#ከመ_ትባርከነ
ከመ ትባርከነ በመስቀልከ ዘወርቅ /2/
ተዋነይ በጽድቅ /4/ እስጢፋኖስ
ሐመልማለ ወርቅ /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ወሪዶ_እመስቀሉ
ወሪዶ እመስቀሉ /2/
እመስቀሉ አብርሃ ለኵሉ /4/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ጥልን_በመስቀሉ_ገደለ
ጥልን በመስቀሉ ገደለ /2/
በመስቀሉ ለሰው ልጅ ሰላምን አደለ /4/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ኀበ_ቀራኒዮ
ኀበ ቀራንዮ ደብረ መድኃኒት
ቀራንዮ /2/ ኀበ ቀራንዮ
የመስቀሉ ቃል ለእኛ
የእግዚአብሔር ኃይል ነው /2/
ለማያምኑት ሞኝነት ነው
ለእኛ ግን ሕይወት ነው /2/
እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ
እንመሰክራለን አማኑኤል አለ
እንመነው አንካደው ፈጣሪያችን ቸር ነው /2/
እንመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት
እንመሰክራለን ማርያም አማላጅ ናት
እንመናት አንካዳት የአምላክ እናት ናት /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን በቲክቶኩ በተለያዩ ሃሳቦች ወደ እናንተ መጥቷል እናም በመከታተል ትክክለኛ የስነልቦና መፍትሔዎችን ያግኙ።
የስነልቦና ባለሞያ Bini Girmachew
🔵በTELEGRAM
/channel/+Ir8pW1XiBJRkNmQ0
🔴በYouTube
https://youtu.be/mtgvrqH3584?si=kQfBtnK5g98Xpgh6
⚪️በTIKTOK
https://vm.tiktok.com/ZMjh3ovnR/
የቅዳሴ ትምህርታችንን ዛሬ ጀምረናል✝
አሁን የተላከውን ቪድዮ እያያችሁ እያቆማችሁ ተለማምዳችሁ የከበዳችሁን ንገሩን።
የቅዳሴ መጽሐፉን በpdf የላክልንላችሁ ስለሆነ እርሱን ከፍታችሁ ጽሑፉን ታነቡ ዘንድ እንጠይቃለን።
📣ጥያቄ ለዝማሬ ዳዊት ኦርቶዶክሳዊያን📣
✝የቅዳሴ ትምህርት ለምዕመናን ለማስተማር አስበናል በቀላል መልኩ። የቅዳሴ ትምህርት መማር የምትፈልጉ እና ቅዳሴ የሚባለውን የማታውቁ ካላችሁ እስኪ ሐሳባችሁን አሁን ንገሩን
#መስቀሉሰ
መስቀሉሰ ለክርስቶሰ ብርሃነ እለ ነአምን
ትብል ቤተ ክርስቲያን /2/
ዛህኑ ለባሕር ወመርሶ ለአሕማር
ዝንቱ ውእቱ መስቀል /2/
#ትርጉም:-የክርስቶስ መስቀል ለምናምን ሰዎች ብርሃን ነው መስቀል የባሕር ፀጥታው የመርከቦች ወደብ ነው ትላለች ቤተ ክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
☦👉🏾 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን❓
👉🏾 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች⁉️
👉🏾 ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን❔
ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን‼️
👉🏾 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል❕
👉🏾 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው❓
👉🏾 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው⁉️
ከላይ ላሉት ጥያቄ መልስ ማግኘት ትፈልጋላችሁ⁉️
👇🏾አሁኑኑ በመቀላቀል መልሱን ያግኙ👇🏾
/channel/+qqK-A9uE2dZkNjRk
/channel/+qqK-A9uE2dZkNjRk
#እፀ_መስቀል ✝
እፀ መስቀል የክብር መውረሻ
ሞትን ድል መንሻ
የክብር ባለቤት - - - እፀ መስቀል
የተሰዋበት - - - እፀ መስቀል
እፀመስቀሉ ነው - - - እፀ መስቀል
የአለም መድኃኒት - - - እፀ መስቀል
#አዝ
እንደእሌኒ ንግስት - - - እፀ መስቀል
ፍፁም አክብራችሁ - - - እፀ መስቀል
ሁላችሁ ገስግሱ - - - እፀ መስቀል
መስቀሉን ይዛችሁ - - - እፀ መስቀል
#አዝ
ያለኃይለ መስቀል - - - እፀ መስቀል
የሰላም አርማችን - - - እፀ መስቀል
ሊጠፋ አይችልም - - - እፀ መስቀል
ሰይጣን ጠላታችን - - - እፀ መስቀል
#አዝ
እሳተ መለኮት - - - እፀ መስቀል
ዙፋኑ የሆነው - - - እፀ መስቀል
ሰይጣንን የሚያነድ - - - እፀ መስቀል
እፀ መስቀሉ ነው - - - እፀ መስቀል
#አዝ
እንደተባረከ - - - እፀ መስቀል
ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ - - - እፀ መስቀል
በመስቀል ብርሃን - - -እፀ መስቀል
ወደ ሕይወት እንገስግስ - እፀ መስቀል
#አዝ
የተዋህዶ ልጆች - - - እፀ መስቀል
ገስግሱ በተስፋ - - - እፀ መስቀል
እፀ መስቀል ያዙ - - - እፀ መስቀል
ጠላት እንዲጠፋ - - - እፀ መስቀል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ
ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።
ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ
ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።
በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን
🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#መስከረም_ጠባ
መስከረም ጠባ ኢዮህ አበባ /2/
መስከረም ጠባ ኢዮህ አበባዬ
ኢዮህ መስከረም ጠባ ለእኛ ኢዮህ አበባ
መስቀል አበራ ኢዮህ አበባ
ለእኛ ሊሆነን እድገት እና ልማት
ኢዮህ ኢዮህ አበባዬ ኢዮህ
መስከረም ጠባ ለኛ ኢዮህ አበባ
በተዋሕዶ የከበረች እናታችንን
የጥበብ ልጆቿ እናከብራታለን
ሃይማኖት ከምግባር ወንጌል መግባ
ስላሳደገቸን የጥበብ መሠረት
ቤተክርስቲያን እናታችን
ጥንትም መሪ እና አስተማሪ በመሆኗ
በዓለም ላይ ታውቋል ዜናዋ
እየተወሳ በዓለም ዜና ያኮራናል
መስቀላችን ኢዮህ አበባ
መስከረም ጠባ ኢዮህ አበባዬ /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "#ዘካርያስ ካህኑና #ቅድስት_ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
¤የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
¤እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
¤ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
¤ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል #እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
¤የአምላክ እናቱ ስትደርስና "#ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
¤ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ #ሰብአ_ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
¤እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና #ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
¤ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ #ድንግል_ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
¤ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
¤ከዚህ በሁዋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
¤ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ #መንፈስ_ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
¤ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ:: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነ ልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::
¤"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "#መጥምቀ_መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::
¤በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)
¤ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት #ደብረ_ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: #ቅዱሳን_ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::
¤ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::
<<¤ አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ (የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች) ¤>>
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)
=>ጌታችን #መድኃኔ_ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን::
ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌼 ዘመን መለወጫ
አስቀድመን ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ማንነትና የዘመን መለወጫ መግቢያው ላይ በስሙ ስለመጠራቱ ተመልክተናል፡፡ ዘመን መለወጫ ደግሞ ለምን እንደተባለና ለምን መስከረም ወር ላይ እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲህ በማለት ያትታሉ፡፡
ሲያትቱም ብርሃናት/ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱም ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱንም ጠንቀቀው ቢቆጥሩት ፫፻፷፬ ቀናት ይሆናል፡፡ ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ ይላልና /መጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፵፱፡፡
በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድረገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡ /መጽሐፈ ኩፋሌ፡ ምዕ ፯ ቁጥር ፩/
በመሠረቱ ዘመን ተለወጠ ሲባል የሚለወጡት ወራቱ ብቻ አይደሉም፡፡ በወቅቱ የሚከሰቱት/የተከሰቱት/ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር /ገጠመኝ ሲሆን ወራቶቹ ግን ያው በየዓመቱ እየተፈራረቁ ይመጣሉ፡፡ ዘመን መለወጫ ላይ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡
ተማሪው ተምሮ ወደቀጣዩ ክፍል /ደረጃ/ የሚለወጥበት፣ ገበሬው የክረምትን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋወራት የሚቀበልበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሶ የፀሐይን ወራት የሚቀበልበት ሌላውም እንደዚያ ሆነው ወራቶቹ በዚያ ዘመን ያለው የተፈጥሮ ክስተቶች የሚለወጥበት ዘመን ተለወጠ እየተባለ ይነገራል፡፡
👉 በቀጣይ የዕንቁጣጣሽ ስያሜ አመጣጥ?
#ይቀጥላል
ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለማሕተቦች የተቀላቀሉት የዝማሬ ዳዊት ቻናል ዩቲዩብ ነው ሊንኩን ተጭነው subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ!
https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ይቤሎሙ_ኢየሱስ
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሁድ እመኑ ብየ
ወእመኑ በአቡየ አበርህ(2) በመስቀልየ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
✞ድል በቀራንዮ✞
ድል በቀራንዮ ድል በጎልጎታ
በክርስቶስ መስቀል ጠላት ድል ተመታ
ድል በቀራንዮ ድል በጎልጎታ
በክርስቶስ መስቀል ጽንፈኛው ተመታ
ቤዛነ ቤዛነ መስቀል ቤዛነ(፪)
ለእለ አመነ መስቀል ቤዛነ
ጠላትን ድል መንሻ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
ርስትን መውረሻ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
ሞትን ማሸነፊያ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
መከራን ማለፊያ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
ሰላምን ማወጃ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
የሕይወት ማስረጃ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
#አዝ
ውበት ጥምቀታችን ✞መስቀል✞ቤዛነ
ኃይል ትምክህታችን✞መስቀል✞ቤዛነ
ነገን መመልከቻ ✞መስቀል✞ቤዛነ
አሳዳጁን መርቻ ✞መስቀል✞ቤዛነ
የዓለም መዳኛ ✞መስቀል✞ቤዛነ
የሰላም መገኛ ✞መስቀል✞ቤዛነ
#አዝ
የድላችን ዓርማ ✞መስቀል✞ቤዛነ
የነፍሳችን ግርማ ✞መስቀል✞ቤዛነ
በደም አሸብርቆ ✞መስቀል✞ቤዛነ
በብርሃን ደምቆ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
ታየ ለምድር ሁሉ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
ሳይነጥፍ ፀዳሉ ✞መስቀል✞ ቤዛነ
#አዝ
የፍቅር መግለጫ ✞መስቀል✞ቤዛነ
የስቃይ መቋጫ ✞መስቀል✞ቤዛነ
ለእኛ ውበታችን ✞መስቀል✞ቤዛነ
ሞት ለጠላታችን ✞መስቀል✞ቤዛነ
የመዳን ምልክት ✞መስቀል✞ ቤዛነ
የአዳም ትምክህት ✞መስቀል✞ ቤዛነ
መዝሙር
ዳዊት በቀለ
"... ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል
በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ..."
ገላ ፮፥፲፬
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ጸጋ_ነሣእነ
ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረከብነ
በኃይለ መስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ
በኃይለ መስቀሉ /2/
ኪያከ እግዚኦ ነአኩት
ወንሴብሐከ እግዚአብሔር /2/
#ትርጉም
ጸጋን ተቀበልን ሕይወትንም አገኘን
በመስቀሉ ኃይል በኢየሱስ ክርስቶስ
በመስቀሉ ኃይል /2/
አቤቱ አንተን /2/ እናመሰግንሃለን
እግዚአብሔር /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
💍ወደ ትዳር የሚሄዱ ለራሳቸው የሚመልሱት ጥያቄ⁉️
✍🏽ተጻፈ በስነልቦና አማካሪ Bini Girmachew
🧔♂የወደፊት ባል የምትሆነው ወንድም ሆይ‼️
1)ሚስትህን በእውነት ትወዳታለህ?በሚገጥማት ችግር የራስህን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለህም ቢሆን ለመርዳት ፈቃደኛ ነህ?
2)ምርጫዋንና መልካም ስብእናዋን ለማድነቅ ፍቃደኛ ነህ?
3) ከተወሰነ ዓመት በኋላ ቢያንስ ከ40ዓመት በኋላ ሚስትህ ይህን ዓለም ስለምትንቅ መንፋሳዊ ፍላጎቷን ታከብርላታለህ?
ፈጣሪ የሌለበት ኅብረት በድን ነውና እባክህ ፈጣሪህን ያዝ...ሙሉውን ጽሑፍ ለማግኘት👈🏾
👇👇👇
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
🛑በYoutube ለመከታተል🛑
👇🏾👇🏾👇🏾
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
ጓደኛ ያበዛ ፣ መከራ አበዛ
ለወጣቶች መልእክት ነው
ሁሉን ሰው መውደድ እንጂ ሁሉን ጓደኛ ማድረግ አይቻልም ፤ ደግሞም ተገቢ አይደለም ። #ሁሉን ሰው በእኩል ማየት እንጂ ለሁሉ ሰው ጓዳን መግለጥ ተገቢ አይደለም ፤ ደግሞም ጎጂ ነው ።
#በሚጠሉህ መሐል ወዳጅህን እንደምታገኘው ፤ ከሚወዱህ መሐልም የሚጠላህን ታገኘዋለህ ። ሁሉ ይወደኛል ብሎ የሚያስብ ጅል ብቻ ነው ። ሁሉ ይጠላኛል ብሎ የሚያስብም ትላንትን ያልረሳ ነው ። #አንተ ቀድሞ ትጠላቸው የነበሩትን አሁን በጣም ትወዳቸዋለህ ፣ ቀድሞ በጣም ትወዳቸው የነበሩትን አሁን ባሰብካቸው ቊጥር....ሙሉውን ለማንበብ
🥰ተጨማሪ አስገራሚ ምክሮችን ለማግኘት
👇👇👇
/channel/+Ir8pW1XiBJRkNmQ0
/channel/+Ir8pW1XiBJRkNmQ0
✝ መስቀሉን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናሎች ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን የሚያስተምር ጠቃሚ ቻናሎች ስለሆኑ መስቀሉን ይጫኑ Join ይበሏቸው
/Start
🔳🔳
🔳🔳
🔳🔳🔳🔳🔳🔳
🔳🔳🔳🔳🔳🔳
🔳🔳
🔳🔳
🔳🔳
🔳🔳
✝መስቀሉ አርማችን ነው።
🌼✞መስቀል አበባ
መስቀል አበባ - - ነህ ውብ አበባ
አደይ አበባ ነሽ - - ውብ አበባ(፪)
መስቀል አበባ - - ተቀብሮ ሲኖር
አደይ አበባ - - ሥነ ሥቅለቱ
መስቀል አበባ - - ዕሌኒ አገኘች
አደይ አበባ - - ደገኛይቱ
#አዝ
መስቀል አበባ - - ጥራጊ ሞልተው
አደይ አበባ - - አይሁድ በክፋት
መስቀል አበባ - - ጢሱ ሰገደ
አደይ አበባ - - መስቀል ካለበት
#አዝ
መስቀል አበባ - - ወንዙ ጅረቱ
አደይ አበባ - - ሸለቆው ዱሩ
መስቀል አበባ - - አሸብርቀው ደምቀው
አደይ አበባ - - ላንተ መሰከሩ
ዘማሪ
በሱፍቃድ እንዳልካቸው
"እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ
ነውና በማስተዋል ዘምሩ።"
መዝ ፵፮፥፯
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጓደኛ ያበዛ ፣ መከራ አበዛ
ለወጣቶች መልእክት ነው
ተጻፈ በስነልቦና ባለሙያ BINI GIRMACHEW
ሁሉን ሰው መውደድ እንጂ ሁሉን ጓደኛ ማድረግ አይቻልም ፤ ደግሞም ተገቢ አይደለም ። #ሁሉን ሰው በእኩል ማየት እንጂ ለሁሉ ሰው ጓዳን መግለጥ ተገቢ አይደለም ፤ ደግሞም ጎጂ ነው ።
#በሚጠሉህ መሐል ወዳጅህን እንደምታገኘው ፤ ከሚወዱህ መሐልም የሚጠላህን ታገኘዋለህ ። ሁሉ ይወደኛል ብሎ የሚያስብ ጅል ብቻ ነው ። ሁሉ ይጠላኛል ብሎ የሚያስብም ትላንትን ያልረሳ ነው ። #አንተ ቀድሞ ትጠላቸው የነበሩትን አሁን በጣም ትወዳቸዋለህ ፣ ቀድሞ በጣም ትወዳቸው የነበሩትን አሁን ባሰብካቸው ቊጥር....ሙሉውን ለማንበብ
🥰ተጨማሪ አስገራሚ ኦርቶዶክሳዊ እና ስነልቦናዊ ጽሑፎች ለማግኘት
👇👇👇
/channel/+Ir8pW1XiBJRkNmQ0
/channel/+Ir8pW1XiBJRkNmQ0
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
#መስቀልከ_ይኩነነ_ቤዛ
መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ /2/
ይኩነነ ቤዛ /4/ መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ዐውደ_ዓመት
ዐውደ ዓመት ለባርኮ
ባርኮ ዐውደ ዓመት/2/
ንዒ ማርያም ለምህረት ወሳሕል/2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?
ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡
በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡
ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡
ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡
አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለማሕተቦች የተቀላቀሉት የዝማሬ ዳዊት ቻናል ዩቲዩብ ነው ሊንኩን ተጭነው subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ!
https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌼 መስከረም 1
ሃይማኖታዊ መሠረት
ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን ሲጽፍ «የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጅ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ» ተብሎ በኢሳይያስ እንደ ተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ላይ ተነሥቶ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ ለኃጢአት ሥርየት እየሰበከ መጣ ብሎ በዘመነ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ገልጾታል።
/የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፵፤ ትንቢተ ኢሳይያስምዕ ፵ ቁ ፫ - ፬/።
የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ ሆኖ መገኘቱን በመረዳት የቤተክርስቲያን አበው የበዓላቱን ድንጋጌ በወሰኑበት ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል የኢትዮጵያ ርዕሰ ዓውደ ዓመት በሚሆን መስከረም ፩ ቀን እንዲከበር በየዓመቱ የዘመኑ መጀመሪያ በእርሱ ስም እንዲጠራ አባቶች ደንግገዋል፡፡ / ድርሳነ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1ጠ 3/
ይህንንም በዓል አባቶቻችን በርእሰ ዓውደ ዓመት ማክበር እንደሚገባ አስበው ያደረጉት ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ሆኖ አይደለም፡፡ ለአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወይም ርእሰ ዓውደ ዓመት «ቅዱስ ዮሐንስ» ይባላል፡፡
መጽሐፈ ስንክሳር የዓመቱን መጀመሪያ /መስከረምን/ ሲያትት «ይህ የመስከረም ወር የተባረከ ነው እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው በማለት ያስረዳል፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከመስከረም አንድ ቀን ጀምሮ ቀኑ እየጎደለ ይሔዳል፡፡
👉 ከዚህ በመቀጠል በዓሉ በተለያየ ስያሜ ስለመጠራቱና ትርጓሜያቸውን እንመለከታለን፡፡
ይቀጥላል
ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለማሕተቦች የተቀላቀሉት የዝማሬ ዳዊት ቻናል ዩቲዩብ ነው ሊንኩን ተጭነው subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ!
https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️