ብሶት
በችግር መሰላል ብታንጠለጥይኝ
በገዛ ገንዘቤ ለሞት ብትሸጪኝ
አትጠራጠሪ አታስቢ ላፍታ
ይቅር እልሻለሁ ደሞ ለይቅርታ
ግን እንደው አንቺ ሴት
በይቅርታ ልኬት
ለበደልሽኝ ሁሉ ምህረት ባደርግም
ይቅር ስልሽ እንጂ ሳምንሽ ግን አልኖርም።😭
بَلِ اللَّهَ فَاعْبُدْ وَكُن مِّنَ الشَّاكِرِينَ
[ አል-ዙመር - 66 ]
ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም፡፡ ከአመስጋኞቹም ኹን፡፡
ጌታዬ ሆይ
የማይመጣን ነገር እንድጠብቅ አታድርገኝ
ሀዘኔን በማይፈራ ሰው ላይ ችክ እንድል አታድርገኝ ለእኔ ባልፃፍከው እና ልቤን በሚጎዳ ነገር ላይም እንድንጠለጠል አታድርገኝ
/channel/richyaneyena
”
ምን አልባትም ህልሞችህ በዩሱፍ ጉድጓድ ውስጥ ወድቀው ሊሆን ይችላል፣
የአሸናፊው(የአላህ) ቅፍለቶች እንደሚመጡ ግን አትዘንጋ።
በህይወትህ ውስጥ ጠንካራም ደካማም የመሆን ምርጫ አለህ ፣
የውሳኔው ባለቤት አንተ ነህ።
ድምፅህን ሳይሆን፤የቃላትህን ደረጃ ከፍ አድርግ ቡቃያን የሚያበቅለው ነጎድጓዱ ሳይሆን ዝናቡ ነው።
ምናልባት በህይወትህ ክፍተትን የፈጠረብህ ይበልጥ ውብ በሆነው ነገር ሊሞላህ ፈልጎ ይሆናል።
/channel/richyaneyena
ከትግስተኛ ሰዎች ጥንካሬን ተማር
ከጥበኛ ሰዎች ደግሞ ብልሀትን ታማር
ከድሀዎች ደግሞ መብቃቃትን ተማር
ከችኩል ሰዎች ደግሞ ችኩልነት
መጨረሻው ፀፀት እንደ ሆነ ተማር።
ጊዜ ሁለት ነው አንድ ቀን ለአንተ ይሆናል፤ አንድ ቀን ባንተ ላይ ይሆንብሀል፤ ለአንተ ሲሆን አትኩራ፤ ........ባንተ ላይ ሲሆን አትጨነቅ ››*~ ~* -አሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)
Читать полностью…ሻወር ከራስ ይጀምራል
በማንኛውም መልኩ ጥንካሬ እንደሌለህ በማሰብ በአንተ ላይ የበላይነታቸው ለማሳየት የሚመጡ ነገሮች በቀላሉ አትፍቀድላቸው።ሁሌም ጠንካራ እንደሆንክ ለውስጥህ እየነገርክ እችላለው በል። የሚመጣብህ ከባድ ነገር በቀላሉ ማሸነፍ እና መወጣት ትችላለህ። የዛን ጊዜ አንተ ለነገሮች መኖር ትተውና ነገሮች ለአንተ መኖር ይጀምራሉ።
/channel/richyaneyena
✍ሪች ነኝ።
« ሁለቱ መላጦች »
ሁለት በራ ሠዎች ሲያልፉ በጎዳና
ዕቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል ያዩና
ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ
ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ።
በኀላም ተማተው በጥፊ በጡጫ
አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ
አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ
ዕቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ።
እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት
እሱ ራሱ በራ ፀጉር የለበት
ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ
ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ?
ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ
የተጣሉበትን ጥቅሙን ሣይረዱ
ከመጣላት በፊት ከመቀያየም
የነገሩን ፍሬ መረዳት መልካም።
በ (ዶ/ር ከበደ ሚካኤል)
አንዳንድ ሰዎች ወደ ህይወትህ ጣልቃ
በመግባት ሰላም ይሰጡሀል አንዳንዶች
ደግሞ ከህይወትህ በመውጣት ሰለም
ይሰጡሀል የሁለቱም ወለታ አለብህ።
ይ ቅ ና ህ!
እግርህ ከተነሳ፣ ለመሄድ ወስነህ፣
ልብህ ከሸፈተ፣ ካጠገቤ ሆነህ፣
ከኔ ርቆ መሄድ፣ ውሳኔህ ከሆነ፣
መለየትን ናፍቆ፣ ልብህ ከጨከነ፣
ወዴ! ሽኝሀለሁ ናፍቆትን ደርቤ፣
መሸኘት ልማዱ፣ ሆኗልና ልቤ፣
ፈጣሪ ካልጻፈው፣ የእህል ውሃን ነገር፣
ይቅናህ በሄድክበት ክፍም አልናገር፣
ያመጣህ ጎዳና፣ ይውሰድህ መልሶ፣
ወትሮም መንገደኛ፣ ይመስላል ደርሶ
/channel/richyaneyena
ሁሉም የራሱ አላማ አለው ነገር ግን
አብዛኛ ሰው አላማውና ፍላጎቱ እስኪሳካ ለማይፈልገው ነገር እስረኛ ሆኖ ይኖራል።
የጉልበትህ ሁሉ መሰረቱ ትዕግስትህ ነው።
አንድ ዛፍ ሲወድቅ ሁሉም ሰው ድምፁን ይሰማዋል።ጫካው የሞላው ዛፍ ሲያድግ ግን ማንም አይሰማውም። ልብ በል ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት እድገትህ ሳይሆን ውድቀትህን ነው። ስለዚህ ላለመውደቅ ጥረት አድርግ።
/channel/richyaneyena
ህይወት ብዙ አይነት ከለርነው ያላት የአንተም ህይወት ሳታስበው ልክ እንደ ቲማቲሙ ውብ ከለር በመሆን ሊቀየር ስለሚችል አሁን ያለህበት የህይወትህ ከለር አጣፍጠህ ኑረው
/channel/richyaneyena
ነገራቶችን ከሚገባቸው በላይ ቦታ አትስጥ ፣ ክብርህን በሰዎች እይታ ውስጥ አትፈልጋት፣ ህሊናህ ውስጥ ፈልጋት፣ህሊናህ ሲረጋጋ ክብርህም ከፍ ይላል…ራስህን ካወክ ስላንተ የተባለው አይጎዳህም፣የዱንያን ጭንቀት አትሸከም እሱ የአላህ ስለሆነ፣
ስለ እርዚቅም አትጨነቅ እሱም ከአላህ ስለሆነ
/channel/richyaneyena
"ሌባው" የመስጅድ ኢማም
=================
ባልና ሚስት ከረመዷን ወራት ባንዱ በሰፈራቸው የሚገኝ መስጂድ ኢማም የሆኑትን ሸይኽ ለፊጥራ ጋበዟቸው። ኢማሙም ግብዣውን በክብር ተቀበሉ። የቤቱ እማወራ የምግብ ማዕዱን ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ እያለች ሳለ ገንዘቧን ጠረጴዛው ላይ ጥላ ወደ ኩሽና አመራች። ፊጥራው ተጠናቀቀ። ኢማሙም ሄዱ። ሚስት ገንዘቧ እንደጠፋ አስተዋለች።
«ገንዘቡን የሰረቀው ማን ነው?» ተብሎ አይጠየቅ ነገር ባልና ሚስት ልጆች የሏቸውም። በወቅቱ ወደቤት የመጡት የመስጂዱ ኢማም ብቻ ናቸው። ውስጧ በጥርጣሬ ተናጠ። ታሪኩን ለባለቤቷ አጫወተችው። የመስጂዱን ኢማም እንዲያማክራቸውና ጉዳዩን እንዲያረጋግጥ ጠየቀችው። «ኧረ ነውር ነው ፤ ባይሆን ከኢማሙ ጋር የፈጠርነውን ግንኙነት አቋርጠን ፋይሉን እንዘጋለን እንጂ እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳት የማይታሰብ ነው» በማለት መለሰላት። ያም ቢሆን ባለቤቷ ኢማሙን ተከትሎ ሶላት ላለመስገድ ወሰነ።
ቀናት በንፋስ ፍጥነት ከነፉ። ቀጣዩ ረመዷን ገባ። ባል ከሚስቱ ጋር ተቀመጠ። «እንግዲህ የእዝነት እና የይቅርታ ወር ስለገባ ያለፈውን መርሳት አለብን። እንደምታውቂው ኢማሙም ቤተሰብ የላቸውም። ስለዚህ ዘንድሮም ቢሆን ፊጥራ ልንጋብዛቸው ይገባል» በማለት ሚስቱን ሹክ አላት። ሚስት ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ «በሃሳብህ እስማማለሁ፤ ነገር ግን የማስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። እርሱም የባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ ስለተሰረቀው ገንዘብ ጉዳይ በግልጽ እንድታወሩ እፈልጋለሁ» አለችው። እርሱም ባቀረበችው ሃሳብ ተስማማ።
የመስጅዱ ኢማም ግብዣውን ተቀብለው ከቤት መጡ። ፊጥራውን ከጨረሱ በኋላ የቤቱ አባወራ ጉዳዩን በይፋ አነሳው። ስለ ገንዘቡ ሁኔታ በቀጥታ ጠየቃቸው። ከፍተኛ የሀፍረት ስሜት ተሰማቸው። እንባቸው በጉንጮቻቸው ላይ ተንኳለለ። ካቀረቀሩበት ቀና አሉ። አይኖቻቸው የእንባ ቋጠሯቸውን እንደፈቱ ነው። ሚስት ፈጠን ብላ « ኢማም ሆይ! ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ?» በማለት ጠየቀቻቸው። «አዎ! ገንዘቡን ያነሳሁት እኔ ነኝ። ያስቀመጥኩትም የመጽሃፍት መደርደሪያው ላይ ከተቀመጠው ብቸኛ ቁርኣን ውስጥ ነው። እንባዬ የፈሰሰውም ረመዷንን ጨምሮ ለ 365 ቀናት ያህል የአላህን መጽሃፍ ገልጣችሁ አንድ ፊደል እንኳ አለመቅራታችሁ ገርሞኝ ነው» በማለት ምላሽ ሰጡ። በዚህ ጊዜ የቤቱ አባወራ በፍጥነት መደርደሪያው ላይ ወደተቀመጠው ቁርኣን አመራ። ገንዘቡንም የቁርኣኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ምዕራፍ መሃል ላይ ተቀመጦ አገኘው። ሚስት እንባዋ ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። ኢማሙን በክፉ በመጠርጠሯም ይቅርታ ጠየቀቻቸው። «ልጄ ሆይ! እኔ ደካማ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ ይልቅ አመቱን ሙሉ ቁርኣኑን ችላ በማለትሽ ይቅርታና ምህረት ከአላህ ጠይቂ» በማለት መከሯት።
እኛስ መቼ ይሆን ለመጨረሻ ጊዜ የአላህን ቃል ከፍተን ያነበብነው? 😢 ነፍሳችንን ሳንዋሽ እውነቱን ለራሳችን እንገረው❗ ወገኖቼ የአላህ ቃል እየጠራን ቢሆንም ችላ ብለነዋል።
ግዙፍ ስጦታ ቁስ ሳይሆን መልካም
ንግግር ነው በመጥፎ ንግግርህ
የሰበርከው ልብ ቁስ እንደ ስጦታ
በመስጠት ወደ ቦታው መመለስ
አትችልም ።
በጣም ጎበዝ ሆኜ ሳይሆን ከችግር ጋር ለረጅም ጊዜ ስለቆየሁ ነው።ጎበዝ የሆንኩት።
@richyaneyena
እኔ የማመሰግነው እምቢ ያሉኝ ሰዎች ነው። በእነርሱ ምክንያት ነው ሁሉንም ነገር በራሴ ማድረግ የቻልኩት።
ሁላችንም የተጎሳቆለ ልብስ እና ጥራት የሌለው የቤት እቃ የሚያሳፍረን ከሆነ የተጎሳቆሉ አስተሳሰቦች እና ጥራት የሌላቸው ፍልስፍናዎችም ሊያሳፍሩን ይገባል......እንግዴህ፣ ከውስጥ ካለው ስጋ ይልቅ ከላይ ያለው የስጋው መጠቅለያ የተሻለ ጥራት ያለው ከሆነ አሳዛኝ ሁኔታ ነው የሚሆነው።
@richyaneyena