ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የማስታወቂያ ሰዓት

መጥተናል! ተመልሰናል!
በዓልዎን በማድመቅ የሚታወቀው ካባ እነሆ በብርሃነ ልደቱንና ጥምቀቱ የማይረሳ ጊዜን እንዲያሳልፉ ስራዎቹን እንካቹ ይላል።

በቡድን ለሚመጡና ብዛት ለሚያዙ እስከ 20% ቅናሽ እንዲሁም አጓጊ የሆኑ ሽልማቶችን ይዞ ይጠብቅዎታል።

እኛን ለማግኘት
📞 +251965875219
📞 +251922501999
አዲስአበባ ፡ ኢትዮጵያ

የቴሌግራም አድራሻችን
@KABAPrint
@KABAPrint

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኅዳር ፯ /7/


በዚች ቀን የእስክንድርያ አገር የሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ።

የዚህም ቅዱስ አባቱ ልጅም አልነበረውም የልዳዊው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ኅዳር ሰባት በደረሰ ጊዜ ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድለት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመነው ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ልጅ ሰጠው ስሙንም በታላቁ ሰማዕት ስም ጊዮርጊስ ብሎ ስም አወጣለት።

የዚህም ልጅ እናትና አባቱ አረፉ እርሱም ከእናቱ ወንድም ዘንድ ተቀመጠ ሃያ አምስት ዓመትም በሆነው ጊዜ በጎ ሥራ የሚሠራ ሆነ ድኆችን እጅግ ይረዳቸው ይወዳቸውም ነበረ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መገሥገሥንም ይወዳል። ለመኰንን አርማንዮስም ሴት ልጅ አለችው ቦታዎችንም በመጐብኘት ደስ ይላት ዘንድ ከባልንጀሮቿ ጋር ወጣች ወደ ደብረ ቊስቋምም ስትደርስ ጣዕም ባለው ድምጽ በመዘመር ሲያመሰግኑ የተሰበሰቡ መነኰሳትን አገኘቻቸው ምስጋናቸውና መዝሙራቸውም ወደ ልቡዋ ገብቶ ተቀረጸ።

ጊዮርጊስንም መነኰሳቱ ስለሚዘምሩት ያስረዳት ዘንድ ጠየቀችው እርሱም ወደማይጠፋ ዕረፍትና ተድላ እንደሚያደርሳቸው ነገራት ወደ አባቷም በተመለሰች ጊዜ በፊቱ ቁማ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነች አባቷም ሊሸነግላት ጀመረ ልጄ ሆይ ይህን አታድርጊ አላት ነገሩን ባልተቀበለች ጊዜ ራሷን በሰይፍ አስቆረጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች ከዚህም በኋላ ልጅህን ያሳታት ጊዮርጊስ ነው ብለው ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ጭካኔውንም አይቶ ወደ ሀገረ እንጽና ሰደደው በዚያም የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ  ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​የምንኩስና ሕይወት አጀማመርና ዕድገት

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድሆች ስጥና ተከተለኝ» «ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ካጣ ምን ይጠቅመዋል?» ብሎ የተናገራቸውን ቃል እንደ እቃ ጦር ታጥቀው የዚህን ዓለም ኃላፊነትና ጠፊነት በሚገባ ተረድተው አእምሯቸውን ጥበብ መንፈሳዊ ማለትም ይህንን ዓለም በመናቅ አበልጽገው የኖሩ የሚኖሩ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ሃይማኖትና ምግባር እንደ ነፍስና ሥጋ የተዋሐደላቸው እግዚአብሔር የሚወደውን ብቻ የሚወዱ እርሱ ባዘጋጀላቸው መንገድ ተጉዘው ከመርገመ ኃጥአው እና ከፍትወታት እኩያት ታግሰው ያሸነፉና ሕጉንና ትእዛዙን የፈጸሙ ለመፈጸም በቦታ ተወስነው የሚኖሩት መነኮሳት ይባላሉ፡፡

የምንኩስና ሕይወት አጀማመር እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ወፍ ዘራሽ የመጣ ሳይሆን ትንቢት ተነግሮለት ምሳሌ ተመስሎለት የመጣ ነው እንጂ፡፡

የምንኩስና ሕይወት አጀማመር ምሳሌ በሕገ ልቡናና በብሉይ ኪዳን ዘመን

ምንም እንኳን ሕግ ወጥቶለት ሥርዓት ተሠርቶለት የተጀመረው በዘመነ ሐዲስ ቢሆንም በቀድሞ ዘመን በሕገ ልቡና በዘመነ ብሉይ ለምንኩስና ሕይወት ምሳሌ የሚሆኑ ከሴት ርቀው ንጽሕና ጠብቀው በምስጋና ጸንተው በደብር ቅዱስ ሲኖሩ የነበሩት ደቂቀ ሴት፣ ሄኖክ በዚህ ዓለም ልጆችን ከወለደ በኋላ ይህ አናኗር ለመንፈሳዊ ፍላጎቱ አጥጋቢ ሆኖ ስላላገኘው የብሕትውና ኑሮ ጀምሯል፡፡ ዘፍ.5÷24 በተጨማሪም መልከጼዴቅ፤ ኤልያስ፣ መጥምቁ ዮሐንስ። ከሴት ወገን በምንኩስና ሕይወት የምትታወቀው ነብይት ሃና ሉቃስ 2÷36 በአጠቃላይ በሕገ ልቡና ለምንኩስና ሕይወት ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው፡፡

የምንኩስና ሕይወት አጀማመር በሐዲስ ኪዳን

በዘመነ ሐዲስ ለገዳማዊ ሕይወት ለምንኩስናና ለብሕትውና ጀማሪውና መሪው መምህረ ትህትና ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይኸውም እንደተጠመቀ ወዲያው ሳይውል ሳያድር ገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳይቀመጥ ከዘረጋ ሳያጥፍ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ምንም ነገር ሳይቀምስ በተባሕትዎ ቆይቷል። በዚህም ለባሕታውያን ብሕትውናን ባርኮና ቀድሶ ሰጥቶአል፡፡ እንዲሁም በድንግልና በመኖር ለደናግልና ለመነኮሳት አብነትና መምህር ሆኗል።

ጌታችን በሚያስተምርበት ዘመን ካደረበት የሚያድሩ ከዋለበት የሚውሉ ከእርሱ የማይለዩ መቶ ሃያ ቤተሰብ እንዲሁም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ለምንኩስና ሕይወት በዘመነ ሐዲስ ምሳሌ ናቸው፡፡

የሥርዓተ ምንኩስና አጀማመር

ምንኩስና ማለት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም በዓለም ያለውን ማንኛውም ነገር ትቶ በቆብ ቃልኪዳን የገባ የሞተ፣ የተለየ፣ ዓለምን የረሳ፣ ራሱን የጠላ ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ ዓላማና ሕይወት በአንድነት የሚኖሩ «ማኅበረ መነኮሳት» ይባላሉ፡፡ በማኅበር ሲራዱና ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ከሰው ተለይተው ቦታ ወስነው ብቻቸውን የሚኖሩት ባሕታውያን ይባላሉ፡፡ ከአንድነት ገዳም ርቀው በሚገኙ አንዳንድ ጫካዎችና ዋሻዎች እንደ መልከጼዴቅና እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ከሰው ጋራ ሳይገናኙ የሚኖሩ የተለየ አለባበስና አስፈሪ ግርማ ሞገስ ያላቸው ባሕታውያንም አሉ፡፡ እነዚህ ዓይነቱ ባሕታውያን በኅብረተሰቡ አጠራር «ግሑሳን» ይባላሉ፡፡ «ግሑስ» ማለት ከሰው ርቆ የሚኖር ባሕታዊ ማለት ነው፡፡

በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ባሕታዊ ቅዱስ ጳውሊ ሲሆኑ ነገር ግን ሕግና ሥርዓት አውጥተውለት እንዲሰፋ ያደርጉት አባ እንጦንዮስ ናቸው፡፡ አባ ጳኩሚስ፤ መቃርስ፣ ዮሐንስ ሐፂር ተነስተው ለምንኩስና መስፋፋት ከፍተኛውን አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ገሊላ እትዊ

እመቤቴ እሰከ መቼ
በባዕድ ሀገር ትኖርያለሽ /2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሀገርሽ ገሊላ ግቢ/2/

ገሊላ እትዊ/4/ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/

እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ
ስደቱ ይበቃሻል    ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቷልብሎ ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነግሮሻል ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰርገላ     ገሊላ እትዊ
ዑራኤል ይመራሻል  ገሊላ እትዊ

ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/


የዝናቡን ጌታ   ገሊላ እትዊ
እናቱ ሁነሽ ሳለ  ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰው አድሮ ገሊላ እትዊ
እያስከለከለ  ገሊላ እትዊ
ውሃ ጥም ጸንቶብሽ ገሊላ እትዊ
አፍሽ ደርቆ ዋለ  ገሊላ እትዊ
ይበቃል እናቴ   ገሊላ እትዊ
እረሀብ ጥማትሽ  ገሊላ እትዊ
ሂጅ ወደ ገሊላ  ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመዶችሽ  ገሊላ እትዊ

ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/


የሰማዕታት አክሊል  ገሊላ እትዊ
የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ
ባርከሽ ሰጠሻቸው  ገሊላ እትዊ
መከራን ስድት  ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደለን  ገሊላ እትዊ
የአንቺው በረከት  ገሊላ እትዊ

ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/


ገጽሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ  ገሊላ እትዊ
እግዝእትነ ማርያም ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ  ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ  ገሊላ እትዊ
መከራ ስቃይ ገሊላ እትዊ

ሀገረኪ ገሊላ እትዊ /2/
ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/
          
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሕዳር ፮ /6/


በዚችም ቀን የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ፊልክስ አረፈ።

የዚህም  ቅዱስ  ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው የቤተክርስቲያንንም ትምህርት  አስተማሩት የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አንስጣስ ዮስም ዲቁና ሾመው ደግሞ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ዮስጦስም ጠባዩን የጽድቁንና፤ የትሩፋቱን ደግነት አይቶ ቅስና ሾመው።

ትሩስ ቄሣርም ከሞተ በኋላ ቴዎድሮስ ቄሣር  ነገሠ ። እርሱም በምእመናን ላይ ታላቅ መከራ አምጥቶ ጭንቅ ፣ በሆኑ ሥቃዮች አሠቃያቸው ። ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም አባት ከዚህ ከሀዲ ታላቅ መከራና ኀዘን ደረሰበት።  ወደ እግዚአብሔርም ልመናውን ተቀብሎ ከሀዲውን በሁለተኛ ዘመነ መንግሥቱ አጠፋው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መፅጽሐፈ  ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኢትዮጵያን ማርልኝ

ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለህ ፀልየሃል
ገብረመንፈስ ቅዱስ አምላክን ማልደሃል
ምልጃ በረከትህ በእኛ ስላደረ
ትውልድ በውዳሴ አንተን አከበረ
(2)

አዝ

ፃድቁ አባታችን ምልጃህ ደግፎናል
በበደል እንዳንዝል ፀሎትህ አግዞናል
ገድልህ አስተማረን ለሀገር መማለድን
የሰማዩን ፍኖት የፅድቁን መንገድን
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አበ ትህትና
የፃድቅ አርአያ የመናኝ ዋስትና
(2)
አዝ

ወልደ አቅሌስያ ሲሳየ ስምዖን
ከደጅህ ስንደርስ እንባረካለን
የገዳምህ ፀበል አያልቅም ታዓምሩ
አይተናል ሲድኑ ብዙኃን ሲማሩ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አበ ትህትና
የፃድቅ አርአያ የመናኝ ዋስትና
(2)
አዝ

አማልደህ ሰላምን የምታሰጥ መምህር
በምልጃ ኪዳንህ ኢትዮጵያዊ የምታስምር
ዛሬም በዘመኗ ምልጃህ አይለያት
አፅናት በሃይማኖት በእምነት አቁማት
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አበ ትህትና
የፃድቅ አርአያ የመናኝ ዋስትና
(2)

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቀን አለው እግዚአብሔር

ቀን አለው እግዚአብሔር ምስኪኑን ሊያነሳ
ጊዜ አለው እግዚአብሔር ታናሹን ሊያነሳ
አይችልም አትበሉ እርሱ ከሃሊ ነው
በሰማይ በምድር የለም የሚሳነው

ዓለም ሙሉ አትሆንም ሁሌ ጎዶሎ ናት
ዛሬ ሐዘን ስቃይ ነገ ደስታ ሀሴት
ሁሉ ሲለዋወጥ የማትቀየር
የሚስኪኞች አባት ቸር ነው እግዚአብሔር

አዝ

ተስፋ ለቆረጠ ተስፋ የሚሆነን
አዲስ ቀን ለግሰህ ነገን የምታኖር
ሁሉም አለቀለት አከተመ ሲባል
ታሪክን ሊቀይር አመሻሽ ይደርሳል
አዝ

ሞገስ እየሆነን በባዕድ አገር
አልፈነዋለን በእርሱ ያን ሁሉ ችግር
ያስቻለን ርሃቡን ጥሙን ስቃዩን
የምንዱባን አምላክ ይክበር ይመስገን
አዝ

ምህረት የማያውቀው አማናዊ ተድላ
ብርታትን የሚያድል የድሆች ከለላ
ለጨለመበት ሰው ብሩህ ነው ንጋት
ቸር ነው የሚራራ የተገፋ አባት

ዘማሪት ቅድስት አለማየሁ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በርባን ነኝ

በርባን ነኝ/3/በአንተ መስቀል የዳንኩኝ/2/
በኃጢአት በበደል የኖርኩኝ በክፋት
ወንበዴ ነበርኩኝ የሚገባኝ መሞት
ሁሉንም እረስተህ በፍቅር ያየኸኝ
ንገረኝ አምላኬ እንደምን ወደድከኝ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


ወንበዴው እኔ ነኝ ሀገር ያስቸገርኩኝ
እጆቼን በበደል በደም የታጠብኩኝ
አንተ ግን ራርተህ ተሰጠህ ስለ እኔ
ዋጋ ከፈልክልኝ ክርስቶስ መድህኔ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


ሞቴን ስጠባበቅ እኔ እንደ ስራዬ
ትክክል ነውና የክፋት ዋጋዬ
አንተ ግን ንጹሁ እኔን የወደድከኝ
ለነፍስህ ሳትሳሳ እስከ ሞት ደረስክ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


በዋጋ ገዝተኸኝ ዳግመኛ እንዳልሞት
ብርታት ሁነኝ እና ልለይ ከኃጢአት
መልካምም እንዳስብ መልካም እንድሰራ
በጽድቅ ልመላለስ ልቦናዬን አብራ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


በዋጋ ገዝተኸኝ ዳግመኛ እንዳልሞት
ብርታት ሁነኝ እና ልለይ ከኃጢአት
መልካምም እንዳስብ መልካም እንድሰራ
በጽድቅ ልመላለስ ልቦናዬን አብራ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ


ዘማሪ አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እረኛዬ

እረኛዬ /3/ መተማመኛዬ
ጠባቂ አለኝ ጠባቂ አለኝ
ክርስቶስ መቼም የማይተወኝ

አዝ

ሕይወት በምድር ላይ ብትሆን ከባድ
ወጥመዷን ማምለጫ ጌታ አለህ መንገድ
እጠባበቃለው ተስፋዬን አጥብቄ
ለዓለም አትተወኝም አልቀርም ወድቄ
በእጅህ ተፈጥሬ ክቡር አርገኸኝ
ከቶ ያለ አላማ መቼ መጣሁኝ /2/
አዝ

በእኔ ላይ ሰልጥኖ ኃጢአት ከነቤቱ
መሽቶ ይነጋብኛል ስባዝን በከንቱ
ሰጥተኸኝ ነበረ ጊዜን ለንስሐ
ትንሽ አድርጌ እንጂ ትልቁን አምሐ
ይነቀል ከልቤ የተተበተበው
አንተን ብቻ ልይህ ጠላቴን ጥለኸው /2/
አዝ

የበጎች እረኛ ቸሩ ጌታችን
ያድነዋል ፈጥኖ በእርሱ ያመነውን
መዝጊያን ለሚያንኳኳ ይከፈታል በሩ
እስከሞት ነውና የክርስቶስ ፍቅሩ
ከጉድጓድ ያወጣል ከጥልቁ ዓለም
ቢዘገይም እንኳን ሚቀድመው የለም /2/
አዝ

ከሀገሬ ብሰደድ ጽናቱን አጥቼ
ገባው ተሰሎንቄ መቅደስህን ትቼ
ጌታዬ መልሰኝ እኔ እመለሳለው
ልቤን ካንተ ሌላ ለማን እሰጣለው
ዓይኖቼም ይሞሉ የጸጸትን እንባ
ደግሞም ተመልሼ ወደ እቅፍህ ልግባ
ደግሞም ተመልሼ ወደ ቤትህ ልግባ

ዲ/ን ዘማሪ በኃይሉ ተበጀ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኅዳር ፫ /3/


በዚች ቀን ከቆሮንቶስ አገር ቅዱስ አባት ኪርያቆስ አረፈ። የዚህም አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና የከበሩ ናቸው የቤተክርስቲያንን ትምህርትና የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩት ከዚህም በኋላ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነ ወደ አባ ጴጥሮስ አቀረቡት እርሱም በላዩ ጸልዮ አናጒንስጢስነት ሾመው።

ከዚህም በኋላ ዘወትር መጻሕፍትን የሚያነብ የቃላቸውንም ትርጓሜ የሚመረምር የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓቷንና ሕጓን የሚያጸና ሆነ በትምህርቱና በእውቀቱም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ  መጻሕፍትንም በሚያነብለት ጊዜ ኤጲስቆጶሱ በእርሱ ደስ ይለው ነበርና። ዕድሜውም ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነ ጊዜ ሚስትን ያጩለት ዘንድ ወላጆቹ ጠየቁት እርሱ ግን ይህን አልወደደም ግን ከገዳማት ወዳንዱ ይሔድ ዘንድ እንዲአሰናብቱት ወላጆቹን ለመናቸው የከበረች የምንኲስናን ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ከኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ ከአባ ቄርሎስ ጋር ተገናኝቶ ስለ ምንኲስና ኀሳቡን ሁሉ ነገረው።

እርሱም በጎ ሥራን ወደሃል አለው ታላቅ አባትም እንደሚሆንና በእርሱም የብዙዎች ነፍሳት ብሩሃን እንደሚሆኑ ትንቢት ተናገረለት ። ከዚህም በኋላ የመነኰሳት አባት ወደ ሆነ በፍልስጥዔም ወደ ሚኖር ወደ ክቡር አባ ሮማኖስ ላከው እርሱም በደስታ ተቀብሎ የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። ከዚህም በኋላ በጾም በጸሎት በስግደት በመትጋት በታላቅ ድካም በቀንና በሌሊት በገድል ተጸምዶ በትዕግሥት በትሕትና በቅንነት ኖረ።

እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጥቶት ወደርሱ የሚመጡትን በሽተኞች ሁሉ የሚፈውሳቸው ሆነ:: ከዚህም በኋላ በመልካም ሽምግልና እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​የለቅሶ ቤት ንፍሮ

ከቀብር መልስ እጅህን ታጥበህ ተስተናግደህ ታውቃለህ? ንፍሮስ ቀምሰህ ታውቃለህ? ንፍሮውን ስትበላ እኔ እንደማደርገው ሽንብራ ሽንብራውን ለቅመህ በልተህ ስንዴውን ለሌላ ሰው ትመርቃለህ ወይስ ሁለቱንም ትበላለህ? በሆድህ "ለምንድን ነው ግን ጨዉን የሚያሳንሱት" እያልክ ተመራምረህ ይሆን?

እኔ ደግሞ ዛሬ ከቀብር መልስ ካልጠፋ እህል ስንዴ ለምን እንደሚቀርብ ልነግርህ ነው። ነገሩ ባሕል ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትም ነው። ቀብረን ከተመለስን በኁዋላ ስንዴ ስንበላ የንፍሮውን ጣዕም ማሰላሰል ትተን ይህንን የጌታችን ቃል እናስታውስ :-

''እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች" ዮሐ 12:24

ከቀብር መልስ በንፍሮ መልክ የምንበላው ስንዴ ኀዘንተኞችን የሚያጽናና ትልቅ መልእክት ይዟል። ክርስቶስ ስንዴ የሚያፈራው ሞቶ በምድር ሲቀበር ነው ብሎ ስንዴን ለእኛ ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል። ቀብረህ ስትመለስ በእጅህ የዘገንከው ስንዴ ቀብረኸው የመጣኸው ወንድምህ ትንሣኤ እንዳለው እየነገረ ያጽናናሃል። በምድር የወደቀ ስንዴን ያልረሳ አምላክ የሞተውን አይረሳም።

ቀብረነው መጣን ብለህ አትዘን፤ ዘርተኸው እንደመጣህ አስብ፤ በመዋረድ ብትዘራውም በክብር ይነሣል፤ በድካም ብትዘራውም በኃይል ይነሣል፤ ለመበስበስ ብትዘራውም ባለመበስበስ ይነሣል ይልሃል ሐዋርያው (1ቆሮ 15:42-43)

ነፍሳችን ከሥጋችን በተለየች ጊዜ በምድር አስከሬናችን ይቀራል። አስከሬን (በግሪክ ስክሪኒዉም) ኮሮጆ መያዣ ማኅደር ማለት ነው። "ንዒ ማርያም ለእግዚአብሔር አስከሬኑ" "የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም ሆይ ነይ" እንዲል። የነፍሳችን ማደሪያ የሆነው ሥጋ ከአዳሪዋ ነፍስ ሲለይ አስከሬን (ማደሪያ) የነፍስ ሳጥን የሚል ስም ይሠጠዋል። ሬሳ የሚለው ቃል የበሰበሰ ነገርን ያሳያል።

ምሥራቃውያኑ የቡድሃና ሂንዱ ተከታዮች ሥጋን የነፍስ እስር ቤት አድርገው ስለሚያምኑ ሥጋ ሲቃጠል ነፍስ ነፃ ይወጣል ብለው አስከሬን ያቃጥላሉ። በዳግም ሥጋዌ (reincarnation) የሚያምኑ በመሆናቸውም አንድ ሰው ድጋሚ ሲፈጠር የተሻለ አካል ይዞ እንዲወለድ አሮጌው ሥጋው መቃጠል አለበት ብለው ያስተምራሉ።

እኛ ግን እንቀብራለን እንጂ በፍጹም አስከሬን አናቃጥልም። የሚቀበር ነገር ዋጋ ያለውና በኁዋላ የሚፈለግ ነገር ነው። ገንዘብ የምትቀብረው ሌላ ጊዜ ልታወጣው ካሰብክ ነው። የምታቃጥለው ግን የማትፈልገውን ነው። የምንቀበረው እንደምንወጣ ስለምናምን ነው። የመለከት ድምፅ ሰምተን እንደምንነሣ ተስፋ ስላለን ምንም ብንሞትም በተስፋ እንቀበራለን። እንደምንበቅል ተስፋ አድርገን እንዘራለን። ሌላው ቢቀር በእሳት ተቃጥለን ብንሞት እንኳን አመዱን እና የከሰለውን አጥንትም ቢሆን በተስፋ እንቀብረዋለን።

''የሙታንን መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን!"

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የግዮን ወንዝ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኅዳር ፪/2/


በዚች ቀን ከአባ ጢሞቴዎስ በኋላ የተሾመ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ጴጥሮስ አረፈ።
እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛ ነው ይህንንም ቅዱስ እግዚአብሔር ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መርጦ በሐዋርያ ማርቆስ ወንበር ላይ ከአስቀመጠው በኋላ የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አካክዮስ እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈለት እንደ ቅዱሳን ቄርሎስና ዲዮስቆሮስ ሃይማኖት ልዩ ሦስት በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን እናሳምናለን።

ይህ አባ ጴጥሮስም እንደ ተቀበላት ገልጦ ስለ ቀናች ሃይማኖት ከራሱም ያለውን ጨምሮ ለመልእክቱ መልስ ጽፎ ከሦስት ምሁራን ኤጲስቆጶሳት ጋር ላካት ። አባ አካክዮስም ተቀበላቸው በቅዳሴና በቊርባንም አንድ ሆኑ ያቺንም መልእክት በቃሉ በሚያምኑ ሕዝብ ፊት አነበባት።

ከዚህም በኋላ ሌላ መልእክትን ጻፈ በውስጧም ከቅዱሳት መጻሕፍት ብዙ ቃላትን ተርጒሞ ወደ አባ ጴጥሮስ ላካት ። ይህም አባ ጴጥሮስ ኤጲስቆጶሳቱን ሰብስቦ ያቺን መልእክት በፊታቸው አነበባት እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው ከቃሏና ከትርጓሜዋም የተነሣ አደነቁ በቀናች ሃይማኖትም ከእርሳቸው ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑን ተማመኑ ።

ይህንን አባት አባ ጴጥሮስንም ከሀድያን ከሆኑ አይሁድ ከአረማውያንም ከመንበረ ሹመቱ እስኪያሳድዱት ድረስ ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ደረሰበት ።
ከጥቂት ወራትም በኋላ ወደ ሹመቱ ወንበር ተመለሰ መንጋውንም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበር ከእነርሱም ርቆ በስደት በነበረበት ጊዜ ከመናፍቃን እንዲጠበቁና በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መልእክቶችን ጽፎ ይልክ ነበር በሹመቱ ወንበርም ዐሥር ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የማስታወቂያ ሰዓት

መጥተናል! ተመልሰናል!
በዓልዎን በማድመቅ የሚታወቀው #ካባ እነሆ በብርሃነ ልደቱንና ጥምቀቱ የማይረሳ ጊዜን እንዲያሳልፉ ስራዎቹን እንካቹ ይላል።

በቡድን ለሚመጡና ብዛት ለሚያዙ እስከ 20% #ቅናሽ እንዲሁም አጓጊ የሆኑ #ሽልማቶችን ይዞ ይጠብቅዎታል።

ይደውሉ።
+251965875219
+251922501999
አዲስአበባ ፡ ኢትዮጵያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለልደትሽ ምስጋና ይገባል

ለልደትሽ ምስጋና ይገባል
ለዓለም መዳን ምክንያት ተወልደሻል
ልደትሽም ለእኛ ልደት ነው
ባንቺ እኮ ነው ፀሐይ ያገኘነው /2/

በሊባኖስ ሰማን አዲስ ዜና
ንጽሕት ዘር ተወልዳለችና
የዓለም ስቃይ ሰቆቃ ሊያበቃ
ተወለደች እንደ ፀሐይ ደምቃ

አዝ

ለዚህ ክብር ይገባል እልልታ
በልደትሽ አይሆንም ዝምታ
የአንቺ ልደት ለዓለም ደስታ ነው
አንቺ ምሥራቅ ልጅሽም ፀሐይ ነው
አዝ

ብርሃን ሆነ በሊባኖስ ዛሬ
በልደትሽ በመላእክት ዝማሬ
አይቋረጥ ምስጋና ከአፋችን
በሊባኖስ ይሰማ ዜማችን
አዝ

ስለክብርሽ ክብር አለን እኛ
ከሊባኖስ ነይልን ወደ እኛ
በአብ ኅሊና ቀድሞውን የታሰብሽ
ትውልድ ሁሉ ብጽዕት የሚልሽ

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እረኛዬ ነህ

እረኛዬ ነህ እረኛዬ ነህ የነፍሴ ቤዛዋ
የቆሰልክላት አንተ የሞትህላት ባለውለታዋ/2/

አዝ

ልሰማራ ልውጣ እንጂ ተማምኜ
አንተ ካለህ ታዳጊዬና አዳኜ
የአለም ሰልፏ ብዙ ነው በፍራቻ
የኔ ሞገስ አጀቤ አንተ ብቻ
አዝ

በቁጣ ቀን ቤቴ በእሳት ሲታጠር
አንተ ባትኖር እኔም የለሁም ነበር
የማያልፈው አለፈ በሕይወቴ
ጋርደህልኝ ከልለኸኝ አባቴ
አዝ

እንዳልደክም እንዳልሞት በመንፈሴ
ከቶ አትስጠኝ አሳልፈህ ለራሴ
ከፍ ያልክ ነህ ከፍ ያልከው በምስጋና
ሁሌም አዲስ ጉልበት የምታጸና
አዝ

ጎደለልኝ የመከራ ሙላቱ
በአንተ ታዞ በጊዜው በሰአቱ
የሳኦል ጦር አለፈ በራሴ ላይ
እንደዘበት ከሞት ጋ ሳልገናኝ

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በመጀመሪያ ለሥላሴ

በመጀመሪያ ለእርሱ ለሥላሴ
ምስጋና ታቀርባለች ማልዳ ነፍሴ
ስለፈጠረኝ እኔን ሰው አድርጎ
ስለፈጠረኝ የእርሱ አምሳል አድርጎ

አዝ

ተጎበኘሁኝ እኔ ለምስጋና
ጌታዬ እኔን አክብሮኛል እና
ሲነጋ ቀኑን በእርሱ እጀምራለሁ
ሲመሽ የአፌን ምስጋና አቀርባለሁ
አዝ

ነፍሴን መገባት ቃሉን ልኮ ለእኔ
ያጣሁት የለም ከእርሱ በዘመኔ
ስሙን እጠራለሁ በአንድም ሦስትነቱ
ስላልተለየኝ ጌታ ቸርነቱ
አዝ

ሥሉስ ቅዱስ ነው ስሙ የአምላኬ
እሰዋለታለሁ ቅኔ ተንበርክኬ
ሥላሴ ስለው ነፍሴን ደስ ይላታል
ከዓለም መከራ እርሱ ፈውሷታል
አዝ

አንድ ነው ስንል ሦስትነቱም አለ
ሦስት ነው ስንል አንድነቱም አለ
ልዩ ሦስትነት ልዩ አንድነት
አኗኗሩ ድንቅ ነው በእውነት

ዘማሪ ጎሳዬ ገላና
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኃይልህ ሲገለጥ በሰማይ

ኃይልህ ሲገለጥ በሰማይ/2/
አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ
ማን ይቆም ይሆን/2/
ከፊትህ ማን ይቆም ይሆን

አቤት ቀንደ መለከት ሲነፋ
አዋጅ ሲታወጅ በይፋ
ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ
ምን ይሆን የእኛ ተስፋ

አዝ

አቤት መላእክት ሰማዩን ሲያርሱት
ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት
ያልታየና ያልተሰማ
ድምጽ ሲሰማ ከራማ
አዝ

አቤት ሰባቱ ነፋስ ተከፍተው
ምድርን ሲያውኳት ቀዝፈው
ሲታዘዝ የባሕር ሞገድ
ምድሪቷን ሊከድናት ለፍርድ
አዝ

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሰሩ ቡሩካን
በምድር የሰሩ ትሩፋት
ሲያቀርቡ ለአምላክ ስብሐት
አዝ

አቤት ኃጥአን ግን ለፍርድ ሲጠሩ
በጨለማ ዓለም ሊቀሩ
የማይጠቅም ዋይታ ሆኖ
መዋረድ ይሆናል አዝኖ
አዝ

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሰሩ ቡሩካን
በምድር የሰሩ ትሩፋት
ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ኅዳር 6

በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው።

ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹን ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው "ያቺ የተባረከች ሀገር ናት" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!! ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰጣት። በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ተዓምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን!! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !!

ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡

ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልዑል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ!

«ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ... ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩ የተዋህዶ ልጆች እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ነይ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት

ነይ አርሴማ ቅድስት ነይ አርሴማ
ነይ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት

አዝ

አርሴማ አርሴማ ነይ አርሴማ
አርሴማ ስልሽ ነይ አርሴማ
እንድታማልጅኝ ነይ አርሴማ
ከአምላክ ፈጣሪሽ ነይ አርሴማ
በደሌን ጭንቀቴን ነይ አርሴማ
ልናዘዝልሽ ነይ አርሴማ
ምሪኝ አርሴማ ሆይ ነይ አርሴማ
እጆቼን ይዘሽ ነይ አርሴማ
ወልድያ ሲሪንቃ ነይ አርሴማ
ልምጣ ከደጅሽ ነይ አርሴማ
አዝ

እንድታማልጅኝ ነይ አርሴማ
ከንጉስ ራማ ነይ አርሴማ
ትለምንሻለች ነይ አርሴማ
ነፍሴ ደጅሽ ቆማ ነይ አርሴማ
ወልድያ ሲሪንቃ ነይ አርሴማ
ሄዶ ያየሽማ ነይ አርሴማ
ቅዱሱን ዝናሽን ነይ አርሴማ
ገድልሽን የሰማ ነይ አርሴማ
ጸበልሽ ፈውስ ነው ነይ አርሴማ
እናቴ አርሴማ ነይ አርሴማ
አዝ

በጉብዝና ወራት ነይ አርሴማ
ፈጣሪህን አስብ ነይ አርሴማ
ብሎ እንዳስተማረን ነይ አርሴማ
በመጽሐፈ መክብብ ነይ አርሴማ
ስለ ጌታ ኢየሱስ ነይ አርሴማ
ስለ ዓለም መድኃኒት ነይ አርሴማ
ስለ ተዋህዶ ነይ አርሴማ
ስለ ፀናች እምነት ነይ አርሴማ
መከራን ተቀበልሽ ነይ አርሴማ
በጉብዝናሽ ወራት ነይ አርሴማ

ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኅዳር ፭ /5/


በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን የወጋ የቅዱስ ለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ነው።

ይህም ቅዱስ በጌታችን ከአመነ በኋላ በቀጰዶቅያ አገር ወንጌልን የሚሰብክ ሆነ ከሀድያን አይሁድም በላዩ ተነሡበት በመኳንንት ዘንድ በሐሰት ወንጅለው በቀጰዶቅያ አገር ራሱን አስቆረጡት ራሱንም ብቻውን ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱዋት። በኢየሩሳሌም የሚኖሩም አይሁድ በአዩዋት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሩዋት።

በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች አንዲት ሴት በቀጰዶቅያ አገር ነበረች ራሱን ከቆረጡበት ጊዜ ጀምራ በተቆረጠበት ቦታ በመቆም ስለርሱ ታለቅስ ነበር የዚያች ሴት ዐይኖቿ ታወሩ። ምናልባት ዐይኖቿ ቢገለጡላት በማሰብ ከከበሩ ቦታዎችና ክብር ይግባውና ከጌታችን መቃብር ለመባረክና ለመለመን ተነሥታ ልጅዋን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች። ኢየሩሳሌምም በደረሰች ጊዜ በዚያ ልጅዋ ሞተ ኀዘንም ተጨመረባት ስለዚህም የመረረ ልቅሶን አለቀሰች ከኀዘኗም ብዛት የተነሣ ተኛች።

ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞተው ልጅዋ ጋር በሕልሟ አየችው። ዕገሌ ከሚባልም ቦታ ሒደሽ ራሴን ከዚያ ውሰጂ አላት። ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ስለዚያ ቦታ ጠየቀች ሰዎችም ወደርሱ አደረሱዋት። ያንንም ቦታ በቆፈረች ጊዜ መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ ወጣ። ራሱ ወደአለችበትም ስትደርስ ታላቅ ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿም በዚያን ጊዜ ተገለጡላት እግዚአብሔርንም አመሰገነች ከልጅዋ ሥጋ ጋር የቅዱስ ለንጊኖስን ራስ ወደ አገርዋ ወሰደቻት በታላቅ ክብርም በአማረ ቦታ አኖረቻት።

በረከቱ ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ዛሬ ነገ ነው!

“አባዬ ዛሬ ነገ ነው?” አለ አቡሽ አባቱን ከተኛበት እየቀሰቀሰ አባት እየተበሳጨ “ምንድን ነው የምትለኝ? አለ፡፡ ዛሬ ነገ ነው ወይ? አባት እንቅልፉ ስላልቀቀው “ሂድና እናትህን ጠይቃት በቃ ልተኛበት አለና እየተበሳጨ ፊቱን ሸፈነ፡፡

ልጅ ወደ እናት ሔዶ ያንኑ ጥያቄ ደገመላት"እማዬ ዛሬ ነገ ነው" እናት አለች

“ምን ማለት ነው ደግሞ ዛሬ ነገ ነው? ማለት?” አለች የልጅዋን የተጋለጠ ደረት እየሸፈነች “ትናንት አስተማሪያችን “ነገ ትምህርት የለም” ብላን ነበር ፤ ዛሬ ነገ ነው? እናት እ እ አዎ ልክ ነህ ዛሬ ነገ ነው” አለች እየሳቀች፡፡

ብዙዎቻችን የምንኖረው ለነገ ነው፡፡ ለነገ እንማራለን ፣ ለነገ እንሠራለን ፣ ይህ ለሕጸኑ ጥያቄ የተሰጠ መልስ ለእኛም ሳያስፈልገን አይቀርም። ለነገ እንገነባለን፡፡ የተፈጠርነው ለዘላለማዊነት ነውና እንደምንኖር አስበን ማቀዳችን ባልከፋ፡፡ ነገር ግን ላላየነው ነገ ስናስብ ያየናትን ዛሬ እንዘነጋታለን፡፡ ለነገ ደመና የዛሬን ፀሐይ እንገፋታለን፡፡ እንዳቀድን እንዳለምን ለመኖር ስንዘጋጅ እንሞታለን፡፡ መጽሐፍ “ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና, “ነገ ለራሱ ያስባልና ለነገ አትጨነቁ! ይላል፡፡ /ያዕ 4፡15 ፤ ማቴ 6፡34/

ሰይጣን ከሚጠቀምበት ሰውን ማጥቂያ መሣሪያም አንዱ “ነገ በሚል ቃል ማዘናጋት ነው፡፡ ነገ እማራለሁ ፣ ነገ እሔዳለሁ ፣ ነገ የታመመ እጠይቃለሁ ፣ ነገ ንስሓ እገባለሁ ፣ ነገ ወደ እግዚአብሔር እመለሳለሁ ፣ ነገ ይሄንን መልካም ነገር እሠራለሁ ነገ ነገ ነገ ፈርኦን የሚባለው ጨካኝ ንጉሥ በመቅሠፍት ጓጉንቸር ተወርሮ ነበር፡፡ በመጨረሻም እስራኤልን እለቃለሁ ሲል ሙሴ ፦ ጓጉንቸሮቹ ከቤትህ እንዲጠፉ መቼ ልጸልይልህ? አለው፡፡

ፈርኦንም ፦ ነገ አለ፡፡ እንግዲህ ዛሬን ከጓጉንቸሮች ጋር ማደር ፈልጓል ማለት ነው፡፡ ወዳጄ በሕይወትህ ውስጥ ጓጉንቸሮች ምንድን ናቸው? ምን ዓይነት ክፉ አመል አለብህ ፣ ምን ዕረፍት ያሳጣህ ፣ ሰላም የነሳህ ነገር አለ? አልላቀቅ ያለህ ሱስ ፣ አልስተካከል ያለህ ድክመት ፣ አልድን ያለህ ቁስል ምንድን ነው? እርሱን መቼ ትላቀቀዋለህ? መቼ መዳን ትሻለህ? ነገ ካልከኝ ፈርኦን መሆንህ ነው? 'አቤቱ እሁን አድን' ካልክ ደግሞ እንደ ዳዊት ትሰማለህ።

ነገ ይህንን ሱስ እተዋለሁ : ነገ ይህን ልማድ እላቀቃለሁ : ነገ ይህን መልካም ነገር አደርጋለሁ የሚል ቀጠሮ ሠርቶ አያውቅም፡፡ ነገ እንላለን እንጂ የሚገርመው በማግሥቱም መልሳችን ነገ ነው፡፡ 'ዱቤ ዛሬ የለም ነገ ነው እንደሚለው የብልጥ ባለሱቅ ማስታወቂያ ነገ ስንሔድ ነገ እየተባለ የምንፈልገውን ሳንሠራ የማንፈልገውን እየሠራን እንኖራለን፡፡ ወዳጄ ነገ የአንተ አይደለችም “የተወደደው ሰዓት አሁን ነው, መኖርህን ሳታውቅ ቀጠሮ አትሥጥ፡፡ ኃይልህ በአሁን ላይ ብቻ ነው፡፡ ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ አሁንን ተጠቀምባት፡፡

አሁኑኑ ተነሥ ያሰብከውን መልካም ነገር ለመሥራት ፣ ክፉውን ነገር ለመተው አደርገዋለሁ ትናንት ኅሊናህ ሲጠይቅህ “ነገ አደርገዋለሁ” ብለህ ነበር ፤ ዛሬም ነገ አትበል ምክንያቱም ሕጻኑ እንዳለው “ዛሬ ነገ ነው”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የኤፍራጠስ ወንዝ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኅዳር ፬ /4/


በዚችም ቀን የደማስቆ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቶማስ በግብጽና በሶርያ እስላሞች በነገሡ ጊዜ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህንንም ቅዱስ ቶማስ ከመምህራኖቻቸው ውስጥ አንድ እስላም በተከራከረው ጊዜ ቅዱስ ቶማስ በረታበት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ አምላክ እንደሆነ በማስረዳት አይሎ ረታው።

ያም እስላም በአፈረ ጊዜ ወደ መኰንናቸው ሒዶ ይህ ክርስቲያናዊ ቶማስ ሃይማኖታችንን ረገመ ብሎ ወነጀለው። መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ በውኑ ሃይማኖታችንን ትረግማለህን አለው፤ ቅዱሱም መርገምስ ከአፌ አልወጣም ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ከእርሱም ሕግ በኋላ ሌላ ሕግ እንደማይመጣ አጽንቼ አስረዳሁት እንጂ ብሎ መለሰለት።

መኰንኑም የእኛስ ሕግ ከእግዚአብሔር ነውን ወይስ አይደለም አለው፤ ቅዱሱም ከእግዚአብሔር አይደለም አለው። በዚያንም ጊዜ መኰንኑ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘና ቅድስት ራሱን ቆረጡት። በመንግሥተ ሰማያትም የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሁሉን ተውኩት እናቴ

ሁሉን ተውኩት እናቴ ሁሉን ለአንቺ
መገፋቴን መውደቄን ተመልከቺ
ልመናዬን ድንግል ሆይ ሳትሰለቺ(2)

አዝ

ቢሆንም ባይሆንም ቢሞላ ባይሞላም
ለዚህች ከንቱ ዓለም እኔ አልጨነቅም
ሁሉን ትቼዋለሁ ከእግሮችሽ በታች
ደካማዋን ልጅሽ ድንግል ተመልከች
አዝ

መልካም ያልኩት ጓዴ ክፉ ሲሆንብኝ
አይቻለሁ በአይኔ ፊቱን ሲያዞርብኝ
የተወጋው ልቤ በአንቺ እንዲፈወስ
በመድኃኒት ልጅሽ ሁሌ ይዳሰስ
አዝ

ጎጆዬን አትርሻት ደሳሳዋን ቤቴን
ዘይት የሌለውን ባዶ ማድጋዬን
አንቺ ከለመንሺው ልጅሽ ያዝንልኛል
ጎዶሎዬን ሞልቶ ፀጋን ያለብሰኛል
አዝ

የዋህ እሩሩህ ነሽ አዛኝ ለፍጥረት
ትችይበታለሽ መስጠት ለሕይወት
የልቤን ፍላጎት ሳልነግርሽ ታውቂያለሽ
እንዳትዘገይ አዛኚቱ ስልሽ

ዘማሪት ትርሃስ ገ/እግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከቶ ምን ይረባል

ከቶ ምን ይረባል ጭካኔን ማብዛት
ፈጥኖ ለሚጠፋው ለዚህ ዓለም ቤት
በቋንቋ በጎሳ መከፋፈል ሞት ነው
የእንጨት ዘር አይቀርም እንኳን ሰው እና ሰው (2)

በጎሳ ሰልጥነው ድንበር የሚያበጁ
በታሪክ አይተናል ለማንም አልበጁ
ያደለው ወገኔ ገነትን በምድር
ሁሉን አጨለምከው ተከፋፍለህ በዘር

አዝ

ወፎች ይበራሉ አህጉር አቋርጠው
ክረምት እና በጋ ጊዜውን ጠብቀው
የሰው ልጅ ብቻ ነው ድንበር የከለለው
ከእንስሳት አንሶ የሚተላለቀው
አዝ

እምቢ በል ወገኔ እንደ አባቶቻችን
አትስማ በፍፁም ዘረኛው ሰይጣንን
በሰውነት ሚዛን ከብረህ እንድትገኝ
በጎሳ በዘመድ በጥቅም አትዳኝ
አዝ

ሁሉም ወገንህ ነው የአዳም ልጅ ነው እና
ስልጡንሁን በፍቅር በቀናው ጎዳና
የክፉዎች ስብከት ሞት ነው መጨረሻው
ለጊዜው ቢመስልህ ሐዘን ነው ፍፃሜው
አዝ

ሃይማኖት ተንቃ ተንገዋላ ከአገር
ሊጠፋ ተቃርቧል ክቡሩ የሰው ዘር
ማፍለስ እና ማፍረስ ህዝብን ማጎሳቆል
ግፍ እና ጭካኔ የዘመኑ ብሂል

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እኔስ ተስፋ አልቆርጥም

እኔስ ተስፋ አልቆርጥም ሁሌ እጠራሻለሁ(2)
አማላጄ አንቺን ይዣለሁ
አዛኚቱ አንቺን ይዣለሁ

አዝ

ዙሪያዬ ሲጨልም ብርሃን ሆንሺኝ
ወዳጅም ሲከዳ አለሁ አልሺኝ(2)
ሕይወቴን ከጥልቁ ማን መለሰው
ቀና ቀና ያልኩት በምልጃሽ ነው(2)
አዝ

ሰናክሬም ሲፎክር ከቶ አልፈራም
እናት አለኝ እና የምትራራ (2)
በረከት አገኘሁ ፍፁም ሰላም
ፍቅርሽ ስላገዘኝ ድንግል ማርያም (2)
አዝ

አትውጣ አክዓብ ተው አትድከም
ድንግልን ይዣለሁ አልረታም (2)
በቃለ ማህሌት ተስፋ አድርጌ
ክብሬም ተቀየረ ማዕረጌ (2)
አዝ

ሰሎሞን ላይፈታው የእኔን ችግር
መጣሁኝ ከደጅሽ ላንቺው ልናገር (2)
ዘወትር የማዜመው ስለ ክብርሽ
መልስ ሆነሽኝ ነው በኪዳንሽ(2)

ዘማሪት ትርሃስ ገ/እግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አላማርርም በሆነው

አላማርርም በሆነው (2)
ማግኘትም ማጣት ከአንተ ነው
አምላኬ ስራህ ድንቅ ነው
ጌታዬ ስራህ ድንቅ ነው

አዝ

ትላንት ዛሬ ላይ ሆኜ
አለፍኩኝ በአንተ ታምኜ
ይህቺም ቀን ስታልፍ አያለሁ
ባታልፍም እንዲህ እላለሁ
ተመስገን
አዝ

ጉዞዬ መልካም ባይሆንም
ኮረብታ ቢበዛበትም
አንድ ነገር ብቻ አምናለሁ
ከአንተ ጋር ሁሉን አልፋለሁ
ተመስገን
አዝ

ይህቺ ዓለም ተደላድላለች
ከሌለው ሰላም እና እረፍት
መኖሩ መኖር አይደለም
ኧረ እኔስ አላማርርም
ተመስገን
አዝ

ወዳጆቼ ቢከፉብኝ
ልፋቴ ባይታይልኝ
አንተ ያልከው ሁሉ ይሆናል
ከአንተ ጋር ብራብ ይሻላል
ተመስገን

ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
መምህር ኸይሩ አለማየሁ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጽርሐ አርያም

ጽርሐ አርያም ጽርሐ አርያም /2/
ክብርሽ ገናና ነው ለዘለዓለም

በመላዕክት ዓለም በሶስቱ ከተማ
በኤረር በኢዮር እንዲሁም በራማ
ውዳሴ ቀረበ ለሰማይ ንግስት
የአምላክን እናት በክብር አየናት

አዝ

በበርሃ ያሉ ዓለምን የናቁ
ውዳሴሽን ደግመው ስምሽን የሰነቁ
አንቺን ስንጠራ ጠላት ገለል ይላል
ማርያም በግርማሽ ከሳሻችን ያፍራል
አዝ

ከእግሮቿ በታች ጨረቃን ተጫምታ
የክብርን አክሊል በራሶቿ ደፍታ
በቅዱሳን ሁሉ ትመሰገናለች
ዓለም የዳነባት ድንግል ማርያም ነች
አዝ

ብርሃንን ለብሳ በንጽህና አጊጣ
ፍጥረትን ስትባርክ በክብር ተገልጣ
ነፍሳት ተቀደሱ በእምነት ከበዋት
ከበሮን አንስተን እንዘምርላት

ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሕዳር ፩ /1/


በዚች ቀን ከአፍራቅያ የሆኑ ቅዱሳን መክሲሞስ፣ ማንፍዮስ፣ ፊቅጦር እና ፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን በሰማዕትነት አረፉ።

እሊህም ቅዱሳን መስተጋድላን ንጉሡ ክርስቶስን ክዶ ክርስቲያኖችን ሲያሠቃይ በአዩት ጊዜ ሃይማኖታቸውን ግልጥ  ያደርጉ ዘንድ በአንድ ምክር ተስማምተው በአንድነት ተሰብስበው ወደ ከሀዲው ንጉሥ ቀረቡ።

ይህ ከሀዲ ዳኬዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገርፉአቸው፣ በእሳት በአጋሉትም ከብረት በተሠሩ በትሮች እንዲደበድቧቸው፣ከዚያም በበርኖስ እላቂ ጨርቅ ከመጻጻና ከጨው ነክረው ቍስላቸውን እንዲያሹአቸው ጽኑዕ ሥቃይን እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ከዚያ የነበሩ ብዙ ሕዝብም ትዕግሥታቸውን በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፴ /30/


በዚችም ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እራስ
የታየበት ነው።

ሔሮድስ ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው። እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት። አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ። የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል።

ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት።

ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት። በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች። ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጸድቅ ጸሎት ይማረን  በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር /ዝክረ ቅዱሳን/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал