#በተለይ_ለኦርቶዶክሳውያን
አምልኮ/ምስጋና/ ማለት ክርስቶስ ራስ ለኾነላት ቤተ ክርስቲያን ለተባለችው አንዲት አካል ብልት ለመኾን የምንጋደልበት ሰማያዊ ሥርዓት ነው። ኦርቶዶክሳውያን በአምልኮ ጊዜ እርስ በእርሳችን ብቻ ሳይኾን ከመላእክትም ጋር ረቂቅ አንድነት አለን። "በሰላም ማሠሪያ (ይህን) የመንፈስ አንድነት ለመጠበቅ እንድንተጋም" ታዘናል። (ኤፌ.4÷3)።
ወደዚህ ሰማያዊ ኅብረት ይመጡ ዘንድም ለዓለም ኹሉ እንደ ሐዋርያቱ እንጮኃለን፤ "ወደ ክርስቶስ ኅብረት በሃይማኖት ኑ" እንላለን። "እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው " እንዲል ሐዋርያው።
(1ኛ ዮሐ. 1÷3)።
ይህን በማድረግ ፈንታ ግን በማይመች አካሔድ ከማያምኑ ጋር መሰለፍ በሃይማኖታችን አይፈቀድም። ስለዚህ ማንም ኦርቶዶክሳዊ በሌላ ማኅበረሰባዊ ጉዳይ እንጂ በሃይማኖት ከማያምኑ ጋር ቢተባበር ራሱን ለካህን ያሳይ፣ በንስሐ ይመለስ።
ወንጌላችንም የሚለው የሚከተለውን ነው:-
"ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?" (2ኛ ቆሮ. 6÷14-15)።
እኔም እላለሁ - ኦርቶዶክሳዊ ከኢሬቻ/ዋቄፈና ጋር ምን ኅብረት አለው?
+ የኢሬቻና የኢኩሜኒዝም አካሔድ መመሳሰል - ሌላው ሥጋት?
የዓለማዊነት (Secularism) አቀንቃኞች ከፖለቲካ ዲሞክራሲን ፣ ከምጣኔ ሀብት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ፣ ከሃይማኖት ፕሮቴስታንቲዝምን ይመርጣሉ፣ ይደግፋሉ። እነዚህ ሦስቱም በዓለማዊነት አቀንቃኞች መደገፋቸው: ለአንድ ማኅበረሰብ በኹሉም መልክ ለዘብተኝነትን ( Liberalism) ስለሚያለማምዱ ነው። አንድ ማኅበረሰብእ ለዘብተኛ ከኾነ ደግሞ ቸልተኝነቱ ይጨምርና ኹሉን ችላ በማለት በእነርሱ ቁጥጥር ሥር ለመዋል ምቹ ይኾናል። ስለዚህ ለዚህ አካሔድ ወግ አጥባቂ (Conservative) ኾነው የሚያስቸግሯቸው ኦርቶዶክሶች ኹሉ (Orthodox Christians, Orthodox Jews, Orthodox Muslims) ጥርስ ውስጥ የገቡ ናቸው። በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የመሰሉ በሥርዓትና በዜማ የደመቁ አብያተ ክርስቲያናትን ለዘብተኛ ለማድረግ በተሐድሶ እንቅስቃሴና በተለያዩ መንግሥታዊ ተጽዕኖዎችም ጭምር እንዲጎዱ ተደርጓል።
ለዚህ ለዓለማዊነት እንቅስቃሴ የተሸረበው ሌላው ሴራ ደግሞ (ምንም እንኳን ጠቃሚ ጎን ቢኖረውም) የኢኩሜኒዝም (Ecumenism) እንቅስቃሴ ነው። ይህን እንቅስቃሴ በቅርቡ እነ ዶክተር ወዳጄነህን የመሳሰሉት እንደሚከተሉት በግልጽ አስረድተው ነበር። በዚሁ እንቅስቃሴ ስም የሚንቀሳቀሱት አንዳንዶች ታዲያ "ከኹሉም ሃይማኖት ጥሩ ጥሩውን ፣ የጋራውን እንውሰድ" በሚል መርሕ ሌላ ዓይነት ፕሮቴስታንቲዝምን ይዘውና ሃይማኖትን በልካቸው አበጅተው ብቅ ብለዋል። ይህንን የሚደግፉት በዋናነት ግላዊነትን የሚያበረታቱት ፕሮቴስታንቶችና ዓለማውያን ናቸው።
ኢሬቻም የዚሁ ኮፒ እየኾነ ነው። በኦሮሞ ፕሮቴስታንቶችና በፕሮቴስታንታዊው ኦዲፒ ከሞላ ጎደል ካለ ምንም ማንገራገር ይደገፋል። ኢኩሜኒዝም በክርስትና ስም የሚንቀሳቀሱትን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ ኢሬቻ/ዋቄፈና ደግሞ ሙስሊሙንም፣ ኦርቶዶክሱንም ፣ ፕሮቴስታንቱንም ማዕከል አድርጓል። ይህም በተለይ ኦርቶዶክሱን በኦሮሙማ ስም ከኦርቶዶክሳዊነት ለማለዘብ የተነደፈ ሴራ ይመስላል።
"ምን ችግር አለው?" የሚል ለዘብተኛ ኦርቶዶክስ ደግሞ በስም እንጂ በግብር የቤተ ክርስቲያን ሊኾን አይችልም። ስለዚህ በተለይ የኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን ትልቅ አስተዋይነትን የሚጠይቅ ጊዜ ላይ እንዳላችሁ ልትገነዘቡት ይገባል። ከኦርቶዶክሳዊነትና በተወዳጅ ባሕል ስም ከመጣ ሌላ እምነት መካከል ያላችሁ የምትወስኑበት ጊዜ እንደኾነ ይሰማኛል።
ኹለቱንም መኾን አይቻልም። ወይ ከጊዜ በኋላ በቅርቡ የሚበርደውን የወቅቱን ሞቅታ መምረጥ ወይም ደግሞ ካለችበት ከፍታ ላይ ሳትወርድ ለዘመናት የኖረችውን ተዋሕዶን መምረጥ ያሻል።
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንንና ምዕመኖቿን፣ ሀገራችንንና ዜጎችን ይጠብቅልን። አሜን።
hilinabzehohite@gmail.com
©ዘሕሊና
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ድንግል_ማርያም_ብዬ
ድንግል ማርያም ብዬ
ስማጸን በስምሽ (፪)
በቅድመ እግዚአብሔር
ልመናዬን አድርሽ (፪)
እኔ ደካማ ነኝ ኃጢአቴ የበዛ
እኔ ጎስቋላ ነኝ በደሌ የበዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በዋዛ ፈዛዛ
ጊዜዬን ያሳለፍኩ በከንቱ በዋዛ
እመብርሃን ስልሽ ፈጥነሽ ድረሽልኝ(፪)
ልመናዬን ሰምተሽ ቆመሽ ለምኝልኝ
ኃጢአቴ ቢበዛም ይዣለሁ አንቺን(፪)
አስምረሻልና በላዒ ሰብን
#አዝ
አንገት የሚያስደፋ በዝቶብኝ ኃጢአቴ
ምልጃሽን ፈለኩኝ ድንግል ሆይ እናቴ
ያን ክፉ ጨለማ እንዳላይ አደራ(፪)
ድንግል ሆይ ከልይኝ ከዲያብሎስ ጭፍራ
#አዝ
እመብርሃን እያልኩ ቆሜ ከደጅሽ
በብርሃን እጆችሽ እንባዬን አብሽ
ዓለም አታላይ ነች ወደሷ ተሳብኩኝ
ታማልጂኝ ብዬ አንቺኑ ተራብኩኝ
ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
"ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ"
መዝ፻፵፩፥፯
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ተአብዮ_ነብሴ
ተአብዮ ነብሴ ለእግዚአብሔር (3)
ሰአሊለነ ማርያም (2)
ሀበወልድክሂር መዳሕኔዓለም
የአብ ሙሽራ ነሽ የወልድም እናቱ
ለመንፈስ ቅዱስ ነሽ ፅራሃዊቱ
በፊትሽ ሰገዱ ቅዱሳን መላእክት
ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
ከዋክብት ብርሃናት ሳይታይ ደመና
ታስበሽ ኖረሻል በአምላክ ህሊና
ገብርኤል ነገረሽ የክብርሽን ዜና
ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
የወርቅ ታቦት ነሽ በሰማይ ያለሽ
የፅድቅ ንግስት ነሽ የተመሰገንሽ
በእናትነትሽ ተመካ ልብሽ
ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
የአለሙን ጌታ በእቅፍሽ አየነው
በመሀፀንሽ አድሮ ቃል ስጋ የሆነው
እግዚአብሔር ስላንቺ ምስጋናው ብዙ ነው
ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
የዳዊት ልጅ ማርያም ትምክህታችን
የአማኑኤል እናት መሰብሰቢያችን
የእግዚአብሔር ከተማ መማፀኛችን
ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
ድንግል በክሊሄም በነፍስም በስጋ
ጎዶሎ ይምላል አንቺን የተጠጋ
ክርስቶስ ወልደሽ ክሳችን ተዘጋ
ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
በፊትሽ ልማፀን ቆምኩኝ ከደጅሽ
ልመናዬ ሁሉ ይግባ ከጆሮሽ
ለሚጠራሽማ ማርያም ቅርብ ነሽ
ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
ሰአሊለነ ማርያም (2)
ሀበወልድክሂር መዳሕኒአለም
ዘማሪ ገ/ዮሐነስ ገ/ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ግሼን_ደብረ_ከርቤ
ሃገራችን ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል። (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው። የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም። "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች። ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም።"
ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው። ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን። ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል።
በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን። ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ።
የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው። እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል።
አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል። አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል።
አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው። ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል።
በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል። ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት በመዳብ በናስ በብር በወርቅ ለብጦ ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል።
በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል። ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል። መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው። ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው።
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
📚ድርሳነ ቅዱስ ገብርኤል
📚መልክዓ ቅዱስ ገብርኤል
የየበዓሉን ድርሳናት መልክዓት የቅዱሳን ታሪክ የምታገኙበትን ቻናል ተቀላቀሉ ከ70,000+ ኦርቶዶክሳዊያን አሉበት ከ350 በላይ pdf መጽሐፍ አሉ።
👇👇👇
/channel/+7Itsth8QSrY2Y2Q0
📚ድርሳነ ቅዱስ ገብርኤል
📚መልክዓ ቅዱስ ገብርኤል
የየበዓሉን ድርሳናት መልክዓት የቅዱሳን ታሪክ የምታገኙበትን ቻናል ተቀላቀሉ ከ70,000+ ኦርቶዶክሳዊያን አሉበት ከ350 በላይ pdf መጽሐፍ አሉ።
👇👇👇
/channel/+7Itsth8QSrY2Y2Q0
በካቴድራሉም ለብፁዕነታቸው የሚመጥን ሥርዓተ ጸሎት ተደርጎ የሕይወት ታሪካቸው ተነቦ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማጽናኛ ቃለ ምዕዳን ተላልፎ ሲያበቃ ሥርዓተ ቀብሩ የሚፈጸም ይሆናል።
በሥርዓተ ጸሎቱ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይገኛሉ።
የብፁዕነታቸው ጸሎትና ቢራኬ ይደርብን
ምንጭ:EOTC public relations
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
ጸሎተኛው፣ ደጉ፣ ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።
የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን
ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
👳♂የርዕሰ ሊቃውንት መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች⛪️
ድንቅ፣ኃያል፣ርትዕት፣ጥንታዊት የሆነች የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ከሚሰብኩ እናም ዕንቁ ከሚባሉት መካከል ቀዳሚው አባት ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳንን ትምህርት የሚያገኙት ብቸኛው ቻናል ነው ይግቡ።
👇🏽👇🏽👇🏽
@abagebrekidan
@abagebrekidan
@abagebrekidan
የደመራ ዓመት
መስቀል የከበረው ትናንት መስሏቸው
ያዩ ተገረሙ ክብሩ አስደንቋቸው
ትናንትና አይደለም የበራው ደመራ
ዘንድሮ ዓመት ፈጀ የመስቀሉ ሥራ
ስንት አይሁድ ተነሥተው መስቀሉን ቀበሩ?
ስንትስ እሌኒዎች ሊያወጡት ቆፈሩ?
ጅጅጋ ሲዳማ ውጡ ተናገሩ
ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ደመራ
በእሳት ተለኩሳ ደምቃ ስታበራ
ካህናት ምእመናን እንደ ችቦ ነድደው
ስንቴ አከበሩት ለመስቀሉ ታርደው?
ስንት ጊዜ አፏጨ ዲያቢሎስ ተቆጣ
ስንት ሟርት ተሰማ ስንት ቁጣ መጣ?
በዕጣን ያልተገኘ ጌታ ያልሞተበት
ቅርፁ መስቀል ሆኖ መዳን የሌለበት
የወንበዴው መስቀል መስቀሉ መስሏቸው
ስንቶች ትተው ሔዱ ከእሌኒ እናታቸው?
ዓለም የዳነበት መስቀሉን ጨብጦ
ስለዘር የሚሰብክ እጅግ ተመስጦ
የተቃጠለውን መቅደስዋን እያየ
"ራስሽን አድኝ" ሲል ሲስቅ የታየ
ዘንድሮ አይደለም ወይ አይሁዱ የለየ?
ዘንድሮ ከበረ ለአንድ ዓመት ደመራ
በማያቆም ጥቃት በማያቆም ሴራ
ቅድስት ተዋሕዶ በጭንቅ ተወጥራ
አባቶችዋን ከፊት እንደ ጦር ሰድራ
በልጆችዋ ጩኸት በገና ደርድራ
በሰማዕታትዋ ደም ተረጭታና ርሳ
በየአደባባዩ ምሕላን አድርሳ
በፓትርያርክዋ ዓይን በምሬት አልቅሳ
እንደ ራሔል ለአምላክ ዕንባዋን አፍስሳ
ለመስቀሉ ቀን ግን ነጭ ልብስዋን ለብሳ
እንደ ቆስጠንጢኖስ በድል ልትነሣ
አምላክዋን ከፍ አድርጋ ኀዘንዋን ልትረሳ
ተስፋ ያደረገችው በመስቀል ታድሳ
ዘንድሮ ነው በዓል ዘንድሮ ደመራ
በዚህ ዓመት ተገኘን ከመስቀሉ ሥፍራ!!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 17 2012 ዓ.ም.
#የደመራው_ምሥጢር
በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ
እግዚአብሔር አምላካችን የሠራቸው ታላላቅ ሥራዎች በምልክት የተገለጡ ናቸው፤ ለምሳሌ የሙሴ መስፍንነት፣ የአሮን ሊቀ ካህንነት የተረጋገጠው በአሮን በትር ምልክትነት ነው፡፡ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ በታዘዘ ጊዜ የሞርያን ተራራ የመረጠው እግዚአብሔር በተራራው ላይ ካሳየው ብርሃን የተነሣ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ መስቀልም የድኅነታችን ምልክቶች ናቸው፡፡ የአሮንና የሙሴ በትሮች፣ የይስሐቅ ቤዛ የሚኾን በግ የተገኘባት ዕፀ ሳቤቅ ደግሞ የእመቤታችንና የመስቀል ምልክቶች ነበሩ፡፡ ወደ ፊት የምንወርሰው መንግሥተ ሰማያት ክርስቶስ ነው፤ እርሱን ደግሞ ያገኘነው ከመስቀል ላይ ነው፡፡
ጥንተ ጠላት ሰይጣን ይህንን ስለሚያውቅ ቅዱስ መስቀሉን አጥብቆ ይቃወመዋል፤ ስለዚህም አይሁድን አነሳሥቶ ከ፫፻ ዓመታት በላይ ተቀብሮ እንዲቆይ አድርጓል፡፡ በመሠረቱ ለሰይጣን ምሥጢሩ ስለማይገባው ነው እንጂ የመስቀሉ ትክክለኛ መቀበሪያ ሥፍራ የምእመናን ልቡና ነው፡፡ ቀራንዮ ለመስቀሉ መትከያነት የተመረጠችውም ቀዳሜ ፍጥረት አዳም የተቀበረው በዚያ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቦታው ‹‹የራስ ቅል ሥፍራ›› /ማቴ.፳፯፥፴፪/ መባሉም የኹላችን ራስ አዳም ዓፅሙ በዚያ ስላረፈ ነው፡፡ መስቀሉ በአዳማውያን ፍጥረታት አእምሮ ውስጥ እንጂ ከዚያ ውጪ የሚኖር ባለመኾኑ ተቀብሮ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥም ፍቅሩ ከሰው ልጆች ልቡና አልወጣም፡፡
ጠላት በሠራው ተንኮል ተቀብሮ እንዳይቀር መስቀሉን እንድታወጣ መንፈስ ቅዱስ ንግሥት ዕሌኒን አስነሣት፡፡ ይህች ሴት ቤቷ በሀብት፣ በንብረት ሞልቶ በነበረበት ጊዜና በገረድ፣ በደንገጡር በምትንቀሳቀስበት ወቅት ምን እንደ ሠራች አልተመዘገበላትም ነበር፤ ከክብሯ ወርዳ በተጣለችበት ጊዜ ግን እግዚአብሔር ለሚፈልገው ሥራ ምቹ ኾና ተገኘች፡፡ እርሷ በተጣለችበት ባዕድ አገር ውስጥ ኾና የመስቀሉን ነገር ታስብ፤ ብርሃነ መስቀሉም ዘወትር በልቧ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ሐሳቧን እንዲያሳካላት የለመነችው አምላክም ኪራኮስ የተባለውን አይሁዳዊ ሽማግሌ ልኮ አቅጣጫውን አመላከታት፤ ኪራኮስ የጀመረውን ምሥጢርም መልአኩ ‹‹ደመራ ደምረሽ፣ ሰንድሮስ የሚባል ነጭ ዕጣን ጨምረሽ አቃጥዪው›› ብሎ ተረጐመላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንደ ነገራት ብታደርግ ጢሱ ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ተመልሶ መስቀሉ ወደሚገኝበት ተራራ ሰገደ፡፡ በጢሱ ምልክትነት መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቍፋሮ መጋቢት ፲ ቀን አልቆ ዕሌኒ መስቀሉን ከልበ ምድር ለማውጣት ችላለች፡፡
መስቀልና ደመራ እንዲህ ነበር የተገናኙት፡፡ ደመራው ለመስቀሉ መገኘት፣ መስቀሉም ለደመራው መሠራት ምክንያት ናቸው፡፡ በዚህ አንጻር መለኮትና ትስብእት በአንድነት መደመራቸው መስቀሉ እንዲሠራ ምክንያት ኾነዋል፡፡ አምላካችን ሥጋ ለብሶ ‹ክርስቶስ› በሚል የተዋሕዶ ስም ሲጠራ ለመከራ መዘጋጀቱን እንረዳለን፡፡ መስቀሉ የሥጋ ብቻ ነበረ፤ አሁን ግን መለኮትም በሥጋ ባሕርይ የመስቀሉ ተካፋይ ኾነ፡፡ ይህም የደመራው ውጤት ነው፡፡ መለኮት አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን መስቀል የተሸከመ ሥጋን ሲዋሐድ መስቀሉን አስወግዶ አልነበረም፡፡ ይኸው በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከምነው መስቀል ነው፡፡ ሥጋ ዓቅም አጥቶ መስቀሉን ከትከሻው ላይ ሳያወርድ ለዘመናት የተጓዘውን ጕዞ መለኮት ኀይል ኾኖት ድካሙን ሳይለቅ ኀያል፤ ኀይሉን ሳይለቅ ደካማ ኾነ፡፡ መስቀል ትርጕሙ መከራ ቢኾነም ነገር ግን እግዚአብሔር ሲያመጣውና ሰው ሲያመጣው ግን ትርጕሙ ይለያያል፤ ሰው ያመጣው መስቀል ኹላችንን ለመከራ፣ ለሞት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡ የእግዚአብሔር መስቀል ግን መከራነቱ ለሰይጣን እንጂ ለእኛ ሕይወታችን ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹መስቀል ብሂል ዕፀ ሕይወት ብሂል፤ መስቀል ማለት የሕይወት ዛፍ ማለት ነው›› በማለት የመስቀልን ትርጕም ነግሮናል፡፡
አዳም ከገነት ሲወጣ በመላእክት እንዲጠበቅ የተደረገው የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መስቀል ነው፡፡ በዕፀ በለስ ምክንያት ኹላችንም እንደ ተጎዳን በዕፀ ሕይወቱም ተጠቃሚዎች ኾነናል፤ አስቀድመን በአዳም መከራ እንደ ተባበርን አሁን ደግሞ በደስታው እንተባበራለን፡፡ ሞትም ሕይወትም አንድ አድርጎናል፡፡ የክርስቶስ መስቀል ኹሉንም በሕይወት አስተባብሯልና፡፡
በአንጻሩ ሰውና ዲያብሎስን ለያይቷል፡፡ የኀጢአት ቁራኝነትን አጥፍቷል፡፡ ጌታችን በማኅፀን ሲፀነስ ጀምሮ የእኛን መስቀል መሸከም ሲጀምር የእርሱ የኾነውን ለእኛ ስለ ሰጠን ከሰይጣን ጋር መለያየታችን በመስቀሉ ተረጋግጧል፡፡ የአምላካችን መስቀል ምልክቱ ደመራ መኾኑ የእኛን ወደ እርሱ መሰብሰብና የጠላታችንን መበተን የሚያረግጥልን ነው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወብየ ካልዓትኒ አባግዕ እለ ኢኮና እምዝንቱ ዐፀድ ወኪያሆንሂ ሀለወኒ አምጽኦን ዝየ፤ ከዚህ በረት ያልኾኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ላመጣቸው ይገባኛል›› በማለት ሊሰበስበን እንደ መጣ ነግሮናል /ዮሐ.፲፥፲፮/፡፡ መስቀሉ ፍጥረት አንድ ደመራ ኾኖ የተሠራበት ስለ ኾነ በደመራ እንዲገለጥ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ኾነ፡፡
መስቀሉ አንድ ደመራ ያደረጋቸው ፍጥረታት
፩. ነቢያትና ሐዋርያት
ነቢያት የሚባሉት ከአዳም እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያሉ አባቶች ሲኾኑ፣ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን የወንጌልን የምሥራች እንዲነግሩ የተላኩ አባቶች ደግሞ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ በእርግጥ ሐዋርያ የኾነ ነቢይ የለም እንጂ ነቢይ የኾነ ሐዋርያ አለ፡፡ ነቢያትና ሐዋርያት በዘመን፣ በክብር እና በግብር የማይገናኙ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መንፈሰ ረድኤት የተሰጣቸው ነቢያት ለሐዋርያት የተሰጠውን መንፈሰ ልደት ለማግኘት አልተቻላቸውም፡፡ ሐዋርያት ግን ኹሉንም አንድ አድርገው ይዘዋል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ስለዚህ ሲመሰክር ‹‹በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጠን›› በማለት አጕልቶ የተናገረው /ዮሐ.፲፥፲፰/፡፡ ነቢያት በዚህ ምድር የእግዚአብሔርን መንግሥት በመፈለግ ብዙ ደክመዋል፡፡
ሊቃውንቱ ነቢያትን በክረምት፣ ሐዋርያትን በበጋ ገበሬ ይመስሏቸዋል፡፡ የክረምት ገበሬ ላዩ ውሃ፣ ታቹ ውሃ ኾኖበት በጭቃ ወጥቶ በጭቃ ይመለሳል፡፡ ወደ ቤቱ ሲገባም ሚስቱ ጨምቃ ያቆየችለትን ጐመን በልቶ ደስ ሳይለው ይተኛል፡፡ ነቢያትም በዚህ ዓለም በጣዖት አምላኪ ነገሥታት፣ በነቢያተ ሐሰት ስብከት ሲንገላቱ ኖረው ሲሞቱም ሲዖል ይገባሉ እንጂ ገነትን አይወርሱም ነበር፡፡ የበጋ ገበሬ በደረቅ ወጥቶ፣ እሸት በልቶ፣ ተደስቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ከቤቱ ሲገባም እንጀራው በሌማት፣ ጠላው በማቶት፣ ሲቀርብለት ደስ ብሎት ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ሐዋርያትም ልጅነትን አግኝተው ለማስተማር ተልከዋል፤ በሔዱበት ኹሉ ተአምራትን እንዲያደርጉ፣ ልጅነትንም እንዲሰጡ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሞታቸው ሲደርስም መንግሥተ ሰማያት ተከፍቶ ይጠብቃቸዋል፡፡
ይቀጥላል!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#መስቀሉ_አበራ
እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ(፪)
መስከረም ሲጠባ ተተክሎ ደመራ
ህዝበ ኢትዮጵያን እዩት ችቦውን ሲያበራ
በታላቁ ብርሃን በመስቀል ደመራ(፪)
በኃጢአት ጨለማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተውጠን ሳለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የክርስቶስ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሃን ሆነልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ትምህርተ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሆኖን ላመንነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በቃሉ ለምንድን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የእግዚአብሔር ኃይል ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
✞ መስቀል ባንዲራችን
የነጻነት አርማችን(፪)
በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አይሁድ አብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ያዳናቸውን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አናውቅም ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የድሉን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ከመሬት ቀብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስሏቸው ነበር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ውጦ የሚያስቀረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በቀራንዮ ጎልጎታ
ጠላታችን ድል ተመታ(፪)
ንግሥቲቷ እሌኒ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በጣም የታደለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ደመራን አቁማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ፍለጋ ጀመረች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀለ ክርስቶስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ወዴት ነው እያለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በጣን ጢስ ተመርታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀሉን አገኘች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በመስቀል መከታ
ቆስጠንጢኖስ ድል ተመታ(፪)
ነገር ግን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተቀብሮ አልቀረም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተራራ አፍርሶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጠላት አሳፈረ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ሲወጣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ታላቅ ሁካታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ድውይ ሲፈወስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አንካሳው ዳነ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሙታን ተነሱ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይመስገን ጌታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ
ክርስቲያኖች እልል በሉ (፪)
መስቀል መከታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይሁን ጋሻችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እንዳይደፈር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ዳር ድንበራችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኢትዮጵያ ኑሪ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእምነት ፀንተሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጌታ በመስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የባረከሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀሉ አበራ
እንደ ፀሀይ ጮራ (፪)
መስቀሉን አምነን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተሳልመነዋል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ከክብሩ ዙፋን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእርሱ ባርኮናል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እንሰግድለታለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የፀጋ ስግደት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእርሱ ላይ ስላለ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኃይለ መለኮት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል የእኛ ጋሻ
የዲያብሎስ ድል መንሻ (፪)
የኢትዮጵያን መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኑ ተመልከቱልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀሉን ብርሃን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ነፀብራቁን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እፀ መስቀሉ ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የእኛ መከታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የተሰጠን ለእኛ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ምልክታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በመስቀል እንመካለን
እንድንበታለን(፪)
የዳዊት ልጅ ያዕቆብ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የሀገራችን ኩራት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የኢትዮጵያ ንጉሥ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጌታን የሚፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሀገሪቱን ሲዞር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ድካሙን ሳይፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሐን እያበራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀሉ ፍቅር
በእኛ ላይ ይደር(፪)
መናገሻ እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የረር አምባ አመራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሲፈለግ ሰንብቶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጊሸን ላይ አገኘ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የአምባሰል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ግማደ መስቀሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አርፏል ከዚያ ስፍራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል መስቀላችን
የክርስቲያን ኃይላችን(፪)
የመስቀል ለታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የደመራው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኢትዮጵያውያን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተደስተው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በሀገር ልብሳቸው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አምረው ደምቀው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በአደባባዩ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተሰብስበው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይዘምራሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀሉ ደመራ
በኢትዮጵያ ሲያበራ(፪)
መዝሙር
በማኅበረ ፊሊጶስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#መስቀል_ብርሃን
መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም
መሠረተ ቤተክርስቲያን /2/
ወሃቤ ሰላም መድኀኔዓለም
መስቀል መድኅን ለእለነአምን /2/
መስቀል ብርሃን ነው ለመላው ዓለም
መሠረት ነው ለቤተክርስቲያን /2/
ሰላምን ሰጪ ነው መድኀኔዓለም
መስቀል አዳኝ ነው ለምናምን ሰዎች /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ኢሬቻ/ዋቄፈና/ ለክርስቲያን ምኑ ነው?
(በዲ/ን ሕሊና በለጠ)
ቤተ ክርስቲያን በባሕርይዋ የአንድ ማኅበረሰብን ባሕል ንቃም ኾነ ተቃውማ አታውቅም። በተቻላት መጠን ማኅበረሰቡ ከነ ባሕሉ ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ሃይማኖቷንና ሥርዓቷን አስተምራ ታስተናግደዋለች እንጂ። ከእርሷ አምልኮ በተቃራኒው የሚያመልክ የአንድን ተገዳዳሪ የእምነት ተቋም አምልኮም በማይገባ መልኩ ተችታና አኮስሳ አታውቅም፤ እውነተኛውን መንገድ ግን በተገቢው መልኩ በጥብዓት ታስተምራለች። የዚያ የእምነት ተቋም አምልኮና እምነት ስሕተት ከኾነ ሰዎች ኹሉ ይድኑ ዘንድ እውነትን ትሰብካለች፤ ወደ እውነት ትመራለች፣ ታደርሳለች።
ኢሬቻ ምንድን ነው? ባሕል ነውን?
መልካም፣ ባሕልስ ከኾነ ቤተ ክርስቲያን የባሕሉን አክባሪ ባሕሉን ሳይዘነጋ ይቀበላት ዘንድ አይገዳትም። እርሷም ከነ ባሕሉ ዐቅፋና ደግፋ ትቀበለዋለች።
ግን ኢሬቻ ባሕል ነው?
አይመስለኝም። ሰሞንኛ ተናጋሪዎችን እንዘንጋቸውና እስኪ እንዴት እንደተከበረ እንመርምር። የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች ውኃ ውስጥ ሣር እየነከሩ ወይም ዛፍን ቅቤ እየቀቡ ፈጣሪን ሲያመሰግኑ የሚያሳዩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ስናይ ነበር። ስለዚህ ይህ በዓል:-
#1ኛ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ነው (ይህም ተደጋግሞ በአክባሪዎቹ እየተነገረ ነው)። በፈጣሪ መኖር ማመን ደግሞ: ለሃይማኖት ህልውና የመጀመሪያው መስፈርት መኾኑን ልብ ይሏል። ስለዚህ ኢሬቻ/ዋቄፈና/ ለሃይማኖትነት ትልቁን መሥፈርት አሟልቷል ማለት እንችላለን።
#2ኛ የታወቀ የምስጋና (አምልኮ?) ሥርዓት (ለምሳሌ:- ሣር ውኃ ውስጥ መንከር፣ ቅቤ መቀባት ...) አለው። ይህም እስልምናም ኾነ ክርስትና የታወቀ የአምልኮ ሥርዓት እንዳላቸው ማለት ነው።
#3ኛ እስልምና መስጊድ፣ ክርስትናም ቤተ ክርስቲያን እንዳላቸው ኹሉ: ኢሬቻም /ዋቄፈናም/ ይህ ሥርዓት የሚፈጸምበት ቦታ (Sacred Place, ለምሳሌ:- ውኃና ዛፍ ያለበት ሥፍራ) አሉት።
#4ኛ ሃይማኖታዊ የአምልኮ ሥርዓት በካህናት እንደሚመራ: ክብረ በዓሉን የሚመሩ የሥርዓት መሪዎች (አባ ገዳዎች?) አሉት።
ስለዚህ ወይ አምልኮ ነው፣ ወይም ደግሞ ከቆይታ ብዛት ወደ ባሕልነት የተቀየረ አምልኮ ነው።
#ዐቢይነጥብ - ከላይ ከጠቀስናቸው ከዐራቱ ለጊዜው አንዱን ብቻ እንምረጥ -
-ፈጣሪ የሚመሰገንበት መኾኑ
ይህ ብቻ "ባሕል ነው" ለሚሉት ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያስገድድ ምክንያት ነው።
ፈጣሪን ማመስገን የሚቻለው በእምነት ነው። በመጀመሪያ ይህን ፈጣሪ ማመንና በጥቂቱም ቢኾን በእምነት ማወቅ ይገባል። ቢያንስ ፈጣሪ መኾኑን በእምነት መረዳት ያሻል። ከዚያም እርሱ በሚፈልገው ሥርዓት እርሱን ማመስገን/ማምለክ ይከተላል። እርሱን ማምለኪያ ውሱን ሥርዓት የለም ቢባል እንኳን: የማመስገኛ ሥርዓቱ "ሥርዓት የለሽ በመኾን" ይገለጻል፤ (non-religiousness is my religion) እንዲል አንድ የፍልስፍና መምህር /ፈላስፋ ላለማለት ነው/)።
ሙስሊሙ ፈጣሪን የሚያመሰግንበት ሥርዓትና ቦታ አለው፤ ሳምንታዊ(ጁምዓ) እና ዓመታዊ (ኢድ አል ፈጥር፣ ኢድ አልአድሃ) የበዓላት ዕለታትም አሉት። ክርስቲያኑም እንዲሁ ከሳምንታዊ ሰንበትን፣ ከዓመታዊ ልደትና ትንሣኤን የመሰሉ (ዕለታዊና ወርኃዊውን ጨምሮ) ብዙ በዓላት አሉት። ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በየበዓላቱና በየታወቀ ሥርዓቱ ፈጣሪን ያመሰግናሉ፣ ያመልካሉ። ነገር ግን ክርስቲያኑ ኢሬቻ የሚል ፈጣሪን የማመስገኛ በዓል በዚቁ (liturgical Calendar) ውስጥ የለም። ሙስሊሙም እንደዚያ።
ሌላው ነጥብ: ኹሉም እምነት ፈጣሪን የተመለከተ መሠረተ-ትምህርቱ (Doctrine/Creed) ከሞላ ጎደል ይለያያል። ሙስሊሙም (ካልተሳሳትኩ) "ላ ኢላህ ኢለላህ መሐመዱር ረሱለላህ" የሚል ሸሀዳ (Creed) አለው። ይህንን አዘውትሮ ያደርሳል። ፕሮቴስታንቱ "ክርስቶስ አማላጄ" (ሎቱ ስብሃት) ይላል። እኛ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ "ኹሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚኾን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን" ከሚለው ጀምሮ የክርስቶስንና የመንፈስ ቅዱስን አንድ የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ጋር መተካከል፣ የቤተ ክርስቲያንን ኲላዊነት፣ አንድነት፣ ቅድስናና ሐዋርያዊነት፣ የጥምቀትን የኃጢአት ማስተሥሪያነት፣ የትንሣኤ ሙታንን ተስፋነት የምንመሠክርበት የዘወትር ጸሎተ ሃይማኖት (Creed) አለን።
እነዚህ እምነቶች ይለያያሉ ብቻም ሳይሆን ይቃረናሉ። እንዴት በአንድነት ምስጋናቸውን ለአምላክ ያደርሳሉ?
እኔ አምላክ የምለውን ክርስቶስን አንዱ ከአጠገቤ "አማላጄ" እያለው እንዴት አንድነት ይኖረኛል? አንዱስ "ነቢይ" እያለው እንዴት አብረን እናመሰግናለን? የኔን አምላክ አማላጅም ፣ ነቢይም ማለት እርሱን ማሳነስ ለእኔም ንቀት ነው።
ሙስሊሙም አላህን አምላክ ይላል። ኢሳን ነቢይ ይላል። እኔ ከጎኑ ቆሜ ኢየሱስ ክርስቶስን "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ስል እንዴት ይዋጥለታል?
አብረን ቡና የምንጠጣ፣ አብረን ኳስ የምንጫወት፣ በንግድ የምንተባበር ሙስሊሞችና ፕሮቴስታንቶች ይኖራሉ። በጣም የምንዋደድ ጓደኛሞችና የሥራ ባልደረቦች ልንሆን እንችላለን። ግን ለአምልኮ ሙስሊሙም መስጊድ፣ ፕሮቴስታንቱም "ቸርች" እኛም ቤተ ክርስቲያን እንሔዳለን እንጂ ፈጣሪን ለማመስገን መስጊድ ወይም ቤተ ክርስቲያን በአንድነት አንሔድም።
አንድ የምንኾንበትንና የማንኾንበትን እንለይ እንጂ! በኢትዮጵያዊነት አንድ ነን፤ በባሕል እንተባበራለን፤ በልማት አንድ መኾን እንችላለን፤ እንኳን በሀገር በቤተ ዘመድም በሃይማኖት መለያየት ይገጥመናል፤ ዝምድናን ጨምሮ ግን ብዙ አንድ የሚያደርጉን ጉዳዮች አሉን። ኾኖም በሃይማኖት አንድ ካልኾንን ከእናቴም ጋር ለጸሎትና ለምስጋና አልቆምም።
እንኳን ከሙስሊምና ከፕሮቴስታንት ጋር ይቅርና በብሉይ ኪዳን በሃይማኖት አንድ ከነበርነው ከይሁዲውም ጋር ፈጣሪን ለማመስገን በአንድነት አንቆምም። የይሁዲው መሠረተ ሃይማኖት ( ሸማ፣ Creed) በእኛው ብሉይ ኪዳን ላይ ዘዳ.6÷4-9 ያለው ንባብ ነው። ይሁዲዎች ይህንን በእጃቸው ያሥሩታል (Teffilin)። በበራቸውም ይጽፉታል (Mezzuzah)። ንባቡ እኛም የምናምንበትና የምናነበው ነው። ነገር ግን ምንም ያኽል ብንወዳቸው ክርስቶስን ከማያምኑት ከይሁዲ እምነት (Judaism) ተከታዮች ጋር የሃይማኖት ኅብረት የለንም።
ወንጌላችንም ያዘናልና "ቢቻለንስ በእኛ በኩል ከሰው ኹሉ ጋር በሰላም መኖርና ሰላምን መከታተል" የክርስትና መርሐችን ነው። (ሮሜ 12÷18፣ ዕብ. 12÷14)። ኾኖም ፈጣሪን የምናመሰግንበት የሃይማኖት ኅብረት የሚኖረን ግን ከተጠመቁት ጋር ብቻ ነው።
#ይቀጥላል
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#የናቁሽ_ሁሉ
የናቁሽ ሁሉ ወደእግሮችሽ ጫማ ይሰግዳሉ
የካዱሽ ሁሉ ይፀፀታሉ
እኛ ግን አንቺን እናከብራለን}2
እናታችነን ፅዮን አንልሻለን}
እናቴ እመቤቴ እኔም እልሻለው
ጌታዬ ባደራ የሰጠኝ አንቺን ነው
ከእግረ መስቀሉ ስር አንቺን አጊኝቻለው
ትውልድ ነኝና ብፅዕት እልሻለው
በድል ነሺዎች ዘንድ በፃድቃን ሰማዕታት
በቅዱሳኑ ና በትጉሃን መላዕክት
የሰለጠነ ነው ስምሽ በእግዚአብሔር ዘንድ
በፍጥረታት ሁሉ እጅግ የሚወደድ
እናቴ ማርያም ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ
ያልሽኝን እንዳልፈፅም የሚከለክለኝ
ብሏልና ልጅሽ በቤተ ዶኪማስ
ለምኝልን ድንግል እንባችን ይታበስ
የጌድዮን ፀምር ዳግማዊቷ ሰማይ
ሕይወትን ያስገኘሽ ወላዲተ ፀሐይ
የሕወትን መና ያገኘነው እኛ
ካንቺ ተወልዶ ነው የአለሙ እረኛ
ዘማሪት መብራት ድርብሣ (አብ-ሳላት)
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
📕 መጽሐፈ ጤፉት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም መቀመጡን እና ሌሎች ጥንታዊያን ታሪኮች የሚናገር መጽሐፍ ነው።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👥ከ133,000 በላይ ባለ ማህተቦች መእመናን ያሉበት ከ1500 በላይ አዳዲስ እና የዱሮ መዝሙሮች ከነግጥማቸው የምታገኙበትን ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን ቻናል አሁንኑ ተቀላቀሉ📍
የመዝሙር ግጥሞች
👇🏽👇🏽👇🏽
https://t.me/joinchat/AAAAAE5K_dyT2-AYoTAW5A
https://t.me/joinchat/AAAAAE5K_dyT2-AYoTAW5A
💒ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት .
አዲስ በ live ብቻ የሚሰጠውን የ tiktok እና YouTube ይቀላቀሉ።
የስነልቦና ባለሞያ Bini Girmachew
እሁድ ከምሽቱ ከ3 እስከ 4 ሰዓት በtik tok Live ትምህርት የምታገኙበት
tiktok.com/@begood2716
በYouTube ደሞ እሮብ ከቀኑ 11-12 Live የምንገባበት ቻናል ነው SUBSCRIBE በማድረግ የተለቀቁትን ትምህርቶች በመመልከት ይጠብቁን
biniGirmachew27" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@biniGirmachew27
የብፁዕ አቡነ ሰላማ ሥርዓተ ቀብር እሁድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻፲፮ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
********
መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የብፁዕ አቡነ ሰላማን የቀብር ሥነሥርዓት በማስመልከት ቋሚ ሲኖዶስ ከቀትር በፊት አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት እሁድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህም መሠረት ነገ ቅዳሜ መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከቀኑ ፱ ሰዓት ላይየብፁዕነታቸው ክቡር አስከሬን ከሃሌ ሉያ ሆስፒታል በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአበው ቆሞሳትና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ጸሎት ከተደረገበት በኋላ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጉዞ በማድረግ ሥርዓተ ጸሎት ተደርሶ ሌሊቱን ሙሉ ጸሎተ ፍትሐትና ሥርዓተ ማኅሌት ሲደረግበት ያድራል።
በማግስቱ እሁድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻፲፮ዓ.ም ጠዋት ሥርዓተ ቅዳሴው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከተካሔደ በኋላ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ አበው መነኮሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ፣የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ታጅበው ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ገዳም በእግር ጉዞ ይደረጋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት #የብፁዕ_አቡነ_ሰላማ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ዕረፍትን በማስመልከት ያስተላለፉት አባታዊ የሐዘን መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
«መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት:–ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው?»
መዝሙር ፹፱፥፵፰
የትህትና፣ የጸሎት ሕይወት እና የመልካምነት ምሳሌ የነበሩት #ብፁዕ_አባ_ሰላማ ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሰማነው በታላቅ ሐዘን ነው።
ያለንበትን ፈተና የበዛበት ዘመን በጸሎት የሚያሻግሩ አባቶችን ማጣት ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ ቢሆንም በቅዱስ መጽሐፍ ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ መኖር የሚችል ማን ነው? እንደተባለ ሰው በምድር ላይ የሚኖርበት ዘመን በእግዚአብሔር ዘንድ የተቆጠረ እና የተለካ በመሆኑ ብፁዕነታቸው ሃይማኖትን ጠብቀውና መልካሙን ገድል ፈጽመው ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር በክብር ተሸጋግረዋል።
ብፁዕነታቸው በዕረፍተ ሥጋ ከእኛ በመለየታቸው ጥልቅ ሐዘን ቢሰማንም በሰማይ የሚጠብቃቸውን ክብር እያሰብን እንጽናናለን።
የብፁዕነታቸውን ነፍስ በቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት አጠገብ ያሳርፍልን!
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውም መጽናናትን ያድልልን!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ይቀድስ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
መስከረም 18 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት
ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ
ምን አይነት ስርዓተ ቢስነት ነው?
ምን አይነት ጨለምተኝነት ነው?
ቅድስት ቤተክርስቲያን የራሷ የዜማ ንዋየ ቅድሳት አሏት። ብሄርተኝነታችሁን ወደ ቤተክርስቲያን ይዛችሁ አትግቡ።
ለራሴ ህይወት ከምጠቀመው በጥቂት 38 ትምህርቶችን ተማሩ ለእናንተም የህይወት ጉዞ ላይ ይጠቅማቹዋል
ተፃፈ በሥነ-ልቦና ባለሞያ Bini Girmachew
1. ከምታወራው በበለጠ አዳምጥ።
2. ውድቀትን ልክ እንደ መማሪያ እድል ቁጠረው።
3. ምስጋናን ቀን በቀን ተለማመደው።
4. ደግ ሁን ፤ ደግ ላልሆኑ ሰዎችም ጭምር።
5. ሁልጊዜም ጉጉ ሰው ሆነህ ቆይ።
6. በሞገስ ሆነህ አይሆንም ማለትን ተማር......ሙሉውን ጽሑፍ ለማግኘት👈🏾
👇👇👇
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
🛑በYoutube ለመከታተል🛑
👇🏾👇🏾👇🏾
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
👆የቀጠለ
ቅዱስ ያሬድም ‹‹ኖትያት ነቢያት ራግናት ሐዋርያት›› በማለት ነቢያትን በዋናተኛ፣ ሐዋርያትን በጀልባ ቀዛፊ መስሎ ይናገራል፡፡ ከቀዛፊዎች ይልቅ ዋናተኞች ይደክማሉ፡፡ ዋናተኞች ውሃው አጥልቋቸው፣ መተንፈስ ተስኗቸው አንዳንዶቹ ከዳር ይደርሳሉ፤ አንዳንዶቹም በድካም በውሃ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ፡፡ ቀዛፊዎች ግን ምናልባት ሞገድና ማዕበል ካላሰጋቸው በስተቀር ይህ ኹሉ ውጣ ውረድ የለባቸውም፤ በጀልባዋ የተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን ለነቢያት በተስፋ እንጂ በአካላ አልተሰጠችም፡፡
ነቢያት ከእርሷ ሳይደርሱ ሞት ቀድሟቸዋል፡፡ ሐዋርያትም በነቢያት ድካም ገብተው ነቢያት የዘሩትን የትንቢት ዘር አጭደዋል፡፡ ወንጌል የነቢያት ዘር ናት፤ ዳሩ ግን ፍሬውን ለመብላት የታደሉት ሐዋርያት ናቸው፡፡ እሸቱ ሲደርስ የገበሬዎቹ የነቢያት ጌታ ክርስቶስ ዘሩን እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ ሐዋርያቱን በእርሻ መካከል ይዟቸው ገብቷል /ማቴ.፲፪፥፩/፡፡ በአበው ፋንታ ውሉድን ለመተካት የመጣው መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በመስቀሉ አንድ ማኅበር አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው መስቀሉን ‹‹ገባሬ ሰላም›› በማለት ይጠራዋል /ኤፌ.፪፥፲፫/፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን አንድ አድርጎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወረሰ የክርስቶስ መስቀል ነውና፡፡
፪. ሙታንና ሕያዋን
አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከመው መስቀል ሞትን አምጥቶብናል፤ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተሸከመው መስቀል ግን ሞትን ገድሎ ሕይወትን ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምክንያት የሞት መውጊያ ሲሰበር፣ የመቃብር ስቃይ ሲቋረጥ፣ የጨለማ ኀይል ሲሻር ከመስቀሉ ሥር ብዙ ሙታን እንደ አሸን ብቅ ብቅ አሉ፡፡ ምድር እስከዚያች ቀን ድረስ ሙታንን ትቀበል ነበር እንጂ ሕያዋንን ማስገኘት አትችልም ነበር፡፡ ሙታንና ሕያዋን የተፈላለጉበት መስቀል የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ በመስቀል ሙታን ሕያዋንን ፍለጋ ከመቃብር ወጥተው ወደ ከተማ ገቡ፡፡ ከታደለው የሕይወት ስጦታ የተነሣ ሞት አካባቢውን ለቆ ስለጠፋ በሩ እንደ ተከፈተለት እሥረኛ ሙታን ከመቃብር እየወጡ ከተማውን ሞልተውታል፡፡ ይህ ዕለት ሙታንን ከሕያዋን ጋር አፍ ለአፍ ያነጋገረ ዕለት ነው፡፡ ደመራው ሙታንን ከሕያዋን የሚለይ አይደለም፤ ታላቅነቱም እስከ ሲዖል ድረስ የሚታይ ነው፡፡
፫. ጻድቃንና ኀጥአን
የአዳም በደል በሕይወት የሚኖሩ ወንድማማቾችን በሁለት ሐሳብ ከፋፍሏቸው ነበር፡፡ የክርስቶስ የጽድቅ መስቀል ግን አንድ ሐሳብ ፈጠረላቸው፡፡ ጻድቁ አቤል ሳይበድል በደል የደረሰበት፣ ሳይገድል የተገደለ መኾኑ ከክርስቶስ ጋር ቢያመሳስለውም ሞቱ ግን ለሰው ልጆች ድኅነት አልጠቀመም፤ የፍጡር ደም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን አይችልምና ኹላችንም በመከራ ውስጥ ለመቆየት ተገደናል፡፡
የክርስቶስ ሞት ግን የድኅነታችን መሠረት ኾነልን፡፡ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መብራት ከፍ ብሎ ሲቀመጥ ኹሉን እንዲያሳይ ከምድር ከፍ ብሎ የተሰቀለው ክርስቶስም ጻድቃነ ብሊትንና ጻድቃነ ሐዲስን በዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል፡፡ በመስቀል ላይ የተፈጸመው ዕርቅ የኀጥአንን በደል ደምስሶላቸዋል፤ የጻድቃንን ጽድቅ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ጻድቃንም ኀጥአንም አንድ ኾነው መንግሥቱን በጸጋው ወረሱ፡፡
ኢያሱ በኢያሪኮ እንዳደረገው አሞራውያን ወጥተው እስራኤል ብቻ ምድሪቱን የወረሷት አይደሉም፡፡ መስቀሉ ለኹሉም አንድ መንግሥትን አውርሷቸዋል፤ ጊዜው የደመራ ነውና፡፡ በምድር ደምቆ የታየው ይህ ደመራ እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስም ይቀጥላል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Share አድርጉት ሌላውም እንዲማርበት።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ፍቅረኛ ለመያዝ ቀና ልብ ይፈልጋል። ከዛ ደግሞ አስተዋይ መሆን አለብን። ምክንያቱም ዘው ብለን የምንገባው የሰው ህይወት ውስጥ ነው።
ስንወጣ ደግሞ የሰውን ልብ እና ቅስሙን ሰባብረን... ህይወቱን አመሰቃቅለን ... ስሜቱን ጎድተን ተስፋ አስቆርጠን ነው የምንወጣው።
ይህን ሁሉ በደል ከማድረሳችን በፊት እስክንበስል ፍቅረኛ አንያዝ።
- ይኸውልሽ <አርግዣለሁ > ብለሽ ፍቅረኛሽን የመፈተን እድሜ ላይ ካለሽ ፍቅረኛ ይቅርብሽ...ሙሉውን ለማንበብ
🌼አየኸው ደመራ
አየኸው ደመራ መስቀል ሲያበራ/2/
መስቀል አለ ወይ ቆሟል ወይ
አለእንጂ ለምጽ ያነጻል እንጂ
ያው ቆሟል ድውይ ይፈውሳል
አምነዋለሁ የት አገኘዋለሁ
አለልህ እሰረው በአንገትህ
ከልብህ ተሳለመው አምነህ
እኮራለሁ በእፀ መስቀል
ይፈውሳል ሙታንን ያስነሳል
ድል ያደርገል ድውይ ይፈውሳል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#በመስቀሉ_ወበቃሉ
በመስቀሉ ወበቃሉ /2/
አዕበዮሙ ለአበዊነ /4/
#ትርጉም:-
በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን
ከፍ ከፍ አደረጋቸወ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️