ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ጥምቀት መግቢያ
👉ለምን ምሥጢር ተባለ
👉ወንዶች በ40 ሴቶች በ80 ቀን ለምን ይጠመቃሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ በእዚህ አይነት መልኩ አጠናቀናል።

ጥያቄ ካላችሁ ያልገባችሁ ነገር ካለ

@zmaredawit_messengerbot

በዚህ ውስጥ በመግባት ጥያቄያችሁን ልትልኩልን ትችላላችሁ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝

የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች ዛሬ ተከታታይ ትምህርታችንን ክፍል ሁለት እንጀምራለን።

👉 ዛሬ ለማየት የምንሞክረው ርዕስ ምሥጢረ ሥላሴ ይሆናል።

ስለዚህ ባለፈው በላክንላችሁ ትምህርተ ተዋሕዶ በሚባለው አፕሊኬሽን በመክፈት አእማደ ምሥጢራት የሚለውን አምድ በመክፈት ምሥጢረ ሥላሴን ታነቡ ዘንድ እንጠይቃለን።

አሁን ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ማጠቃለያ ትምህርት በድምጽ የምንልክ ይሆናል ተከታተሉ።

ይህንን መልእክት ያያችሁ እና ለመማር እና ለማዳመጥ ዝግጁ የሆናችሁ

👍 ይህንን ምልክት ላኩልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼አዲሱን አመት በገና ክራር እና መሰንቆ መማር ይፈልጋሉ?🌼

👉እንኳን ደስ አለዎት ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ የ2016 የትምህርት መርኃ-ግብሮችን አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ ነው።

👉በአዲስ አመት የሚጀመር
⏱የስድስት ወር
⏱የሦስት ወር የትምህርት መርኃ-ግብር ያዘጋጀን ሲሆን

የመመዝገቢያ ቀን ከጷግሜ 6-መስከረም 4 ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው መስከረም 5 ቅዳሜ ዕለት ይሆናል። ይደውሉ ይመዝገቡ


   📒 ለመመዝገብ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ወይም በቴሌግራም አካውንታችን በውስጥ መስመር ልታወሩን ትችላላችሁ።

☎️ 0965083251
0956861468
    0912085085

ወይም በቴሌግራም
   @Orthodoxtewahed0
ልታዋሩን ትችላላችሁ ቶሎ በመመዝገብ በመንፈሳዊ መሳሪያ ጊዜዎትን ይጠቀሙ።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አዲስ መጽሐፍ በገበያላይ

#ኦርታዶክሳዊ_ወጣት_እና_ፈተናዎቹ

#ዮጋ በስፊው ተዳሰዋል
ዲን ዳግማዊ ሰሎሞን አዘጋጅቶታል።ወንድሜ ዲን ዳግማዊ
#ኦርቶዶክስ_መልስ_ናት የሚል መጽሐፍ አስነብቦን ነበር።

የጀርባ ዋጋ
#320ብር
ዋና አከፋፋይ
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store
በCBE 1365 ለሚያስገቡ 250ብር ብቻ።

#አንዱን_ርዕስ_እንጋብዛችሁ
#ዘፈን_ለማቆም_ምን_ላድርግ? (የብዝዎቻችን_ጥያቄ_ነው አይደል?)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.facebook.com/groups/271884238121590/permalink/647188570591153/?mibextid=Nif5oz

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_በ0912044752_0925421700_ይደውሉ!
/channel/BetMetsahfte

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

3. ቤተ ክርስቲያናችን የመንፈሳዊ ኮሌጆቿን ቁጥር ከፍ በማድረግ የአገልጋይ መምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ባላት እቅድ መሠረት ተጠንተው ከቀረቡት መካከል በ2016 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ፣ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ሁለት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ፣ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት ርእሰ ከተማ ውስጥ ለሚገኙት የምስክር ጉባኤ ቤቶች በኮሌጅ ደረጃ በጀት እንዲመደብላቸው እና በከንባታ ሐድያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሆሣዕና ከተማ ላይ አንድ የካህናት ማሠልጠኛ እንዲከፈት ጉባኤው ወስኗል፡፡

4. ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ እየደረሱባት ያሉት ከፍተኛ የሆኑ ፈተናዎችን ተቋቁማ ሕልውናዋን አስከብራ መቀጠል ትችል ዘንድ ፡-

ሀ. ውስጣዊ ችግሮቻችን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በጠበቀ በውይይት እንዲፈቱ፣

ለ. ውጫዊ ችግሮችንና የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ በችግሮቹ ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመነጋገር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና የቤተ ክርስቲያናችን መብትና ሕልውና ተጠብቆ እንዲቀጥል እንዲደረግ፣

ሐ. ለቤተ ክርስቲያናችን ሕልውና አደጋ የሆኑና ሊሆኑ የሚችሉ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን አስመልክቶ በአግባቡ ተጠንተውናበማስረጃ ተተንትነው ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

5. ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን በእጅጉ አሳዝኖታል፡፡ በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራልን የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላችሁ በሁሉም አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ የበኩላችሁን ሚና በመወጣት እናት አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአደራ ጭምር በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

6. በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተከሠተ ያለው ችግርና ፈተና የሚወገደው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በሕብረት ለችግሮቹ መፈታት ድርሻ እንዳለን አውቀን እንደየእምነታችን አስተምህሮ በጸሎትና በምሕላ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር በንስሓ መመለስ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ስለ ሀገራችን ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸምና መላው ሕዝበ ክርስቲያንም በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

7. የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክና ለሀገረ መንግስት ምሥረታና እድገት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በማዕከል ደረጃ በማስረጃ አስደግፎ በመጻፍና በማደራጀት ትውልዱ እንዲረዳው በማድረግ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሕልውና አደጋ የሆነውን የሐሰት ትርክት መከላከል ይቻል ዘንድ የዝግጅት ሥራው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል በሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ተቆጣጣሪነት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና የታሪክ ተመራማሪዎችን በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡

8. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎና ሚና በተመለከተ ጉባኤው በስፋት የተወያየ ሲሆን ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ ችግራችንን እንደሚፈታና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚነገሩትን የሐሰት ትርክቶች ሁሉ የሚታረሙበት እንደሚሆን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖረን ተሳትፎና ሚና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈጸም ሆኖ የምክክር ኮሚሽኑም ይህን የቤተ ክርስቲያናችን እቅድ በመርሐግብሩ በማካተት ቤተ ክርስቲያናችን የድርሻዋን እንድትወጣ እድሉን እንዲያመቻችልን ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

9. የመረጃ ቋት መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሁሉም ክልል አህጉረ ስብከት ደረጃ በማቋቋም እና እለት እለት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚከሰቱትን ችግሮችና የመብት ጥሰቶች በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ ለዋናው ማዕከል የመረጃ ቋት በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ በአንዱ ቦታ ችግር ሲደርስ በመላ ሀገሪቱ እና በውጭው ክፍለ ዓለማት ባሉት አህጉረ ስብከት በአንድነት ድምፅ መሆን ይቻል ዘንድ ተጠሪነታቸው ለዋናው ማዕከል የሆኑ የመረጃ ቋት ማዕከላት በሁሉም አህጉረ ስብከት ተቋቁመው ወደሥራ እንዲገቡ ጉባኤው ወስኗል፡፡

10. የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ የሚዳሰሱና እና የማይዳሰሱ ቅርሶችንና በአጠቃላይ ንዋየ ቅድሳቶቻችን ግለሰቦች እና ተቋማት በሕገወጥ መንገድ አትመውና አሳትመው በማሠራጨትና ትክክለኛ ቅጅውን አዛብቶ በማተም ቤተ ክርስቲያናችን ለሐሰተኛ ትርክት እንድትዳረግ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈጸመባት መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በኩል የተጀመረው የአዕምሯዊ ንብረት ምዝገባ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም እንዲከበር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት አህጉረ ስብከት ሥር የተቋቋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚተዳደሩበት እራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ባለመኖሩ በመዋቅራዊ አስተዳደራችን ላይ ከፍተኛ ክፍተት ሲፈጥር የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ ለውጭው ክፍለ ዓለማት አህጉረ ስብከት እና አብያተ ክርስቲያናት እራሱን የቻለ መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ የፀደቀ በመሆኑ በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት ሁሉም አህጉረ ስብከትና አብያተ ክርስቲያናት በጸደቀው መተዳደሪያ ደንብ ብቻ ሥራቸውንና አገልግሎታቸውን እንዲያከናውኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

12. የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኮሌጆች ወጥ የሆነ የጋራ መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖራቸው በማሰብ ጉባኤው አስቀድሞ ተዘጋጅ እንዲቀርብ ባዘዘው መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ መርምሮ በማጽደቅ በሁሉም በተቋቋሙትም ሆነ ወደፊት በሚቋቋሙት ኮሌጆች ሥራ ላይ እንዲውል ጉባኤው ወስኗል፡፡

13. ገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት፣ የአብነት መምህራን እና ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአጠቃላይ ክብረ ክህነት እና ትምህርተ ኖሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡

14. የቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ፣ ተቋማዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ መብቶች መከበርና የእምነት ነጻነታችንን እና የምእመናንን ደኅንነት በሕግ አግባብ ማስከበር ይቻል ዘንድ ልክ እንደ ዋናው መሥሪያ ቤት በሁሉም ክልሎች ውስጥ ባሉት አህጉረ ስብከት የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ጉባኤው ወስኗል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የ2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስተዳደራዊ ጉዳይን የያዘ የመሪ እቅድ ተጨማሪ ግብዓት ተጨምሮበት ለግንቦት ርክበ ካህናት እንዲቀርብ መወሰኑን ገለጹ፡፡ በጸደቁ አጀንዳዎች ላይ ላለፈው አንድ ሳምንት ሲወያይ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ በማድረግ መግባባት በሰፈነበት ሁኔታ ጉባኤውን ማጠናቀቁን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በማጠናቀቂያው በሕግ በመሪ እቅድ ትግበራ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች ጥናት ላቀረቡ እና ማብራሪያ ለሰጡ ባለሙያዎች በብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችንአስመልክቶ ቅዱስነታቸው ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ እንደሚሰጡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ የኢኦተቤክ ቴቪ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንደምን አመሻችሁ የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን
ዛሬም የቅዳሴ ትምህርታችንን እንቀጥላለን።

በደንብ እየተለማመዳችሁ እየቻላችሁት እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። የከበዳችሁ ክፍል ካለ አሳውቁን በደንብ እንዲከለስ።

✝የቅዳሴ ትምህርቱን በደንብ እየተለማመዳችሁ ከሆነ "እየተለማመድን" ነው ብላችሀለ ቴክስት ላኩ አሁን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለሰ/ት/ቤቶች መማሪያነት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ተዘጋጅቶ ወደ እንቅሰቃሴ እየገባ በሚገኘው የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ ለ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ  ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ቀርቧል።

ማብራሪያውን የሰጡት የአገር አቀፍ ሰ/ት/ቤት አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው እንደተናገሩት የሰ/ት/ቤች ሥርዓተ ትምህርትን ለመቅረጽ እጅግ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል።

አሁን ተቀርጾ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚጠበቀው ሥርዓተ ትምህርት 6 ዋና ርእሶች እና አንድ ደጋፊ ርእስ ያለው ሲሆን ለዘንድሮው ዓመት ትግበራ እንዲሆን 42 መጽሐፍት ታትመው እና በሊቃውንት ጉባኤ ተገምግሞ ዝግጁ ሆኗል።

አቅራቢው በተጨማሪ እንደገለጹት ሥርዓተ ትምህርቱ አሁን ያለው ትውልድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተረድቶ መንፈሳዊ ወጣት እንዲሆን የሚያስችል ዕውቀትን የያዘ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዳሉት አሁን ያለውን ትውልድ ለማዳን ሰ/ት/ቤትን ማጠናከር የግድ ይለናል ብለዋል።

በተጨማሪም ሁሉም አኅጉረ ስብከቶች ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልእክት አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​እንኳን #አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!

አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል።

አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ።

አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ

ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው።

በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር።

በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል።

ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል።

ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል።

ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል።

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ።

#ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14 
ለወዳጅዎ ያጋሩ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🧰ሳጥኑን ክፈተው🗃

አንድ ለማኝ በአንድ ስፍራ ላይ ከሰላሳ ዓመታት በላይ ቁጭ ብሎ ምጽዋትን ከአላፊ አግዳሚው ይማጸን ነበር። አንድ ቀን አንድ ጸጉረ ልውጥ በአጠገቡ ሲያልፍ በእጁ ላይ ያለችን በእድሜ ብዛት የነተበችን ባርኔጣ ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከቀኝ ወደ ግራ እያወዛወዘ እንዲመጸውተው ድምጹን ከፍ አድርጎ ለመነው። ጸጉረ ልውጡ ሰውዬም ቆም ብሎ “አንዳች የምሰጥህ ነገር የለኝም” አለው።

ቀጥሎም ጠየቀው “የተቀመጥክበት ምንድነው?” በማለት...ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሠላም የተወደዳችሁ እህት ወንድሞቼ።

እስከ አሁን የተላኩትን የቅዳሴ ክፍሎች ተለማመዳችኋቸው?

የከበዳችሁ ካለ በኮመንት ላይ አስቀምጡልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ላልመጣላችሁ ስነ ልቦናችሁን የሚያጠነክር ድንቅ ጽሑፍ

ውድቀት

✍️ Bini Girmachew  ( ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን )
                               
ከውድቀት አንድ እውነት ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ከመከራ መማር እንደምንችል ነው። ነገር ግን እያንዳንዱ ውድቀት ተመጣጣኝ የሆነ አዎንታዊ አፀፋ እንዳለው የሚያውቁ ጥቂቶች ብቻ ናቸው።

በጊዜያዊ ሽንፈት እና በውድቀት...ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​#ቃል_ኪዳንዋ

ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችን ምድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማዕቷ ለትውልድ የሚተላለፍ የዘላለም ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡

መታሰብያዋን ያደረገ ስሟን የጠራ፣ በስሟ ቤተ ክርስትያን የሠራ፣ የተራበውን በስሟ ያበላ፣ የተጠማውን በስሟ ያጠጣ፣ የገድሏን መጽሐፍ የጻፈውን፣ ያጻፈውን፣ ያነበበውን፣ የተረጎመውን፣ ሰምቶም በልቡ ያኖረውን፣ የልቡን መሻት እንደሚፈጽምለት እና በመንግስተ ሰማያት እንደ እርሷ የክብር አክሊል እንደሚያቀዳጀው፤ ሥዕሏን አሥሎ በክብር በቤቱ አስቀምጦ ሽቶ እየረጨ ቢጸልይበት ጸሎቱ እንደሚሰማና ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ እንደሚያሸተው፣ ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በስሟ የሰየመ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስም እንደሚሰጣቸው፣ ዕጣን፣ ስንዴና መብራትን፣ ልብሰ ተክህኖ፣ መጋረጃ ቢሰጥ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስ እንደሚለብስ፣ ያለ ወቀሳ ያለከሳ ባህረ ሲኦልን ተሻግሮ መንግስቱን እንደሚወርስ ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡

፨ ሰማዕቷን ከሌሎች ቅዱሳን ልዩ የሚያደርጋት ታሪክ ፨

በግብጽ አገር አርባ ዓመታት የነገሠ ባለ 12 ክንፉ ብጹአዊ አቡነ ሙሴ የሚባሉ ታላቅ ጻድቅ አሉ፡፡ እኝህ ጻድቅ ከንግስና ወደ ምንኩስና የተሸጋገሩ መንፈሳዊ አርበኛ ናቸው፡፡

ታድያ እኝህ ጻድቅ የቅዱሳን፣ የሰማዕታትን ዓጽም እሰበሰቡ ደግላቸውን እያጻፉ፣ ቤተ ክርስትያን በመስራት፣ ታቦታቸውን በማክበር፣ በበዓላቸውም ቀን ይቀድሱ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ታቦት ለማሰናዳት፣ ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ በወርቅ የተለበጠ እና በላዩ በሮማይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት ያገኛሉ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰቡ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመሩ፡፡ ግን የቅድስት አርሴማን ግድልና የሞቷን ዜና አላገኙም። ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች እና የሰማዕትነቷን ሥራ ያስረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አመለከቱ፡፡

ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለአቡነ ሙሴ ተገልጦ ‹‹ብጽአዊ ሙሴ ሆይ የብጽእት አርሴማን ሥራ እነግርህ ዘንድ ስማ፡፡ ይህቺ ሰማዕት ገና አልተጸነሰችም፣ አልተወለደችም፤ በወርቅ ዓምድ በሕይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ፡፡ ነብዩ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይጻፋል እንዳለ እርሷም በኋለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች፤ በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል፡፡

ተአምሯ የሚነገረው በኢትዮጲያ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰብያ መጥራት አትተው፡፡ ጽላትዋም ከአንተ ጋር ይኑር፡፡ የመቅደስዋም ህንጻ በህንጻህ ቦታ ጎን ይኑር፡፡ ስምህ በተጠራበትም የስሟ መታሰብያ ይጠራል›› ብሎ መልአኩ ወደ ላከው እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡

አቡነ ሙሴም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ ሰማዕቷም ገና ሳትወለድ በፊት እንደ እመቤታችን በእግዚአብሔር ህሌና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ እኛም እንደ እንደ ጻድቁ አቡነ ሙሴ በሰማዕቷ ጸሎት እና ቃል ኪዳን ልንጠቀምባት ይገባል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዮንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶም ስለ ዮፍታሔ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነብያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና›› ነው ያለው፡፡ /ዕብ 11÷32/ እኔም ስለ እዚች ድንቅ ብርቅ እና ከወርቅ በላይ የከበረች ከአልማዝም በላይ የተወደደች ስለ ሰማዕቷ ለመተረክ ጊዜ ስለማይበቃን እዚህ ላይ ይብቃን፡፡

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ጸሎት፣በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

በሰማዕቷ በቅድስት አርሴማ ስም ‹‹ሼር›› አድርገው ለወዳጆ ይዘክሩ፡፡

መስከረም 29/1/12 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይሄንን የቅዳሴ ትምህርት ምዕመናን ተለማመዱት ቅዳሴ መማር ለምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን የተዘጋጀ ነው።

ለምታውቋቸው ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችሁ የዝማሬ ዳዊትን ቻናል ሊንክ ላኩላቸው።ከእኛ ጋር በሕብረት ሆነው ቅዳሴውን ይማሩ እና እኩል ያስቀድሱ ዘንድ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝

ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች?
እስከ አሁን ድረስ ምሥጢረ ሥላሴ እና ምሥጢረ ሥጋዌን ያየን ሲሆን በእነዚህ ርዕሶች ላይ ጥያቄዎች ካላችሁ አሁን መጠየቅ ትችላላችሁ። ሰብስበን መልስ እንሰጣለን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አምስቱ አእማደ ምሥጢራት መግቢያ ፩

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሉቃስ ወንጌል ሲነበብ የምንለው ይህንን ይሆናል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቅዳሴ ትምህርታችን ከክፍል 40-49
ተለማመዱት የከበዳችሁ ካለ በጥያቄ መጠየቂያው በኩል ላኩልን።

ለምትወዷቸው ጓደኞቻችሁ ቅዳሴ ይማሩ ዘንድ ላኩላቸው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

15. ወጣቱ ትውልድ በእምነቱ ጸንቶና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ በእውቀትና በሥነምግባር ይታነጽ ዘንድ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር እና አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡

16. የ2016 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀትን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል ተዘጋጅቶ የቀረበውን የበጀት ድልድል ጉባኤው መርምሮ በማጽደቅ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

17. የቤተ ክርስቲያናችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱት እና የልማት ተቋማት የሚጠናከሩት ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር እና በእቅድ ተደግፎ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የሀብትና የንብረት አስተዳደር ማስፈን ሲችል መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡

በመሆኑም በባለፈው ጉባኤ የጸደቀው የ10 ዓመት የመሪ እቅድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት የመሪ ዕቅዱ አፈጻጸም እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን


አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻውን ሥርዓተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
በመሆኑም ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-
1. የ2016 ዓ.ም. የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ያሳለፈውን የጋራ የአቋም መግለጫ በመመርመርና አስፈላጊውን ማሻሻያዎች በማድረግ የበጀት ዓመቱ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መመሪያ እንዲሆን ጉባኤው አጽድቆታል፡፡

2. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀቱን የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን መወጣት ትችል ዘንድ በአዲስ እንዲደራጁ ተጠንተው የቀረቡትን የአህጉረ ስብከት ይደራጅልን ጥያቄዎችን በመመርመር፡-
ሀ. የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣
ለ. የሰሜን ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት
ሐ. የጎፋና ባስኬቶ ዞን ሀገረ ስብከት
መ. የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት እራሳቸውን ችለው ሀገረ ስብከት ሆነው ተደራጅተው እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቅዳሴ ቀጣዩ ክፍል እነሆ👇👇👇

የከበዳችሁ ካለ ንገሩን። በደንብ ተለማመዱት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች።
የቅዳሴ ትምህርታችንን በደንብ እየተከታተላችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን።

🙏ለሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን ለምታውቋቸው ቶሎ ከእኛ ጋር ሆነው የቅዳሴውን ትምህርት ተምረው እኩል ከእኛ ጋር ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የሚባለው ሳይገባቸው ተሰላችተው ወደ 🏠 ከሚመለሱ።

አሁን እናንተ ይሄንን ቻናላችንን ለምታውቁት ሰው ሁሉ ስልካችሁ ላይ ላለው ሰው ሁሉ እንዲቀላቀሉን ሊንኩን ልካቸውላቸው ከእኛ ጋር በፍቅር ይማሩ ዘንድ በትኅትና እንጠይቃለን። ወደ ቻናላችን እንዲቀላቀሉ ይህንን ሊንክ ላኩላቸው

/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የመጀመሪያው ጸልዩ የሚለውን ዲያቆኑ ሲል ምዕመናን ምን እንላለን የሚለውን አዳምጡ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "፪ኛ ሳምንት" "በዓለ አብርሃ ወአጽብሃ ወዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ" "ጥቅምት ፬"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤ መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢት ዓለም፤ ወልጡ አምልኮትየ በፀጋክሙ ፍፁም፤ እምአምልኮ ጣኦት ግሉፍ አሐዱ ድርኅም።

ዚቅ
ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎሙ፤ ናርዶስ ፀገየ ውስተ አፉሆሙ።

ማኅሌተ ጽጌ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ ለእረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን (ጽላተ ኪዳን)፤ ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን።

ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለእረፍት ጽላተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ ኅቡረ ንትፈሣሕ ዮም በዛቲ ዕለት።

ማኅሌተ ጽጌ
ፄነወኒ ተአምርኪ ሶበ ይነፍሑ ነፋሳት፤ ከመ ጼና ገነት ዘይጼኑ እምርኁቅ ፍኖት፤ መዓዛ አፈዋት ማርያም ወጽጌ መንግሥት ቡርክት፤ ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት፤ ጽጌ ጽጌ ጽጌ አሮን ዘክህነት።

ወረብ
ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት/፪/
መዓዛ አፈዋት ማርያም መዓዛ አፈዋት ወጽጌ መንግሥት/፪/

ዓዲ (ወይም)
ወረብ
ጼነወኒ ተአምርኪ ነፋሳት ሶበ ይነፍሑ/፪/
መዓዛ አፈዋት ማርያም ወጽጌ መንግሥት ጽጌ መንግሥት አብርሃ ወአጽብሃ/፪/

ዚቅ
ሠርፀ መንግሥት ዘእምሥርወ ዕሤይ፤ ወጽጌ ንጽሕት ዘእምጒንደ ዳዊት፤ ወብኪ ይትሜዓዙ ኲሎሙ ቅዱሳን።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ
ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
"ወንዒ ሠናይትየ"/፪/ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/

ዚቅ
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ፤ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፤ ወኲሉ ነገራ በሰላም።

ዓዲ (ወይም)
ወትወጽእ እምግበበ አናብስት፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ኲለንታኪ ሠናይት፤ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቌ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ
በወርቅ ወበዕንቊ ወበከርከዴን፤ ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ፤ መድኃኒቶሙ ለነገሥት።

ሰቆቃወ ድንግል
እፎ ጎየይኪ እምፍርሐተ ቀትል እምገፀ ሄሮድስ ቊንጽል፤ ወለተ አናብስት ግሩማን እለ ይጥሕሩ በኃይል፤ ኢፈቀድኪዮ በምድር ለመንግሥተ ዓለም ወብዕል፤ እስመ ልማዱ ትሕትና ለፍሬ ከርሥኪ ልዑል፤ ከማሁ ግዕዘኪ በምግባር ወቃል።

ወረብ
ወለተ ግሩማን አናብስት ግሩማን እለ ይጥኅሩ /፪/
እፎ ጐየይኪ ጐየይኪ እምገጸ ሄሮድስ /፪/

ዚቅ
ሃሌ ሉያ እምሊባኖስ ትወጽእ መርዓት፤ ወትወጽእ እምግበበ አናብስት፤ እምታዕካ ዘነገሥት፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ፤ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል።

መዝሙር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወዕፁብ፤ ለዘሃሎ መልዕልተ አርያም፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንጹሕ፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባሪ ያዕርፉ ባቲ፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን፤ ከመ ጽጌ ደንጎላት ዘውስተ ቌላት፤ ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።

ዓራራይ
በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት፤ በጊዜሁ ቆመ በረከት፤ ናርዶስ ጸገየ በውስተ ገነት፤ ሐመልማለ ገነት፤ አስካለ በረከት፤ ወሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት።

ዕዝል
ባረከ ዓመተ ጻድቃን፤ ወአጽገበ ከርሠ ርኁባን፤ ባዕል ውእቱ የአክል ለኲሉ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት።

ሰላም
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ፤ ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤ ሐረገ ወይን፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ ሐረገ ወይን፤ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ ወጸገወ ሰላመ ለኲሉ።

🌹💚 @ortodoxmezmur 💚🌹
🌹💛 @ortodoxmezmur 💛🌹
🌹❤️ @ortodoxmezmur ❤️🌹

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

˙     የተዋህዶ ፍሬዎች
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
     ከ1ኛ ዓመት ጀምሮ
መንፈሳዊ ኮርሶች ሚሰጡበት
                  እና
  ታላቅ ዓመታዊ የውድድር
   መድረኮች የሚገኙበት
               ቻናል ነው   

     🌹መልካም ትምህርት🌹
        🌹መልካም ፈተና🌹
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቅዳሴው ትምህርታችን ቀጣዩ ክፍል እነሆ
እያዳመጣችሁ እና እየተለማመዳችሁ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#አርሴማ

አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት(2)
ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት

አርሴማ------ታምርሽ ልዩ ነው
አርሴማ------ገድልሽ አስደናቂ
አርሴማ------ስምሽ ብርሃን ነው
አርሴማ------ማለዳ ፈንጣቂ

አዝ_______________

አርሴማ------ስምሽን እየጠራ
አርሴማ------ጠግቧል የተራበው
አርሴማ------ምስኪኑም ዘመረ
አርሴማ------ባንቺ አልፎ መከራው

አዝ_______________

አርሴማ------ፅኑ ነው ኪዳንሽ
አርሴማ------የተሰጠሽ ከአምላክ
አርሴማ------በአይኔ አይቻለው
አርሴማ------ጠላት ሲንበረከክ

አዝ_______________

አርሴማ------ዓለም ይስማው ዛሬ
አርሴማ------ዜና ተጋድሎሽን
አርሴማ------ይገረም ይደነቅ
አርሴማ------ይመስክር ዝናሽን

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​#አርሴማ_ቅድስት_ሰማዕት

አጠር በጠር ያለ ታረኳ
በቀሲስ ሄኖክ ወልደ- ማርያም

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከሚያከብሩ ብሩካን ከሆኑ፤በጾም በጸሎት በስግደት በትጋት ከሚኖሩ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስ ከእናቷ ከቅድስት አትናስያና በጥር 6 ቀን የተወለደች ደገኛ የገድል አርበኛ ናት፡፡

በተለይ ስትወለድ ይህ ቀረሽ የማትባል እጅግ መልከኛ እና ግርማዋ የሚያስፈራ ነበር፡፡ እናት እና አባቷም በጾም በጸሎት በስዕለት ስላገኟት እስከ 3 ዓመት ካሳደግዋት በኃላ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም በተሰራች ቤተ ክርስትያን ታገለግል ዘንድ ሰጧት፡፡ እመቤታችንን 12 ዓመት አገልግላ ያለፈቃድዋ በቤተሰቦችዋ ግፊት በ15 ዓመቷ ዳሯት፡፡ ሰማዕቷ ግን ዓለማዊ ሕይወት ባለመፈለግዋ ወደ ገዳማዊ ምናኔ ህይወት ገብታለች፡፡

በዚያን ዘመን ብዙ ሰማዕታት ያስፈጀ ጨካኙ የሰው አውሬ ካሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ መላኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሴት ሊያገባ ሽቶ በየአገሩ ሁሉ ፈልገው መርጠው ያመጡለት አንድ አሽከሮቹን አዘዘ፡፡

እንግዲህ የሰማቷ አሳዘኝ የመከራ ሕይወት ከዚህ ነው የሚጀምረው፡፡

የዲዮቅልጥያኖስ ሠራዊቶች አርሴማ የምትባል ውብ ሴት በሮሜ በአንድ ገዳም እንዳለች ሰሙ፡፡ አዋቂዎችም የሰማዕቷን ውብ መልኳን ስለው ለንገሡ ለዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ስዕሏን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና በሥጋዊ ጋብቻ አብሯት ሊኖር እንዳሰበ ለመኳንንቱ ነግሮ ለሠርግ እንዲመጡ አዘዘ፡፡

ቅድስት አርሴማ ይህንን በሰማች ባወቀች ጊዜ ከደናግሉ ጋር የንጉስ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነው አርመንያ አገር ሸሸች፡፡ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ የከበረች አርሴማን አስፈልጎ ባጣት ጊዜ በአርመንያ እዳለች ሰማ፡፡

ዲዮቅልጥያኖስም ለአርመንያው ንጉሥ ለድርጣድስ ከእሱ ሸሽታ እንደሄደች እና ባስቸኳይ አስጠብቆ እንዲልክላት አዘዘው፡፡ ደናግሉ ይንን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሰወሩ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በክብር ያመጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ሰማዕቷም ወደ እርሱ መምጣትን እንቢ ባለች ጊዜ በመሬት እየጎተቱ ወደ ንጉሡ አቀረቧት፡፡

ድርጣድስ የቅድስት አርሴማን ደም ግባት እና ውበት ባየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ የመንፈስ እናቷን አጋታን አባብላ እሺ ታሰኛት ዘንድ አዘዛት፡፡ አጋታም ወደ ሰማዕቷ ሄዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት ‹‹እወቂ ይህ ርኩስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ምሽራሽን ክርስቶስን እንዳትተይ›› ብላ አጸናቻት፡፡

ንጉሥ ድርጣድስም ሰማዕቷን ይዞ ወደ እልፍኝ ሊያስገባት ከአደባባይ መካከል ተነስቶ ድንግል አርሴማ በእጁ ያዛት፡፡ በዚያን ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው፡፡ ድርጣድስም በጦትነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለነበር በታናሽ ብላቴና ስለተሸነፈ መኳንንቱ ፊት ስለተዋረደ አፈረ፡፡

ከዚህ በኃላ በሰው አንደበት ለመናገር የሚከብድ መከራና ስቃይ አጸናባት፡፡ ሰማዕቷም ከንጉሡና ከጋሻ ጃግሬዎቹ የሚደርስባትን መከራ በመታገስ በረታች፡፡ ንጉሥ ድጣድስ በሰማዕቷ ላይ የሚያደርሰውን ሥጋዊ መከራ የልቡ ስላልደረሰለት ጡቷን በማስቆረጥ ዓይኗን በወረንጦ በማስወጣት ቢያሰቃያትም ሰማዕቷ ይበልጥ በክርስቶስ ፍቅር ጸናች፡፡ በሚደርስባትም ነገር ደስ ተሰኘች፡፡

ወዳጆቼ እኛ በሚደረስብን ሥጋዊ ህመም ስቃይ መከራ ፈተና እንደሰታለን? አንደሰትም ይልቁንም እናማርራለን፡፡ ምንያቱም የክርስቶስ የመከራ ሕይወት ውስጣችን ስላልገባ ነው፡፡ ክርስቶስ ጋር ለመድረስ መንገዱ፣በአጋንንት እና በሥጋ እየተጎዱ መሆኑን ስለማንረዳ ነው፡፡ ብንረዳም የደስታ እንጂ የመከራ ትከሻ ስለሌለን ነው፡፡ የመከራ ትከሻ ቢኖረንም ትዕግስት ስለሌለን በመከራችን አንጸናም፡፡

በመጨረሻም ንጉሥ ድርጣድስ የሚያደርገውን ሲያጣ አንገቷን በሰይፍ ሊያስቆርጥ ወሰነ፡፡ ከዚህ በኃላ ንጉሥ ድርጣድስ ቡርክት ቅድስት አርሴማን ወደ መገደያ ወንዝ እንዲወስዷትና በዚያም የከበረ ራሷን ይቆርጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን ወታደሮች አንገቷን ሲቆርጧት ያይ ዘንድ ከእርሷ ጋር ወጣ፡፡ ሰማዕቷ በምትገደልበት ትይዩ ከሠራዊቱ ጋር ተቀመጠ፡፡

የእጃቸው ክንድ የበረታ ልባቸው ግን የጨከነ ሮማውያን ወታደሮች ሰይፍ ይዘው ወደ ሰማዕቷ ቀረቡ፡፡ ሰማዕቷ ሞቷ ሰማያዊ እረፍቷ ስለሆነ በደስታ ትመለከታቸው ነበር፡፡ ቅድስት አርሴማም ወታደሮቹን የጸሎት ጊዜ እንዲሰጧት ጠይቃቸው ፈጣሪዋን ካመሰገነች በኃላ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ ወገቧን ታጥቃ አንገቷን ከፍ አድርጋ ለሚቆርጧት ታመቻችላቸው ነበር፡፡

ቆራጮች ወታደሮች ከቅድስት አርሴማ ግርማ የተነሳ ደንግጠው ሰይፋቸውን እንደያዙ በምድር ላይ ወደቁ ሰይፋቸውንም ጣሉ፡፡ ሰማዕቷም እያበረታታች ‹‹የታዘዛችሁትን ፈጽሙ›› ትላቸው ነበር፡፡ ወታደሮቹም ‹‹እኛስ ወዳንቺ መቅረብ እና አንገትሽን መቁረጥ አልቻልንም በግንባርሽ ላይ ያለው ትዕምርተ መስቀል አስፈርቶና፤ግንባርሽን ካልሸፈንሽልን አንገትሽን ፈጽሞ ልንቆርጥ አንችልም›› አሏት፡፡

ሰማዕቷም ለወታደሮቹ ፊቴን የምሸፍንበት ቁራጭ ልብስ ወይም ቁራጭ ጨርቅ ስጡኝ አለቻቸው፡፡ እነሱም ቁራጭ ጨርቅ ጣሉላት እሷም ፊቷን ሸፈነች፡፡

ቅድስት አርሴማም ንጉሥ ድርጣድስ እና ሠራዊቱ ሕዝቡም እየተመለከቱ ምስከረም 29 ቀን አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ፡፡ ወዳጆቼ እኛን ጌታችን እንደ እነ ቅድስት አርሴማ፣ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ወዘተ አንገታችሁን ተቆረጡልኝ ሰማዕት ሁኑልኝ አላለንም፡፡ ኃጢአትን ከእናንተ ሰውነት ቆርጣችሁ ጣሉት ነው ያለን፡፡

የዝሙትን ፍላጎት ከሰውነታችሁ ቁረጡና ደም አላባ ሰማዕት ሁኑ ነው የተባልነው፡፡ የኃጢአቶችን ተቀጽላ ከሥጋችሁ ላይ ቁረጡና በንስሐ ጻድቅ ሁኑ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት በደማችሁ ዋጋ ገነት ግቡ ሳይሆን በደሜ ፈሳሽት መንግስቴን ውረሱ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት ጽኑ መከራን በሥጋችሁ ተቀበሉ ሳይሆን ቅዱስ ሥጋዬን ብሉና የርስቴ ተካፋይ ሁኑ ነው ያለን፡፡ ሰማዕት ሁኑ ሳይሆን በእኔ መስዋዕትነት ዳኑ ወደ መንግስቴ ጎዳና አቅኑ ነው ያለን፡፡ አወይ አለመጠቀማችን እንደ እኛ ያደለው ማን አለ?

ቅድስት አርሴማም በሰይፍ ስትሰየፍ ከአንገቷም ደም፣ውኃ፣ወተትና ማር እንደ ክረምት ነጠብጣብ እየተንጠባጠበ መነጨ፡፡

ደም ከአንገቷ የመነጨው ስለ ሃይማኖትዋ ቆራጥነት ስለ ሞት አለመፍራት እና የጌታችንን መከራ ተሸክማ ሰማዕት ስለሆነች ነው፡፡

ውኃ የፈሰሰው ስለ ብዙ ጸሎትዋ፤ስለልመናዋና የቤተ ክርስትያን መጻሕፍትንና ምስጢራትን ሁሉ ልብ ስለምታደርግ ነው፡፡

ወተት የመነጨላት ስለ ክብሯ ስለ ከፍታዋ እና ንጽሃ ድግልናዋን ስለጠበቀች ነው፡፡

ማር የወረደው ስለሚያስደንቅ የፊቷ ወዝ፣ደም ግባቷ፣ስለ ጣፋጭ የከንፈሯ ቃልና የሰማዕታት ሁሉ እህት ስለሆነች ነው፡፡

ከዚህ በኃላ ብሩህ የሆነ የደመና አምድ ወረደና በላይዋ ጋረዳት፡፡ ወደ ሰማይም እንደ መብረቅ ሳባት፡፡ የቅዱሳን መላእክትም ማህበር ነፍሷን አሳረጓት፡፡ በክብር በእልልታ በዝማሬና በማህሌት ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አስገቧት፡፡

እርሷ እንደ ሞተች ባወቁ ጊዜ ወታደሮቹ ደናግሉን ሁሉ ጫማቸውን እየበሱ እራሳቸውን ቆረጡ፡፡ ቁጥራቸውም ሰባ ሁለት ነፍሳት ነበሩ፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📚ሚተራሊዮን በpdf የምታገኙበትን ከ 75,000 በላይ አንባቢያን ያሉበትን ቻናል ይቀላቀሉ።

ከ350 በላይ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በPDF ያገኙበታል።
👇🏾👇🏾👇🏾
/channel/+iJJR03jZN9FkMjg0
/channel/+iJJR03jZN9FkMjg0

Читать полностью…
Подписаться на канал