እንዲህም የሚል አለ
“መውሊድ ለማክበር ሰሂህ ሀዲስ ሳይሆን፣
ሰሂህ ቀልብ ነው የሚያስፈልገው፡፡”
እውነታው ግን ሰሂህ ቀልብ ያለው ሰው ያለ ሰሂህ ሀዲስ (ያለ ቁርዓን ማስረጃ፣ ያለ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና) በልብ ወለድ ተነስቶ አምልኮን አይፈፅምም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትዕዛዝ የሌለበት ስራ የሰራ ስራው ተመላሽ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙትን ነገር መስራት ስራን ማበላሸት ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል
[47:33] ۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَلَا تُبْطِلُوٓا۟ أَعْمَٰلَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ (ያልታዘዛችሁትን በመስራት) ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡
/channel/SadatTextPosts
አሰላሙአለይኩም ኢንሻ አላህ ነገ እሁድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 3:00 ሰኣት "ታኩር ለእናቱ ኮንደም ሲያቀብል ነበርን?" በሚል ርእስ youtube live ይኖራል። አዘጋጅ ወንድም ሳለሐዲን አቡ አሕላም። በዚህ ሊንክ መከታተል ትችላላችሁ።
https://youtube.com/live/hWgu-MwvbeY
አስደሳች ዜና
🎓ታላቅ የቁርአን ሒፍዝ ምርቃት ፕሮግራም
መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዐሪ የቁርአን ሒፍዝ ማእከል በበጋና በክረምት ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን ቅዳሜ ነሀሴ 25/2016 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በደማቅ ፕሮግራም እንደሚያስመርቅ ስናበስረዎ በታላቅ ደስታ ነው ።
በፕሮግራሙም ላይ የተላያዩ መሻዪኾች, ኡስታዞችና የሙሐደራ ግብዣ ይኖራቸዋል ።
በመሆኑም እርሶ የፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል ።
አድራሻ: አጠና ተራ እፎይታ የገቢያ ማእከል ህንዖ አዳራሽ
ማሳሰቢያ: የ አዳራሽ መግቢያ ምንም አይነት ክፍያ ስለሌለው ቦታ ሳይሞላባቹህ ቀድማቹህ እንድትገኙ ሰንል እናሳስባለን .
/channel/Abulabas
/channel/Kurantejwid
የመውሊድ ውድድር
ፈተና አንድ
1) ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስንት ጊዜ ነው መውሊድ በኣል ላይ የተሳተፉት?
___________________
2) የትኛው ከተማ ላይ ነበር መውሊድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሃባዎች የተከበረው?
_____________________________________
3) ሰሃባዎች የትኛውን አይነት የመውሊድ አወጣጥ ነበር ለታቢኢኖች ያስተማሩት?
________________________________________________________
4) ምን አይነት ምግብ ነበር በመውሊድ ወቅት ሲመገቡት የነበረው?
________________________________________________________
5) መውሊድ ላይ በሰሃባዎች ሲዜሙ ከነበሩ ዘፈኖች ውስጥ ዋናዋናዎቹን ጥቀስ
___________________________________
___________________________________
• አስታውሱ ሁሉም መልሶች ከሚከተሉት መሰረታዊ ምንጮች ነው መሆን ያለባቸው፡
1. ከቁርኣን፣
2. ከሀዲስ፣
3. ከሰሃባዎች ንግግር
በደንብ አስባችሁ፣ ጊዜያችሁን ውሰዱና ቁርኣንን ፈትሹ፣ ቡኻሪ ሙስሊም እና ሌሎች የሀዲስ መዛግብትን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
የተተረጎመ
/channel/SadatTextPosts
ለምንድን ነው የኢሳን (አለይሂ ሰላም)፣ የአቡበክር፣ የኡመርን፣ የኡስማንን፣ የአልይን ልደት የማናከብረው?
እነሱ ስሜታቸውን ተከትለው
‹‹የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት የምናከብረው ለሳቸው ያለንን ውዴታ ለመግለፅ ነው፡፡›› ይላሉ
ጥያቄው
ሙስሊም የሆነ ሰው ነብያትን፣ ሰሃባዎችን መውደድ፣ እናት አባቱን መውደድ፣ ኡለማዎችን መውደድ ግዴታው ነው፡፡ ታድያ ከነብያት ውስጥ ለምሳሌ ከ5ቱ የቁርጠኝነት ባለቤት ከሚባሉት ውስጥ የሆነውን ታላቁን ነብይ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) ለሱ ያለንን ውዴታ የምንገልፀው የልደት ቀኑን በማክበር ነውን?
በፍፁም
ሰሃባዎችን እንድንወድ ታዘናል፡፡ ታድያ ለምን የአቡበክር ሲዲቅን፣ የኡመርን፣ የኡስማንን፣ የአልይን ልደት አናከብርም?
መልሱም
ስላልታዘዘ እና በዚህ መንገድ ስላልሆነ ለነሱ ያለንን ውዴታ የምንገልፀው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ከአላህ ቀጥሎ ከነፍሳችን፣ ከልጆቻችንና፣ ከማንም በላይ አስበልጠን መውደድ አለብን፡፡ ለሳቸው ያለንን ውዴታ የምንገልፀው
1) ያዘዙትን ሁሉ አቅም በቻለው መልኩ በመታዘዝ፣
2) የከለከሉትን ሁሉ በመከልከል፣
3) የተናገሩትን ሁሉ እውነት ነው በማለት፣
4) የተዉትን፣ ያላሳዩንን እኛም በመተው፡፡ ምክንያቱም መልካም ሆኖ ያላሳዩን ነገር የለምና፡፡
5) ሰለዋት በማውረድ እና የመሳሰሉትን
እሳቸው በህይወት በነበሩ ግዜ አላህ ዘንድ የተከበረ፣ የተወደደ፣ ቅርብ የተባለው ወንድማቸውን ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ልደት ነሷራዎች ቢያከብሩትም እሳቸው ግን አላከበሩትም፡፡ በጣም የሚወዷት ልጃቸው ፋጢማ (ረድየላሁ አንሃ) ልደቷን አክብረውላት አያውቁም፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዳላቸው ‹‹ወዳንተ የተወረደልህን ተከተል›› እሳቸው ከአላህ የታዘዙትን ብቻ ነው የሚከተሉት፡፡
በሸሪዐችን አቂቃ የተባለ አንድ ሰው ሲወለድ ደስታችንን በግለጫ፣ ጌታችንን ማመስገኛ ወንድ ልጅ ከተወለደ 2 በግ፣ ሴት ልጅ ከተወለደች 1 በግ ይታረዳል፡፡ አበቃ፡፡
ታድያ ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና) ለነዛ ውድ ሰሃባዎች የበቃቸው ዲን ለእኛ አይበቃንምን?
ሱና ላይ እንቁም ከሃቅ በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ የለም፡፡ ከሱና በኋላ ቢድዐ እንጂ ሌላ የለም፡፡
‹‹እኛ መውሊድን የምናከብረው ለነብዩ ያለንን ውዴታ ለመግለፅ ነው፡፡›› የሚሉ ሰዎች የሚከተሉት ምርጦች
-) ሙሃጂሮች፣ አንሷሮች፣ 10ሩ የጀነት ሙሽሮች፣
-) ታቢኢኖች፣ አትባኡ ታቢኢን፣
-) ኢማም አቡ ሃኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊኢ፣ ኢማሙ አሕመድ፣
-) ኢማሙል ቡኻሪ፣ ኢማሙ ሙስሊም፣ ነሳኢ፣ አቡ ዳውድ፣ ትርሚዚ፣ ኢብን ማጃ፣ እነ ሱፍያን አሰውሪ፣ እነ አብደላህ ኢብን ሙባረክ፣ እና ሌሎችም ፈርጦች አይወዷቸውም ነበርን ልትሉን ነው?
ወይንም እንዴት ውዴታቸውን መግለፅ እንደነበረባቸው አልገባቸውም ወይንም አያውቁም ልትሉን ነው?
ይልቁንስ መውሊድን የጀመሩት የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ የሰሃባዎችና፣ የአማኞች ጠላቶች የሆኑት ሺዐዎች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ይበቃናል ሸር ለመሆኑ፡፡
አላህ ሃቁን ይምራን፣ በሃቅም ላይ ያፅናን፡፡
/channel/SadatTextPosts
👆አሰላሙአለይኩም የአላህ ባሪያዎች። አካውንቴ አልተጠለፈም አብሽሩ። ይህ ወጣት የገዛ እናቱን በዚህ መልክ በአደባባይ ስላሰደበ፣ ለሌሎች መመከሪያ ይሆን ዘንድ ከቁርአን እና ሀዲስ ኢስላም ምን እንደሚል በእርጋታ የነገው ፕሮግራም ላይ ስለሚገለፅ እንከታተል። ለታዋቂነት ሲባል በመከራ ያሳዳጉን እናት እና አባቶቾችንን ማሰደብ ነውር ነው።
Читать полностью…👆አሰላሙአለይኩም ወንድም እና እህቶች ከዚህ ቪድዬ በፊት በስህተት ዘፈን ያለበትን የዚህን ኺድዬ ለቅቂ ነበር አፉ በሉኝ። ይሄኛው ነው መልስ የተሰጠበት
Читать полностью…ስለሚወዷቸው ይዋሹባቸዋልi
~
ሙሐመድ አወል በመንዙማው አማካኝነት በከፍተኛ መጠን ሺርክን አስፋፍቷል። "የኢትዮጵያ ዑለማዎች ታሪክ" የሚለው መንዙማው በሺርክ ስንኞች የታጨቀ ነው። ባጠመማቸው ሁሉ እንዳይጠየቅ ሞት ሳይቀድመው በፊት ተውበት ቢያደርግ ራሱ ነው የሚጠቀመው። ሙሐመድ አወል "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" እያለ የተለመደውን የአሽዐሪያ ቅዠታዊ ፍልስፍና የሚያስተጋባበትም አለው። በተያያዘው ድምፅ ላይ ደግሞ በውዱ ነብያችን ﷺ ላይ ባደባባይ ሲቀጥፍባቸው ይታያል። ቃል በቃል እንዲህ ነው ያለው፦
"ሐዲሥ አደለም እምነግራችሁ። የዑለማዎች አነጋገር ነው። 'መውሊድ ሰምቶ በጆሮው፤ መውሊድ ሰምቶ የቀረ አይወደኝም' ብለዋል ነብያችን። ተጠርቶ ደግሞ የቀረ ይጠላኛል' አሉ።"
በቅድሚያ በእሱና መሰል ሰዎች ለምትሽወዱ ወገኖቻችን! ወላሂ በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ላይ ምላሽ የምንሰጠው ብሽሽቅ እያማረን አይደለም። ይልቁንም በእምነታችሁ ጉዳይ የማንም መጫወቻ ከመሆን እንድትወጡ ለማንቃት ነው። እነዚህ ሰዎች በኢስላም ስም ኢስላምን የሚያጠለሹ፣ ነብዩን ﷺ በመውደድ ስም በሳቸው ላይ የሚዋሹ ሰዎች ናቸው።
1ኛ፦ ሰውዬው "ሐዲሥ አደለም እምነግራችሁ" ካለ በኋላ "መውሊድ ሰምቶ በጆሮው፤ መውሊድ ሰምቶ የቀረ አይወደኝም ብለዋል ነብያችን" ይላል። ሐዲሥ ምን እንደሆነም አያውቅም። ስለ ሐዲሥ ያለው ግንዛቤ በዚህ መጠን ነው። አያሳፍርም? ወይስ ሌሎችን ለመወንጀል ያለው ጉጉት ነው እስከሚዋሽ ያደረሰው? ሐዲሥ ካልሆነ ለምንድን ነው "... ብለዋል ነብያችን" የምትለው? ያላሉትን በስማቸው ትቀጥፍባቸዋለህ? ልብ በሉ! ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
لا تكذبوا علي فإنه من كذب علي فليلج النار
"በኔ ላይ አትዋሹ። በኔ ላይ የዋሸ ሰው እሳት ይግባ!" [አልቡኻሪይ፡ 106]
በሌላ ሐዲሣቸውም እንዲህ ብለዋል፦
إن من أعظم الفِرَى أن ... يقول على رسول الله (ﷺ) ما لم يَقُلْ
"ከከባባድ ቅጥፈቶች ውስጥ የሆነው አንድ ሰው በአላህ መልእክተኛ ላይ ያላሉትን ማለቱ ነው።" [አልቡኻሪይ፡ 3509]
2ኛ፦ ምናልባት " 'ሐዲሥ አደለም እምነግራችሁ። የዑለማዎች አነጋገር ነው' ብሏል። ከራሱ አልተናገረምኮ" የሚል ካለ ይሄ ከተጠያቂነት ነፃ አያደርገውም። ሐዲሥ እንዳልሆነ እያወቀ የቀጣፊዎችን ንግግር በነብያችን ﷺ ስም ማውራት በቂ ጥፋት ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
مَنْ حَدَّثَ عَنِّي بِحَدِيثٍ يُرَى أَنَّهُ كَذِبٌ، فَهُوَ أَحَدُ الْكَاذِبِينَ
"ውሸት እንደሆነ የሚታሰብን ወሬ በኔ ላይ ያወራ ሰው እርሱ ራሱ ከውሸታሞቹ አንዱ ነው።" [ሙስሊም፡ ገፅ፡ 7]
ልብ በሉ! ውሸት ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። ውሸት አፀያፊ ወንጀል ነው። ውሸትን ክፉኛ በሚኮንኑት ነብይ ስም ሲፈፀም ደግሞ ይበልጥ የከፋ ይሆናል። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
إن كذبا علي ليس ككذب على أحد، من كذب علي متعمدا فليتبوأ مقعده من النار
"በኔ ላይ መዋሸት በማንም ላይ እንደመዋሸት አይደለም። በኔ ላይ እያወቀ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ።" [አልቡኻሪይ፡ 1291]
3ኛ፦ ይህንን ከንቱ ንግግር "የዑለማዎች አነጋገር ነው" የሚለውም ሌላ ቅጥፈት ነው። ይሄ የዑለማእ ሳይሆን በዲን ስም የሚነግዱ ቀጣፊዎች ንግግር ነው። ዑለማእ በሌላ ሰው ላይ ያውም በነብዩ ﷺ ላይ አይዋሽም። ኢማሙ አሕመድ በነብዩ ላይ የሚዋሽን ሰው ፋሲቅ ነው፣ አመፀኛ! ምስክርነቱም ዘገባዎቹም ተቀባይነት የለውም። ቢመለስና ሁኔታው ቢስተካከል እንኳ! በሱ ላይ ለማክበድ ሲባል! አብዛኞቹ በነብዩ ﷺ የሚዋሹ ሰዎች ኢስላምን ማጥፋት የሚሹ መና. .ፍቃን ናቸው ይላሉ።
4ኛ:- " 'መውሊድ ሰምቶ የቀረ አይወደኝም' ብለዋል" የሚለውን አስተውሉት። የዚህ ቅጥፈት አላማው ሁለት ነው። አንዱ የሸሪዐ እውቀት የሌላቸውን ሰዎች አስፈራርቶ የመውሊድ አጫፋሪ ማድረግ ነው። ሁለተኛው አላማ መውሊድ የሚቃወሙ ሰዎችን በጠላትነት ለመፈረጅ ነው። በነዚህ አካላት የምትሸወዱ ወገኖቼ ሆይ! ወላሂ በነዚህ ለራሳቸው እንጀራ ሲሉ እናንተን እሳት ላይ በሚማግዱ ሴረኞች ተንኮል እንዳትሸወዱ። ፈፅሞ ለነዚህ በነብዩ ﷺ ስም እንኳ ከመዋሸት ለማይመለሱ አሳሳቾች እንዳትሟገቱ። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّاۤ أَنزَلۡنَاۤ إِلَیۡكَ ٱلۡكِتَـٰبَ بِٱلۡحَقِّ لِتَحۡكُمَ بَیۡنَ ٱلنَّاسِ بِمَاۤ أَرَىٰكَ ٱللَّهُۚ وَلَا تَكُن لِّلۡخَاۤىِٕنِینَ خَصِیمࣰا }
"እኛ በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን። ለሸፍጠኞችም ተከራካሪ አትሁን።" [አኒሳእ፡ 105]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
/channel/IbnuMunewor