የቀድሞ የኢህእዴግ ምልምል የመጅሊስ ሰዎች አሁንም ከጀርባ ውሳኔ እየሰጡ መሆኑ ተሰማ
-------RN05------
.
የአዲስ አበባ መጅሊስ በአዲስ ከተማ የሚገኘውን የሙስሊም መቃብር እንዳያጸዳ በክፍለ ከተማው ደህንነት መታገዱ ተሰማ፡፡
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘውን የእስላም መቃብር እንዳያስመነጥር በክፍለ ከተማው ደህንነት መከልከሉን የአር ኤን ታማኝ ምንጭች አረጋግጠዋል፡፡
.
እንደምንጮቻችን ከሆነ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የደህንነት ሃላፊ አቶ አስራት በተለምዶ እስላም መቃብር በመባል የሚታወቀውና እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ የሚገኘውን ጫካ በማስመንጠር አካባቢውን ለማጽዳት ያደረገው እንቅስቃሴ በመንግስት ደህንነት እንደታገደ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
.
አዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የመቃብር ቦታው ጫካ ከመሆኑ ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ የደህንነት ስጋት መሆኑን ተከትሎ ነው ለማስመንጠር የተነሳሳው፡፡
አካባቢው ለበርካታ አመታት ሳይመነጠር ጫካ ከመሆኑ የተነሳም ለበርካታ ወንጀለኞች መደበቂያ ዋሻ ሆኖ ያገለግላል በሚል በተደጋጋሚ ሪፖርቶች መቅረባቸውን ተከትሎ ነው ም/ቤቱ ቦታውን ለማጸዳት እንቅስቃሴ ያደረገው አድርጎ የነበረው ።
.
የም/ቤቱን እንቅስቃሴ የክፍለ ከተማው ደህንነት ሃላፊ አቶ አስራት ያገዱት የቀድሞው የህዋሃት መራሹ መንግስት የክፍለ ከተማው መጅሊስ ሹመኛ ሸህ ሰኢድ የመቃብር ቦታው እንዲጸዳ ፈቃደኛ አይደሉም በሚል ምክንያት እንደሆነም ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
.
የደህንነት ቢሮ ሃላፊው የቀድሞው የክፍለ ከተማው መጅሊስ ሸህ ሰኢድ ከእኛ ጋር የደህንነት አባል ሆነው እየሰሩ በመሆኑ ያለእሳቸው ፈቃድ በክፍለ ከተማው ውስጥ የሚሰራው ስራ አይጸድቅም የሚል ምላሽ እንደሰጡም ከታማኝ ምንጮቻችንን ለማወቅ ተችሏል።
.
የደህንነት ቢሮ ሃላፊው የቀድሞው የህወሃት መራሽ የመጅሊስ ሹመኞች ከመንግስት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማው የቀድሞ ሹመኛ ፈቃድ ካልሰጡ የመካነ-መቃብር ጽዳቱ እንደማይከናወን አስረግጠው ተናግረዋል።
.
በአንድ በኩል ከፍተኛ ም/ቤቱን የክፍለ ከተማው የቀድሞ የመጅሊስ ሹመኞች ስለመነሳታቸው ደብዳቤ እንዲጽፉ የጠየቀው የደህንነት ቢሮው በሌላ በኩል በሙፍቲ ሃጂ ኡመር ሃምሌ 19/2013 የተጻፈው የቀድሞው የክፍለ ከተማ መጅሊስ አመራሮች ወደስልጣናቸው እንዲመለሱ በጻፉት ደብዳቤ መሰረት ወደስልጣናቸው ተመልሰዋል የሚል ሃሳብ አንጸባርቋል።