የዓለምን በደል
የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክት ትቶ
ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - - - አዝ - - - - - -
የሰማያት ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - - - አዝ - - - - - -
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - - - አዝ - - - - -
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቀን ሲመሠርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ታህሳስ 29/04/2015 ዓ.ም
✝የበዓለ ልደት ምስባክ
ምስባክ ፦ መዝ 71÷ 10
ነገሥተ ተርሴስ ወደሰያት አምኃ ያበውዑ።
ነገሥተ ሳባ ወዐረብ ጋዳ ያመጽኡ።
ወይሰግዱ ሎቱ ኲሎሙ ነገሥተ ምድር።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በድንግል ትህትና
በድንግል ትህትና አለምተደነቀ /2/
እዉነተኛ መጠጥ ከሆዷ ፈለቀ /2/
ሰዉ የሚድንበት ሮማንና ገዉዝ /2/
ከሆዷ ፈለቀ እንደ ምንጭ እንደወንዝ /2/
አዝ
ፀጋን ስላደላት የመዉለድ ስጦታ/2/
በፍቅር ሳበችው የፍጥረቱን ጌታ /2/
ሰማያዊዉ አምላክ ከእርሷ ሥጋንነሳ /2/
ፀሐይ ስለወጣ ቀረልን አበሣ /2/
አዝ
እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ እርሷን አያህሉም /2/
አዝ
እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ ድንግልን አይቀድሙም /2/
አዝ
እግዚአብሔር ምድርን አየና በመላ /2/
ማርያምን አገኛት ከቤተ-መቅደሱ ከቤቱ ተጥላ
ከመላዕክቱ ጋር እየተጫወተች /2/
የሰማዩን መና እየተመገበች /2/
ሙሉ ዜማው በዚሁ ይወርዳል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 🛑 የክርስቶስን ልደት እንዴት ላሳልፍ? ሶሪያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የሚለን ነገር አለው
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/aPgfhmGg2FU
https://youtu.be/aPgfhmGg2FU
አማን በአማን
አማን በአማን /4/
መንክር ስብሐተ ልደቱ
#ትርጉም፡-
እውነት በእውነት /4/
ድንቅ ነው የጌታ ልደት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በጎል ሰከበ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ /2/
ቤዛ ኩሉ ዓለም/2/ ዮም ተወለደ /4/
#ትርጉም፡-
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቀለለ
የዓለም መድኃኒት/2/ ዛሬ ተወለደ/2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በቀደም በምስጢረ ሥጋዌ ዙሪያ በተማማርነው መሠረት ነገ ምሽት ላይ የጥያቄ ፕሮግራም ይኖረናል። እናንተም ጥያቄ ካላችሁም ማስቀመጥ ትችላላችሁ!
Читать полностью…ሳር ቅጠሉ
ሳር ቅጠሉ ሰርዶ ሰንበሌጥ ቀጤማ
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምለም የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተሞልተው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ (፪)
ያ ትጉህ እረኛ ሳለ በትጋት
ብርሃን ተገለፀ በእኩለ ለሊት
ጥሪ ተድርጎለት ከሰማይ ሠራዊት
ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ (፪)
የእረኝነት ስራ ተንቆ እንዲኖር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበረ
የብዙ ሰው ራስ መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ (፪)
የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌታ ተወለደ እልል እልል በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉስ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ (፪)
ስለተወለደ መድኅን የኛ ተስፋ (፪)
በደል ተወገደ ሐጢአትም ጠፋ (፪)
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ (፪)
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/
አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#የልደት_ወረብ
#አንፈርዓፁ
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል /2/
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ /2/
"ቅኝት ዜማ"
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 🛑 ጻድቃን ላይ ለሚዘባበቱ መናፍቃን እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጥልን! የጻድቁ ተክለሃይማኖት አጭር ታሪክ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/6geWAZ_doak
https://youtu.be/6geWAZ_doak
✝ማስታወቂያ✝
👉በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ።
በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርታችን ዙሪያ የተላኩ 4 ጥያቄዎች ነበሩ መልሶቻቸው እነዚህ ናቸው👇
1.መ (ሀ እና ለ)
2.መ ሁሉም
3.ሐ. ከ2 ባህርይ 1 ባህርይ፤ ከ2 አካል 1 አካል መሆን ማለት ነው
4.መ ሁሉም።
እነዚህን ይመስላሉ😊 በትክክል እንደመለሳችኋቸው ተስፋ አደርጋለሁ።
እስከ አሁን ምሥጢረ ሥላሴ እና ምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርትን በድምጽ ልከንላችሁ ስትማሩ ነበር እንደ ድንገት ያላዳመጣችሁ ወይም ያለፋችሁ ካላችሁ ወደ ላይ በመውጣት ታዳምጡ ዘንድ እንጠይቃለን።
ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ እነዚህን 5ቱን አእማደ ምሥጢራት ማወቅ አለበት የኦርቶዶክስነታችን መሠረት ስለሆነ። ስለዚህ ትምህርቱን ከታች እናስቀምጥላችኋለን ወደ ላይ ወጥታችሁ አዳምጡት።
👉 በሁለቱም ርዕሶች ዙሪያ የተጠየቁ ጥያቄዎች አሉ እነርሱን የጠየቃችሁ እህት ወንድሞች የአሁኑ ሰኞ 3:00 ላይ መልስ የምንሰጥበት ስለሆነ እንድታዳምጡ እንጠይቃለን።
መልካም በዓል
አንፈራፁ
አንፈራፁ ሰብዓሰገል /2/
ረኪቦሙ ህፃን /2/ ዘተወልደ ለነ /4/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ታህሳስ 29/04/15 ዓ.ም
ዕለተ በዐለ ልደቱ ለእግዚእነ
✝በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡
ዲ/ን ገላ 4 ÷1_12
ን/ዲ 1 ዮሐ 4÷9_ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 13÷16_22
ምስባክ፦መዝ 79÷1
የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቀ ዓረብ።
ወዘልፈ ይፄልዩ በእንቲአሁ።
ወኲሎ አሚረ ይድኅርዎ።
ትርጉም፦
እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል።ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይፀልያሉ።ዘወትር ይባርኩታል።
ወንጌል፦ ሉቃ 2 ፥1 - 21
ቅዳሴ፦ ጎርጎርዮስ ካልእ
👉 @ortodoxmezmur
በጎለ እንስሳ
በጎለ እንስሳ /4/
በጎለ እንስሳ ተወለደ አማኑኤል/4/
#ትርጉም፡
በእንስሳት በረት አማኑኤል ተወለደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ወላጆች ለልጆቻችሁ የልደትን በዓል አስተምሩ የማይጠቅም የዓለም ስጦታ ከምትሰጧቸው በነፃ የተሰጠንን ክርስቶስ ስጧቸው!
#ልደተ_ክርስቶስ /የገና በዐል/
በአዜብ ገብሩ
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? ዛሬ ስለጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት /ገና በዓል/ እንነግራችኋለን፡፡ በደንብ ተከታተሉን፡፡ እሺ?
ልጆች በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ፡፡ አውግስጦስ ቄሳር የተባለ ንጉሥ ሰው ሁሉ ይቆጠር ዘንድ አዘዘ፡፡ በትእዛዙ መሠረትም ሰው ሁሉ ሊቆጠር ወደየትውልድ ከተማው ሄደ፡፡
ዮሴፍና እመቤታችንም ሊቆጠሩ ከናዝሬት ወደ ትውልድ ሥፍራቸው ወደ ቤተልሔም ሄዱ፡፡ በቤተልሔም ሳሉም እመቤታችን የምትወልድበት ቀን ደረሰ፡፡ በዚያ ሥፍራም ብዙ እንግዳ ስለነበር እነ ዮሴፍ የሚያርፉበት ቦታ አላገኙም ነበር፡፡ ማደርያም ስላልነበራቸው በከብቶች ማደርያ በበረት ውስጥ እመቤታችን ልጅዋን ወለደችው፡፡
በጨርቅ ጠቅልላ እዛው በበረት ውስጥ አስተኛችው፤ በዚያ ሀገር ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ሌሊት ከብቶቻቸውን ይጠብቁ ነበር፤ የእግዚአብሔር መልአክም በእረኞቹ አጠገብ ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤ በጣምም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው ‹‹እነሆ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ‹‹እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡
ይኸውም ጌታ እና እግዚአብሔር የሆነ መድኃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እናንተም ባገኛችሁት ጊዜ ምልክቱ እንዲህ ነው፡፡ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ እነዚህ እረኞች እርስ በርሳቸው ‹እስከ ቤተልሔም እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን ነገር እንወቅ አሉ፡፡
ፈጥነውም ሄዱ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን አገኙአቸው፡፡ ሕፃኑንም በበረት ውስጥ አገኙት፡፡ በአዩትም ጊዜ የነገሩአቸውን ሰምተው በጣም ተደነቁ፡፡ እረኞቹም እንደነገሩአቸው ባዩትና በሰሙት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ‹‹በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን በምድርም ለሰው ልጆች በጎፈቃድ ሆነ›› ብለው እያመሰገኑና እያከበሩ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡
አያችሁ ልጆች እነዚህ ክርስቶስን ሊያዩ የመጡ ሰዎች ደስተኞች ነበሩ፤ ስለዚህ ልጆች እኛም በቤተ ክርስቲያን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በደስታ ልናከብር ይገባናል፡፡ ከመላእክት ጋር ሆነንም ‹‹በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን›› እያልን እንዘምር፡፡ እንግዲህ ልጆች መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ እሺ፡፡
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
🔸 የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ዕውቀቶች
🔸 ንግግሮች እና ቃለምልልሶች በግእዝ
🔸 መሠረታዊ የግስ እና የስም ጥናቶች
🔸 በግእዝ ቋንቋ ዙሪያ መረጃዎች'ና ዜናዎች
🔸 ዕለታዊ መዝገበ ቃላት
🔸 የወዳሴ ማርያም እና የመዝሙረ ዳዊት ንባብ ትምህርት
🔸 የባሕረ ሐሳብ ትምህርት
🔸 ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች እና ኮርሶችን እና የመሳሰሉትን እየሰጠን እንገኛለን።
🌺 ቤተሰብ ሆነው ይከታተሉን 🌺
▫️ ○ ▫️
@MesereteGeez
@MesereteGeez
@MesereteGeez
▫️ ○ ▫️
ኢየሩሳሌም
እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆን/2/
ኢየሩሳሌም/3/ በሆን ጌታ ሲወለድ ባየን
እንድ አረኞች ወይም ሰብአ ሰገልን በሆን/2/
ኢየሩሳሌም/3/ በሆን ጌታ ሲወለድ ባየን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የልደት ወረብ
ቤዛ ኲሉ ዓለም
ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ /2/
የዓለም ሁሉ መድኃኒት ዛሬ ተወለደ /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በኤፍራታ ምድር
በኤፍራታ ምድር በቤተልሄም/2/
ጌታ ተወለደ ከድንግል ማርያም/2/
ብራናዊው ኮከብ ከሰማይ ዝቅ አለ/2/
ፍጥረትም ዘመረ ሀሌ ሉያ እያለ/2/
አዝ
መንጋውን በሌሊት ሲጠብቁ እረኞች
ከሰማይም ሰሙ ታላቅ የምስራች
በመላእክት ግርማ ምድር ስታበራ
የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ
አዝ
ድንገትም የሰማይ ሰራዊት ተገልጠው
ባንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋር ሆነው
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሰላምን በምድር በጎ ፍቃድ ለሰው
አዝ
ቤተልሄም ሄደው ጌታን ተሳለሙ
ከእናቱ ጋራ ሆነው በግርግም አገኙት
የመላእክትን ዜማ እረኞች አወሩ
በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ
አዝ
በመዝሙር ቢሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ
ህፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈለጉት
እርሱ ነው ለሰዎች የድነት ምልክት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#የልደት_ወረብ
#አንፈርዓፁ
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል /2/
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ /2/
"አቀራረብ"
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝
ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች?
እስከ አሁን ድረስ ምሥጢረ ሥላሴ እና ምሥጢረ ሥጋዌን ያየን ሲሆን በእነዚህ ርዕሶች ላይ ጥያቄዎች ካላችሁ አሁን መጠየቅ ትችላላችሁ። ሰብስበን መልስ እንሰጣለን።
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/
አዝ
በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና
ተክለሃይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ
ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#ልደት
መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።
#ዕድገት
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።
#መጠራት
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።
#አገልግሎት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት።
1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።
2ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::
#ገዳማዊ ሕይወት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።
እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል።
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል።
#ስድስት_ክንፍ
ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው።
#በዚያም :-
-የብርሃን ዐይን ተቀብለው
-6 ክንፍ አብቅለው
-የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
-ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
-ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
-ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።
#ተአምራት
የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
ሙት አንስተዋል
ድውያንን ፈውሰዋል
አጋንንትን አሳደዋል
እሳትን ጨብጠዋል
በክንፍ በረዋል
ደመናን ዙፋን አድርገዋል።
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::
#ዕረፍት
ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል።
ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️