የተስተካከለ እና ያማረ ቁመና ለወንዶችም ለሴቶሽም በሀገራችን በአቀራረቡ እና በአይነቱ ለየት ያለ * በአጭር ጊዜ ውስጥ ያማረና የተስተካከለ ሰውነት ለማምጣት *ክብደት ለመጨመርም ይሁን ለመቀነስ እረከስ ባለ ወጪ ምን መመገብ እንዳለብን እና ምን አይነት እንቅስቃሴ እንደምንሰራ -If You Want Any Advice And To Send Your Pictures @Rasmure
ሰላም ውድ የ @shegerfitness ቤተሰቦች ዛሬ የምናነሳው ስለ Progressive Overload(በሂደት ክብደት መጨመር) ነው። ይህ ማለት የጂም አሰራራችን፣ ምግባችን እና እረፍት አደራረጋችን ስህተት ከሌለበት ሰውነታችን የግድ ይጠነክራል።
ምሳሌ: ዛሬ ቤንች ፕሬስ በ50 ኪሎ ቀሎህ ክሰራህ የሚቀጥለው ምትሰራበት ቀን ላይ ኪሎ መጨመር ወይ ደግሞ ድግምግሞሹን መጨመር አለብህ። ያለበለዛ ሰውነትህ ለማደግ እና ጥንካሬ ለመጨመር በቂ ምክንያት እየሰጠከው አይደለም ማለት ነው ። ስውነትህ ጡንቻ ሚጨምረው ቀጣይ ለሚያጋጥምህ ከባድ ጭነት ተዘጋጅቶ ለመጠበቅ ነው፤ ለዛም ነው ክብደት ማንሳት ለጥቂት ወራት ከራቅን ሰውነታችን ጡንቻዎቹን ሚያፈርሳቸው።
ግን ስህተቱ ሚከሰተው አብዛኛው ሰው የመጀመሪያዎቹ 3 እስከ 6 ወር የነበረው የፍጥነት ጥንካሬ መጨመር እስክ ዘላለም ሚቀጥል ስለሚመስለው ነው። ለምሳሌ ስንጀምር ቤንች 20 ኪሎ ብቻ ቢሆን ምናነሳው በሚቀጥለው ሳምንት በአንዴ 25 ኪሎ ማንሳት ልንጀምር እንችላለን። ይህ አይነት ፍጥነት ግን እስከ መጨረሻው ሊቀጥል አይችልም። ለምሳሌ 80 ኪሎ ሚመዝን ሰው ቤንቹ 80 ኪሎ ቢሆን ሚቀጥለው ሳምንት 85 ልሞክር ቢል ይከብደዋል። የዛኔ አብዛኛው ሰው የሰውነቴን አቅም ደረስኩኝ ብሎ ተቀብሎ አመቱን እንዳለ በ80 ኪሎ ቤንች ይሰራል ማለት ነው። አመቱን እንዳለ ጥንካሬ ሳንጨምር አባከንነው ማለት ነው። ግን ቤንች ላይ አንድ ሰው የሰውነቱን 1.5 እጥፍ ለማንሳት ማቀድ አለበት። ይህ ሰው በ80ኪሎ ሰውነቱ 120 ኪሎ ቤንች መድረስ ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ ፖቴንሻሉን ሳይደርስ እጅ ሰጠ ማለት ነው።
ስለዚህ ኪሎ በስንት መጨመር አለብን?
ኮምፓውንድ ኤክሰርሳይሶች ላይ ከመጀመሪያዎቹ 3-6 ወር በኋላ ጥንካሬ ቀስ እያለ ነው ሚጨምረው። ሚመከረው በ2.5 ኪሎ ጨምረን መሞከር ሲሆን ይህ ማለት በባር ቤል (ዘንግ) በእያንዳንዱ ሳይድ ትንሽዬዋን 1.25 ፕሌት መክተት ነው። አብዛኛው ሰው ንቆ ይተዋትና በአንዴ 5 ኪሎ ጨምሮ ሲሞክር ይከብደውና ተስፋ ይቆርጣል። 1.25 ኪሎዋን ከተን ዛሬ ሰራን ማለት ሚቀጥለው ላይ 1.25 በ 2.5 ቀይረን እንሞከራለን። እሱን ከቻልን 2.5 ላይ ሌላ 1.25 ከትህ ሚቀጥለው ላይ ትሰራለህ። እንደዛ እያደረግን ቀስ በቀስ ቤንች ፕሬስ ግፊታችንን በወራቶች ውስጥ ከ80 ኪሎ ወደ 100 መቀየር እንችላለን ማለት ነው።
ይህን ለመከታተል ስልካችን ላይ መመዝገብ እንችላለን።
ለምሳሌ:
week one:
1)bench press 20kg
2)military press 10 kg
3)triceps extension 12kg
Week two
1)bench press 25kg
2)military press 14kg
3)triceps extension 15kg
ይሄ መልእት ጠቃሚ ሁኖ ካገኛችሁት ለወዳጆ እያጋሩ ሌላም ሰው ለመጥቀም ሞክሩ
/channel/shegerfitness
💪🔥``motivation``🔥💪
👊የሚገርምህ ነገር ይቺ የዛሬዋ ቀን ካሁን በፊት የማናውቃት ካሁን በኋላም የማናገኛት በፈጣሪ የተሰጠችን ልዩ ቀን ናት!..ታዲያ ይቺን ቀን ካልተጠቀምክባት ዳግመኛ አታገኛትምና ለህልምህ ጣርባት... መልካም ሰው ሆነህ አሳልፍባት!!
......
👊መሆን የነበረብህን ለመሆን መቼም አይረፍድም..የድርጊት ሰው ከመሆንህ በፊት የውሳኔ ሰው ሁን። ውሳኔህ ግልፅ ከሆነ ድርጊትህ አድካሚ አይሆንብህም።
pls Join And Share🙏🙏
👇👇👇👇👇👇
👉 @shegerfitness 👈
👉 @shegerfitness 👈
👆👆👆👆👆👆
The best preparation for good work tomorrow is to do good work today
Stay focus my peoples💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼
ክረምቱን በእስፖርት ለመለወጥ ለፈለግን ጥራቱን የጠበቀ protein powder በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘንላቹ መተናል
አዲስ አበባ ለሆናቹ ያሉበት ድረስ ይዘንላቹ እንመጣለን
ለመግዛት @Rasmure 👈ላይ ያናግሩኝ
ክረምቱን በስፖርት💪💪💪💪💪
ሩጫ ምን ጥቅም አለው ❓
ብዙዎቻችን ስፖርት ሲባል ቀድሞ ወደ አዕምሮአችን የምመጣው ሩጫ ነው።
ሩጫ በውድድር ስናይ ወደር የለሽ የገቢና የዝና ምንጭ ነው።
ነገር ግን እዚህ ጋር ማውራት የፈለኩት ስለ ሩጫ ጥቅም በ አኗኗራችን ላይ ነው።
ሩጫ ጠንካራ አጥንት እንድን ገነባ ያደርገናል፣ ክብደት እንድንቀንስ ይረዳናል።
ጤነኛ ክብደት እንድኖረን ያግዛል ፣ ጠንካራ ጡንቻም እንደዛው።
☞ የስኳር በሽታ ስጋትን ይቀንሳል።
☞ የአጥንት ክብደት ይጨምራል።
☞ የአዕምሮ ጤንነት ይጠብቃል።
☞ የልብ ምትን ያስተካክላል፣ ከልብ በሽታ ይከላከላል።
☞ ከልብ በሽታ፣ ከደም ግፊት ና ከስትሮክ ይከላከላል ።
☞ የልብ ምት፣ የደም ዝውውር ና የኦክስጅን ስርጭትን በማስተካከል ለቆዳችን ንውትረንትን በማቃበል አድስ የቆዳ ሰሎች እንድፈጠሩ ያግዛል።
👉 ጥናቶች እንደሚያሳዩ :- በቀን ከ 5-10 ደቂቃ ፣ በሰዓት ለ6 ማይል ፍጥነት መሮጥ፣ ለጤንነታችን ወሳኝነቱ የላቀ ነው ይላል።
~
✍️ RasMurat
/channel/shegerfitness
ሩጫ ምን ጥቅም አለው ❓
ብዙዎቻችን ስፖርት ሲባል ቀድሞ ወደ አዕምሮአችን የምመጣው ሩጫ ነው።
ሩጫ በውድድር ስናይ ወደር የለሽ የገቢና የዝና ምንጭ ነው።
ነገር ግን እዚህ ጋር ማውራት የፈለኩት ስለ ሩጫ ጥቅም በ አኗኗራችን ላይ ነው።
ሩጫ ጠንካራ አጥንት እንድን ገነባ ያደርገናል፣ ክብደት እንድንቀንስ ይረዳናል።
ጤነኛ ክብደት እንድኖረን ያግዛል ፣ ጠንካራ ጡንቻም እንደዛው።
☞ የስኳር በሽታ ስጋትን ይቀንሳል።
☞ የአጥንት ክብደት ይጨምራል።
☞ የአዕምሮ ጤንነት ይጠብቃል።
☞ የልብ ምትን ያስተካክላል፣ ከልብ በሽታ ይከላከላል።
☞ ከልብ በሽታ፣ ከደም ግፊት ና ከስትሮክ ይከላከላል ።
☞ የልብ ምት፣ የደም ዝውውር ና የኦክስጅን ስርጭትን በማስተካከል ለቆዳችን ንውትረንትን በማቃበል አድስ የቆዳ ሰሎች እንድፈጠሩ ያግዛል።
👉 ጥናቶች እንደሚያሳዩ :- በቀን ከ 5-10 ደቂቃ ፣ በሰዓት ለ6 ማይል ፍጥነት መሮጥ፣ ለጤንነታችን ወሳኝነቱ የላቀ ነው ይላል።
~
✍️ RasMurat
/channel/shegerfitness
የተመጣጠነ ምግብ /balanced diet
ለጥሩ ጤንነት እድገትና ጥገና ፣ አመጋገባችን ሰውነታችን የሚፈልገውን ሁሉ በተገቢው መጠን ሊኖረው ይገባል። በተጨማሪም ጥሩ ምግቦች እና የውሃ መጠን ሊኖረው ይገባል። እንዲህ ዓይነቱ አመጋገብ የተመጣጠነ ምግብ ይባላል ፡፡ ትክክለኛውን ዓይነት ምግብ መመገብ ብቻውን በቂ አይደለም።
ትክክለኛ አይነት ማለት ፕሮቲን ብቻ ወይም አታክልቶችን ብቻ ማዝወተር አይጠበቅብንም ሁሉንም ስናመጣጥነው ውስጣዊ ጤንነት የማሰብ ችሎታችንን ለማዳበር እና አካላዊ መዳበር በአጠቃላይ ለጤነታችን ይጠቅመናል
ስለዚህ በ ፐርሰንት ስንከፍለው
አታክልቶች40%
ፕሮቲን25%
ካርቦአይድሬት 25%
ጤናማ ስቦች 10%
ስለዚህ በምንችለው አቅም አመጋገባችንን ብናስተካክለው እላለው
Pls share @shegerfitness🙏🏼
Best exercise for big triceps
Pls share @shegerfitness and support as🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼
4. ጥራጥሬዎች፡- ባቄላ የዶክተር ሃርላን ተመራጭ የፕሮቲንና የበሽታ ተከላካይ ቫይታሚኖች መገኛ ነው፡፡ ባቄላ፣ ሽምራ፣ አተር እና የመሳሰሉት የጥራጥሬ አይነቶች ጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ‹‹ቆዳችን ከፕሮቲን የተሰራ ነው፡፡ ጥራት ያላቸው በቂ ፕሮቲኖች የማያገኙ ከሆነ ችግሩ ቆዳዎ ላይ ይንፀባረቃል፡፡ ይላሉ፡፡ ጂያን ኮሊም ባቄላና አሳ የቆዳን ውበት እንደሚያሳምሩ ይገልፃሉ››
5. አጃ፡- ጥናቶች እንደ አጃ፣ ዳቦ፣ ፓስቲ፣ ቡናማ ሩዝ ያሉት የእህል አይነቶች የመጉረብረብ ስሜትን እንደሚቀንሱ ገልፀዋል፡፡ ‹‹እነዚህ ምግቦች ለቆዳችን ጠቃሚ የሆኑትን እንደ ታሚንና ራይቦ ፍላቪን ያሉትን የቫይታሚን ቢ ዝርያዎችን ይዘዋል፡፡ የእነዚህ እጥረት በቆዳችን ላይ ሽፍታ እንዲወጣና ቆዳችንም ወዝ አልባ እንዲሆን ያደርገዋል››
እናመሰግናለን
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @Rasmure ፈታ ብላቹ ማናገር ትችላላቹ
👇👇👇share በማረግ ተባበሩን🙏
@shegerfitness @shegerfitness
@shegerfitness @shegerfitness
የቴምር 10 የጤና ጥቅሞች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
1. #የደም ማነስ ካለብዎት በሚገባ ያድንዎታል።
2. #ለአይን ጤንነት እና አይንን ከመታወር ይታደጋል።
3. #ለስንፈተ ወሲብ ፍቱን ነው።
4. #የሆድ ድርቀትን ይከላከላል/ይፈውሳል፤ እንዲሁም ተቅማጥን ይከላከላል።
5. #ክብደትን ለመጨመር ይረዳል።
6. #ጤናማ ልብ እንዲኖረን ያደርጋል።
7. #ጉልበት/ኃይል ይሰጠናል ወይም እንዲጨምር ያደርጋል።
8. #ጤናማ የሆነ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ያደርጋል።
9. #ጥርሳችን ጤናማ እና ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል።
10. #ለእርጉዝ ሴቶች በጣም ጠቃሚ ነው።
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
11. @shegerfitness ለወዳጅ ጒደኛዎ share በማረግ ትብብራችሁን አሳዩን🙏
የማንጎ ጥቅሞች
-----------------
1-ወደ 20 የሚጠጉ ለሰውነት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን እና ቫይታሚኖችን ይይዛል
2-ሁለት ማንጎን ብቻ መመገብ በሙሉ ቀን ውስጥ የሚያስፈልገንን ቫይታሚን-c
እንድናገኝ ያረዳል
3-በሽታን የመከላከል አቅም ያሳድጋል
4-በውስጡ ተፈጥሮአዊ ስኳር ስላለው ስኳር አምሮታችንን በሌሎች አርቴፊሻል ስኳሮች እንዳንወስድ ይረዳናል
5-የጉሮሮ እና የጥርስ ጤንነት ይጠብቃል
6-የቆዳን ውበት ይጠብቃል
እንጉዳይ(Mushroom)የመመገብ የጤና ጥቅሞች
------------------------
1-በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የኮልስትሮል መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል
2-ለልብ ጤና
3-ለጭንቅላት ጤንነት
4-ለአጥንት እድገት እና ጥንካሬ
5-በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሳደግ
6-ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል
/channel/shegerfitness
ቡና የመጠጣት ጠቀሜታዎች
------------------------
1-የሀይል ደረጃችን ያሻሽልልናል
2-የ አድሬናሊን(adrenaline) መጠን በሰውነት ውስጥ እንዲጨምር ያግዛል
3-ሪቦፋላቪን(riboflovin)፣ማንጋኒዝ፣ፖታሲየም እና አንቲኦክሲደንትስ(antioxifants) የሚባሉ ለሰውነት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን እንድናገኝ ያግዛል
4-የነርቭ የሽታ የመያዝ እድላችን እንዲቀንስ ያደርጋል
5-የጉበት እና የጨጒራ ጫፍ ካንሰር ቀድሞ ለመከላከል ይረዳል
pls share @shegerfitness 💪💪
በ tik Tko መተናል like እና Follow በማረግ አብሮነታቹን አሳዩን💪🏼💪🏼https://vm.tiktok.com/ZMNJNPctv/?k=1
Читать полностью…https://vm.tiktok.com/ZSJndW7M8/
በ tiktok መተናል like እና follow በማረግ አብሮነታችሁን አሳዩን
ሩስያዊው የአስር አመት ልጅ 5,713 ፑሽ አፕ በመምታት ሪከርድ አስመዝግቧል ።
ሩስያዊው የአስር ዓመቱ ኢልማን ካድዙሙራዶቭ ከፎዶርቭስኪ በየቀኑ ዘጠኝ ማይል ሩጫን ጨምሮ ከባድ የልምምድ ክፍለ-ጊዜዎች የሚያሳልፍ ሲሆን ዛሬ በሩሲያ በሱርጉት አውራጃ በሚገኘው የትምህርት ቤት የስፖርት ማእከል በሦስት ሰአት ተኩል ውስጥ 5,713 ፑሽ አፕ በመስራት የአለም የልጆች ፑሽ አፕ ሪከርደን ይዟል።
ከዚህ ቀደም ከእሱ እድሜ ክልል የሚገኘውና በቺችን ዋና ከተማ ግሮንዚ የሚኖረው የ10 አመት ልጅ 4,784 የሰራውን ፑሽ አፕ ነው ዛሬ ኢልማን ካድዙሙራዶቭ ከፎዶርቭስኪ የሰበረው። [አርቲ ሚዲያ]
@Shegerfitness
@shegerfitness
💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼🔥🔥🔥
✅Full Shoulder Exercise Library.
-
🔥EXERCISES:
✅Barbell Press
✅Seated Dumbbell Press
✅Alternating Cable Machine Front Raises
✅Seated Alternating Dumbbell Neutral Grip Front Raises
✅Lateral Dumbbell Raises
✅Seated Lateral Raise Machine
✅Dumbbell Reverse Flyes
✅Reverse Fly Machine
✅Dumbbell Shrugs
Pls share @shegerfitness @shegerfitness
5ቱ የማያስረጁ እና 5ቱ የሚያስረጁ ምግቦች
የሚያስረጁ ምግቦች
የአመጋገብ እቅድዎ በውስጥና በውጭ ወጣት ሆነው እንዲቆዩ የማድረግ ብቃት አለው፡፡ በጠዋት ተነስተው መስተዋት ፊት ሲቆሙ የሚያስቡት ‹‹ዋው! አምሮብኛል?›› አሊያም ‹‹መቼ ነው እንዲህ ያረጀሁት?›› ብለው ነው? ሁለተኛውን የሚሉ ከሆነ ፍሪጅዎን፣ ማዕድ ቤትዎና የምግብ ጠረጴዛዎ ላይ የሚያኖሩትን ምግብ ይጠራጠሩ፡፡ እርጅና በሁላችንም የመጣና ማቆም የማይቻል ቢሆንም አንዳንድ አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች ያለ ዕድሜያቸው አርጅተን እንድንታይ ያደርጋሉ፡፡ የእነዚህ ምግቦች ጉዳት በውጫዊ እኛነታችን ላይ ብቻ የሚገደብ አይደለም፡፡ ውስጣዊ ጉዳትም ያደርሳሉ፡፡
ጥራት ወሳኝነት አለው (Quality Counts)
‹‹በቅባትና በስብ የተጥለቀለቁ ምግቦችን መመገብ ሰውነታችንን እንዲቆጣ ያደርገዋል›› ይላሉ ‹‹Just tell me what you eat!›› የሚለው መፅሐፍ ደራሲና በቱሌን ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሴር የሆኑት ቲሞቲ ሃርላን፡፡
‹‹የጥራትና የጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ይዘታቸው ዝቅተኛ የሆነ Trans fats (ስብ የበዛባቸው ምግቦች) የሰውነታችንን የመቆጣት ስሜት ያነሳሳሉ፡፡ እርጅና ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የሰውነት የመጉረብረብ ሁኔታ ነው፡፡ ‹ክራብ የተሰኘውን ከባህር የሚገኝ ምግብ በመመገቤ የተነሳ ከዕድሜዬ በላይ ያረጀቡ እመስላለሁ› ብለው ቢጠይቁኝ መልሴ አዎ! የሚል ይሆናል›› ይላሉ ዶክተሩ፡፡
‹‹ለምሳሌ በጣም ብዙ ስኳርና በፋብሪካ ሂደት ውስጥ ያለፈ ካርቦሃይድሬትስ ያላቸው ምግቦች (processed carbohydrates); AGE (Advanced Glycation End) የተሰኘው ጎጂ ንጥረ ነገር እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ይህ ንጥረ ነገር ለበርካታ ጎጂ በሽታዎች ያጋለጣል፡፡ ከእነዚህ የልብና የስኳር በሽታዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በጅማቶችና በቆዳ ፋይበሮች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ›› ይላሉ የካሊፎርኒያ የህዝብ ጤና ማዕከል አማካሪና የአሜሪካ የስነ ምግባር ማህበር ቃል አቀባይ የሆኑት አንድሪያ ጂያን ኮሊ፡፡
ጎጂ ተብለው የሚመደቡ ምግቦችን መመገብ የሚያደርሰው ጉዳት በአካላዊ አቋማችን የተወሰነ አይደለም፡፡ ከእነዚህ ምግቦች አብዝቶ መመገብ የመቆጣትና መጉረብረብ ስሜትን ይጨምራል፡፡ የደም ቅዳዎች ደም እንዲረጋባቸው ያደርጋል፡፡ ክብደት እንድንጨምርም ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከፀጉራችን እስከ ጥፍራችን ድረስ ላለው ጤና መጥፎ ዜና ነው፡፡
ሊቀንሷቸው የሚገቡ ምግቦች
ወዝና ቁመናዎን ጠብቀው ከዕድሜዎ ጋር ሲተያይ ወጣት መስለውና ሆነው መታየት ከፈለጉ የእነዚህን አምስት ምግቦችና መጠጦች አወሳሰድዎን ይቀንሱ፡፡
1. የድንች ጥብስና በቅባት የተነከረ የድንች ጥብስ
በዘይት እየተነከረ የሚጠበስ ማንኛውም ምግብ በጎጂ ንጥረ ነገሮች በTrans Fates የታጨቁ ናቸው፡፡ ይህም በመላው አካላችን ውስጥ የመጉረብረብ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ በዕለታዊ ማዕድዎ ላይ የድንች ጥብስ መጠንዎን ከ1% በታች እንዲያደርጉ የአሜሪካ የልብ ማህበር ይመክራል፡፡
2. ዶናት እና በስኳር የተሞሉ ፓስቴዎች
እነዚህ ምግቦች የተለያዩ አይነት ጎጂ ንጥረ ነገሮችን ይዘዋል፡፡ በአብዛኛው Transe fates በከፍተኛ መጠን ይገኙባቸዋል፡፡ በስኳር የተሞሉም ናቸው፡፡ በፊታችን ላይ መጨማደድና ሽብሽባትን የሚያስከትለው AGE መገኛዎችም ናቸው፡፡
3. ሃት ዶግና ቋሊሟ
የትኛውም በፋብሪካ ፕሮሰስ ተደረገ ሥጋ፣ የአሳማ ሥጋና የመሳሰሉው በቅባት ያበደ ጥብሳ ጥብስ ከጥቅሙ ጉዳቱ እጅግ ያመዘነ ነው፡፡ saturated የተሰኘው ጎጂ የስብ አይነት በከፍተኛ መጠን ይገኝባቸዋል፡፡ የመለብለብና የመቆጥቆጥ ስሜትን የሚያባብሱት ናይትሬትስ የተሰኙ ንጥረ ነገሮች እንዲከማቹም ያደርጋሉ፡፡
4. ቀይ ሥጋም ቢሆን በጥቂቱ ይመገቡ
ጎጂ ስብ በሰውነታችን እንዳይከማች ቀላ ያሉ (ስብ ያልያዙ) ሥጋዎችን እንደንመገብ ይመከራል፡፡ ይህም ቢሆን ለደም ቆዳዎች (arteries) አስደሳች ሁኔታን አይፈጥርም፡፡ የአሜሪካ የስነ ምግብ ማህበር እ.ኤ.አ በ2010 ባወጣው መመሪያ ላይ የተለያዩ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ (ቀይ ሥጋን ያጠቃልላል) ጠቃሚ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ የአሜሪካ የልብ ማህበር በበኩሉ ጎጂ ኮሌስትሮልን የያዙ ምግቦችን እንድናስወገድ ካልተሳካልን ደግሞ ዕለታዊ ፍጆታችንን ከ7% በታች እንዳደርግ ይመክራል፡፡
5. አልኮል
አንዳንድ የአልኮል አይነቶች ለእርስዎ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የበዛ የአልኮል አወሳሰድ በእርግጠንነት ያለ ዕድሜዎ ያረጁ ሊያስመስልዎ ይችላል፡፡ ለሴት በቀን አንድ (አንድ ብርጭቆ ወይን ወይም ቢራ) ሲመከር ለወንዶች የሴቷን እጥፍ ቢወስዱ አይጎዳም፡፡ በቀን በአማካይ አንድ ወይም ሁለት መለኪያ አልኮል ቢጎነጩ ለልብዎ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያ ካለፈ ግን የእርጅና ሂደትዎን ያፋጥናል፤ እንደ ጉበት እና አንዳንድ የካንሰር ህመሞች ያሉ ተያያዥ በሽታዎችንም ያስከትላል፡፡ የማይጠጡ ከሆነ የጤና ባለሙያዎች እንዲጠጡ አይመክሩዎትም፡፡ የሚጠጡ ከሆነ ግን ለዶክተርዎ ከመናገር አይቆጠቡም፡፡ የሚያሳስበዎ የጤና ችግሮች ከእርስዎ የአልኮል አወሳሰድ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሊነግርዎ ይችላል፡፡ ‹‹ከሁሉም በላይ ይላሉ…›› ዶ/ር ሃርላን ‹‹ተገቢውን ማዕድንና ቫይታሚን የያዙ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምግቦች መመገብ የሚፈጠረውን የመጉረብረብ ስሜት ይቀንሳል፡፡ በጥሩ ውስጣዊና ውጫዊ አቋም ላይ እንዲገኙ ያደርጋል፡፡ የሜዲትራኒያን የአበላል ዘዴ የሚሰኘው የአመጋገብ ባህል ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ካንሰር፣ አልዛይመርና የልብ ህመሞችን ያስወግዳል››
ልናዘወትራቸው የሚገቡ ምግቦች
ሃርላን እና ጂያን ኮሊ ጥቅማቸው ከፍተኛ የሆኑትን፣ ወጣት የሚያስመስሉትንና ጤናማ የሚያደርጉትን (super foods) እንድናዘወትር ይመክራሉ፡፡
‹‹ይህ ሲባል ግን የተወሰኑ ምግቦችን መርጣችሁ እነሱ ላይ ማተኮር ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሁኔታ ትልቁን ምስል እንዳትመለከቱት ያደርጋል›› አሳ ወይንም ፍራፍሬዎችን ብቻ ሳይሆን አበባ ጎመን፣ ስኳር ድንች፣ ሳልመን (አሳ)፣ ሽምብራ እና የዶሮ ሥጋን መመገብ ለአጠቃላይ ጤንነት ይጠቅማል›› ይላሉ ዶክተር ሃርላን፡፡
ሁለቱም ኤክስፐርቶች ለጤናችን በጣም ጠቃሚ ነው ያሉትን የሜዲትራንያን የአመጋገብ ዘዴ እንድናዘወትር ይመክራሉ፡፡ የመረጧቸውን አምስት ከማዕዳችን ላይ መጥፋት የሌለባቸው ምግቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ሰላጣ፡- ሰላጣ በሽታ ተከላካይ ቫይታሚኖች ተብለው በሚጠሩት በቫይታሚን ኤ እና ሲ የበለፀጉ ሲሆን የመቆጣትና የመጉረብረብ ስሜትን ይዋጋሉ፡፡ ሌሎች ጥቁር አረንጓዴ ቀለም ያላቸው እንደ አበባ ጎመንና ስፒናች ያሉትን በማዕዳችን ላይ ማካተት ያስፈልጋል፡፡
2. ቲማቲም፡- እንደ ሃብሃብ፣ ወይን፣ ዘይቱን፣ አስፓራገስ፣ ቀይ ጎመን ሁሉ ቲማቲም በበሽታ ተከላካዮች የበለፀገውን Lycopene ያስገኝልናል፡፡
3. ሳልመን፡- እንደ የባህር አሳዎች ቱና እና ሄሪንግ (herring) ሁሉ ሳልመን በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የበለፀገ ነው፡፡ የሰውነት መመረዝን ይከላከላል፡፡
pls Share👇👇👇👇👇👇👇👇
@shegerfitness @shegerfitness
@shegerfitness @shegerfitness
🍃ሠላጣ 🍃ሠላጣ 🍃ሠላጣ 🍃ሠላጣ
🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗🥗
#ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሠዉነት ክብደት ላላቸዉ ሠዎች የሚመከር ሲሆን የደም ዉስጥ ስር መጠንንም ይቀንሳል፡፡
@shegerfitness
#ሠላጣ በዉስጡ የያዘዉ ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለዉ ንጥረ ነገር ደግሞ የሠዉነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
pls ይሄ ነገር ከጠቀማቹ share👇
@shegerfitness @shegerfitness