በቻናሌ ውስጥ በማስተላልፈው ፕሮግራም አስተያየት ከአላችሁ ይህንን @Richyanyena ሊንክ በመጫን በግል አናግሩኝ!!
ህይወት የሰጠችን ውስብስብ ጎዳና እንደዚህ ነው እጣው።
ቆሽሸህ ተንቀህ ነው ስኬት የሚመጣው።
አጥንትን ሚያደቅ ቅስም ሚሰባብር ሰው ክፉ ነው ቃሉ።
ግን ማይፀዳ አይደለም የቆሸሸ ሁሉም።
ያሻቸውን ያውሩ በፍፁም አትልፋ ከሰው አፍ ለመውጣት ኋላ ያስቀርሃል ተፀያፊ ማጣት።👌
ሁሉም ቢክድህ ሁሉም እውነትን ለመደበቅ ቢንቀሳቀስ ሁሉም እንደሌለህ ቢቆጥርህ ብቻህን ደካማ ነህ።አሏህን ይዘህ ግን ጠንካራ ነህ።ወደ አሏህ ስትጠጋ ከእሱ በሆነ ሀይል ይሰጥሃል አሏህ ልብህ ያፀናዋል።ጉልበት ይሆንሃል ውስጥህ ልብህ እንዳይሰበር ይጠግንሃል።
Читать полностью…ተጠንቀቁ
የትም ቦታ ላይ ከምታውቁት ሰውም ይሁን ከማታውቁት ሰው ቢላክ ይህ ሊንክ እንዳትከፍቱት አካውንታቹ ላይ ያለው ብር ሃክ አድርገው ሙጭጭ አድርገው ነው ሚያጥቡላችሁ።
ወደ አካውንታችን ገቢ ሚያደርግ ሊንክ ከተገኘ ግን ላኩልን አስተግፊሩላህ😂
ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው‼️
በሐዲሥ የመጡ ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው ሁነት፣ ቀንና ወቕቶች፦
①) ከውዱእ በኋላ፣
②) ሱጁድ ላይ፣
③) በእኩለ-ለሊት፣
④) የዓረፋ ቀን ላይ፣
⑤) ዝናብ ሲዘንብ፣
⑥) ፆመኛ ሲያፈጥር፣
⑦) ከፈርድ ሶላቶች በኋላ፣
⑧) ለሌሎች ዱዓ ስታደርጉ፣
⑨) የታመሙትን ሲትጎበኙ፣
⑩) በዩኑስ ዱዓ አላህን የለመነ፣
⑪) ከሓጅ ወይም ከዑምራ በኴላ፣
⑫) የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት፣
⑬) በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር፣
⑭) በጁሙዓ ቀን ከዓስር ሶላት በኋላ፣
⑮) በአዛንና በኢቃም መካከል ባለው ጊዜ።
ዱአ ላይ ከማይዘናጉትና ዱአቸውን በማንኛውም ሰዓት ከሚቀበላቸው ባሮቹ መካከል ያድርገን።
የምንነዳው መኪና የምንኖርበት ቤት የምንለብሰው ልብስ በጠቅላላ በመጨረሻዎቹ የህይወታችን ደቂቃ ላይ ትርጉም አልባ ናቸው።
ከዘላለም አንፃር ህይወታችን ስናየው እጅግ በጣም ኢምንት ነው። እቺ ኢምንት የሆነችው ህይወት እቺ ማታ ታይታ ጠዋት ለምትጠፋው ህይወት አለባበሳችን አመጋገባችን የምንኖረው ኑሮ ስኬታችን ዲፋይን ያደርገዋል ብዬ አላምንም።እውነተኛ ስኬት የምትረጋገጠው መጨረሻዎቹ የህይወታችን ደቂቃ ላይ ነው።በሩጫው መስመር ላይ አሸናፊው የሚረጋገጠው በመጨረሻዎቹ ደቂቃ ብቻ ነው ሚሆነው።ምናልባት ሩጫው ሲጀመር ብዙዎች ፈጥነው ሊሮጡ ይችላሉ ። ምናልባትበሩጫው መስመር ላይ ብዙዎች ትጥቃቸው እጅግ በጣም ያማረ ሊሆን ይችላል። አሸናፊው ግን ሚረጋገጠው በመጨረሻ በመጨረሻ ሰዐት ላይ ብቻ ነው። እውነተኛ ስኬትም ምትረጋገጠው በመጨረሻዎቹ የህይወታችን ደቂቃዎች ላይ ብቻ ነው። እያንዳንዱ ሰው ይህች ምድር ለቆ ከመሄዱ በፊት ቢያን ቢያንስ ለእያንዳንዱ ሰው አሏህ ሶስት ሶስት ደቂቃ ህይወታችን ወደ ኋላ መለስ ብለን እንድናይበት እንደሚሰጠን ይሰማኛል። በእነዚህ ሶስት ደቂቃዎች ውስጥ ታድያ ትናንትናችን ስንመለከተው
የነዳነው መኪና
የገዛነው ቤት
የለበስነው ልብሶች እና
የበላናቸው ምግቦች በጠቅላላ ትርጉም አልባ መሆናቸው እንረዳለን።😭
በግል መጥታችሁ እባክሽ እህቴ አዘገጃጀቱ ንገሪን ያላችሁኝ በሙሉ አዘገጃጀቱ መጀመሪያ ይቆላል ሁሉም ነገሩ እንደ ቡና ነው ከዛም በሲኒ ወይም በኩባያ መጠጣት።
Читать полностью…አንድ የሀብታም ልጅ እናቱ ከድሀ ጎረቤቶቻቸው አንድ ስኒ ጨው እንዲሰጧት ስትጠይቅ ሰማና ቤታቸው ከተመለሱ በኃላ.....
ልጁ፡- "እንዴ እማየ! ትላንት ለአንድ ወር የሚበቃ ጨው ገዝተሽ እያለ እንዴት እነዚያ ምስኪን ጎረቤቶቻችንን ጨው ትጠይቂያቸዋለሽ?" አላት።
እናቱም፡- "አየህ ልጀ! እነሱ ድሆች ስለሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሁሌም ከኛ ይጠይቃሉ። አንድ ስኒ ጨው የጠየኳቸው ጨው ርካሽ ስለሆነ እንደማያጡና እንደማይጎዳቸው ስለማውቅና እኔም ከነሱ የምፈለገው ነገር እንዳለ ተሰምቷቸው ከኛ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሳይሸማቀቁ ዘና ብለው እንዲጠይቁን ለማስቻል ነው!" አለችው።
ፈጣሪ እንዲህ ያለውን አስተዋይ አእምሮና ደግ ልብ ይስጠን!
ይህን ዱዓ እናብዛ
“አልላሁመ ኢንነከ ዐፉዉን ቱሒቡል ዐፍው ፈዕፉ ዐንኒ”
'አላህ ሆይ አንተ ይቅርባይ ነህ፣ ይቅር ማለትንም ትወዳለህ፣ ይቅር በለን!
የተፈጥሮ ኡደትን በማደናቀፍህ አትራፊ ልትሆን አትችልም፡፡ ቢበዛ እንቁላሉን ብታገኝ ነው፡፡ ረጋ ብለህ ካስተዋልክ ግን እንቁላል የምትፈለፍልልህን “ዶሮ” ታገኛለህ፡፡ ምርጫው ያንተ ነው፡፡አሏህ ትዕግስቱን ይስጠን!
Читать полностью…*ወደ አላህ እንሽሽ*
ሰውን ስንፈራ ከሰው እንሸሻለን፡፡ አላህን ስንፈራ ግን ወደ አላህ እንሸሻለን፡፡
የፈጠረን ጌታ አላህ ሁሌም መሸሻችን መጠጊያችን ነው፡፡
አጥፍተን ማንኳኳት የማንፈራው ቤት የሱ ብቻ ነው፡፡
አላህን ያዙ፣
አላህን ተማመኑ፣
ወደ አላህ ሽሹ፡፡
ከሚያሳምማችሁ ነገር ሁሉ ወደ አላህ ሽሹ፡፡
ከሚያስፈራችሁ ነገር ሁሉ ወደ አላህ ሸሹ፡፡
ሸክም ሲከብዳችሁ፣
ሀሳብ ሲጫናችሁ፣
ሲጨንቃችሁ፣
ሲሰለቻችሁ፣
ብቸኝነት ሲሰማችሁ፣
ሁሉ ነገር ሲያስጠላችሁ፣
ተስፋ መቁረጥ ሲያገኛችሁ፡፡
ወደ አላህ ሽሹ።
ከዱንያ ፈተና፣
ከሕይወት ሞት መከራ፣
ከመጥፎ ውሎና አዳር፣
ወደ አላህ ሽሹ፡፡
ከብቸኝነት፣
ከድካም፣
ከስንፍና፣
ከመጥፎ ሀሳብ፣
ከፍርሃት
ወደ አላህ ሽሹ፡፡
በተለይ ደግሞ
ከፈተና በኋላ፣
ከውድቀት በኋላ፣
ከውርደት በኋላ፣
ከኃጢኣት በኋላ፣
ከሰው ጠብቃችሁ ካጣችሁ በኋላ… ሁሉ ወደ አላህ ሽሹ፡፡
ጌታዬ፣
ጥላዬ፣
ከለላዬ፣
መከታዬ፣
ሰታሪዬ፣
ጥፋት አበዛህ ብለህ የማትመልስ፣
ለመምጣት ዘገየህ ብለህ የማታባርር ፣
ሁሌም የማታሳፍር አንተ ብቻ ነህ፡፡
ደህና ባትሆን እንኳን ደህና ነኝ በላቸው።
t.me/richyaneyena
የእናንተ ጊዜ እስኪመጣ ቀረት ማለት ልመዱ!
t.me/richyaneyena
እኔ እንደ ራሴ ትልቅ ንግግር ምናገረው አንድ ሰው ስላሰበ ስለሄደ አይከብርም። ማንኛውም ሰው እንደ አስተሳሰቡ አይከብርም።እንደዛማ ቢሆን ኖሮ ሁሉም ያም ያም ይከብር ነበረ።አይደለም እንሳሳታለን አሏህ ሲደግፈን ብቻ ነው ምንከብረው።ያለነው ሳንዋደድ ለሞተው እንናደዳለን።ብዙ ግዜ ተናጋሪዎች እብድ ቢሆኑም አዳማጮች አቅለኛ መሆን ግድ ይላል።ብር ሊመጣ ይችላል የሰው ህይወት ግን ላይመጣ ይሄዳል።ምንም ነገር ቢገጥመን በንዴት ጊዜ እራስ እንደመቆጣጠር ጥበብ በዚህ ምድር ላይ አልተሰጠንም።በጥቅሉ ስራችን ይወቀን ካልሆነ ኑሮዋችን እራሱ በቁማችን ሞታችን ነው።.
ሪች ነኝ✍
ትልቁን ትምህርት የምታገኘው ከትልቁ ስህተት ነው። የማትረሳው ደስታ የምታገኘው ከከባድ ጭንቀት በኋላ ነው።ሁሉም ነገር የሚሆነው በምክንያት ነው የገጠመኝ ነገር ምን ሊያስተምረኝ ነው በል።ምክንያቱም የአንድ ነገር መጨረሻ የሌላ ነገር መጀመሪያ ነው።
Читать полностью…ስማኝ ስማኝ ሳቂታ ሰው ስታይ
ምን አስደስቶት ነው የሚል ሃሳብ ካለህ
ይቅር አትጠይቀው
በመሳቅ ይሆናል ሀዘን ሚደብቀው።
አንድ ጠበቃ የውሃ ጉድጓዱን ለመምህር ሸጠለት። ከሁለት ቀን በኋላ ጠበቃው ወደ መምህሩ መጥቶ እንዲህ አለው፡ "ጌታዬ፣ ጉድጓዱን ሸጥኩልህ እንጂ በውስጡ ያለውን ውሃ አልሸጥኩልህም! ውሃውን መጠቀም ከፈለግክ ተጨማሪ መክፈል አለብህ።"
መምህሩ ፈገግ አለና እንዲህ ሲል መለሰ፡ "አዎ፣ እኔም ወደ አንተ ልመጣ ነበር። ልልህ የነበረው ውሃህን ከእኔ ጉድጓድ ውስጥ እንድታወጣ ነው፣ አለበለዚያ ከነገ ጀምሮ ኪራይ መክፈል ትጀምራለህ።"
ይህን ሲሰማ ጠበቃው ተደናግጦ "ኦ! ዝም ብዬ እየቀለድኩ ነበር!" አለዉ።
መምህሩ እየሳቀ "እንደ አንተ ያሉ ሰዎች እኮ ከእኛ ዘንድ ተምረው ነው ጠበቃ የሚሆኑት!" አለው። ይባላል።😜
የተሻለ ቦታ ላይ መቀመጥ ማለት የተሻለ ማሰብ ነው ማለት ኣይደለም።
ይነጋል ብሎ አለማሰብ እንጂ ጨለማ አይገድልም ።
ተስፋ ከታጣ ቀን እራሱ ቀን ሆኖ አይውልም። ተስፋ አትጣ
ቴምር አላልኩም የቴምር ፍሬ ነው ያልኩት
የቴምር ፍሬ ብዙ ጠቀሜታዎች!!
የቴምር ፍሬ 10 ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው
1. የደም ማነስ ካለብዎት በሚገባ ያድንዎታል።
2. ለአይን ጤንነት እና አይንን ከመታወር ይታደጋል።
3. ለስንፈተ ወሲብ ፍቱን ነው።
4. የሆድ ድርቀትን ይከላከላል/ይፈውሳል፤ እንዲሁም ተቅማጥን ይከላከላል።
5. ክብደትን ለመጨመር ይረዳል።
6. ጤናማ ልብ እንዲኖረን ያደርጋል።
7. ጉልበት/ኃይል ይሰጠናል ወይም እንዲጨምር ያደርጋል።
8. ጤናማ የሆነ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ያደርጋል።
9. ጥርሳችን ጤናማ እና ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል።
10. ለእርጉዝ ሴቶች በጣም ጠቃሚ ነው።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.andi.alquran.en
Читать полностью…የአንድ ሰው ጥንካሬ ሦስት ቦታዎች ላይ ይንፀባረቃል ይላሉ ኢማሙ ሻፊዒ
* ሰዎች ሀብታም ነው ብለው እስኪያስቡት ድረስ ድህነቱን ሲደብቅ፣
* ሰዎች የተስማማ እስኪመስላቸው ድረስ ንዴቱን ሲያፍን፣
* ሰዎች ድሎት ዉስጥ ነው ብለው እስኪያስቡ ድረስ ችግሩን ሲቋቋም።
ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል
"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም"
ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ
"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው
አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"
ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም" 50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው
ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት
ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!
ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ
"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"
በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት😍
❤️መልካምነት ለራስ ነው❤️ ከፌስቡክ መንደር
•=> ጠንካራ ሁን!.
®፧ በህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ልፍስፍስ ከሆነ ሰው "ይልቅ ፥በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ቆራጥ የሆነ ሰው በንቃት ውስጥ ነው ።
(ዐሊይ ኢብኑ አቢጧሊብ)
®፧ ሰዎች የአንተን ውስጣዊ ማንነትህን ባለማወቃቸው ከውጫዊ ማንነትህ በመነሳት የሚሰጡት ፤ምስክርነት አንተ ስለራስህ ያለህን ትክክለኛ ዕውቀት እንዳይሸፍንብህ ።"
(ኻሊድ-ኢብኑ ሰፍዋን)
®፧ ውሳኔ ሳትሰጥ አስተንትን ፥ወረራ
ሳትፈፅም ተዘጋጅ ፥ሳትጀምር አማክር ።
(ኢማሙ - አሻፊይ)
@richyaneyena
ከአዕምሮ የበለጠ ሃብት፣
ከመሃይምነት የበለጠ ድህነት፣
ከመልካም ስብዕና የበለጠ ጣፋጭ ኑሮ የለም።
(ዐሊይ ኢብን አቡ ጧሊብ)
የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ሚስ ሊያደርጓቸው የሚችሉ 5 ምግቦች
ሙዝ
ዘቢብ
ዱባ
ቲማቲም
አቦካዶ
እነዚህ ምግቦች ከፍተኛ ፖታሽየም ስላላቸው የደም ግፊት ለማስተካከል ሚናቸው ከፍተኛ ነው።
በነገራችን ላይ ግፊት ያለባቸው በቀን ከ2 ሲኒ ☕ቡና በላይ የሚጠጡ ሰዎች ለሞት ተጋላጭነታቸው ይጨምራል የሚል ጥናት በቅርብ ዲሴንበር ላይ ወጥቶዋል ስለዚህ ወይም በጣም ቀንሱ ወይም ደግሞ ቡና☕አቁሙ
ሰው ሁሉ ሚወደው ጅልን እንጂ ባለ ራዕይ አይደለም።
t.me/richyaneyena