@richyaneyena
የፍቅር በረካ
ገና በጅምሩ በአቦል ፍቅርህ ያኔ
እንቅፋት ቢመታኝ ልደፋልሽ እኔ
አቦል ፍቅርህ አልቆ ቶና ሲጣድማ
እያየሽ አትሄጂም ወልጋዳ ጠማማ
የባሰው መጣና በፍቅርህ በረካ
ስትሳል ሰማውህ ለሰፈርህ አድባር
ከትልቋ ዋርካ
ድፍት አርጋት እያልክ በመንገዱ ሳንካ
ታጥቦ ተለቅልቆ የጥላቻ አተላ
ፊቴ ሳይደፋ
ማቄን ጨርቄን ሳልል አንተ ካለህበት ከአጠገብህ ልጥፋ።🏃♀
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር።
Читать полностью…" ቢሆንም.... "
1 ሰዎች ( አብዛኞቹ) ስሜታዊ ናቸው ፣ ጥቅማቸው እንጂ አያሳስባቸውም ፣ ቢሆንም ውደዳቸው
2 መልካምን ስትሰራ ሰዎች በውስጥትህ የተደበቀ የእኔነት ስሜት እንዳለብህ ያሙሀል ፣ ቢሆንም መልካምን አድርግ
3 ስኬታማ ስትሆን አስመሳይ ጓደኞችን እና እውነተኛ ጠላቶችን ታፈራለህ ፣ ቢሆንም የስኬት ሰው ሁን
4 ዛሬ የምትሰራው መልካም ውለታ ነገ ይረሳል ፣ ቢሆንም ደግ ዋል
5 እውነተኛነትህ ና ግልፅነትህ ለትችት አሳልፈው ይሰጡሀል ፣ ቢሆንም እውነተኛ እና ግልፅ ሁን
6 ትላልቅ ሀሳብን የያዙ ታላላቅ ሰዎች በተራ ሰዎች ሊስተጓጎሉና ሊቆሙ ይችላሉ ፣ ቢሆንም በትልቁ አስብ
7 ሰዎች ደካሞችን ይወዳሉ ፣ አምባገነኖችን ይከተላሉ ፣ ቢሆንም ለደካሞች ስትል ታገል
8 ለአመታት የገነባሀው በአንድ ለሊት ሊወድም ይችላል ፣ ቢሆንም በግንባታህ ላይ ፅና
9 ሰዎች እርዳታህን በጣም ይሻሉ ፣ ስታግዛቸው ደግሞ አንተን ያጠቁሀል ፣ ቢሆንም እገዛህን አትንፈጋቸው
10 ለዚች ዓለም አንተ ዘንድ ያለውን ምርጥ ነገር ስታበረክት አንዳንዱ በመጥፎ ይመልስልሀል ፣ ቢሆንም ምርጥ ነገርህን አበርክት
@richyaneyena
*ምላስና ማህበራዊ ህይወት*
▪️ምላስ ስጋ ከመሆኑ ጋር ግን አጥንት ይሰብራል፤ ትንሽ ከመሆኑ ጋርም ብዙ ነገሮችን ያበላሻል፣ ባልና ሚስትን ያፋታል፣ ወላጅና ልጅን ያለያያል፣ ወዳጅን ከወዳጁ ጋር ያቆራርጣል፣ ሀገር ያፈርሳል፣ ከፍ ሲልም የአንድን ሰው ዱኒያና ኣኺራን ያበላሻል (ትርፍ ቃል ተናግሮ ያስገድላል- አካል ያስጎድላል፤ የኩፍር ቃል ተናግሮም ጀሀነም ያስወርዳል።
▪️ስለዚህ ሙስሊም ሆይ ምላስህን ከእባብ መርዝ የበለጠ ተጠንቀቀው ህይወትህን እንዳያበላሽ!
ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፣
قَال ابنُ تَيميَّة رحِمهُ اللهُ "المـَرأةُ إذَا طالَ لِسانُها؛ قَصُرتْ أيَّامهَا مَع زَوجِهــا)!" الفتَاوَى (٣٦٠ /٢٣)
"ሴት ልጅ ምላሷ ከረዘመ ከባሏ ጋር የምታሳልፋቸው ቀናቶች ያጥራሉ! (ቶሎ ይለያያሉ)"።
▪️ሙስሊም ከማንኛውም ሰው ጋር መልካም ንግግር ሊናገር የሚገባው ከመሆኑ ጋር ከቤተ-ሰቦቹን ዘውትር በተለያዩ ጉዳዮች ከሚገናኛቸው ሰዎች ጋር ሲሆን ይበልጥ ንግግሩን ሊያሳምርና ለቃላቱ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል።
አድማጭም የሰዎችን ንግግር በጥሩ ለመተርጎምና ለመረዳት ጥረት ማድረግና ከመጥፎ ጥርጣሬ መራቅ ይጠበቅበታል።
▪️አላህም በተከበረው ቃሉ ለነቢዩ ሙሐመድ ﷺ *("ለባሮቼ ከቃላቶች ውስጥ ይበልጥ ጥሩ የሆኑ ቃላትን እየመረጡ እንዲናገሩ ንገራቸው፤ ሸይጣን ለሰዎች ግልጽ ጠላት ነው በመካከላቸው ያሉ ግንኙነቶችን ያበላሻል")* ብሏቸዋል።
▪️ሸይጣን መጥፎ ቃላትን እንድንናገርና ጥሩውንም ቢሆን በመጥፎ እንድንረዳው በማድረግ መልካም ግንኙነቶቻችንን ማበላሸት ስለሚፈልግ በተቻልን ያክል
መልካምን ቃል እንጂ ባለመናገር በሩን እንዘጋጋበት።
*"መልካም ንግግር ሰደቃህ/ምጽዋት ነው*" ነቢዩ ሙሐመድ- صلى الله عليه وسلّم
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
@richyaneyena
በህይወትህ ውስጥ ጠንከር ያሉ ፈተናዎች ልያጋጥሙህ ይችላሉ
ተምረህ ምትፈተንበት ሳይሆን
ተፈትነህ ምትማርባቸው ስለዚህ
እንደዚህ አይነት ፈተናዎች
ጥንካሬነት ይለግሱሀል የመቋቋም አቅምህ ያዳብሩልሀል
ሁሌም ግን ፈተና ሲበዛብህ
ወደፊት መራመድን እንጂ ወደሗላ መመለስን እንዳትመርጥ።
@richyaneyena
የሰዎች ነገር ይገርመኛል አካሉ ለሞተሰው ያለቅሳሉ ልቡ ለሞተሰው
ግን አያለቅሱም…ኢማሙ ሻፊኢይ
አንዳንድ ሰዎች አሉ ከሩቅ
መልካቸው ልክ እንደ ብርቱኳን
ያምራል ስትጠጋቸው ደግሞ
ፀባያቸው ልክ እንደ ሎሚ ይመራል
ፈራን ፍቅርን ፈራን
እንዳልተዛመድን
እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን
ጉርብትና ናድን
እኛ ማለት ትተን
እኔነት ለመድን!
@richyaneyena
فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا
[ ሱረቱ አል-መዓሪጅ - 5 ]
መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡
إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا
[ ሱረቱ አል - ኢሻራሕ - 6 ]
ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
ዣንጥላ ዝናብን አያስቆምም፤
ግን በዝናብ እንድትቆም ይረዳሀል።
በተመሳሳዩ በራስ (መተማመን)
ለውጤታማነት ዋስትና አይሆንም፤
ነገር ግን ዓላማህን አንድትፈፅም
እድል ሊሆንህ ይችላል።
ከፍቅር…እዝነት ይገዝፋል
ምክንያቱም ፍቅር ተፈጥሮ ነው
እዝነት ግን ተሰጦበነው ምክንያቱም
ጨካኝም ማፍቀር ይችላል ማዘን ግን አይችልም።
@richyaneyena
አስተውል
ራስ መበደል።
በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሁነህ ራስ የመበደል ስራ አትስራ። ምክንያቱም ሻወር ሚጀምረው ከራስ ነው እንደ ሚባለው ሁሉ ራስህ መበደል የጀመርክ ቀን ነው ውድቀትህ ሚጀምረው። ራስ መበደል ማለት በራስ መተማመናችን ይገድልብናል። የምንሰራው ማንኛውም ስራ ያኮላሽብናል ሁል ጊዜ ጭንቀታም በመሆን ደስታ ይርቀናል ደስታ ራቀን ማለት የአላስፈላጊ በሽታዎች በሰባ መሆናችን አይቀሬ ነው። እራሳችን እየረሳን ስለ ሰዎች ህይወት ማንነታችን ሽጠን ሳንወድ በግድ አዕምሮዋችን የአስተሳሰባቸው ባሪያ እናደርገዋለን። ይህ ማለት ደግሞ የራሳችን ደስታ ገድለን ለሰዎች ደስታ እንኖራለን ማለት ነው። ራሳችን መበደል ስንጀምር ለሳራችን ክብር መስጠት እናቆማለን መልበስ፣መዘነጥ፣መደሰት፣ከኢባዳ መራቅ ወዘተ ቀስ በቀስ ከእኛ እየራቁ ይሄዳሉ።ራስ መበደል የጀመርን ቀን ኪሳራ ውስጥ እንደሆንን ሊገባን ይገባል።
@richyaneyena
አንዳንድ ሰዎች ልክ እንደ አስለቃሽ
ጭስ ናቸው በመጥፎ ማንነታቸው
ድንበር በማለፍ ልብህን እየሰበሩ
ያስለቅሱሀል።
@richyaneyena
ጤነኛ ሆኖ እንዲኖር እንደ መድሀኒት
ሁሌም ሰበብ እየሆንክለት እሱ ግን የመታመምህና በሽተኛ የመሆንህ
ሰበብ የሚሆንም በሽተኛም ሰው አለ።
@richyaneyena
"መሪነት ስልጣን ሳይሆን ኃላፊነት ፤ ገዥነት ሳይሆን አገልጋይነት ፤ ድሎት ሳይሆን መስዋዕትነት ነው ።"
በሰዎች ላይ ጉልበትህን
እንጂ እውቀትህን አትቆጥብ። ጉልበት አላቂ ነው እውቀት ግን አያልቅም።
الَّذِينَ يُنفِقُونَ فِي السَّرَّاءِ وَالضَّرَّاءِ وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ
[ ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 134 ]
ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡
@richyaneyena
ለምንወዳቸው ሰዎች ብለን
ከብዙ ሰዎች ጋር እንርቃለን
በስተ መጨረሻ እነሱም ለሚወዱት
ሰው ብለው ከኛ በመራቅ
ልባችንን እንደሌለ አድርገው ይሰብሩታል………..💔
@richyaneyena
مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ يَهْدِ قَلْبَهُ ۚ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
[ ሱረቱ አልተጋቡን - 11 ]
ከመከራም (ማንንም) አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን (ለትዕግስት) ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
ሱብሀን አላህ ጊዜው እንዴት ይከንፋል ነገ ረጀብ 1 ይሆናል እና "አላሁመ ባሪክ ለና ረጀብ ወ ሻእባን ወበሊግና ሸህሩ ረመዳን! በዱዓም በኢባዳም እየበረታን !
Читать полностью…ጨካኝ እዝነት የለውም
ምቀኛ እረፍት የለውም
ውሸታም ክብር የለውም
ከሀዲ ጓደኛ የለውም
ችኩል ትርፍ የለውም
ንፉግ ደስታ የለውም።
@richyaneyena
አንድን ሃገር ለማጥፋት የኒውክሌር ቦምብ ወይም ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል አያስፈልግም። የትምህርት ጥራቱን ዝቅ ማድረግ ብቻ ይበቃል።
ያኔማ
ህመምተኞች በቀሽም ዶክተሮቻቸው እጅ ይሞታሉ
ህንፃዎች በማይረቡ መሃንዲሶች እጅ ይደረመሳሉ
ገንዘብ በአላዋቂ ኢኮኖሚስቶች እጅ ይባክናል
የሰው ልጅ መንፈስ በሆዳም የሃይማኖት አስተማሪዎች እጅ ይላሽቃል
ፍትህ በኢፍትሃዊ ዳኞች እጅ ይበደላል።
የትምህርት ጥራት መውደቅ የሃገርም መውደቅ ነው።
@richyaneyena
የመናገር ብቃት ብቻ
ሳይሆን ዝም የማለትም
ብቃት ይኑርህ...
ቦንብም ይጮሃል ቆርቆሮም ይጮሃል። ነገር ግን ስራቸው ለእየቅል ነው። ቆርቆሮ በነካኸው አጋጣሚ ሁሉ ይጮሃል ጉዳት ግን አያደርስም። ቦንብ በምትፈልገው ውስን ቦታ ብቻ ይጮሃል አደጋ ያደርሳል። ስለዚህ ብዙ ሰው ቆርቆሮ ሳይሆን ሚፈራው ቦንብ ነው። አንተም ዝምታህ እንደ ቦንብ ይሁን።
@richyaneyena
ከሰዎች ሳይሆን ከትላንት
ማንነትህ ተፎካከር ምክንያቱም
ከሰው ሗላ ያስቀረህ ሰው ሳይሆን
የትላንትናው መጥፎ ማንነትህነው
የአእምሮ ውበት አዳዲስ ሃሳቦች
ማፍለቅ ነው። የምላስ ውበት
ዝምታ በማብዛት ነው። የንግግር
ውበት ደግሞ ሀቅ እውነት መናገር ነው!
@richyaneyena