መስከረም ፲፮
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።
አምና እንዳደረግነው ዘንድሮም በየ አካባቢያችሁ የደመራ በዓልን በምን መልኩ እያከበራችሁ እንደሆነ ጥራት ባለው ፎቶ ከእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ጋር በማድረግ በ 📩 @Zimaredawitmessanger ብትልኩልን፣ ለመላው የዝማሬ ዳዊት ቤተሰብ እናደርሳለን።
መሟላት ያለባቸው
መስቀል ቤዛነ
መስቀል ኃይልነ መስቀል ፅንዕነ
መስቀል ቤዛነ መድኃኒትነ
የዓለም ቤዛ (3) ለእኛ
ሰጠን መዳኛ (2)
አዝ
አዝ
አዝ
እሰይ እልል በሉ
እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2)
እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2)
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መስከረም ፲፭
መስቀለ ኢየሱስ
የፀቡ ግድግዳ የፈረሰበት
አጋንንትም አፍረው የወደቁበት
ዕፀ መስቀሉ ነው የሰው ልጅ ሕይወት (2)
አዝ
አዝ
አዝ
ተገኘ መስቀሉ
ለእኛ ለምናምነው መስቀል ኃይላችን ነው
ጠላትን ድል መንሻ መስቀል አርማችን ነው
ተነሱ ዘምሩ ክርስቲያኖች ሁሉ
ተገኘ መስቀሉ እሰይ እልል በሉ (2)
አዝ
አዝ
አዝ
መስቀል ኃይላችን
መስቀል ኃይላችን መስቀል ተፈጥሮአችን
መስቀል(2) ይላል መላው አካላችን
ሞትን ድል ነስተናል በከበረው ስሙ
ቀድሶታል እና ክርስቶስ በደሙ(2)
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ
በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ኮነ ሕይወትነ
እንዘምር ሆነን በደስታ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ሆኖናል ከፍታ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መስቀል ክብሬ ነው
ምልክቴ ነው ከቀስት ማምለጫዬ
መስቀል ክብሬ ነው ከክፉ መውጫዬ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መስቀል ኃይላችን
መስቀል (2) ኃይላችን ጠላትን ማጥፊያችን (2)
በመስቀል እንመካለን እንድንበታለን (2)
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን አደራችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን።
መንፈሳዊ የዜማ ስቱዲዮ ያላችሁ ወንድም እህቶች በውስጥ በኩል መልዕክት ይላኩልን። የምታውቁም ካላችሁ ጠቁሙልን @Zimaredawitmessanger 📩
ይለይብኛል
ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል /2/
አዝ
አዝ
አዝ
ይላል አንደበቴ
ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው
ትናንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ
ትልሃለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
በብርሃን ፀዳል
በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የፅጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ ሲሰማኝ እርካታ/2/
አዝ
አዝ
አዝ
መስቀል አበባ
መስቀል አበባ ነህ ውብ አበባ
አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ(2)
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መስከረም 16/1/2017 ዓ.ም
ምልክቴ ነው አርማዬ
ምልክቴ ነው አርማዬ
መስቀሉ መሸሸጊያዬ (3)
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!
ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት
የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ መስከረም ዐሥራ አምስት የሥጋው ፍልሰት ነው።
የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ባለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ አለ አለው።
ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራዕይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ።
በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስገና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።
ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር፤ ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ አረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከአምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው፤ እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።
በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም፤ ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነች።
ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ይቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም ጋር ወጣ ከወደቡም በክብር አንሥተው ወደ መንግሥት አዳራሽ እስከ አስገቡት ድረስ በፍጹም ደስታ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተሸክመውት ተጓዙ።
ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በእርሱ ተአምራትን ገለጠ በሠረገላ ሥጋውን ጭነው በሁለት በቅሎዎች በሚስቡት ጊዜ ቍስጣንጢንዮስ ከሚሉት ቦታም ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስንም ሥጋ በዚያ እንዲያኖሩ ስለ ፈቀደ የሚስቡት በቅሎዎች ቆሙ። አልተንቀሳቀሱም በቅሎዎችንም ይመቷቸው ጀመሩ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ ይገባል የሚል ቃል ከአንዱ በቅሎ ሰሙ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉም አደነቁ።
እግዚአብሔርንም አመሰገኑት የበለዓምንም አህያ ያናገራት እርሱ እነዚህን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከሙትን በቅሎዎች ያናገራቸው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ንጉሡም በዚያ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ይህን የከበረና ንጹሕ የሆነ ዕንቈ ባሕርይ በውስጧ እንዲያኖሩ አዘዘ። ይኸውም የተመሰገነና የተባረከ ሐዋርያ የዲያቆናት አለቃና የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው የእስጢፋኖስ ሥጋው ነው።
የሰማዕቱ በረከት ይደርብን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መስቀል አርማ ለክርስቲያን
መስቀል አርማ ለክርስቲያን
ክርስቶስ በደሙ አትሞ የሰጠን
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መስቀል ተመርኩዘን
መስቀል ተመርኩዘን ወንጌል ተጫምተን
ሃይማኖትን ሰበክን በክርስቶስ አምነን
ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያንን ክርስቶስ አለልን
አዝ
አዝ
አዝ
መስከረም ፲፬
ምሥጢረ ቁርባን
ቁርባን ፤ ማለት፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምኃ፣ መስዋዕት፣ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማለት ነው።
በብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ቁርባን (መስዋዕት) ምሳሌዎች
1. የመልከ ጼዴቅ መስዋዕት ዘፍ 14፥ 18። ዕብ 5 ፥6። ዕብ 6 ፥1። ህብስቱ የሥጋው፤ ወይኑ የደሙ ምሳሌ፤ መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ፤ አብርሐም የምዕመናን።
2. የእስራኤል ፋሲካ። ዘፀ 12፥ 1። ሞት የዲያብሎስ፤ እስራኤል የምዕመናን፤ በጉ ደግሞ የክርስቶስ ምሳሌ።
3. የእስራኤል መና። ዘፀ 16፥ 13። መና የጌታችን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም፤ እስራኤል የምዕመናን፤ ደመና የእመቤታችን
በብሉይ ኪዳን መስዋዕት ቁርባን ያቀረቡና በረከት ያገኙ አባቶች
1. አዳም አባታችን አዳም ባቀረበው መስዋዕት ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ቃል ገባለት። ዘፍ 3፥ 22። ገላ 4፥ 4።
2. ኖኅ ባቀረበው መስዋዕት ለኖኅና ለልጆቹ ምድርን ዳግም በመቅሰፍት እንደማያጠፋት በቀስተ ደመና ምልክት ቃል ገባላቸው። ዘፍ 9፥ 1። ዘፍ 9፥ 8።
3. አብርሐም ዘፍ 18፥ 3። አባታችን አብርሐም ባቀረበው መስዋዕት በዘርህ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ የሚለውን የተስፋ ቃል ሰማ፤ ያም ዘር የተባለው ለጊዜው ይስሐቅ ሲሆን፤ ፍጻሜው ግን ለጌታ ነበር።
4. መልከ ጼዴቅ ዘፍ 14 ፥ 17። መዝ 109፥ 4። ዕብ 5፥ 6። በእግዚአብሔር ፊት ባቀረበው መስዋዕት ክህነቱ ለዘለዓለም ተብሎለት የክርስቶስ ምሳሌ ሆነ። ዕብ 7፥ 1።
5. ዳዊት መዝ 131፥ 11። መስዋዕት ባቀረበበት ሠዓት ከአብራክህ የተገኘው ልጅህ በዙፋንህ ይነግሣል ተባለለት፤ ይህም ለጊዜው የተነገረው ለሰሎሞን ሲሆን ፍጻሜው ለክርስቶስ ነበር። መዝ 71 ፡1። ሌሎችም በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ መስዋዕታቸውን እያቀረቡ በረከት ተቀብለዋል።
ምሥጢረ ቁርባን በሐዲስ ኪዳን
በብሉይ ኪዳን ዘመን ይቀርብ የነበረው የመስዋዕት ቁርባን፤ ከበግ፤ ከላምና፤ ከተለያዩ እንስሳት ነበር። በሐዲስ ኪዳን ግን እንስሳት በቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕት (ቁርባን) ሆነው አይቀርቡም መስዋዕት ሁሉ በክስቶስ ሥጋና ደም ተጠቃሏል። ይህንም የአዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተው ራሱ ጌታችን ሲሆን ፤ በጸሎተ ሐሙስ ማታ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እንዳሉ በመጀመሪያ መስዋዕተ ኦሪትን ሰርቶ ካሳለፈ በኋላ ኅብስቱና ወይኑን ባርኮ “ነገ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬና የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው ብሉ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው”። ማቴ 26፥ 26።
ዛሬ ካህኑ ኅብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ ጸሎተ ቅዳሴውን እየጸለየ ሲባርከው እንደዚያ ጊዜው ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑም ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል። ይህንም ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም በምንቀበልበት ጊዜ ለእኛ ሲል የተቀበለውን መከራና ስቃይ እያሰብን ራሳችንን በንስሓ ከኃጢአት ንጹህ አድርገን ከንስሓ የቀረውን በደላችንን እንደሚደመስስልን ፤ ከበደል እንደሚያነጻንና የዘለዓለም ሕይወት እንደሚሰጠን አምነን መሆን አለበት። በ1ቆሮ 11 ፥ 23 “ይህንም ለመታሰቢያዬ አድርጉት ”የሚለው ቃል ሥጋውንና ደሙን በምንቀበልበት ጊዜ ስለሰው ልጆች ሲል በቀራንዮ አደባባይ የተቀበለውን መከራና በልባችን ውስጥ የተሳለውን አምላካዊ ፍቅሩን እያስታወስን እንድንኖር ነው መታሰቢያ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይረሳ ነገርን ነውና። ገላ 3፥1
ጌታችን ይህን ምሥጢር ከማሳየቱ (ከመመስረቱ) በፊት በዮሐ 6 ፥ 25-8። “ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ (ሕይወትን የሚሰጥ) ነው ”በማለት ስለምሥጢረ ቁርባን በስፋት አስተምሯል። ክፍል ፪ ይቀጥላል
እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱስ ስጋው ከክቡር ደሙ እንድንሳተፍ መልካም ፍቃዱ ይሁንልን። አሜን!
ምንጭ:- የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት የተልኮ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መስቀል ብርሃን ነው
መስቀል ብርሃን ነው ለመላው ዓለም
ፍቅርን የሚያድል የሚሰጥ ሰላም
መድኅን ክርስቶስ በደሙ ያከበረው
ለክርስቲያን መስቀል ትምክህት ነው
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መስከረም ፲፫
በዚች ቀን ታላቅና ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ባስልዮስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
በአንድ ወቅት አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው። አንድ ሰይጣንም መጥቶ ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። ዲያብሎስም ክርስቶስን ክጃለሁ ብለህ ፃፍ እና የምትፈልገውን አደርግልሀለው አለው። እርሱም የክህደቱን ቃል ጻፈለት።
በማግስቱ ጠዋት በሃገረ ገዥው ቤት ታላቅ ግርግር ሆነ። ልጃቸው "ያን አገልጋይ ካላጋባችሁኝ ራሴን አጠፋለሁ" አለች። ቢለምኗትም ልትሰማ አልቻለችም። ወላጆቿ ግራ ስለተጋቡ ከምትሞት ብለው እያዘኑ ልጃቸውን ከአጋንንት ጋር ለተዛመደ ሰው ሰጡ። እነርሱ ተጋብተው ኑሯቸውን ቀጠሉ። ወላጆች ግን ስለአንድ ልጃቸውን ይጾሙ ይጸልዩ ነበር። አንድ ቀንም ባሏን ጠርታ "ቤተ ክርስቲያን ተሳልመህ፤ ቆርበህ፤ ስመ እግዚአብሔር ጠርተህ፤ ታውቃለህ?" አለችው። እርሱም "በጭራሽ አላውቅም" አላት። "ለምን?" ብትለው የሆነውን ነገር ሁሉ ነገራት። ለረዥም ሰዓት አለቀሰች። ፈጥናም ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ሒዳ ከእግሩ ሥር ወድቃ አለቀሰች።
ቅዱሱም ያን ሰው "መዳን ትፈልጋለህ?" አለው። ሰውየው መልሶ "ያቺን ደብዳቤ መመለስ የሚቻል ቢሆንማ እፈልግ ነበር" አለው። ወደ ራሱ በዓት ወስዶ አስገባውና በ4 አቅጣጫ በመስቀል አተመው። "ከ3 ቀን በሁዋላ እመጣለሁ" ብሎት ሔደ። ቅዱሱ ያለ ዕረፍት ይጋደልም ጀመር። በ3ኛው ቀን መጥቶ "እንዴት ነህ?" አለው "አባቴ! አጋንንት አሰቃዩኝ" አለው፤ "አይዞህ!" ብሎት ወጣ። በ6ኛው ቀን መጥቶ "አሁንስ?" አለው:: "አባ! ስቃዩ ቀረልኝ: ግን ደብዳቤዋን እያሳዩ ያስፈራሩኛል" አለው:: "በርታ" ብሎት ሔደ።
እንዲህ በ3 በ3 ቀናት እየተመላለሰ ለ13 ጊዜ ጠየቀው። በ39ኛው ቀን መጥቶ "ዛሬ ምን አየህ" ቢለው "አባ! አጋንንትን ከእግርህ በታች ስትረግጣቸው አየሁ" አለው። ቅዱስ ባስልዮስ በ40ኛው ቀን ደወል ደውሎ መነኮሳት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ያን ሰው ከመሃል አቁሞ "እግዚኦ በሉ" አላቸው። ሲጨርሱም ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ ሁሉም ደስ ብሏቸው ምስጉን እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይህንን ቅዱስ አባት ባስልዮስን እያከበሩ ወደ ቤታቸው ገቡ።
በረከቱ ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ብዙ ልጆች አሉት
ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለፍፁም ምልጃው ለኔግን ይለያል
መላአኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መስከረም ፲፪
በድንግል ማርያም እመን። እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን።
መንፈሳዊ የዜማ ስቱዲዮ ያላችሁ ወንድም እህቶች በውስጥ በኩል መልዕክት ይላኩልን። የምታውቁም ካላችሁ ጠቁሙልን @Zimaredawitmessanger 📩
መስከረም ፲፩
ንስሐ
ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፡ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለመንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። ሉቃ.፭፥፲፬