ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
09 ноября 2024 04:07
ኑ በብርሃኑ
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ/2/
የፍቅርን ህይወት እንድትለብሱ
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ
ሁሉን በሚችል በአምላክ ጥላ
በእረፍት ውኃ ስር አርፈናልና
ሰላምና ፍቅር ሕይወት በሚሰጥ
ወደ ጌታችን እንሂድ እንሩጥ
አዝ
ምህረትና ፍርድ በእጁ የያዘው
የሰላም አባት መድኃኒዓለም ነው
ሕይወት የሆነን በመስቀል ውሎ
ብርሃን ሰጠን ጨለማን ሽሮ
አዝ
የሚያስደነግጥ የሚያስጨንቀን
ይጠፋልና እርሱን ተማጽነን
በቀን ከሚበር ፍላፃ ሆሉ
ይታደገናል በቅዱስ ቃሉ
አዝ
እግርህ በድንጋይ እንዳይመታ
በፈተና ውስጥ እንድትበረታ
መቅሰፍት ከቤትህ እንዲከለከል
ይጠብቅሀል ሌሊትና ቀን
አዝ
ስሙን ያወቀ ሕይወት መሆኑን
ይመላለሳል ከኃይል ወደ ኃይል
ረጅም እድሜ ይጠግባል እርሱ
ብርሃን ይሆናል የፀጋ ልብሱ
አዝ
አቤቱ አንተ ተስፋ ነህና
የምትመግብ የፍቅር መና
ማዳንህ እኛን አስደስቶናል
እንዲህ ያለ ክብር ከየት ይገኛል
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
08 ноября 2024 11:00
እንዲህ እናምናለን
እንዲህ እናምናለን እንታመናለን /2/
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር
ብለን /2/
የእግዚአብሔር አብ ፍቅሩ ይሰፋል ይረቃል
ልጁን እስኪሰጠን እንዲሁ ወዶናል
በደብረ ታቦር ላይ እርሱን ስሙት ላለው
በመዝሙር ለቃኘን ምስጋና ይድረሰው /2/
አዝ
አብርሃም ይስሐቅን አባት እንደሆነው
አይደለም ልደቱ በአማን ልዩ ነው
የተወለደ ነው ከቶ አልተፈጠረ
ከአባቱ ጋራ ቅድመ ዓለም የኖረ /2/
አዝ
ሊያጽናናን የሚላክ ከአብ የሚወጣው
በሃምሳኛው ዕለት ወደኛ የመጣው
የራሱ የሆነ ፍጹም አካል ያለው
ጰራቅሊጦስ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ነው
የራሱ የሆነ ፍጹም አካል ያለው
ጰራቅሊጦስ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አዝ
በእደ ዮሃንስ ሲጠመቅ በማይ
ወልደ አምላክ መሆኑ ስንሰማ ከላይ
በአምሳለ እርግብ ወርዶ በእርሱ የኖረው
ለአካላዊው ቃል እስትንፋስ ሕይወት ነው /2/
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
08 ноября 2024 04:02
ስለ ማይነገር ስጦታው
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
ቸል ያላለን አምላክ ስንጓዝ ማዕበሉን አቋርጠን
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
አዝ
የሕይወት እስትንፋስ ዘራብን ሕያው እንድንሆን
ይህን ያደረገ አምላካችን እግዚአብሔር ይመስገን
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
አዝ
ነፋስን ገስፆ ማዕበል አቁሞ ሚያሻግር
የዓለም ፈተና ቢበዛ እሱ መጠጊያችን
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
አዝ
ዳግም እንዳንሞት በሞቱ ሞትን የረታልን
የምንመካበት ትንሣኤ ሰላምን ለሰጠን
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
አዝ
ከሲኦል እስራት ተፈተን ነጻ የወጣንበት
መስቀሉን ለሰጠን ለአምላካችን እንዘምር በእውነት
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገ
አዝ
ነፋስን ገስፆ ማዕበል አቁሞ ሚያሻግር
የዓለም ፈተና ቢበዛ እሱ መጠጊያችን
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሰናይ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
07 ноября 2024 05:00
ጥቅምት ፳፰/28/
በዚች ቀን ቅዱስ መርትያኖስና መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፉ።
እኒህም ለቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ ::አርዮሳዊ የሆነው ሁለተኛው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን በአርማንያ በሥውር እሥር ቤት ውስጥ አንቀው እንዲገድሉት ካደረገ ቡኃላ እኒህ ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ የዕረፍቱን ቀን ገድሉንም ጻፉ::አርዮሳዊውንም ንጉሥ ረገሙት ::
ንጉሡም እንደረገሙት በሰማ ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደ እርሱ አስቀረባቸው በሰይፍም ገደሏቸው:: በዚያም በገደሏቸው ቦታ ቀበሩአቸው እስከ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመንም በዚያ ቦታ ኖሩ እርሱም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ሥጋቸውን ወደ ቍስጥንጥንያ በክብር አስመጣ ያማረች ቤተክርስቲያንንም ሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖረ በዚችም ቀን በዓልን አደረገላቸው።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
06 ноября 2024 18:29
ምሥጢረ ጥምቀት
ጥምቀት የቃሉ ፍቺ መነከር፣ መዘፈቅ፣ በጥልቅ ውኃ ውስጥ መግባት፣ መጥለቅ፣ በውኃ መታጠብ፣ ውኃን በገላ ላይ ማፍሰስ ማለት ነው፡፡ ብዙ ሊቃውንት ስለ ጥምቀት ሲያስተምሩ “አጥመቀ›› አጠመቀ ካለው ግዕዝ ግስ የተገኘ እንደሆነና ትርጉሙም በውሃ መነከር መዘፈቅ... የሚል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ጥምቀት ማለት ከቀደመው አባታችን ከአዳም በደልንና ኃጢአትን እንደ ሐብትና ንብረት እየወረስን በነበርንበት ሁላችንም የሰው ልጆች በተፈርዶ በነበርንበት፣ እግር ከወርች ታስረን በጨለማ /በሲዖል/ እንኖርበት ከነበረው ዓለምና እኛ ራሳችን የፈጸምነውን በደልና የሰራነውን ኃጢአት ሁሉ ደምስሶ በመንፈስ ቅዱስ እንደገና እንድንወለድ ያደረገን በአፈጻጸሙ የመጀመሪያ የሆነ የእምነታችን ምሥጢር ነው፡፡
የሰው ልጅ መንፈሳዊ ልደትን /ልጅነትን/ የሚያገኘው በእምነትና በምሥጢረ ጥምቀት ነው፡፡ በጥምቀት የተጀመረ ማንነት ሜሮንና ቁርባን ይከተሉትና መንፈሳዊ ልደታችንን ክርስቲያናዊ ዕድገታችን ከጸጋ ወደ ተሻለ ጸጋ፣ ከክብር ወደ ተሻለ ክብር እንዲሻገር ይሆናል፡፡
ለዚህ ነው ጥምቀት አዲስ ሕይወትን ከሚያስገኙ መንፈሳውያን ምሥጢራት መካከል የሚመደበው፡፡ እምነት ከሁሉ እንደሚቀድም ጥምቀትም በክርስትና ያለንን አንድነትና እምነት የሚመሰክርልን የእምነት ምሥጢር ስለሆነ የምሥጢራት ሁሉ መጀመሪያና ወደ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ የሚያገባ በር ነው።
ጥምቀት አፈጻጸሙ ሁለት ዓይነት ነው። የሚፈጸመው ካህኑ በጸሎተ ክርስትና መሠረት ሥርዓተ ጸሎቱ ተፈጽሞ ካለቀ በኋላ፡-
- የተደራጀ አቅም ባላቸው አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በክርስትና ቤት ውስጥ ለዚሁ ተግባር ይሆን ዘንድ በተዘጋጄ የመጠመቂያ ገንዳ ወስጥ ተጠማቂ ሕጻናትን በመንከር እና
- በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ደግሞ በጻሕል ተሞልቶ የተጸለየበትና የተባረከውን ውሃ በተጠማቂው ሕጻን አካል ላይ በማፍሰስ የሚፈጸም ሲሆን በምሥጢራቱ አፈጻጸምም ሆነ በሚገኘው ጸጋ ምንም ልዩነት እንደሌለ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ጥምቀት ምንድን ነው?
ሰዎች፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃና በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው ሀብተ ውልደት፣መንፈሰ ልደት የሚገኙበት፣ የሰማያዊ መንግሥት ባለቤቶች ለመሆን የሚበቁበት ከኃጢአትና፣ ከዲያቢሎስ ቁራኝነት ነፃ የሚወጡበት አምላካዊ ፈቃዱ የሰጠን ሥርዓት/ሐብት/ ነው፡፡
የሚከተሉት ነጥቦች በጥንቃቄ እንመልከት፡፡
☞ “… እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት'' በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አዳነን እንጂ ..." ቲቶ 3÷5 - "...ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር /ሰማያዊ/ መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡'' ዮሐ.3÷5 12
☞ “…ንስሐ ግቡ፣ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ..." ሐዋ.2÷38 እንዲል፡፡
እንግዲህ አንድ ሰው ሲጠመቅ በሌላ በማንኛውም መንገድ ገንዘብ ሊያደርገው
ከማይችለው ጸጋ እግዚአብሔር ተሳታፊ ይሆናል፣ ሊያደርገው ከማይችለው በማይመረመር በልዑል እግዚአብሔር አሠራርም በሚታይ ሥርዓት የማይታይ ፍጹም በረከትንና የልጅነት ጸጋን ይቀበላል፡፡ ሰው ሁሉ በእንዲህ ባለ ሥጋዊ አዕምሮ ሊመረምረው የማይችለው፤ ከጥበባትም ሁሉ በሚልቅ ወደር በማይገኝለት አምላካዊ ጥበብ ወደ እግዚአብሔር ይቀርባል፤ እርሱንም መስሎ ከእርሱም ጋር በሞቱና በትንሣኤው ይተባበራል::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስዋሰው ወግስ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
06 ноября 2024 04:59
ጥቅምት ፳፯ /27/
በዚች ቀን ቅዱስ አባት የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አረፈ።
ይህ አባት በወንበር ተቀምጦ ሕዝቡን በሚያስተምራቸው ጊዜ የወገኖቼን ኃጢአታቸውን፤ የከፋች ሥራቸውንም እያየ ዘወትር ያለቅስ ነበር።
ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ በኃጢአተኞችም ጐዳና ያልተጓዘ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል።
የንጉሡም መልክተኛ አባ መቃርስ በንጉሥ ሃይማኖት እንደማያምን በአወቀ ጊዜ ተቆጥቶ ከኵላሊቱ ላይ ረገጠው ያን ጊዜም ሙቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ከነቢይ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት ከወደደው ክርስቶስም የመንግስተ ሰማያትን ዘውድን ተቀዳጅቶ ሔደ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
05 ноября 2024 11:46
ዘጸአት ነዉ ለሕዝቡ
ዘጸአት ነዉ ለሕዝቡ
በደም ታስሯል ወጀቡ
ፅኑ ክብርን ያየነዉ
ኢየሱስን ይዘን ነዉ ክርስቶሰን ለብሰን ነዉ
የግብፁ ፈረኦን በግፍ ሲያስጨንቀን
ክቡደመዘአረት ሙሴ ተነሳና ከራምሴ
መንጋዉን ይዞ ወጣ እየቀናበ ቃዱስ በሲና
ያመንፈሳዊ መጠጥ ያመንፈሳዊ መብል
ክርስቶስ ነበረ እኛን የሚከተል
አዝ
በራፍሊም እንዳንቀር ተወልን ምስክር
በኢያሱ ወልደ ነዌ እያዳነን ከአርዌ
ከነአን ሄደ ከፊት እየመራ
ስሙ መድሀኒት ሆነን
እሰራኤል ዘነፍስ ነን ድል ባደረገዉ ጌታ
ኢያሪኮ ሲኦል ፈረሷል በእልልታ
አዝ
በፋርስ ነገስታት ወድቆብን ባርነት
በኤርሚያስ የለወዝ በትር
እየታየን በምስጢር
እንደ ብረት አምድ ቅጥር አድረጎን
የእሳቱን ወጀብ አለፍን
በምልክት በራዕይ ተስሎ በሰማይ
ማምለጫችን ሆነ በጎልጎታ ላይ
አዝ
ከጥላታችን መዳፍ መከራ ቢወነጨፍ
የጠበቅነዉ መሲህ ደርሷል
ሸክማችንም ተራግፏል.
የመቤጀት ቀን ቀርቦ ዘፅአት
ጠቅልለንወጣን ከሞት
በደሙ አጊጠናል እርስቱን እንወርሳለን
በጽዮን ተራራ ለበጉ እየዘመርን
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ ጻድቅ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
05 ноября 2024 04:00
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆች እኮ ነን
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ እናት ልጆች እኮ ነን
ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነዉ ግዛቱ አብረን እንወርሳለን
የተካፈልኩትን ንብረት አትፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል ብዙ ነዉ የእርሱ መንግስት
አይክፋህ እባክህ ወንድሜ ፍቅር ይበልጣል ከሀብት
አዝ
ፊትህ በሀዘን አይጥቆር ድንጋዩን ጣለዉ ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ የአንተም መስዋዕት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነዉ መታዘዝ ንጉስ ያደርጋል
አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም
አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 ноября 2024 11:00
ደጅ ጠናሁ
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔንን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሁኝኝ ቀሪዉ ዘመኔን /2/
የመከራዉ ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንችን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንችም ደግነት
ባርያሽን ሰወረኝ ከአስጨናቂዉ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ
ልቤ በአንች ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጥላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ
እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክራቸዉ ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸዉ
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸዉ
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ
ከአዉደ ምህረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችኝ ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለዉ
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነዉ
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 ноября 2024 04:00
ንሴብሆ
ንሴብሆ/2/ ለእግዚአብሔር/2/
ስቡሃ ዘተሰብሃ/2/
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/
ምስጉን ነው የተመሰገነ/2/
አዝ
ባሕሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍጹም ነጻ ወጣን
ህይወት የሚሆነን መና ነው ምግባችን
አዝ
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
አዝ
ከዓለት ላይ ውሀ ፈልቆልን ጠጣን
ይህን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግን
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆኗል
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
አዝ
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
03 ноября 2024 11:48
አረሳት ኢትዮጵያን
አረሳት ኢትዮጲያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በ ሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ
ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠር ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ
አዝ
ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
አዝ
ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት
አዝ
ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 ноября 2024 16:42
በዚህ ስም የሚጠራ Bot በዝማሬ ዳዊት እና በሌሎች መንፈሳዊ ግሩፕ ላይ የሚለቃቸውን ከመንፈሳዊ ይዘት ውጭ የሆኑ ነገሮች ብናጠፋ፣ ብሎክ ብናደርገውም ልንቆጣጠረው አልቻልንም። በመሆኑም ጉዳዩን እስክንፈታው ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን።
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 ноября 2024 11:01
በቤተ መቅደስህ ያሳደከኝ
በቤተ መቅደስህ ያሳደከኝ
ለአፌ ጥበብን ያስተማርከኝ
የልጅነቴ አምላክ ወዴት አለህ
በዚህ ዓለም ሀሳብ ክንዴ ዛለ
አዝ
የአሸዋ ላይ ህንፃ ሆኗል ቤቴ
ያረገርጋል መሰረቴ
ጠላት ሰልጥኖብኝ ደክምያለሁ
ዛሬ ብቻዬን ቀርቻለሁ
አዝ
አባካኝ ሆኛለሁ አመጸኛ
ለዚህ ዓለም ሀጢአት የማልተኛ
ነፍሴ ተንገላታች በመከራ
ማን ያገናኛት ካንተ ጋራ
አዝ
ሰላሜ ነህ አንተ ትዝታዬ
ጽፌ ያኖርኩህ በእንባዬ
አለም ወስዳኛለች በዘፈኗ
እባክህ ስራኝ እንደገና
አዝ
አመጸኞች ሁሉ ቤትህ ገቡ
ምሕረት ፍቅርህን እያሰቡ
እጅህን ዘርግተህ አቀፍካቸው
ባንተ ቀለጠ ልቦናቸው
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 ноября 2024 04:02
ለቤሩታዊት የደረሰ
ለቤሩታዊት የደረሰ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ገሰገሰ
ፈጥኖ ሊያወጣኝ ከመከራ
ቆሟል ከጎኔ ከእኔ ጋራ
ስጋው ሲመተር አልፈራም እሱ
ሰባት አክሊላት ጭኗል በእራሱ
በደብረ ይድራስ በዛ ተራራ
የልዳው ፀሐይ ተብሎ ተጠራ
አዝ
ዓለምን ስትዞር በነጭ ፈረስ
አንድ ግዜ እርዳኝ ጊዮርጊስ ድረስ
ስሙን ለጠራ አምላከ ጊዮርጊስ
ሲደርስ ይፈጥናል ከአውሎ ንፋስ
አዝ
ለእሳት ለግለት ስጋውን ሲሰጥ
ፍርሃት የለበት ወይም መደንገጥ
ኡዲያኖስ አፋሮ ጣኦት ወደቀ
በጊዮርጊስ ጽናት ጌታ ታወቀ
አዝ
ከሹመት ይልቅ መርጠህ መከራ
ወንጌሉን ሰበክ አንዳች ሳትፈራ
በጭንቀት ሆነ ላንተ ንግስና
ብድራትህን አይተሃልና
አዝ
መስተጋድል ነህ ሃያል ገናና
መክብበ ሰማይት የእምነት ጀግና
ስምክን ስጠራ ከቤትህ ቆሜ
ይቀልልኛል የኃጢአት ሸክሜ
ዘማሪት መቅደስ ማርዬ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 ноября 2024 11:00
አለ ለእኔ የተሻለ ነገረ
አለ ለእኔ የተሻለ ነገር /2/
ዛሬን ባዝን ለጊዜው ብቸገር
አለ ለእኔ የተሻለ ነገር
በእጄ የጨበጥኩት በድንገት ቢበተን
ዙርያዬን ቢከበኝ ያላሰብኩት ሀዘን
እንባዬ በደስታ መቀየሩ አይቀርም
እተማመናለው በጌታዬ አላፍርም
አዝ
ሀብቴን ልጄን ባጣ እርሱ እንደወደደ
የእዮብ መከራ በእኔም ከወረደ
እራቁቴን መጣው እንዲሁ ሄዳለው
ከዚህ የላቀውን ከእርሱ እጠብቃለው
አዝ
መከራው ቢከብደኝ ከዙፋን ወርጄ
ከርስቴ ብሰደድ በአቤሰሎም ልጄ
ቀኑ እስከሚነጋ አልፈራም ጨለማ
ዳግም እለብሳለው የጽዮንን ግርማ
አዝ
አሳዳጄ ቢያይል ጉልበቱ ቢፀና
ተግዳሮቱ በዝቶ ወደ እኔ ቢያቀና
የከበረው ድንጋይ አለ በወንጭፌ
እቋቋመዋለው እርሱን ተደግፌ
አዝ
በናባው ተራራ ቢሆን መቃብሬ
ከነዓን ባልገባ ከህዝቡ ጋር አብሬ
አለኝ በሰማይ ቤት እጅግ የከበረች
በጆሮ ያልተሰማች በአይንም ያልታየች
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
08 ноября 2024 18:29
ምሥጢረ ተክሊል
ተክሊል የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን ከለለ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው ትርጓሜውም ከለለ ሲል አከበረ፣ ለየ፣ ቀደስ ፣አጨ፤ ተክሊል ሲል ደግሞ ክብር ማለት ነው፡፡ ተክሊል በክርስትና ሃይማኖት የሚኖሩ ለባልና ሚስትነት የተፈቃቀዱ ወንድና ሴት ጥንዶች ሁለቱ አካላት በፍፁም አንድ ሃሳብ (አንድ ልብ)፣ አንድ ፈቃድ እና አንድ አካል የሚሆኑበትና ሁለትነት ጠፍቶ በአንድነት ባልና ሚስት ሁነው ተጣምረው መኖር የሚያስችላቸው ቅዱስ ምሥጢር ነው፡፡ ዘፍ 2÷18-24 ማቴ 19÷5
ጸሎተ ተክሊል ካህናት በሙሽራው እና በሙሽሪት (በመርዓዊና በመርዓት) መካከል የሚፈጽሙት የጽኑዕ አንድነት ቃል ኪዳን (የጋብቻ ውል)፤ ወንድና ሴት በባልና ሚስትነት ተስማምተው በመኖር የዘለዓለም ሕይወትን መውረስ የምታስችለውን ትዕዛዘ እግዚአብሔር የሚፈጽመበት በግዙፋዊ አይን የማያዩትን፣ በሥጋዊ ልቡና የማይመረምሩትን ረቂቅ መንፈሳዊ ውህደት የሚያጎናጽፍ ምሥጢር ነው፡፡
እነሆም አንድ ሰው ቀርቦ መምህር ሆይ የዘለዓለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው:: እርሱም ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው:: እርሱም የትኞችን? አለው
''ኢየሱስም አታመንዝር አለው. . . "
ማቴ 19÷16-19
ጸሎተ ተክሊል ተጋቢዎች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በካህናት ጸሎትና ቡራኬ ጸጋ እግዚአብሔርን የሚጎናፀፉበት፣ እንደ ክርስቶስ እና ቤተ ክርስቲያን በፍፁም ፍቅር እና አንድነት የሚስተፃመሩበት በቅዱስ ቁርባን ማኅተምነት የሚፀና ምሥጢር ነው፡፡ በመሆኑም ጋብቻ ጊዜያው ተባብሮ የመኖር ዘዴ ሳይሆን እስከ ዕለተ ሞት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ (የማይፈርስ)፣ ላከበሩት የሚያስከብር የመረዳዳትና የአንድነት መንፈሳዊ ጸጋን የሚያጎናጽፍ መንፈሳዊና ማኅበራዊ የሕይወት ማዕርግ ነው። የጋብቻ ቃል ኪዳንን ተክሊል የሚያሰኘው ሙሽሮች ቃል ኪዳን በሚፈጽሙበት ወቅት የከበረ፣ በልዩ ጌጥ የተንቆጠቀጠውን የራስ ጌጥ፤ ሽልማት የክብር ጉልላት የሆነ ቆብ (ተክሊል) በራሳቸው ላይ ስለሚደፉ ነው።
ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክቱ ''ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል
ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ'' ኤፌ 5÷31-32
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ''ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻችውን ሊውዱአቸው ይገባቸዋል የገዛ
ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና'' ኤፌ 5÷28-30
በሥነ ፍጥረት ታሪክ እንደተረዳነው አዳም ሲፈጠር ብቻውን ቢሆንም ዘግይቶ ሄዋን ከአካሉ ተከፍላለች፡፡ በመሆኑም የሔዋን ገላ ማለት የአዳም ገላ እንዲሁም የአዳም ገላ ደግሞ የሔዋን ገላ በመሆኑ ባል ሚስቱን ቢወድ ራሱን ወይም ገላውን ሚስትም ባሏን ብትወድ ራሷን ወይም ገላዋን የምትወድ መሆኑን አስገንዝቦናል።
በተጨማሪም አዳም እና ሔዋን ዕፀ በለስን በልተው በኃጢአት ከመውደቃቸው እና ክብራቸው ከመገፈፉ በፊት ብርሃን ለብሰው ስለነበር ጸጋና አይተፋፈሩም ነበር፡፡ ዛሬም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በሚፈጸም አንድነት ሰው የገዛ ገላውን ኢያፍርምና፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ሁለቱም
አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
08 ноября 2024 05:00
ጥቅምት ፳፱ /29/
በዚችም ቀን የተመሰገነና የከበረ የደብረዘኸኝ መምህር ጸቃውዐ ድንግል አረፈ።
የዚህም ቅዱስ አባቱ ካህን ነው በጥበብ እና በበጎ ተግሣጽም አሳደገው መለኮታዊ ትምህርትን ሁሉ አስተማረው አድጎ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አባቱ ከአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ለመምህርነትም ተመርጦ በአባ ገብረ ማርያም ወንበር ላይ ተሾመ።
በዚያንም ጊዜ አባቱ ለልጁ የምንኵስና ልብስ አለበሰው ስሙንም ጸቃውዐ ድንግል ብሎ ሰየመው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ ያለ ማቋረጥ በጾም እና በጸሎት ብዙ በመስገድም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ሰዓትበደረሰ ጊዜ ጥቂት ታሞ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
07 ноября 2024 11:00
ምስጋናው ይቀጥል
ምስጋናው ይቀጥል ዝማሬው ይቀጥል
እግዚአብሔር ስላለ ከያዘ የማይጥል
በምናየው ነገር በምንሰማው ወሬ
እንዳይቆም ምስጋና እንዳይቆም ዝማሬ
የሰማዕታቱ ደም የፈሰሰው በምድር
አይተናል ሲያስቀጥል የክርስትናን ዘር
እንድናምን ብቻ መች ተጠራንና
በእሳቱም መካከል ቅኔ አለን ምስጋና
አዝ
መች ማጥፋት ይቻላል እሳትን በእሳት
አይቆምም ማህሌት ቅዳሴ ሰዓታት
ከሰማዩም በላይ ከሰማዩም በታች
ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ነገም አለች
አዝ
የዓለም ጨው ሆነን በዓለም የበዛነው
እየተደበደብን እየተገፋን ነው
በገደሉን ጊዜ ቁጥራችን ይበዛል
ከሞትም በኋላ ህይወት ይቀጥላል
አዝ
የተስፋይቱን ምድር ተነሱ እንወርሳለን
በመዝሙር በእልልታ ቅጥሩን እያፈረስን
የሰላዮቹን ቃል ሰምታችሁ አትፍሩ
በሃይማኖት ጽኑ በእምነታችሁ ቁሙ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
07 ноября 2024 03:59
መክፈል የማልችለው
መክፈል የማልችለው አለብኝ ውለታ/2/
ተነግሮ የማያልቅ አለብኝ ውለታ /2/
አምላክ ተመስገን የኔ ጌታ
ይችው ነች አቅሜ ለስጦታ /2/
በዘመኔ ሁሉ የደገፍከኝ በእጆችህ
ጌታ ዘርዝሬ አልጨርሰው ውለታህ
ምስኪን ባሪያህ ለውለታህ አሁን ምን እከፍላለሁ
ሌላ አትሻም አንተ የአቅሜን ይኸው አመሰግናለሁ
አዝ
ስናቅ እንዳልነበር እኔ በሰዎች ተጥዬ
ከውድቀቴ አንስተህ ሰው አረከኝ ቸር ጌታዬ
ነፍሴ ለውለታህ በምስጋና ተሞልታለች
ጠዋት ማታ ስምህን እያነሳች ታመሰግናለች
አዝ
ነፍሴ መሸሸጊያ አጥታ አንተ ስላየሀት
ከለምለም መስክ ወስደህ ጌታ አሳረፍካት
የከበዳት ሸክም ቀሎ በአንተ እረፍት አገኘች
ይኸው በሰዎች ፊት የአንተን ክብር ትመሰክራለች
አዝ
አይቸኩልም እግዚአብሔር ለእርሱ አለው ጊዜ
ሲጠሩት ይሰማል ደግሞ ያወጣል ከትካዜ
የጽድቅንም መንገድ እያሳየ ይመራናል
ወደ ህይወት መንገድ እረኛችን ወስዶ ያሳርፈናል
ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሰናይ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
06 ноября 2024 10:58
አልፈርድም እኔ
አልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ኃጢአት
በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌታ ሲመጣ በኃይል በሥልጣን
በቸርነቱ አምላክ ባይተወው በደሌን ሁሉ
ውስጤ ቢፈተሽ በተሰጠኝ ሕግ በቅዱስ ቃሉ
በምን ምግባሬ ሰውን አያለው ዐይኔን አቅንቼ
በደሌ በዝቶ ለራሴ ሳላውቅ ለኃጢአት ሞቼ
አዝ
ይልቅ የአንዱን ሸክም ሌላው ሰው አዝሎ መጓዝ ይሻላል
መፍረድ ከመጣ አንድም ሰው አይድን ሁሉም በድሏል
ወንድም ወንድሙን እየከሰሰ ለፍርድ አቁሞ
አሕዛብ ያያል በንትርኩ እጅግ ተገርሞ
አዝ
ክርስቲያን ሆኖ ከወንድሙ ጋር እየተጣላ
ዓለም ዳኘችው በፀብ ፍርድ ቤት ታረቁ ብላ
ክርስቲያን ሆነን በአሕዛብ መሃል እየተካሰስን
አምላክ አዘነ የመስቀሉን ስር ዓላማ ሽረን
አዝ
መቼ ከሰሰ የከሰሱትን የገረፉትን
አይተናል እንጂ ለጠላቶቹ ምሕረት ሲለምን
ለጽድቅ ስራ ለእውነት ብለን መተናል እንጂ
ማነው የሾመን በወንድሞች ላይ አርጎ ፈራጅ
አዝ
መቼ ከሰሰ የከሰሱትን የገረፉትን
አይተናል እንጂ ለጠላቶቹ ምሕረት ሲለምን
ለጽድቅ ስራ ለእውነት ብለን መተናል እንጂ
ማነው የሾመን በወንድሞች ላይ አርጎ ፈራጅ
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
06 ноября 2024 04:05
ቸሩ ሆይ
ቸሩ ሆይ ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ አማኑኤል ናና
የእስራኤል መና ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ መድኃኔዓለም ናና
አዝ
ቸሩ ሆይ ለዓይነ ስውር መሪ
ቸሩ ሆይ ምርኩዝ መመኪያ ነህ
ቸሩ ሆይ አንተን የሚመስል
ቸሩ ሆይ ምንም ነገር የለም
ቸሩ ሆይ ምሕረትና ፍቅርህ
ቸሩ ሆይ ወሰን ወደር የለው
ቸሩ ሆይ ሳንወድህ ወደድከን
ቸሩ ሆይ ፈልገህ ጠራህን
አዝ
ቸሩ ሆይ ሰምተህ እዳልሰማህ
ቸሩ ሆይ አይተህ እንዳላየህ
ቸሩ ሆይ ሁሉን ታልፈዋለህ
ቸሩ ሆይ ፍቅራዊ አባት ነህ
ቸሩ ሆይ አማኑኤል ጌታ
ቸሩ ሆይ ቸሩ ፈጣሪያችን
ቸሩ ሆይ ውለታህ ብዙ ነው
ቸሩ ሆይ ለእኛ የዋልክልን
አዝ
ቸሩ ሆይ በከብቶች ማደሪያ
ቸሩ ሆይ በዚያች ትንሽ ግርግም
ቸሩ ሆይ ተወልዶ አዳነን
ቸሩ ሆይ ጌታ መድኃኔዓለም
ቸሩ ሆይ እልል በሉ ሰዎች
ቸሩ ሆይ አንድ ላይ ዘመሩ
ቸሩ ሆይ ስብሐት ለእግዚአብሔር
ቸሩ ሆይ በአርያም በሉ
ዘማሪ፦ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
05 ноября 2024 05:01
ጥቅምት ፳፮/26/
በዚች ቀን ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞች ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ።
ይህ ቅዱስ የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከሐዋርያት ጋር ከተቀበለ በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ተሾመ።
በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ:: በውስጧም ሃይማኖትን አስተማረ ከዮናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው።
የዚያች አገር ገዢም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 ноября 2024 18:29
የሰው ልጅ ከውድቀት በኋላ
የሰው ልጅ ፍጹም የተለወጠው በእግዚአብሔር ላይ ሲያምፅ ነው። ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተለየው፤ ያን ጊዜ የክብር ልብሱ ተወሰደበት፤ ያን ጊዜ ሐፍረትና ውርደት አገኘው፤ ያን ጊዜ ከመላእክት ሕይወት ወርዶ የዚህ ዓለም ጭንቀት የሚገዛው ፣ ጥሮ ግሮ የሚበላ፣ ልብሱ ከእንስሳት የተገኘ ቆዳ፣ እጅግ ብርቱ የኾኑ ፍትወታትና ሥጋዊ መሻቶች የሚጸኑበት፣ የሚርበው፣ የሚጠማው፣ የሚደክምና የሚሞት ኾነ።
እግዚአብሔርን መስሎ የሚያድግበት አቅም በውስጡ የነበረ ቢኾንም፥ የሰይጣንን ምክር ሰምቶ በአቋራጭ ያልተገባ ክብርን በመሻቱ ምክንያት፥ ያን ጊዜ የማያድግ ይልቁንስ ቁልቁል የሚወርድ ኾነ። እንደ እንስሳት የሚኖር አላዋቂ ኾነ። እንደ እንስሳት መኖርም የሰው ልጅ የመጨረሻ የውርደት መገለጫ ነበር።
የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሮ ሳለ እንደ እንስሳት ሲኖር ማየት በእውነት ጥንቱን እንስሳ ኾኖ በተፈጠረ በተሻለው ነበር የሚያስብል ኾነ። ከጌታ በታች ገዢ ሲኾን ይህን ባለማወቁና ከዕፀ በለስ ሰርቆ በመብላቱ በፍቃዱ ራሱን አዋርዷልና፥ ባሪያ ኾኖ ጌቶች ያልኾኑት የሚገዙት ኾኗልና እጅግ አሳዛኝ ፍጥረት ኾነ። በኃጢአት ብዛት ጠቁሮ በሰማያውያን አምሳል መኖር ተሳነው።
ቅዱስ ኤፍሬምም ይህንን ሲያይ፡-
"አዳም ከንግሥና ወርዶ ከእንስሳት መኖሪያ ሲያየው እንዴት እንደ ወደቀ እያሰበ ዳዊት አለቀሰለት (መዝ.48፡13)። ሸሽቶ ከዱር እንደ ተደበቀ የዱር እንስሳትን መሰለ። ከወደቀበት መርገም የተነሣም ከእንስሳት ጋር ሣርና ሥራሥር በላ፤ ጓደኛቸው ኾኖም እንደ እነርሱ ሞተ አለ።
ስለዚህም እውነተኛ ሰው መኾን ተሳነው። ሰውን ሰው የሚያስብለው የሰው መልክ ዓይን፣ አፍንጫ፣ አፍ ስላለው አይደለምና። እነዚህ የሰውነት ብልቶች ናቸውና። ሰው ብለን ልንጠራው የሚገባን የሰው ልጅን ጠባይ መገለጫ ገንዘብ አድርጎ ሲገኝ ነውና፤ እርሱም ማሰብ መቻሉና በዚያ መሠረት የቅድስና ሕይወትን መያዝ ነው።
ቀድሞ ይገዛቸው ይነዳቸው የነበሩት ብዙ እንስሳት በእርሱ ላይ የሚነሣሡበት ኾኑ። ምንም እንኳን ቀድሞ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ የተገኘ ኾኖ ሳለ እንደ መላእክት ይኖር የነበረ ቢኾንም፥ ሲወድቅ ግን ወደ እርሱ የሚመለስ ኾነ። መንፈስ ቅዱስ የማይመራው የማይነዳው ኾነ። ቀድሞ የነበረው እጅግ አስደናቂ ዐዋቂነትን አጥቶ በድንግዝግዝ የሚጓዝ ኾነ። ሞት ሙስና፣ ክፋት የአዳም አዲሶቹ መገለጫዎቹ ኾኑ።
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ፥ አዳም ከእግዚአብሔር ጋር አፍ ለአፍ የማይነጋገር ኾነ። በእርሱና በእግዚአብሔር መካከል ኃጢአት እንደ ግድግዳ ኾኖ ቆመ። በዚህ ኹኔታ ውስጥ ላየውም ከላይ እንደ ተገለፀው አዳም እጅግ የሚያሳዝን ፍጥረት ኾነ። ሰውነቱ በኃጢአት ለመጠቃት እጅግ ተጋለጠ። ሞት ከተፈረደበት በኋላ ፍትወታት ወደ ባሕርዩ ዘልቀው ስለ ገቡ ደግ ሥራን ለመሥራት ከባድ ኾነበት። ልጓም የሌላት ፈረስ እንዲሁ እንደምትላተምና እንደምትወድቅ፥ ሰውም እንደዚህ ኾነ። ከምንም በላይ ደግሞ የአዳምና የሔዋን አንድነት ወደ መፍረስ ተቃረበ። በዲያብሎስ ምክር ምክንያት አዳምና ሔዋን እየተካሰሱና አንዳቸው በአንዳቸው ላይ እያመካኙ ወደ መለያየት የተቃረቡ ኾኑ።
ሲወድቅ የሚጠቅሙት (መንሻ የሚኾኑት)፥ ግን ደግሞ የውድቀቱ ማሳያ የኾኑ መገለጫዎች ወደ ባሕርዩ ዘልቀው ገቡ። ምክንያቱም ፍርሐት ሲመጣበት ስለ ኃጢአት፣ ኀዘን ሲመጣበት ስለ ኃጢአት፡ ሞት ሲመጣበት ስለ ኃጢአት እንዲያስብ እንጂ እርሱን ለመጉዳት የመጡ አይደሉምና። እግዚአብሔር እነዚህን ኹሉ የሰጠው በበደል ላይ በደል እየጨመረ እንዳይጠፋ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ትንሿ ቤተክርስቲያን
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 ноября 2024 05:01
ጥቅምት ፳፭/25/
በዚች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ።
የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው። በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው። አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው።
ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በዚያንም ጊዜ እጅግ ለመስማት የሚዘገንን መከራ እና ስቃይ በህፃኑ ላይ አደረሰበት የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው።
ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚለይበት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ወርዶ ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት በደረቱም ላይ አድርጎ ወደ አየር አወጣው። የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
03 ноября 2024 17:07
አጌጥንበት ስምህን
አጌጥንበት ስምህን
ተዋብንበት ፍቅርህን
ሞገሳችን ሆነሃል
የጽድቅ ልብሳችን አማኑኤል /2/
ተዋህዶ የአዳምን ሥጋ
አማኑኤል ሆነ ከእኛጋ
በግርግም በቤተልሔም
ተወልዶ ሆነልን ሰላም
አዝ
ብንጠግብ በልተን ጠጥተን
ብንገባ በሰላም ወጥተን
ልጆችን ወልደንም ብንስም
ጠርተን ነው ጌታ ያንተን ስም
አዝ
ቢያምርብን ቢሞቀን ለብሰን
ብንረሳ ለቅሶና ሀዘን
ፍቅርህ ነው ዛሬን ያሳየን
ተመስገን እንልሃለን
አዝ
በባዕድ ሀገር ብንኖር
ቢገጥመን መከራ ችግር
ነጩን ልብስ ለብሰን ታይተናል
መስቀሉን ከማህተቡ ጋር
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
03 ноября 2024 08:00
ጥቅምት ፳፬ /24/
በዚች ቀን መስተጋድል መነኰስ አባ አብላርዮስ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ጋዛ ከሚባል አገር ነው። ወላጆቹም አረማውያን ናቸው የዮናናውያንንም ትምህርታቸውንና ፍልስፍናቸውን አስተማሩት ሰውነቱ ለጥበብ ማደሪያዋ እስከሆነ ድረስ በዕውቀቱ ከጓደኞቹ በላይ ሆነ።
ከዚህም በኋላ ከሀገሩ የሌለ መልካም የሆነ ጥበብን ከውጭ አገር መማርን ወዶ ተነሥቶ ወደ እስክንድርያ ሀገር ሔደ መምህራንም ሁሉ ከሚኖሩበት ቦታ ገብቶ ከእሳቸው ዘንድ ብዙ ትምህርትን ተማረ በዚያንም ጊዜ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ለመማር ተነሣሥቶ ቸኰለ የቤተክርስቲያንንም መጻሕፍት ብዙዎቹን አነበበ የእስክንድርያ ሊቀጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስም ይተረጒምለትና ያስረዳው ነበር።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በምንኵስና ሕግ ጸንቶ ገድልን ተጋደለ ወደ አባ እንጦንዮስም ሔዶ መንፈሳዊ የሆነ ጥምቀት ተጠመቀ ከዚያም መንኵሶ የትሩፋትን ሥራ እየተማረ በእርሱ ዘንድ ብዙ ወራት ኖረ።
ወላጆቹም እንደሞቱ በሰማ ጊዜ ሒዶ የተዉለትን ገንዘባቸውን ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች መጸወተ ከዚህም በኋላ ከሶርያ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባ በዚያም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት በመትጋት ፍጹም ገድልን ተጋደለ በየሰባት ቀን እስኪመገብ ድረስ ምግቡም የዱር ሣር ነበር።
እግዚአብሔርም ሀብተ ትንቢትን ሰጥቶት ልቡናው ብሩህ ሆነ ድንቆች ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ ኤጲፋንዮስንም ያመነኰሰውና ለደሴተ ቆጵሮስም ኤጲስቆጶስ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረለት እርሱ ነው። ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም ካገለገለ በኋላ በሰላም አረፈ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 ноября 2024 12:18
የጥቅምት ፳፬ ማኅሌተ ጽጌ🌹
👉 @
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 ноября 2024 05:40
ጥቅምት ፳፫ /23/
በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኀምሳ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ አረፈ።
ይህም አባት ከመኑፍ አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን ነው ወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ያላቸው ነበሩ ታናሽም ሁኖ ሳለ አባትና እናቱ ትተውት ሲሞቱ ድኃ አደግ ሆነ አንድ እግዚአብሔርንም የሚወድ ሰው አሳደገው።
አድጎ በጐለመሰም ጊዜ የወላጆቹን ገንዘብ ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጥቶ ከአንድ ጻድቅ ሽማግሌ ሰው አባት ዘንድ መነኰሰ በበጎ ገድል ሁሉ እየተጋደለ ኖረ።
ይህም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መናፍቃንን የሚገሥጻቸው ሆነ ሕዝቡንም ከአባቶቻቸው፤ በተቀበሏት በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አስተማራቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ለእነርሱም ሥውር የሆነውን ተርጕሞ ያስረዳቸዋል ያስገነዝባቸዋልም በትምህርቱና በጸሎቱም እንዲህ ጠበቃቸው ጌታችንም በእጆቹ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ያማረች ገድሉንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አረፈ።
መላ የሕይወቱም ዘመን ሰባ ስምንት ነው ከምንኵስና በፊት ሃያ ዓመት በምንኵስና ተጋድሎ ሠላሳ ዘጠኝ ዓመት በሊቀ ጵጵስና ሹመት ዓሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 ноября 2024 18:32
የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት
እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥረው እንደ መላእክት አድርጎ ነው። ቅዱስት መላእክት ለባውያን፡ ሥጋዊ መሻት የሌለባቸው ከኃጢአት የነጹ እንደ ኾኑ ሁሉ የሰው ልጅም ሲፈጠር ምንም እንኳን ሥጋን የለበሰ ቢኾንም እንዲህ ኾኖ ነበር። የሰው ልጅ ያልተለመደ ዓይነት መልአክ ኾኖ የተፈጠረ ነው። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ አዳምንና ሔዋንን ኹለት መላእክት" የሚላቸውም ለዚህ ነው። ከቅዱሳን መላእክት ጋር ኾኖ ከአምላክ ጋር አንድነት የነበረው፡
ዲያብሎስና እርሱን የተከተሉት መላእክት እንዲቀኑ ያደረጋቸው የሰው ልጅ ሕይወት ነበር። ምንም እንኳን ሥጋን የለበሰ ቢኾንም እንደ ረቂቃኑ” መላእክት መኖሩ፣ በአንድ ጊዜ ረቂቅና ግዙፍ ፍጥረት መኾኑ ነበር ያስቀናቸው::
ይህ ሰው ለሞት የተፈጠረ አልነበረም። ምንም እንኳን ካለ መኖር ወደ መኖር የተፈጠረ እንደ መኾኑ በባሕርዩ ሊሞት የሚችል ማለት ሞት የሚስማማው ገና የተፈጠረ ቢኾንም፥ ሕያው ባሕርይ በኾነው በራሱ በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠረ በመኾኑ ሕጉን በመጠበቅና ፈጣሪውን በማወቅ ይህንን አርአያ እግዚአብሔርን ቢጠብቅ ግን አይሞትም ነበር። እግዚአብሔር ሕያው የምታደርገውን ነፍስ የሰጠው ስለ ኾነ ብሩህ፡ ውብ፡ ለባዊ፡ መልካም ሥራዎችን ለመሥራት ዓቅም ያለው የተፈጠረ ነው፥ ይሀ በርግጥም ልዩ ክብር እንደ ነበረ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘቡል) ሲገልፀውም፡-
ከዚህ ክብር የሚበልጥ ምን ክብር አለ? ከዚህ ትምክሕት የሚበልጥ ምን
የሚያስመካ ነገር አለ?... ሰውን በእርሱ አምሳል እንደ ፈጠረው እንዲመሰክር ከመኾን የበለጠ የሚያስመካ ምን ነገር አለ?" ይላል ።"
ሙስና፡ ሞት፡ ሕማምና ድካም የመጡበት ከዚህ በኤደን ገነት ውስጥ ይኖርበት ከነበረው የንጽሕናና የድንግልና ሕይወት ፈቀቅ ሲል ነው። ሞት የሚስማማው ኾኖ የተፈጠረ ቢኾንም፥ በገዛ ፈቃዱ እንዳይሞት ማድረግ ይችል የነበረው የሰው ልጅ መዋቲ የኾነው ከበደለ በኋላ ነው።
ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ የተፈጠረ ቢኾንም፥ ክብሩ ግን ሰማያዊ ነበር። አፈርና ትቢያ የኾነው፡ እግዚአብሔር የነገረውን ባለ ማመን ብሎም ባለመታዘዝ ሲበድል ነው። ጥንቱን ከትቢያ የተፈጠረ ቢኾንም እስኪወድቅ ድረስ ክብሩ እፍ ተብላ ከተሰጠችው ነፍሱ የተነሣ ከፍ ያለ ነበር። ስለዚህም እንደ መላእክት ስለሚበላው፡ ስለሚጠጣው፣ ስለሚለብሰው፡ ስለ እንቅልፍ፣ ወጥቶ ወርዶ ስለ መሥራት፣ በአጠቃላይ ስለዚህ ዓለም ኑሮ የሚጨነቅ አልነበረም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይህን ግልፅ አድርጎ ሲነግረንም እንዲህ ይላል፡-
ምንም እንኳን በዚህ ምድር ላይ ሥጋ ለብሶ ቢኖርም ፍትወተ ሥጋ ሳይኖርበት እንደ ሰማያውያን መላእክት ኾኖ ይኖር ነበር። በትረ መንግሥቱን ይዞ የንግሥና ዘውዱን ጭኖ፡ ሐምራዊ መጎናጸፍያውን አድርጎ እንዳጌጠ ንጉሥ በነጻነትና በፍጹም ደስታ ይኖር ነበር። አንድም ነገር ሳይጐድልበት እጅግ ባለጸጋ ኾኖ በገነት ይኖር ነበር።"
ይበላ የነበረ ቢኾንም፤ በአንድ መልኩ ጥሮ ግሮ የሚበላ አልነበረም፡ በሌላ መልኩ ደግሞ አሁን የምናውቀው ዓይነት ረሃብና ጥም ስለ ነበረበት አይደለም። መላእክት እንደማይርባቸውና እንደማይጠማቸው ኹሉ፥ ሰውም እንደዚህ ነበር። ሰውስ ይቅርና ዛሬ ሥጋ በል የምንላቸው እንስሳትም ከውድቀት በፊት ምግባቸው ማር እንጂ ሥጋ እንዳልነበረ
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ይነግረናል።'
በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምንም እንኳን ሥጋ የለበሰ የነበረ ቢኾንም፥ በሥጋው ብቻ የታጠረ ግን አልነበረም። መላእክት ሥጋዊ ፍላጎት እንደ ሌለባቸው ኹሉ' ሰውም ይህ ኣልነበረበትም። መላእክት ልብስ እንደማያሻቸው ኹሉ' ሰውም ልብስ የሚያስፈልገው አልነበረም። ልብሱ፣ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ እንደሚነግረን
የክብር ልብስ ነበር ይህን የክብር ልብስ ለብሶ እያለ' እስራኤላውያን ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፊቱን ሳይሽፍን ማየት የማይቻላቸው እንደ ኾኑ፥ የምድር ፍጥረታትም አዳምንና ሔዋንን ማየት አይቻላቸውም ነበር። አዳም ለእንስሳቱ ስም ሲያወጣላቸውና በፊቱ ሲያልፉ እንኳን ቀና ብለው ማየት ሳይቻላቸው አጎንብሰው ነበር። አዳም ለብሶት የነበረውን የክብር ልብስ ማየት አይቻላቸውም ነበር።' እንስሳቱስ ይቅሩና ዲያብሎስ ይህን የአዳም ክብር በግልፅ ማየት አይቻለውም ነበር።" አዳም ይህን የክብር ልብስ ለብሶ ሲኖር ከግዙፍ ልብስ ዕራቁቱ እንደ ኾነ እንኳን አያውቅም ነበር። ስለዚህ አሁን የምናውቀው ዓይነት ልብስ ለሰው ልጅ የተሰጠው "ለዚያ አጊጠዉበት ለነበረው የብርሃን ልብስና ከሥጋ መሻቶች ነጻ ኾነው ለኖሩበት ሕይወት ያልተገቡ ኾነው በመገኘታቸው ነው።'' የቆዳ ልብስ የተሰጣቸው ለዚያ የክብር ልብስ ያልተገቡ ኾነው በመገኘታቸው ብቻ ሳይኾን ላለማመናቸውና ላለመታዘዛቸው ማዘከሪያ እንዲኾን ነው።
ዳግመኛም የሰው ልጅ በራሱ ላይ ብቻ ሳይኾን በሌሎች በሚታዩ ፍጥረታት ላይ ንጉሥ ኾኖ ይኖር የነበረ ነው። መጨረሻ ላይ መፈጠሩ፣ ሌሎቹ ፍጥረታት ኹሉ እርሱ እንዲጠቀምባቸው መዘጋጀታቸው በገነት ውስጥ ያለ ጣር መኖሩ፡ እንስሳቱ ኹሉ ስም እንዲያወጣላቸው ወደ እርሱ መምጣታቸውም ይህን ንግሥናውን በግልፅ የሚያስረዱ ናቸው። ፍርሐትና መንቀጥቀጥ የመጣበት ከበደለ በኋላ ነው፤ ሔዋን ከእባብ ጋር ያለ ፍርሐት መነጋገርዋ ይህን የሚያሳይ ነው።
የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት እጅግ ዐዋቂና ጠቢብም ጭምር ነበር። ይህም ሳይሳሳትና ሳይደግም ለእንስሳቱ ስም በማውጣቱ ታውቆአል።
ነጻነትም ነበረው። ከመበደሉ በፊት የሚያሻውን በጎ ነገር ለማድረግ አያቅተውም ነበር። በጎ ማድረግን አስቦ ማድረግ ያቃተው ሲበድል ነው።
ከእግዚአብሔር ጋር እንደ ባልንጀራ አፍ ለአፍ የሚነጋገር ነበር። አባት ለልጁ ኹሉን ነገር እንደሚያስተምረው፥ እግዚአብሔርም ለአዳም ኹሉን ነገር ያስተምረው ነበር። በኋላ ሲወድቅ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠውም የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ስለ ራቀ ነው። አጠገብ ላለ ወዳጅ ደብዳቤ አይጻፍምና።በጎውንና ክፉውን የሚያውቅ መለየት የሚችል ነበር። መለየት የማይችል ቢኾን ኖሮ ባልተጠየቀ ነበርና።
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ ትንሿ ቤተክርስቲያን
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 ноября 2024 05:03
ጥቅምት፳፪ /22/
በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ።
ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።
በኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።
ንጉሥ ኔሮንም እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ።
ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…