ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አንድ ስም አለ

አንድ ስም አለ ከአፌ የማለየው
በዘመን ብዛት የማልተወው
ማርያም/3/ እላለሁ
መዳኔን ሳስብ ምክንያቴን እንዴት እረሳለሁ

አዝ

እኔማ ውዳሴዋን ከልጅነት ጀምሬ
ከአንደበቴ ሳለየው አለሁኝ እስከዛሬ
አላጥፍም አትሮንሱን ተርኬም አልጨረስኳት
ዘመኔ ሲያበቃ ነው የምስጋናዬ እልባት
በቀን ካልጠራሁት ስሟን ካልደጋገምኩት
ቀኑም ቀን አይሆንም ይጎልብኛል ሰላም
አዝ

አንድ ጊዜ ታትማ ተስላ ከአይምሮዬ
የአገልግሎቴ ምዕራፍ የመቅደስ ትዝታዬ
ሲበዛ የማይሰለች የስሟ መጣፈጥ
ማርያም ስል ዉዬ አድራለሁ ቃሉ ከማር ቢበልጥ
በቀን ካልጠራሁት ስሟን ካልደጋገምኩት
ቀኑም ቀን አይሆንም ይጎልብኛል ሰላም
አዝ

ሞቴን ሞተልኝ እና የማህፀኗ ፍሬ
እርቆ የነበረው ተመለሰልኝ ክብሬ
ፍቅሯ እየቀሰቀሰኝ እነሳለው ማልጄ
ሰላም ለኪ እላለሁ ሰላም እንዲሆን ደጄ
በቀን ካልጠራሁት ስሟን ካልደጋገምኩት
ቀኑም ቀን አይሆንም ይጎልብኛል ሰላም
አዝ

የንጉስ እናት ሁና ይደንቃል ትህትናዋ
ጨመረ በትውልዱ የመወደድ ግርማዋ
ጨለማው ተገፎ ነው አሻግሬ ማየቴ
ብርሃን የከበባትን አስቀድሜ ከፊቴ
በቀን ካልጠራሁት ስሟን ካልደጋገምኩት
ቀኑም ቀን አይሆንም ይጎልብኛል ሰላም

ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሣሙኤል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

መስከረም 16 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እሰይ አበራ መስቀሉ

እሰይ አበራ መስቀሉ ለዓለም ሁሉ
ይለኮስ ችቦ ደመራ ጨለማው ይብራ

አዝ

የጥል ግድግዳ ፈረሰ እሰይ አበራ
ዳግም እምባችን ታበሰ እሰይ አበራ
ሕይወት ነው ለእኛ መስቀሉ እሰይ አበራ
ታምነናል እና በቃሉ እሰይ አበራ
አዝ

አይሁድ በክፋት ቢነሱ እሰይ አበራ
የሐሰት ካባ ቢለብሱ እሰይ አበራ
እሌኒ ሄደች ገስግሳ እሰይ አበራ
ቆስጠንጢኖስን አንግሳ እሰይ አበራ
አዝ

ዛሬም ኃይል አለው መስቀሉ እሰይ አበራ
አንድ አልፎበታል ለሁሉ እሰይ አበራ
አንሸሽገውም ከእውነት እሰይ አበራ
መውጊያውን ስለወጋበት እሰይ አበራ
አዝ

የመስቀሉ ቃል ለአመነው እሰይ አበራ
ከሞት ማምለጫ ስንቅ ነው እሰይ አበራ
ለዓለም ቢመስል ሞኝነት እሰይ አበራ
ተከፍሎበታል ስርዬት እሰይ አበራ

ዘማሪት ትርሃስ ገ/ እግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥልን በመስቀሉ ገደለ
በመስቀሉ ለሰው ልጅ ሰላምን አደለ
🥰እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ 🙏ከመስቀል አደባባይ 🥰

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።

📍 ወለጋ ነቀምት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፲፯


በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ለከበረ መስቀል በዓሉ ነው።

ንግስት ዕሌኒ የጎልጎታን ኮረብታ በአስጠረገች ጊዜ የከበረ መስቀልን አገኘችው ታላቅ ኮረብታም የሆነበት ምክንያት እንዲህ ነው ። ብዙ ድንቆች እና ተአምራቶች ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት መስቀል ይደረግ ነበና አይሁድ ተቆጡ።

እንዲህም ሥርዓትን ሠርተው አዘዙ በይሁዳ አገር ሁሉና በኢየሩሳሌም ቤቱን የሚጠርግ ሁሉ ወይም አፈር ወይም ጉድፍ የሚጠርግ በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ እንዲጥል አዘዙ።

እንዲህም እያደረጉ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣችበት ጊዜ ድረስ ከሦስት መቶ ዓመት በላይ ኖሩ።

እርሷም በመጣች ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል እስከሚያሳዩዋት ድረስ አይሁድን ይዛ አሠቃየቻቸው ያንን ኮረብታም እንዲቆፍሩ አስገደደቻቸው በመጨረሻም የከበረ መስቀሉ ከተቀበረበት ተገልጦ ወጣ ።

ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራች በዚች ቀንም አከበሩዋት ለመስቀሉም በዓልን መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን አከበሩለት።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።

📍 ሐዋሳ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።

📍 አ.አ መስቀል አደባባይ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።

📍 አ.አ ጎፋ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።

📍 በመቂ ከተማ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ መስቀል አበራ ሰማይም በከዋክብት ደመቀ።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን! አሜን🙏

📍 ሞጆ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
📍 ምስራቀ ጸሐይ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል አበራ

መስቀል አበራ ሰማይን አስጌጠ
በብርሃኑ ፀዳል ምድር ተለወጠ
ፀሐይን አሳየ ከሁሉም በላይ
ተዓምሩ ድንቅ ነው በምድር በሰማይ

አዝ

የመስቀሉን ነገር ለማያምኑት ሁሉ
ሞኝነት ነው እና እንዳለ በቃሉ
መስቀሉን ፍለጋ እሌኒ ተነሳች
ከተቀበረበት ከቦታው ደረሰች
አዝ

ለሦስት መቶ ዓመታት የተቀበረውን
በቆሻሻ ብዛት ተራራ የሆነውን
ኪራኮስ ነገራት የመስቀሉን ነገር
የደመራው እና የእጣኑን ምስጢር
አዝ

እጣንን አጢሳ ደመራን ደምራ
ማስቆፈር ጀመረች ታላቁን ተራራ
የግራውን መስቀል ቀድማ ብታገኘው
ህሙማን አምጥታ ፈትና ተወችው
አዝ

ሙት የማያስነሳ ህሙማን የሚያድን
መስቀልን አገኘች ሁለተኛውን
በደስታ መንፈስ ቁፋሮን ቀጠለች
ይህን ያሳያትን እያመሰገነች
አዝ

ብርሃን ተሞልቶ ሦስተኛውም መስቀል
ከተቀበረበት ወጣ በታላቅ ኃይል
ሙታንም ተነሱ ድውይ ተፈወሰ
በክርስቶስ መስቀል ዓለም ተቀደሰ
አዝ

ጥልን በመስቀሉ ገደለ (2)
በመስቀሉ ለሰው ልጅ ሰላምን አደለ(2)
አዝ

አማን በአማን(2)
መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም መሰረተ ቤተክርስቲያን(2)
አዝ

እውነት በእውነት(2)
መስቀል ብርሃን ነው ለመላው ዓለም መሰረት ነው የቤተክርስቲያን (2)

ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
📍 በምዕራብ አርሲ ዶዶላ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል

ዮም በዓለ መስቀሉ በሰማያት በላዕሉ(2)
ወዘነግሠ በምድር ( 2) ለአሕዛብ(2)

አዝ

የተዋሕዶ ሰንደቅ የሃይማኖታችን አምድ
መስቀል እፀ ሕይወት መርህ እና መንገድ
ጋሻ መመከቻ የዲያቢሎስን ፆር
መመልከቻችን ነው የገነት ደጅን በር
መስቀሉሰ ለክርስቶስ
ብርሃን እለ እለ ነአምን
ትብል ቤተክርስቲያን
(2)
ዛሕኑ ለባሕር ወመርሶ ለአሕማር
ዝንቱ ውእቱ መስቀል
(2)
አዝ

ርስተ ቤተክርስቲያን ዋልታ ጉልላቷ
ውበትና ጌጥ ነው አለት መሰረቷ
የኃጢዓትን ባህር ከፍለን ያለፍንበት
መስቀል በትረ ሙሴ ጥል የተሻረበት
መስቀል ብርሃን ለኵሉ ዓለም
መሠረተ ቤተክርስቲያን
  (2)
ወሐቤ ሰላም መድኃኔዓለም
መስቀል መድኅን ለእለ ነአምን
(2)
አዝ

የብርሃን አውታር የጽድቅ በር መግቢያ
ለተዋህዶ ልጆች ማህተም መለያ
የሕይወታችን ቅጥር ከጠላት መሸሻ
መስቀል ከለላ ነው በደልን ድል መንሻ
መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ
መስቀል ቤዛነ
( 2)
እኸ መድኃኒትነ ለእለ አምነ(2)
አዝ

የአዳም ዘርን ወዶ ጌታ የዋለበት
ዲያቢሎስ ተዋርዶ እርቅ የተገኘበት
ለክርስቲያን ወደብ አርማና ምልክት
መስቀል አመልካች ነው የክርስቶስን ሕይወት
ጸጋ ነሳይነ ወሕይወተ ረከብነ
በኃይለ መስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ
በኃይለ መስቀሉ
(2)
ኪያከ እግዚኦ ነአኲት ወንሴብሐከ እግዚአብሔር (2)
አዝ

ጸጋን ተቀበልን ሕይወትንም አገኘን
በመስቀሉ ኃይል በኢየሱስ ክርስቶስ
በመስቀሉ ኃይል
(2)
አቤቱ አንተን(2)እናመሰግንሃለን እግዚአብሔር
አቤቱ አንተን ቅዱስ(2)እናመሰግንሃለን ቅዱስ እግዚአብሔር(2)

ዘማሪ ዲ/ን ዘለዓለም ታከለ(ዘጎላ )
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ቤተ ክርስቲያን

ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?
በቀጥተኛ ትርጉም ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ቤተ እና ክርስቲያን  ከሚሉት ሁለት የግእዝ ቃላት የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቲያኖች  መኖሪያ /ቤት/ ማለት ነው፡፡ ይህም የክርስቶስ ቤት፣ የክርስቲያኖች  መሰባሰቢያ ቤት የሚል ትርጉም አለው፡፡

በግሪክ አቅሌስያ ትባላለች፤ የምርጦች ጉባዔ ማለት ነው፡፡ ይህች የምርጦች ጉባዔ የእግዚአብሔር ሕዝብ የነበሩት ጉባዔ እስራኤልን ያመለክታል፡፡

በዘይቤያዊ ፍቺ ቤተ ክርስቲያን ስንል ሦስት ትርጉም አለው ፡-

፩. ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን:- ተሰባስበን የምናስቀድስባት፣ የምንማርባትና ሌሎች ምሥጢራትን የምንፈጽምባት ናት፡፡ ይኽችም ቤት ጌታችን ኢየሱስ ቤቴ ስላላት የክርስቶስ ቤት እንላታለን፡፡

ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ  የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤ እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት  አላቸው።” ሉቃ. ፲፱ ፥ ፲፮

በዘመነ ሐዲስ የማርቆስ እናት የማርያም ቤት  የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ ሐዋርያት በዚያች  ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው ይጸልዩ ነበር፡፡
ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ  ነበር፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት  አጥብቃ ታደረግ ነበር። የሐዋ.፲፪፥፭ 


፪. የክርስቲያኖችን ስብስብ፡- በክርስቶስ አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖች ሁለትና ከዚያ በላይ የሚኖራቸው ስብስብ ቤተ ክርስቲያን ይባላል፡፡ ምክንያቱም በዚያ የእምነት አንድነት ውስጥ እግዚአብሔር አለና፡፡

“ሁለት  ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።” ማቴ. ፲፰ ፥ ፳ እንደተባለ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የበደለንን መክረን አልሰማ ቢለን ለቤተ ክርስቲያን ንገራት ያለን ለዚህች  የአባቶች ካህናት እና የምእመናን ስብስብ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን  ነው፡፡ ማቴ. ፲፰ ፥ ፲፯ ስለዚህች ቤተ ክርስቲያን በተለይም በሐዲስ  ኪዳን በተደጋጋሚ ተጽፏል፡፡ የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ የሐዋ. ፲፩፥፳፪፣ ፲፫፥፩፣ ሮሜ.፲፮፥፩፣ ፩ኛ.ቆሮ.፲፮፥፲፱፣ ፊልሞ.፩፥፪፣ ፩ኛ.ጴጥ. ፭፥፲፫ 

፫. እያንዳንዱ ክርስቲያን ፡- በእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች፣ የክርስቶስ አካላት ናቸውና ቤተ መቅደስ ይባላሉ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ
“የእግዚአብሔር  ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ  አታውቁምን?” ፩ኛ.ቆሮ.፫፥ ፲፮ ብሎ የተናገረው፡፡
እንዲሁም በሌላ ቦታ  “ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣኦት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ  የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና ፪ኛ ቆሮ. ፮ ፥ ፲፮ እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም  እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።” እንደተባለ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ማደሪያ ነንና ቤተ ክርስቲያን ተብለን  እንጠራለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- ሥራዓተ ቤተክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ነው ኃይላችን

መስቀል ነው ኃይላችን
ሞገስ ነው መመኪያችን
ላመነው መስቀል ለእኛ
አርማ ነው የመዳኛ

አዝ

የክርስቶስ ዙፋኑ
ቀራንዮ መካኑ
መስቀል ብርሃን ነው
በአንገታችን ያሰርነው
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)
አዝ

ጠላትን መመከቻ
ፍቅርን መመስረቻ
ከጦር ከቀስት ያመለጥነው
መስቀሉን ጋሻ አርገን ነው
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)
አዝ

ለማያምኑት ሞኝነት
ለታመንበት ሕይወት
መስቀሉ ነው ምልክት
የለንም ትምክህት
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)
አዝ

የደከሙት ማረፊያ
የስደተኞች መኖሪያ
መስቀል ድልድይ ነው
እሳቱን የሚያሻግረው
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)

ዘማሪ ዲያቆን አቤኔዘር ፍቃዱ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ

መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ (2)
ይኩነነ ቤዛ ይኩነነ ቤዛ (2)
መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ

አዝ

የድኅነት አርማችን የክብር ጌጣችን
ፍቅርን ያየንበት ነው መታረቂያችን
የክርስቲያን ትምክህት የመዳን ምልክት
እርሱን ለምንፈራ ያደለን በረከት
አዝ

እሌኒ አገኘችው ከዓመታት በኃላ
በደመራውም ጢስ ወጣ ከተራራ
የአይሁድ ክፋታቸው በዛው ያላስቀረው
ለምናምን ለእኛ መስቀል ኃይላችን ነው
አዝ

እግሮቹ የቆሙበት በክብር ለሰዓታት
እፀ መስቀሉ ነው የመዳን ምክንያት
እንሰግዳለን እኛም ይህንን ይዘን
በአበው ትውፊት ትምህርት ጸንተን
አዝ

ለእለ ይፈርሁከ ለምንፈራው ለእኛ
የሰጠን ምልክት መስቀል ነው መዳኛ
ነገሩ ገብቶናል ሞኝነት አደለም
ከሚድኑት ተርታ እንቁም ዘለዓለም
አዝ

መድኃኒተ ነፍስ ለኩሉ ፍጥረት
ሰላምን ያደለን የእርቅ ምክንያት
ዛሬም እንድናለን በእፀ መስቀሉ
በእርሱ የሚባርኩ ካህናት ስላሉ

ዘማሪት ፍሬ ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።

📍 አ.አ መስቀል አደባባይ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በዓል 🙏 🙏 🙏
📍 ሰሚት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/አርሴማ ቤ/ክ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እፀ መስቀል

እፀ መስቀል የክብር መውረሻ
ሞትን ድል መንሻ (2)

አዝ

የክብር ባለቤት እፀ መስቀል
የተሰዋበት እፀ መስቀል
እፀ መስቀሉ ነው እፀ መስቀል
የእኛ መድኃኒት እፀ መስቀል
አዝ

እንደእሌኒ ንግስት እፀ መስቀል
ፍፁም አክብራችሁ እፀ መስቀል
ሁላችሁ ገስግሱ እፀ መስቀል
መስቀሉን ይዛችሁ እፀ መስቀል
አዝ

ያለኃይለ መስቀል እፀ መስቀል
የሰላም አርማችን እፀ መስቀል
ሊጠፋ አይችልም እፀ መስቀል
ሰይጣን ጠላታችን እፀ መስቀል
አዝ

እሳተ መለኮት እፀ መስቀል
ዙፋኑ የሆነ እፀ መስቀል
ሰይጣንን የሚያነድ እፀ መስቀል
እፀ መስቀሉ ነው እፀ መስቀል
አዝ

እንደተባረከ እፀ መስቀል
ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ እፀ መስቀል
በመስቀል ብርሃን እፀ መስቀል
ወደ ሕይወት እንገስግስ እፀ መስቀል
አዝ

የተዋህዶ ልጆች እፀ መስቀል
ገስግሱ በተስፋ እፀ መስቀል
እፀ መስቀል ያዙ እፀ መስቀል
ጠላት እንዲጠፋ እፀ መስቀል

ዘማሪ በሱፍቃድ እንዳርጋቸው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን

📍 ወሊሶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ🙏

ደቡብ ምዕራብ ~ ከፋ ክልል ~በቦንጋ  ከተማ የመስቀል በዓል አከባበር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።

📍 ባህርዳር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼🌼🌼                                       🌼🌼🌼
                            🌼🌼🌼
                            🌼🌼🌼
                 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
                 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
                 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
                            🌼🌼🌼
                            🌼🌼🌼
                            🌼🌼🌼
                            🌼🌼🌼
                            🌼🌼🌼
"ደስ ይበለን እልል በሉ፣
       አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ፣
              በብርሃን መላት ዓለምን በሙሉ"


በዓሉ የደስታ፣ የሰላም የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን፡፡

                           🌼🌼🌼

የአስኮ መካነ ሕይወት ቅዱስ አማኑኤል እና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ መስቀል አበራ ሰማይም በከዋክብት ደመቀ።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን! አሜን🙏

📍 ጌቴሴማኒ ቅድስት ኪዳነምህረት> ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
አያት ደራርቱ አደባባይ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይጠብቅ።
📍 በወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከትና ባሕታ ለማርያም ቤተክርስቲያንን

ትንሽ ስለቦታው :-
እኔ እንግዳ ነኝ ከአ.አ ለስራ ሄጄ ነው ቦታው በተወሰኑ ግለስቦች (ኢ-አማንያን) በሆኑ ሰዎች በልማት አሳበው ደብሯን ለተወሰነ ግዜ ቦታ ተቀይሮ ነው ያለው ህዝቡም ተበታትኖ በዚህ መልኩ ሲያከብሩ እንዲው ድምፅ ከሆናችኋቸው በማለት ነው!! ፈጣሪ ያክብርልኝ መልካም በዓል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
📍 ፈረንሳይ ለጋሲዮን አደባባይ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የደመራ ዓመት


መስቀል የከበረው ትናንት መስሏቸው
ያዩ ተገረሙ ክብሩ አስደንቋቸው
ትናንትና አይደለም የበራው ደመራ
ዘንድሮ ዓመት ፈጀ የመስቀሉ ሥራ

ስንት አይሁድ ተነሥተው መስቀሉን ቀበሩ?
ስንትስ እሌኒዎች ሊያወጡት ቆፈሩ?
ጅጅጋ ሲዳማ ውጡ ተናገሩ

ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ደመራ
በእሳት ተለኩሳ ደምቃ ስታበራ
ካህናት ምእመናን እንደ ችቦ ነድደው
ስንቴ አከበሩት ለመስቀሉ ታርደው?

ስንት ጊዜ አፏጨ ዲያቢሎስ ተቆጣ
ስንት ሟርት ተሰማ ስንት ቁጣ መጣ?
በዕጣን ያልተገኘ ጌታ ያልሞተበት
ቅርፁ መስቀል ሆኖ መዳን የሌለበት
የወንበዴው መስቀል መስቀሉ መስሏቸው
ስንቶች ትተው ሔዱ ከእሌኒ እናታቸው?

ዓለም የዳነበት መስቀሉን ጨብጦ
ስለዘር የሚሰብክ እጅግ ተመስጦ
የተቃጠለውን መቅደስዋን እያየ
"ራስሽን አድኝ" ሲል ሲስቅ የታየ
ዘንድሮ አይደለም ወይ አይሁዱ የለየ?

ዘንድሮ ከበረ ለአንድ ዓመት ደመራ
በማያቆም ጥቃት በማያቆም ሴራ
ቅድስት ተዋሕዶ በጭንቅ ተወጥራ
አባቶችዋን ከፊት እንደ ጦር ሰድራ
በልጆችዋ ጩኸት በገና ደርድራ

በሰማዕታትዋ ደም ተረጭታና ርሳ
በየአደባባዩ ምሕላን አድርሳ
በፓትርያርክዋ ዓይን በምሬት አልቅሳ
እንደ ራሔል ለአምላክ ዕንባዋን አፍስሳ

ለመስቀሉ ቀን ግን ነጭ ልብስዋን ለብሳ
እንደ ቆስጠንጢኖስ በድል ልትነሣ
አምላክዋን ከፍ አድርጋ ኀዘንዋን ልትረሳ
ተስፋ ያደረገችው በመስቀል ታድሳ

ዘንድሮ ነው በዓል ዘንድሮ ደመራ
በዚህ ዓመት ተገኘን ከመስቀሉ ሥፍራ!!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 17 2012 ዓ.ም.
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​👆የቀጠለ

ቅዱስ ያሬድም ‹‹ኖትያት ነቢያት ራግናት ሐዋርያት›› በማለት ነቢያትን በዋናተኛ፣ ሐዋርያትን በጀልባ ቀዛፊ መስሎ ይናገራል፡፡ ከቀዛፊዎች ይልቅ ዋናተኞች ይደክማሉ፡፡ ዋናተኞች ውሃው አጥልቋቸው፣ መተንፈስ ተስኗቸው አንዳንዶቹ ከዳር ይደርሳሉ፤ አንዳንዶቹም በድካም በውሃ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ፡፡ ቀዛፊዎች ግን ምናልባት ሞገድና ማዕበል ካላሰጋቸው በስተቀር ይህ ኹሉ ውጣ ውረድ የለባቸውም፤ በጀልባዋ የተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን ለነቢያት በተስፋ እንጂ በአካላ አልተሰጠችም፡፡

ነቢያት ከእርሷ ሳይደርሱ ሞት ቀድሟቸዋል፡፡ ሐዋርያትም በነቢያት ድካም ገብተው ነቢያት የዘሩትን የትንቢት ዘር አጭደዋል፡፡ ወንጌል የነቢያት ዘር ናት፤ ዳሩ ግን ፍሬውን ለመብላት የታደሉት ሐዋርያት ናቸው፡፡ እሸቱ ሲደርስ የገበሬዎቹ የነቢያት ጌታ ክርስቶስ ዘሩን እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ ሐዋርያቱን በእርሻ መካከል ይዟቸው ገብቷል /ማቴ.፲፪፥፩/፡፡ በአበው ፋንታ ውሉድን ለመተካት የመጣው መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በመስቀሉ አንድ ማኅበር አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው መስቀሉን ‹‹ገባሬ ሰላም›› በማለት ይጠራዋል /ኤፌ.፪፥፲፫/፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን አንድ አድርጎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወረሰ የክርስቶስ መስቀል ነውና፡፡

፪. ሙታንና ሕያዋን

አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከመው መስቀል ሞትን አምጥቶብናል፤ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተሸከመው መስቀል ግን ሞትን ገድሎ ሕይወትን ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምክንያት የሞት መውጊያ ሲሰበር፣ የመቃብር ስቃይ ሲቋረጥ፣ የጨለማ ኀይል ሲሻር ከመስቀሉ ሥር ብዙ ሙታን እንደ አሸን ብቅ ብቅ አሉ፡፡ ምድር እስከዚያች ቀን ድረስ ሙታንን ትቀበል ነበር እንጂ ሕያዋንን ማስገኘት አትችልም ነበር፡፡ ሙታንና ሕያዋን የተፈላለጉበት መስቀል የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ በመስቀል ሙታን ሕያዋንን ፍለጋ ከመቃብር ወጥተው ወደ ከተማ ገቡ፡፡ ከታደለው የሕይወት ስጦታ የተነሣ ሞት አካባቢውን ለቆ ስለጠፋ በሩ እንደ ተከፈተለት እሥረኛ ሙታን ከመቃብር እየወጡ ከተማውን ሞልተውታል፡፡ ይህ ዕለት ሙታንን ከሕያዋን ጋር አፍ ለአፍ ያነጋገረ ዕለት ነው፡፡ ደመራው ሙታንን ከሕያዋን የሚለይ አይደለም፤ ታላቅነቱም እስከ ሲዖል ድረስ የሚታይ ነው፡፡

፫. ጻድቃንና ኀጥአን

የአዳም በደል በሕይወት የሚኖሩ ወንድማማቾችን በሁለት ሐሳብ ከፋፍሏቸው ነበር፡፡ የክርስቶስ የጽድቅ መስቀል ግን አንድ ሐሳብ ፈጠረላቸው፡፡ ጻድቁ አቤል ሳይበድል በደል የደረሰበት፣ ሳይገድል የተገደለ መኾኑ ከክርስቶስ ጋር ቢያመሳስለውም ሞቱ ግን ለሰው ልጆች ድኅነት አልጠቀመም፤ የፍጡር ደም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን አይችልምና ኹላችንም በመከራ ውስጥ ለመቆየት ተገደናል፡፡

የክርስቶስ ሞት ግን የድኅነታችን መሠረት ኾነልን፡፡ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መብራት ከፍ ብሎ ሲቀመጥ ኹሉን እንዲያሳይ ከምድር ከፍ ብሎ የተሰቀለው ክርስቶስም ጻድቃነ ብሊትንና ጻድቃነ ሐዲስን በዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል፡፡ በመስቀል ላይ የተፈጸመው ዕርቅ የኀጥአንን በደል ደምስሶላቸዋል፤ የጻድቃንን ጽድቅ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ጻድቃንም ኀጥአንም አንድ ኾነው መንግሥቱን በጸጋው ወረሱ፡፡

ኢያሱ በኢያሪኮ እንዳደረገው አሞራውያን ወጥተው እስራኤል ብቻ ምድሪቱን የወረሷት አይደሉም፡፡ መስቀሉ ለኹሉም አንድ መንግሥትን አውርሷቸዋል፤ ጊዜው የደመራ ነውና፡፡ በምድር ደምቆ የታየው ይህ ደመራ እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስም ይቀጥላል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Share አድርጉት ሌላውም እንዲማርበት።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал