ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ስለ_ዳግም_ምፅዓት
(አቶ አለሙ አጋ በገና)
ቅኝት - ሰላምታ

እንዲህ አርገን ሥራውን ሁሉ አምነን
እናምናለን ዳግም ይመጣል ብለን
ነገር ግን ዳግም ይመጣል ስላልን
ከፃድቃን ከመላእክትም ቢሆን
የሚያውቅ የለም የሚመጣበት ቀኑን
ባላወቅነው ባልመረመርነው ሰዓት
ግሩም ሆኖ ይመጣል እንጂ ድንገት
መጀመሪያ የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ከያለበት ይሰበሰባል በአንድ አፍታ
አጥንታችን ትቢያ የሆነው አፈር
ጅብ የበላው የተበተነው ከዱር
የራስ ፀጉር የእግር ጥፍራችን ሳይቀር
ተሳስቶ የአንዱ ወደ አንዱ ሳይዞር
በየራሱ ይሰበሰባል ሁሉም
ይመታል የአዋጅ ነጋሪት ዳግም
ነፍስ የሌለው በድን ይሆናል ፍፁም
በሶስተኛው የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ይነሳሉ መልካም የሠሩ በእልልታ
የብርሃን ልብስ የብርሃን ቀሚስ ለብሰው
እንደ ፀሐይ እንደ ጨረቃ ደምቀው
እግዚአብሔርን ፈጣሪያቸውን መስለው
ይሰሙና በቀኙ ቆመው ፍርዱን
ከማያልፈው ተድላ ደስታ በቀር
ጠግቦ ቁንጣን ተርቦ ስስት ሳይኖር
ገብቶ መውጣት አግኝቶ ማጣት ችጋር
የሌለባት ደገኛይቱን ሀገር
ይወርሳሉ መልካም የሠሩ በምድር
ኃጥአንም እጅግ ከጭራ ቀጥነው
መልካቸውም እጅግ ከቁራ ጠቁረው
ከላይ ከታች የጨለማ ልብስ ለብሰው
ዲያብሎስን አለቃቸውን መስለው
ይሰሙና በግራ በኩል ቆመው
በመንቀጥቀጥ የሚፈርደውን ሰምተው
ከልቅሶና ጥርስ ማፋጨት በቀር
ተድላ ደስታ የሌለባትን ሀገር
ይወርሳሉ ክፉ የሠሩ በምድር
እንዲህ አርገው መጻሕፍት ሁሉ እንዳሉ
በየሥራው ይከፈለዋል ለሁሉ
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም አሜን

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በጾም

በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ
ወበጸሎት ትትሐሠይ መንፈስ /2/

መአልትና ሌሊት በጾም ጸሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመች በጾምና ጸሎት
አዝ
ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው
ፊቱን የበራለት አርባ ቀን ጾሞ ነው
በሲና ተራራ ተቀብሎ ህግን
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድን
አዝ
የጸሎት እናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን
ብንተጋ በጸሎት ከንስሐ ጋራ
ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ
አዝ
አንድበትም ይጹም ዓይንም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድሀን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲህ ነው የበደለን ክሶ

ዘማሪ መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ኪዳን እናደርሳለን ባሉ ከሕገ ወጡ ተሿሚ ወገን በሆኑ 4 ግለሰቦች አማካኝነት ከቤተ ክርስቲያኑ ሽቶ፣ ዕጣንና መብዓት ይዘው ሲወጡ መያዛቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁኔታውን የተመለከተው የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ጥይት በመተኮስ ምእመናን ተሰብስበው ሁለቱ ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ዝርፊያ የፈጸሙት ግለሰቦችን ምእመኑ ለከተማው ፖሊስ ያስረከበ ቢሆንም የከተማው ፖሊስ ግን ግለሰቦቹ ይህንን አያደርጉም አውቃችሁ ነው በሚል ያለምንም ማጣራት ግለሰቦቹን መልቀቁ ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ የቤተ ክርስቲያኑን ጠባቂ ለምን ወደ ሰማይ ተኮስክ በሚል ማሰራቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ መግቢያ ድልድይ እየተሠራ እንደሆነ ተገለጸ።

የቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ በቅዱስ ላሊበላ ከታነጹት 11 ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ሲሆን የቤተ መቅደሱ መግቢያ ከቤተልሔሙ የጸሎት ቤት ፊት ለፊት በምሥራቅ በኩል ይገኛል። በሌላ በኩል ከቤተ አማኑኤል ቤተ መቅደስ በሚመጣ ተሻጋሪ ድልድይም መግባት የሚቻል ሲሆን ድልድዮቹ ከዛፍ ግንዶች ርብርብ እንደተሠሩ ርዝመታቸውም 10 ሜትር መሆኑ ይነገራል።

በዛሬው ዕለት ወደ ቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ መግቢያ ድልድይ በፈረንሣይ ላሊበላ ዲቨሎፕመንት ፕሮጀክት አማካኝነት እየተሠራ እንደሚገኝ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#የአድዋ_ድል_ቤተ_ክርስቲያን_በገነባችው_የሥነ_ልቡና_ልዕልና_የተገኘ_ነው::

ክፍል ሦስት
አፈ ሊቅ አክሊሉ ገብረ ኪሮስ የተባሉ ሊቅ ‹‹ለኢትዮጵያ ታሪኳ-ነው መልኳ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው የአድዋውን ድል መሠረት እንደሚከተለው ገልጠዋል።
‹‹… ምኒልክን ለአድዋው ድል ያበቃቸው
አንዱም ፣ ኦርቶዶክሳዊ እምነታቸውና የልብ ጸሎታቸው ነው።›› (ገጽ፣፷፭)
ዳንኤል ሮኘስ የተባለ ታዋቂ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ‹‹የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ታውቋታላችሁን?›› በሚል ርእስ ባዘጋጀው መጣጥፍ ላይ የሚከተለውን አስፍሯል።
“ወራሪዎች ምድርዋን የያዙባት መሆኑን ታሪክ ያወሳል፤
ነገር ግን ሃይማኖት የእንቅስቃሴ መሣሪያዋ ሆኖ በመገኘቱ በነፃነት ተመልሳ ተገኝታለች››
የአድዋን ድል በቀጥታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ጋር ያያያዙት ሌሎችም ኢትዮጵያን በአፍሪካ እንደምትገኝ ኢየሩሳሌም አድርገው መቍጠር ጀምረው ነበር። ፕሮፌሰር ሬይሞንድ ጆናስ ‹‹ THE BATTLE OF ADWA:-African victory in the age of Empire›› በተሰኘው ታሪካዊ መጽሐፋችው ‹‹የዓድዋን ድል ተከትሎ በመላው ዓለም ተበትነው ያሉ ዝርዋን አፍሪካውያን የዓድዋን፣ የምኒልክንና የነጻይቱን አገር ኢትዮጵያን ስም በልዩ ሁኔታ ማንሣት ጀመሩ፤ ጥቁር ሕዝቦች እንደ ታላቂቷ ጽዮናዊት ኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ጉዞ ማድረግ ጀመሩ።›› ሲሉ መግለጻቸው ለዚህ ምስክር ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የኢትዮጵያ ገበዝ
የኢትዮጵያ ጠባቂ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ላይ መንግስት ተኩስ ከፍቷል! ምዕመኑ በዓሉን ማክበር ታቦቱን ማንገስ አልቻሉም።

ተዋግቶ ኢትዮጵያን ላስከበራት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መሳርያ ይገባዋል???‼️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቐለ አሉላ ኣባነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሰላም ገብተዋል።

በአየር ማረፊያው ሲደርሱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የቤተ ክህነት ሠራተኞች እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምእመናን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መች ይረሳል
የበገና መዝሙር

መች ይረሳል የዋለልን ውለታ
ቸርነቱ እፁብ ፍቅር የጌታ
የታተመው በልባችን ፅላት
ሞትን ገድሎ የሠጠንን ህይወት

በጥፋቱ ቢወጣ አዳም ከገነት
ቃል ገባለት ዳግም ሊሰጠው ህይወት
ህያው ጌታ አምላክ ፈጣሪ ሳለ
ስለ ቃሉ በእፀ መስቀል ላይ ዋለ
አዝ
በአይሁድ እጅ በፅኑ ተንገላታ
የፍቅር አባት ክርስቶስ የእኛ ጌታ
ሥጋው ደክሞ ቅዱስ ደሙ ፈሰሰ
እዳችንን በሞቱ ደመሠሠ
አዝ
ስንጠላው እርሱ አብዝቶ ወደደን
ስለ ፍቅሩ ሞትን ገድሎ አዳነን
ባርነትን ኃጢአትን ከኛ ጥሎ
ነፃ አወጣን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ
አዝ
ሰላማችን የድንግል ማርያም ፍሬ
ይገባዋል ምስጋና ዝማሬ
ስለ ፍቅሩ ስላረገልን ሁሉ
ተቀኙለት ፍጥረታት ዝም አትበሉ

መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#እያለፈ_ነው_ዘመኔ

እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ/2/ 
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ/2/ 

በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ/2/ 
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ/2/ 

የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ /2/ 
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ /2/ 

እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/ 
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ/2/ 

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ/2/ 
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ/2/ 

ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/ 
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ/2/ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ወዴት ወድቆ ይሆን
የበገና ዝማሬ

እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶ
መልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው ወጥቶ
ለአጨዳው ምጽአት ለበጋው አዝመራ
ወዴት ወድቆ ይሆን ክረምት የተዘራ /2/

ዘወድቀ ውስተ ፍኖት ሲዘራ ያለቀው
አእዋፍ ሰማይ መሳጤ ነጠቀው
ዘወድቀ ዲበ ኮክሕ ጥልቅ አፈር ከሌለው
በደስታ እየሰማ በችግር የካደው
ዘወድቀ ውስተ ሦክ ተጨንቆ እንዳይወጣ
በዓለም ትካዜ በስፍጠተ ብዕል ታንቆ ፍሬ አጣ

ውስተ ምድር ሠናይ የወደቀም ነበር
ዘወሀበ ፍሬ ሰምቶ ሚተገብር
ጌታዬ ከአራቱ ስፍራዎች በምሳሌ ካልከው
ወዴት ወድቆ ይሆን ከእኔ ልብ የላከው
እባክህ ጎተራ አበጅተህ ለአጨዳ ስትመጣ
ከፍሬያማው ክምር ዕድል እንዳላጣ

ከእሾህ ከጭንጫ ላይ ከመንገድ እንዳልቀር
ልቤ ልብ አግኝቶ በምግባር እንዲኖር
ራሴን መስማት ትቼ ላንተ ፈቃድ ልደር

ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ለምን_ጠላኸኝ_ወንድሜ

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ አባት ልጆችኮ ነን
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ የእናት ልጆችኮ ነን
ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን

የተካፈልኩትን ንብረት
አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ
ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል
ብዙ ነው የርሱ መንግስት
አይክፋህ እባክህ ወንድሜ
ፍቅር ይበልጣል ከሃብት
#አዝ
ፊትህ በሐዘን አይጥቆር
ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ
እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ
ያንተም መስዋዕት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው
መታዘዝ ንጉሥ ያደርጋል
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ አገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም

ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✣ የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ✣

╔════●◉❖◉●══════╗
ቅድስት
╚════●◉❖◉●══════╝
✢ Share ✢
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በዓብይ ጾም በገና ክራር እና መሰንቆ ለመማር ለምትፈልጉ ደውሉልን ተመዝገቡ።✝


ዓብይ ጾምን በመንፈሳዊ ዝማሬ ያሳልፉ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ችግር ምክንያት የተደራጀው የሽምግልና ኮሚቴ እስከ አሁን የሰራቸውን ስራዎች ለዐቢይ ኮሚቴው ሪፖርት አደረጉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተከሰተው የቀኖና፣የሃይማኖትና የአስተዳደር ጥሰትን ተከትሎ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር ምክንያት ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት የተደራጁት የሽምግልና ኮሚቴዎች (የሀገር ሽማግሌዎች) ችግሩ ከተፈጠረ ወዲህ በኮሚቴው የተሠሩ ሥራዎችን እና ወደፊት ሊሠሩ ስለሚገባቸው ጉዳዩች ለዐቢይ ኮሚቴ፣ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለመንበረ ፓትርያርክ እና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ዛሬ የካቲት ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም ሪፖርቱን አቅርቧል።

በቀረበው ሪፓርት ላይም ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በሽምግልና ኮሚቴው ወደፊት በሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ ከዐቢይ ኮሚቴው ምክረ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን ወደፊትም የቤተክርስቲያን አንድነትና ሉአላዊነት እስከሚረጋገጥና ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ መደበኛ አገልግሎታችን እስከሚቀጦል ድረስ የተጣለባቸውን መንፈሳዊ አገልግሎት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ፤ በመግለጽ ጉባኤው በጸሎት ተጠናቋል።

ምንጭ፡ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅዱስ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

አስቀድሞ የነበረ አሳልፎ የሚኖር
በሥልጣኑ ያጠፋልን ሙስና መቃብር
ከአባቱ ጋር ትክክል ነው በኃይል በጌትነት
በዓለም ሊፈርድ የሚመጣው በክብር በትስብእት

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

የሰው ፍቅር አገብሮት ወደ ምድር የመጣ
ከሰማያት የወረደው ወደ ሰማይ የወጣ
ከምስጉኖች ይልቅ ምስጉን ከግሩማን ግሩም
የጠቢባን ጠቢብ ጌታ የሚመስልህ የለም

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አማኑኤል

ብንዳስሰው ብንበላው ደግሞም ብንጠጣው
ረቂቁ የገዘፈው ሥጋን ተዋሕዶ ነው
በደመናት መጋረጃ የተሰወረ እሳት
በግርግም ውስጥ አገኘነው በግዕዘ ሕፃናት

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

ሰማያትን የዘረጋ ውኆችን የፈጠረ
የማይታይ የሚታየው በእርሱ ተፈጠረ
ሁሉን በእጁ የጨበጠ አሸናፊው ልዑል
በቤተልሔም ተወለደ ከማርያም ድንግል

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

ዘማሪ መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምኵራብ
 
እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስትኛ ሳምንት አደረሰን!
 
የዐቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት ‹ምኵራብ› ይባላል፡፡ አይሁድ በሰቀላማ መሰሉ አዳራሽ በምኵራብ ጸሎት ያደረጉ ነበር፤ ስለዚህም “የጸሎት ቤት” ተባለ፡፡ የቃሉ ስያሜም የተገኘው ‹‹በመቅደስም በሬዎችን፣ ላሞችን፣ በጎችን፣ ርግቦችን፣ የሚሸጡትን አገኘ›› ተብሎ ከተገለጸው ቃል ነው፡፡ ‹ምኵራብ› የሚለው ቃልም በአማርኛ ‹መቅደስ› ተብሎ ተተርጕሟል፡፡ (ዮሐ.፪፥፲፬) 
 
ምኵራብ አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈጸምበት እንዲሁም ሕገ ኦሪት የሚነበብበት በአይሁድ የሚሠራ መካነ ጸሎት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀዳሚት ሰንበት በምኵራብ በርካታ ሕዝብ ይሰበሰብበት ስለነበር ሊያስተምራቸው ተገኝቶ ነበር፡፡ እርሱም ከዚያ እንደደረሰ  “በመቅደስም በሬዎችና በጎችን ርግቦችን የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ። የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፤ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ። ርግብ ሻጮችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል” አላቸው። (ዮሐ.፪፥፲፪-፲፮)
 
ስለዚህም ምኵራብ በተባለው የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምኵራብ የገባበትንና ማስተማሩን የሚነገርበት፣ በምኵራብ ይሸጡና ይለውጡ የነበሩትን ሻጮችንና ለዋጮችን የገሠፀበትና ከቤተ መቅደስም ከነሸቀጣቸው ያስወጣበት፣ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ማደሪያ፣ የስሙ መጠሪያ እንዲሁም የጸሎት ሥፍራ መሆኗን ያስረዳበትና ያወጀበትና በቤተ መቅደስ የንግድ ሥራ ማከናወን እንደማይገባ ያረጋገጠበት ዕለት ነው፡፡
 
አምላካችን እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጎብኘን!
 

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መቄዶንያ የ1 ሚሊየን ዶላር ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱን ገለጸ።

መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ የ1 ሚሊየን ዶላር የማሰባሰብ መርሐ ግብር እንደሚካሔድ ተገልጿል፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያው ዋና ዓላማ ማዕከሉ በመገንባት ላይ ለሚገኘው ባለ 12 ወለል ሕንጻ የ1ሚሊየን ዶላር በመሰብሰብና በርና መስኮቱ በመግጠም ሕንጻው እስኪጠናቀቅ ድረስ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ታስቦ የተዘጋጀ መርሐ ግብር መሆኑ ተነግሯል፡፡

መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ምንም ዓይነት የውጪ ድጋፍ የሌለው በመሆኑ እስከ አሁን እያገዙ ያሉ ግለሰቦች ወደፊትም እንዲያግዙ ለማድረግ እንዲሁም የሚሠራቸውን ሥራዎች ቁጥር ለመጨመር በማሰብ የተጀመረው ሕንጻ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ2.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚፈጀው ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ ሕንጻ በተጀመረ በ3 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ግንባታው 70% ተጠናቋል።

ማእከሉ በአሁኑ ሰዓት ከ10 በላይ ከተሞች ከ7ሺ በላይ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማንን እየረዳ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም አገልግሎቱን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ለማድረግና ከ20ሺ በላይ አረጋውያንን እና አእምሮ ሕሙማንን ለመርዳት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ በዶንኪ ትዩብና በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የካቲት 26 እሑድ ከ9 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠይቋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አንድ ጣልያናዊ ተዋጊም ‹‹በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ወደ ቀኝና ወደ ግራ እየተመላለሰ ወደ ጦርነቱ ግቡ ኢጣሊያኖችን ማርኩ እያለ ትእዛዝ ሲሰጥና ሲዋጋን የዋለ ማነው?›› ብሎ መጠየቁ እየተገለጸ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጋዥነት መገለጹም እዚህ ላይ መነሣት የሚገባው ነው። (በአድዋ ጦርነትና ድል...፣፶፫)። ይህንንም በአንድ ባለ ቅኔ፡-
‹‹ኃይል ውእቱ ዘጊዮርጊስ፣
አኮኑ ኵዕናት
በላዔ ሮማዊት ነፍስ፣
ዘጌዴዎን ምኒልክ
ዘአውረደ በዐውደ ሮምያ
ጠለ ደም እምርእስ። (በአድዋ ጦርነትና ድል...፣ ፶፪)።
(የሮማዊትን ነፍስ (ሰውነት) የበላ (ድል ያደረገ) የጊዮርጊስ ኃይል እንጂ ጦር አይደለም፣የጌዴዎን ምሳሌ ምኒልክ በሮምያ አደባባይ ከራስ ላይ እስካወረደ ጠብታ ደም።) ተብሎ የተነገረ ነው።
የአድዋ ድል ብሔራዊና ዓለም ዐቀፋዊ ትሩፋቱ ባሻገር ሃይማኖታዊ ትሩፋቱም መነገር የሚገባው ነው። ‹ኢትዮጵያውያንን እንደ እስራኤል ዘነፍስ መቍጠርና ሀገሪቱንም ጸጋ እግዚአብሔርን የታደለችና ሀገረ እግዚአብሔር እንደ ሆነች አድርጎ ማየት፣ ሀገረ እግዚአብሔር ከሆነች ዘንድም መደፈር የለባትም በሚል እሳቤ ድንበሯን መጠበቅና በዚህም ሂደት መሠዋት የዜግነት ክብር ብቻ ሳይሆን ጽድቅም ነው ብሎ ማመን› ለኢትዮጵያውያን አዲስ እሳቤ ባይሆንም በአድዋ ድል ግን ይበልጥ ጠንክሯል፤ ከዓለም ሕዝብ መካከልም ይህንን ያመኑ እጅግ ብዙ ነበሩ። ከነጮች ተፅዕኖ ነፃ የሆነ  የጥቁሮች የሃይማኖት እንቅስቃሴ በተለይ በአሜሪካና በደቡብ አፍሪካ ‹ኢትዮጵያኒዝም› በሚል ስያሜ እንዲጀመር መሆኑ ለዚህ ምስክር ነው።
ለማጠቃለል ያህል የአድዋ ድል ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በገነባችው የመንፈሳዊ ሥነ ልቡና ብርታትና ለሀገርና ለሃይማኖት እስከ ሞት የመጋደል ወኔ የተገኘ መሆኑ ከድሉ እኩል መነገር ያለበት ነው። ኢትዮጵያውያን የኢጣሊያን ወረራ በሀገረ እግዚአብሔር ላይ እንደ ተደረገ ሰይጣናዊ ጥቃት ነበር የቈጠሩት። ለዚህም ነው ድሉን እንኳን ሰይጣን ድል ከተነሣበት ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር በማመሳሰል
‹‹ሞዖ ለሞት
ሠዐሮ ለጣዖት
ገብረ ትንሣኤ በሰንበት›› እያሉ ዳግመኛም
‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ
ተሐፂባ በደመ ሰማዕታት››
ብለው እየዘመሩ ያከበሩት። (በአድዋ ጦረነትና ድል…፣ ፷)።
የአድዋ ጦርነት ሊጀመር ሰዓታት በቀሩበት ጊዜ እንደ ተዋጊ ሳይጨነቁ፣ ሁሉን ትቶ በተጠንቀቅ ከመቆምና የነደፉትን የውጊያ ስልት ከማሰላሰል ይልቅ ‹እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ይበልጣል› በሚል ታላቅ የሥነ ልቡና ዐቅም ዐፄ ምኒልክ፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ ራስ መኮንን፣ ራስ መንገሻ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ …ወዘተ በአድዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እያስቀደሱ ነበር። በርግጥ ከዚህም በኋላም ንጉሡ በእርጋታቸው ጸንተው ዕለቱ ጊዮርጊስ በመሆኑ አሁንም ወደማይጕዓጕዓ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ልባዊ ጸሎትን አቅርበው ነበር። በጦርነት መጀመሪያ የመጨረሻው ሰዓት ለዚያውም ዐቅሙ እጅግ የሚገዝፍ ጠላት ከፊት ተደግኖ እንዲህ ዓይነት መረጋጋትን ያሳዩ ሌሎች ተዋጊዎች መኖራቸው እጅጉን አስገራሚ ነው። ይህ በርግጥም መንፈሳዊ ጥብዐት እንጂ ምን ይባላል?
በአድዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፡ ተሰብስበው ሲያስቀድሱ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ቀዳሽ ነበሩ። እርሳቸውም ከቅዳሴ በኋላ ሲያስተምሩ እንዲህ አሉ፡-
‹‹ልጆቼ ሆይ… ዛሬ የእግዚአብሔር ፍርድ የሚፈጸምበት ቀን ነው። ኺዱ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ ሙቱ፤ እግዚአብሔር ይፍታህ››። (ጳውሎስ ኞኞ፣ ፪፻፫)።
በእውነት የእግዚአብሔር ፍርድ በዕለቱ ተፈጸመ፤ ለሀገርና ለሃይማኖት የተሠዉትን ሁሉ ነፍሳቸውን ይማርልን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አባቶቻችን ይህንን የበዛ የ"መንግስት" ንቀት በዝምታ ማለፍ የለባቸውም! መግለጫ እንጠብቃለን!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዓድዋ የኢትዮጵያ ከፍታ

🎇 ለፌስቡክ, ለቴሌግራም እንዲሁም ለተለያዩ ሶሻል ሚድያ እንደ ፕሮፋይል መጠቀም ይችላሉ

ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ አቀኑ።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው  ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ተቀብለዋል ።

ምንጭ: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዜና ሽፋን ጥቆማ

የብፁዕ ወቅት አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን ፲ኛ ዓመት በዐለ ሢመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጁት "ዜና መዋል ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ" እና "ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ " የተሰኙት መጽሐፍት የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ይመረቃሉ።

ስለሆነም በደብዳቤው ላይ የተጠቀሳችሁ የሚዲያ ተቋማት በዕለቱና በቦታው በመገኘትና ዘገባውን በመስራት ለሕዝብ ይፋ እንድታደርጉ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን ።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዜና ዕረፍት

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል

በረከታቸው ይደርብን።

ምንጭ፡ EOTC TV

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሄደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ /፪/

ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ጽናት
አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያጽናናት
ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ
እሕት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

መቅደላዊት ማርያም ሶሎሜ ዮሐና
ማርያምን አይዋት ጸንቶባት ሐዘኗ
በልቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው
ዕንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው
ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳ ነው
ያዕቆብም አልቅሷል በሌላ የሠው ደም
ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ጠብቶ ስለአደገ የድንግልና ጡቷን
መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን
በደም ተሸፍኖ ብታየው ውበቱን
ለይልኝ አለችው ከሥጋዋ ነፍሷን

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሔደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ

በእንተ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሠላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን!

✝በዓብይ ጾም በገና፣ክራር ወይም መሰንቆ መማር ትፈልጋላችሁ?✝

እንግዲያውስ ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ
በዓብይ ጾም ምዝገባ ጀምረናል የ6 ወር እና የ3ወር ትምህርቶችን።


🫴መማር ለምትፈልጉ ቶሎ ይደውሉ እና ይመዝገቡ ☎️ 0956861468 ወይም 0912085085

በቴሌግራም ለማውራት ደግሞ @Orthodoxtewahed0


👉በገና፣ክራር እና መሰንቆ መሳሪያዎችን መግዛት ለምትፈልጉም ደውሉልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በወለጋ ነቀምቴ ከተማ መንበረ ጵጵስናው በሚገኝበት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ውጥረት ተከስቷል።

የብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሀገረ ስብከት በሆነው በነቀምቴ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስን ትእዛዝ በሚቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን እና ሕገወጡን ተሿሚ እንቀበላለን በሚሉ ከሌላ አካባቢ በመኪና ለሁከት እንዲመጡ በተደረጉ ሰዎች መካከል ውጥረት መከሰቱ ተገልጿል።

ጉዳዩ የተከሰተው ነገ የሚታሰበውን ወርኃዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓል ምክንያት በማድረግ ሕገወጥ ተሿሚ የሆነውና ደጋፊዎች ነን የሚሉ ወደ ገዳሙ እንገባለን በማለታቸው እና በሰንበት ተማሪዎች፣ ኦርቶዶዶክሳውያን ወጣቶችና የአካባቢው ምእመናን ቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘ አካል በገዳሙ አይገባም በማለታቸው ነው።

ውጥረቱን ለማርገብ የመከላከያ ሠራዊት የተገኘ ሲሆን የከተማው ከንቲባና የከተማው ፖሊስ አዛዥ ጉዳዩን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ከብሔርና ፖለቲካ ጋር በማገናኘት መፍትሔ ሳይሰጡ በማባባስ ላይ እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ምእመናን፣ ወጣቶችና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቁ ይገኛሉ።

ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በሕገ ወጥ መንገድ በወሊሶ የተሾሙ 25 "ኤጲስ ቆጶሳት" በቅዱስ ሲኖዶስ መወገዛቸው እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ማገዱ ይታወሳል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሠላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን!

✝በዓብይ ጾም በገና፣ክራር ወይም መሰንቆ መማር ትፈልጋላችሁ?✝

እንግዲያውስ ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ
በዓብይ ጾም ምዝገባ ጀምረናል የ6 ወር እና የ3ወር ትምህርቶችን።


🫴መማር ለምትፈልጉ ቶሎ ይደውሉ እና ይመዝገቡ ☎️ 0956861468 ወይም 0912085085

በቴሌግራም ለማውራት ደግሞ @Orthodoxtewahed0


👉በገና፣ክራር እና መሰንቆ መሳሪያዎችን መግዛት ለምትፈልጉም ደውሉልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስሆነም የደረሱትን እና እየደረሱ ያለትን ጉዳቶች በተመለከተ ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ማሰባሰቡ ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ እና አሁንም የሕግ ክፍሉ በተለያየ መንገድ በሚደርሰው መረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ በውስንነት ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሶ መረጃ እና ማስረጃ ያላቸው ማናቸውም ምእመናን እና ምእመናት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጆቻችሁ ላይ ያለ የሰነድ፤የድምጽ፤ እና የምስል ማስረጃዎቻችሁን በሙሉ ከዚህ በታች በተቀመጡት አማራጭ የመረጃ መንገዶች ታሳውቁን ዘንድ የሕግ ክፍሉ ያሳስባል፡፡

በመሆኑም ፦
፩. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ውስጥ ተቀጥራችሁ ስትሠሩ የነበራችሁ እና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ከሥራ እና ከደመወዝ የታገዳችሁ እንዱሁም የተሰናበታችሁ በሙሉ ዝርዝር መረጃውን በመላክ እንድታሳውቁን፤

፪. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ሙለ መረጃ በመላክ እንድታሳውቁን፤

፫. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ሙለ መረጃ በመላክ እንድታሳውቁን፤ እያሳሰብን ያላችሁን ማናቸውም መረጃ እና ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከተነገረበት ከዛሬ የካቲት ፲፰ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ጀምሮ በስልክ ቁጥር +251985585858 በዋትስአፕ፤ በቴሌግራም ወይም በኢሜይል አዴራሻችን፡-eotcer@gmail.com የሞቱትን፤ የተጎደትን፤ የታሠሩትን እና የተሰወሩትን ሰዎች ስም እና የድርጊቱን ውጤት የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ ታጋሩን ዘንዴ በቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላፋሇን፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

Читать полностью…
Подписаться на канал