጨቱ ነው።

የስልጤ ዞን አስተዳደር " በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ ህዝብና መንግሥት የጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ደፋ ቀና የሚሉ ሦስት የግብርና ባለሙያዎች አሉበት ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው
" ብሏል።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ፥ በባጃጅ ሲጓዙ የነበሩ 8 ተሳፋሪዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ገልጾ " አደጋው ዘግናኝ  ነው " ብሎታል።

የሟቾቹ አስክሬን በመቆራረጡና በደም በመጨማለቁ ፊታቸውን በማጠብ ነው ማንነታቸውን መለየት የተቻለው።

ፖሊስ " ጉዳት አድራሹ አውቶብስ በከፍተኛ ፍጥነት ይሽከረከር እንደነበር መረጃዎች አሉ  ነገር ግን ተጨማሪ የማጣራት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ " ሲል ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ገልጿል።


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Hibir Diaspora

For Ethiopians & Ethiopians with foreign nationalities who are living and working abroad.

For more information visit our website
https://www.hibretbank.com.et/diaspora/

Hibret Bank
United, We prosper!

📞Call us toll-free at 995.
🤳 Join our Telegram community and connect with us. /channel/HibretBanket
🌐 Follow us across all our social media platforms and visit our website on linktr.ee/Hibret.Bank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" መንግስታችን እንዳይፈርስ እስከ ሞት ድረስ እንታገላለን ፤የጦርነት ነጋዴዎች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " - አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ

ዛሬ በመቐለ  " እምቢ ለጦርነት እምቢ ለመፈንቅለ መንግስት !! " በሚል መሪ ቃል የሰሞኑን የወታደራዊ አመራሮች መግለጫ የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።

በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

በጊዚያዊ ኣስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ በሰልፉ ላይ ተገኝተው " የሰላም ዋስ የሆነው ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ አይሆንም ፥ የጦርነት ነጋዴዎች ይብቃችሁ " ብለዋል።

" የሻዕብያ ተላላኪዎች አቁሙ !" ሲሉ በምሬት የተናገሩት ከንቲባው " መንግስት ለማፍረስ የተሄደው ርቀት አይሳካም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ ህዝቡም እንዲከበሩ ያግዝ " ብለዋል።

" የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት እንዲተገበር ፣ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዲከበር እና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ  ቁርጠኛ መሆን አለበት " ያሉት ከንቲባው " የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላም ብቻ መሆኑን በማመን ወጣቱ ትግሉ አጠናክሮ ይቀጥል " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ ከመቐለ በተጨማሪ በሌሎችም ከተሞች ጊዚያዊ  አስተዳደሩን ለመደገፍ እና " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው መገለጫ እና ውሳኔና በመቃወም  ወጣቶች በበዙባቸው ሰልፎች  ተካሂደው ነበር።

በዚህም ፦
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የትግራይ ህዝብ ጥቅም በሰላም ብቻ ነው የሚረጋገጠው !
-  ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ !
- የፕሪቶሪያ ስምምነት ይከበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!

የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች ተደምጠዋል።

ትላንትና ዛሬ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የትግራይ ኃይል መኮንኖችን የሚደግፉና የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ የሚገኝ ሲሆን ሰልፎቹ የፖሊስን ክልከላ በጣሰ መንገድ ነው እየተካሄዱ ያሉት።

በህወሓት የፖለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና መከፋፈል ወደ ፀጥታ ኃይል አመራሮች መዛመቱ ህዝቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏል።

ትግራይ ከአስከፊው እና አውዳሚው ጦርነት ገና በቅጡ ሳታገግምና ችግሮች ሳይፈቱ ወደ ሌላ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ሁኔታ እየታየ መሆኑ በርካቶችን አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ከነገ ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጠጫ መንገዶች ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ይሆናሉ።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፤ በአዲስ አበባ ከተማ በ2ኛው ዙር ከሚለሙት የኮሪደር መስመሮች መካከል የሲሚት- ጎሮ መንገድ አንደኛው መሆኑ አስታውሷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሲ ኤም ሲ- ፔፕሲ - ጎሮ - መንገድ  ልዩ ቦታው ሳፋሪ መብራት አካባቢ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት አጠገብ የመንገድ ቆረጣ እንደሚከናወን ገልጿል።

ከነገ ጥር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጠጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆኑ አሳውቋል።

አሽከርከሪዎች ይህንኑ አውቀው አማራጭ መንገዶችን  እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት (4:38 ላይ) ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 36 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሆነ የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል ገልጿል።

መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 መመዝገቡን አሳውቋል።

በርካታ ሰዎች የዛሬው ከወትሮው የተለየ ነበር ብለዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የነበረበት አካባቢ ያሉ ወገኖች " አስፈሪ " ሲሉ ገልጸዋል።

ንዝረቱ የተሰማባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከወትሮው የተለየ እንደነበር ታውቋል።

ለአብነት አዲስ አበባ ብዙ ሰዎች ህንጻ ላይ የነበሩ ተሰምቷቸው መደናገጣቸውን ገልጸውልናል። ለተወሰኑ ሰከንዶች የቆየ ቢሆንም የህንጻ ንቅናቄ ስሜት ፣ የመንስታወት መርገፍገፍ እንደተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል " 4ኛ ፎቅ ላይ በተቀመጥኩበት መስታወቱ ፣ የቤት እቃዎች ሲነቃነቁ፣ እኔም በተቀመጥኩበት በወትሮ በተለየ ንዝረት ሲሰማኝ ነበር " ብሏል።

ሌላ 12ኛ ፎቅ ላይ የነበረ የቤተሰባችን አባል " ያስፈራ ነበር " ሲል ክስተቱን አስረድቷል።

ከዚህ ባለፈ ንዝረቱ ከተሰባቸው ቦታዎች አንዱ የጅሌ ጥሙጋ አካባቢ ሲሆን የወረዳ አስተዳደር ህንፃ ላይ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በድንጋጤ ከህንጻው መውረዳቸውን ከሰራተኞቹ ለመረዳት ተችሏል።

Photo Credit - Omer Al Faruq

@tikvahethiopa

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በአዲስ አበባ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ለሞት የሚዳርጉ 5 መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?

➡ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ከፍተኛ የሞት አደጋ የሚያስከትሉ 5 መንገዶች ተለይተዋል።

➡ ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ ተብለው የተለዩት ፦
° መገናኛ፣
° ኃይሌ ጋርመንት፣
° ቦሌ ሚካኤል፣
° ጦር ኃይሎች
° ቻይና ካምፕ መንገዶች ናቸው። በአማካይ በዓመት ከ6 እስከ 13 ዜጎች በእነዚህ መንገዶች በሚደርሱ የተሽከርካሪ አደጋቸው ሕይወታቸውን ያጣሉ።

➡ ከመንገዶቹ አንዳንዶቹ የእግረኛ መተላለፊያ የላቸውም ፤ አሽከርካሪዎች ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ከፍጥነት ወሰን በላይ እያሽከረክሩ አደጋ ያደርሳሉ።

➡ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በሚደርሰው የትራፊክ አደጋ፣ በአብዛኛው ሕይወታቸውን የሚያጡት ወንዶች ናቸው። መገናኛ አካባቢ አደጋ ከደረሰባቸው 13 ሰዎች አብዛኞቹ ወንዶች መሞተዋል።

➡ አደጋ የሚደርሰው ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በተለይም ሰንበት ወይም የዕረፍት ቀናት ከመንገድ መጨናነቅ ነፃ ስለሚሆኑ፣ ተከትሎ በፍጥነት ማሽከርከር ምክንያት የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነው።

➡ አደጋዎች የሚያሳዩት ተቆጣጣሪ ተቋማትም ሆኑ አደጋ አድራሾችና ተጎጂዎች የሚያደርጉት ጥንቃቄ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው።

➡ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ከሌሎች የተሽከርካሪ ዓይነቶች አብላጫውን አደጋ የሚያደርሱትም እነሱ ናቸው።

➡ በዓለም የጤና ድርጅት የትራፊክ አደጋ ሥጋት መንስዔዎች ተብለው የተለዩት በፍጥነት ማሽከርከር፣ ጠጥቶ ማሽከረከር፣ የደኅንነት ቀበቶ አለመጠቀምና የራስ ቅል መሸፈኛ አለመጠቀም ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ።

➡ 43 በመቶ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረክራሉ። በዚህ ምክንያት ችግሩ ትኩረት ያሻዋል።

➡ በየዓመቱ ከ400 የሚበልጡ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ። የጥናቶች የትኩረት አቅጣጫ የፍጥነት መገደቢያ መጠቀምና ሥር ነቀል የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስገልጋል።   

(የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት መረጃ)

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል።

በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች ያካተቱ ሰልፈኞች ደግሞ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚነት (null and void እንዲሆን) እንዳይኖረው ፤ ጦርነት የሚፀየፉና ጅምር ሰላም እና ለውጡ እንዲቀጥል የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል።

በሰሜናዊ ምዕራብ ፣ ማእከላዊ ዞኖች መቐለ ከተማ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት ብቻ የጠራቸው ሰልፎች ሲካሄዱ ፤ በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች በደጋፊ እና ተቃዋሚ በአንድ ጊዜ የተጠሩ ሰልፎች ተከናውነዋል።

በውቅሮ ከተማ የፀጥታ አካላት በራስ ተነሳሽነት ለመውጣት በሞከሩት ላይ ለመበተን የሞከሩ ሲሆን ፤ በዓዲግራት የነበሩት የለውጥ ደጋፊዎች ላይ ግን ለመበተን የተደረገ ሙከራ እንደሌለ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዘግቧል።

ትናንት ጥር 17/2017 ዓ.ም  በደቡባዊ ዞን የተለያዩ ከተሞች " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው ውሳኔ የሚቃወም ጦርነት የሚያወግዝ ሰላምና ለውጥ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ የተካሄደ ሲሆን ዛሬ እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት የጠራው ሰልፍ በዞኑ አልተካሄደም።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት በጠራው ሰልፍ የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?

- የትግራይ ሰራዊት ውሳኔ ይተግበር !!
- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በአስቸኳይ ይስተካከል !!
- የፕሪቶሪያ ውል ይተግበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የህወሓት ህጋዊነት በአስቸኳይ ይመለስ !!
- የውጭ ጣልቃ ገብነት አንቀበልም !!
- ሰራዊታችን ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ አንቀበልም !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት መተግበር ለትግራይ እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ዋስትና ነው !!

በራስ ተነሳሽነት ወጣቶች በብዛት በተሳተፉባቸው ሰልፎች የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?

- የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም !!
- የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የህዝብ አገልጋዮች እንጂ የአንድ ቡድን ከለላ አይደሉም ! 
- የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
- የሚቆም ትግል እና ለውጥ የለም !!
- ወጣቶች ለልማት እንጂ ለጦርነት አንሰልፍም!!
- የተረጋጋ መንግስት ለመትከል የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው !!
-ጊዚያዊ አስተዳደሩ ወደ መደበኛ መንግስት የሚያሸጋግረን በቸኛ ህጋዊ ተቋም ነው !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲፀና እንፈልጋለን !!

... ሲሉ ተደምጠዋል።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ ዛሬ ጥር 18/2017 ዓ.ም መቐለ ጨምሮ በመላው ትግራይ የሚካሄደው ሰልፍ መግባባት የተደረገበት እና የተሟላ ጥበቃ የሚደረገበት ነው ያለ ሲሆን ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በኩል ጥር 17/2017 ዓ.ም  ባወጣው መግለጫ ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የተጠራ እና የተፈቀደ ሰልፍ የለም ብሎ ነበር።

የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ህወሓት ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በቂ ጥበቃ ለመስጠት በመቸገሩ ምክንያተት ቀን እንዲቀየርለት ሲጠይቅ : የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ  ትእዛዝ ተላልፈው ስበብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ በሚያካሂዱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ማስጠንቀቁ መዘገባችን ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ እስከ አሁን ባለው መረጃ በድጋፍ እና በተቃውሞ በኩል የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ሰላማዊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ ፓሊስ እንዲሁም የሰላም እና  የፀጥታ ቢሮ የሚሰጥ መረጃ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MPESASafaricom

እኛ ለወዳጅ ለመላክ እንዘጋጅ እንጂ ብሩን ፈጥኖ በማድረስ M-PESA አለልን ፤ ከM-PESA ወደ M-PESA ገንዘብ ስንልክ ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ በነፃ እንስተናገዳለን!

#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🚨 " ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የተፈቀደ የተጠራ ሰልፍ የለም " - የትግራይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

🔵 " እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም መቐለ ጨምሮ በመላው ትግራይ የሚካሄደው ሰልፍ መግባባት የተደረሰበት እና የተሟላ ጥበቃ የሚደረገበት ነው " - በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት

🔴 " ህወሓት ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በቂ ጥበቃ ለመስጠት ስለምንቸገር ቀን እንዲቀይር እናስታውቃለን " - የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን


እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም ጥር 14/2017 ዓ.ም " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚደግፍ እና የሚቃወም ሰልፍ መጠራቱን ተከትሎ ፓሊስ ሰልፉን መሸፈን የሚችል የሰው ሃይል ስለሚያንሰው እንዲቀየር ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ ጥር 17/2017 ዓ.ም ፓሊስ የሰጠው የሰልፍ ክልከላ ማሳሰብያ በመጣስ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የተለያዩ ከተሞች " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂደዋል።

እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ ፓሊስ " በቂ ጥበቃ ስለሌለኝ ሰላማዊ ስልፍ የሚካሄድበት ቀን እንዲቀየር " ቢያሳስብም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ሰልፉ የተሟላ የፀጥታ ጥበቃ ያለውና ተፈፃሚ የሚሆን ሲል የፅሁፍ መግለጫ ሰጥቷል።

" እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም መንግስት በመቐለ የጠራው ሰብሰባም ይሁን ሰልፍ የለም " ያለው የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ፤ " ሰልፍ ይካሄዳል " በማለት ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ የሚያደናግሩት አካላት እና ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Are you a bold innovator with a vision to contribute to Africa's economic prosperity? 🌍
The Jasiri Talent Investor Program is seeking exceptional entrepreneurs from Ethiopia🇪🇹,Kenya🇰🇪, Rwanda🇷🇼. We're looking for individuals with the potential to build high-impact ventures that disrupt industries, open new markets, and redefine how we live and work.

Check out our ideal candidate profile to see if you have what it takes to join Cohort 8.

To apply visit, https://jasiri.org/jasiri-talent-investor/

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከእርዳታዎች ጋር በተያያዘ በአስቸኳይ የሥራ ማቆም ትዕዛዞችን አስተላልፉ " - ሾልኮ የወጣው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ደብዳቤ

የአሜሪካ መንግሥት የውጭ እርዳታ እንዲቆም መወሰኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለባለስልጣናት እና ለውጭ አገራት ለሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች የላከው የውስጥ ማስታወሻ እንዳሳየ ቢቢሲ ዘግቧል።

ቢቢሲ ሾልኮ የወጣውን ይህ ማስታወሻ መመልከቱን ገልጿል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የውጭ ፖሊሲያቸው ውጤታማነት እና ወጥነት እስኪገመገም ድረስ ለ90 ቀናት የውጭ የልማት ድጋፍ እንዲቆም ባለፈው ሰኞ ዕለት የሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ አስተላልፈው ነበር።

የእርዳታ ማቆም ውሳኔውም ይህንን የተከተለ ነው።

አሜሪካ ከዓለማችን ትልቁ ዓለም አቀፍ እርዳታ ለጋሽ ስትሆን በእኤአ 2023 ፤ 68 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን ከመንግሥት የተገኘ መረጃ ያስረዳል።

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያስተላለፈው ትዕዛዝ ከልማት እርዳታ እስከ ወታደራዊ ድጋፍ ድረስ የሚሸፍን ሊሆን እንደሚችል የጠቆመ ነው።

ሾልኮ የወጣው የውስጥ ማስታወሻ ለድንገተኛ የምግብ ዕርዳታ እንዲሁም
#ለእስራኤል እና #ለግብጽ ወታደራዊ ድጋፍ በስተቀር ሁሉም የውጭ ልገሳዎች እንዲቆሙ የሚያዝ ነው።

በውጭ አገራት ላሉ የአሜሪካ ኤምባሲዎች የተላከው የውስጥ ማስታወሻ ፤ " እያንዳንዱ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ወይም ማራዘሚያ እስካልተገመገመ እና እስኪጸድቅ ድረስ አይለቀቅም " ይላል።

የአሜሪካ ባለስልጣናት " ከእርዳታዎች ጋር በተያያዘ በአስቸኳይ የሥራ ማቆም ትዕዛዞችን እንዲያስተላልፉ እና ይህም ግምገማውን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እስኪወስንበት ጊዜ ድረስ የሚቆይ ይሆናል " ሲልም ያትታል።

በተጨማሪም እርዳታዎች የፕሬዚዳንት ትራምፕን የውጭ ፖሊሲ ግቦች የተከተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በሁሉም የውጭ እርዳታዎች ላይ ሰፋ ያለ ግምገማ በ85 ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ያዛል።

አዲሱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ፤ " አሜሪካ በውጭ አገራት ገንዘብ ማውጣት ያለባት አገራችንን ጠንካራ፣ ደኅንነቷ የተጠበቀ ወይም የምትበለጽግ  ካደረገ ብቻ ነው " ሲሉ ከዚህ ቀደም ተናግረው ነበር።

አንድ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን የእርዳታ ማቆም ውሳኔው በአሜሪካ ልገሳ በሚደረግላቸው የውጭ እርዳታ ፕሮግራሞች ላይ " ከበድ ያለ ተጽዕኖ " እንዳለው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላችኋል " - በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት

በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ፤ ትናንት ጥር 15/2017 ዓ.ም  " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠውን መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም መግለጫው ፥ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት" የነሃሴው " ብሎ ሲጠራው ራሱን ደግሞ " ነባር " በማለት ገልጿል።

" የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን "  በሚል ያወጡት መግለጫ የ " ነሃሴው ህወሓት ህዝቡን እና ሰራዊቱ ለመበታተነ የሰራው ክፋት ውጤት ነው " በማለት ገልፆታል።

" የነሃሴው ህወሓት ህዝብን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያልተቀበለው ጉባኤ  በማካሄድ ነባሩን ህወሓት እንዲዳከም ሰርቷል " ሲል በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት ፤ " ወታደራዊ አምባገንነት ታግሎ ዴሞክራሲያዊ እና ህዝባዊ መንግስት የጨበጠ ህዝብ ወደ ኋላ አይመለስም " ብሏል።

" የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን "  በሚል ስም የወጣውን መግለጫ " የጦርነት አዋጅ ነው ፤ በህዝብ ላይ አፋኝ አስተዳደር የሚጭን ተቀባይነት የሌለውና የውድቀት ጥሪ " ሲል ገልጾታል።

" ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላቹሃል " ያለው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " የጦርነት አዋጃችሁ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፍርሶ ፤ ትግራይ ለአህጉራዊ ዓለምአቀፋዊ ተነጥሎ እና ውግዘት የሚዳርግ ህዝቡን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው " ሲል አክሏል።

የአነ አቶ ጌታቸው ቡድን መግለጫውን መላ የትግራይ ኃይል አባላት እንዲያወግዙት ጠይቆ " ህዝብን እና መንግስታችሁ በሚስጡዋችሁ አቅጣጫ ብቻ እንድትንቀሳቀሱ ጥሪያችን እናቀርባለን " ሲል አሳስቧል።

ህዝቡ እና ወጣቱ በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ገልጾ ይህንኑ በመገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትግሉ በማጠናከር ለመብቱ ለአንድነቱ እና ለህልውናው በመታገል የተደቀነበት አደጋ እንዲመከት ጥሪ አቅርቧል።

ለህዝቡ ፣ ለዳያስፓራ ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ስም የወጣው መግለጫ እንዲያወግዙት ጠይቀዋል።

መግለጫውን ያወጡት አመራሮች ያለፈ ታሪካቸው ከሚያጎድፍ ተግባር በመውጣት አሁን የፈፀሙት ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርሙ እና ታሪካቸው እንዲያድሱ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴 “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” - ሙስሊም ተማሪዎች

🔵 “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” - ዲላ ዩኒቨርሲቲ 

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው እየተስተጓጎሉ በመሆኑ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠንከር ያለ ስሞታ አቅርበዋል።

የተማሪዎቹ ዝርዝር ስሞታ ምንድን ነው ?

“ ኒቃብና ጥቁር ማስክ እንዳንለብስ ነው የተከለከልነው። ክልከላው የጀመረው ከአንድ ወር በፊት ነበር። በዚህም ማመልከቻ አስገብተን ነበር መልበስ እንዲፈቀድልን። ሆኖም ግን ምላሽ ሳይሰጠን ቆዬ።

ትምህርታችን በስርዓት እንዳንከታተል አስተጓጎሉን። ቅዳሜ፣ አንዲት እህት ማስክ አድርጋ፣ ሂጃብ ለብሳ በምትገባበት ወቅት ኦዲያ ካምፓስ በሁለቱም በሮች እንዳትገባ ከልክለዋታል።

እንዲያውም ወንዶቹ የግቢው ጥበቆች አስፈራርተው ፊቷን አስከፍተዋታል። እንደዛም ሆኖ ማስክ ለብሳ ወደ ግቢ መግባት እንደማትችል ነግረው መልሰዋታል። 

ቅዳሜ ከሰዓት ሁለት ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎች ግቢ ሊገቡ ሲሉ ተከልክለዋል። ለምን እንደተከለከሉ ሲጠይቁ ‘ ለደህንነት ሲባል ፊታችሁ መሸፈን የለበትም ’ አሏቸው።

ለደኅንነት ሲባል ከሆነ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በሴት ጥበቃ ተፈትሸው፣ አይዲያቸውን አሳይተው እንዲገቡ ሲጠይቋቸው ‘ ያንችን ፊት ማየት ምንም አይሰራልኝም። ፊትሽን ለምታሳይው አሳይ ’ የሚል መልስ ተሰጠን።

ከዚያ በኋላም ሰኞ እለት ደግሞ ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ መልበስ እንደማይቻል በፕሬዜዳንቱ ጭምር ተወሰነ። የተማሪ ተወካዮች ጠርተው ይህን አሳወቋቸው።

ጥበቃዎቹም ውሳኔውን በመጥቀስ ‘አናስገባም’ አሉን። ማክሰኞ እለት ማታ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን።

ረቡዕ ጠዋትም ከለር ማስክ አድርገው የገቡትን በፌደራል ጭምር አስፈራርተው ፊታቸውን እንዲገልጡ አድርገው፣ ሂጃብም ማውለቅ እንዳለባቸው አሳሰቧቸው።

ከሰኞ ጀምሮ ክላስም እየተከታተልን አይደለም፣ ኤግዛም አልፎናል፣ አሳይመንትም እያለፈን ነው። ማውለቅ ስለማንችል ከግቢ ውጪ ነን። በቃ ከተማሪነት ውጪ ባለ ህይወት ነን። እንደ ሴትነታችን ትልቅ የመብት ጥሰት ነው የተፈጸመብን። 

ከምሽቱ 3 ሰዓት እንዳንገባ ሲከለክሉን የት እንድናድር፣ ምን እንድንለብስ፣ ምን እንደምንምገብ ያሰቡትን አናውቅም። ስለዚህ እንደንገባ ቢፈቅዱም እንዲህ ያደርጉበት ምክንያትን ሊጠየቁ ይገባል ”
ሲሉ ተናግረዋል።

ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅናቸው ስማቸው እንዲነገር ያልፈቀዱ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ ስለጉዳዩ በዩኒቨርሲቲው ፌስ ቡክ ገጽ የወጣውን መረጃ እንድንጠቀም ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎቹ ነቃብ፣ ማስክና ሂጃብ ለብሰው እንዳይገቡ ተከልክለው ከግቢ ውጪ በመሆናቸው ትምህርት እያለፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፤ መከልከሉ ልክ ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

በምላሻቸው፣ “ እንዲህ አይነት ነገር የለም። የተሳሳተ መረጃ ነው። ማንም ተማሪ እዚህ ግቢ በተፈቀደለት ሰዓት ይገባል፤ ይወጣል ” ሲሉ መልሰዋል።

“ የተቋሙንም ሆነ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት አስተዳደር መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” ብለዋል።

ተማሪዎቹ በተጨባጭ ከግቢ ውጪ እንደሆኑ፣ ክላስ እያለፋቸው እንደሆነ በድጋሚ የገለጽንላቸው እኝሁ አካል፣ በድጋሚም “ የለም ” የሚል ማስተባበያ ነው የሰጡት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የጌዴኦ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን ተማሪዎች ደረሰብን የሚሉት ክልከላ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲው “ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” ብሏልና እናንተ ጉዳዩን አይታችሁት ነበር ? ሲል ማረጋገጫ ጠይቋል።

ምክር ቤቱ ምን መለሰ ?

“ ጉዳዩ ከወር በፊት ደርሶን ነበር። እየቆየ ከፍ እያለ መጥቶ ተማሪዎች ግቢ ለመግባት ሲከለከሉ እኛም ደብዳቤ ፅፈን ነበር ችግሩ እንዲፈታ።

ዩኒቨርሲቲው እርከን ያልጠበቀ ጉዳይ ተደርጎ ታይቶ ነው፤ ተማሪዎቹን እናገኛቸዋለን የሚል ጥሩ ስሜት ነበረው። 

የእስልምና አለባበስ ከጥንት ጀምሮ ራሱን የቻለ ሊቃውንቶች ያስቀመጡት ነው። ይሄ የተሻለውና ተመራጭ የሆነው አለባበስ ነው ” ብሏል።


(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🌟 ቴሌብር ሱፐርአፕን በዋይፋይ መጠቀም ተቻለ!!

ቴሌብር ሱፐርአፕዎ ላይ መለያ (Account) ይግቡ፣ በመቀጠል Access on Wi-Fi የሚለውን በመመምረጥ እና መስማማትዎን በማረጋገጥ ለተገደበ ጊዜ አልያም ለሁልጊዜ ደኅንነቱ እንደተጠበቀ ማስተካከል ይችላሉ፡፡

💁‍♂️ አንድ ጊዜ ካስተካከሉ በኋላ በድጋሚ ማስተካከል ሳይጠበቅብዎ በዋይፋይ ወይም በሌላ ሲም ካርድ ዳታ ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕዎ መግባትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

⚠️ ከአገር ውጪ ቴሌብር ሱፐርአፕን  መጠቀም ከፈለጉ ከአገር ከመውጣትዎ በፊት እንዲያስተካክሉ ይመከራል፡፡

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ይሄ የመጨረሻ ደብዳቤያችን ነው ! " - ጠቅላይ ምክር ቤቱ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጨረሻ ያለውን ደብዳቤ ጻፈ ለትምህርት ሚኒስቴር ፅፏል።

ምክር ቤቱ ፤ ኢስላማዊ አልባሳት ስለለበሱ ብቻ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው የሚጠይቅ የመጨረሻ ያለውን ደብዳቤ ለትምህርት ሚኒስቴር ጽፏል፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢስላማዊ አለባበስ ጋር በተያያዘ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጫናና ከትምህርት መፈናቀል በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ውይይቶች ሲያደርግ መቆየቱንና በዚህ ወር ብቻ ለትምህርት ሚኒስቴር ሶስት ጊዜ ደብዳቤዎችን መጻፉን ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር እስከ አሁን ተገቢ ምላሽ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳላገኘና አሁንም ችግሩ በዲላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ መፈፀሙን አመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ም/ቤቱ የመጨረሻ ባለው በዚህ ደብዳቤ ኢስላማዊ ልብስ ስለለበሱ ብቻ ትምህርት የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተገፎ ወደ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ የተከለከሉ የዲላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአፋጣኝ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱና ለችግሩ ዘላቂ አስተዳደራዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቋል፡፡

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውጤቱ ህዝብን እና አገር የሚያጠፋ አካሄድ በመሆኑ መቆም አለበት " - የተለየ አቋም ያላቸው ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች 

በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ የትግራይ ኃይል አመራር መኮንኖች ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ያወጡት መግለጫ ተቃውሞ እየገጠመው ነው።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደርን በመቃወም በብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ያልተሰጠው ጉባኤ ያካሄደው በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት እውቅና እንደሚሰጡ ያስታወቁት የትግራይ ኃይል አመራሮችን ጊዚያዊ አስተዳደሩ በፅኑ ተቃውሟቸዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩን መግለጫ ተከትሎ በአመራሮቹ ሰብሰባ ላይ የተሳተፉ የተለየ አቋም እንዳላቸው የገለጹ ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች ፥ " የሰራዊት አመራር በመሆን የፓለቲካ ፓርቲ የሚመስል ሰራዊት ለመገንባት የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤቱ ህዝብን እና አገር የሚያጠፋ አካሄድ እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

የተለየ አቋም እንዳላቸው በመግለጫቸው ያሳወቁት ከፍተኛ አመራሮቹ ፤ " አንድ የፓለቲካ ፓርቲ እና በዚህም በዚያም ያሉት ቡድኖችን የሚመለከት አጀንዳ ላይ መወያየት እና አቋም መያዝ ከሰራዊቱ ተልእኮ ውጪና ወታደራዊ ወንጀል በመሆኑ በጥብቅ እንቃወማለን " ሲሉ አብራርተዋል።

" ስለሆነም ከሰራዊቱ ተልእኮ እና የስራ ስምሪት ውጪ ' ጠላት ነው ' በሚል ፍረጃ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ፕሬዜዳንት ለመቀየር የሚደረግ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ተቋማዊ አሰራር የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም በጥብቅ እንጠይቃለን " ሲሉ አክለዋል።

የክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡብ ምስራቃዊ ፣ የደቡባዊ ዞን ኦፍላ ወረዳ እንዲሁም በራስ ተነሳሽነት መሰባሰባቸውን የገለፁ የመቐለ ከተማ ወጣቶች ባወጡት መግለጫ ፤ " ወታደራዊ  መኮንኖች ከተልእኮ እና ከተሰጣቸው ህዝባዊ እና መንግስታዊ  ስምሪት ባፈነገጠ መልኩ ወደ አንዱ ቡድን በማዳላት ያወጡት መግለጫ በአስቸኳይ እንዲያርሙት " ሲሉ ጠይቀዋል።

የትላንቱ የመግለጫ ተቃዋሚዎች  ፤ " አመራሮቹ ያወጡት ህገ-ወጥ መግለጫ ጅምር ሰላሙ የሚያጨልምና የሚያመክን በመሆኑ ፤ ለህግ እና ስርዓት ተገዢ ከሆኑ አመራር እና አባላት ጋር በመሆን እስከ መጨረሻ ብፅናት እንደምንታገላችሁ ልናሳውቃችሁ እንፈልጋለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የትላንቱን መግለጫ በመቃወም ለቪኦኤ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " የትግራይ ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ እንዲሆን የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ስህተት ነው ፤ ወታደራዊ መኮንኖቹ ፓለቲከኛ መሆን ካሰኛቸው ወታደራዊ ሃላፊነታቸው በመተው የፈለጉት ፓርቲ አባል መሆን ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ያደረጉት ስህተት ግን በአስቸኳይ እንደሚያሩሙት ተስፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” - ሠራተኞቹ

በርካታ ቅሬታዎች ያደሩባቸው ከ350 በላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሱቫል ሠራተኞች ለቅሬታቸው አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም።

“ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሩቫል ሰርቪሶች ተቋርጠዋል ” ብለው የነበረ ሲሆን፣ ሠራተኞቹን የሚያስተዳድረው አይሰን የተሰኘው ድርጅት ቅሬታውን በውይይት እንደፈታ ትላንት ምላሽ ሰጥቶን ነበር።

የትራንስፖርት መገናኛ ሠራተኛ ማኀበራት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን፣ ሠራተኞቹ ደመወዝ ሊጨመርላቸው ስምምነት ላይ እንደተደረሰ፣ ሌሎች ጥያቄዎቻቸው በሂደት እንዲፈቱ፣ ለዛሬ ሠራተኞቹ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ነግሮን ነበር።

ሠራተኞቹ አቋርጠውት ወደነበረው ሥራ ተመለሱ ?

ለቅሬታዎቻችሁ " መፍትሄ አላገኘንም " በማለት መብታችሁን ለማስከበር ካደረጋችሁት የሥራ ማቆም አድማ በኋላ ዛሬስ ወደ ሥራ ተመለሳችሁ ? ስንል ጠይቀናቸዋል። 

ሠራተኞቹም፣ “ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” የሚል ምላሽ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

ሠራተኞቹ ፦

“ ሥራ ጀምረናል። ግን ገና ብዙ የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ። ሁሉም ቀስ እያሉ ይስተካከላሉ። የደመወዙ ጭማሪ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።

ሌሎቹን ጉዳዮች በተመለከተም ከቀጣይ ሳምንት ጀምረን ወደ ድርድር እንገባለን። 

ሁሉም ሠራተኞች ወደ ስራ ተመልሰዋል። ምክንያቱም ማንም ሰው ባደረገው የሥራ አድማ ምክንያት አሉታዊ ነገር እንዳይደርስበት ተፈራርመን ነው የተመለስነው ” ብለዋል።


በጉዳዩ ዙሪያ የሚፈጠር አዲስ ነገር ካለም የምንከታተልና መረጃም የምናደርሳችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Подписаться на канал