ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ደብረ ዘይት፡- ዳግም ምጽአት

ዘመነ ሥጋዌ የጌታችን መገለጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመለከትንበት፣ ይህም ከሰማያት ወርዶ እኛን ለማዳን ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው በመሆን ዓለምን ያዳነበት ነው፡፡ እርሱ እንደ ሰው ተወልዶ፣ እንደ ሕፃናት በጨርቅ ተጠቅልሎ፣ ጡት ጠብቶ፣ በየጥቂቱ አድጎ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በእግር ተመላልሶ፣ እንደ ሰው ተርቦና ተጠምቶ፣ ኀዘን መከራን ተቀብሎ በፍጹም ፍቅሩ አድኖናል፡፡

ፈውሰ ነፍስ በሆኑት ትምህርቶቹ ዓለምን አጣፍቶ፣ አዳኝ በሆኑት እጆቹ ልምሾዎችን፣ ድዊዎችንና አንካሶችን አድኖ፣ ጎባጣን አቅንቶ፣ የዕውራንን ዓይን አብርቷል፡፡ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ መሆኑንም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቀ መለኮት እጅ ተጠምቆ አስመስክራል፡፡ ብርሃነ መለኮቱ በታየበት በደብረ ታቦር ተራራም አምላክነቱን ገልጧል፡፡ (ማቴ.፫፥፲፫-፲፯፣፲፯፥፩-፰)

ይህን ሁሉ ያደረገው ሰዎች አምላክነቱን አውቀን፣ ከሰማየ ሰማያት የወረደውና መከራን ተቀብሎ በመስቀል ላይ የሞተው ለእኛ ድኅነት መሆኑን እንዲሁም ድንቅ ሥራውን የፈጸመበት ይህን ጥበቡን ተረድቶና፣ የእጁን ሥራ፣ የቃሉን ተእምራት ያመነውን ሁሉም እንደሚድነን ሲያበስረን ነው፡፡ በተጓዳኝም በመዋዕለ ስብከቱ ስለ ዳግም ምጽአቱና ምልክቶቹ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በዝርዝር በደቀ መዛምርቱ በኩል አሳውቆናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ (ማር.፲፫፥፫-፴፯)

“መቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ለብቻቸው ጠየቁት። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራብም ትገረፋላችሁ፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።

ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤ በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ፤ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፤ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።

በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤ በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና። ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።

በዚያን ጊዜም ማንም እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ። እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ። በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል፤ ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል። ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።ሰ ማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።

ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም። ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም። ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፤ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ። እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮህ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና፤ ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።”

ወንድሞች ሆይ! ጊዜ ዋጋው የላቀ በመሆኑና የጌታችንንም የፍርድ ቀን የሚያውቅ አለመኖሩን በቅዱስ ወንጌል ስለተነገረን በበጎነት፣ በቅንነትና በእምነት ጽናት ሆነን በጸሎት እንዲሁም በጾም፣ በትጋትና በክርስቲያናዊ ምግባር በመታነጽ በሃይማኖት ልንኖር ይገባናል፡፡ ዘወትርም ለሕጉ በመገዛትና ትእዛዙን በመፈጸም እስከ መጨረሻው ጸንተን “ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና” ልንባል ያስፈልጋል፡፡ (ማቴ.፳፭፥፴፬‐፴፮)

ዕድል ፈንታችን መንግሥተ ሰማያት መውረስ ይሆን ዘንድም በምድራዊ ሕይወታችን መከራ ሥቃይ ተቀብለንና ለነፍሳችን መሥዋዕት መክፈል ይገባል እንጂ “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና” ከመባል ይሠውረን፡፡ (ማቴ. ፳፭፥፵፩‐፵፫)
የአምላካችን ቸርነትና ረድኤት አይለየን፤ አሜን!

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#በስራዬ

በስራዬ የት ይሆን መግቢያዬ(፬)
ጨነቀኝ ጠበበኝ ኸረ ወዲያልኝ
ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍሴ ወዲያልኝ

ተሽክሜ የኃጢያት ክምር(፪)
ይመሻል ይነጋል በከንቱ ስዞር(፪)
ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ(፪)
ዋ ለነብሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ(፪)
#አዝ
በድያለሁ ወዳንተ ጮሃለሁ
ይቅር በለኝ እማፀንሃለሁ
ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜያለሁ(፪)
#አዝ
አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ(፪)
እየጓጓሁ ለዚች ለሥጋዬ(፪)
በንስሐ ሳላጥበው እድፌን(፪)
ልትደርስ ነው ያች ፈተና ቀን(፪)

መዝሙር
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"በደላችንን ይቅር በለን"
ማቴ፮፥፲፪

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​"ጾምን አጋመስነው አትበሉ"

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
ብዙ ሰዎች ደስ ተሰኝተውና እርስ በእርሳቸው፡- ግማሹን ጾም ፈጽመናል፤ የጾሙ እኩሌታ አለፈ ሲባባሉ ተመልክቻለሁ፡፡

እኔ ግን እነዚህ ሰዎች በዚሁ ምክንያት ደስ ሊላቸው እንደማይገባ እመክራቸዋለሁ፤ የጾሙ እኩሌታ ማለፉን ሳይኾን የኃጢአታቸው እኩሌታ መኼዱን መወገዱን ያስቡ፤ እንደዚያ ከኾነም ሐሴት ያድርጉ፡፡

ደስ ልንሰኝበት የተገባው ነገር ይኼ ነውና፡፡ ሊታይ የሚገባው ይኼ ነው፤ ጥንቱም እነዚህን ኹሉ ነገሮች የምናከናውናቸው ስሕተቶቻችንን እንድናስተካክል፣ ጾሙ ሲጀምር እንደ ነበርንበት ሳይኾን እንድንነጻበት፣ ክፉ ልማዶቻችንን ወደ ጎን አድርገን የተቀደሰውን በዓል በዓለ ትንሣኤን እንድናከብር ነውና፡፡

እንደዚህ ካልኾነ ግን ጾሙን መጨረሳችን በራሱ ለእኛ ታላቅ ጉዳትን ይዞ ከመምጣት ውጪ ሌላ ምንም ረብ ጥቅም አይሰጠንም፡፡

ስለዚህ ብዙ ጊዜ መጾማችንን ብቻ አንመልከት፤ ይህ ምንም ትልቅ ነገር አይደለምና፤ ይልቁንስ በዚህ ጾም ራሳችንን አሻሽለን እንደ ኾነ፣ ጾሙ ከተፈታ በኋላም የዚሁ ፍሬ ጎምርቶ ይታይብን እንደ ኾነ ሐሴት እናድርግ፡፡

የክረምት ጥቅሙ ይበልጥ የሚታወቀው ወራቱ ካለፈ በኋላ ነውና፡፡

የዚያን ጊዜ የአበባው ማበብ፣ የአዝመራው ማፍራት፣ ሌሎች ዕፅዋትም በቅጠላቸውና በፍሬያቸው በወርሐ ክረምት ያገኙትን ጥቅም ግልጽ አድርገው ይናገራሉና! በእኛም ዘንድ ልክ እንደዚህ ይኹን፡፡

በወርሐ ክረምቱ በብዛትም በዓይነትም የተለያየ ዓይነት የዝናብ ጠብታዎችን ተቀብለናል፤ ብዙ ተከታታይ ትምህርቶችን ተምረናል፤ መንፈሳዊ አዝርእት ተዘርተዉብናል፤ የቅምጥልነት እሾኽም ቈርጠን ጥለናል፡፡

ስለዚህ ጾሙ በተፈታ ጊዜ የጾሙ ፍሬ ይከብበን ዘንድ፣ ከጾሙ የሰበሰብናቸውን መልካም ነገሮችም ጾሙን ራሱን እናስታውሰው ዘንድ የሰማነውን ነገር አጽንተን በመያዝ እንትጋ።

በእንተ ሐውልታት፣ ፲፰፥፩-፪
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አቤት የዚያን ጊዜ

አቤት የዚያን ጊዜ
ክርስቶስ ሲመጣ (፪)
ትንሹም ትልቁም (፫)
መድረሻውን ሲያጣ

ከምስራቅ ከምዕራብ
ከሰሜን ከደቡብ (፪)
አየራት/መላእክት/ ሲላኩ (፫)
መአትን ለማዝነብ፤
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ (፪)
የት ይሆን መድረሻው(፫)
የት ይሆን መንገዱ
አዝ
ጻድቃን በቀኝ በኩል
ኃጥአን በግራ (፪)
ሲነፋ መለከት (፫)
ሲደለቅም ዕንዚራ
ምድር ቀውጢ ስትሆን
አጽም ሲሰበሰብ (፪)
ሐፍረት ይይዘዋል (፫)
ሰው ለፍርድ ሲቀርብ
አዝ
ጩኸት ሲበረታ
የማይጠቅም ለቅሶ (፪)
እንደ ቍራ ጠቁሮ (፫)
ጽልመትን ተላብሶ
ገነትን ሲያገኙ
ጻድቃን በስራቸው (፪)
ኃጥአን ወደ ሲኦል (፫)
ተፈረደባቸው።

መዝሙር
ሊቀመዘምራን
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አለምን ዞሬ አየሁት

አለምን ዞሬ አየሁት
ሁሉን በተራ ቀመስኩት /2/
ፈፅሞ የለም /2/
ሰላም እንደ ልጂሽ ቤት

ሀብቴን ንብረቴን ጨረስኩና
ጉልበቴ ሁሉ ደከመና /2/
ጎስቋላ ሆንኩኝ /2/
ደካማ የሌለው ጤና

ስቃ አሳስቃ ተቀብላ
መልኳን አስውባ ተኳኩላ /2/
ዛሬ ጣላችኝ /2/
ይቺ አለም አይረባም ብላ

የትላንትናው ወዳጆቼ
ዛሬ ሲሆኑ ጠላቶቼ /2/
ባክኜ ቀረሁ /2/
በዓለም ላይ ተንከራትቼ

የአባቴ ቤት ሲናፍቀኝ
ፍቅሩ ምህረቱ ትዝ ሲለኝ
ሁሉንም ትቼ/2/
ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ

ልጁም አንድባል ባይገባኝ
ባሪያህ እሆን ዘንድ ቢፈቅድልኝ /2/
ጎስቋላ ልጁ ደካማ ልጁ
ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁ

እናቴ አንቺን ንቄ ትቼ
የአባቴን ቤት እረስቼ
ተሰቃየሁን ተንከራተትኩኝ
ልደሰት ባለም ገብቼ

አባቴ ሲያየኝ ተደስቶ
ጎረቤቶቹን ሁሉን ጠርቶ
ሠርጉን ደገስ /2/
የበደልኩትን ረስቶ

እስካሁን ድረስ በድያለው
አለም ደና ሁኝ አብቅቻለው
ወደ አባቴ ቤት/2/
ዳግመኛ ተመልሻለው

©ማኅበረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🔰የዲ/ን አቤል ተስፋዬ መዝሙሮች

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ደብረ ዘይት - ምጽዓተ እግዚእነ
🎤 በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

🙏ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሳማ ሰንበት

ወደ ሳማ ሰንበት-ዓመታዊው የመንፈሳዊ ጉዞ መዳረሻ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም በእኩለ ጾም መንፈሳዊ ተጓዦች ሊሳለሙበት የሚያቀኑትን ስፍራ በሀገራችን ከሚገኙ የመንፈሳዊ ቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ ነው ሲል ሳማ ሰንበትን እንዲህ ያስጎበኘናል፡፡
(ሔኖክ ስዮም) 

ይህ ጉዞ ከዛሬ ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት እንደጀመረ የሳማ ቀበሌ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ባለፉት ሃያ ዓመታት ከዓመት ዓመት ተአምር እየሆነ መጥቷል፡፡

ከአዲስ አበባ ምስራቃዊ አቅጣጫ የሚገኘውን ሳማ ሰንበት ልንጎበኝ እየሄድን ነው፡፡ ብቻችንን አይደለም እየሄድን ያለንው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አውቶቢሶችና ሚኒባሶች ሰው ሞልተው እንደኛው ጉዞ ላይ ናቸው፡፡ ዋና ዋና ለሚባሉ ከተሞች ማለትም ለአዲስ አበባ፣ ለቢሸፍቱ፣ ለሞጆ፣ ለአዳማ፣ ለዝዋይና ለአረርቲ የሚቀርብ በመሆኑ በዓመት አንዴ ከተሜዎች የማይቀሩበት መንፈሳዊ ስፍራ ሆኗል፡፡

በኦርቶዶክስ ምዕመናን ዘንድ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው የአብይ ጾም እኩሌት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ይህንን ቀን ደብረ ዘይትን ተሻግረው ሳማ ሰንበት የሚያሳልፉ መቶ ሺዎች ናቸው፡፡ ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ተጉዘን መጥተናል፡፡ ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ በሚባለው ወረዳ እንገኛለን፡፡ ይህቺ በዓመት አንድ ቀን ሰው መርፌ ሳያስጥል የሚጠቀጥቃት ስፍራ ሳማ ቀበሌ ውስጥ ትገኛለች፡፡

ሳማ ሰንበት ደርሰናል፡፡ ክቧ ቤተ ክርስቲያን ግንባሯ ላይ እንደሻሽ የጠመጠመችው በሚመስለው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም አሸብርቃለች፡፡ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ህንጻዋ ዘመናዊ ይሁን እንጂ ሳማ ሰንበት ከተተከለ ሶስት መቶ ዓመታትን ያለፈ እድሜ እንዳለው የአካባቢው አባቶች ይናገራሉ፡፡ ሰው ቁጥር የለውም፡፡ የቤተክርስቲያኗ ቅጥር ጊቢ እንዲህ መፈናፈኛ ያጣው ብዙው ሺ ከደጃፉ ቆሞ ነው፡፡

ሳማ ሰንበት በዓመት አንድ ግዜ የደብረ ዘይት በዓል የሚከበርባት ስፍራ ስትሆን እንደ አንዳንዶች ግምት ይሄ ስፍራ በዚህ መልኩ በዓለም ሁለተኛው ብቸኛ ደብረ ዘይት በድምቀት የሚከበርበት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ስፍራውን የተለዩ ካደረጉት ውስጥ ለመውረድ የሚያስፈራው የጠበሉ መንገድና ዋሻው የተለየ ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው፡፡

ከሳማ ሰንበት እየወጣን ነው፡፡ የሰው ብዛት መንገዳችንን ሰዓት የሚበላ ሊያደርገው ይችላል፡፡ የምንጃርን ሸንኮራ እየከሰከስን በምዕመናኑ ዝማሬ ተመስጠን ዳግም አዲስ አበባን አሰብናት፡፡ በሰላም ለቀዋት የወጡ አውቶቢሶች በሰላም ደጃፏን ርግጠው ተሳላሚዎቹ በየቤታቸው ይገቡ ዘንድ።

የቻላችሁ ነገ ሄዳችሁ አድራችሁ የበረከት ተካፋይ ሁኑ! አላሰብኩበትም አትበሉ ሁሉን ፈፃሚ እግዚአብሔር አምላክ ነው በችግር ምክንያት የማትችሉ ግን እርሱ በፈቀደ ግዜ እንዲያደርሳችሁ ጸልዩ!

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት

ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል።

ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው።

በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።

የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩

ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። "
" በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል።

ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸ ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል።

ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
" እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል " ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። "

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር

መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (2)
ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (2)

ፊቱን እየፀፉት/ እየተንገላታ (2)
በጦር እየወጉት /ይሰጣል ይቅርታ (2)
እነርሱ እየጠሉት/ እርሱ ይወዳቸዋል (2)
አስረው ሲጎትቱት/ ይከተላቸዋል (2)
#አዝ
ፃድቁን ሃጥእ ነው/ እውነትን ሃሰት (2)
እያሉ ሲጮሁ /ይሰቀል ይሙት (2)
እየመረመረው/ ፍጡር ፈጣሪን (2)
ክርስቶስን አስሮ/ ፈታው በርባንን (2)
#አዝ
ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ
በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ (2)
ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሃሞት (2)
ደሙን አፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት (2)
#አዝ
ግምጃን አለበሱት/ ቀሚሱን ገፈው (2)
በራሱም አኖሩ/ እሾህ ጎንጉነው (2)
የአይሁድ ንጉስ ሆይ/ እያሉ ዘበቱ (2)
ለህይወት ሆናቸው/ የክርስቶስ ሞቱ (2)

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🔰የመምህር ሲሳይ ደምሴ መዝሙሮች

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…
Подписаться на канал