richyaneyena | Неотсортированное

Telegram-канал richyaneyena - ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

1510

በቻናሌ ውስጥ በማስተላልፈው ፕሮግራም አስተያየት ከአላችሁ ይህንን @Richyanyena ሊንክ በመጫን በግል አናግሩኝ!!

Подписаться на канал

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሰው አያልቅስብህ።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አዎ አንቺ ጀግና ሴት ነሽ።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

እንዳትሰሚያቸው።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሩዝ ለፊት ጥራት

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ሄሊኮፕተር በመጠቀም ጥረት እየተደረገ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
***

በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር እሳት አደጋ እና ስጋት መከላከል እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል ብለዋል።

አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ባለው ጥረት የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ሄሊኮፕተር ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት ሁሉ ጥረታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አሳስባለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው።

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አንዷ ሁለት ቂጣ አቀረበችና ለሼኽየው እነሼኽ የጀመዓ አምዋት ሰደቃ አላለችም :-D ሼኽየው ደሞ የሐብታም ቤት ነው ብለው ደረሶቻቸውን አስከትለው ነበር የሄዱት ብልጭ አለባቸውና በቁራሽ ቂጣ ነው የጀመዓ አምዋቶችሽን ሰደቃ የምታወጭው በይ አሁን ወይ አምዋቶችሽን ቀንሽ ካልሆነ ደህና ነገር አቅርቢ አሏት አሉ 😊

ምን ለማለት ፈልጌ ነው እንግዳ ሲገባ እናንተን ብሎ ሲመጣ በአለ ነገር ደስ አስደርጋችሁ ሸኙ!

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

➩ ነቢዩ (ﷺ)እንዲ ብለዋል።
“በዚያ ከአርሹ ጥላ በስተቀር ምንም ጥላ በሌለበት ቀን (የፍርዱ ቀን)፤ አላህ ሰባት ሰዎችን በአርሽ ጥላ ስር ያኖራቸዋል።እነሱም፡-

➊ ፍትሃዊ መሪን፣

➋ አላህን በመገዛት ወጣትነቱን ያሳለፈ፣

➌ ልቡ ከመስጅድ ጋር የተቆራኘን ሰው፣

➍ ለአላህ ብቻ ብለው በአላህ መንገድ ላይ የተዋደዱንና በርሱም መንገድ ላይ የተለያዩ (ሲለያይም ለአላህ ብለው)፣

➎ አንዲት ቆንጆ ሴት ራሷን ለዝሙት አዘጋጅታለት ‘አላህን እፈራለሁ’ በማለት እምቢ ያለች፣

➏ በድብቅ ምጽዋት የሚሠጥ ሰው፣

➐ ብቻውን ሆኖ አላህን ሲያስታውስ አላህን ፈርቶ አይኖቹ በእንባ የሚሞላና ጉንጮቹ የሚርሱ ሰው”

(አል-ቡኻሪ ዘግበውታል 

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ውጭ ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ ምትል አሽቃባጭ!

ድሃ ወንድ አልፈልግም ትላለች"
ሜካፑን ብትታጠብ እኮ ራሷ ወንድ ናት..😒

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ልባም ሴት!

በስኬት መንገድ ላይ የምትገኝ ሴት ከመከራዋ ጥንካሬ ታተርፋለች።
በፈገግታዋ ቀኗን ታሳምራለች።
ከችግርዋ በላይ በችግር ፈቺነትዋ ታምናለች።
የሴትነትዋ ጥበብ በመጠቀም ቤትዋ ታሳምራለች።
በጊዛዊ ደስታ ልቧ አይማረክም።
በወንዶች አጉል ማታለያ ቃላቶች አትሸወድም።
ለነገሮች አትቸኩልም በማስተዋል ትራመዳለች።
ያሰበችው እንኳን ባይሳካ ተስፋ አትቆርጥም።
ይህች ሴት ልባም ሴት መሆኗ አትርሳ።

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

መረጃና ጥቆማ
ውጭ ሃገር በተለይም አረብ ሃገር ሆናችሁ በተለይም በንግድ ባንክ ብር አስቀምጣችሁ አካውንታችሁን ሳታንቀሳቅሱ ቢያስን ሁለት አመት ያለፋችሁ እህቶችና ወንድሞች …

ያስቀመጣችሁት ገንዘብ መኖር አለመኖሩን ቸክ አስደርጉ …ሳይንቀሳቀሱ ብዙ ግዜ የቆዩ አካውንቶችን የሚበረብሩና ገንዘቡን ወደ ራሳቸው አዛውረው የሚዘርፉ የባንክ ሰራተኞች እየተበራከቱ መጥተዋል …በዚህ መንገድ አመታት ስደት ላይ የለፉበትን ገንዘብ የተዘረፉና ችግር ላይ የወደቁ በርካቶች ስለመሆናቸው እየተሰማ ነው

t.me/richyaneyena
     መረጃና ጥቆማውን ለሌሎችም ሼር አድርጉት

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የረበና ሰላም በእነዛ ከአላቸው እያካፈሉ ድሆች በሚያስደስቱት ከፊታቸው ፈገግታ በማይጠፋ ሰዎች ላይ ይስፈን! 👏

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሰበር ዜና
አሁን በኢትዮ ሰአት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8 ሰአት ከ40 አካባቢ …የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለድጋሜ የፕሬዝደንትነት ምርጫ ውድድር ቅስቀሳ ላይ እያለ የግድያ ሙከራ ተፈጸመበት …ትራምፕ ተከታታይ ጥይት የተተኮሰበት ቢሆንም ጆሮውና ጉንጩ ላይ በጨረፍታ ከመመታቱ ውጭ የከፋ ጉዳይ እንዳላጋጠመው እየተነገረ ነው

ተኩስ የከፈተው ግልሰብና አንድ ሌላ የስብሰባው ታዳሚ ህይወታቸው ማለፉም ተጨምሮ ታውቋል

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

መስመያቸው ጥጥ እኮ ነው።
t.me/richyaneyena

የደበቡ አፍሪካ ሌባ ጉድ እዩ 😄😄

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የአቲካ ታሪክ ተከታትላችሁ አንብባችሁ የጨረሳችሁ ጥሩ ትምህርት እንደቀሰማችሁ ተስፋ አደርጋለው።

ስለ መጅኑን ለይላ(ቀይስ) የፍቅር ታሪክ ማንበብ ምትፈልጉ 👍ላይክ የማትፈልጉ 👎ደስላይክ አድርጉ

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

እችላለሁ ብለው ካመኑ ፈጣሪን ታምኖ የማይቻልና የማይደረስበት የአላማ ጥግ አይኖርም !!

ሙሉ አካል ይዘው በትንሽ እንቅፋት ተስፋ ቆረጥን ብለው ራሳቸውን ለሚያጠፉ ወጣቶች ይህ ሰው መመከሪያ ነው …ማሻ አሏህ !!

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የአረብ ሀገር ልምድ ያለሽ አረብኛ በደንብ መናገር የምትችዪ እና ቀልጣፋ የሆንሽ አጠቃላይ (እዛው መኖር) የምትችዪ ታማኝ እና ተያዥ ማምጣት ምትችዪ ካለሽ 1 ሰራተኛ ይፈለጋል። ስራ ቦታው ጦርሃይሎች ሲሆን ድርጅቱ የሲዮሲ ተማሪ ማሰልጠኛ ተቋም ነው። በግል አናግሪኝ።

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

በትናንቱ ስህተት ዛሬዋ አትወቅስም።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

እናታችን እንዲህ እያሉ
ይመክሩናል ተመከሩ!

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

በእርግጥም መረዳዳቱ መልካም ነው።

ነገር ግን ጉራጌ ምን ብለው ይተርታሉ በእንቸት ዳፋ እንቸት ጠፋም ይላሉ። ምን ማለት ፈልጌ ነው ይህ ሙሲባ እራሳችን ምንፈትሽበት ነው የሰው ልጅ መጠኑ ይብዛ ይነስ የሙሲባው አይነት ይለያይ እንጂ ሙሲባ (አደጋ) የማይደርስበት ሰው የለም። ሚመጣው አደጋ በወንጀላችን በምንሰራው መጥፎ ሰራ ፈጣሪ ሲተሳሰበን ነው።ነገር ግን በአንድ ሰው ወንጀል አካባቢው ያለ ማህበረሰብ አብሮ ተጠቂ ይሆናል። በአንድ ሰው መልካም ስራ ደግሞ አካባቢው ላይ ያለው ማህበረሰብ ከአደጋ ይድናል። ፈጣሪ መልካም ሰርተው በእነሱ ሰበብ ሰዎች ሚድኑበት መልካም ስራ ያሰራን።
የሰራተኛ ላብ ላቡን ሳይደርቅ ክፈሉ!
ስትሸጡ ሚዛን አታጓድሉ!
በፎርጂድ እቃ በውሸት የፈጣሪ ቃል እጠራችሁ አትሽጡ!
በመልካሙ ነገር ባዕድ ነገር እየጨመራችሁ አትሽጡ!
ባበደራችሁት ገንዘብ ወለድ አትቀበሉ!
በሰራችሁት ስራ በገንዘባችሁ ምፅዋት ስጡ!
እናት አባቶቻችሁ በመካደም ከእርግማን ራቁ!
በስራ ባልደረቦቻችሁ አትመቀኙ አትቅኑ!
ወላጅ አልባ የቲሞች ተንከባከቡ!
የፈጣሪ ትዕዛዝ በአግባቡ ተግብሩ!
ኢንሻ አሏህ መጥፎ ነገር አይደርስባችሁም።መጥፎ ነገር ከደረሰባችሁም ፈጣሪ ስለሚወዳችሁ ነው

ሪች✍

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ከውጭ በተለይም ከአረብ ሃገር ወደ ኢትዮ የምትገቡ ወገኖች በተለይ እህቶች አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ላይ እባካችሁ ጥንቃቄ አድርጉ …ደጋግመን እያሳወቅን ነው ግን ብዙዎቻችሁ አትሰሙም ስትነገሩ

የራሳችሁ የምታውቁት ሰው ቤተሰብ ካልሆነ ማንንም ሰው አትቅረቡ ልሸኛችሁ ቢላችሁ አምናችሁ መኪና ላይ አትግቡ

አሁን ላይ ደግሞ አረብኛ ተናጋሪ ሴቶችን አሰማርተው ነው እየዘረፉ ያሉት ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ አራት እህቶች ሙሉ ሻንጣና ንብረታቸውን በዚህ መንገድ ተዘርፈዋል

አረብኛ ስለተናገሩ ብቻ አትመኑ…ተናግረናል

መል ዕክቱን ለሌሎችም ሼር በማድረግ አስተላልፉ በጎነት ለራስ ነው🙏

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ከገበያ የተሰረቀ አህያ በባለቤቱ በር ሲያልፍ ጊቢ ውስጥ በመግባት አልወጣም በማለቱ አህያውን የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ከገበያ ውስጥ ከታሰረበት የተሰረቀ አህያ  ከባለቤቱ በር ሲያልፍ ከጊቢው በመግባት ተመልሶ አልወጣም በማለቱ የአህያው ሰራቂ በቁጥጥር ስር ውሎ በእስራት መቀጣቱ የባሌ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

በባሌ ዞን በሀረና ቡሉቅ ወረዳ መልከሀራባ በተባለ አካባቢ ከገበያ ውስጥ የተሰረቀው አህያ በባለቤቶቹ ጊቢ ሲያልፍ ተመልሶ በመግባት አልወጣም በማለቱ የአህያው ሰራቂ በቁጥጥር ስር ውሎ በእስራት መቀጣቱን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

የሀረና ቡልቅ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ጉዮ ጭቁሩ እንደገለፁት ተከሳሽ አሚን ሀሰን ሁሰኔ የተባለው ግለሰብ ከገበያ ውስጥ ታስሮ የነበረ የአቶ አብዱል  ሁሴን አህያ ከታሰረበት በመውሰድ ወደ መኖሪያ አካባቢው ይዞት በመሄድ ለሳምንታት እሱ ዘንድ እንዳስቀመጠው ገልፀዋል።

ከሳምንታት ቆይታ በኋላም ተከሳሽ ከገበያ ፈቶ የወሰደውን አህያ በመንዳት አንጋቱ የተባለ ገበያ ለመሸጥ እየነዳ እያለ ከገበያ የተወሰደው አህያም የአቶ አብዱላሂ ሁሴን ጊቢ ሲደርስ በረት ውስጥ በመግባት አልወጣም በማለቱ በተፈጠረ የግርግር ድምፅ አህያ የጠፋባቸው ባለቤት ወተው ሲመለከቱ ከሣምንታት በኋላ አህያው ገቢያቸው ውስጥ በመገኘቱ ወዲያውኑ ጉዳዩን ለፀጥታ አካላት በማሳወቅ ተከሣሹ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

የአህያው ባለቤት አቶ አብዱላሂ ሀሰን ቀደም ሲል ለአካባቢያቸው የፀጥታ አካላት ከሳምንት በፊት አህያቸው ከገበያ ውስጥ እንደተሠረቀባቸው በማመልከታቸው የፀጥታ አካላት ወዲያውኑ አህያውን ከገበያ ፈቶ በመውሰድ ሊሸጥ የሞከረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውለው ለፖሊስ ማስረከባቸው ገልፀዋል። ፖሊስም  እጅ ከፍንጅ የተያዘው ግለሰብ ላይ በአፋጣኝ የምርመራ መዝገብ በተያዘው አህያ ኤግዚቢትነት እና በሰው ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቤ ህግ መላኩን ገልፀዋል።

አቃቤ ህግም ከ ፖሊስ የተላከለትን መዝገብ ተመልክቶ በአፋጣኝ ችሎት ክስ በመመስረት የክስ መዝገቡ ለሀረና ቡሉቅ ወረዳ ፍርድ ቤት መላኩን ተናግረዋል።የሀረና ወረዳ ፍርድ ቤትም መስከረም 15 ቀን 2017 በዋለው ችሎት ተከሳሽ አሚን ሀሰን ሁሴን ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ ሁለት አመት ከ አራት ወር እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ረዳት ኢኒስፔክተር ጉዮ ጭቁሩ ለብስራት ጨምረው ገልፀዋል።ከገበያ የተሰረቀው አህያ ባለቤቶቹ ጊቢ በመግባት አልወጣም በማለት የሰረቀውን ግለሰብ እጅ ከፍንጅ በማስያዙ በርካቶችን አስገርሟል።
😆😆😅😅

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አንዷ ናት አሉ!

ገበያ ሂዳ በጣም ዘንቦባት በርዷት ቤትዋ ስትገባ ቶሎ እሳት አቀጣጥሉኝ አለች።

እሳቱም ተቀጣጥሎ በደንብ ሙቋት ብርዱም ጠፍቶ ነሸጥ ስትል፡

"ጌትዬ ይህንስ የመሰለ ነገር አኼራም ላይ አታሳጣኝ" አለች።

ከባልዋ ጋር ተነቋቁረው ነበርና እሱም ቀበል አደረገና "አትጨነቂ! ባትለምኚውም በስራሽም አታጪውም" አላት ይባላል።

ዱዓችንን እያስተዋልን😊

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ቺስታ ነው አትበይ አግቢው።

ባሪያ ሚያደርግሻ ባል ነው ምትፈልጊው?
t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አሳዛኙ ልብ ሰባሪው የጅምላ ድንገተኛ እልቂት በጎፋ የሞቱት ቁጥር ብዛት ከ219 በላይ መሆኑ ተረጋገጠ።😥😥😥😥

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የዱባይ አስተዳደር የሰው ሃይል ፖሊስ አባላቱን በሮቦት ፖሊሶች እያጠናከረ መሆኑ አነጋግሪ ሆኗል እነዚሁ ሮቦት ፖሊሶች በቅርቡ በሌሎችም የኢማራት ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል
tt.me/richyaneyena
ቪድዮውን ከታች ይመልከቱ

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

እንግዳ የማይገባበት ቤት መላኢካ አይገባም ረሱል ( ሰ.ዓ.ወ )

ሚስት ባሏ በተደጋጋሚ እንግዳ ይዞባት እየመጣ ትሰላችና ስሞታ ለማቅረብ ወደ ረሱል( ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ አቀናች ።

እርሳቸውጋርም ደርሳ ችግሯን አንድ፣በአንድ ዘርዝራ ትነግራቸው ጀመር ነብዩም( ሰ.ዐ.ወ) ዝም ብለው ከመስማት በቀር ምንም አልመለሱላትም
ከዚያም ተመልሳ ሄደች፣ ከሄደች በኃላ ነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) ባሏን አስጠርተው ዛሬ አንተ ቤት እንገዳ ነኝ አሉት ።

ባል በጣም ተደስቶ ለሚስቱ ነገራት ። ሚስትም አላመነችም የአለማት እዝነት የሆኑት ነብይ እቤቷ ሊገቡ ስለሆነ በጣም ተደሰተች እናም
ቤት ያፈራውን ነገር በደስታ አዘጋጀች።

ነብዩ ( ሰ.ዐ.ወ ) ገብተው ከተስተናገዱ በኃላ ለባልየው ስወጣ ሚስትህ እኔ በምወጣበት በር ወደዛ እንድትመለከት ንገራት አሉት። ረሱል ( ሰ.ዐ.ወ) ሲወጡ ሚስት፣ ተመለከተች።ልክ ሲወጡ ከኃላቸው
ጊንጥ፣እንሽላሊት፣ ሌላም ጎጂ ነፍሳቶች ተከትሏቸው ሲወጡ አየች

ሚስት በጣም ደነገጠች። ከዚያም ነብዩ ( ሰ.ዐ.ወ ) እንዲህ አሉ "አንድ እንግዳ ከተጠራበት ቤት ገብቶ ሲወጣ ልክ እንደዚ ከዛ ቤት ችግር፣በላ እና ጎጂ ነፍሳቶች ተከትለውት ይወጣሉ
አይ ዱኒያ
እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው። ረሱል ( ሰ.ዐ.ወ ) እንዲህ ብለዋል... አላህ ኸይር የፈለገለት ሰው ስጦታ ይልክለታል ፣ ያስጦታ ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ እንግዳ ሲገባ ሪዝቀ ይዞ ይገባል ሲወጣ የቤቱን ወንጀል ጠርጎ ያስወጣል ።

" እንግዳ የማይገባበት ቤት መላኢካ አይገባበትም" እንግዳ ወደ ጀነት አመላካች ነው። በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር"
እንግዳ መጋበዝ አለብኝ ብለን የግድ ከአቅማችን በላይ መጣጣር የለብንም ቤት ካፈራው ሊላሂ ብለን ብቻ እንግዳው ቀልቡን ለማስደሰት በኢኽላስ ከሆነ እንግዳው የሚያስደስተው የምግብ አይነት ሳይሆን እሱን አክብረን መጥራታችን ነው
አላህ እንግዳን የምናከብርበት ተውፊቅ ይስጠን
t.me/richyaneyena
ለወዳጅ ዘመዶዎ ይደርስ ዘንድ ሼር ያድርጉ

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

#መጅኑኑ_ለይላ

#ክፍል_ሁለት [❷]

ከምድር እምብርቷ መካ በስተ ደቡብ አቅጣጫ የምትዋሰነው የነጅድ ገጠራማ ከተማ እንደ ወትሮው ደንገዝገዝ ብላ ቀኗን እየገፋች ነው፡፡ ጊዜው ገና ልጅ ቢሆንም ፀሀይዯ ግን  ጠንክራለች፡፡ የነጅድ ሻኢሮች ከፀሀዯ ለመከለል በየበረንዳው እና በየቴምሩ ዛፍ ስር ተቀምጠው የተለመደውን የግጥም እንካ ስላንትያቸውን ማዶ እና ማዶ ሁነው ይወራወራሉ፡፡ ክፍት ጀለብያ ሳሳ ካለ ነጭ ሱሪ ጋር ለብሶ ጥቁር ጫማ የተጫማ ሸጋ ወጣት "ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እናንተ የብዕር ጌቶች"፡፡ እያለ  በመሀላቸው አልፎ ካደባባይ ሚንበሩ#1 ላይ ቆመ፡፡ ከሚንበሩ ላይ የቆመውን ገጣሚ ለማዳመጥ ባንድ ጊዜ ጠባቧ የነጅድ አደባባይ በሰው ጎርፍ ተራወጠች፡፡ መጅኑን ነበር፡፡ ውሀ ጠምቶት በበረሀ እንደሚጓዝ የንግድ ቅፍለት የግጥም ጥም ያሰከራቸው የነጅድ ነዋሪዎች ከመጅኑን ፊት ተጀገጀጉ፡፡ መጅኑን በቋንቋ ጥልቀቱ እና በጠንካራ መልዕክቱ እስከዛሬ ድረስ ተወዳጅነትን ያተረፈ ጉምቱ ገጣሚ ነው፡፡ በአረቡ አለም ያለ የአንድ ወጣት እጣፋንታ ከሶስት ነገሮች ሊወጣ አይችልም፡፡ ወይ ነጋዴ ነው ፣ አልያም ጀይሽ#2 ነው ፣ ወይ ደግሞ ሻዒር#3 ነው፡፡  ታዳ እንደ ለይላ እና መጅኑን ላሉ የፍቅር ውድቅተኞች ብዕር ከማነቅ ውጭ  ምን አይነት እጣ ፋንታ ሊፃፍላቸው ይችላል!! ጥሩ ስነ-ግጥም ከጥልቅ የስሜት ባህር ይቀዳል፡፡ ለ14 ክፍለ ዘመናት እንደጣፈጠ ዛሬ ድረስ የቆየው የመጅኑነ-ለይላ ጥዑም ስነ-ግጥምም የተጨለፈው ከዛ ጥልቅ የስሜት ባህር ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ (ከፍቅር ፣ ከህመም ፣ ከናፍቆት ፣ ከእጦት)!  መጅኑን እሱን ለማድመጥ ያሰፈሰፉትን የግጥም ዛረኞች  ትኩረታቸውን እንዳገኘ እንዲህ ሲል ..... በአራት ስንኝ ብቻ የህይወቱን ትልቅ ሚስጥር ባደባባይ አነቦጨው፡፡

ተዐለቅቱ ለይላ ወሂየ ጊሩን ሶጊረቱን
ወለም የብዱ ሊልአትራቢ ሚንሰድይሀ ሀጂሙ
ሶጊረይኒ ነርአልበሂመ ያ ለይተ አነና
ኢለል የውሚ ለም ነክቡር ወለም ተክቡሪል በሂሙ!!

እንዲህ የሚል ሀሳብ አለው..."እኔ ለይላን የምወዳት ያኔ ነው፡፡ ያኔ ገና ህፃን ሳለች ፣ ህፃን ሳለሁ፡፡
ምንም ጓደኛ ሳታፈራ ፣ ምንም ጓደኛ ሳይኖረኝ፡፡
ገና ጡቶቿ እንኳን ብቅ ብቅ ሳይሉ በእረኝነት ጊዜአችን ያኔ.... ጀምሬ ነው የምወዳት፡፡
ታዳ ዛሬ ላይ እንዲህ ስል አምርሬ ተመኘሁኝ "ያ ጊዜ ባለበት በቆመ ፣ እንሰሳዎቹም ሳያድጉ ፣ እኛም ሳናድግ በዛ ሁናቴ ለዘላለም በኖርን ብዬ ተመኘሁኝ"፡፡ ብሎ እንደጨረሰ እድምተኛው ሁሉ እያልጎመጎመ ቅሮቱን ገለፀ፡፡ ከግጥሙ ባሻገር የቀይስ መደዴነት አስገርሟቸዋል፡፡ እሱ ግን ምንም አልደነቀውም፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየለየለት ነው፡፡ ከለይላ መውደድ የተገፋ ከነጅድ ቢነጠል ተገፋሁኝ ብሎ አያለቃቅስም፡፡ እንኳን ከነጅድ ከአለም ቢጣል ኢምንት ታክል አይገደውም፡፡ "እንኳን ከዚች ትንሽ አለምና ከግዙፏ ለይላም ተገፍቻለሁ"!! ሲል ለይላ የለለችበትን ባዶ አለም ያቀላታል፡፡  ከዛው ሚንበር ሳይወርድ ከእድምተኞቹ መሀል እንደ ሙዚቃ የሚስረቀረቅ ሌላ የልጅ አገረድ ድምፅ በለቅሶ ታጅቦ ተሰማ፡፡ ሁሉም ድምፁ ወደመጣበት አቅጣጫ ሀሳቡን እና ጆሮውን ቀስሮ የልጅ አገረዷን ጥዑም ግጥም በትኩረት ማድመጥ ጀመረ፡፡ ለይላ ነበረች፡፡ የመጅኑንን የፍቅር ኑዛዜ ስትሰማ አላስችልሽ ብሏት ከቆመችበት ጥጋት መደ መጅኑን እየተራመደች በጀበሉ ሰውባን የቋጠረችውን የፍቅር ቁጥርጥር ፈትታ ባደባባይ ተናዘዘች፡፡ ለዘመናት ያረገዘችውን ፍቅር ወለደች፡፡
ፈኣጃበት ለይላ ወሂየ ባኪየቱን ለማ ሰሚአት ሺእረሁ.....

ወኩሉን ሙዝሂሩን ሊናሲ ቡግዶን
ወኩሉን ኢንደ ሷሂቢሂ መኪኑ
ተኽቡሩነል ኡዩኑ ቢማ አረድና
ወፊል ቀልበይኒ ሰመ ሀወን ደፊኑ

"ሁላችንም ሌሎች ሰዎች ስለ ፍቅራችን እንዳያውቁ እንጥራለን፡፡ ማወቃቸውን እንፈራለን ወይም አያስደስተንም፡፡ ግና በልቦቻቸው ውስጥ ጥሩ እና ምቹ ቦታ አላቸው፡፡ የኔና አንተም ፍቅር ምንም እንኳን ይፋ ባይወጣ አይኖቻችን ግን ያሳብቃሉ፡፡ በውስጣችን እጅግ የጋለ ፍቅር እንደተቀበረ አይኖቻችን ይናገራሉ"፡፡ ስትል ፊቷ በእምባ እየታጠቡ ሽሽጉን መውደዷን ገለፀችለት፡፡ የእድምተኛው ሹክሹክታ እና ጉምጉምታ በርክቶ ተሰማ፡፡
በአረባውያን ወግ ከትዳር በፊት ያለ የፍቅር ግንኙነት በፍፁም ውግዝ እና ቅባሎት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት ያለን ወዳጅነት ተቀብለው በፍፁም ለትዳር አያበቁትም፡፡ ምድር ተገልብጦ ሰማይ ቢደፋ አይታሰብም!! ለይላም ይህን ፈርታ ነበር እንደ ጀሂም#4 እሳት የሚፋጅ ፍቅሯን በልቧ ውስጥ አዳፍናው የቆየችው፡፡  ከእርሱ ጋር ጀነት የሆነን ነገ አልማ ነበር ከሬት የሚመረውን መሪር ውሳኔ እየመረራት የተጋተችው፡፡ መጅኑን ግን የሷን ሽሽት እና  ቸልታ ባለ መፈለግ ወስዶት ተስፋ ቆርጦ ለእብደት እየዳዳው ነው፡፡ ለዛም ነው ውስጡ የሚንተከተከውን ፍቅራዊ ጎመራ ባደባባይ በግጥም ያስተነፈሰው፡፡ እሷም የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ብላ የውስጧን እውነት ገለፀችለት፡፡

ከለይላ የወጡትን ቃላቶች ሲሰማ ከቆመበት ሚንበር ላይ ጣረ ሞት እንዳየ ሰው ሰውነቱ ዝሎ ፣ እግሩን ብርክ ብርክ እያለው ቁልቁል ትክክክክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም እምባ በሚያወርዱት በመንታ አይኖቿ ሽቅብ አስተዋለችው፡፡ በገሀድ አለሙ እና በህልሙ መሀል ያለ ጭንብርብር ምስል እያየ መሰለው፡፡ በሆነ አንድ ለሊት ላይ ምናቡ የፈጠረው ክስተት ነገር!! በዛች ደቂቃ ደስታ ፣ አለማመን ፣ ፍርሀት ፣ ቁጭት ፣ ግርምት እየተፈራረቁ አናወዙት፡፡ ከፊቱ የቆሙት ሰዎች ተገለባበጡበት፡፡ አይኑ ላይ ቀለማቶች ተንቦዣቦዡ፡፡ ያይኖቹን ሽፋሽፍት ገርበብ አድርጎ አስለምልሞ ከድኗቸው ከቆመበት ሚንበር ቁልቁቁል ተዝለፍልፎ ተፈጠፈጠ፡፡ በደስታ ብዛት ካሳበደቺው አለሙ ከእግሯ ስር እራሱን ስቶ ተዘረረ፡፡ ያ.....ቀይ መልከኛ ገፁንም የደም ጎርፍ አጨቀየው፡፡

ኣካባቢው በጩኸት እና ግር ግር ሲናጥ ለይላ በድንጋጤ ከወደቀበት መሬት ላይ አፋፍሳ እየጮኸች ጭኗ ላይ አስተኛችው፡፡ በእጆቿ ደሙን እየጠረገች ስቅስቅቅቅቅቅቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ከመጅኑን ጭንቅላት የሚፈሰው ደም እንደ ዘምዘም ውሀ ያለ ማቋረጥ ፈለቀ፡፡ ከከበቡት ሰዎች ውስጥ አንድኛው እጁን ወደ መጅኑን አንገት ሰዶ በደም ዝውውሩ የሞት ሽረቱን ጉዳይ ቸክ አደርጎ ዝም አለ፡፡ ለይላ እንደ እብድ እየጮኸች ምን ሆነ???? በህይወት አለ????? ተናገር እንጂ! እያለች የጥያቄ መዐት አዥጎደጎደችበት፡፡

ክፍል ሶስት ይቀጥላል . . .

አስረጅ ፦
#1"ሚንበር" (መንበር / ከፍታ ቦታ)
#2"ጀይሽ"  (ወታደር / ጦረኛ)
#3"ሻኢር" (ገጣሚ)
#4"ጀሂም" (ጀሀነም / ገሀነም)፡፡

t.me/richyaneyena

ይቀጥላል....

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

(መጅኑነ ለይላ)

ክፍል 1


ፍቅር |መሀባ|
የፍቅር ምንድንነት ሲፈታ ህመምነቱ ይገለፃል፡፡ አዎ እውነትም ፍቅር ህመም ነው፡፡ ከሰውነት ጀምሮ እስከ ውሳጤያዊ ነፍሳችን የሚዘልቅ ረቂቅ ደዌ!! ህመሙ በተሰማን ቁጥር ደስ በሚያሰኝ ስሜት በያንዳንዷ ህዋሳችን ደርሶ ሀሴት የሚያስደርግ ህመም!! እኛም ያን ህመም እያደር ይበልጥ እንዲያመን ወደን እንመኘዋለን፡፡ ለህመሙ ስጋ እና ነፍሳችንን እንፈቅዳለን፡፡ ምን አይነት ያማረ ህመም!! እነዛም እውነተኞቹ ታማሚያን(አፍቃሪ) ከዛ ህመም መዳንን እና ማገገምን አይሹም፡፡ ይልቁንስ ትክክለኛው ስቃይ ፣ መጥፎው ስቃይ....ከፍቅር ህመም ውስጥ በመውጣት በሚዳነው ድነት ውስጥ ባለው እውነተኛ አለም ላይ ነው፡፡ (መዳን ማለት ለነሱ መታመም ነው)፡፡ የፍቅር ህመም ማለት ደግሞ ለነሱ ሲገለፅ ከእያንዳንዷ የስቃይ ፍሬ የፍቅርን ጣፋጭ ወይን ጨምቆ በፍቅር ፅዋ መጎንጨት ነው፡፡

ለይላ እና መጅኑን ያን አይነት ህመም የታመሙ ፅኑ የሁብ ህሙማን ነበሩ፡፡ ካራቱ ሁለፋዑ ራሺዲን#1 አገዛዝ በኀላ የኡመውዮች ሀገረ መንግስት በሚያስተዳድረው የአረቢያ ግዛት ውስጥ ነጅድ (ሪያድ) በምትባል ከተማ ውስጥ ለፍቅር ኑረው ለፍቅር የሞቱት ህያዋውያን፡፡ በፍቅር አለም ድሙቅ ታሪክ የፃፉ አሳዛኝ ስብዕናዎች፡፡ በአረባዊ የፍቅር ወቄት ሲመዘኑ ከአልፈን ኡሉፋ#2 ጥንዶች አንድ እነሱ ሚዛን የደፉ የፍቅር መለኪያዎች፡፡ "ሹዐዳኡል ሁብ"፡፡ (የፍቅር መስዋዕት)የተሰኙት መጅኑን እና ለይላ፡፡

የውልደት ጊዜአቸው በዘመነ ሂጅራ#3 አቆጣጠር 24ኛ ሂጅራ ገደማ ላይ በሞቃታማዋ የገጠር ከተማ ነጅድ ውስጥ ነው፡፡ በኢሮጵያኑ የዘመን ቀመር ደግሞ 645 ዐ.ም ላይ፡፡ (የሰዕድ ቢን መህዲ ልጅ ለይላ ቢንት ሰዕድ እና የሙለወህ ልጅ ቀይስ ኢብኑል ሙለወህ)፡፡ ሲወለድ ካባቱ ዘንድ ቀይስ ኢብኑ ሙለወህ የተሰኘ ሙሉ ስም ወጣለት፡፡ በኀላ ላይ በለይላ ፍቅር ደግሞ በሰዎች ዘንድ "መጅኑን"#4 የሚል ቅፅል ስም ታክሎለታል፡፡ ከለይላ ጋር ከነፍሳዊ የፍቅር ቁርኝት ባሻገር በስጋ ዝምድናም ጭምር ይተሳሰራሉ፡፡ ለይላ ለቀይስ (ለመጅኑን) የአጎቱ ልጅ ነች፡፡ ከመጅኑን ቤተሰቦች አንፃር የርሷ ቤተሰቦች በሀብታቸው የታፈሩ እና የተከበሩ መሊካውያን ቢሆኑም በአረባዊ የልጅ አስተዳደግ ባህል መሰረት ከልጅነታቸው ጀምሮ በጀበሉ ሰውባን#5 ኮረብታዎች ላይ በፍየል እረኝነት መጅኑን ጋር አንድ የበረሀ አሸዋ ተራጭተው ፣ ባንድ አኮሌ የፍየል ወተት ተጎንጭተው ፣ አንድ የጋራ ንፋስ ምገው ነው ያደጉት፡፡ ያ ጊዜ ለቀይስ የህይወቱ አስኳል ነበር፡፡ ቀይስ የሚለውን የወላጆቹን ስም አስፍቆ "መጅኑን" ያስባለው ፍቅር በጮርቃ ልቡ ውስጥ የተጠነሰሰው ያኔ ነበር፡፡ ኮልታፋ አፉን በግጥም እንዲፈታ ያደረገው የለይላ ፍቅር.... ያኔ ነበር አሊፍ ያለው፡፡ በአለም ኑረቱ ላይ ያሳለፈውን እድሜ ሲቆጥር ያንን ዘመን ብቻ አስልቶ ይናገራል፡፡ እጅግ የሚናፈቅ እና አይረሴው የህይወቱ ክፍል ነውና ከዛ በኀላ እንደሞተ ነገር ......"በህይወት የነበርኩት ያኔ ነበር!" ሲል እነዛን ወርቃማ ጊዜያቶች በግጥሞቹ ይቀኛቸዋል፡፡ በጀበሉ ሰውባን የረኝነት ወቅት በለይላም ልብ ውስጥ የቀይስ ደዌ ተጋብቶባት በሴት የልጅነት ልቧ ፍቅሩን ቋጥራለች፡፡

በዚህ ሁኔታ የልጅነት እረኝነት ጊዜያቸው አልፎ ወጣትነትን ተላበሱ፡፡ ለይላ እና መጅኑን ላይ የአካል እና የሥነ-ልቦና እድገት ተስተዋለ፡፡ ከእድሜአቸው ጋር ፍቅራቸውም እኩል አብሮ ገዘፈ ፣ ጦፈ፡፡ ቀይስ በእሳታዊው ወጣትነቱ ላይ ልቡ ውስጥ የሚፏፏመው የፍቅር እሳት በጅጉ ተቀጣጠለ፡፡ የለይላም እምቡጥ አበባነት በእድሜ ፍካት ፈነዳ፡፡ እንደ አረቢያን ሰህራ#6 ባዶ ሜዳ በነበረው ሰውነቷ ላይ ጡቶቿ ጉች ጉች አሉ፡፡ እንደ ተወርዋሪ ፍላፃ ጭብጥ የማይሞላ ወገቧ ዳሌዋን አጎላ፡፡ ፀጉሯ የኮንያን ሀሮች አስንቆ ዳሌዋ ላይ ተጎዘጎዘ፡፡ ያቺ....ሙጫዋ#7 ፣ እረኛዋ ለይላ ዛሬ....ላይ ሌላ! ሆነች፡፡ ውብ ውጫዊ ገጿ ከጥልቅ ግጥም አዋቂነቷ ጋር የነጅዱን ቀይስ መጅኑን አደረጉት፡፡ ጠዋት..."ለይላ" ፣ ቀትር... "ለይላ" ፣ ማታም... "ለይላ"፡፡ እንደ ደረሳ ሲዋክ ሁል ጊዜ ለይላ ከመጅኑኑ አፍ ላይ ዋለች፡፡ ከፊል ወጣትነታቸውንም ያለ ማንም ከልካይ በሰመሪን እና ገዷ ውብ ቦታዎች አይረሴ ውብ የፍቅር ጊዜያትን አሳለፉ፡፡ ነገር ግን እነዛ ውብ ጊዜያቶች ለመጅኑን እና ለይላ አይንን ጨፍኖ እንደመግለጥ ያክል ቅፅበታዊ ነበሩ፡፡ ውብ የሆኑ ነገሮች ምንንን ቢረዝሙ አጭር ናቸው፡፡ ውድ የሚያደርጋቸውም ይህ ተዐምራዊ ጠባያቸው ነው፡፡

ጊዜው በሄደ ቁጥር እድሜ እሚሉት ክፉ ዳኛ በጉርምስና ወግ አጥሮ መተያየትን ከለካላቻው፡፡ ዳር የሌለው መነፋፈቅን ፈረደባቸው፡፡ ከጀበሉ ሰውባን የፍቅር መቅደሳቸው ነጥሎ ለይላን ከቤት አዋላት፡፡ መጅኑንም ለይላን በየቀኑ እንዳሻው ማየት ተስኖት ፣ ሀሩር በሆነ መውደዱ ላይ ናፍቆት ታክሎበት ከውስጡ እሳት ጎመራ፡፡ ነደደ ፣ ተቃጠለ ፣ ተንገበገበ !! ናፍቆት ጥፉው ፣ ናፍቆት ክፉው!!....ይሉኝታ አሳጥቶ እያክለፈለፈ ከለይላ ደጅ ያደርሰዋል፡፡ በግጥሞቹ ደጋግሞ ለይላን ያስቀኘዋል፡፡ ለይላ ይህንን ስትሰማ እንዳልሰማች ታልፈዋለች፡፡ መጨረሻም ለቀይስ ፊት ነስታ ጀርባ ሰጠቺው፡፡ መልስ የሚሹ ግጥሞቹን ሰምታ እንዳልሰማች አለፈቻቸው፡፡ በዚህ ድርጊቷ ክፉኛ ልቡ ተሰበረ፡፡ የልጅነት ፍቅራቸው ለይላ ላይ ተዳፍኖ እሱ ላይ ብቻ እንደተጋጋመ ተሰማው፡፡ በለይላ አለመወደድ ፣ በለይላ አለመፈለግ አይነት ስሜት ደበተው፡፡ ሰርክ አይኑ እምባ ቀረዘዘ ፣ ልቡ ተሰብሮ ተሰቀዘ ፣ ህይወት ኑረቱ ቀዘቀዘ ፣ ገፁ ፈዞ ደበዘዘ......ሙሉ አለሙ ተቃወሰ፡፡ የወጣት አሞቱ ፈሰሰ፡፡ በቃ!! ያ..ጅንኑ ቀይስ መጀነነ!! በዚህም ሳቢያ "መጅኑን" ተሰኘ፡፡

ነገር ግን ያኔ...ለይላም ከመጅኑኑ ያላነሰ የፍቅር እሳት እየበላት ማንም እንዳያውቅና እንዳይሰማባት በውስጧ ቀብራዋለች፡፡ የማትተነፍሰው የሚያቃጥል ረመጥ ሆኖባት ሁሉን ስሜቷን በሽሽግ እንደተፀነሰ ልጅ በሆዷ አርግዛ ከልቧ ማጀት ደብቃዋለች፡፡ ግና በሆድ ያለን የፍቅር ሽል አፍ ባያወራው ፍቅራዊ ህጉ እርግዝናን ያሳብቃል፡፡ ለይላም ምንም እንኳን ለመጅኑን ግድ እንደሌላት ነገር ፊት እየነሳች ብትገፋውም ስለሱ የሚሰማት ውስጣዊ ፍቅር ናፍቆቷን ፣ መሻቷን ፣ መውደዷን .... አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ወጣትነቷ ከመጅኑኑ ደረት ላይ ሊጥል ይገፋታል ፣ ከውስጧ የሚንጣት የግጥም ዛር "ቀይስ" ፣ "ቀይስ" እያስባለ ሊያስለፍፋት ይዳዳዋል፡፡ ግና አትፈቅድለትም፡፡ ግን ደግሞ በሌላ በኩል በሷ እጦት ወደ እብደት ጎዳና ዳዴ የሚል የነፍሷ ሰው አለ፡፡

ታዳ ለምን ደበቀችው???

t.me/richyaneyena
ክፍል ሁለት ይቀጥላል..

አስረጅ ፦
#1"ሁለፋኡ ራሺዲን" አራቱ የኢስላሙ አለም ነገስታት (አቡበክር ፣ ኡመር ፣ ኡስማን ፣ አልይ)፡፡
#2 "አልፈን ኡሉፋ" ሺህ እና ከሺህ በላይ፡፡
#3"ሂጅራ" የአረቢያን(ኢስለማዊ)የዘመን መቁጠሪያ፡፡
#4"መጅኑን"እብድ፡፡
#5"ጀበሉ ሰውባን" የሰባንን ተራራ(በአረብያ ግዛት የሚገኝ) ቦታ፡፡
#6"ሰህራ" በረሀ፡፡
#7"ሙጫዋ" ህፃኗ፡፡

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

#አቲካ

#ቆንጆ_ነች_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ

#ክፍል_አስራ_አንድ(የመጨረሻዉ ክፍል)_11

ሰይዲና ኡስማን ቤታቸው ቁጭ ብለው ቁርአን እየቀሩ ሳለ የፊትና ሰዎች መተው የቤታቸውን በር በእሳት ካቃጠሉ በዋላ የተከበረ ቤታቸውን ደፍረዉ ገቡና በሚዘገንን ሁኔታ በሰይፍ 9 ጊዜ ወጉዋቸው።ከዚያም 3 ለአላህ ነው 6 ለራሳችን ነው በማለት ፎከሩ።ሰይዲና ኡስማን ንፅህ ደማቸው እየቀሩት በነበረው የአላህ ቁርአን ላይ እደጅረት ፈሰሰ።ከዚህ የፊትናን በር የሚዘጋ ወንድ ጠፋ ።የአላህ ራሕመት ሆኖ ግን ታላላቆች ሰሃቦች ይሄ ክስተት ሳያዩና ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ጊዝያቶች ብዙወቹ ሞተዋል ።በዚህም ስበብ መዲና ውስጥ በየለቱ እርስበርስ የደም መፍሰስ ቁምነገር ሆነ።ይሄንን ማየት ያልፈለገውና ወደአላህ ቶሎ በፍጥነት መሄድ የፈለገው ታላቁ ሰሃብይ ሰይዲና አሊ ኢብኑ አቢጣሊብ በአንዳች መፍተሔ መጣላቸው ።ሸሂድ ሆኖ ለማለፍ አቲካን ለትዳር መጠየቅ ነው እናም ደፈፍረው አደረጉትና ጠየቁዋት።አቲካም የነበረባትን ሃዘን ሳይቀላት ሰይዲና አሊን አግብታ ምን እንደሚፈጠር ስላወቀች ጉዱዩን ጉዳዬ ሳትለዉ ይሄን መልስ አሳወቀች ።አሊ ሆይ እኔ ላንተ እንደምኞትህ ቀልኪዳን እገባለሁ ሸሂድነትን በአላህ ፍቃድ ታገኛለህ አላችው።አዎ ሰይዲና አሊም አቲካን በተመኙበት ጥቂት ቀናት ውሰጥ ሸሂድነትን አገኙ። ከዛ በዋላ አቲካን ለትዳር የጠየቃት እና ለአራተኛ ጊዜ የገባት ሰይዲና ሁሴን ሆኑ። የረሱላችን የልጅ ልጅ ነበሩ።አቲካ ከሰይዲና በመጋባቱዋ ከረሱል ጋር አመችነት አገኘች ።በቀደመው ትዳሯ አቲካ እቤቷ ነበር የባለቤቶቹዋን ሸሂድነት ስትሰማ የነበረው ።አሁን ግን ሁኔታዎች ተቀየሩ ።ዉዱ ባሉዋ በሄደበት አብራው በመሄድ ጂሃድ ላይም ተሳታፊ መሆን ጀመረች ።ሸሂድነትም ከመጣ ከባሏ ጋር አብራ አንድላይ መቅመስ ናፈቀች ።ይሄንን የምጠላ ማን ሴት አለች?
ከእለታት ባንድ ቀን ኩፌ በሚባለው የኢራቅ ከተማ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረ ።ሰይዲና ሁሴን አቲካ ፊት በአሰቃቂ ሁኔታ አይኗ እያየ ተገደሉ ። ይሄ ሲፈጠር አቲካ የውዱን ባለቤቷን እራስ ከወደቀበት አፈር ላይ አንስታ በለቅሶ እና በሃዘን ያማካለ ኡኡታዋን ገዳዮች እንኳን ደፈረው መስማት በከበዳቸው ሁኔታ ጮሀች።የአቲካ ሀዘን እጅጉን የከፋ ደረጃ ደረሰ ።አቲካ ከዚህ ቀን አንስታ ከሁሉ ነገራት እራሱዋን አግልላ ስትኖር ቆየች።የሃዘኗ ክብደት ለብቻዋ መሸከም ከብዷዋት ሌተቀን ስታነባ ያማረ እና ውብ አይኗ ለአይነ ስውረነት ተዳረገ።ቢሆንም ግን አሁንም የትዳር ጥያቄዎች እንደጎረፉ ነዉ ።አቲካ ግን ጥያቄዎቹን ሁሉ ረሱል አማቼ ናቸው በሳቸው ላይ ማንንም አልደርብም ስትል መለሰች።አሁን ግን ሁሉም ነገር ታሪክ ሆነ። ያቺ ቆንጆ ሴት በሂጅራ አቆጣጠር በአርባኛው አመት ላይ ታማ ሞተች።ያሁሉ በጎ ስራና ለባል ሃቅ የከፈለችው መሰዋእትነት ውዴታ እና ፍቅሯ ትእግስት እና ኢባዳዋን ይዛ ወደ አኼራ ሄደች።የዘመኑ ውዱዋ እህቴ ሆይ ምን ይዘሽ ይሆን ?

t.me/richyaneyena

#ተፈፀመ,,,,,,,

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

"ፈራን"

ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን...።

"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን

"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን

"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን

"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የሰይጣን ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ

"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…
Подписаться на канал