ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

138693

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . #ዝማሬ_ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

አለምን ዞሬ አየሁት

አለምን ዞሬ አየሁት
ሁሉን በተራ ቀመስኩት /2/
ፈፅሞ የለም /2/
ሰላም እንደ ልጂሽ ቤት

ሀብቴን ንብረቴን ጨረስኩና
ጉልበቴ ሁሉ ደከመና /2/
ጎስቋላ ሆንኩኝ /2/
ደካማ የሌለው ጤና

ስቃ አሳስቃ ተቀብላ
መልኳን አስውባ ተኳኩላ /2/
ዛሬ ጣላችኝ /2/
ይቺ አለም አይረባም ብላ

የትላንትናው ወዳጆቼ
ዛሬ ሲሆኑ ጠላቶቼ /2/
ባክኜ ቀረሁ /2/
በዓለም ላይ ተንከራትቼ

የአባቴ ቤት ሲናፍቀኝ
ፍቅሩ ምህረቱ ትዝ ሲለኝ
ሁሉንም ትቼ/2/
ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ

ልጁም አንድባል ባይገባኝ
ባሪያህ እሆን ዘንድ ቢፈቅድልኝ /2/
ጎስቋላ ልጁ ደካማ ልጁ
ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁ

እናቴ አንቺን ንቄ ትቼ
የአባቴን ቤት እረስቼ
ተሰቃየሁን ተንከራተትኩኝ
ልደሰት ባለም ገብቼ

አባቴ ሲያየኝ ተደስቶ
ጎረቤቶቹን ሁሉን ጠርቶ
ሠርጉን ደገስ /2/
የበደልኩትን ረስቶ

እስካሁን ድረስ በድያለው
አለም ደና ሁኝ አብቅቻለው
ወደ አባቴ ቤት/2/
ዳግመኛ ተመልሻለው

©ማኅበረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

/channel/boost/ortodoxmezmur

የቴሌግራም ፕሪሚየር ተጠቃሚ የሆናችሁ በሙሉ የዝማሬ ዳዊት ቻናልን ከላይ ባስቀመጥነው ሊንክ ቡስት እንድታደርጉልን እንጠይቃለን።

ስለምታደርጉልን መልካም ነገር እግዚአብሔር ይስጥልን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በርባን ነኝ

በርባን ነኝ/3/ባንተ መስቀል የዳንኩኝ/2/
በኃጥያት በበደል የኖርኩኝ በክፋት
ወንበዴ ነበርኩኝ የሚገባኝ መሞት
ሁሉንም እረስተህ በፍቅር ያየኸኝ
ንገረኝ አምላኬ እንደምን ወደድከኝ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


ወንበዴው እኔ ነኝ ሀገር ያስቸገርኩኝ
እጆቼን በበደል በደም የታጠብኩኝ
አንተ ግን ራርተህ ተሰጠህ ስለ እኔ
ዋጋ ከፈልክልኝ ክርስቶስ ስለ እኔ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


ሞቴን ስጠባበቅ እኔ እንደ ስራዬ
ትክክል ነውና የክፋት ዋጋዬ
አንተ ግን ንጹሁ እኔን የወደድከኝ
ለነፍስህ ሳትሳሳ እንከ ሞት ደረስክ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


በዋጋ ገዝተኸኝ ዳግመኛ እንዳልሞት
ብርታት ሁነኝ እና ልለይ ከኃጥያት
መልካምም እንዳስብ መልካም እንድሰራ
በጽድቅ ልመላለስ ልቦናዬን አብራ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ

ዘማሪ አቤል ተስፋዬ የበገና ዝማሬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#የአንተ_ሥራ

የአንተ ሥራ የአንተ ሥራ
የአንተ ሥራ ለዓለም ይወራ (፪)

በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት
መጻጉዕ ተብሎ ተኝቶ ባዐራት
ዘመን ያስቆጠረ ሠላሳ ስምንት
ተነሳ ተባለ አገኘ ምህረት
#አዝ
ሰውነቱ ደቆ እጅግ የታመመ (፪)
በሱ ድንቅ ስራ አልጋ ተሸከመ (፪)
#አዝ
ወገን ያልነበረው ወድቆ የተረሳ (፪)
ምሕረት አገኘና በድንገት ተነሳ (፪)
#አዝ
ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ሲናገር
ያልተፈቀደውን ይሄው ሰንበት ሲሽር
አየነው ሰማነው አያሻም ምስክር
ብለው ተነሱበት በጠማማ ምክር

መዝሙር ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ"
ዮሐ፭፥፰

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

መዝሙር ዘመጻጒዕ
21/07/16 ዓ.ም

የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ ፵፥፫
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኲሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ

ትርጉም
እግዚአብሔር በሕማሙ አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውንም ከደዌው የተነሣ ይለውጥለታል
እኔስ አቤቱ ይቅር በለኝ እላለሁ

የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፭፥፩ - ፳፭
ቅዳሴ፦ ቅዳሴ ለእግዚእነ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🔰የመምህር ሲሳይ ደምሴ መዝሙሮች

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🔰የአቶ ዘርፉ ደምሴ (የደምሴ ደስታ ልጅ) መዝሙሮች

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🔰የሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ
መዝሙሮች

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የመፃጉዕ - አልጋ

ጸሐፊ - ትዕግስት
አንባቢ- ዓ.ማርያም
ለእህታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

✞ መፃጕዕ

ሰው የለኝም ያለ በሠው የተረሳ
የዳነው መፃጕዕ ያዳነውን ረሳ

በአምስቱ እርከኖች በአእማደ ምስጢራት
ቤተ ሣይዳ ላለች ከመቅደስ ላኖርካት
በበደል ለምናዝን ምህረትን ፍለጋ
በንስሐ ማረን ከዓራተ ዝንጋኤ ከኃጥያት አልጋ
አዝ
በጠበሉ ደጃፍ ለፀኑት የሚላክ
ለቀድሶተ ማይ የሚወርደው መልዐክ
በመንገድ ጠብቆ ሞትን የሚያሳልፍ
ዛሬም ይድረስልን ቀድመው ከገቡት ጋር ነፍሳችን እንድታርፍ
አዝ
አልጋው ተሸክሞት ደክሞ ለሚጨነቅ
አልጋን አሸክመህ ህመም የምታርቅ
ደዌያችንን ነስተህ ቆስለህ የምትፈውስ
የመፃጕዕ ረዳት የነፍሳት መጠጊያ መድኃኒት ክርስቶስ
አዝ
የባሰ እንዳያየው ቃሉን ያልጠበቀ
እጁን ሰዶ ፀፍቶ ከደዌው ታረቀ
ሰንበትን የሻረ ከሚሉት እንዳንውል
ለትንሳኤው ደስታ የሰንበትን ጌታ ዓርብን እንከተል

ዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜፀጋ ዮሐንስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መጻጒዕ

እንኳን አደረሳቹ የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መጻጒዕ ለ 38 ዓመት በአልጋ ላይ ተኝቶ የሚኖር አንደ ሰው ነበረ እርሱም #መጾጒዕ ይባላል።

((ዮሐ5፥1-11)) ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ ኢየሱስም ወደ አየሩሳሌም ወጣ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ "ቤተ ሳይዳ" የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች አምስትም መመላለሻ ነበረባት

በእነዚህ ውስጥ የወኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና፣ ዕዉሮች፣ አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ በዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር አንደንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከወኃውን መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።

በዚያም "ሠላሳ ስምንት" ዓመት ያህል ይታመም የነበረ አንድ ሰው ነበረ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ ልትደን ትወዳላህን? አለው

ድውዮም፦ አዎ ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ወስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም! ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳላሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለስለት፣

ኢየሱስም ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው፣ ወዲያውም ሰውየው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።

ያም ቀን "ሰንበት" ቀን ነበረ ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው "ሰንበት" ነው አልጋውን ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት እርሱ ግን ያዳነኝ ያ ሰው "አልጋውን ተሸክመህ ሂድ" አለኝ ብሎ መለሰላቸው።

((ማቴ9÷1)) በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ እነሆም በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ ኢየሱስ እምነታቸውን አይቶ ሽባውን አንተ ልጅ አይዞህ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው

((መዝ 40፥3)) እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳላ ይረዳዋል መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል።

አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በየጸበሉ በሆስፒታሉ የታመሙትን ምህረትህን ለሚናፍቁ የምህረት እጅህን ዘርጋላቸው እኛንም የመጣብንን መቅሰፍት በቸርነትህ ያዝልን!

የሐዋሪያት የነብያት የቅዱሳን አበው ጸሎት ልመና የተቀበልክ አምላክ የእኛንም ተቀበል! አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал