የማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን ላይ ይገኛል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል የተመሠረተበትን 25 ኛ ዓመት እና የማእከሉን ጠቅላላ ጉባኤ በዴንቨር ኮሎራዶ በማካሄድ ላይ ይገኛል::
ጉባኤው ቤተ ክርስቲያን ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እና የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ እና ሀገራዊ ኃላፊነቷን በሚገባ ልትወጣበት የምትችልበትን መንገድ ላይ በጥልቀት እየተወያየ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያን የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት" የሚለው አዲሱ የማኅበሩ ርዕይ ስለሚሳካበት ስልት በመወያየት ላይ ይገኛል::
በጉባኤው ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ዶ/ ር ሙሉጌታ ስዩም ከኢትዮጵያ የተገኙ ሲሆን ከመላው አሜሪካ የተሰባሰቡ የማኅበሩ አባላት: የባለድርሻ አካላት ተወካዮች: በዴንቨር ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል::
የዴንቨር ንዑስ ማዕከል ከ 25 ዓመት በፊት የአሜሪካ ማእከል የተመሠረተበት ቦታ ነው::
መልካም ዜና
የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው ጊዚያዊ ዕግድ መነሳቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታውቋል።
መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ ተፈተዋል።
ትናንት ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም በጸጥታ አካላት ተይዘው የነበሩት የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ በዛሬው ዕለት ተፈተው ወደ ሥራ ቦታቸው ተመልሰዋል።
በተጨማሪም መምህር ተሾመ በየነ እና ዲ/ን ዮናስ ትናንት ምሽት ከ 3:00 ሰዓት በኋላ ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ተወስደዋል።
መዝሙር ዘዕርገት
#ዐርገ_በስብሐት
ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት /2/
ወነበረ በየማነ አቡሁ /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን!!!
‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፡፡›› መዝ 67(68)፡33፡፡
‹‹ አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፡፡ ዘምሩ፣ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፣ ለንጉሣችን ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ፤ በማስተዋል ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል፡፡ ›› መዝ 47፡5-8፡፡
‹‹ ነሆም አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፡፡ እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው፡፡ ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፣ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡ ›› ሉቃ 23፡50-53፡፡
‹‹ #ዕርገት ›› የሚለው ቃል ዐረገ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ‹‹ ከፍ ከፍ አለ ፣ ወደ ሰማይ ወጣ ›› ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ላይ ‹‹ በስምሽ በመለመን በመማጸን የሰው ልጆችን ጸሎት ያሳርጋሉ ›› እንዲል፡፡ እንዲሁም በእሁድ ውዳሴ ማርያም ላይ ‹‹ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ›› እንዳለ፡፡
በተጨማሪም በራእይ 8፡4 ላይ ‹‹የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር በመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ›› በማለት ዐረገ የሚለውን ቃል በአማርኛ ‹‹ወጣ›› በማለት ይገልጸዋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ሞቶ ድኅነትን ከፈፀመ በኋላ በሦስተኛው ቀን የሞትን መውጊያ ሰብሮ ተነሣ፡፡ ከዚህ በኋላ በሞቱ ቀቢጸ ተስፋ ይዟቸው የነበረውን ሐዋርያትና አርድዕትን በተደጋጋሚ ትንሣኤዉን በመግለጥ ያጽናናቸው ነበር፡፡ ጌታችን ከሞት ከተነሣ ከኋላ ለአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ኪዳንንና ትምሕርተ ሕቡዓትን በዝርዝር አስተምሯቸዋል፡፡
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ ጀምሮ እስከ 40 ቀን ድረስ ሐዋርያትን ፣ አርድዕትን በጠቅላላው 120ውን ቤተሰብ ሲያጽናና ቆይቶ ለቅዱስ ጴጥሮስ የፕርትክና (ታላቅ አባት የመሆን) ሥልጣንን ከሰጠው በኋላ 120ውን ቤተሰብ ወደ ደብረ ዘይት ይዞአቸው ወጣ፡፡ በዚያም ሳሉ ‹‹ኃይልን እስክትለብሱ ድርስ በኢየሩሳሌም ጸንታችሁ ቆዩ›› የሚለውን ታላቁን የዕርገት መልእክት አስተላልፎ ከምድር ከፍ አለ፡፡
በመላእክት ምስጋና ‹‹በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ›› እንዲል ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ከዐይናቸዉም ተሰወረ፣ ሐዋርያትም ወደላይ አንጋጠው አንገታቸውን አቅንተው ይመለከቱ ነበር፡፡ ሐዋ 1፡2፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለቱ ብርሃናውያን መላእክት እንዲህ ሲሉ ተናገሯቸው ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ! ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁ እንዲሁ ይመጣል፡፡››
ይህ ታላቅ የተስፋ ቃል የመላእክት ንግግር ከቅዱስ ዳዊት ትንቢት ጋር የተዛመደ ሲሆን የጌታችን ምጽአት በምሥራቅ በኩል እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡ ሁለቱ መላእክት በንግግራቸው በዚህ ሲሄድ እንዳያችሁት በግርማ ደግሞ በዚህ ይመጣል ብለው ነበር፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ ›› መዝ 67(68)፡33 በማለት ይናገራል፡፡ በመሆኑም ጌታችን ያረገው በምሥራቅ ነው ፤ ደግሞ ለፍርድ የሚመጣው በምሥራቅ ነው ማለት ነው፡፡
#ይቀጥላል
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 1 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም ጉልላት እንደመሆኗ ሰላም መሠረታዊ ተልእኮዋ ነው፡፡ ስለዚህ ወቅታዊውን ችግር ታሳቢ በማድረግ በመላው አገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉ ተቋማት ጋራ የሚሠራ፣ በሀገሪቱ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የሚኖረው የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
በትግራይ ክልል በሚገኙት አህጉረ ስብከት ተቋርጦ የነበረው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነትን በተመለከተ ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ተሠይሞ በሥራ ላይ የሚገኘው ልዑክ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ተልዕኮውን እንዲፈጽም ምልዓተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖቻችን ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ አስቸኳይ የሆነ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ሃያ ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ውሎው ችግር ባለባቸውና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት ፱ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ውሳኔ አሳለፈ።
ምንጭ: EOTC TV
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ፣ የሀገሪቱን የሚዲያ ሕግ በመሻር በዚህ መልኩ የማኅበረ ቅዱሳንን ሚዲያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አግጄያለሁ ብሏል:: በየቦታው የነበረው መንግሥታዊ ኦርቶዶክሳውያንን የማሳደድ፣የማፈናቀል፣የመግደል እና ፍትህ የመንፈግ ጥቃት አሁን ተቋማቷን በግልጽ ወደ ማፍረስ እና ወደ ማጥፋት ተሸጋግሯል::
Читать полностью…ሰበር ዜና
++++++++++++++++++++++++++++++
"በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው ዓለማዊ አጀንዳ ቢያራምዱም በከፍተኛ ትዕግስት ስናልፋቸው የነበሩ አባቶች ዛሬም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ቤተክርስቲያንን ሲገፉ በዝምታ የምናይበት ሂደት አይኖርም፡፡"
++++++++++++++++++++++++++++++
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግርን ለመቅረፍ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐብይ ኮሚቴ በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደት ላይ መግለጫ አወጣ።
በአለፉት ሁለት ሦስት ቀናት በአባቶች ዘንድ ውይይት ተደርጎበት ስምምነት ላይ ሳይደረስበት የቀረው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደትን አስመልክቶ በተደረገው ውይይት ላይ በአባቶች የተፈጠረው የሐሳብ መከፋፈልና አለመግባባት ሁኔታ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ለኮሚቴው በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል ሲል ከ10 በላይ ማኅበራትን የወከለው ኮሚቴው በመግለጫው ጠቅሷል።
በየጊዜው በሚነሱ ወሳኝ የቅድስት ቤተክርስቲያን አጀንዳዎች ውስጥ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ጀርባቸውን የሚሰጡ፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ዓለማዊ አጀንዳ የሚያራምዱና ከዛሬ ነገ የቤተክርስቲያንን ፍቅርና ምህረት ተረድተው ወደልባቸው ይመለሳሉ በማለት በከፍተኛ ትዕግስት ስናልፋቸው የነበሩ አባቶች ዛሬም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ቤተክርስቲያንን ሲገፉ በዝምታ የምናይበት ሂደት አይኖርም ያለው ኮሚቴው
በዚህ ታሪካዊ ወቅት ለቅድስት ቤተክርስቲያን መቆም ሲገባችሁ እየሰማችሁ እንዳልሰማችሁ ሆናችሁ በዝምታ የምትመለከቱ አባቶችም ሆነ ዋነኛ የችግሩ አካላት የሆናችሁ አባቶች በእግዚአብሔርም በታሪክም በእኛም በልጆቻችሁ የሚያስጠይቃችሁ መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን ሲል አፅንዖት ሰጥቷል።
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/
አዝ
በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና
ተክለሃይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ
ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ያሬድ_ፈልፈለ_ማሕሌት
ያሬድ ፈልፈለ ማሕሌት
ወቅኔያት ወባህረጥበባት/፪/
እስመኮንከ መራሔመዘምራን
ለኢትዮጵያ ያሬድ ካህን ጥዑመልሳን/፪/
እንኳን ለቅዱስ ያሬድ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳቹ ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለባለሥልጣኑ ፈጣን ምላሽ ምስጋና ታቀርባለች
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ በማኅበረ
ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ፣ #ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ያስተላለፈውን ጊዜያዊ እገዳ እንዲያነሣ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በዛሬው ዕለት ለባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ያቀረበችውን ጥያቄ በመቀበል፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተጻፈለት ደብዳቤ እንደደረሰው፣ ሳይውል ሳያድር ጊዜያዊ እገዳውን ማንሣቱን አስታውቋል።
ስለኾነም፣ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችውን ጥያቄ በአዎንታ ተመልክቶ አፋጣኝ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠቱ፣ ከፍ ያለ ምስጋናን እናቀርባለን፤ ለወደፊቱም ተቋማዊ ግንኙነታችንን የበለጠ በማጠናከር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መኾናችንን እንገልጻለን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
ምንጭ: EOTC public relation
#ጠንቋዮ
👉 "አሻግረን የምናየውን ነገር ሁሉ አቅርበን እኔ ብሆን ኖሮስ ብለን ልናጤነው ይገባል"
👉 ፈገግ ብለው ትምህርት የሚያገኙበት ድንቅ ወግ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
መዝሙር ዘዕርገት
#ዐረገ_በስብሐት
ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ
በስብሐት በእልልታ
ዐረገ ዐረገ በእልልታ /2/
ሞትን ድል አድርጎ የሰራዊት ጌታ
ዐረገ ዐረገ በእልልታ /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#የቀጠለ
የጌታችን ዕርገት ምሳሌ እና ትንቢት አለው፡፡ ምሳሌው እንደምን ነው ቢሉ የቅዱስ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን አድሮ በሦስተኛው ቀን መውጣቱ ለትንሣኤው ምሳሌ እንደሆነ ሁሉ እንዲሁ የቅዱስ ኤልያስ ዕርገትም ለጌታችን ዕርገት ምሳሌ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን ቅዱስ ኤልያስ በመላእክት እርዳታ በፈቃደ እግዚአብሔር ያረገ ሲሆን ጌታችን ግን በፈቃዱ በራሱ ኃይል ዐርጓል፡፡
ትንቢቱም ቅዱስ ዳዊት ‹‹ ወደ ሰማይ ላረገው ለእግዚአብሔር ዘምሩ ›› መዝ 67(68)፡33 ብሎ የተናገረው ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹ወደ ላይ ዐረግህ ምርኮን ማረክህ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ›› (መዝ 67፡18) የሚል እናገኛለን፡፡ በመጨረሻም የጌታችን ታላቁ የዕርገት መልእክት ‹‹ኃይልን እስክታገኙ በኢየሩሳሌም ጽኑ›› የሚለው ታላቅ መልእክት ነው፡፡
ጌታችን በኢሩሳሌም እንደተወለደ እንዳደገ እንዳስተማረ እንደተሰቀለ በቤተ ክርስቲያንም በቤተልሔም ሥጋው ደሙ የሚዘጋጅባት ቃሉ የሚነገርባት በቤተ መቅደስ ሥጋው የሚቆረስበት ደሙ የሚፈስባት ቦታ ናትና ኢየረሳሌም የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ስለሆነም ቅዱስን የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲሁም ጸጋ ለማግኘት በቤተ ክርስቲያን መጽናት እንደሚገባ በአጭር ዐረፍተ ነገር ያስተማረው ታላቅ በዓል ነው፡፡
የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም ፣ ምክንያቱም ፈጽመው ክፋትን የተመሉ አይሁድና በኋላም የሚነሣ የረከሱ መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ ነው፡፡ ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሸብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ፡፡
ይህ የዕርገት በዓል ከጌታችን ዓበይት (ታላላቅ) በዓላት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጌታችንን የዕርገት በዓል ሁለት ጊዜ ታከብራለች፡፡ ይኸውም በመጀመሪያ ጌታችን ያረገበትን ጥንተ በዓሉን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የቀመር በዓል ነው፡፡
ዓመታዊ በዓላት ዓዋድያት (Movable Feasts) እና ዓዋድያት ያልሆኑ (Immovable Feasts) ተብለው በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ ዓዋድያት (Movable Feasts) የሚባሉት በቅዱስ ዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት መባጃ ሐመርን ተከትለው ወደፊት ወደኋላ በመመላለስ በየዓመቱ በተለያየ ቀንና ወር የሚውሉት ናቸው፡፡ እነዚህም እንደ ስቅለት፣ ሕመማት፣ ትንሣኤ፣ ደብረ ዘይት ፣ ሆሣዕና ፣ ዕርገትና ጰራቅሊጦስ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ዋድያት ያልሆኑ (Immovable Feasts) የሚባሉት ደግሞ ሁልጊዜም በወር ውስጥ በሚገኝ በታወቀ ቀን ብቻ በቋሚነት የሚውሉት ናቸው፡፡ እነዚህም እንደ ፅንሰት (ትስብእት) ፣ ልደት ፣ ጥምቀት ፣ ደብረ ታቦር ፣ ቃና ዘገሊላ ፣ ዘመን መለወጫ ፣ መስቀል ፣ 33ቱ የእመቤታችን በዓላት ፣ የመላእክት ፣ የሰማዕታትና የቅዱሳን በዓላት ናቸው፡፡
የጌታችን ዓበይትና ንዑሳት በዓላት፡- ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታችንን በዓላት ማክበር የጀመሩት የከበሩ ሐዋርያት ናቸው፡፡ ሠለስቱ ምእት ደግሞ ከ325 ዓ.ም ጀምረው በዓላቱ በቀኖና በሕግ እንዲከበሩ አዘዋል፡፡ ለዚኽም በፍትሐ ነገሥቱ ላይ የተጻፈውን በማስረጃነት ማየት እንችላለን፡፡ ‹‹እግዚአብሔር የጠመመውን እያቀናላቸው፣ የጎደለውን እየሞላላቸው የጌታን በዓላት ማክበር እንዲገባ 318 ሊቃውንት በጉባኤ ኒቅያ በእግዚአብሔር አጋዥነት የጌታችንን በዓላት ያከብሩ ዘንድ፣ ተአምራቱን ይገልጹ ዘንድ፣ ምስጋናውንም ይናገሩ ዘንድ አዘዙ ተናገሩ›› እንዲል፡፡ (ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ፣ ገጽ 260)
የጌታችን ዓበይት በዓላት ዘጠኝ ናቸው፡፡ እነዚህም፡- ፅንሰት (ትስብእት)፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ደብረ ታቦር፣ ሆሣዕና፣ ስቅለት፣ ትንሣኤ፣ ዕርገትና ጰራቅሊጦስ ናቸው፡፡
የጌታችን ንዑሳት በዓላት የሚባሉትም ዘጠኝ ሲሆኑ እነርሱም ስብከት ፣ ብርሃን ፣ ኖላዊ ፣ በዓለ ጌና ፣ ግዝረት፣ ልደተ ስምዖን ፣ ቃና ዘገሊላ ፣ ደብረ ዘይትና መስቀል ናቸው፡፡ የጌታችን የከበረ የዕረገቱ ረድኤት በረከት ይደርብን!
በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ላረገ አምላካችን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ከአብ ሕይወት ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ለዘለዓለሙ አሜን!
📜 ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በወቅታዊ ችግር ምክንያት በመላው ሀገራችን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ሁሉ በአጠቃላይ ችግሮቹን በጥናት በመለየት፣ ቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ልጆቿን በማስተባበር ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ የማጽናናትና የመጎብኘት መርሐ-ግብሮች እንዲደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
መቀሌ የሚገኘው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የሠራተኞችን ደመወዝና የሥራ ማስኬጃ በጀት እንዲለቀቅና በ2016 በጀት ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል መደበኛ የሆነ የመማር ማስተማሩ የሥራ ሂደት እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጪው ዐሥር ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግብ መሪ ዕቅድ በማጽደቅ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅሮች ተግባራዊ እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን ቀደምት አበው በቅድስት ሀገረ ኢየሩሳሌም ገዳማት እንዲስፋፉ ሁሉ የነሱን አሰረ ፍኖት በመከተል በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ ካልፎርኒያ ግዛት የተቋቋመው ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የአስተዳደር፣ የጽሙና፣ የትምህርትና የምርምር ማዕከል እንዲመሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
በኦሮምያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት ተፈጥሮ በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በአህጉረ ስብከትና በአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት ስለተቋረጠ፣ በርካታ ምእመናንና ካህናት በእስርና እንግልት ላይ ስለሚገኙ በዚሁ መነሻነት ችግሮች እንዲቀረፉና ወደ መደበኛው የአሠራር መዋቅር እንዲመለስ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን በመሠየም ከፌዴራልና ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመወያየት ችግሮች እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
የመንፈሳዊ ኮሌጆች መከፈት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር በተመለከተ በኢሉ አባቦራ የመቱ ፈለገ ሕይወት የነገረ መለኮት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲከፈት የተፈቀደ ሲሆን በሌሎች አህጉረ ስብከት ሊከፈቱ የታሰቡ ኮሌጆችን እና የአብነት ት/ቤቶችን መሠረታዊ ጥናት ተደርጎ ለ2016 ዓ.ም. የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ክፍት በሆኑና በተደራቢነት በተያዙ፣ ጉልህና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው በኦሮምያ ክልልና በደቡብ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ላይ 9 ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ወደፊትም ተደርበው በተያዙና አስፈላጊ በሆኑ አህጉረ ስብከት እንደአስፈላጊነቱ በመንበረ ፓትርያርክ ተጠንቶ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩትን አላስፈላጊ ግጭቶች የዜጐች መፈናቀል፣ ስደት ተወግዶ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር፤ ለማድረግ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡ እንዲሁም በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላም እና ዕርቅ እንዲሰፍን በመመኘት እና በመጸለይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤ በጸሎት አጠናቋል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ የሆኑት መምህር ተሾመ በየነ በጸጥታ አካላት ተወሰዱ።
በቋሚ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም የተቋቋመውን ሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሜቴ በጸሐፊነት እንዲያገለግሉ ተመድበው የነበሩት መምህር ተሾመ በየነ በዛሬው ዕለት በጸጥታ አካላት ተወስደዋል።
መምህር ተሾመ የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ ሲሆኑ ኅብረቱን ወክለው በተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ቤተክርስቲያንን እያገለገሉ የነበሩ ወንድም ናቸው።
በዛሬው ዕለት ከ ቅዱስ ኡራኤል አካባቢ የጸጥታ አካላት ነን በሚሉ ግለሰቦች የተወሰዱት መምህር ተሾመ በአሁኑ ሰዓት የተወሰዱበት ቦታ እንደማይታወቅ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
መምህር ተሾመ ከዚህ በፊት ከዐቢይ ኮሚቴው አባላት ጋር በጋራ በመሆን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በኩል መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን ከዐቢይ ኮሚቴው በጸጥታ አካላት የተወሰዱ ሁለተኛው ሰው ሆነዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን የቅሬታ ደብዳቤ አስገባ።
ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለማኅበረ ቅዱሳን በጻፈው ደብዳቤ በጊዜያዊነት የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃዱን ማገዱን አስታውቆ ነበር።
ማኅበሩም ደብዳቤው ተጽፏል ከተባለበት እና በተለያዩ ሚዲያዎች ከተሰራጨ ከአንድ ቀን በኋላ ማለትም ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም የደረሰው መሆኑን በመጥቀስ እግዱ ተወሰኖበታል የተባለው ዘገባም ምንም የሕግ ስህተት የሌለበት እና ከሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ጋር እንደማይጻረር የሚያስረዳ የ ቅሬታ ደብዳቤ ለባለሥልጣኑ አስገብቷል።
🇪🇹 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ❓
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ መዝሙራት
📖▓⇨→Audio ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👇👇👇👇
✝▓⇨→ሌሎችንም ለማግኘት...
ቤተክርስቲያን ከማይጠፋ ዘር በክርስቶስ ደም የተመሠረተች እንጂ እንደ ፖለቲካ ምክር ቤት በዘር በጎሣ የተመሠረተች አይደለችም። ቤተክርስቲያን የሁሉም ለሁሉም ነች ያለው ዐብይ ኮሚቴው ዛሬ በወከባና በጫና ለተለየ ብሔርና ጎሣ ተለይቶ የኢጲስ ቆጶስ ሲመት ቢሰጥ ነገ በዚህ ሰበብ ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል ዘርና ቋንቋን መሠረት አድርጎ የሚከተለውን ጥያቄና በጥንታዊት ሐዋርያዊት ዓለም አቀፋዊት አንዲት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተነጣጠረውን የፈተና እና የመከራ ማእበል መመለስም መዳኘትም ይከብዳል ብሏል።
ይህን ጽንፍ የወጣ አጀንዳ በድምጽ ብልጫ በማስወሰን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖናን በመጣስ መፍትሔ የሚያመጡ መስሎአቸው የሚተጉ አባቶችም ቤተክርስቲያንን ወደማትወጣው መከራና ፈተና እየገፏት እንደሆነ ሊረዱት ይገባል ብለን እናምናለን።
በዚህ መግለጫ ብፀዓን አባቶችንን በታላቅ ትህትና ዐቢይ ኮሚቴው ማሳሰብ የሚፈልገው ይህ አጀንዳ አስተዳደራዊ ሳይሆን ሃይማኖታዊ/ዶግማዊ እና ሥርዓታዊ/ቀኖናዊ አጀንዳ በመሆኑ በሕገ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንቀፅ 19፡ 5፡ ሐ መሰረት በሙሉ ድምጽ እንጂ በድምፅ ብልጫ ስምምነት ተደርጎበት ውሳኔ ላይ ሊደረስ የማይገባው አጀንዳ መሆኑንም ኮሚቴው በሚገባ ያምናል ብሏል፡፡
በተለይም ይህ አለመግባባት እየሰፋ መጥቶ ውሳኔው በድምጽ ብልጫ የሚደረግ ከሆነ ሕገ ቤተክርስቲያንን እና ቀኖና ጥሰትን ስለሚያመጣ፤ ውጤቱም በብፁዓን አባቶች መካከል ያለውን መከፋፈል አስፍቶ ቤተክርስቲያንን ወደ ከባድ ፈተና የሚያደርስ ጉዳይ በመሆኑ ብፁዓን አባቶች በፍፁም መከባበር፤ ምድራዊ እና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ፍጹም ጸያፍ እና የተወገዙ በሆኑ ጉዳዮች፣ዘርን፣ ቋንቋን፣ ጎጥን ፖለቲካን፣የግል ጥቅምንና ፍላጎትን ሳይሆን የረቂቃኑ እና ግዙፋኑ፤ የሰማያውያን እና የምድራውያን ልዩ ጉባኤ፤አንዲት የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማዕከል በማድረግ ብቻ አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ሆናችሁ በእርጋታ በመነጋገር ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚጠቅም ውሳኔ በአንድ ድምፅ ሰጥታችሁ እንደምትወጡና የአሁኑንም ሆነ የሚመጣውንም ትውልድ የመከራ ቀንበር እንደምታቀሉ ባለሙሉ ተስፋ ነን፡፡
መግለጫው ከቅዱስ ሲኖዶስ የምንጠብቀው ውጤት በማለት ዐራት ነጥቦችን ዘርዝሯል።
0ቢይ ኮሚቴው በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከተከናወነው ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ጋር በተያያዘ በቤተ ክርስቲያን ላይ የተጋረጠው አደጋ መነሻ አድርጎ የተቋቋመ ሲሆን ከ10 በላይ ማኅበራትን ማለትም ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፣ ከነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የምዕመናን ኅብረት፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ ጴጥሮሳውያን ኀብረት፣ የጎልማሶች እና ወጣቶች ማኅበር፣ ከወልዳ ዳንዲ አቦቲ፣ ከደጆችሽ አይዘጉ ማኅበር፣ ከሕግ ባለሙያዎች እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች የተወጣጣ ነው፡፡
ተክለሃይማኖት ባህታዊ
ተክለሃይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
በአደባባዩ ተተክለሀል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሀል
አዝ
ቃልኪዳን አለህ የገነነ
ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውኃ አጠጥተን
ዋጋችን በዝቷል አባታችን
አዝ
እኛም ሆነናል ልጆችህ
ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ
በምልጃህ ጸሎት ትሩፋት
ቤታችን መላ በረከት
አዝ
ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሀል
አዝ
ተሰባበሩ ጣኦታቱ
አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ከአፍህ ወጥቶ
የአምላክ አድርጓል ሁሉን ገዝቶ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
"እኔ የሃይማኖት መምህር ነኝ፤ በተከሰስኩበት ወንጀል አልተሳተፍኩም"
መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ከ4 ጠበቆቻቸው ጋር የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ይግባኝ ወንጀል ችሎት ዛሬ ረፋድ ቀረቡ።
ግንቦት 4/2015 ዓ᎐ም ባሕር ዳር ከተማ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ የመጡት መምህር ኃ/ማርያም ግንቦት 7 በነበረ ችሎት ፖሊስ በጠየቀው መሠረት ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ይታወሳል።
ሆኖም ትናንት ግንቦት 10/2015 ዓ᎐ም በጠየቁት ይግባኝ መሠረት ዛሬ ግንቦት 11/2015 ዓ᎐ም ረፋድ 4 ሰዓት ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ይግባኝ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
በችሎቱ 4 ጠበቆች የቆሙላቸው ሲሆን ክሱ "በማኅበራዊ ሚዲያ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ᎐᎐᎐" የሚል ነው። ለዚህም ማስረጃ ለማምጣት የሚያስፈልገው አትሞ ማምጣት ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ 14 ቀናት መቀጠሩ አግባብ አይደለም።" በሚል ክርክራቸውን አቅርበዋል።
መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ በበኩላቸው" እኔ የሃይማኖት መምህር ነኝ፤በተከሰስኩበት ወንጀል አልተሳተፍኩም፤ በአሁኑ ሰዓት ወሎ ዩኑቨርስቲ በሰጠኝ እድል በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ 2ኛ ድግሪ ተማሪ ነኝ።እዚህ በመሆኔ ፈተና እና መሰል ጉዳዮች እያለፉኝ ነው፤ይህም 1 ተጨማሪ ዓመት የሚያስደግመኝ በመሆኑና ብፈለግም የታወቀ አድራሻ ያለኝ በመሆኑ የዋስትና መብት ይሰጠኝ።" ሲሉ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ለሰኞ ግንቦት 14/2015 ዓ᎐ም 3 ሰዓት የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ለማየት እና በዛው ቀን 5 ሰዓት ከሁለቱ ወገን በቀረበው መከራከሪያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል።
😇ስለ ቁርባን ከምዕመናን የመጣ ጥያቄ😇
👉ሕንደኬ:
ይቅርታ ግን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን በየሳምንቱ የምትችል ሰውነት አለች?እሳት ነውና በየሳምንቱ...ሲባል ሰምቻለሁ
እንዴት ነው ይህ ነገርስ???
👉መልስ👈
በገዳም ያሉ መነኮሳት፣በዓለም ላይም ያሉ መንፈሳዊያን እናት እና አባቶች ይቀበላሉ።
እንዴት ቢሉ ለመነኮሳቱ እግዚአብሔር አምላክ መልአኩን ሁልጊዜ በመላክ በቤተክርስቲያን ቆርበው ሲወጡ ክፉ ቃል ከተናገሩ ሰዎች፣ በመጥፎ ግብር ለሚውሉ ሰዎች የተላከው መልአክ በጉጠጥ(በመቆንጠጫ) ከሆዳቸው ውስጥ የቆረቡትን ቁርባን አልተገባቸውምና፣አላከበሩትምና በጉጠጥ አውጥቶ በበረኃ ላሉ ገዳማውያን ያድላቸዋል።
😔እኛ ቆረብን ብለን ስንኩራራ መልአኩ በጉጠጥ ምን ያህል ጊዜ ከሆዳችን ውስጥ የከበረውን የአምላክ ሥጋ እና ደም አወጣው?😣 በቸርነትህ አድነን አቅም የለንምና ጠብቀን