quranhikimina | Неотсортированное

Telegram-канал quranhikimina - መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

1029

https://telegram.me/quranhkmna ቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያርጉት አላማችን በሲህር በጅን ባይንናስ የታመሙ ሙስሊሞችን ወደ ሽርክና ፀበል እዳይሄዱ ወደ ቁርአን ፈውስ ብቻ እዲጠቀሙ ማመላከት ነው ‹‹ከቁርዓን ለሰዎች መድሀኒትና እዝነት የሆነ ቁርዓን አውርደናል፡፡›› ኢስራእ ለጥያቄ ለአስተያየት https://t.me/Bequranhkmna

Подписаться на канал

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

🏷️ዛድ ጤና ቁ/11

💠እራሳችንን እራሳችን በቁርኣን እናክም!

◻️ከቁርኣን መገለጫዎች መካከል አንዱ "ሺፋእ/ መድሃኒት" መሆኑ ነው።
ከፋቲሓ ስሞች መካከልም አንዱ "አሽ'ሻፊየህ/ፈዋሹዋ" የሚለው ነው።

◻️ቁርኣንና ነቢያዊ ዚክርና ዱዓዎች (ሩቃ) ለሁሉም አይነት በሽታና ችግሮች መፍትሄ ናቸው።
ማንኛውም በቁርኣን ፈውስነት የሚያምን ግለሰብ ፋቲሓንና አጫጭር (እራሱ በቀላሉ መቅራት የሚችላቸውን) ሱራዎች እንኳ ቢሆን እየቀራ ለራሱ ሩቃ ማድረግ ይችላል።

◻️ሩቃ ለማድረግ የግድ ሰው ጋር መሄድ ወይም ሰው መጥራት አይጠበቅብንም።
ለህጻናትና ራሱን ለማያውቅ(መቆጣጠር) ለማይችል ሰውም ቢሆን ሩቃ አድራጊ ፍለጋ ርቆ ለመሄድ ሳንገደድ፤ በቤተሰብ፣ የግድ ከሆነም በዘመድና ጎረቤት ማስደረግ ይቻላል።

◻️ዋናው ነገር ብዙ መቅራቱ ሳይሆን አላህን በሚፈራና ተወኩል ባለው ልብ፣ በቁርኣን ፈዋሽነት አምኖ ፋቲሓና እነ ቁል-አዑዙን ወዘተ.. እየደጋገሙ መቅራት በቂ ነው!። ነቢዩና ﷺ ሰሓቦቻቸውም በነዚህ ምእራፎች ሩቃ ያደርጉ ነበር።

◻️በተለይ አሁን ባለንበት የኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ላይ በሌላ ሰው ሩቃ ማስደረግ ተገቢ አይደለም።
በተለይም መቀራረብና ከሩቃው ጋር "ቱ...ቱ.../እትፍ-ትፍ" ማለት ካለበት!!

◻️ታላቁ የዲን ሊቅም ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ "እንደ ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው ለሌላ ሰው ሩቃ ሲያደርግ "ቱ...ቱ.../እትፍ-ትፍ" ማለት እንደሌለበት" ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት አማራጭ ከጠፋና በሰው ማስደረጉ የግድ ከሆነ አሁን ላይ ሩቃውን "ቱ... ቱ..." ሳይሉ ማድረግ ይቻላል።

🔅በመሆኑም ሁሉም ለራሱ የሚችለውን የቁራኣን ሱራ ወይም አንቀጾችን በመቅራት ሩቃ ሊያደርግ ይገባዋል።ሁሉም የቁርኣን ሱራና አንቀጾ ለሙእሚኖች ፈውሶች ናቸውና!

@ዛዱል መዓድ

🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

👉  ከቀደምት ሊቃውንቶች ምርጥ ንግግር

"خلق الله الملائكة عقولاً بلا شهوة ، وخلق البهائم شهوة بلا عقول، وخلق ابن آدم وركب فيه العقل والشهوة ، فمن غلب عقله شهوته التحق بالملائكة ، ومن غلبت شهوته عقله التحق بالبهائم " .

"አላህ መላኢካን ዐቅል ሰጥቶ ያለ ስሜት ፈጠራቸው። እንሰሳትን ደግሞ ስሜት ሰጥቶ ያለ ዐቅል ፈጠራቸው። የሰውን ልጅ ፈጥሮ ዐቅልና ስሜት አደረገለት። ዐቅሉ ስሜቱን ያሸነፈለት ሰው ወደ መላኢካ  ይጠጋል። ስሜቱ ዐቅሉን ያሸነፈበት ሰው ደግሞ ወደ እንሰሳ ይጠጋል ‼

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ይህ የዶላር መጨመር ሰውን አነጋገረው የወሬ ርዕስ ሆነ የአብዛኛው ሰው አጀንዳ ዶላር ጨመረ ዶላር ጨመረ ሆኗል።


የዝሙት መጨመር የወንጀል መበራከት የሽርክ መስፋፋት የዚህን ያክል መነጋገሪያ ቢሆን ኖሮ በዚች ምድር ለውጥን ባስተዋልን ነበር

ግና ስለ ሀጢያት ምንም የሚያሳስበው የለም። ግንኮ የዶላር መጨመርም ሆነ የድርቅ አደጋም ሆነ የጦርነት መከሰትም ሆነ የወረርሽኝ ስርጭት በወንጀል በተለይም በሽርክ የመጣ ነው።

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ዛሬ ዛሬ በተለይ ከገጠርም አልፎ ከተማ ውስጥ መሽጎዋል።

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

      t.me/Darutewhide

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ስታገኝ ለጋሽ ስታጣ ታጋሽ ሁን ‼

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

የልብና የግንባር ዓይን እይታዎች

የግንባር ዓይን አላህ የከለከለውን ሲያይ የልብ ዓይን ሐቅን ከማየትና ከመከተል፣ እንዲሁም ኣኺራን አሻግሮ ከማየት ይታወራል።
የግንባር ዓይን አላህ የከለከለውን ከማየት ሲታቀብ ደግሞ የልብ ዓይን በርቶ ሐቅን ያያል፤ ከዱኒያ አልፎ ኣኺራንም አሻግሮ በማየት ለቀጣዩ ዓለም ህይወት በሚገባ ይዘጋጃል።

📝 ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

🚫 ወንድሜ የሴትን ልጅ ፈተና ተጠንቀቅ❗ ኮፒ

የሴት ልጅ ፈተና ልክ እንደዚህ ታሪክ 👇 ከሱና ሊያንሸራትትህ አልፎም ዲንህን ሊያስቀይርህ ይችላልና ተጠንቀቅ።
ታሪኩ እንዲህ ነው:- በግብፅ ከተማ ውስጥ አንድ ከመስጂድ የማይጠፋ መስጂድን በአዛን በሷላት አጥብቆ የሚይዝ ሙዓዚን ነበረ። በርሱም ላይ ጥሩ ለዲኑ መታዘዝና የኢባዳህ ብርሃኖች ይታዩበት ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ ሚናራህ ወጣ ታዲያ አዛን ላይ ሳለ ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ አንዲትን እንስት ይመለከታል፡፡ ወዲያውኑ በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቅና፣ በፍጥነት እርሷ ወዳለችበት ቤት ሄዶ ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች።

እሱ ፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው የምፈልገው❗️
እሷ ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"ብላ ጠየቀችው
እሱ ፡- "ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን መሰባሰቢያ ይዘሺዋል" አላት
እሷ ፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ ልልህ አልችም አለቸው
እሱ ፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት
እሷ ፡- "አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ (ክርስቲያን) ነኝ አባቴ 
         ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም" አለችው
እሱ ፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት
እሷ ፡- እንደዛ ያደረግክ እንደሆን እኔም ፍቃደኛ ነኝ አለችው

ከዚያም ይሄ ሰው እሷን ለማግባት ሲል ነሳራ (ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት ተቀመጠ፣ ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወድቆ
ወዲያውኑ ህይወቱ አለፈች። እሷንም እስልምናውንም አጥቶ በኩፍር ላይ ሞተ ።

ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይል ነበር :- "አላህ አንድም ነብይ አልላከም ሸይጧን በሴት ፈተና ሲያጠፋቸው ከነርሱ ላይ ተስፋ ባይቆርጥ እንጂ"
📚 [መውሱዓቱ ሊብኒ አቢ ዱንያ 4/540]

አልሀሰን ኢብኑ ሷሊህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ሲል ይናገራል :- ሸይጣን
ለሴት ልጅ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ "አንቺ የኔ ግማሽ ጎኔ ነሽ፣ እኔ በአንቺ የምወረውርብሽ ቀስቴ ነሽ፣ ደግሞም ባንቺ ከወረወርኩ አልስተም፣ አንቺ የሚስጥሬ ቦታ ነሽ፣ አንቺ የኔ የጉዳዬ መልዕክተኛ ነሽ"
📚 [መውሱዓቱ ሊብኒ አቢ ዱንያ 4/539]

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
"ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ የሆነ ፈተና ከኋላዬ አልተውኩም"
📚 [ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል ]

ወንድሜ ከእንዲህ አይነት ፊቲና አላህ ይጠብቀን 🤲

[አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ ሊብኒ አልቀይም : ገፅ-167]

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

🌾የጁሙዓ ኹጥባ በአማርኛ  🌾

             ቁ/248

🔆 የመልካም ስነምግባር ምንነትና ትሩፋት

     እሁድ 16/7/1445 ዓ.ሂ

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

       የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇

🔎  https://t.ly/QEogK
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

🌐/channel/ahmedadem

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

🌿የማይቀርበት ታላቅ የሙሀደራ ግብዣ🌿


🎙በሸይኽ አሕመድ ሸይኽ አደም

🕌 በላፍቶ ቢላል መስጂድ!!!

🗓ሰኞ,ታህሳስ 22/04/2016E.C

🕝ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

📍ሴቶችንም ወንዶችንም ተጋብዛቹሀል❗️❗️❗️

💡አይደለም መቅረት ማርፈድ እራሱ ያስቆጫል❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

📚💡« ጥቂት ስለ ጀነት »
        
🎙በ ሸይኽ አህመድ ሸይኽ ኣደም

/channel/umulquranalfatihaonlinequrancen

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

/channel/quranhikimina
ቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያርጉት አላማችን በሲህር በጅን
ባይንናስ የታመሙ ሙስሊሞችን ወደ ሽርክና ፀበል እዳይሄዱ
ወደ ቁርአን ፈውስ ብቻ
እዲጠቀሙ ማመላከት ነው

‹‹ከቁርዓን ለሰዎች መድሀኒትና እዝነት የሆነ ቁርዓን አውርደናል፡፡›› ኢስራእ

ለጥያቄ

ለአስተያየት

https://ummalife.com/umma1697914509

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

فايرا 134 Fyra:
የቁርአን ቻናሎች በቃሪኦቻቸው ስም የሚያገኙበት!!!!

1 @mishary_rashid_al_afasi
2 @Yassen_Al_Jazairi
3 @Sheikh_Abu_Bakr_Al_Shatri
4 @Sheikh_Muhammad_Al_Luhaidan
5 @Abdulbasit_Abdussamed1
6 @Sheikh_Abdul_Rahman_Al_Sudais
7 @Ali_Al_Huzaifi
8 @Khalifah_At_Tonaeijy
9 @Ahmad_Al_Ajmy
10 @Sheikh_Saad_Al_Gamidi
11 @Emad_Al_Mansary
12 @Abdullah_ibn_Al_Basfar
13 @Sheikh_Nasser_Al_Qatami
14 @Abdulhadi_Kanakeri
15 @Sheikh_Maher_Al_Muaiqly
16 @Sheikh_Adel_Rayan
17 @Khalil_Al_Hussary
18 @Sheikh_Muhammad_Ayyub
19 @Abdullah_Awad_Al_Juhany
20 @Abdul_Rashid_Ali_Sufi
21 @Mohamed_Siddiq_El_Minshawi
22 @Abdul_Rahman_Al_Ossi
23 @Sheikh_Saud_Al_Shuraim
24 @Yasser_Al_Dosarii
25 @Muhammad_Al_Kurdi1
26 @Fares_Abbad1
27 @Sheikh_Salah_Bukhatir
28 @Imad_Zuhair_Hafez
29 @Muhammad_AbdulKareem
30 @Ahmad_Misbahi
31 @Abdulaziz_Az_Zahrani
32 @Ibrahim_Al_Asirii
33 @Abdulbosit_Qobilov1
34 @Abdullah_al_Matrood1
35 @Afzal_Rafiqov1
36 @Hani_Ar_Rifai
37 @Abdullah_Ali_Jaber
38 @Sheikh_Muhammad_Jibril
39 @Jazza_Alswaileh
40 @Bandar_Balila
41 @Mohammad_Al_Tablawi
42 @Wadee_Al_Yamani
43 @Ghassan_Al_Shorbajyi
44 @Zaki_Dagistan
45 @Ahmad_Al_Lahdan
46 @Abdullah_Xalif
47 @Yasser_Al_Qureshi
48 @Nabil_Al_Rifai
49 @Salah_Al_Hashem
50 @Shirazad_Taher
51 @Tawfeeq_As_Sayeghh
52 @Rashid_Al_Arkani
53 @Sheikh_Mustafa_Ismail
54 @Ali_Yakupovv
55 @Abdullah_Kamel
56 @Mahmud_Ali_Albanna
57 @Sheikh_Idris_Abkar
58 @Hassen_Saleh
59 @Moeedh_Al_Harthi
60 @Ahmed_Naina
61 @Waleed_Al_Naehi
62 @Saber_AbdulHakam
63 @Mohammad_Saleh_Shah
64 @AbdulMuhsin_Qasim
65 @Salah_Al_Budair
66 @Akram_Alalaqimy
67 @Jamaan_Alosaimii
68 @Abdulmohsen_Harty
69 @Abdul_Wadood_Haneef
70 @Mohammad_Al_Abdullah
71 @Yahya_Hawwa
73 @Hlaljmaea

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ከሁለት ዓመት በፊት ወደ አኼራ የሄደው ሙሉ ሰውነቱ ፓራላይዝድ የነበረው ታዋቂው ዳኢ አብደላህ ባነእማ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል...

    "በነገራችን ላይ ሸህ አብደላ 'ረሂመሁሏህ..አንገታቸው
እና ምላሳቸው ብቻ ነበር የሚንቀሳቀሠው 'ተኝተው ነበር ዳዕዋ የሚያደርጉት አላህ ይዘንላቸው..

"አንዴ እያስተማሩ እያለ እንዲህ አሉ.." ከኔ በባሰ ሁኔታ ያለው ሰው አለ ብዬ አላስብም ነበር

  "ምክንያቱም ከ ጭንቅላቱ በስተቀር ሌላ ሰውነቱ ስለማይንቀሰቀስ ..

  "አንድ ሼኽ እንዲህ አለኝ ካንተ  በባሰ ሁኔታ ያለ ሰው ጋ ዛሬ እወስድሃለው  እንዳሉትም ወደ ሰውየው ጋ  ሄዱ..'''

አብደላ በርግጥም ባየው ነገር ደነገጠ ልክ እንደሱ ሙሉ ሰውነቱ አይንቀሳቀስም  ከዚህ የባስው ደሞ መስማትና መናገር አይችልም አስባችሁታል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ

ይህ ሰው አንድ ሚያሳዝን ነገር አጋጥሞታል

አንድ ቀን ቤተሰቦቹ ወደ ክፍሉ ሲገቡ ልብሱ ላይ ደም ተመለከቱ እሱም እያለቀሰ ነበር ደሙን ተከትለው ሲሄዱ ጣቶቹ ተቆርጠው ነበር

ምን ተፈጠረ??

እንዴት ጣቶቹ ሊቆረጡ ቻሉ??

ለካ አይጥ ገብታ ሁለት ጣቶቹን በልታቸው  ነበር ልክ እንደ ሞተ ሰው መንቀሳቀስም ሆነ እርዳታ መጠየቅ ስለማይች እጆቹን ስትበላ እያመመው ዝም ብሎ ይመለከታት ነበር

አንተስ?

☞በእጆችህ ምን አደረክ '? በእግሮችህ? በአይንህ?በጀሮህ?

'አላሏሁ ሱብሓነ ወተኣላ በሠጠን ኒዕማወች ሁሉ?

"እኔ..ምንም

الحمدلله الذي عافانا مما ابتلى به كثيرا من خلقه

አላህ በሰጣቹህ ጤንነት አመስግኑ ጊዜው ሳይረፍድ  ወደ አላህ በተውበት ተመለሱ  ይላል ሼኽ አብደላህ ረሂመሁሏህ

አልሃምዱ ሊላህ ተቆጥረው ለማይዘለቁት ፀጋዎችህ

"ከአረበኛ ወደ አማረኛ ተተረጎመ! "ተውቡ ኢለሏህ ከሚለው ነቅል!

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

አቡ ሐይደር ጂንኖች ወንድሞቻችን ናቸው

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ከምንም በላይ የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር እድሜዬ ጨምሮ መልካም ስራዬ ሳይጨምር ጀንበር የምትጠልቅበት ቀን ነው ።
  ☞ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ አንሁ

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ቤት ውስጥ ቴሌቪዥን ያስገባችሁ ሰዎች ልጆቻችሁ በምን እየተቀረፁ እንደሆነ ከዚህ ቪዲዮ ተመልከቱማ

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

መለከል መውት የዱንያ ቆይታውን ለማገባደድ ጥቂት ሴኮንዶች የቀረውን ፍጡር ከሌሎች ነጥሎ ለመውሰድ ባሻው መንገድ ይመጣል። ይህ ክስተት «ሟች ይህን ቢያደርግ ኖሮ ይህ አይፈጠርም ነበር» የሚል ክፍተት እንደሌለው የሩቅ ምስጢራት ግርዶ ላልተገለጠልን የመሬት ነዋሪዎች መማሪያ ነው። ቀለሙ ተነስቷል ፤ ወረቀቱም ደርቋል

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ዱንያ ጀርባዋን ሠጥታን እየሄደች ነው፤
አኺራ ፊቷን ወደኛ አዙራ እየመጣች ነው፤
የአኺራ እንጂ የዱንያ ሰው አትሁኑ ፤
ዛሬ ሥራ እንጂ ምርመራ የለም፤
ነገ ምርመራ እንጂ ሥራ የለም።
[ዐሊ ኢብኑ ጧሊብ]

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ከረመضاን በኋላ ሰላት ያቆማቅችሁ ወንድም እህቶች ሆይ እስኪ ስሙ!
ልጅቱ ሸኽየው ጋር ትደውልና ፦  "ያ ሸይኽ እኔ ሙስሊም አልነበርኩም አሁን ግን እስልምናን ተቀብያለሁ ቤተሰቦቼ መስለሜን ካወቁ ትልቅ ፈተና ይገጥመኛል እና ሻወር (መፀዳጃ) ቤት ውስጥ ተደብቄ መስግድ እችላለሁን!?"
ሱብህበሏህ ! 
ታድያ ወዳጄ ሆይ ! አላህ ኢስላምን ከሰጠህ በኋላ ምን ሆንኩ ብለህ ምንስ ኡዝር አለኝ ብለህ ሰላት መስገድን ትተዋልህ!?

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

◦ ታውቃለህ አንድ ቀን ላትመለስ ትሄዳለህ !

- ዘመድ ወዳጆችህ ሁሉ አንድቀን ትለያቸዋለህ

- ምርጡ ፍራሽህና ትራስህ አንድ ቀን በአፈር ይቀየራል

- ወዳጆችህ ሁለ አንድ ቀን የቀብር ጉድጓድ ስር ጥለውክ ይመጣሉ

❗️ምርጥ ሰው ከሆንክ ለዚህ ቀን ተዘጋጅ ❗️

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ክፉ ልክፍት!... ድንቅ መድሃኒት!
~
ሰውየው፡-
* “ቀድሞ (ለማጨት ሳስባት) በሚስቴ በምደነቅ ጊዜ … አላህ የሷ አይነት በዓለም ላይ የፈጠረ አይመስለኝም ነበር፡፡
* ካጨኋት በኋላ ብዙዎቹ ሴቶች የሷው አምሳያ ሆነው አገኘሁ፡፡
* ካገባኋት በኋላ #ብዙዎቹ ሴቶች ከሷ የበለጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ተገነዘብኩ፡፡
* ተጋብተን ጥቂት አመታት ካለፉ በኋላ ግን #ሁሉም ሴቶች ከሷ የሚበልጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ደመደምኩ” አለ፡፡

ሸይኹ በዚህን ጊዜ፡- “ይልቅ ከዚህ የከፋውን አልነግርህም?” አሉት፡፡
“ይንገሩኝ” አለ ሰውየው፡፡
“የዓለም ሴቶችን በሙሉ ብታገባም በየጎዳናው የሚልከሰከሱ ውሾች ከአለም ሴቶች ሁሉ በላይ ቆንጆዎች ይሆኑብሃል!!” አሉት።
ሰውየው፡- በስሱ ፈገግ አለና “ለምን እንዲህ አሉ?” ሲል ጠየቃቸው፡፡
ሸይኹ፡- “ምክንያቱም ችግሩ ከሚስትህ አይደለም፡፡ ችግሩ የሰው ልጅ ስግብግብ ልቦና፣ ልክስክስ አይን ሲኖረውና አላህን ከማፈር፣ ከሐያእ ሲራቆት ነው፡፡ በዚህን ጊዜ አይኑን የመቃብሩ አፈር እንጂ አይሞላውም፡፡ ልክ ነብዩ ﷺ ‘የአደምን ልጅ አፈር እንጂ አይኑን አይሞላውም…’ እንዳሉት፡፡ ሰውየ!! ችግርህ አይንህን አላህ ከከለከለው ነገር አለመስበርህ ነው፡፡ ይልቅ ሚስትህን ልክ እንደ ቀድሞዋ (ከአለም ሴቶች ሁሉ ቆንጆ) የምታደርግበትን ዘዴ እንድነግርህ ትፈልጋለህ?” አሉት፡፡
“አዎ” አለ ሰውየው፡፡
“አይንህን ስበር!!” አሉት ሸይኹ!!
ከአንድ ዐረብኛ ፅሑፍ የተቀዳ ነው፡፡

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ዑማ ላይፍ አፕ ለእኛ ለሙሥሊሞች እውነት እውነቷን ልናወራ ዘንድ ይፈቅዳል ። አውርዱት ይጠቅማችኋል 🥰 ummalife


በኡማ ላይፍ አካውን ይከተሉን

https://ummalife.com/umma1697914509

Читать полностью…

መንፈሳዊ ህክምና ጂን ሲህር እንዲሁም አይንናስ

ህጻናትን ከቤት ወደ ሌላ ስፍራ ይዘናቸው ስንወጣ በሰውና በጂንኒ አይን (አይነ-ናስ ወል-ጂን) እንዳይለከፉ ቀጥሎ ያለውን ዚክር አናታቸውን በመያዝ እንበል፡- 

1. አንድ ህጻን ብቻ ከሆነ፡- ‹‹ኡዒዙከ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ፣ ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ፣ ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ›› 

2. ሁለት እና ከዛ በላይ ከሆኑ፡- ‹‹ኡዒዙኩማ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ፣ ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ፣ ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ›› 
(ቡኻሪና አቡ ዳዉድ)፡፡ 

የዚህ ዚክር ትርጉም፡- 

1. ‹‹አዒዙከ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ›› ማለት፡- ሙሉ በሆነው የአላህ ቃላት እጠብቅሀለው ማለት ነው፡፡ ወደ አንድ መንደር ወይም ቤት ሲገባ ‹‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ-ታምማቲ ሚን ሸርሪ ማ-ኸለቅ›› ያለ ሰው፡ ያንን ቤት እና መንደር ለቆ እስኪወጣ ምንም እንደማይደርስበት በሌላ ሐዲሥ ተነግሮአል፡፡ 

2. ‹‹ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ›› ማለት፡- ከሸይጧናትና ከመርዛማ ገዳይ ነገራት (ሙሉ በሆነው የአላህ ቃል እጠብቅሀለሁ) ማለት ነው፡፡ 

3. ‹‹ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ›› ማለት፡- ከክፉ አይኖች በጠቅላላ (ሙሉ በሆነው የአላህ ቃል እጠብቃለው) ማለት ነው።

Читать полностью…
Подписаться на канал