🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ
ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።
ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ
ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።
በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን
🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌼ምስባክ
መስከረም 1/1/2017 ዓ.ም
🌼የዐውደ አመት ምስባክ🌼
ምስባክ ፦ መዝ 64 ÷ 11-13
ትርጉም ፦
🌼 ዘመን መለወጫ
አስቀድመን ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ማንነትና የዘመን መለወጫ መግቢያው ላይ በስሙ ስለመጠራቱ ተመልክተናል፡፡ ዘመን መለወጫ ደግሞ ለምን እንደተባለና ለምን መስከረም ወር ላይ እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲህ በማለት ያትታሉ፡፡
ሲያትቱም ብርሃናት/ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱም ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱንም ጠንቀቀው ቢቆጥሩት ፫፻፷፬ ቀናት ይሆናል፡፡ ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ ይላልና /መጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፵፱፡፡
በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድረገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡ /መጽሐፈ ኩፋሌ፡ ምዕ ፯ ቁጥር ፩/
በመሠረቱ ዘመን ተለወጠ ሲባል የሚለወጡት ወራቱ ብቻ አይደሉም፡፡ በወቅቱ የሚከሰቱት/የተከሰቱት/ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር /ገጠመኝ ሲሆን ወራቶቹ ግን ያው በየዓመቱ እየተፈራረቁ ይመጣሉ፡፡ ዘመን መለወጫ ላይ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡
ተማሪው ተምሮ ወደቀጣዩ ክፍል /ደረጃ/ የሚለወጥበት፣ ገበሬው የክረምትን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋወራት የሚቀበልበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሶ የፀሐይን ወራት የሚቀበልበት ሌላውም እንደዚያ ሆነው ወራቶቹ በዚያ ዘመን ያለው የተፈጥሮ ክስተቶች የሚለወጥበት ዘመን ተለወጠ እየተባለ ይነገራል፡፡
👉 በቀጣይ የዕንቁጣጣሽ ስያሜ አመጣጥ?
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ይቺን ዓመት ተወኝ
ከአመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እንዳጎሳቆልኲኝ
አውቃለሁ አምላኬ ፍሬን ለመቀበል እንዳመላለስኩሁህ
ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅዬ ደርቄ ጠበኩህ
ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም
ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አለየኝም ከዓለም
አዝ
የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ
የኔን ክፋት ተወው መላክህን ሰምተህ ይቺን ዓመት ተወኝ
አዝ
አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር
ብዙ ጊዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር
ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይሔን ጊዜ ሰምተኸኝ ነበር
ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮዬ አልፎ በአዲስ ተቀየረ
አዝ
ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ
እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ
የቃልህን ውሃ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ
ወደ ልቤ ሳይሰርግ ሕይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈሶ ቀረ
አዝ
ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ
በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ
ብዙ ጥቅስ አገኘው ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ
ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁኝ በበደል ተኝቼ
አዝ
ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርፀኝ ተማሪ ብሆንም
ይቺን ዓመት ተወኝ ደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም
እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ
ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መዓዛ እንዲደርሰኝ
አዝ
የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሽከመኝ አትሰልቸኝ አደራ
ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት አይሰሩ ስሰራ
አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ
አዝ
ቦታስ የሚይዙ ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸዉ
ልክ እንደ ዘንባባ የተንዥረገገ ተጋድሎ ፅድቃቸው
ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው
አዝ
እኔ አይደለሁም ቦታስ የሞትይዘው ያንተው እናት ናት
ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት
ይቺን ዓመት ተወኝ ከስሯ ሆናለው ባፈራ ምናልባት
አዝ
ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት
ሺ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንት ናት
ይሔ ዓመት አልፎ ዳግም ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ
እባክህን ጌታ ይቺን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ
ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሚ ጸጋ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጷጉሜ 5
ስለ ሹመቱም ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ እንጂ ቸልም አላለም።
🌼 አበባ አየሽ ወይ 🌼
እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2)
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ጌቶች አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ዘመን መጣ ብለን
አበባ አየሽ ወይ ለምለም(2)
ባልንጀሮቼ "
ግቡ በተራ "
በእግዚአብሔር መቅደስ "
በዚያች ተራራ "
እንድታደንቁ "
የአምላክን ሥራ "
ህይወት ያገኛል "
እርሱን የጠራ "
አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)
አበባ አየሽ ወይ ለምለም (2)
ክረምት አለፈ "
ጨለማው ጠፋ "
የመስቀሉ ቃል "
ሆነልን ደስታ "
እናገልግለው "
ቤቱ ገብተን "
ትንሽ ትልቁ "
ተሰልፈን "
አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)
አበባ አየሽ ወይ ለምለም(2)
ያንን ኩነኔ "
ዘመነ ፍዳ "
የሞቱ በራፍ "
ያ ምድረበዳ "
ልክ አንደ ክረምት "
ሄደ ተገፎ "
ፀሐይ ወጣልን "
ጨለማው አልፎ "
አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ (2)
አበባ አየሽ ወይ ለምለም(2)
ይኸው መስከረም "
ይኸው ፀሐይ "
ንጉሡ ወርዶ "
ከላይ ሰማይ "
አውደ ዓመት ሆነ "
ደስታ ሰላም "
ፍቅር ሲገለጥ "
በአርያም "
አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)
አበባ አየሽ ወይ ለምለም(2)
ይኸው አበባ "
ለምለም ቄጤማ "
አዲሱ ዘመን "
አምጥቷልና "
በሩን ክፈቱ "
መኳንንቶቹ "
የክብር ንጉሥ "
ይግባ ቤታችሁ "
አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)
አበባ አየሽ ወይ ለምለም(2)
ቤታችሁ ይሙላ "
ሰላም ደስታ "
ሰጥቷችሁ እርሱ "
የሁሉ ጌታ "
ከዘመን ዘመን "
ያሸጋግራችሁ "
የሽበትን ዘር "
ይሸልማችሁ "
አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ
ይሸታል ዶሮ ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ
አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ
ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጎሳ ልብየ
ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ/2/
ወአነ አይድ ቅዳሴሃ ለማርያም/2/
እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለሁ
እንደ አባቴ ዳዊት በበገና እዘምራለሁ
ቀን ከሌሊት ሳልል ለምስጋና እተጋለሁ
የኃጢአቴ ቁስል እንዲፈወስ እጮሃለሁ
ምርኩዜ ነሽና እመቤቴ በአንቺ እመካለሁ
አዝ
አዝ
አዝ
ጷጉሜ 4
እኛ የወንድማችንን በደል ብንሰውር እግዚአብሔርም በደላችንን ይሠውርልናል።
✞ ሩፋኤል ብዬ ✞
ሩፋኤል ብዬ ስጠራው ምስጢሬን ሁሉ ሳወራው
ትላንት የረዳኝ ጸሎትህ ዛሬም ይድረሰኝ ለልጅህ
ሩፋኤል ብዬ አንደበቴ ለምዶት ስምህን
ሩፋኤል ብዬ ልጅነቴ ቀምሶት ፍቅርህን
ሩፋኤል ብዬ የህይወቴ ቅጥር ሲላላ
ነፍሴ ትጮሀለች ሩፋኤል ሩፋኤል ብላ አዝ
ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት
ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት
ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ
ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ
አዝ
ሩፋኤል ብዬ ህመሜ እንዳይጸና ክፋቱ
ሩፋኤል ብዬ መድሐኒት እንዲሆን ሀሞቱ
ሩፋኤል ብዬ ካጠገቤ እንዳትርቅ ከጎኔ
ትዳሬ እንዲጸና ሩፋኤል እንዲበራ አይኔ
አዝ
ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት
ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት
ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ
ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ
ዘማሪ ሚኪያስ መንገሻ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ፈታሔ ማሕፀን
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ቅዱሳን መላእክት ምእመናን ለመርዳት ለማገልገል ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት አይደሉምን? ( ዕብ ፩÷፲፬) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም "የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ"( ራእዩ ለዮሐንስ ፰÷፬) በማለት ተናግሯል።
ቅዱሳን መላእክት ያለማያቋረጥ ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ለተልእኮ ይፋጠናሉ። የሰውን ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ምሕረት ወደ ሰው አድርሰው በእምነት ያጸናሉ። "በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው" (ራእ. ፰÷፪) የሚለው የሚያስረዳን ለተልእኮ መፋጠናቸውን ነው። ሄኖክም “በሰው ሰውነት ላይ የተሾሙ ከከበሩ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው” (ሄኖ.፮÷፩-፵፪) ብሏል።
የሰዎችን ልመና ወደ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና በረከት ወደ ሰው የሚወርድባት ዕለት"ርኅወተ ሰማይ” ትባላለች። ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች። እንዲህ የሚባለው በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት የሚያሳርጉበት፣ አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንጂ።
ቅዱስ ሩፋኤል ልቡናን ደስ የሚያሰኝ፣ ባለ መድኃኒት፣ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ ቍልፍ የተሰጠው፣ የሴቶችን ማሕጸን የሚፈታና ሳይጨነቁ እንዲወልዱ ምጥን የሚያቀል መልአክ ነው። "ለሰብእ ወለእንሰ ፈታሔ ማሕጸኖሙ አንተ" እንዲል። የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረና ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ መላእክት መካከል አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ "(ጦቢያ ፲፪÷፲፭) የሚለው የሚያስገነዝበው ተራዳኢነታቸውን፣ ባለሟልነታቸውን፣ አማላጅነታቸውን ነው።
ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ"(ሐዋ. ፲÷፬) የሚለው የመላእክትን አገልግሎት የሚገልጥ ነው። መላእክት ሰዎችን ይራዳሉ፣ የሰውን ጸሎት ያሳርጋሉ፣ ያማልዱሉ፣ ሰዎችን ከመከራ ነጥቀው ያወጣሉ። "የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህን ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ፣ እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው። ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ። ስበክ እንዲህም በል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል (ዘካ፣ ፩÷፲፪÷፲፬) የሚለው አማላጅነታቸውን የሚገልጥ የማጽናኛ ቃል ነው።
ጦቢያና መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱ ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው። መልአኩም ለጦቢያ አባትህ ከዘመዶችህ ወገን አግባ ያለህን ቃል አስብ አለው። ራጉኤልም ልጁ ሣራን ለጦቢያ አጋባት። ተመግበውም ከጨረሱ በኋላ ጦቢያን ወደ እርሷ አገቡት፤ ወደ እርሷም በገባ ጊዜ የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤልን ነገር አሰበ፤ የዕጣን እራሪ ወሰደ፤ ከዚያም ዓሣ ከልቡና ከጉበቱ ጨምሮ አጤሰው። ሽታውም ያን ጋኔን በሸተተው ጊዜ እስከ ላይኛው ግብፅ አውራጃ ድረስ ሸሸ። መልአኩም ጋኔኑን አሰረው( ጦቢ ፰÷፩) የተባለው የሚያስረዳን የመላእክትን ተራዳኢነት ነው።
ጦቢያ የሰርጉን በዓል በጨረሰ ጊዜ ወደ አባቱ ቤት ከሚስቱ ከሣራና ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር ተመለሱ። ሩፋኤልም አለው፥ "ያባትህ ዐይኖች እንዲበሩ አውቃለሁ፤ አንተ ግን ያን ሐሞት ያባትህ ዓይን ኳለው፤ በተኳለም ጊዜ ብልዙ ከአይኑ ይወጣል በደህናም ያያል። ጦቢያም የአባቱን አይን ኳለው ዓይኑም በራለት”( ጦቢ ፲፩÷፮) ተብሎ እንደተነገረው እግዚአብሔር ከዚህ ክፉ ወረርሽኝ ጠብቆን በሰላም በጤንነት ለሚመጣው ዓመት ያድርሰን። የጦቢትን ዓይን ያበራውን የቅዱስ ሩፋኤልን ዓመታዊ በዓል አክብረን በረከት ለማግኘት ያብቃን።አሜን!!
ዲ/ን ተመስገን ዘገየ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጳጉሜን
ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡
ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡
የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌼ምስባክ
ምስባክ ፦ መዝ 141÷ 6-8
ትርጉም ፦
🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?
ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡
በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡
ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡
ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡
አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ይችን አመት ተወኝ
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ።
🌼ዘመን ተሰጠን🌼
ዘመን ተሰጠን ለምስጋና
ዘመን ተሰጠን ለውዳሴ
ተመስገን ሥላሴ
ቸርነትን ሰጠን ዘመን ለፍስሐ
ይቺም እድሜ ለእርቅነች ለንስሀ
ጥበባችን መቼ ሆነ እውቀታችን
ምሕረትህ በዝቶልን ነው መቆማችን
ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት
አዝ🌼
አዝ🌼
አዝ🌼
🌼 አበባ አየሽ ወይ 🌼
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ።
🌼 መስከረም 1
ሃይማኖታዊ መሠረት
ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን ሲጽፍ «የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጅ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ» ተብሎ በኢሳይያስ እንደ ተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ላይ ተነሥቶ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ ለኃጢአት ሥርየት እየሰበከ መጣ ብሎ በዘመነ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ገልጾታል።
/የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፵፤ ትንቢተ ኢሳይያስምዕ ፵ ቁ ፫ - ፬/።
የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ ሆኖ መገኘቱን በመረዳት የቤተክርስቲያን አበው የበዓላቱን ድንጋጌ በወሰኑበት ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል የኢትዮጵያ ርዕሰ ዓውደ ዓመት በሚሆን መስከረም ፩ ቀን እንዲከበር በየዓመቱ የዘመኑ መጀመሪያ በእርሱ ስም እንዲጠራ አባቶች ደንግገዋል፡፡ / ድርሳነ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1ጠ 3/
ይህንንም በዓል አባቶቻችን በርእሰ ዓውደ ዓመት ማክበር እንደሚገባ አስበው ያደረጉት ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ሆኖ አይደለም፡፡ ለአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወይም ርእሰ ዓውደ ዓመት «ቅዱስ ዮሐንስ» ይባላል፡፡
መጽሐፈ ስንክሳር የዓመቱን መጀመሪያ /መስከረምን/ ሲያትት «ይህ የመስከረም ወር የተባረከ ነው እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው በማለት ያስረዳል፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከመስከረም አንድ ቀን ጀምሮ ቀኑ እየጎደለ ይሔዳል፡፡
👉 ከዚህ በመቀጠል በዓሉ በተለያየ ስያሜ ስለመጠራቱና ትርጓሜያቸውን እንመለከታለን፡፡
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የሰማይም የምድርም ጌታ
የሰማይም የምድርም ጌታ
በዝቶልናል እጅግ ስጦታ
በጎነትህ ቸርነትህ
እረድቶናል ክቡር ስምህ። (2)
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
✞ ቅዱስ ሩፋኤል ✞
አዝ
አዝ
አዝ
ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ። ጦቢት፲፪፥፲፭
ሩፋኤል ይቅር በለኝ
አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ
ከልጆች ጋር ተሯሩጬ
በጠበልህ እየታጠብኩ
የውኃ ጨው እየቀመስኩ
ሩፋኤል አሳድገኝ
እንደ ታላቆቼ አድርገኝ
ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ
ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ
ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ
ጠበል ሲወርድ ተሸሸግሁኝ
ከበረከትህ ሸሸሁኝ
ከቡራኬህ አመለጥኩኝ
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ
ስላበቃ ልጅነቴ
በቆሸሸ ሰውነቴ
በረከሰ ማንነቴ
እንዳላረክስ ጠበልህን
ተጠለልኩት ጥምቀትህን
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጳጉሜ 3
ርኅወተ ሰማይ (ሰመይ የሚከፈትባት)
ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
ዳግመኛም ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ ናት።
ቀዋምያን
ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት
ኡራኤል ወሩፋኤል/2/
ይትፌነዉ ለሣህል/2/
እምኀበ ልኡል/2/
ትርጉም፦
ለነፍሳት የቆሙ እነዚህ መላእክት
ኡራኤልና ሩፋኤል/2/
ከልኡል ዘንድ ለይቅርታ/2/
ይላካሉ ከልኡል/2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
📣የዛሬው ምሽት ስለ ነገረ ማርያም የነበረን ትምህርት በእዚህ ላይ እናበቃለን📣
ቅዳሜ ምሽትም በተመሳሳይ ሰዓት 2:00 ላይ ቀጣዩን ክፍል የምንቀጥል ይሆናል። ሁላችሁም ቅዳሜ 2:00 ላይ ጠብቁን።
👉እስከ አሁን የነበረውን ትምህርት ከወደዳችሁት በኮመንት ላይ አሳውቁን።
ከ8,000 ሰው በላይ ይሄንን ቻናል በአንድ ቀን ውስጥ እየተመለከተው ግን ለምትወዷቸው ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችሁ የእኛን ቻናል እንዲቀላቀሉ ለምን እንደማትልኩላቸው አላውቅም።
🤲እባካችሁ ድንግል ማርያምን አትወዷትም? ጓደኞቻችሁስ በደንብ ፍቅሯ እንዲያድርባቸው አትፈልጉም? ለምን አትልኩላቸውም?
አሁን ድንግል ማርያምን ከወደዳችኋት ለ20-30 ጓደኞቻችሁ አሁን በኃላፊነት የቻናላችንን ሊንክ ላኩላቸው አሁን። ከእዛም ከላካችሁ በኋላ ልከናል ብላችሁ ኮመንት አድርጉ🙏🙏🙏
ሊንኩ 👉 /channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur