ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#የአድዋ_ድል_ቤተ_ክርስቲያን_በገነባችው_የሥነ_ልቡና_ልዕልና_የተገኘ_ነው::

ክፍል ሦስት
አፈ ሊቅ አክሊሉ ገብረ ኪሮስ የተባሉ ሊቅ ‹‹ለኢትዮጵያ ታሪኳ-ነው መልኳ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው የአድዋውን ድል መሠረት እንደሚከተለው ገልጠዋል።
‹‹… ምኒልክን ለአድዋው ድል ያበቃቸው
አንዱም ፣ ኦርቶዶክሳዊ እምነታቸውና የልብ ጸሎታቸው ነው።›› (ገጽ፣፷፭)
ዳንኤል ሮኘስ የተባለ ታዋቂ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ‹‹የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ታውቋታላችሁን?›› በሚል ርእስ ባዘጋጀው መጣጥፍ ላይ የሚከተለውን አስፍሯል።
“ወራሪዎች ምድርዋን የያዙባት መሆኑን ታሪክ ያወሳል፤
ነገር ግን ሃይማኖት የእንቅስቃሴ መሣሪያዋ ሆኖ በመገኘቱ በነፃነት ተመልሳ ተገኝታለች››
የአድዋን ድል በቀጥታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ጋር ያያያዙት ሌሎችም ኢትዮጵያን በአፍሪካ እንደምትገኝ ኢየሩሳሌም አድርገው መቍጠር ጀምረው ነበር። ፕሮፌሰር ሬይሞንድ ጆናስ ‹‹ THE BATTLE OF ADWA:-African victory in the age of Empire›› በተሰኘው ታሪካዊ መጽሐፋችው ‹‹የዓድዋን ድል ተከትሎ በመላው ዓለም ተበትነው ያሉ ዝርዋን አፍሪካውያን የዓድዋን፣ የምኒልክንና የነጻይቱን አገር ኢትዮጵያን ስም በልዩ ሁኔታ ማንሣት ጀመሩ፤ ጥቁር ሕዝቦች እንደ ታላቂቷ ጽዮናዊት ኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ጉዞ ማድረግ ጀመሩ።›› ሲሉ መግለጻቸው ለዚህ ምስክር ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የኢትዮጵያ ገበዝ
የኢትዮጵያ ጠባቂ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ላይ መንግስት ተኩስ ከፍቷል! ምዕመኑ በዓሉን ማክበር ታቦቱን ማንገስ አልቻሉም።

ተዋግቶ ኢትዮጵያን ላስከበራት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መሳርያ ይገባዋል???‼️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቐለ አሉላ ኣባነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሰላም ገብተዋል።

በአየር ማረፊያው ሲደርሱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የቤተ ክህነት ሠራተኞች እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምእመናን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መች ይረሳል
የበገና መዝሙር

መች ይረሳል የዋለልን ውለታ
ቸርነቱ እፁብ ፍቅር የጌታ
የታተመው በልባችን ፅላት
ሞትን ገድሎ የሠጠንን ህይወት

በጥፋቱ ቢወጣ አዳም ከገነት
ቃል ገባለት ዳግም ሊሰጠው ህይወት
ህያው ጌታ አምላክ ፈጣሪ ሳለ
ስለ ቃሉ በእፀ መስቀል ላይ ዋለ
አዝ
በአይሁድ እጅ በፅኑ ተንገላታ
የፍቅር አባት ክርስቶስ የእኛ ጌታ
ሥጋው ደክሞ ቅዱስ ደሙ ፈሰሰ
እዳችንን በሞቱ ደመሠሠ
አዝ
ስንጠላው እርሱ አብዝቶ ወደደን
ስለ ፍቅሩ ሞትን ገድሎ አዳነን
ባርነትን ኃጢአትን ከኛ ጥሎ
ነፃ አወጣን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ
አዝ
ሰላማችን የድንግል ማርያም ፍሬ
ይገባዋል ምስጋና ዝማሬ
ስለ ፍቅሩ ስላረገልን ሁሉ
ተቀኙለት ፍጥረታት ዝም አትበሉ

መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#እያለፈ_ነው_ዘመኔ

እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ/2/ 
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ/2/ 

በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ/2/ 
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ/2/ 

የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ /2/ 
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ /2/ 

እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/ 
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ/2/ 

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ/2/ 
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ/2/ 

ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/ 
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ/2/ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ወዴት ወድቆ ይሆን
የበገና ዝማሬ

እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶ
መልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው ወጥቶ
ለአጨዳው ምጽአት ለበጋው አዝመራ
ወዴት ወድቆ ይሆን ክረምት የተዘራ /2/

ዘወድቀ ውስተ ፍኖት ሲዘራ ያለቀው
አእዋፍ ሰማይ መሳጤ ነጠቀው
ዘወድቀ ዲበ ኮክሕ ጥልቅ አፈር ከሌለው
በደስታ እየሰማ በችግር የካደው
ዘወድቀ ውስተ ሦክ ተጨንቆ እንዳይወጣ
በዓለም ትካዜ በስፍጠተ ብዕል ታንቆ ፍሬ አጣ

ውስተ ምድር ሠናይ የወደቀም ነበር
ዘወሀበ ፍሬ ሰምቶ ሚተገብር
ጌታዬ ከአራቱ ስፍራዎች በምሳሌ ካልከው
ወዴት ወድቆ ይሆን ከእኔ ልብ የላከው
እባክህ ጎተራ አበጅተህ ለአጨዳ ስትመጣ
ከፍሬያማው ክምር ዕድል እንዳላጣ

ከእሾህ ከጭንጫ ላይ ከመንገድ እንዳልቀር
ልቤ ልብ አግኝቶ በምግባር እንዲኖር
ራሴን መስማት ትቼ ላንተ ፈቃድ ልደር

ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ለምን_ጠላኸኝ_ወንድሜ

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ አባት ልጆችኮ ነን
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ የእናት ልጆችኮ ነን
ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን

የተካፈልኩትን ንብረት
አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ
ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል
ብዙ ነው የርሱ መንግስት
አይክፋህ እባክህ ወንድሜ
ፍቅር ይበልጣል ከሃብት
#አዝ
ፊትህ በሐዘን አይጥቆር
ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ
እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ
ያንተም መስዋዕት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው
መታዘዝ ንጉሥ ያደርጋል
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ አገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም

ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✣ የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ✣

╔════●◉❖◉●══════╗
ቅድስት
╚════●◉❖◉●══════╝
✢ Share ✢
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በዓብይ ጾም በገና ክራር እና መሰንቆ ለመማር ለምትፈልጉ ደውሉልን ተመዝገቡ።✝


ዓብይ ጾምን በመንፈሳዊ ዝማሬ ያሳልፉ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ችግር ምክንያት የተደራጀው የሽምግልና ኮሚቴ እስከ አሁን የሰራቸውን ስራዎች ለዐቢይ ኮሚቴው ሪፖርት አደረጉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተከሰተው የቀኖና፣የሃይማኖትና የአስተዳደር ጥሰትን ተከትሎ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር ምክንያት ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት የተደራጁት የሽምግልና ኮሚቴዎች (የሀገር ሽማግሌዎች) ችግሩ ከተፈጠረ ወዲህ በኮሚቴው የተሠሩ ሥራዎችን እና ወደፊት ሊሠሩ ስለሚገባቸው ጉዳዩች ለዐቢይ ኮሚቴ፣ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለመንበረ ፓትርያርክ እና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ዛሬ የካቲት ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም ሪፖርቱን አቅርቧል።

በቀረበው ሪፓርት ላይም ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በሽምግልና ኮሚቴው ወደፊት በሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ ከዐቢይ ኮሚቴው ምክረ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን ወደፊትም የቤተክርስቲያን አንድነትና ሉአላዊነት እስከሚረጋገጥና ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ መደበኛ አገልግሎታችን እስከሚቀጦል ድረስ የተጣለባቸውን መንፈሳዊ አገልግሎት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ፤ በመግለጽ ጉባኤው በጸሎት ተጠናቋል።

ምንጭ፡ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቤተክርስቲያን ያወጀችውን አዋጅ ተከትሎ ሃይማኖታዊ ተልእኳቸውን በመፈጸማቸው ከሥራ የተባረሩ፣ የታሰሩና የተንገላቱ ኦርቶዶክሳዊያን ሪፖርት እንዲያደርጉ የተላለፈ ጥሪ

በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕድ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕገ ወጥ የኤጴስ ቆጰሳት ሢመት ጋር በተያያዘ በተፈጠሩት ችግሮች እንዱሁም ችግሮቹን መነሻ በማድረግ ቅዱስ ሲኖድስ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በጾም እና በምህላ አዋጁ መነሻነት ምእመናን ሰማእትነትን ከፍለዋል፤ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ያለአግባብም ታስረዋል፤ በሕገወጥ መንገድ ተንከራተዋል፤ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ከፍለዋል፤ እንዲሁም ከደመወዝ እና ከሥራ ገበታቸው ጭምር ታግደዋል፤ ተሰናብተዋልም፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቅደስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን እና በምእመናን ላይ እየደረሱ ላሉ ጥቃቶች እና ጉዳቶች እንዱሁም ሕገ ወጥ ተግባራትን በመከታተል ተገቢውን ሕጋዊ ምላሽ መስጠት የሚችል የሕግ ባለሙያዎች አማካሪ እና ድጋፍ ሰጭ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጎ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬  🛑 የአባ አጋቶን ምላሽ “ከመልካም ሥራ ሁሉ የትኛው በጎ ሥራ ከሁሉ የበለጠ ጥረት ይጠይቃል?” - Aba Agaton Tsom ena tselot
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ከስር ባስቀመጥነው LINK ይመልከቱ!
https://youtu.be/HWVnYh7shmw
https://youtu.be/HWVnYh7shmw

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ክበር ተመስገን ጌታችን
ዘለሰኛ መዝሙር

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​በዝማሬ ዳዊት Tube የተላለፉ ትምህርቶች

1⃣ ኦርቶዶክስ እና የዓለም እምነቶች
https://youtu.be/HXh1IUuBOrE
2⃣ እግዚአብሔርን እንዴት መውደድ እንዳለብን
https://youtu.be/Asx80GdsDDE
3⃣ 666 እና የውጭ ዘፋኞች
https://youtu.be/3iFggkALrws
4⃣ ዘፈን እንዴት ተፈጠረ? ማንስ አስተማረን?
https://youtu.be/1P421kYHutU
5⃣ ስለ ቶ መስቀል ክፍል 1
https://youtu.be/qevNJ5hYQ90
6⃣ ስለ ቶ መስቀል ክፍል 2
https://youtu.be/3H0FkrKbg9A
7⃣ ስለ ቶ መስቀል የመጨረሻው ክፍል
https://youtu.be/2QB2Ra7FHf8
8⃣ ሴጋ የፈጸመ የተክሊል ጋብቻ ይገባዋልን?
https://youtu.be/hnt5Y1F4TDY
9⃣ በጸሎት መሀል ወሬ ማውራት
https://youtu.be/2VsM6cVwgcU
1⃣0⃣ ቅዠት ምንድን ነው?
https://youtu.be/m6eD1pzyIWM
1⃣1⃣ የምግብ ሰዓት ጸሎት
https://youtu.be/pjBReIJQ-Q4
1⃣2⃣ የምእመናን አለባበስ ምን ይመስላል
https://youtu.be/fKuDfxWKUyY
1⃣3⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል አንድ
https://youtu.be/HBb3vZBZqzs
1⃣4⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል ሁለት
https://youtu.be/PbmNFCYro4I
1⃣5⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት የመጨረሻው ክፍል
https://youtu.be/1NKzUoqtucs
1⃣6⃣ ስለ ቅዱስ ቁርባን ክፍል አንድ
https://youtu.be/Oji7daT4obw
1⃣7⃣ ንስሐ መግባት ለምን እንፈራለን?
https://youtu.be/kIkhOnUJm_A
1⃣8⃣ ሕማማት
https://youtu.be/NMHnlH0YLEE
1⃣9⃣ ስለ ዓቢይ ጾም
https://youtu.be/uErRRCkMsU0
2⃣0⃣ ዘጠኙ አጾማት
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣1⃣ ለፓስተር ዳዊት የተሰጠ ምላሽ
https://youtu.be/hK473EGk0qs
2⃣2⃣ ለዮናታን አክሊሉ የተሰጠ ምላሽ
https://youtu.be/m8sFeVaja4I
2⃣3⃣ ጸሎት ምንድን ነው?
https://youtu.be/ZFYd4X-eGBo
2⃣4⃣ ክርስቲያናዊ የሆነ ጾም እንዴት እንጹም
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣5⃣ ከፍቅረኛዬ ጋር ወደፊት ስለምንጋባ አሁን ግንኙነት ብንፈጽምስ?
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣6⃣ ግብረ አውናን ምንድነው?
https://youtu.be/1XgZf6hq8bs
2⃣7⃣ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ማድረግ ያለብን ዝግጅት?
https://youtu.be/TQeWVmN47PY
2⃣8⃣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ? 81 ወይስ 66
https://youtu.be/Iggo8ws7quM


በዝማሬ ዳዊት የተላለፉ አጭር ታሪኮች

1⃣ የሰይጣን ጥያቄ
https://youtu.be/mHGEluQCJNY
2⃣ ባላገሩ
https://youtu.be/Kcftb4CReyg

👉 የልደት (ገና) መዝሙሮች
https://youtu.be/iSWmxwIJAac
👉 የጥምቀት መዝሙሮች
https://youtu.be/ESAE29ZvF3o
👉 አጫብር ወረብ
https://youtu.be/phssFP3KCRg
👉 መጾሙን ይጾማል - የበገና መዝሙር
https://youtu.be/q0TcGVnRGb4
👉 ማን ይመራመር - የበገና መዝሙር
https://youtu.be/dHqXNw_27R8
👉 የሰርግ መዝሙሮች
https://youtu.be/Xyc7R1Gk2Fs
👉 ዓለምን ዞሬ አየሁት? - የበገና
https://youtu.be/YP5ugEAYQRg
👉 ስለ ቸርነትህ - የበገና
https://youtu.be/KGBhL_7pA1c

ለሁሉም ሼር ያድርጉ ላላወቁት እናሳውቅ!
Subscribe ማድረግዎን እንዳይዘነጉ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አባቶቻችን ይህንን የበዛ የ"መንግስት" ንቀት በዝምታ ማለፍ የለባቸውም! መግለጫ እንጠብቃለን!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዓድዋ የኢትዮጵያ ከፍታ

🎇 ለፌስቡክ, ለቴሌግራም እንዲሁም ለተለያዩ ሶሻል ሚድያ እንደ ፕሮፋይል መጠቀም ይችላሉ

ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ አቀኑ።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው  ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ተቀብለዋል ።

ምንጭ: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዜና ሽፋን ጥቆማ

የብፁዕ ወቅት አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን ፲ኛ ዓመት በዐለ ሢመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጁት "ዜና መዋል ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ" እና "ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ " የተሰኙት መጽሐፍት የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ይመረቃሉ።

ስለሆነም በደብዳቤው ላይ የተጠቀሳችሁ የሚዲያ ተቋማት በዕለቱና በቦታው በመገኘትና ዘገባውን በመስራት ለሕዝብ ይፋ እንድታደርጉ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን ።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዜና ዕረፍት

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል

በረከታቸው ይደርብን።

ምንጭ፡ EOTC TV

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሄደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ /፪/

ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ጽናት
አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያጽናናት
ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ
እሕት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

መቅደላዊት ማርያም ሶሎሜ ዮሐና
ማርያምን አይዋት ጸንቶባት ሐዘኗ
በልቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው
ዕንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው
ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳ ነው
ያዕቆብም አልቅሷል በሌላ የሠው ደም
ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ጠብቶ ስለአደገ የድንግልና ጡቷን
መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን
በደም ተሸፍኖ ብታየው ውበቱን
ለይልኝ አለችው ከሥጋዋ ነፍሷን

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሔደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ

በእንተ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሠላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን!

✝በዓብይ ጾም በገና፣ክራር ወይም መሰንቆ መማር ትፈልጋላችሁ?✝

እንግዲያውስ ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ
በዓብይ ጾም ምዝገባ ጀምረናል የ6 ወር እና የ3ወር ትምህርቶችን።


🫴መማር ለምትፈልጉ ቶሎ ይደውሉ እና ይመዝገቡ ☎️ 0956861468 ወይም 0912085085

በቴሌግራም ለማውራት ደግሞ @Orthodoxtewahed0


👉በገና፣ክራር እና መሰንቆ መሳሪያዎችን መግዛት ለምትፈልጉም ደውሉልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በወለጋ ነቀምቴ ከተማ መንበረ ጵጵስናው በሚገኝበት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ውጥረት ተከስቷል።

የብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሀገረ ስብከት በሆነው በነቀምቴ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስን ትእዛዝ በሚቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን እና ሕገወጡን ተሿሚ እንቀበላለን በሚሉ ከሌላ አካባቢ በመኪና ለሁከት እንዲመጡ በተደረጉ ሰዎች መካከል ውጥረት መከሰቱ ተገልጿል።

ጉዳዩ የተከሰተው ነገ የሚታሰበውን ወርኃዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓል ምክንያት በማድረግ ሕገወጥ ተሿሚ የሆነውና ደጋፊዎች ነን የሚሉ ወደ ገዳሙ እንገባለን በማለታቸው እና በሰንበት ተማሪዎች፣ ኦርቶዶዶክሳውያን ወጣቶችና የአካባቢው ምእመናን ቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘ አካል በገዳሙ አይገባም በማለታቸው ነው።

ውጥረቱን ለማርገብ የመከላከያ ሠራዊት የተገኘ ሲሆን የከተማው ከንቲባና የከተማው ፖሊስ አዛዥ ጉዳዩን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ከብሔርና ፖለቲካ ጋር በማገናኘት መፍትሔ ሳይሰጡ በማባባስ ላይ እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ምእመናን፣ ወጣቶችና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቁ ይገኛሉ።

ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በሕገ ወጥ መንገድ በወሊሶ የተሾሙ 25 "ኤጲስ ቆጶሳት" በቅዱስ ሲኖዶስ መወገዛቸው እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ማገዱ ይታወሳል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሠላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን!

✝በዓብይ ጾም በገና፣ክራር ወይም መሰንቆ መማር ትፈልጋላችሁ?✝

እንግዲያውስ ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ
በዓብይ ጾም ምዝገባ ጀምረናል የ6 ወር እና የ3ወር ትምህርቶችን።


🫴መማር ለምትፈልጉ ቶሎ ይደውሉ እና ይመዝገቡ ☎️ 0956861468 ወይም 0912085085

በቴሌግራም ለማውራት ደግሞ @Orthodoxtewahed0


👉በገና፣ክራር እና መሰንቆ መሳሪያዎችን መግዛት ለምትፈልጉም ደውሉልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስሆነም የደረሱትን እና እየደረሱ ያለትን ጉዳቶች በተመለከተ ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ማሰባሰቡ ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ እና አሁንም የሕግ ክፍሉ በተለያየ መንገድ በሚደርሰው መረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ በውስንነት ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሶ መረጃ እና ማስረጃ ያላቸው ማናቸውም ምእመናን እና ምእመናት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጆቻችሁ ላይ ያለ የሰነድ፤የድምጽ፤ እና የምስል ማስረጃዎቻችሁን በሙሉ ከዚህ በታች በተቀመጡት አማራጭ የመረጃ መንገዶች ታሳውቁን ዘንድ የሕግ ክፍሉ ያሳስባል፡፡

በመሆኑም ፦
፩. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ውስጥ ተቀጥራችሁ ስትሠሩ የነበራችሁ እና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ከሥራ እና ከደመወዝ የታገዳችሁ እንዱሁም የተሰናበታችሁ በሙሉ ዝርዝር መረጃውን በመላክ እንድታሳውቁን፤

፪. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ሙለ መረጃ በመላክ እንድታሳውቁን፤

፫. በማናቸውም የፌዳራል፤ የክልል እና የከተማ መስተዳደር ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ሙለ መረጃ በመላክ እንድታሳውቁን፤ እያሳሰብን ያላችሁን ማናቸውም መረጃ እና ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከተነገረበት ከዛሬ የካቲት ፲፰ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ጀምሮ በስልክ ቁጥር +251985585858 በዋትስአፕ፤ በቴሌግራም ወይም በኢሜይል አዴራሻችን፡-eotcer@gmail.com የሞቱትን፤ የተጎደትን፤ የታሠሩትን እና የተሰወሩትን ሰዎች ስም እና የድርጊቱን ውጤት የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ ታጋሩን ዘንዴ በቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላፋሇን፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የአባ ሳዊሮስ፣ አባ ኤዎስጣቴዎስ እና አባ ዜና ማርቆስ እግድ በፍ/ቤት መነሳቱ ተገለጸ።

ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕግ ክፍል በተሰጠው መግለጫ እንደተገለጸው የካቲት 03 ቀን 2015 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ ያስተላለፈውን እግድ የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ ማንሳቱ ገልጸዋል።

በሕገ ወጥነት የተሾሙትም 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ ወስኗል ብለዋል።

በተጨማሪም ዛሬ ጠዋት በነበረው ችሎት ፍርድ ቤቱ ፓስተር ብንያም ሽታዬ በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ቢወስንም ፖሊስ ይግባኝ በማለቱ ምክንያት ለፊታችን ሰኞ ተቀጥሯል።

በተያያዘ የቤተ ክርሰቲያንን መግለጫ በፌስ ቡክ ገጻቸው አጋርተዋል /share ያደረጉ/ የተባሉ ሁለት የፖሊስ አባላት አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።

በጾመ ነነዌ ጥቁር ለብሳችኋል በሚል ምክንያት ሠራተኞቻቸውን ያገዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮሚሽንና የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ላይ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ ይህንን ትእዛዝ በማውረዱ ክስ ተመስርቶበታል።

ከዚህም ባለፈ ይህንን የፈጸሙና ያስፈጸሙ ተቋማትና ግለሰቦችም ላይ ክስ ቀርቧል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዐብይ ጾም ለምን የንሰሐ መዝሙር ብቻ ሆነ?

🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ድምፀ
👉🏾በዐብይ ጾም ለምን ከበሮ አይመታም❓
👉🏾በዐብይ ጾም ለምን ፅናፅል አንጠቀመም❓
👉🏾በዐብይ ፆም መብላት የሌለብን ምግቦች በየአመቱ ጥያቄ እሚያስነሳው 👉🏾🐠🐟 ዓሳን አለመብላት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በርግጥ ብዙ ያልሰማችሁት ት/ት አለ የፈለጋችሁትን አርዕስት በመምረጥ ከስራቸው ባለው Link በመግባት ማዳመጥ ትችላላችሁ። ታዲያ በዛው Subscribe ማድረጋችሁን እንዳትረሱ።

ሼር በማድረግ ለሁሉም አድርሱልን
ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን❤

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬  🛑 ልጆቻችንን ለታቦት እንስጥ ወይስ ለክርስትና እናት እና አባት? ከእናንተ ለተጠየቀው ጥያቄ የተሰጠ መልስ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ መልሱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/MGu9vE6vImw
https://youtu.be/MGu9vE6vImw

እናንተም ያላችሁን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ!

Читать полностью…
Подписаться на канал