richyaneyena | Неотсортированное

Telegram-канал richyaneyena - ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

1900

በቻናሌ ውስጥ በማስተላልፈው ፕሮግራም አስተያየት ከአላችሁ ይህንን @Richyanyena ሊንክ በመጫን በግል አናግሩኝ!!

Подписаться на канал

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አፉታን አሏህ ይወዳል ኡፉ በሉኝ። ለተከበረው ረመዳን በሰላም አደረሳችሁ!

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አሁንስ ምርር ያለኝ ነገር የሴቶችን ውሸት መስማት ነው ጭራሽ ጆሮዬን ሰጥቼ ብሰማት
.
ምጣዳችን ፍላሽ ይቀበላል ትበለኝ😏😒

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ትንሽ ፈገግታ !

መልካም ስትሆን ለሰዎች ምን እየሰጠኃቸው አንዳለህ አታውቅም ፈገግ ብለህ በማየትህ ብቻ ትልቅ ተስፋ የሰጠኃቸው ብዙዎች አንዳሉ ገምተህስ ታውቃለህ? ስለዚህ ወዳጄ ምንም ማድረግ ባትችል እንኳን ከልብህ ፈገግ ብለህ ለሰዎች ሰው እንዳላቸው እንዲሰማቸው አድርግ ውጤቱ ብዙ ነዉ

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

በክፍለ ሀገር በተለይም በደቡብ በዳእዋው ዘርፍ በገጠር በመዘዋወር ታላቅ አስተዋፆ እያደረገ ለሚገኘው በንፅፅር ዳእዋ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት አንዱ ለሆነው ኡስታዝ ሙሀመድ ከድር መኪና ለመግዛት ቲክቶክ ላይ እህት እና ወንድሞች ርብርብ እያደረጉ ነው:: ዛሬ ቅዳሜ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከስር ባለው የአቡአማር ቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ገቢ ማሰባሰቢያ ይደረጋል:: እናንተንም እንዳትቀሩ ተጋብዛችኋል
ሊንኩ ይኼው
https://vt.tiktok.com/ZS8me9yXJ/

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሰውዬው በሀዘን ስሜት ፊቱ ቅጭም ብሎ ወደ ቤቱ ገባ። «ለመሆኑ ዛሬ ምን አጋጠመህ ?» በማለት ሚስቱ ጠየቀችው። «የከተማው ከንቲባ ሁለተኛ ሚስት የማያገባ ካለ ስቅላት ይጠብቀዋል» የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ አላት።
t.me/richyaneyena
ምን ብትለው ጥሩ ነው ...

«አላህ ለሸሂድነት ስላጨህ ምስጋና ማቅረብ አለብህ» አለችው 😂

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

«ውድ» ወንድሜ ብሎ ወሬውን የሚጀምር ሁሉ ተስፋ ይሰጠኛል ብለህ አታስብ። ኢትዮ ቴሌ እንኳ «ውድ» ደንበኛችን በሚል አማላይ መልዕክት ወሬውን ጀምሮ «ያለዎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው» ብሎ ይሰናበተሃል👌

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

as wa we wb እንዴት ናችሁ ውዶቼ? አላህ የተመሰገነ ይሁን ጠፍቼ ነበር ተመልሻለው አልኸምዱሊላ።

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ለፈሪ ዱላ ለጥሩ ሰዎች
ደግሞ መጥፎ ሀሳብ
እንዳታነሳ ሁለቱም ጥለውህ
ይሽሻሉ♡

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ራስህን እመነው!

ችግር ሲገጥምህ የምትሸሽ ወይኔ አለቀልኝ ብለህ የምትፈራ ከሆነ ችግርህ ሁሌም እንደ ጥላህ ሲያሳድድህ ይኖራል! አለበለዚያ ግን ምናባቱ ያመጣል ብለህ የገጠመህን ችግር ከተጋፈጥከው እንደ ንስር ተረጋግተህ ከላይ ወደታች ካየኸው ያ መከራ እንደ ዝሆን ግዙፍ ቢሆን እንኳን እንደ ቁጫጭ አንሶ ይታይሀል።

ወዳጄ ከአሏህ ቀጥሎ ራስህን እመነው ካንተ አቅም በላይ የሆነ ምድራዊ ፈተና የለም! ምክንያቱም ለማሸነፍ ነው የተፈጠርከው!💪

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

እያዘንክ አትኑር!

ትላንትክ መቃብር ውስጥ ሞቷል! ነገክ ደግሞ በማህፀን ውስጥ ሊወለድ ተዘጋጅቷል! ለፀሀይ ቦታውን የማይለቅ ለሊት የለም፡፡ እያዘንክ አትኑር! እንደሌላው መዝናናት ይገባሀል መሳቅም ያምርብሀል!
ከንግዲህ አንተም እኔም ለድላችን እንዘምራለን እንጂ ስለችግራችን አናለቅስም! የሚያጋጥሙህን ችግሮች ተምረህባቸው በድል ታልፋቸዋለህ!
እናም በመጨረሻ አንተን ማስቆም የማይታሰብ ነገር ይሆናል!

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ትናንሽ ብርሀኖች ግዙፍ ጭለማዎችን ያስወግዳሉ ትናንሽ መልካም ሀሳቦች
ወደ ትላልቅ ስኬት መሻገርያ መሰላል ይሆናሉ. t.me/richyaneyena
ምንም ጊዜ ትላልቅ ነገሮች በትናንሽ ሀሳቦች የተገነቡ መሆናቸውን አትዘንጋ

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

በእራስሽ ተማመኚ ለራስሽ በምትተምኝው ዋጋ ልክ ነው ሌሎች ሚገዙሽ።

የዚህች እህታችንን ፖስት ሳይ በጣም አዘንኩኝ ለሁላችንም ' ለህታችን እራስሽን ከሌላዋ ጋር አታወዳድሪ ሁሌም ቆንጆ ልዩ እንደሆንሽ አስቢ ተቀበይ በራስሽ ተማመኚ እቺ ህይወት ለደካሞች ግድ የላትም ማንም አንቺ ለሚሰማሽ የበታችነት ስሜት ግድ የለውም ማንም ሊረዳሽ አይችልም በሁሉም ሰዎች ፊት ሳትሸማቀቂ በጥንካሬና በራስ መተማመን ተራመጂ ምንልባት የአንቺ ቦታ ላይ መሆን ሚመኙ ሌሎች ሴቶች ሊኖሩ ይችላሉ ለራስሽ የምሰጭውን ግምት ዝቅ አታድርጊ ከበታችነት ስሜት ውጪ አላህ በሰጠሽ ፀጋ አመሰጋኝ ሁኚ

የኡሙ ሰሊም ረ.ዐ የአነስ ቢን ማሊክ ረ.ዐ እናት ታሪክ ላስታውሳቹ የአነስ አባት ማሊክ መልኳን ሳያያት ያገባታል ቤቱ ከገባች በኃሏ መልኳ አስቀያሚ በመሆኑ ከግዜ በኃሏ ጥሏት ይሄዳል ከዛም ተመልሶ ሲመጣ የአነስ እናት ያ ማሊክ ከመጥፎው ውስጥ ጥሩውን ልታገኝ ትችላለህ አለችው ነገር ግን ማሊክ ንግግሯን ችላ ብሎ ድጋሚ ጠፋ ከ20ዓመታት በኃሏ ወደ ከተማው ተመልሶ አንድ መስጅድ ውስጥ ሊሰግድ ገባ አንድ ወጣት እጅግ በጣም ማራኪ በሆነ መንገድ ሀዲስ ሲናገር ሰማው በወጣቱ አንደበት ይማረክና አጠገቡ ላለው ሰው ይህ ማነው ብሎ ሲጠይቀው ከ20ዓመት በፊት ከተማውን ጥሎ የጠፋ ማሊክ የሚባል ሰውዬ ልጅ ነው አለው ታሪኩ እዚህ ላይ ባያበቃም ላጠቃለውና

ኡሙ ሰሊም ባሏ አስቀያሚ በመሆኗ ጥሏት ቢጠፋም የበታችነት ስሜት ሳይሰማት ፍፁም በሆነ በራስ መተማመንና ጥንካሬ ልጇን አነስን በዲን ተርብያ አንፃ በስነምግባር ኮትኩታ አሳድጋው የረሱል ሰ.ዐ.ወ የቅርብ ጏደኛ እንዲሆን አድርጋዋለች ለዛም ነው የሴት ልጅ ውበት የፊቷ ገፅታና ፋሽን አዋቂነቷ አይደለም ያልኩት እናም አላህ ውበታችንና አቋማችንን ሳይሆን የልባችንን ንፅህና ነው ሚያየው ትክክለኛ ሰዎችም በአደብሽና በመልካም ስነምግባርሽ ነው ውበትሽን ሚለኩት

ለራሳችን ስንል ጠንካራ በራሷ የምትተማመን ሴት እንሁን እቺ አለም ለደካሞች ቦታ የላትም

t.me/richyaneyena
ሪች ነኝ✍

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ዝምተኛው ገዳይ

==ለደም ግፊት ሕክምና መከተል ያለብን የጥንቃቄ መመሪያ==

#ሰርቫይቫል
ለወዳጆችዎ ማጋራት አይዘንጉ!
ደም ግፊት(#Hypertension) ወይም በተለምዶ በሃገራችን ደም ብዛት ስለሚባለው በሽታ አብዛኛው ሰው መጠነኛ ግንዛቤ አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ነገር ግን በደም ግፊት ምክንያት የሚደርሰውን ሌሎች ተያያዥ የጤና ጉዳቶች የሰውነት ጉዳትና የህይወት ህልፈት በሚመለከት ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ ነው፡፡ የደም ግፊት እንደ በሽታ የሚቆጠረው ከጤናማ በላይ ሲሆን ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ያጋጠማቸው ሰዎች ደግሞ መድኃኒት መጀመር እንዳለባቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን መድኃኒት የሚጀመርበት የደም ግፊት መጠን ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ነው የሚሆነው፡፡ በተለይም በእድሜ በኩልና ሌሎች ተደራቢ በሽታዎች ባሉባቸው ሰዎች ላይ፤ በመሆኑም እነኝህን መመሪያዎች ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡

እንደሚታወቀው የደም ግፊት ሲለካ ሁለት ቁጥሮች አሉ በአንግሊዝኛ (systolic ) የላይኛው እና (diastolic ) የታችኛው ቁጥር፡፡ እነዚህ ቁጥሮች አንዱ ወይም ሁለቱ ከመጠን በላይ ሲሆኑ የደም ግፊት አለ ይባላል፡፡ ማሰተዋል ያለብን እነዚህ ቁጥሮች ከመጠን በላይ ሲሆኑ ምንም የህመም ስሜት ወይም ምልክት ላይኖር እንደሚችል ነው፡፡ ዋናው ችግር ይህ የደም ግፊት በጊዜ ካልታወቀ ሊያስከትል የሚችላቸው የተላየዩ በሽታዎች መኖራቸው ነው፡፡ ዋነኞቹ ችግሮች ስተሮክ (stroke) ወይም የነርቭ ምች(ከህይወት ማለፍ ጀምሮ የሰውነት ክፍልን ሽባ በማድረግ የሚታወቅ)፣ ድንገተኛ የልብ ህመም (Heart attack)፣ የኩላሊት መድከም (Kidney failure) እና ሌሎች ተያያዥ በሽታዎች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን በሽታዎች ለመከላከል የህመም ስሜትም ባይኖርም የደም ግፊት ምርመራ አልፎ አልፎ ማድረግ ተገቢ ነው፤ ችግሩ መኖሩ ከታወቀም በመድኃኒት አማካኝነት ጤናማ ደረጃ ወይም መጠን ላይ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

በአሜሪካ (Joint National Committee - JNC) በሚባል የህክምናና ሌሎች ባለሙያተኞች ያሉበት ኮሚቴ ሐኪሞች ለደም ግፊት ሕክምና ታካሚዎች መቼ መድኃኒት መጀመር እንዳለባቸው እንዲሁም ምን ዓይነት መድኃኒቶች መጠቀም እንዳለባቸው መመሪያ ያወጣል፡፡ ይህ መመሪያ በየጊዜው ሲወጣ ቁጥርን መሰረት ያደረገ ሲሆን በቅርቡ የወጣው መመሪያ (JNC 8) ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህ መመሪያ ለአሜሪካውያን የወጣ እንደመሆኑ መጠን ሀገር ቤት ለሚኖሩ ሰዎች ተግባራዊ መደረግ አለበት ለማለት በሀገር ቤት በቂ ጥናት ማድረግ የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ ሁኔታው ያን ያህል የሰፋ ልዩነት የሚኖረው እንደማይሆን ግምቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜም ለተለያዩ በሽታዎች የምዕራባውያኑን የሕክምና ትምህርት ስለምንጠቀም ይህ መመሪያ ደግሞ አገልገሎት ላይ መዋል ይችላል ብለን ልንወስድ እንችላለን፡፡ ሌላው ተጨማሪ ነገር ከመድኃኒቶች ጋር ሌሎች የሚደረጉ ነገሮች ለምሳሌ የሚበላውን የጨው መጠን መቀነስ፤ በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ የመሳሰሉት አስፈላጊ መሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

በተጨማሪ ይህን መመሪያ የምናካፍለው አብዛኞች ሰዎች በየቤታቸው ወይም በሌላ አጋጣሚ ደም ግፊታቸው ለክተው ቁጥሮችን የሚያውቁ ከሆነ ወደ ሀኪም ቀርበው ህክምና እርደታ እንዲጠይቁ ለማነፃፀሪያነት እንዲጠቀሙ ነው፡፡ እነኝህ የቁጥር መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ለአዋቂዎች እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች መድኃኒት መጀመር የሚገባው (systolic ) የላይኛው ቁጥር ከ150 ወይም ከ 150 በላይ ከሆነ ወይም (diastolic ) የታችኛው ቁጥር 90 ና ከዛ በላይ ከሆነ ነው፡፡
2. እድሜያቸው ከ60 ዓመት በታች ለሆኑ አዋቂዎች ደግሞ መድኃኒት መጀመር የሚገባው የላይኛው ቁጥር 140 ወይም ከዛ በላይ ሲሆን የታችኛው ቁጥር ደግሞ 90 ወይም ከዛ በላይ ሲሆን ነው፡፡
3. የኩላሊት በሽታና የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች ግን በማንኛውም እድሜ ክልል ቢሆኑም የደም ግፊት መድኃኒት የሚጀመረው የላይኛው 140 ወይም ከዛ በላይ ከሆነ የታችኛው ደግሞ 90 ወይም ከዛ በላይ ከሆነ ነው፡፡
4. ሰዎች መድሃኒቶች ከጀመሩ በኋላ አስፈላጊ ክትትል ማድረግ የሚኖርባቸው ሲሆን የሚፈለገው የደም ግፊት መጠን በአንድ ወር ውስጥ አስፈላጊ መጠን ካልወረደ የመድሃኒቱ ጉልበት መጨመር ወይም ሌላ ተደራቢ መድሃኒት መታዘዝ ይኖርበታል፡፡ እዚህ ላይ ግን ደም ግፊታቸው አደገኛ ደረጃ የሆነባቸው ሰዎች አንድ ወር ድረሰ ይቆዩ ማለትም አይደለም፡፡ ሰለዚህ ነው ሐኪምዎ የሚወስንልዎትን ነገሮች በትክክለ መከተል አስፈላጊ የሚሆነው፡፡

እንግዲህ ከላይ እንደተጠቀሰው የደም ግፊት መጠን ከፍ ሲል ስሜትና ምልክት ስለማይሰጥ በጊዜ ካልታወቀና ቁጥጥር ስር ካልዋለ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ጉዳት ስለሚያደርስ ማንኛውም እድሜው 18 አመት የሞላው ሰው የደም ግፊቱን መጠን አልፎ አልፎ እንዲለካ የሚመከረው፡፡ ከተለኩ በኋላ ቁጥሮች ከፍ ያሉ ከሆነ የግድ ሐኪም ማማከር ተገቢ ነው፡፡ የደም ግፊትዎን ይለኩ!

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አላህ ሆይ
በሌሎች ላይ ስመለከተው የምጠላውን ነውር በራሴ ላይ አታሳየኝ 🤲

በሽተኛው ቅንጣት ሳያደክም በዙሪያው ያሉ ጤነኛ ሰዎችን በሙሉ የሚያደክም ብቸኛ በሽታ «ደደብነት» ነው።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ኢትዮጵያውያን_እናቶቻችን ከሚጠቀሙባቸው_ባህላዊ_መድኃኒቶች በጥቂቶቹ እናስጨብጣቹ።

ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹን...በየቤታችን ውስጥ እናቶችን ይጠቀሙበታል።

1. ጤና አዳም፦ ቅጠሉም ሆነ ፍሬው ለሆድ መታወክ ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎች መሰል ሕመሞች መድኃኒት ነው።
2. ዳማከሴ፦ ለጉንፋን ፣ ለከባድ ራስ ምታት (ማይግሬን) በአፍንጫ ተስቦ የሚወሰድ ፣ ለመተንፈሻ ቧንቧ ችግርና አጠቃላይ ለምች ፍቱን መድኃኒት ነው።
3. ሬት ቅርፊቱ ተልጦ የሚገኘው የውስጡ ዝልግልግ የማር ወለላ የመሰለው ነገር ከሌላ ምግብ ጋር አዋህዶ በመምታት የከሱ ሕፃናት ቢመግቡት ወዲያውኑ ያፋፋቸዋል ፣ ለቁስል ቢቀቡት ወዲያው የመፈወስ ኃይል አለው ፣ ለፎረፎር ቢቀቡት፣ የስኳር በሽተኞችና የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች አድርቀው ፈጭተው እንደ ሻይ አፍልተው ቢጠጡት የመፈወስ አቅም አለው።
4. የጫት ቅርፊት፦ ስጋ በልቶ አልፈጭ ብሎት ሆዱ የታወከ ሰው ወቅጦ ቀቅሎ ቢጠጣው ይድናል።
5. አርማ ጉሳ፦ አረንጓዴውን ቅጠል በማድረቅ ወቅጠው እንደ ሻይ ለረጅም ጊዜ በመጠጣት የስኳር ህመምተኞች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ፈጥኖ የማውረድና የመቀነስ አቅም አለው። ቅጠሉን ደግሞ በአረንጓዴነቱ ወቅጠው ጨምቀው ቢጠጡት ከቁርጥማት የመፈወስ ኃይልና የምግብ አፒታይት የመክፈት ኃይል አለው።
6.ነጭ ሽንኩርት፦ ለደም ዝውውር ፣ ለጨጓራ ፣ ለውስጥ ካንሰር፣ ለመተንፈሻ አካል፣ ለወሲብ ማነቃቂያነት እና በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲንሸራሸር ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ አዋቂዎች አብነት በመጥቀስ ይናገራሉ።
7. የኮክ ዛፍ ቅጠል፦ የጋማና የቀንድ ከብቶች በድንገት ሲታመሙም ሆነ ሰዎች በድንገተኛ በሽታ ሲያዙ ከጤና አዳም ጋር ተወቅጦና ተጨምቆ ሲጠጡት ከህመማቸው ይፈወሳሉ።
8. ግራዋ፡- ቀን ተመርጦ 7 ቅጠሉ ተቀንጥሶ በሰው እጅ መድኃኒት ለበላ ሰው ቢያጠጡት የመፈወስ ኃይል አለው ፣ እንዲሁም በግራዋ የታጠበ እቃ(እንስራ) ሽታን የሚያመጡ ባክቴሪያዎችን ያጠፋል። ከዚህ በተጨማሪም ግራዋ የተተከለበት ቦታ እባብ ፈፅሞ አይኖርም።
9. የነጭ_ባህርዛፍ_ቅጠሉ፦ ቅጠሉን በውሃ ተፈልቶ ቢታጠኑት የመተንፈሻ አካል ችግርም ሆነ የትኛውም የጉንፋን ዓይነትን ያለ ኪኒን በሁለት ቀን ውስጥ ፈውስ ያገኛል።
10. ቀይ ሽንኩርት፦ ለአጠቃላይ ጤንነትና ለደም ዝውውር ጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር የዘር ፈሳሽ እጥረት ላጋጠማቸው ሰዎች በብዛት ለማመንጨት እንደሚያገለግል አባቶች ይናገራሉ ፤ ኮረሪማና ቆንዶ በርበሬ እነዚህ በአንድ ላይ ተቀምመው ለራስ ምታትና ለሆድ ቁርጠት ፍቱን መድኃኒት ናቸው።
11.ዞጓራጋጅ(አማርኛ ስሙን ለጊዜው አላቀውም) ቅጠሉ በእንጨት የሚጠመጠም ሆኖ እንደ አሚቾ ስር የሚያኮርት ሲሆን ይኸው ስሩ ትክትክ ለያዘቸው ሕፃናትና ወባ ለያዛቸው ሰዎች አገልግሎት እንደሚውል አባቶች ይናገራሉ።
12.ኦሞሮ፦ ይህ አረንጓዴ ተክል የእግር ወለምታ ላለባቸውና ሰውነታቸው ተቀጥቅቶ ደም ለቋጠረባቸው ቅጠሎቹን በውሃ ቀቅሎ ቦታውን በቅጠሉና በተቀቀለው ውሃ ደጋግመው ሲያሹት እጅግ ፍቱን መድሐኒት ነው እንዲሁም ሴቶች በወሊድ ወቅት የፈሰሳቸውን ደም ለመተካትና በወር አበባ ጊዜ ተቀቅሎ እንዲጠጡት ይደረጋል። ይህ መድኃኒት የቅጠላቅጠል ዝርያ ሲሆን ለወለደች ሴትና የወር አበባ ያየች ሴት ከአንድ ሣምንት ላላነሰ ጊዜ እየተቀቀለ እንዲጠጡት ይደረጋል። ምክንያቱም ቁርጠትን ይከላከላል፣ሆድ ያጥባል ተብሎ ስለሚታመን ነው።
13. እንስላል፦ በውሃ ተቀቅሎ ሲጠጣ የተዘጋ የሽንት ትቦ ይከፍታል።
14. የምድር እምቧይ ስሩ /አሚቾው/፡- ተወቅጦ የታመሙ ከብቶች እንዲጠጡት ሲደረግ ከብቶቹ ይድናሉ።
15. መቅመቆ፦ የተባለ ተክል ስሩ ተወቅጦ እንዲደርቅ በማድረግ ዱቄቱ 2 ወይም 3 በሻይ ማንኪያ በውሃ በማፍላት እንዳሻይ ቢጠጣ የደም ግፊት ይቀንሳል።
16.የእንጆሪ ቅጠል፡- በንፅህና ደርቆ ተወቅጦ በሻይ መልክ ተፈልቶ ቢጠጣ የስኳር ህመምን ይቀንሳል።
17. ፌጦ፦ ለድንገተኛ ህመምና ውጋት ተወቅጦና ተበጥብጦ በመጠጣት ከህመም መፈወስ ይቻላል።
18.ቀበርቾ /ቾሳ/፡- ከስራስር ክፍል የሚመደብ ሲሆን አገልግሎቱም ለድንገተኛ ህመም ፣ ውጋት ወዘተ በማኘክ የሚወሰድ ፈዋሽ መድኃኒት ነው።
19.ጣዝማ ማር፦ ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የማር ዓይነት ሲሆን ከነጭ አዝሙድና ኮረሪማ ጋር በመቀላቀል ጠዋት ጠዋት ሁለት ማንኪያ በመውሰድ ከሳል ፣ ከአስም ፣ ከቁርጥማት ወዘተ ህመም መገላገል ይቻላል። ይህንን መድኃኒት የወሰደ አንድ ሰው መድኃኒቱ እንዲሠራ ቢያነስ ከአንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ጊዜ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይጠጣ ይመክራል።
20. ሎሚ፡- ለብዙ ዘመናት ከምግብ መመረዝና ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት የሆድ በሽታ ለመፈወስ ሲጠቀሙት የቆየ ባህላዊ መድኃኒት ነው።
21.ልምጭ፦ ከድንገተኛ ህመም ፈዋሽ ሲሆን የጥርስ መፋቂያ ዓይነትና ለብዙ በሽታዎች ፍቱን መድኃኒት ነው፤ከበሽታዎቹም መካከል የአፍንጫ ነስርና ላለበት ሰው ነስሩን ለማስቆም ቅጠሉን በመበጠስና በማሸት ቢያሸቱት ፍቱን መድኃኒት ነው።
22. እንቆቆና መስመስ፦ ለሆድ ትላትልና መሰል በሽታዎች ተፈጭቶና ተበጥብጦ ከኮሶ ጋር በመደባለቅና በመጠጣት ለኮሶ ትልና መሰል የሆድ ህመም መድኃኒት ነው።
23. የጥቁር ገብስ አረቄ፡- የጥቁር ገብስ አረቄ ለአስም በሽታ ጠዋት ጠዋት ሁለት መለኪያ ቢወስዱት በሽታውን ማስታገስ ይቻላል።
24.ሰንሰል እና_አግራ፦ ሰንሰል ከሀገር በቀል መድኃኒት ውስጥ የሚካተት ሲሆን ቅጠሉን በመበጠስ ተወቅጦ በሻይ ብርጭቆ አንድ በባዶ ሆድ ሲጠጡበት በወፍ በሽታ ለተጠቃ ሰው ፍቱን መድኃኒት ነው።
25.የእንሰት ስር(አምቾ)፡- ከውስጥ አካሉ የሚገኘው ውሃ እና አሚቾው ተቀቅሎ ደጋግሞ መብላት ከወፍ በሽታ ይፈውሳል እንዲሁም እንዲመግል የተፈለገ የተጎዳ የሰውነት አካልም ሆነ በሰውነት የወጣ ማንኛውም እባጭ መግል ሆኖ እንዲፈነ/እንዲወጣ የእንሰት አምቾ ተደጋግሞ ይበላል ፣ የተሰበረ አጥንት በወጌሻ ማጀል ሲያስፈልግ የተሰበረው ቦታ ለማለዘብ (ለማለስለስ) አምቾውን በእርጎ እያማጉ ደጋግሞ መብላት ነው ፣ በጠቦት ሾርባ ደጋግሞ መብላት በመኪናም ሆነ በጦር ሜዳ ስጋው የተቦጨቀ ወይም አጥንቱ ላይ አደገኛ ስብራት ያጋጠመው ቁስሉ እንዲሽር(እንዲጠገን) ያደርጋል።
26. ኮሶ፡- የደረቀ የኮሶ ዛፍ አበባ ከእንቆቆና መስምስ ወቅጦ በብርጭቆ በመጠጣት የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትልን ጠራርጎ ማስወጣት ይቻላል።
27. ሽፈራው:- የዚህ ዛፍ ቅጠል የማያድነው በሽታ የለም ይባላል የስኳር መጠንን ይቀንሳል ፣ የደም ግፊትን ይቀንሳል ፣ የደም ዝውውርን ያቀላጥፋል ቅጠሉን.... እንደ ሻይ ተፈልቶ ፣ ዱቄቱ ተወቅቶ በውሃ መጠጣትም ይቻላል ፤ እንዲሁም እንደ ጎመን ቀቅሎ መብላትም ይቻላል።
እነዚህ እፅዋቶች እንደየ አከባቢው አጠራር ስማቸው ሊለያይ እንደሚችል ግንዛቤ ይወሰድ t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

መግዛት ሚፈልግ በጣም ኦርጅናል እቃ በግል አናግሩኝ
1, ቫኪዩም ክሊነር

2, የአባያ የመጋረጃ የሸሚስ ወዘተ መተኮሻ

3, 4 አይን የኤሌክትሪክ ኦቭን መሉ ለሙሉ በኤሌክትሪክ ሚሰራ ነው

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

በመልካም ከተረጎምከው ትንሽ ነገር በህይወትህ አስተዋፆ የሚያደርግ ሰው በጣም ትልቅ ባለ ውለታህ ነው።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሚስት ባሏ ሞቶ እሪሪሪሪሪ ብላ ስታለቅስ ያያት ውይ ስታሳዝን ምን ያህል ብቶደው ነው ምንማን እያሉ ሲያወሩ ዞር ብላ ስለምወደው እኮ አይደለም አንድ ሰው ሲሞት ቤተሰቦቹ አምርረው ካለቀሱ ቅጣቱ የበረታ ይሆናል ሲባል ሰምቼ ነው አለች አሉ 🙆‍♀️
t.me/richyaneyena
ምን ያህል ቢበድላት ነው🙄😅
አይ ሴቶች😂

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሰውዬው አራቱም ሚስቶቹ ተመሳሳይ ክስ አቅርበውበት ችሎት ላይ ቆሟል። ዳኛው «ከናንተ መካከል በዕድሜ ትልቅ የሆነችው ሚስቱ ትናገር» ሲል አንዳቸውም ሳይተነፍሱ ቆመው ቀሩ። ዝምታ ሰፈነ። እስካሁን ድረስ የክሱ ፋይል ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ተልኳል።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

t.me/richyaneyena

ውዶቼ በህይወት ስንኖር እጅግ በጣም ብዙ ፈተናዎች እንጋፈጣለን ነገር ግን አሏህ ይፈትነናል እንጂ ብቻችንን አይተወንም ወደ እርሱ እንድንማጸን ይፈልጋል ከዛ በኃላ አዛኙ አላህ በጠበቅነው ባሰብነው ሳይሆን ባላሰብነው መንገድ ነገሮች አሏህ ያመቻቻል ።ለምኑልኝ እቀበላለው ብሎናል እኛ ግን እርሱ ከመለመን ቦዝነናል። አሏህ ለምኑት ወላሂ ሰጪ ነው ስንለም ታድያ ንያችን ጠባብ መሆን የለበትም አሏህ ሰፊ ነገር ይወዳል።እኛ ግን ትሽን ነገር ነው ምንጠይው ለምን። አሏህዬ አንገቴ ማስገባበት ቤት ስጠኝ እንላለን ሌላ ሰውነታችን ውጭ ሊያሳድረው ነው ቆይ?ውይስ ሙሉ ኮንፕሌት ነገር መስጠት ያቅተዋል? ሰፋ አድርጋችሁ ለምኑ ስትለምኑ ይሰጣል ሰጪ ነው። የባዳ የዘመድ ወኪል አብዛልኝ በሉት ረቢል አለሚን ያበዛላችኃል። በዚህ አጋጣሚ ትንሽ ጉዳይ ገጥሞኝ ሰበብ ሆኖ ጉዳዩ ለፈታልኝ የአኸሯ ወንድሜ በአሏህ አመሰግናለው። ዱንያ አኸራው አሏህ ያመቻችለት ንያው አሏህ ይሙላለት አሚን በሉ!!!

هَلْ جَزَآءُ ٱلْإِحْسَٰنِ إِلَّا ٱلْإِحْسن

የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?

Aal-e-Imran 3:148

فَـَٔاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ ثَوَابَ ٱلدُّنْيَا وَحُسْنَ ثَوَابِ ٱلْءَاخِرَةِۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

አላህም የቅርቢቱን ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው፡፡ አላህም በጎ አድራጊዎችን ይወዳል፡፡

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሁሌም ቢሆን የምትወደው ነገር በአንተ ህይወት ውስጥ ውብ ሆኖ የሚከሰተው አንተ ሁሉንም ነገር በትግስት አሪፍ አድርገህ ስትተውነው ነው

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አቋም

አቋም የሌለው ሰው በንፋስ አቅጣጫ ይመራል በዚህ ሲሉት በዚያ ሁሌም በተመራበት ነው የራሱ የሆነ የእኔ የሚለው መንገድ አይኖረውም የራሱ የሆነም ህይወት አይኖርም የሌሎችን ህይወት እየኖረ የሌሎችን ህልም እያሳካ እኔ የኔ የሚለው ነገር ሳይኖረው ማንነቱ ሳይታወቅ ያልፋል ፤ ሁሌም ቢሆን የኔ የምንለው የምንመራበት ህግ እና አቋም ልንገነባ ይገባናል ያኔ የኔ ያልነውን የተመኘነውን ውብ ህይወት ለማጣጣም እድል ይኖረናል!

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

በማንኛውም ነገር መዘግየትህ አትጥላው


ፈጣሪ ያዘገየህ ምናልባት ለአንተ ለአንቺ መልካም የተሻለ ነገር አስቦ ሊሆን ይችላል። በስራ፣ በፍቅር፣በትዳር፣ በጤና ወዘተ ፈጥነህ ስኬታማ አለመሆን አትጥላው ጉንዳን ያሰበችበት ቦታ ለመድረስ ከ100 ጊዜ በላይ ወድቃ ትነሳለች። ንብ ሚጣፍጠው ማር ለማዘጋጀት ከ1000 ጊዜ በላይ አበባ ለመቅሰም ይመላለሳል። ስለዚህ የአንት የአንቺ የህይወት ውጣ ውረድ አትጥያቸው አትጥላቸው ወደ ስኬት ሚያሻግሩ መንገዶች ሊሆኑ ይችላሉ። ፈንድሻ እንዴት እንዲህ አማርሽ ሲሏት እሳቱ ስለተቋቋምኩኝ ነው አለች ይባላል።ስለዚህ ወዳጄ ነውጥ ከሌለ ለውስ ስለሌለ ድካምህ እንደ ስኬት ቁጠረው እፎይታ መምጣቱ አይቀርም።

t.me/richyaneyena

ሪች ነኝ✍

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ማሰብ በቂ አይደለም የተግባር ሰው ሁን!

"ስፖርት መስራት እጀምራለሁ፣ አንድ መፅሀፍ በሳምንት አነባለው፣ በጠዋት እነሳለው፣ ራሴን አሻሽላለው" ብለህ ካሰብክ ቆየህ ፤ ግን መቼ ነው ወደ ተግባር የምትገባው? ሁልጊዜ ሰኞ ሲመጣ ወይ ወሩ ሲያልቅ፣ ወይ አመቱ ሲፈፀም ማቀድ አልሰለቸህም?

ወዳጄ ምግብ የበላ እንጂ ለመብላት ያሰበ አይጠግብም እኮ! መድሀኒቱን የዋጠ እንጂ ስለ መድሀኒቱ አብዝቶ ያወቀ አይድንም እኮ! ማወቅ ማሰብ ማቀድ አሪፍ ቢሆንም ተግባር ከሌለው ግን በዜሮ ነው ሚባዛው! ስለዚህ አንዱን ዕቅድ አሁኑኑ ጀምረው!
t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ያለፈውንን ይቅር በል !

ቂም መያዝ አቁም በደሉኝ ተገፍቼ ነበር ሰው ለእኔ ክፉ ነው ጥሩ የሚያስብልኝ የለም ብለህ ማሰብህን ተው ሁሉን ነገር ፈተና አታድርገው ሰው ሁሉ ሆን ብሎ አንተን ሊያጠቃህ እና ሊበድልህ የሚተጋ አይደለም ምናልባት አንዲት ሴት ባልጠበቅኸው ሁኔታ አስከፍታህ ይሆናል ያ ማለት ግን ሁሉም ሴት አንተን ሊጎዳ የተዘጋጀ ነው ማለት አይደለም ይጎዱኛል ብለህ ከቀረብህ ግን እመነኝ መጎዳትህ አይቀርም ምክንያቱም አንተ የምታየው ሁሉ መጥፎ ነገሩን ብቻ ስለሆነ ስለዚህ ይቅርታ አድርግ እናም ሁሌም አዲስ ህይወት ጀምር ሁሉም ነገር ባለበት አይቀጥልም !

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

መሥጂድን ማን ይሥራ?

ኩፋሮች የአላህን መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፦

9፥17 ለከሓዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲኾኑ የአላህን መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ مَا كَانَ لِلْمُشْرِكِينَ أَن يَعْمُرُوا مَسَاجِدَ اللَّهِ شَاهِدِينَ عَلَىٰ أَنفُسِهِم بِالْكُفْرِ ۚ أُولَٰئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ وَفِي النَّارِ هُمْ خَالِدُونَ

የአላህን መስጊዶች የሚሠራው በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ፣ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፣ ግዴታ ምጽዋትንም የሰጠ ከአላህም ሌላ ማንንም ያልፈራ ሰው ብቻ ነው፦
9፥18 የአላህን መስጊዶች የሚሠራው በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ፣ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፣ ግዴታ ምጽዋትንም የሰጠ ከአላህም ሌላ ማንንም ያልፈራ ሰው ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከተመሩት ጭምር መኾናቸው ተረጋገጠ፡፡ إِنَّمَا يَعْمُرُ مَسَاجِدَ اللَّهِ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَلَمْ يَخْشَ إِلَّا اللَّهَ ۖ فَعَسَىٰ أُولَـٰئِكَ أَن يَكُونُوا مِنَ الْمُهْتَدِين

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ዝንጅብል ጥቅምና ጉዳቱ

ዝንጅብል ስንጠቀም መወሰድ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች

ዝንጅብል ለጤና እጅግ ጠቃሚ ከሚባሉ የቅመም አይነቶች አንዱ ነው ፡፡
የህክምናው ዘርፍ የጤና ባለሞያዎች ፤ ዝንጅብል ለጤናችን አጠቃላይ ስለሚሰጠው ጥቅም በተደጋጋሚ ምክር ይለግሳሉ፡፡ነገር ግን ማን እና መቼ መወሰድ እንዳለበት ከዚህ በታች የጤና ምክሩ ተቀምጧል፡፡

ዝንጅብል -------
1. ጥቅም
 የሰውነት በሽታ መከላከል ብሎም ደም ፍሰት ማሻሻል
 ተቅማጥ, የሆድ ድርቀት, እና መጥፎ ጨጓራ ለማከም
 ሳል, የወር አበባ ቁርጠት, የልብ ጉዳዮች, የጡንቻ, የአጥንት ሕመም ለማስታገስ
 ቁርጠት ለመከላከል, ማቅለሽለሽ, የደም ግፊት, የኮሌስትሮል, ማይግሬን, ሄሞሮይድስ, የካንሰር ስርጭት የመከላከል አቅም አለው ፡፡

መለስተኛ እና ከባድ ሁኔታዎች ሁለቱንም የማስታገስ ፤ የመከላከል አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ ሁለገብ (Cure All) ያደርገዋል ይላሉ፡፡

ለዚህ ነው ዝንጅብል ከፍተኛ አንቲ-ሴፕቲክ የሚባለውና በባህላዊ መንገድም ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው ፡፡

ታዲያ የጥቅሙን ያህል ጉዳትም ስላለው አወሳሰድ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው ያለናል መረጃው ፡፡

ከሁሉም በላይ አወሳሰዳችንን ማስተካከል ከቻልን በዝንጅብል ምክንያት ሊከሰት የሚችል አሉታዊ ጎን ማስቀረት ይቻላል ፡፡

2. እነማን ከዝንጅብል መራቅ ይኖርባቸዋል?
 ነፍሰጡር ሴቶች
 ዝንጅብል ኃይለኛ ድብልቅ ንጥረ ነገር ስላለው አለጊዜው እርግዝና እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል
 ስለዚህ በተለይ በእርግዝና የመጨረሻ ወራትዎ ከዝንጅብል ይራቁ ፡፡
 ለስኳር እና ከፍተኛ የደም ግፊት ኪኒን የሚወስዱ ሰዎች
 ሄሞፊሊያ እና የደም ህመም ያለባቸው ሰዎች
 ክብደት ለመጨመር ለሚፈልጉ ሰዎች ዝንጅብል አይመከርም ፡፡
t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ዝምተኛው ገዳይ

የደም ግፊት (Hypertension)

የደም ግፊት ምንድነው?
የደም ግፊት ከልብ ምት የሚመነጭ እና ደም በሰውነት እንዲዘዋወር የሚረዳ የግፊት ሀይል ነው። የደም ግፊት ከሚገባው በላይ ሲጨምር የደም ቧምቧዎችን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። ይህም የደም ብዛት ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት (hypertension ወይም high blood pressure) ይባላል።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

፦ ሀብት ጨዋ አያደርግም.. ድህነትም ለባለጌነት ምክንያት አይሆንም።
፦ አዕምሮ እንዲሰራ ተሰጠን እንጂ ተሰርቶ አልተሰጠንም።
፦ ከቻልክ የምትወደውን ስራ ስራ.. ካልቻልክ የምትሰራውን ስራ ውደድ። ለመጥላት ምክንያት ከምትፈልግ ለመውደድ ምክንያት ፈልግ።
፦ መቀየር ያለብን ነገር ቢኖር የምናየውን ነገር ሳይሆን የምናይበትን መንገድ ነው።
፦ ያጣነውን ትተን ያለንን እንቁጠር።
፦ በህግ. በምግባር. በትምህርት. በጥበብ የተገነባ ህሊና ክፉ አስተሳሰብ አይኖረውም።
፦ ፍቅር ውበት ነው። ውበት ደግሞ የልዩነት ውህደት ነው። ጠንካራ ፍቅር በልዩነት የሚሳል ኢትዮጵያዊነት ነው። ድክመት የጥንካሬ ሸራ ሲሆን በፍቅር ይሸፈናል።
፦ ወሳኙ የምንኖርበት ቦታ ሳይሆን አኗኗራችን ነው። ከጠባቡ ብቸኝነታችን ወደ ሰፊው ና ጠቅላላው የሰው ልጅ ምልከታ ከፍ እስካላልን ድረስ ኖርን አንበል። ለምን? የሰው ልጅ ትልቁ ጠላቱ አስተሳሰቡ ነውና። t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አንድ ቀን የገባህ እለት ትንሿን ኩሬ ለማይሻገሩልህ ሰዎች ውቅያኖስ ማቋረጥህ ታቆማለህ! Nomore

Читать полностью…
Подписаться на канал