radionegashi | Другое

Telegram-канал radionegashi - Radio Negashi Channel

24

Radio Negashi Broadcastig Channel

Подписаться на канал

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/r8UoDnIArhA

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/WAyPwmY_gNE

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/Rs3MKFyD5Tg

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/yhdIV0mDY24

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/1Yyu-y3lgts

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

👉ድጋፍ እና ነቀፌታችን ነግያችንን በማያበላሽ እና የሃገራችንን እና የአለም አቀፍ ህግ ድንበሮችን ባከበረ መልኩ ቢሆን!
👉ብልጽግናም ህወሃትም አላፊ ናቸው ደርግም ፣ አጼዎቹም እንዳለፉት ሁሉ ! ህዝባችንን በጋራ ብንታደግ!! ንጹሃን ህዝብንና ተፋላሚን ብንለይ!!
.
----- የአቅል አይምሮ ትዝብት ለ RN05---
.
የኢሳት ባልደረባ ስትሆን እና እንደ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ሲሳይ አጌና "ምርጥ እና የተለየህ ኢትዮጵያዊ" ነህ ተብሎ ሲነገርህ፣ የኤርትራንም ሆነ እሺ ያልህን ጦር ሁሉ አስገብተህ ቁረጠው፣ በጅምላ ደብድበው ፣ የትግራይን ህዝብ እንዳለ በኢኮኖሚ አስቃየው ስትል ትቆይና መንግስትም ያልከዉን ሁሉ ፈጽሞ ዉጤታማ ሆነህ የደስ ደስ ሻምፓኝ ከፍተህ ላይፍ ስትጨፍር ከርመህ ድንገት ቀና ስትል ነገሩ ሁሉ ባንተ ልክ አለመሆኑን ስታይ "ትግራዋይ የተባለዉን ሁሉ ሰብስበህ ማጎርያ (concentration camp) ዉስጥ ክተተው " ብለህ እንደ መሳይ መኮንን ሌላ ገራሚ ትዕዛዝ ትሰጣለህ!
.
አቶ መሳይ እንዲህ ነበር የጻፈው
----
" ጥብቅ መልዕክት ለመንግስት!
አሁንም አልረፈደም። የትግራይ ተወላጆችን፣ ከህወሀት ጋር ግንኙነት የሌላቸውንም ቢሆን በጊዜያዊ ማቆያ(concentration camps) ጣቢያዎች እንዲሰባሰቡ ማድረግ ያስፈልጋል። አሜሪካን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት፣ ወደ ጦርነቱ ከመግባቷ በፊት በሀገሯ የሚኖሩ የጃፓን ዜጎችን በሙሉ ወደካምፕ አስገብታ ነው የጃፓን ወራሪንና የሂትለርን ጦር ማሸነፍ የቻለችው። ጃፓኖችን በብብቷ ስር ወሽቃ ወደ ጦርነቱ መግባት የሽንፈት መጀመሪያ መሆኑን በመረዳቷ እርምጃውን ወስዳለች። ኢትዮጵያም ከዚያ የከፋ አደጋ ውስጥ ናት። የደሴው ግብግብ ዋናው ተዋናይ ከህዝቡ ጋር አብረው የሚኖሩት የህወሀት ደጋፊዎች መሆናቸው በስፋት ታምኗል። እነሱን በጉያ ይዞ ጦርነቱን ማሸነፍ በፍጹም የሚቻል አይደለም። ለእነሱም ደህንነት ተብሎ እርምጃው በአስቸኳይ ሊወሰድ ይገባል።
መሳይ መኮንን"
------
ይህ በድፍረት ብቻ የሚናገር የጦር እና የአለም አቀፍ ህግን የማያውቅ፣ የሰላም እና የጦርነት ወቅት ባህሪዎችን ብሎም በጠላት ላይ ስላለው መብት እና ግዴታ እንዲሁም በጦርነት ወቅቶች ያሉ የሲቪል ዜጎችን የሚመለከቱ ቀይ መስመሮችን ያልለየ ጋዜጠኛ ይህ አባባሉ ምን ሊያመጣበት እንደሚችል እንኳን በቅጡ የተረዳ አይመስልም፡፡
.
አንዳንድ የዋሆች ድርጊቶች እንጂ ንግግሮች በአለም ፍርድ ቤት የሚገትሩ መሆናቸዉን ልብ አይሉትም! ሃላፊነት እንደሚሰማው እና ብዙ ሰው እንደሚከተለው ጋዜጣኛ እንዲህ አይነት ንግግሮቹን ሲናገር ጭብጨባዉን ወይንም ከመንግስት በኩል የሚመጣን ዳረጎትን ብቻ አይቶ ከሆነ እጅግ የዋህ መሆኑን ሊረዳ ይገባል፡፡
.
ሌሎችም የኢሳት አይነት ሚድያ ላይ ያሉ ጋዜጠኞች ራሳቸዉን እንደምርጥ እና ብቸኛ ታማኝ ኢትዮጵያዊ አድርገው ስለሚቆጥሩ የሚናገሩት እና የሚሰሩትን ነገር ከካድሬነት ምህዳር ዉጭ በሃገር ዉስጥ እና በአለም አቀፍ ህግጋት መነጽር ሲፈትሹ አይታዩም!
.
የሚገርመው እነደነዚህ አይነት በእውቀት ሳይሆን በስሜት የተሞሉና በመንግስት ወይንም በጭብጨባ እውቅና የተቸሩ ሰዎች በሚናገሩት እና በሚሰሩት ነገር ሰበብ ነገ ሊላው የማህበረሰባችን ክፍል ምን አይነት ችግር ዉስጥ ሊገባ እንደሚችል ለማሰብ አልታደሉም!
.
ወንጀለኛን በወንጀሉ ልክ በህግ መቅጣት እንጂ የደቦ ፍርድ ያዉም በግልጽ በሚድያ በጽሁፍ እና በድምጽ ማስተጋባት አላዋቂነት ካልሆነ በቀር ሌላ ሊሆን አይችልም!!
.
ጀርመኖች በሂትለር ፣ጣልያኖች በሙሶሎኒ ጠያፍ ስራዎች እስከዛሬ እንደሚሸማቀቁት ሁሉ አሜሪካኖች እስከዛሬ የሚያፍሩበት፣ የሚወቀሱበት እና የሚሸማቀቁበት ፣ በ2ኛው የአለም ጦርነት ወቅት "ጃፓናዊ አሜሪካዊያኖችን" ሳይቀር ወደ 120 ሺ የሚጠጉ የጃፓን ዝርያ ያላቸዉን ዜጎች በጅምላ በማጎርያ ጣብያ (concentration camp) ያጎሩበትን፣ በኋላም በ1988 ሮናልድ ሬጋን በይፋ በአሜሪካን መንግስት ስም ይቅርታ እንዲጠይቁና ከፍተኛ ካሳ እንዲከፍሉ የተገደዱበትን አሳፋሪ ታሪክ ትክክል ነበር ብሎ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዲፈጸም መስበክ አስደንጋጭ የሚሆነው የዚህ አይነት ሰዎችን አምኖ የሚኮለኮልላቸዉን እና አምኖ የሚደግፋቸውን ሰው "ምንም አያገናዝብም" በሚል ምን ያህል እንደሚንቁት ማሳያ ነው፡፡
.
ይህ ኢትዮጵያዊያንን በብሄር፣ በሃይማኖት፣ በአመለካከት እና በተለያዩ መገለጫዎቻቸው "እየለየህ በጅምላ አጉረው!" ማለት የጀመሩ ሃላፊነት የማይሰማቸው ሰዎች ነገ ሂትለር በጁዎች ላይ እንዳደረገው "በጅምላ ፍጃቸው" ከማለት የማይወገዱ መሆኑን ከአካሄዳቸው መረዳት ይቻላል፡፡
.
በሃገር ስም ለሚቀያየሩ መንግስታት ብለን ከመስመር ባፈነገጠ መንገድ የምንሰጣቸው ድጋፎች ነገ በህዝባችን ላይ የሚያስከትሉትን ጦሶችን ቀድሞ ማስላት የብልህነት ምልክት ነዉና በሁሉም በኩል ያላችሁ ካድሬዎች አለቆቻችሁን ስትደግፉ አንደኛ በሃገር ስም ባይሆን ፣ ሃገር ሲባል ሰፊ ነዉና ፣ሁለተኛም ለነገ ሌላ ማጥ ዉስጥ በማይከተን መልኩ በጭብጨባ እና በባለስልጣናት ሙገሳ ላይ ባልተመሰረተ መንገድ ቢሆን ይመረጣል፡፡
.
ምክር ለአቶ መሳይ / ባሁኑ ወቅት ያለኸው ኢትዮጵያ ስለሆነ (ካልተመለስክ) ይህንን አድርጉ ያንን ፍለጡ ቁረጡ ከማለት እና መንግስትንም አሳስቶ ካንተ ባለፈ ሌላ አለማቀፍ የጦር ወንጀል ዉስጥ እንዲገባ ከማድረግ ብሎም ሃገራችን እና ህዝባችን ከማይወጡት ተከታታይ የበቀል አዘቅጥ ዉስጥ ከመክተት ለሃገርህ ባለህ "ልዩ ፍቅር" ሁሉንም ትተህ መሳርያ አንግተህ መከላከያዉን አልያም የአማራ ልዩ ሃይሉን ያም ካልተመቸህ ፋኖን ማገዝ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ!

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

የመንግስት Plan B (እቅድ 2) "ሲቪሉን ህዝብ ገብተህ ተጨፋጨፍ" የሚል ሊሆን አይገባም!
----- የአቅል አይምሮ ትዝብት ለ RN05-----
.
በትላንትናው እለት የፌደራል እና የክልል መንግስታት መሪዎች ባህርዳር ከተማ ተገናኝተው ወቅታዊዉን ጦርነት በማስመልከት ግምገማና ቀጣይ እቅድ ባወጡበት ስብሰባ እንደ ፕላን B (እቅድ 2) የሚመስል ዉሳኔ አስተላልፈዋል፡፡ ከመግለጫቸው መሃልም በዋናነት
.
"ሕወሃት የጀመረውን ሀገር የማውደም እና የማፍረስ ተልዕኮ በመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት ብቻ መቀልበስና መቅበር አይቻልም። መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በማነቃነቅና ባለቤት በማድረግ የአገርን ህልውና ከሁሉ አቀፍ ጥቃት መከላከል ያስፈልጋል፡፡" የሚል ይገኝበታል፡፡
.ማንኛዉም ጦርነትን የሚያካሂድ አካል እቅድ አንድ እና ቢያንስ ተጠባባቂ እቅድ 2 ይኖረዋል፡፡
የተሻለ ወታደራዊ እቅድ ማዉጣት የሚችሉ ደግሞ ከዛም ያለፉ እቅድ 3 እና ከዛም በላይ ይኖሯቸዋል፡፡
.
አሁን ባለው የሀገራችን የእርስ በእርስ ጦርነት በመንግስት በኩል በ 5 ቀናት ያልቃል የተባለው ጦርነት አመት ሙሉ ሲወስድ ነገሮች እየከበዱ እንደሚመጡ ከመገንዘብ ይልቅ በአሸናፊነት ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ የቆየው የመንግስት የጦር እቅድ 1 (Plan A) አለመስራቱ ሲታወቅ በ Plan B (እቅድ 2) ነት የቀረበው ሃሳብ የተሻለ የሰራዊት እና የአደረጃጀት ቁመና ወይንም ቢያንስ ጠንከር ባሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ የድርደር ሃሳብ አይደለም፡፡
.
ከዛ ይልቅ በመከላከያ እና በተለያዩ አደረጃጀቶች፣ ድሮኖችን ጨምሮ በከፍተኛ የጦር መሳርያ ሲካሄድ የነበረዉ ጦርነት ቃል በቃል በቂ እንዳልሆነ እና ለዉጤት እንደማያበቃ ካመኑና ከገመገሙ በኋላ የደረሱበት የእቅድ 2 (Plan B) ዉሳኔ አሁን ህዝቡ ከደጀንነት ብሎም ከምልምል ሰልጣኝ ወታደርነት አልፎ በነቂስ ወጥቶ ደረቱን ለጥይት እንዲሰጥ እና እንዲሰዋ በዚህም "ሀገሩን እና መንግስቱን" እንዲጠብቅ የሚያል ትርጓሜ ያለውን መመርያ ነው፡፡
.
ይህ በሂደት ህዝቡን እያፈሱ ወደ ጦር ሜዳ መዉሰድን የሚያስከትል እና በከፍተኛ ትጥቅ እና ወታደራዊ አቋም ላይ ካለ አካል ጋር ህዝቡ ያገኘዉን ነገር እያየዘ በብዛት ግን ባልተመጣጠነ የጦር ቁመና በገፍ እንዲያልቅ የሚያደርግ አደገኛ ዉሳኔ ነው፡፡
.
ይህ ዉሳኔ በመንግስት ኪሳራ ህዝብ መዳን ሲገባው ፣ በተገላቢጦች "በህዝብ ኪሳራ መንግስትን ማዳን" ወደሚል አደገኛ መንገድ ስለሚያመራ ውሳኔው ለድል የማያበቃ ብቻ ሳይሆን ህዝብን ለከፍተኛ እልቂት የሚዳርግና የሀገርንም ህልውና ክፉኛ የሚፈታተን ነው፡፡
,
ለሀገር እና ለህዝብ የሚያስብ መንግስት በዚህ ሁሉ በጀት፣ በዚህ ሁሉ ጦር እና የሰለጠነ መከላከያ የሚያካሂደው ጦርነት "አያዛልቀንም" ፣"ለድል አያደርሰንም" ብሎ ከገመገመ እንግድያው ለራሱ ህልዉና መጨነቁን በመተው ሀገር እና ህዝብን የሚያድንበትን ሰላማዊ ሃሳብን እንደ እቅድ 2 (Plan B)ለማቅረብ ቢተጋ እና የድርድር መንገዶችን ቢከፍት እንጂ ይህንን "ዱላ እና ጎራዴ ወይንም ቢላ እየያዝክ ተቀላቀል" የሚል እንደምታ ያለዉን ዉሳኔ ወታደራዊ አማራጭ ብሎ ሊጠቀም ከቶ አይገባም!

https://www.facebook.com/RNZeroFive/posts/4421834001185693

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

ጠያቂው በራሱ ጥያቄ ቢጠየቅ!!! ኢዜማ ወ ጠ/ሚ አብይ አህመድ
------ @የአቅል አይምሮ ትዝብት ለ RN05----
.
ኢዜማ ጠ/ሚ አብይ አህመድን ፓርላማ ቀርበው በጦርነቱ ዙርያ እንዲያብራሩ እና ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሾችን እንዲሰጡ መጥራቱ ተሰምቷል፡፡ በመሰረቱ ይህ ከአንድ የፓርላማ አባል የሚጠበቅ እና ለሌሎቹም አር አያ የሚሆን ነው!
.
ሀገር በጦርነት ስትታመስ ዜጎች ሲረግፉ፣ ረሃብ እና ስደት የህዝባችን የእለት ተእለት የህይወት ክፍል ሲሆን መንግስትን ጠርቶ ቃልህን ስጥ ማለቱ ታድያ ፓርላማ ወይንም ተገዳዳሪ ፓርቲ ለዚህ ወቅት ካልሆነ ለመቼ ነው የሚያሰኝ ነው፡፡
.
ኢዜማዎች በጥሪያቸው ላይ ጠ/ሚንስትሩ ጦርነቱን መች እንደሚያገባድዱ፣ ሃገሪቷም ዳግም እንዲህ አይነት የጦርነት ቅዋሴ ዉስጥ እንዳትገባ ምን አይነት ስራ እየሰሩ እንደሆነ መተው ተጠየቅ ሊባሉ እንደሆነ ነው የሚያብራራው፡፡
.
እንግዲህ ጠ/ሚሩ ጥሪዉን ተቀብለው ከቀረቡ ሂደቱን የምንከታተለው ይሆናል፡፡
ከዛ ባለፈ ግን “ኤርትራን የህልዉናችን ማሰርያ ናት” እስከማለት የደረሰው የኢዜማ የጦርነት አጋፋሪነትን አመራሮቹ ምላሽ እንዲሰጡበት ለነሱም ሌላ አካል ደብዳቤ መጻፍ ሳያስፈልገው የሚቀር አይመስልም፡፡
.
ይህ ጦርነት የጠ/ሚንስትሩ እዳ ብቻ ሳይሆን ከኢዜማ ጀምሮ ብዙ "ተጠየቅ" ሊባሉ የሚገባቸው ባለ እዳዎች መኖራቸው ሊዘነጋ አይገባም!
.
ባጭሩ ጠያቂውም ከመጠየቅ አይድንም ነው! https://www.facebook.com/RNZeroFive/posts/4409782925724134

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/tQo1ovf8Wng

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/0Iq6x2yIQQM

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

የወለዬ እናቶች እምባ! ከትግራይ እናቶች የቀጠለ የመላው ሃገራችን እናቶች እምባ ነው! ኑ! በጋራ እናብሰው!
------
@የአቅል አይምሮ ት ዝብት ለ RN05

አንዳንዶች መንግስትን ለምን ትወቅሳላችሁ ሲሉ ይሰማል፣ ታድያ እነዚህ እናቶች አቤት ማለት ያለባቸው ለTDF ወይንም ለኦሮሞው ጦር ነዉን?
.
ከዛ ይልቅ
👉አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠህ ስለ ጦርነት ልትፈላሰፍ ትችላለህ
👉ጎጃም ዉስጥ ተደላድለህ እና ገጥመን መስሎኝ ልትል ትችላለህ
👉ኦሮምያ ዉስጥ ሆነህ ገንዘብ በማዋጣትህ ጦርነቱን የተሳተፍክ ሊመስልህ ይችላል
👉ደቡብ ሆነህ ሰንጋ ስላዋታህ ለሃገርህ እና ለህዝብህ መቶ ጊዜ የሞትክ ሊመስልህ ይችላል
👉ዉጭ ሃገር በሰላም እየኖርክ "ጁንታዉ እና ኦነግ ሼኔ አስቸገሩት፣ አዉሮፓ እና አሜሪካን ሴራ እየሰሩበት ነው እናም ብርቅዬ መንግስታችንን አትውቀሱት ይልቅ ዝም ብላችሁ ታገሱት ምን ያድርግ? ድሉ ቅርብ ነው!" ልትል ትችላለህ

ሌላም ሌላም
.
የወሎ እናቶች ግን ልጆቻቸዉን ከቀበሮ እና ከጅብ ለመታደግ ሌላ የህይወት ህልዉና ዉስጥ ገብተዋል!
.
ለዚህ መፍትሄው በአስቸኳይ ጦርነቱን ማቆም እና የንግግር ፖለቲካን መጀመር ነው፡፡ ያኔ ነው እናቶች ወደቅዬአቸው ተመልሰው እፎይ የሚሉት!
.
የእርስ በርስ ጦርነት ሁሌም ተጠቃሚ የሚያደርገው ጥቂቶችን እንጂ ብዙሃኑ ህዝባችንን አይደለም! ብዙው ሞቶ እና አልቆ ጥቂቶች ያንን እየዘከሩ ፣ዝና፣ ሃብት፣ ስልጣን የሚያገኙበት በአጠቃላይ በአንዱ ሞት ህይወታቸዉን የሚቀጥሉበት ነው!
.
"የተፈናቀሉትን እንደጉማቸው ነገር ግን ጦርነቱ ይቀጥል" የምትሉ ወገኖች የህዝባችንን መሰረታዊ ችግር ከምንጩ ለማጥፋት ፍላጎት እንደሌላችሁ እና በዉስጣችሁ ያለው ጥላቻ እና እልህ ይበርድ ዘንድ ወገኖቻችንን ለተራዘመ ሰቆቃ እየዳረጋችሁ መሆኑን መገንዘብ ያሻል!
.
ጎበዝ #ጦርነት_አይበጀንም የምንለው በማሸነፍ እና በመሸነፍ ጉንጭ አልፋ ትንተና ዉስጥ ሆነን ሳይሆን ህዝባችንን ለሰቆቃ ሃገራችንን ለመፈራረስ እንደሚዳርግ የሃገራችን እና የአለም ተሞክሮን ስለምንገነዘብ ነው!
.
ሀገር በህግ እና ህዝብን ለአደጋ በማያጋልጥ መርህ እንጂ በቂም እና በበቀል እና በመንፈሳዊም ሆነ አለማዊ ተስፋ አይመራም!

ጊዝያዊ ፍጆታን በመለገስ ብቻ ሳይሆን፣ሰላምን በመስበክ እና ጦርነትን በመቃወም የወለዬ እናቶችን እንባ! በአስተማማኝ እናብስhttps://www.facebook.com/RNZeroFive/videos/471705410694987/

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/BLIN-GDDcs0

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/3kffAtisj0E

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/rl_T7virCDE

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/URMdWyCNNsQ

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://www.facebook.com/144633445572458/posts/4490247127677713/?sfnsn=scwspmo

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

👉ግለሰቦች በማንነታቸው ሳይሆን በተጠረጠሩበት ወንጀል ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ተገለጸ
👉በከተምዋ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በበኩላቸው ይህ ሃሰት ነው ብለዋል
-------------------------------------------------------
RN05 / ኅዳር 3.2014 (12.11.2021)
.
በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ባለው የከተማውን ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ ግለሰቦች በማንነታቸው ሳይሆን በተጠረጠሩበት ወንጀል ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝና በከተማዋ ከተመዘገቡት ከ23ሺ በላይ መሳሪያዎች ውስጥ 42 በመቶ ፍቃድ እንደሌላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ዮናስ ዘውዴ ገልጸዋል።
.
እየተያዙ የሚገኙት ብሄርንና ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው በሚል እየተነገረ የሚገኘው ወሬ መሰረት የሌለው መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው፤ እየተካሄደ የሚገኘው አገርን የማዳን ሥራ ነው፣ ተጠርጣሪዎች ንጽህናቸው ከተረጋገጠ ለተንገላቱበት ይቅርታ እየተጠየቁ ይለቀቃሉ ብለዋል። ወቅቱ አገርን ለማዳን በሚደረግ ርብርብ ላይና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በመሆኑ የጸጥታ አካላት የተጠናከረ የጸጥታ ሥራ እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ በተደረገውም አሰሳ አሸባሪን ሲደግፉ፣ መረጃ ሲሰጡና ገንዘብ ሲያዘዋውሩ የተገኙ መኖራቸውን ጠቁመዋል ሲል የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዘግቧል ፡፡
.
አቶ ዮናስም ሆነ ሌሎች ባለስልጣናት በከተማዋ ማንነት እና ብሄር ላይ ያተኮረ እስር እና እንግልት የለም ይበሉ እንጂ በአዲስ አበባውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በየእለቱ በማንነታቸው ብቻ እየታሰሩ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ::
.
በተለይም በመርካቶአካባቢ ፖሊሶች ያለ ማዘዣ በመምጣት የንግድ ሱቆቻቸውን እየበረበሩባቸው መሆኑንና ከዚህ በተጨማሪም በሚያሳፍር ሁኔታ ከፖለቲካ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው የሚታወቁ ቤተሰቦቻቸው እስር እና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነም ጠቁመዋል አፈሳው ከእለት ወደ እለት በመጨመሩ ሳቢያም በርካቶች በስማቸው ምክንያት ብቻ ከቤት በነጻነት መውጣት እንዳልቻሉም ይናገራሉ ለአብነትም መወልወያ በመሸጥ የሚተዳደሩ ቤተሰቦቿ የተያዙባት ግለሰብ እንደተናገረችው ከሆነ እየተሰራ ያለው ነገርእጅግ አሳፋሪናሚዛናዊነት የጎደለው እንዲሁም ከመንግስት የማይጠበቅ ድርጊት ነው ስትል ኮንናዋለች::
.
በተመሳሳይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በግለሰባዊ ማንነቱ የታሰረ አንድም ሰው የለም ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሁኔታውን አስተባብለዋል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ይህንን ያሉት ከአልጀዚራ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሲሆን ህጻናትና ሴቶችም በእስሩ ላይ አሉበት ይህ ለምን? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም ህጻናት እንዳሉበት መረጃው የለኝም ያሉ ሲሆን መረጃን መሰረት በማድረግ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እና ፍተሻ እንደሚደረግና ፖሊስ በሚያደርገው ምርመራ ግለሰቦቹ ነጻ ከሆኑ እንደሚለቀቁ ተናግረዋል ተጠርጥረው የተያዙ የመንግስታቱ ድርጅት እና የአለም ምግብ ፕሮግራም ሰራተኞችንም በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደሩ ተገቢው ምርመራ ተደርጎ ነጻ ሆነው ከተገኙ እንደሚለቀቁ አስረድተዋልhttps://www.facebook.com/RNZeroFive/posts/4463423737026719

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

ተጠባበቁን!

ከዛሬ ባሻገር!
----------
.
ሀገራችን ዳግም "የአሸናፊዎች ፍትህ" ይገጥማት ይሆን? በሚል መወያያ ርዕስ ልዩ የራድዮ የቀጥታ ስርጭት ይኖረናል!
.
እንግዳችን ኢኮኖሚስት የፖለቲካ ተንታኝ እና ጸሃፊ ናቸው!
.
ብዙዎች ያለፈው ላይ ተሰንቅረው ዛሬያችንን አበላሽተዋል ፣ ሊሎች ነገን የዘነጋ ዛሬን ለማስታመም ይተጋሉ! እኛ ስለነግያችን አሻግረን እናስባለን!
.
ትላንት ምን አበላሸን? ዛሬስ ምን እየዘራን ነው ? ነገስ ምን ልናጭድ እንችላለን? ብለን እንጠይቃለን!
.
ለመሆኑ ስለ አሸናፊዎች ፍትህ ያውቃሉን? እንግድያው የሚያዉቁትን ይጻፉልን!
.
ይምጡ አብረዉን ስለነገው ይምከሩ!
.
ዛሬ ሀሙስ በኢትዮ ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ

RN05

---------------------------------------------------
አዲሱን ዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ:
https://www.youtube.com/c/RN05channel
ቴሌግራም: /channel/RNZeroFive
FB: www.facebook.com/RNZeroFive

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

ተጠባበቁን
---RN05---

ከረዳት ተመራማሪ ኢብራሂም አብዱ እና ከአክቲቪስት እና ጋዜጠኛ ኢሳቅ እሸቱ (Talk Ethiopia with Isaac - ቶክ ኢትዮጵያ) ጋር በመሆን ወሎን በጦርነቱ መነጽር የምንመለከትበት / የሀገራችንንም ነባራዊ ሁኔታ የምንቃኝበት ዝግጅት ይጠብቃቹሃል!

በዛሬው ምሽት ተጠባበቁን!! RN05
---------------------------------

አዲሱን ዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ:
https://www.youtube.com/c/RN05channel
ቴሌግራም: /channel/RNZeroFive
FB: www.facebook.com/RNZeroFive

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/3ufXE9L0gL4

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://www.facebook.com/144633445572458/posts/4422975914404835/?sfnsn=scwspmo

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/F5s1PPVTHfQ

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://www.facebook.com/144633445572458/posts/4405088402860253/?sfnsn=scwspmo

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/9Ch6l7j6qw8

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/qjg_dBPU_ws

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/vpR4Abyx9IM

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://www.youtube.com/watch?v=V2qP3vJPs2c

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/ue0Wzpq_JwI

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

@ የአቅል አይምሮ ትዝብት ለRN05

ጋዜጠኞች በሰላሙ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በጦርነትም ወቅት አስፈላጊ ናቸው፡፡ እንደዉም የኛ ሃገር ጦርነት የተድበሰበሰ እና በወገን እና በሃገር ላይ እየደረሰ ያለው በትክክል ምን እንደሆነ ሊታወቅ ያልቻለዉ፣ ከዛ ይልቅ ሁሉም የራሱን ፕሮፖጋንዳ ብቻ እንዲያናፍስ ምክንያት ከሆኑት ነገሮች ዋነኛው ከተዋጊ ወይንም እነሱ ከሚደግፉት ወገን ብቻ ነገሮችን የማያዩ ነገር ግን በትክክል ህዝቡ ላይ እየሆነ ያለዉን የመዘገብ አቅም ያላቸው የግል ጋዜጠኞች ወደ ጦሩ ሰፈር እንዲሄዱ አለመደረጉ ነው፡፡
.
ጋዜጠኞች በጦርነት ወቅት፣ ትግራይም ይሂዱ ወሎ፣ አፋርም ይሂዱ ወለጋ ቢቻል ጋዜጠኛ መሆናቸዉን ፣ ሚድያ መሆናቸዉን የሚያሳይ ነገርን መጠቀም እንጂ ተዋግተው ለማይዋጉት ጦርነት መሳርያ እየያዙ መታየት ከሙያው አኳያ አግባብ አይደለም!! በዚህ መሃል ቢያዙ እንኳን መሳርያ አንግተው ስለተገኙ በጀኔቫው ስምምነት መሰረት መብታቸው እንዳይጠበቅ ያግዳቸዋል፡፡
.
ይህ ነገር እየተደጋገመ በመሆኑ መሳርያዉን ለመሳርያ አንጋቢው መተዉ ግድ ይላል፡፡ ባይሆን ጋዜጠኞች በጦርነት አካባቢዎች ተገኝተው ሚናቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ ሌሎች ጥበቃ ሊያደርጉላቸው ይገባል፣ ከዛ ዉጭ ግን ከሙያዊው እና አለማቀፍ ህጎች አንጻር ጋዜጠኞች ለፎቶ ሲሉ እንኳ መሳርያን ማንገቱን መተዋቸው ይመረጣል፡፡




https://www.facebook.com/RNZeroFive/posts/4358499597519134

Читать полностью…

Radio Negashi Channel

https://youtu.be/Teb725NUEPg

Читать полностью…
Подписаться на канал