ሰበር ዜና
ከቀኖናና ከህግ ውጪ በተደረገው ሲመት ከተሾሙት መካከል አባ ጸጋዘአብ አዱኛ በዚህ ሰዓት ቤተክርስቲያንን ይቅርታ ለመጠየቅ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የይቅርታ ደብዳቤ አስገብተዋል።
በደብዳቤአቸውም ያሳደገቻቸውን፣ ያስተማረቻቸውንና ለዚህ ክብር ያበቃቻቸውን ቤተክርስቲያን ማሳዘናቸውን ገልጸው ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባ ቶማስ የቂሊያ ሜትፖሊታን እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ።
ምንጭ: EOTC TV
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን መብትና ክብር አስጠባቂ ኅብረት ወቅታዊ መግለጫ
“ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት፤ቅድስት በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን”
ጸሎተ ሃይማኖት
ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተፈጸመውን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን የወጣ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠ "ሲመተ ጵጵስና" በቀጥታ በቤተ ክርስቲያን ህልውና ላይ የተቃጣና ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ መንበረ ፕትርክናውን በመገዳደር ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የተሰነዘረ ጥቃት አድርገን እንደምንወስደው ለመግለጽ እንወዳለን፤
ስለሆነም፡
አሁን ላይ የተፈጠረው ችግር ሊፈታ የሚገባው የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት በመከተል እንደመሆኑ መጠን ለጉዳዩ ባለቤት ለቤተ ክርስቲያን ብቻ መተው አግባብ መሆኑን እየገለጽን መንግሥት ሰላምና ጸጥታ የማስከበር ኀላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን እናሳስባለን። የመንግሥት ኀላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣት የችግሩ ፈጣሪና መሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሁነኛ ማስረጃ ነው። ይህን ኀላፊነቱን ባልተወጣ መጠን ችግሩ ሀገርን ሊያፈርስና ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ወደ ነበርንበት አገራዊ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባን የሚችል መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ሰበር ዜና
"መንግሥት ቤተ ክርስቲያንና አባቶችን የመጠበቅ ኃላፊነቱን ካልተወጣ ልጆቻቸው ለመጠበቅ ተዘጋጅተናል፤ በቂ ዝግጅትም አድርገናል።"
የመንፈሳዊ ማኅበራትና የኅብረቶች የጋራ መግለጫ
ዛሬ ጥር 16 ምሽት ማኅበረ ቅዱሳን፣ አገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት፣ ምእመናን ኅብረት ፣ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት፣ የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በጋራ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫውም የማኅበራቱ ተወካዮች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካጋጠማት ታሪካዊ ክስተት አንጻር ከመቼውም ጊዜ በላይ የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና የምናስጠብቅበት እና ከአባቶቻችን ጎን የምንቆምበት ወቅት በመሆኑ በኅብረት መክረን አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ብለዋል።
ማኅበረ ቅዱሳንን ወክለው የተገኙት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም በመግለጫው እንደተናገሩት የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ያቃለለ የነገ የሐዋርያዊ አገልግሎትን ያሰናከለ በመሆኑ አባቶቻችን ይህንን ያማከለ ውስኔ እንዲወስኑ እንጠይቃለን ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም መንግሥት እጁን ከዚህ ሂደት እንዲያነሳ ይልቁንም የእሱ ግዴታ የሆነውን ጥበቃ እንዳያነሳ ይህ ካልሆነ ግን ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያን እስከሰማእትነት ለመታደግ የታመኑ ናቸው ብለዋል። ምእመናንም ሳይደናገጡ በጸሎት እንዲተጉ እና ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖራቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል።
ከመንግሥት ጋርም በቀጣይ ችግሩን እንዲረዳና ቤተ ክርስቲያን የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ እድል እንዲሰጣት መወያየታቸውን በመግለጽ የዜጎችን ደህንነት ካልጠበቀ ግን ከተጠያቂነት አይድንም ሲሉ ገልጸዋል።
"የኖላዊነት ኃላፊነታችሁን የዘነጋችሁ ወንድሞቻችን እና ሌሎችም ሰዓቱ ከማለቁ አስቀድሞ ወደ ልባችሁ በመመለስ ወደ ቀድሞው ማንነታችሁ ተመለሱ" ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ አሳሰቡ።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠበቂ በትናንትናው ዕለት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ "ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን" አስመልክቶ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው (ዮሐ.10፥1)በሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መልዕክታቸውን የጀመሩት ብፁዕነታቸው በትናንትናው ዕለት በወሊሶ በተፈጸአው ኢ-ቀኖናዊ "ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በእጅጉ አዝናለች ብለዋል።
መከራና ፈተና ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተለይተው የማያውቁ ቢሆንም ካለን መከራንና ችግርን የማለፍ ልምድ በመማር ይህንን አስቸጋሪ እና ፈታኝ ወቅት በጥበብ እና ብስለት በተመላበት አኳኋን ልናሳልፈው ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
አሳስበዋል።
ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ብዙ መናገር ቢቻልም ያለንበት ወቅት ይህንን ለመናገር ጊዜው ባለመሆኑ ምዕመናን ልጆቻችን ሁሉ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አፈጻጸም ራሳችሁን ዝግጁ በማድረግ ፤ መንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስኑትን ውሳኔ በትዕግስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን ብለዋል።
ብፁዕነታቸው በዚህ ስህተት ውስጥ የገባችሁ የኖላዊነት ኃላፊነታችሁን የዘነጋችሁ ወንድሞቻችን እና ሌሎችም ሰዓቱ ከማለቁ አስቀድሞ ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ ወደ ቀድሞው ማንነታችሁ ትመለሱ ዘንድ ጸሎታችን መሆኑን እንገልጻለን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው።
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት አሸገ፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት መታሸጉን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በፌስቡክ ገጽ አስነብቧል።
በትናንትናው ዕለት 3ቱ አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመናድ እና ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለመከፋፈል በማቀድ 26 መነኮሳትን ሾመናል በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
ትላንት በተመለከትነው አስነዋሪ እና ሥርዐተቢስነት የተሞላበት ጉባኤ /ጉባኤ ከለባት/ የመንግስት እጅ እንዳለበት ግልጽ ነው። በቅርቡ በሌሎች እምነቶች የሰራውን የመከፋፈል ሴራ በኦርቶዶክስ ላይ ሊሳካ እንደማይችል ማወቅ ይኖርበታል።
ይህ ንግግር ዝግጅቱ በሃይማኖታዊ የመንግሥት ኔትዎረክ ውስጥ መረጃ እንደነበረ ይጠቁማል። ከሳምንት በፊት ቤተክርስቲያንን ለማዘናጋት ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ የነበሩና አንዲጠይቁ የላኳቸው አካላት ለዚህ ሤራ እየተዘጋጁ ነበር ማለት ነው። የማስመሰል ጭምብል ወልቋል።
ጉዳዩ ከአሁን በኋላ የእውነተኛ ክርስቲያኖችና አባቶች፣ አንዲሁም ዋናው የአግዚአብሔር ነው። ቁማርተኞቹ በእምነትም በኩል እንዲህ ያሉ ጎበዝ ተጫዋቾች ናቸው።
በጉባኤ ከለባት በህገወጡ ቡድን ከተሾሙት የስልጣን ጥመኞች ዝርዝር መካከል 👇👇የሚገኙበት
1. አባ ተክለ ሃይማኖት ።።።።።።። የቀድሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
2. አባ ገብረ እግዚአብሔር ።።።።።። የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ
3. አባ ሽኖዳ ።።።።።።።።። አለም ገና ኢየሱስ አስተዳዳሪ
4. አባ ወልደ ጊዮርጊስ ።።።።።።። ወለቴ ዮሐንስ አስተዳዳሪ
5. አባ ገብረ ኢየሱስ ።።።።።። አለም ገና ሚካኤል አስተዳዳሪ
6. አባ ገብረማርያም ነጋሳ ።።።።። የኦሮምያ ቤተ ክህነት መስራች
7. አባ ጳውሎስ ከበደ ።።።።። የሐረር ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበረና በተሐድሶነት የተባረረ
8. አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ።።።።።።። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጽሐፍ መምህር
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ ።
መግለጫውን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።
ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :-
1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት በሀሣብና በጸሎት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ: EOTC TV
እጅግ አሳዛኝ ዜና!
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የምስካየኅዙናን መድኃኒአለም ገዳም የበላይ ጠባቂ በዛሬው ዕለት እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ 25 ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመዋል!!!
በዛሬው ዕለት በወሊሶ መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ ለስልጣን ጥማት ያደረባቸውን 25 ኤጲስ ቆጶሳት አድርገው ሾመዋል።
ከአንድ የቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የማይጠበቅ እና ህገ ቤተክርስቲያንን የሚፃረር ድርጊት ይፈፅማሉ ብለን የማንጠብቃቸው አቡነ ሳዊሮስ ይሄንን አድርገዋል።
ቤተክርስቲያኒቷ በራሷ ስርዓት እና ህግ የምትገዛ ሆኖም ሲኖዶሳዊት የሆነችውን ይቺ ሀገር የሆነችውን ቤተክርስቲያን ብትንትኗን ለማውጣት ይሄን ያህል መንገድ መራመዳቸው እጅግ የሚያሳዝን ተግባር ነው።
በአስቸኳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለምመናኗ መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ቃና_ዘገሊላ
በዛሬው ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት ነው። ሰርግ ደግሶ የነበረው ዶኪማስ አዘጋጅቶት የነበረው ወይን ጠጅ አልቆ በተጨነቀ ጊዜ ችግሩን ቀርቦ ሳይነግራት ማለቁን አውቃ ልጄ ሆይ ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል በማለት ተናግራ ውሃው ወደ ወይን ጠጅ እንዲለወጥ የማማለድ ተግባር የፈጸመችበት ዕለት ነው።
አምላካችን ጋብቻ ክቡር መሆኑን ዓለም እንዲረዳ ያደረገበት፣ ሰዎች ያዘጋጁት ነገር ተንጠፍጥፎ አልቆ በተጨነቁ ጊዜ እመቤታችን ለልጇ አሳስባ ጎደሏቸው እንዲሞላ ፣ጭንቀታቸው እንዲወገድ የምታደርግበት በዓል ነው።
ጥንቱ ዕለቱ የካቲት 23 ቀን ቢሆንም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የውሃን በዓል ከውሃ በዓል ጋር ማክበር ይገባል ብለው የሚጠጡት አልቆባቸው ተጨንቀው የነበሩበት ቃና ዘገሊላ የውሃ በዓል በመሆኑ ከውሃ በዓል ከሆነውና የእዳ ደብዳቤያችን ከተደመሰሰበት ከጥምቀት ጋር እንዲከበር በማድረጋቸው በዛሬው ዕለት እናከብረዋለን።
ዛሬ የዶኪማስ ጭንቀት ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ምክንያት የሚከሠት የክርስቲያኖች ሁሉ ጭንቀት የተቃለልበት ዕለት ነው። እመቤታችን ዶኪማስ ሳይለምናት ጭንቀቱን እንዳቃለለችለት ለልጅሽ አሳስቢልን ብለን ብንማጸናት የማይፈጸምልን ነገር፣ የማይወገድልን ጭንቀት አለመሆኑን የተረዳበት ዕለት ነው። በዓሉን ማክበር የሚገባንም ይህን እያሰብን ነው። አምላካችን ከበዓሉ በረከት ይክፈለን።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት እንኳን አደረሳችሁ እያለህ
ማስታወቂያ
ለጥምቀት በዓል ልብስ አዘጋጅተው ሊሆን ይችላል። የሰ/ት/ቤታችን የጥምቀት ቲሸርት ግን የግድ ሊኖሮት ይገባል ምክንያቱም
1ኛ የሰ/ት/ቤቱን ዘርፈ ብዙ የሆነውን አገልግሎት ይደግፋሉ
2ኛ የደብራችንን ጥምቀተ ባህር ይደግፋሉ
3ኛ ቲሸርቶቻችን ለጥምቀት በዓል ብቻ ሣይሆን በተለያዩ በዓላት ወቅት የሚለበሱ ናቸው። ከፍተኛ በሆነ ጥራት ስለምናትማቸው ለቲሸርቶቻችን ጥራት ምስክር እናንተ ናችሁ።
4ኛ በረከት ለእርሶም ለቤተሰቦም ይዘው ይገባሉ ደቤትዎ።
ስለሆነም በከፍተኛ ጥራት ጥቂት ቲሸርቶችን አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ
09 27 43 42 37
09 93 51 29 98
09 12 33 01 26
09 04 15 82 43
09 22 58 05 95
እንዲሁም የሰ/ት/ቤቱ መዝሙር ቤት ቢመጡ በሚፈልጉት ሳይዝ ያገኛሉ።
ዋጋው 399 ብር ብቻ
ቦታ: በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች እንደምን ቆያችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን
በዓለ ጥምቀትን በያላችሁበት እንዴት ልትቀበሉት አሰባችሁ? እስቲ በየሰፈራችሁ የሰራችሁትን ወይም የተሰራውን የበረከት ሥራ ከ1 ደቂቃ ባልበለጠ ቪድዮ አጋሩን! ለመላው ዓለም እናዳርሰዋለን።
ከምትሉኩልን መሐከል በጥሩ አቀራረጽ የተላኩትን መርጠን በTelegram, YouTube እንዲሁም በTiktok እናጥለቀልቀዋለን። ከምትልኩልን ቪድዮ ጋር የሰፈሩን ስም አብራችሁ መላክ እንዳይረሳ።
ለመላክ ይህን ይጠቀሙ! እንደደረሰን Seen ብለን በመላክ እናሳውቃለን።
@zmaredawit_messengerbot
🎬 🛑 ለምን ኢትዮጵያ ብቻ በኦርቶዶክስ ላይ ተዋህዶ ተብሎ ተቀጠለ?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ መልሱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/5ObRY_PMmis
https://youtu.be/5ObRY_PMmis
እናንተም ያላችሁን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ!
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለ3 ቀናት የሚቆይ ጸሎት አወጀች፡፡
በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ከተጠናቀቀነ በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ እንዲሆን አዋጅ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ( ዶ/ር ) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል፡፡
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ውጪ የሚደረግን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማይቀበል የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአቋም መግለጫው አስታውቋል።
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ
ልዩ ጽሕፈት ቤት፣
ካይሮ፡ 24 ጃንዋሪ 2023 ዓ/ም (ጥር 16 ቀን 2015 ዓ/ም)
የአቋም መግለጫ
የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አቡነ ሳዊሮስ በተባሉ ጳጳስ የተፈጠረውን ቤተ ክርስቲያንን የመክፈልና ራሳቸውን በኢትዮጵያ የኦሮሞ ክልል ፓትርያርክ አድርገው የመሠየም ተግባር ሙሉ ለሙሉ የማይቀበለው ፍጹም ሕግን የጣሰ መሆኑና እና በእሳቸው መሪነት ተሾሙ የተባሉ 26 ጳጳሳት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕግ የጣሱ እንዲሁም መሠረት ያለውን እና ቋሚ የሆነን ከጥንት ጀምሮ በትውልዱ ሁሉ ሲተላለፍ ከመጣውን ከኦርቶደክስ ቀኖና እና መመሪያ ሕገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ዕውቅና ውጭ የሚደረግን ሢመት ዕውቅና አትሰጥም አትቀበልም።
ከዚህ በተጨማሪ ኮሚቴው (የውጭ ጉዳይ) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት እየገለጽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፤ ሜትሮፖሊታን የሆናቸሁ ሁላችሁ ጥንታዊነት እና በታሪክ የበለጸገች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ትሥሥር በፍቅርና በሰላም ሁናችሁ እንድትጠብቁ በጥብቅ አደራ እንላለን፡፡
🎬 🛑 ምስጢረ ሥጋዌ የክርስቶስ ሰው መሆን የመጨረሻው ክፍል | አምስቱ አዕማደ ምስጢራት |
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/ZwEn8GvaEgM
https://youtu.be/ZwEn8GvaEgM
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱን የሰጠውን የመኖሪያ ቤት ውል አቋረጠ ቤቱንም አሸገ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ከጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠ ትዕዛዝ የተሰጣቸውን ከድርጅቱ የተሰጣቸውን መኖሪያ ቤት ውል በማቋረጥ ቤቱን ተረክቧል።
ድርጅቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ሕገ ወጥ መንገድ የቤተክርስቲያናችንን ቀኖናና ሕግጋት በመጣስ በትላንትናው እለት የተሰጠውን ሕገ ወጥ ሹመት ተከትሎ ዋነኛ አስተባባሪና ተሿሚ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ ነው።
ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#አስቸኳይ_የቅዱስ_ሲኖዶስ_ምልዐተ_ጉባኤ_ተጠራ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በአገር ውስጥ እና በውጪ አገር ያሉ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ከነገ ጀምሮ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንዲመጡ አሳስቧል።
መንግሥትም በተፈጠረው ችግር አስፈላጊውን ጥበቃ እንያደርግ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን እንዲረጋጉ መልእክት አስተላልፏል።
🎬 🛑 ምስጢረ ሥጋዌ የክርስቶስ ሰው መሆን | አምስቱ አዕማደ ምስጢራት | ክፍል አንድ!
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/GhPT-R0G4D0
https://youtu.be/GhPT-R0G4D0
👉ጥምቀት_ምንድን_ነው?
ተወዳጆች የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ነገረ ጥምቀቱን እንዲህ መናገር እንጀምራለን
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
✅ ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል።
✅ ጥምቀት “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ፍቺውም በገቢር መንከር፣ መድፈቅ፣ መዘፈቅ፣ በተገብሮ መነከር፣ መደፈቅ፣ መዘፈቅ፣ መላ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው።
✅ በሌላ አገላለጽ ጥምቀት ማለት በተጸለየበት ወይም በተለየና በከበረ ውኃ (ማየ ገቦ ወይም ማየ ሕይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር መጥለቅ፣ መዘፈቅ፣ መነከር ማለት ነው። በመሆኑም የምንጠመቅበት ውኃ ተራ ውኃ አይደለም።
✅ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው።
💎የጥምቀት በዓል ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው
💎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓተ አክብሮት መሠረት በየዓመቱ ከጥር አሥር እስከ አሥራ አንድ ቀን በደማቅ ሥነ ሥርዓት በካህናት፣ በምዕመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አገልግሎት ይከበራል።
💎 በዓሉ የሚከበረው ጌታ በዕደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ምሥጢረ ጥምቀትና ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተበት ዕለት በመሆኑ ነው። ጌታ የተጠመቀው በተወለደ በሠላሳኛው ዓመት ሲሆን ያ ወራት ዮሐንስ መጥምቁ ሕዝቡን እየሰበሰበ የንስሐ ጥምቀት የሚያጠምቅበት ጊዜ ነበር:: 📗ማቴ. 3:1📗
ታሪካዊ የጥምቀት በዓል አከባበር በኢትዮጲያ
💧ታላቁ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሲነሳ ኢትዮጵያውያን ሩቅ ዘመንን ተሻግረን የቅዱሳን ሰማዕት አባቶችን፣ የሊቃውንት አባቶችን አስተምሮት እናዘክራለን።
💧በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል።
💧በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
💧ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና እንክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል።
💧የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ።
💧ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ።
💧ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት timqet celebration በዐዋጅ አስነግረው ነበር።
💧ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ካወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።
💧ኢትዮጵያ ዜና ጥምቀተ ክርስቶስን ከሰማችበት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በተለይም ከአጤ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (6ኛው መ/ክ/ዘ) ወዲህ የጥምቀትን በዓል ዛሬ በሚታየው አኳኋን ስታከበር እንደ ቆየች ይታመናል።
💧በክብረ በዓሉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት ታቦታት በካህናቱ ሃሌታ፣ በምእመናኑ እልልታ እና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ በተቋቋሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙሮች ታጅበው በተመሳሳይ አኳኋን እንደሚመለሱ ይታወቃል።
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።
መዝሙረ ዳዊት ፻፶፥፮
💎ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል። የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል። የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።
💎ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው።
✅ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው።
✅እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው።
✅ኢያሱ የጌታ፣
✅እስራኤል የምእመናን፣
✅ዮርዳኖስ የጥምቀት፣
✅ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው።
✅ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣
✅ታቦቱ የጌታችን፣
✅ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣
✅ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው።
✅ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል።
✅‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው።
👉ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ።››።
💎ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው። ከወንዝ ዳር ያለ መጠለ
ያ መዋልና ማደር አይቻልም። በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር። በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ።
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በላስታ የላሊበላ መዋኛን፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። እኒህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ።
💎እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
ምንጭ ፦ ሥርዓተ ተዋህዶ ርትዕት
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
#በጎል_በጎል
በጎል በጎል ሰብአ ሰገል /4/
በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱለት /4/
ፀሐይ /2/ ፀሐይ ሰረቀ /2/
ፀሐይ ሰረቀ ክርስቶስ ተጠምቀ /4/
#አዝ
አንቺ ዮርዳኖስ ምንኛ ታደልሽ /2/
የእግዚአብሔር መንፈስ ከላይ ወርዶብሽ
የዓለም መድኃኒት ተጠመቀብሽ /2/
#አዝ
ድንግል ማርያም ንፅህት ቅድስት /2/
የጌታዬ እናት ምስጋና ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ አንቺን መርጦሻል /2/
#አዝ
አዲስ ሙሽራ ሲመጣ እያያችሁ/2/
የዮርዳኖስ ወንዞች ስለምን ሸሻችሁ/2/
#አዝ
እናንት ተራሮች እግር ሳይኖራቹ/2/
እንዴት እንደ ጊደር ሽቅብ ዘለላችሁ/2/
#አዝ
ድንግል ማርያም ያስገኘሽው ፍሬ/2/
ሕዝቦቹን ለማዳን ተወለደ ዛሬ
ሕዝቦቹን ለማዳን ተጠመቀ ዛሬ /2/
#አዝ
እልል እልል ደስ ይበለን /2/
ወልድ ተወልዶ ነጻ ወጣን
ዮሐንስ አጥምቆ ድል አገኘን /2/
ዜማው በዚሁ ነው የሚወርደው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👉 "የምወደው ልጄ ይህ ነው!"
✍ ጸሐፊ:- ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
🎤 አንባቢ:- ብንያም ብርሃኑ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️