ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 сентября 2024 12:17
ይላል አንደበቴ
ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው
ትናንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ
ትልሃለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ
አዝ
የትናንት ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው
ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው
ወደ እረፍቴ ወጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ
ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ (2)
አዝ
በጥልቁ በረሃ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ
መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ
በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ
ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ (2)
አዝ
የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል
ለእኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል
ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ
የጌታዬ ሃሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ (2)
አዝ
ትናንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ
የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ
በባሕርይው ቅዱስ የሌለው አምሳያ
ስሙ ወደቤ ነው መልህቄን መጣያ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 сентября 2024 05:00
በብርሃን ፀዳል
በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የፅጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ ሲሰማኝ እርካታ/2/
አዝ
እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ሕልሜ
የቀን ምኞቴ ነው/2/
አዝ
እሩሩህ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህሊናዬ እረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን
ሕሊናዬ ይትጋ/2/
አዝ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይጻፍብኝ
በልዩ ሕብር/2/
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 12:28
ሰባቱ መንጦላይት
ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት
አዝ
አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ
ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ
እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ
ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ
ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ
ከመሰወሪያው ዘንድ ከልጅሽም ሊደርስ
ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 04:59
እግዚአብሔርን አመስግኑት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት/2/
አዝ
ሰማይን ያለምሰሶ
ምድርንም ያለ መሠረት
ያጸናው እርሱ ነው
ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
የባሕርን ጥልቀት የመጠነ
ዳርቻዋን የወሰነ
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ማዕበል ነፋስ የሚገስጽ
ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ
ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት
እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ንጹሀ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ
የነገስታት ንጉሥ አልፋና ኦሜጋ
ዘላለም እርሱ የማይለወጥ
እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ጥበብን የሚገልጥ ጥበበኛ
ፍርድን የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ
እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም
እግዚአብሔር ግሩም ነው ዘለዓለም
ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 сентября 2024 06:07
መስከረም ፱
በዚህች ቀን መጺል በምትባል አገር ኤጲስ ቆጶስ የነበረ፤ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ።
በወቅቱ ዲዮቅልጥያኖስ የተባለ ክፉ ሰው በንግስና ላይ የነበረበት ግዜ ነበር። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም። የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው። መከራውም እየገፋ ሲመጣ ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት። በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ወደደ።
ሕዝቡንም ሰብስቦ አቆማቸው፤ ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትዕዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ለሰማዕትነት እንደተዘጋጀ ነገራቸው። ይህንንም በሰሙ ግዜ ሁሉም አለቀሱ። የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተወናለህ፤ እንድትሄድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ። ቅዱሱም ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። አንዳንድ አባቶችም አብረን እንሞታለን ብለው አብረውት ሄዱ።
በኋላም መኰንኑ ጽኑ የሆነ መከራ አደረሰባቸው ፤አባቶች ግን በታላቅ ትዕግስት ጸኑ። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ። በዚህች ዕለትም የሕይወት አክሊልን በመንግስተ ሰማያት ተቀበሉ።
በረከታቸው ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 19:37
ስግደት
ስግደት ማለት መዋረድ፣ ማጎንበስ፣ መንበርከክ፣ በግንባር መውደቅ፣ ግንባርን ምድርን አስንክቶ መሬት ስሞ መመለስ ማለት ነው።
ስግደት ለምን ይጠቅማል?ስግደት ከአምላካችን ፀጋ እና በረከትን እንድናገኝ እንዲሁም ክፉ መንፈስ ከእኛ እንዲርቅ ይረዳል። በቤተ ክርስቲያን ሁለት አይነት ስግደቶች አሉ፦እነሱም
፩.የአምልኮ (የባህሪይ) ስግደት
ይህ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ብቻ አንተ አምላኬ ነህ በማለት የምንሠግደው ስግደት ነው። ማቴ 4፥10
፪.የአክብሮት (ጸጋ) ስግደት
ለመላእክት ለቅዱሳን ለፃድቃን ለሰማዕታት የሚሰገድ ስግደት ነው። በፀሎት ጊዜ በተለይም ስግደትን የሚያነሳ አንቀፅ ሲገኝ ህሊና ተሰብስቦ የአንክሮ፣ የተደሞ፣ የትህትና ስግደት ይሰገዳል። ስግደት በቤተክርስቲያን እንዲሰገድ መጽሐፍ ቅዱስ ያዝዛል። ቤተክርስቲያን በሌለበት ቦታ ደግሞ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንሰግዳለን።
ስርዓተ ቤተክርስቲያን በወር ውስጥ አምስት ቀናት ስግደት እንዳይሰገዱባቸው ያዛል፦1. የበዓለ ወልድ እለት (በየወሩ በ29) እና በጌታችን አበይት በአላት
2. የእመቤታችን ወርሃዊ መታስቢያ (በየወሩ በ21) እና በእመቤታችን በዓላት
3. የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ (በየወሩ በ12)
4. ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ)
5. ሰንበተ ክርስቲያን (እሁድ) እና በዓለ ሀምሳ።
በእነዚህ ቀናት የማይሰገድበት ምክንያት
📌 ዕለተ
ቅዳሜ ጌታችን ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ከስራው ያረፈበት ቀን ስለሆነ።
📌 ዕለተ
እሁድ ጌታ ከሙታን መካከል ተለይቶ የተነሳበት ቀን ስለሆነ።
📌
በ12 በዓለ ቅዱስ ሚካኤል ራዕ᎐፲፪ኀ ሰይጣን የወደቀበት ቀን ስለሆነ።
📌
በ21 በዓለ ማርያም የነፍሳችን ዕረፍት ነጻ የወጣንባት ስለሆነ።
📌
በ29 በዓለ እግዚአብሔር የነጻነት ቀን ጌታ የተወለደበት ቀን ስለሆነ።
የአምልኮት ስግደት ሦስት ደረጃዎች አሉት እነርሱም;-
፩᎐ ሰው አድርገህ ከመሬት ፈጥረኸኛልና ስንል ወደ ምድር ጉልበትና ግንባራችንን እናስነካለን።
፪᎐ በኃጢአት ወድቄ በንስሐ እነሳለሁ ስንል ከሰገድንበት ብድግ እንላለን።
፫᎐ ብሞት በትንሣኤ እነሳለሁ ስንል ከሰገድንበት ቦታ በሁለት እግሮቻችን እንቆማለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 06:01
መስከረም ፰
በዚህች ቀን ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ፤ ቅን፤ የዋህ፤ ጻድቅ፤ የነቢያት አለቃ የቅዱስ ሙሴ ዕረፍቱ ነው።
ከኮከብም ኮከብ እንደሚበልጥ ከነቢያት ሁሉ ደግሞ ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል። የቅዱስ ሙሴ አባት
እንበረም እናቱ ደግሞ
ዮካብድ ይባላሉ። ቅዱስ ሙሴ በተወለደ ወቅትም የእስራኤል ወንድ ልጆች ይገደሉ ነበር። ወላጆቹም እርሱን ለማሸሽ ሲሉ ገና በ3ወሩ በግብጽ /ዓባይ/ ወንዝ ውስጥ ጣሉት።
የፈርዖን ልጅም ከወንዝ ላይ ባገኘችው ግዜ ለእርሷ ልጅ ይሆናት ዘንድ ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው። ስሙንም
ሙሴ ያለችው እርሷ ናት፤ ትርጉሙም ከውሃ የተገኘ ማለት ነው። ወላጆቹ ግን በተወለደ ወቅት ፊቱ ያበራ ነበርና
ምልክአም ብለው ስም አውጥተውለት ነበር። እናቱ ዮካብድም በሞግዚትነት ገብታ ልጇን ማንም ሳያውቅ አሳድጋዋለች።
በቅዱስ መጽሐፍ እንደምናነበው ቅዱስ ሙሴ ኮልታፋ ነው፤ ይህም ገና በ5 አመቱ ፈርኦንን በጥፊ በመምታቱ እሳት አበሉት በዚህም ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል። 40 አመት በሞላው ግዜም አንድ የግብጽ ሰው አንዱን ዕብራዊ ሲያጠቃው ተመልክቶ ለዕብራዊው ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው ከዚያም ወደ ምድያም ሸሽቷል።
ቅዱስ ሙሴ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ግብጻውያን ላይ ዘጠኝ መቅሰፍት በአስረኛውም ሞተ በኩር መታ። እሥራኤልንም ነጻ አወጣ። መልካም ተጋድሎንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት ዐረፈ።
በረከቱ ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 сентября 2024 12:27
ድንቅ አድርጎልኛል
ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ 2
አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ 2
አዝ
ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር
ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ
ድንቅ አድርጎልኛል እረክሼ ሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምጻቱ
ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ
አዝ
ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ
ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት
ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል እንዲህ ለወደደኝ
አዝ
ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ
ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል
ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 сентября 2024 05:04
የሥላሴን መንበር
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት
ድንግልን ከመሃል ሚካኤልን ከፊት
አእላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍራት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት
አዝ
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ልዩ ተ0ምር ሊያዩ የታደሉ
በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ/ 2/
አዝ
የቅዱሳን ህብረት የቅዱሳን ሀገር
ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር
ጽድቅና ርህራሄ የተሞላ ሰማይ
እግዚአብሔር ያድለን በትንሳኤ እንድናይ/2/
አዝ
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ በሰማይ መላዕክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ልዩ ተዐምር ሊያዩ የታደሉ
በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ/ 2/
ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 сентября 2024 19:10
የተወደደ ቀን
የተወደደ ቀን የተወደደ ዓመት
ወደ አባቴ መቅደስ የተመለስኩበት
አንባር ቀለበትን የተሸለምኩበት
የተወደደ ዓመት
አዝ
አምሽቶ የመጣ
አይገባም አትበሉ(2)
አባክኖ የመጣ
አይገባም አትበሉ(2)
ፍቅር ስለሆነ
እግዚአብሔር ለሁሉ(2)
ልጅ ቤቱን ይወርሳል
እንደተስፋ ቃሉ(2)
አዝ
ከናዝሬት መልካም ሰው
አይወጣም እያሉ(2)
ፊልጶስ ናትናኤል
ይነጋገራሉ(2)
አድርጎታልና
ውሀውን ወይን(2)
ዛሬም ለውጦኛል
ወስዶታል ልቤን(2)
አዝ
እኔ ነኝ አላማው
እኔ ነኝ ሀሳቡ(2)
አባቴ ደግ ነው
የሚራራ ልቡ(2)
ዘጠና ዘጠኙ
ታምነውት እያለ(2)
አንዱን ይፈልጋል
ወዴት ነህ እያለ(2)
አዝ
ሁሉን አይቻለሁ
ሁሉን መርምሬአለሁ(2)
አለም ካንተ ሌላ
እንደሌለ አውቃለሁ(2)
እንደማይለወጥ አባትነትህ ወዳጅነትህ
ጠፍቼ ስመጣ
አየሁት ልጅህ(2)
ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 сентября 2024 06:00
መስከረም ፮
በዚህች ዕለት ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ አረፈ። ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ በትንቢተ ኢሳይያስ 7፥14
"ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች"
የሚል ነበር ።በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ ሰዎች ግን ለንጉስ ሕዝቅያስ "ይህ ትንቢት ላንተ ነው ድንግል የተባለችዋ ኢየሩሳሌም ስትሆን ወንድ ልጅ የተባለው ደግሞ አንተ ነህ" አሉት።
ንጉሱም ይህን ሰምቶ አልገሰጻቸውምና። እግዚአብሔርም በንጉሱ ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው። እንዲህም አለው
ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ። መጽ ነገ ካልዕ 20:1
ይህ እንደሆነ ንጉሱ በጽኑ ታመመ ደከመ። ንጉሡም በልቡ ተጸጽቶ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ ሲል ተማጸነ። እግዚአብሔርም ንስሐውን እንደተቀበለው እና በዘመኑም ላይ 15 ዓመታትን እንደጨመረለት ነቢዩ ነገረው።
በኋላ ዘመንም ንጉስ ምናሴ ጣዖትን ያመልክ ነበር። ነቢዩም በአደባባይ ገሰጸው። ምናሴም በዚህ ተበሳጭቶ ነቢዩ ኢሳያስን በዚህች ዕለት በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው። ቅዱሱም ተጋድሎውን ፈጸመ።
በረከቱ ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 сентября 2024 23:00
የዕለቱን ስንክሳር በአጭሩ ማንበብ ይፈልጋሉ፤ ጠዋት እና ማታ የምንለቃቸውንም ዝማሬዎች ማዳመጥ ይፈልጋሉ፤ በተጨማሪም የምንለቃቸውን ትምህርቶች ማግኘት እና ማንበብ ይፈልጋሉ። ነገር ግን ዝንጉ አይምሮ ነውና ያለን ማስታወስ አቅቶን የዝማሬ ዳዊት ቻናልን ከፍተን ሳናይ ከቴሌግራም እንወጣለን። ይህም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ቴሌግራም ላይ ካሉ ብዙ ቻናሎች መሀከል ስለሚደበቅ ነው።
በመሆኑም ቻናላችንን ከላይ Pin በማድረግ ወደ ቴሌግራም በሚገብ ግዜ ሁሉ ከፊት ለፊት ስለሚያገኙት የምንለቃቸው ነገሮች በሙሉ አያመልጧችሁም።
Pin ለማድረግ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ።
1. የዝማሬ ዳዊት ገጽን ለትንሽ ግዜ ጫን ብለው ይቆዩ።
2. ከላይ ምስሉ ላይ እንደሚታየው ቻናሉን
Mark ካደረገላችሁ በኃላ Pin የሚል ጽሁፍ ካያችሁ እርሱን መንካት ወይም በቀይ ሰንጠረዥ የጠቆምናትን ምልክት መንካት።
በዚህ መልኩ ቻናላችንን PIN ማድረግ ትችላላችሁ።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን።
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 сентября 2024 06:00
መስከረም ፭
በዚህች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስ እና በርናባ ጋር በሰማዕትነት አረፈች።
ቅድስት ሶፍያ አስቀድማ አረማዊት ነበረች ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ነበሩ። እርሷም በልቧ የወላጇቿ ሃይማኖት ከንቱ እንደሆነ ከመረመረች በኋላ ወደ መኖፌ ኤጲስቆጶስም ሄዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በክርስቶስ ታመነች። እርሱም ሃይማኖትን የቤተክርስቲያንን ሕግ አስተማራት።
ከዚሕም በኋላ ከልጆቿ ጋር በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጠመቃት። የሀገሩ ገዢ ለጣዖት መስገድን ትታ ክርስቲያን እንደሆነች በሰማ ጊዜ ከልጇቿ ጋር ብዙ ስቃይን አሰቃያት። ገዢውም ልጇቿ አይተው ይፈሩ ዘንድ በጅራፍ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ እናታቸውን ከግርፋት ሲሰውራት አዩ።
ከዚህም በኋላ ወደ እስር ቤት ወስደው አሰሯት እራሷንም በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የድል አክሊልንም ተቀበለች። ከዚህም በኋላ ልጆቿን ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ አስፈራራቸው እንቢ ባሉት ጊዜም እያከታተለ አንገታቸውን አስቆረጠ።
ምስክርነታቸውንና ተጋድሏቸውን ፈጸሙ። ከመቃብራቸውም፤ በሽታውንና ደዌውን ሁሉ የሚፈውሱ ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።
የጻድቅ መታሰቢያው ለዘለዓለም
ይኖራል።
መዝ ፻፲፩፡ ቁ ፮
በረከታቸው ይደርብን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 сентября 2024 11:03
ለውዳሴሽ ልትጋ
ለውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ አለው 2
እመቤተ ኧኸ እመቤተ ስልሽ እውላለው
ከልቤ አቀርባለው ምስጋናን ለስምሽ
ተመስክሮልሻል ብፅዕት ተብለሽ
የሰላምታ ድምፅሽ ያልነካው ማን አለ
ጽንሱ በማህፀን በደስታ ዘለለ
አዝ
ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ
እመቤተ ስልሽ ይቀላል ሸክሜ
ቅኔ ማህሌቱ ሰአታት መዝሙሩ
ያመሰግኑሻል ምድርና ጠፈሩ
አዝ
እናቱ ነሽና አንቺ ለኢየሱስ
አድሮብሽ ይኖራል እግዚአብሔር መንፈስ
ሰዓሊ ለነ ብዬ ቀኑን ጀምራለው
ልጅሽን አምኜ ነገም እኖራለው
አዝ
ነይ ነይ እልሻለው እንደት ካህናቱ
በሰዓታት ጸሎት ቆሜ በሌሊቱ
ዝም አልልም እኔ አወድስሻለው
ያለምን መከራ እረሳብሻለው
ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 сентября 2024 05:00
አጥቷል ጎሎበታል
አጥቷል ጎሎበታል ብለህ ሳትንቀኝ
ለዚህ ያደረስከኝ ጌታዬ እኔ ማነኝ
ይሞላል አይቀርም ባንተ ሸለቆዬ
ጠብቃለሁና ቀንህን ጌታዬ
አዝ
ሀዘን ፅልመት ክፉ ዘመን
ቢገጥመኝም እንኴን
ያልፋል ሁሉም ታሪክ ሆኖ
በፊትህ ሲለካ
ማን ጎደለ ማን አፈረ አንተን የጠበቀ
ፀና ልቤ በእግዚአብሔር ይሄን እያወቀ
አዝ
ባለም ስፍራ ባይኖረኝም
ብሆንም ጎስቇላ
አምላኬ ሆይ ካንተ በቀር
አልሄድ ወደ ሌላ
ጌታዬ ሆይ በፍለጋ ወጣሁ ከመቃብር
ስመሰክር እኖራለሁ ስራህን ስናገር
አዝ
ቀን ለክተህ ጊዜን አይተህ
ሰውን የማትከዳ
ያለ ወረት ትመጣለህ እኔን ልትረዳ
ከእነ ኤልያስ ወንድሞቼ ባልስተካከልም
ማማ ሆነህ ከፍአረከኝ አንተ ሰው አጥልም
አዝ
እንደ እናት ልጅ እንዳልቆጥርህ
ከዚህም ትበልጣለህ
ካንተ በቀር ያፈቀረኝ
በምድር ስለሌለ ስለ
ስምህ መነቀፌ ክብሬ ነው ማረጌ
በምን መንገድ ላስደስትህ እንደምን አድርጌ
ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 сентября 2024 06:05
መስከረም ፲፩
በዚህችም ቀን በእስክንድርያ አገር ትህትናን ገንዘብ ያደረገች ቅድስት ታዖድራ አረፈች።
ቅድስት ታዖድራ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ወላጆቿ ያመጡላትን ባል እሺ ብላ አገባች። በሥጋ ወደሙም ተወስነው ኖሩ። አንድ ቀን ግን ከቤተክርስቲያን ስትመለስ፤ በመልኳ ምክንያት ለኃጢአት ይፈልጋት የነበር አንድ ጎረምሳ ያዛት። በአቅምም አልቻለችውም፤ የሚፈልገውንም አድርጎ ከክብር አሳነሳት።
ታላቅ ኀዘን አዘነች፤ መሪር የሆነ ልቅሶንም አለቀሰች። የወንዶችንም ልብስ ለብሳ ወንድ መስላ ስሟንም ቴዎድሮስ በማለት በወቅቱ የሴቶች ገዳም አልነበረምና የወንዶች ገዳም ገባች። የምንኩስና ልብስንም ለበሰች። ሰይጣን ግን ፈተናውን አጸናባት።
በአንድ ወቅትም አንድ ወንድ ከአንዲት ብላቴና ጋር አመነዘረ፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። ወላጆቿም ድንግልናሽን ያጠፋው ማነው ብለው ጠየቋት። ሰይጣንም በእርሷ አድሮ፤ በገዳም ውስጥ የሚኖር አባ ቴዎድሮስ የሚባል ነው አለች። ወላጆቿም የተወለደውን ልጅ ወስደው ለገዳሙ አበምኔት የአባ ቴዎድሮስ ልጅ ነው ብለው ሰጡት።
አበምኔቱም ቅድስት ታዖድራን ልጁን አስይዘው ከገዳም አባረሯት። በበረሀም በብዙ ፈተና ሰባት አመት ኖረች። በኋላም ዳግመኛ ተቀብለው ወደ ገዳም አስገቧት። ጥቂት ቀንም ኖረች፤ መልካም ተጋድሎዋንም ፈጽማ በዚህች እለት አረፈች።
በረከቷ ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 19:55
ንስሐ
ንስሐ ማለት ሐዘን፣ፀፀት፣ ቁጭት፣ ቀኖና፣ የኃጢአት ካሣ ማለት ነው፡፡ ንስሐ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መፀፀቱን ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው፡ ንስሐ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ደግሞ ንስሐ ማለት ወደ እግዚአብሔር መመለስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ፣ ከኃጢአት መራቅ፣ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው።
ንስሐ ለመግባት ስናሳብ ከታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት አለብን፦1. በአጥቢያችን ከሚገኝ ቤ/ክ ክህነት ያላቸው በአገልግሎት ላይ ያሉ መልካም መንፈሳዊ ምግባር ያለቸውን አባቶች የንስሐ አባት መያዝ፤
2. የሰራነውን ኃጢአት ማመንእና በሰራነው ኃጢአት ከልብ አብዝተን መፀፀት፣ማዘንና ማልቀስ፤
3. እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በፍጹም ትህትና ራስን በማዋረድ መጠየቅ፤
4. ከእኛ ኃጢአት ይልቅ የእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅር ባይነት እንደሚበልጥ እና ይቅር እንደሚለን ያለጥርጥር ፍጹም ማመን፤
5. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን ንስሐ ለመግባት እና ቀኖናችንን ለመቀበል ማሰብ እና መወሰን፤
6. ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሰራናቸውን ኃጢአቶች ለማስታወስ መሞከር ከተቻለም ለማስታወስ ይረዳን ዘንድ በጽሑፍ መያዝ፤
7. ዳግም ወደ ሰራነው ኃጢአት እንደማንመለስ ለራሳችን ቃል መግባትና መወሰን፣ኃጢአትን መጸየፍ፤
8. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን የሰራነውን ኃጢአት ሳንደብቅ በግልፅ መናዘዝ።
9.የሚሰጠንን ቀኖና በትክክል መተግበር፤
10. ዳግም ወደ ኃጢአት እንዳንመለስ ራሳችንን በቃለ እግዚአብሔር ማነጽ፤
11. ዳግመኛ ለንስሐ መዘጋጀት።
ንስሐ ከሚደገሙ ምስጢራት መካከል አንዱ ነው። ሰዎች እንደመሆናችን በተደጋጋሚ በኃጢአት እንወድቃለን ስለዚህ በተደጋጋሚ ንስሐ ልንገባ ይገባናል ማለት ነው። ኃጢአት ለንስሐ አባት መናዘዝ ለምን አስፈለገ? ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘው ትዕዛዝ ስለሆነ ነው።
ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፡ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለመንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። ሉቃ.፭፥፲፬
ንስሐ ከገባን ቀኖናችንን በስርዓቱ ከፈፀምን በኋላ ንስሐችንን ፍፁም የሚያደርገው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ነው። ዮሐ 6፥33
ብዙዎቻችን መቁረብን እንደ ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ ለአዛውንቶች ብቻ አድርገን ስለምንቆጥር ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም። ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና። ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን። አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 06:04
መስከረም ፲
በዚህች ዕለት ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል፤ ከሠሌዳዋም ቅባት የሚንጠፈጠፍባት የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ተዐምር ተገለጠ።
ይህችን ሥዕል የሳላት ቅዱስ ሉቃስ ነው። ወደ ጸዴንያ እንዴት መጣች ቢሉ፤ አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች በቤቷም እንግዳ ትቀበል ነበር። ድንግል ማርያምንም አብዝታ ትወዳት ነበር። በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ በእንግድነት መጣ። በማግስቱ ስትሸኘው ወዴት ነህ ብላ ጠየቀችው። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሆነ ነገራት። እርሷም ሲመለስ የእመቤታችንን ሥዕል አምጣልኝ አለችው።
ከዚህም በኋላ ከቦታው ደርሶ ሥዕሏን ሳይገዛ ተመለሰ፤
በመንገድም ሥዕሏን ለምን አልገዛህም? የሚል ድምጽ ሰምቶ ተመልሶ ገዛ። በጎዳናው እየተመለሰ ሳለም የሚያስፈሩ ወንበዴዎች፤ ኋላም አንበሳ ገጠመው፤ የያዛት ሥዕልም ቃል አውጥታ አዳነችው።
አባ ቴዎድሮስም ይህን ድንቅ ተአምር ባየ ግዜ ሥዕሏን ወደ ሀገሩ ሊወስዳት ወደደ። በሌላ ከተማም አድርጎ ሊሄድ መርከብ ተሳፈረ።
በመርከቧ ሳለም ታላቅ ነፋስ ተነስቶ አቅጣጫውን አስቀይሮ ወደ ጸዴንያ ወሰደው። ኋላም ቢመሽበት ማርታ ቤት ሄደ እራሱን ግን አልገለጠም። በማግስቱም ተሰውሮ ከከተማው ሊወጣ ቢሞክር መውጫው ጠፍቶት ሲዞር ውሎ ተመለሰ። እንዲህም እያለ ሶስት ቀን ሆነው። ማርታም ይህን ተመልክታ ምን እንደሆነ ጠየቀችው። እርሱም ሁሉንም ነገራት።
በኋላም የመነኩሴውን እጅና እግር ስማ ሥዕሏን ተቀበለች። በታላቅ ክብርም አስቀመጠቻት። ያም መነኩሴ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ።
የእመቤታችን በረከት ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 сентября 2024 12:03
ምክንያት ስላለኝ ነው
ምክንያት ስላለኝ ነው የምዘምርልሽ
ምክንያት ስላለኝ ነው ቅኔ እምቀኝልሽ
አሁንም ይብዛልኝ ፍቅርሽ/2/
ከዚህ በላይ እንዳመሰግንሽ
አዝ
አውቃለሁ ከደጅሽ ምን እንዳገኘሁኝ
አስታውሰዋለሁ ሸክሜን እንደጣልኩኝ
የለመንኩሽ ሁሉ መቼ ከንቱ ቀረ
ሰይጣን ተመለሰ እያቀረቀረ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/
አዝ
ልቤ አርፏል በአንቺ በእናቴ አማላጄ
እንቅፋት እሾሁ አይበቅልም በደጄ
በሚጣፍጥ ዜማ በኤፍሬም ውዳሴ
ሳሸበሽብልሽ ትረካለች ነፍሴ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/
አዝ
ውለታ ያለበት የማይከፈል
ሲመሽም ሲነጋ ያመሰግናል
ማርያም ማርያም ይላል ምድርና ሰማዩ
በልጅሽ መከራ ሞቶለት ገዳዩ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 сентября 2024 05:00
በበጎ ፍቃዱ
በበጎ ፍቃዱ ሁሉ በእርሱ ሆነ (2)
ነገር ሁሉ በርሱ ተከናወነ (2)
አዝ
ሰማይና ምድር ግብሩን ተናገሩ
ፈጥሯቸዋልና እንዲገለጥ ክብሩ
በፈጠረው ፍጥረት የሚታወቅ እሱ
እግዚአብሔር ይመስገን ስሙን አወድሱ
አዝ
አልሆነም ያለእርሱ ፍፁም አንዳች ነገር
ብንመረምረው በሰማይ በምድር
ፍቃዱ ነውና መልካምና በጎ
ሰርቶ አሳይቶናል ሁሉን ውብ አድርጎ
አዝ
ክረምትና በጋ ሌሊትና ቀን
ሁሉን አሳይቶ ጌታ አስተማረን
ያደረገው ሁሉ እንከን የሌለው
ለዚህ ቅዱስ አምላክ ምሳሌም የለው
አዝ
ያዘነውን ያውቃል ደስም ያለውን
ሁሉ በእርሱ ፍቃድ ስለ ሚከወን
ችግርና ደስታም ለበጎ ነውና
ይህን ያስተማረን ይድረሰው ምሥጋና
ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 12:00
ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ
ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በሥላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2)
አዝ
ተጥሎ አዝኖ የኖረው
በልጅሽ ነው ቀናቀና ያለው
ንጉሱን ስትወልጂ በበረት
ተፈታ አዳም ከእስራት
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
አዝ
ከሚያስብ ከማይዘነጋ
ፍጥረቱን ከሚያረጋጋ
ስላለሽ በእግዚአብሔር ቀኝ
ለኃጥአን ድንግል ለምኝ
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
አዝ
ከሰማይ ሰማያት ወርዶ
መለኮት ሥጋን ተዋህዶ
አየነው በጠባብ ደረት
ወሰንሽው በአጭር ቁመት
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
አዝ
ሰነድ ነሽ መታረቂያችን
ከተማም መማፀኛችን
በሰማይ በምድርም ያሉ
ለክብርሽ ቅኔ ይቀኛሉ
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 05:01
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ
ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ/2/
አዝ
ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለኔ
ወዳጅ እና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ
ምን አለኝ እና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ
እኔስ ተሸንፌያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ
አዝ
ተሰድጄ ብወጣ ወተሃል ከኔ ጋራ
ትናንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ
ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ
ወጥመዴን ስበር እና አፌን ሙላው በእልልታ
አዝ
በእስረኞች መሃል ሆኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ
አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ
መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅ እና ዘመዴ
አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ
አዝ
መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ
ደክመህ አልፈህልኛል እጆቼን አበርትተህ
ሁሌ በሬ ላይ ቆመህ ደጃፌን የምትመታ
ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ
ብያለሁ ማራናታ/4/
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 сентября 2024 06:02
መስከረም ፯
በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እናት፤ የከበረች ኤልሳቤጥ አረፈች።
ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ካህን ለሆነው ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት። ነገር ግን እስከ እርጅና ዘመናቸው ልጅ መውለድ አልቻሉም ነበር። የኤልሳቤጥ እድሜ 90 የዘካርያስም 100 ደርሶ ነበር። እግዚአብሔርም ትዕግስታቸውን እና ጽድቃቸውን ተመልክቶ በመልዐኩ ገብርኤል አብሳሪነት ታላቅ የሆነ ነቢይን ሰጣቸው።
የኤልሳቤጥ የስድስት ወር ጽንስም የድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማ ግዜ በደስታ ዘሏል። ቅዱስ ዮሐንስም 2 ዓመት ከ6 ወር በሞላው ግዜም ንጉስ ሔሮድስ የተወለደውን ንጉስ /ኢየሱስ ክርስቶስን/ ለማጥፋት ተነሳ። አይሁዶችም ለንጉስ ሔሮድስ
ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ሲወለድ ደግሞ የከፈተ ዮሐንስ የሚባል አለና እርሱን ግደል አሉት።
ቅድስት ኤልሳቤጥም ቅዱስ ዮሐንስን ይዛው ሸሸች። አባቱ ካህኑ ዘካርያስን ግን በቤተመቅደስ ውስጥ ገደሉት። ቅድስት ኤልሳቤጥም ዮሐንስን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 ዓመታት ቆየች። ቅዱስ ዮሐንስም 5 ዓመት በሞላው ግዜ በዚህች ዕለት ቅድስት ኤልሳቤጥ በዚያው በበርሃ አረፈች።
በረከቷ ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 сентября 2024 19:38
አሥራት
ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ላይ አሥራትን ካልከፈለ እግዚአብሔር አምላክ ሰርቃችሁኛል ይላል።አሥራት የሚለው ቃል ዐሠረ (ዓሥር)
አደረገ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ፍቺውም ከአሥር (10) አንድ ማለት ሲሆን ይህንንም ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው።አሥራት ሰው ጥሮ ግሮ ሠርቶ ከሚያገኘው ከላቡ ገቢ ለእግዚአብሔር ከአሥር አንድ እጁን ወይንም ከመቶ አሥር ክፍሉን ለእግዚአብሔር መሥጠት ማለት ነው።
አሥራት በሕገ ልቦናና በሕገ ኦሪትም ይሠጥ ነበረ።ለምሳሌ በሕገ ልቦና አብርሃም አባታችን ለካሕኑ ለመልከጼዲቅ አሥራትን እንደከፈለ በቅዱስ መጽሐፍ ተገልጧል።
አብርሃምም ከሁሉ አሥራት ሠጠው።ዘፍ ፲፬÷፳አባታችን ያዕቆብም ቤቴል ብሎ በሰየማት በሎዛ ምድር እግዚአብሔር ቢገለጥለት በሥፍራው የእግዚአብሔር ቤት እንደሚታነጽና እርሱም አሥራት እንደሚያደርግ ቃልኪዳን አደረገ።
ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ። ዘፍ፳፰÷፳፪
እግዚአብሔር አምላካችን ሙሴን በሲና ተራራ ካዘዘው ትእዛዝ አንዱ አሥራትን ስለመክፈል ነው።ይሕም በዘሌ ፳፯÷፴፡፴፫ ተጽፎ ያለው ነው።ስለዚህ አሥራትን ማውጣት የአምላክን ሕግ መጠበቅና መፈጸም ነው።
ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ላይ አሥራትን ካልከፈለ እግዚአብሔር አምላክ ሰርቃችሁኛል ይላል።
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትን ሚል 3:8
አሥራት የሚከፈለው ለካሕናት መገልገያ በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር መንግስት ማስፋፊያ ነው። ካሕናት ሙሉ በሙሉ ጊዜያቸውን ሁሉ አምላካቸውን እንዲያገለግሉ ሕዝቡንም እንዲጠብቁ ነው።
አሥራትን በዘመነ ወንጌልም በዘመነ ክርስትናም እንደሚፈጸም ክብር ይግባውና ጌታችን እንዲህ ብሎ አዟል።
የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ የማቴ ፳፪÷፳፩
እግዚአብሔር አምላክ ዘጠኙን ሊባርክልን አንዷን ብቻ ለኔ ሥጡኝ ሲለን
ገንዘብ አምላኪዎች እንዳንሆን ከእርሱም ይልቅ ገንዘብን እንዳንወድ ወይም ለእርሱ ያለንን ፍቅር ያይበት ዘንድ ስለሚፈልግ አሥራትን በኩራትን ምፅዋትንና ለጋስነትን አስተማረን አንድም ቸር ለጋስ መሆን እርሱን መምሰል ነውና። ስለዚህ እኛም ይህን በመረዳት ከምናገኛት ገቢያችን ላይ አነሰም በዛም ሳንል አስራታችንን በስርአቱና በጊዜው እናውጣ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!ምንጭ:- መጽሐፈ አሚን ወሥርዓት
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 сентября 2024 17:39
እንደ ዝማሬ ዳዊት ገጽ ከሁለት አመት በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል እና ቢራ ዙሪያ ትልቅ የሆነ የሚድያ ንቅናቄ ቢያደርግም ግቡን ሳይመታ ቀርቶ ነበር።
አሁንም የተጀመረው የግዜ ጩኸት ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ነገሩን ከኛ በዘለለ ከላይ ባሉ አባቶቻችን ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በሕግ ዕውቀት ያላችሁ የተዋህዶ ልጆችም ቤተ ክርስቲያናችሁ ትፈልጋቹሀለች። የኛን ክብር ማስጠበቅ እምንችለው እኛው ነን።
እንደ ማሳሰብያ ማስተላለፍ የምንፈልገው መልዕክት ግን በተለያዩ ሶሺያል ሚድያ ይህን ድርጊት በመቃወም የተለያየ ቪድዮ በምትሰሩ ግዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ስዕለ አድኅኖ ክብር በማያወርድ እና ኦርቶዶክሳዊ ሥነምግባርን በተላበሰ መልኩ ሊሆን ይገባል። በአንዳንድ ቦታ ያልተገባ ድርጊት ስላስተዋልን ነው።
/channel/ortodoxmezmur/12787
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 сентября 2024 05:20
ታላቅ በሆነው
ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ቆምኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ ለአለም ተሰማ
አዝ
ስመጣ ባልጋ ነበረ
ተስፋዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በጠበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት
አዝ
ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር የታጨሽ
የእምነቴ ሐሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለሁኝ በህይወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል
አዝ
እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
ባንቺ አፍሮ የሄደ ማነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል
አዝ
ስመጣ ባልጋ ነበረ
ተስፋዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት።
ዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሠ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 сентября 2024 18:07
በዘባነ ኪሩብ
በዘባነ ኪሩብ ለሚቀመጠው
በእሳት ድንጋዮች ቅጥሩን ላጠረው
ዘምሩ ለእግዚአብሔር ለጌታ ዘምሩ
የተከበረ ነው በሰማይ በምድሩ 2
አዝ
ኢሳይያስ ሲያየው እጅግ አፈረ
የተፈራ ነው የተከበረ
የሰማይ ደጆች ተንቀጠቀጡ
ለቅዱስ ስሙ ክብርን ሲሰጡ
አዝ
ያልተቀደሰ ለምጽ ያነደደው
እንዴት ይችላል ሊያመሰግነው
በል ፍቀድልኝ ፍቅር ነህና
ልግባ መቅደስህ ላቅርብ ምስጋና
አዝ
ዙፋንህ ታየኝ ትምክህቴ ሆይ
ስትመሰገን በሰማይ ላይ
ሲያመሰግንህ ያልተደሰተ
ባይተዋር አልሁን አልውጣ ካንተ
አዝ
ቅኔ የሞላበት ያን ሰገነት
ልቀላቀለው ተመኘው በእውነት
ልዘምርልህ ባይገባኝም
ዝም የሚል ልሳን አልሰጠኸኝም
ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 сентября 2024 05:01
አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ
አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ
በውስጡ ለመኖር እናፍቃለሁ
ሰላም እንድሆን በቤት በደጄ
ወደ ማደርያህ ልምጣ ማልጄ
እንድሰለጥን በመላእክት ዜማ
የሕወትን ቃል ከአፍህ ልስማ
እንዲቀል ሸክሜ ከትክሻዬ
ወደ ዙፋንህ ልቅረብ ጌታዬ
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
አዝ
ተመለሰልኝ ደስታ ሰላሜ
ቤትህ መጥቼ በመሳለሜ
ስጋዬም ዳነ ታደሰች ነፍሴ
ወደ ማደርያህ በመግስገሴ
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
አዝ
የተማርኩባት የሰላም ቅኔ
የተባረከው እድሜ ዘመኔ
የተለወጠው ሞቴ በሕይወት
እኔ እናፍቃለሁ የእግዚያብሔርን ቤት
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
አዝ
የሰማይ ዜማ የሚሰማባት
ሰዎች ከሀዘን የሚጽናኑባት
የጸሎት ስፍራ የአምልኮት ቦታ
ቤተክርስትያን ውድዋ ስጦታ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 сентября 2024 06:02
መስከረም ፬
በዚህች ዕለት የእስክንድርያ ሊቀጳጳሳት አባ መቃርስ አረፈ።
አባ መቃርስ ከታናሽነቱ ጀምሮ በገድል የተጠመደ ነበር የምንኩስናንም ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጣ።በዚያም መነኮሰ በምንኩስናም ያለውን ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ።
ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀጳጳስ አባ ሚካኤል በአረፈ ጊዜም ኤጲስቆጶሳቱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሂደው
አባ መቃርስን ሊሾሙት ተስማሙ። አባታችን ግን ለዚች ሹመት የተገባው አይደለሁም ብሎ ሹመቱን እንቢ አለ ቢሆንም ግን
በገመድ አስረው ሾሙት።
በሹመቱ ወራትም ከራሱ ከሚገባውን ግብር ለቤተክርስቲያን ይሰጣል ለድኖችና ለችግረኞችም ይመጸውታል እንጅ ከቤተክርስቲያን ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም። በሹመቱም ሃያ ሰባት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም በአገልግሎት ደስ አሰኝቶ በዚህች ዕለት አረፈ።
በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
13 сентября 2024 19:36
የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም
የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም አለው። ምሳሌውን ግልጽ ለማድረግ ከታች ያለውን ስዕላዊ መግለጫ እንመለከት እና ወደ ትንታኔው እንሂድ።
ከበሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ግራና ቀኝ ሲመታ ስንመለከልት ጌታችን በአይሁድ እጅ በጥፊ መመታቱን ያስታዉሰናል።
፩. ሰፊው የከበሮው አፍ
የመለኮት ምሳሌ ነው። ይህ የከበሮ አፍ የጌታችንን የባህሪ አምላክነት ምሉዕ በኵለሄ መሆኑን ስልጣኑ ወሰን ድንበር እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው። የአፉን መስፋት ስንመለከት በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በህልውና በመለኮት ባሕርይ አባቱ ከአ ባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ ሁሉን የያዘ ሁሉን የሚገዛ መሆኑን እናስባለን።
፪. ጠባቡ የከበሮው አፍ
የትስብእት ምሳሌ ነው በመዝሙር ጊዜ
እየተቆረቆረ ድምጽ የሚሰጠው ጠባቡ
የከበሮ አፍ የወልድ እግዚአብሔርን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ መገለጥ የሚያመለክተን ነው። ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ እሱ በስልጣኑ ሽረት በመለኮቱ ኅልፈት የሌለበት ቢሆንም ስጋን ተዋህዶ ተገልጧል። ይህንን ጠባብ የከበሮ አፍ ስንመለከት ሁሉን የሚገዛ እሱ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን እናስባለን። ዩሐ፤፩፡፩-፩፬
፫. ከበሮው የሚለብሰው ጨርቅ
ከበሮ የጌታችን ምሳሌ እንደሆነ ከላይ
አይተናል። ከዚህ አንጻር የለበሰው ጨርቅደግሞ በዕለተ ዓርብ አይሁድ ጌታችንን ያለበሱት ጨርቅ (ቀይ ከለሜዳ) ምሳሌ ነው።
''ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት'' ማቴ 26:28
፬. በከበሮው ላይ የተለጠፈው ጠፍር
በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። ጠፍሩን በከበሮው ላይስንመለከት በጌታችን ጀርባ ላይ የታየውን ሰንበር እናስታውሳለን።
''እጆቼን እና እግሮቼን ቸነከሩኝ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ'' መዝ 21(22):16
እንዲል ጌታችን አጥንቱ እስኪቆጠር ጀርባው እስኪቆስል ተገርፏልና የዚያ
ምሳሌ ነው።
፭. የከበሮው ማንገቻ
የከበሮውን መምታት ስናስብ በአንገታችን የምናስገባው ማንገቻ ጌታችንን አስረው የጎተቱበት ገመድ ምሳሌነው። አይሁድ ጌታችንን ወደ ቀራኒዮ ሲወስዱት የእጁ መጋፊያና መጋፊያ እስኪገጥም ድረስ በገመድ የእንግርግሪት አስረው ጎትተውታል ማንገቻውን ከበሮው ላይ ስናይ ይኽንን ጌታችን የታሰረበትን
ገመድ እናስታውሳለን።
በተጨማሪም በከበሮ ውስጥ የሚገኙት አምስት ጠጠሮች የአምስቱ አእማደ ሚስጥራት ምሳሌዎች ናቸው።
Читать полностью…