ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም 16/1/2017 ዓ.ም


ምስባክ ፦ መዝ 59÷4-5
ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ        
ከመያምስጡ እመገጸ ቅስጥ                     
ወይድኃኑ ፍቁራኒከ
             
ትርጉም ፦
ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ
ለሚፈሩህ ምልክቱን ሰጠሃቸው
ወዳጆችህ እንዲድኑ
              
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምልክቴ ነው አርማዬ

ምልክቴ ነው አርማዬ
መስቀሉ መሸሸጊያዬ (3)

አዝ

ከቀስቱ ፊት ያመለጥኩበት መስቀሉ
ገዳዬን የረታሁበት መስቀሉ
በምጥ ወልዶኝ ሰው የሆንኩበት መስቀሉ
በይቅርታው የከበርኩበት መስቀሉ
የመስቀሉ ቃል ለእኔ ኃይሌነው
ጥልቁን ጨለማ በእርሱ አልፋለሁ (2)
አዝ

ሕይወት በዛ ከሰላሙ ጋር መስቀሉ
ተሰበከ ሰላም እና ፍቅር መስቀሉ
የድል አርማ ይዤ ተነሳሁ መስቀሉ
ምልክቴን መስቀሉን አየሁ መስቀሉ
የነሀሱን መዝጊያ ከፍቶታል ደሙ
በፍጥረት መሃል በዝቷል ሰላሙ (2)
አዝ

ሃሌሉያ ስለማዳኑ መስቀሉ
እንዳከበረኝ ተወግቶ ጎኑ መስቀሉ
እሳት መሃል አልፋለሁ ገና መስቀሉ
ምልክቴ መስቀል ነው እና መስቀሉ
ትምክህት የለኝም ከመስቀል ሌላ
ከእርሱ ላልለይ አለኝ መሃላ (2)
አዝ

የጠላቴ መውጊያው ተመታ መስቀሉ
ቀራንዮ ሲያድነኝ ጌታ መስቀሉ
ከእንግዲህ እማ የመስቀሉ ነኝ መስቀሉ
የጠላት ጦር ሞት የማይገዛኝ መስቀሉ
ጥልን ገድሎታል ታውጇል ሰላም
ከፍ አድርጎኛል መድኃኔዓለም (2)

ዘማሪ ገዛኸኝ ኤርባ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!

​​ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት

የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው  ቅዱስ እስጢፋኖስ መስከረም ዐሥራ አምስት የሥጋው ፍልሰት ነው።

የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ባለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ አለ አለው።

ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራዕይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ።

በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስገና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።

ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር፤ ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ አረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከአምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው፤ እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።

በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም፤ ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነች።

ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ይቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም ጋር ወጣ ከወደቡም በክብር አንሥተው ወደ መንግሥት አዳራሽ እስከ አስገቡት ድረስ በፍጹም ደስታ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተሸክመውት ተጓዙ።

ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በእርሱ ተአምራትን ገለጠ በሠረገላ ሥጋውን ጭነው በሁለት በቅሎዎች በሚስቡት ጊዜ ቍስጣንጢንዮስ ከሚሉት ቦታም ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስንም ሥጋ በዚያ እንዲያኖሩ ስለ ፈቀደ የሚስቡት በቅሎዎች ቆሙ። አልተንቀሳቀሱም በቅሎዎችንም ይመቷቸው ጀመሩ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ ይገባል የሚል ቃል ከአንዱ በቅሎ ሰሙ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉም አደነቁ።

እግዚአብሔርንም አመሰገኑት የበለዓምንም አህያ ያናገራት እርሱ እነዚህን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከሙትን በቅሎዎች ያናገራቸው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ንጉሡም በዚያ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ይህን የከበረና ንጹሕ የሆነ ዕንቈ ባሕርይ በውስጧ እንዲያኖሩ አዘዘ። ይኸውም የተመሰገነና የተባረከ ሐዋርያ የዲያቆናት አለቃና የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው የእስጢፋኖስ ሥጋው ነው።

የሰማዕቱ በረከት ይደርብን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል አርማ ለክርስቲያን

መስቀል አርማ ለክርስቲያን
ክርስቶስ በደሙ አትሞ የሰጠን

አዝ

የመስቀሉን ነገር ላመንንበት ለእኛ
ጠላትን ድል መንሻ ሆኖናል መዳኛ
የመስቀሉን ነገር ላላመኑ
ሆናቸው ሞኝነት ራቁ ከካህኑ
አዝ

መስቀል ላይ ነበረ የቀኙ ቀማኛ
እድሜውን የጨረሰ ሆኖ ወንጀለኛ
የመስቀሉን ነገር ቢረዳ እና ቢያምን
አዳምን በመቅደም ወረሰ ገነትን
አዝ

አይሁድ ነገሥታቱ የኦሪት ካህናት
ምስጢረ ስጋዌ ያልተረዱ በእውነት
መስቀሉን ቢያደርጉት መቅጫ ወንጀለኛ
ክርስቶስ በደሙ አረገው መዳኛ
አዝ

የመስቀሉ ፍቅር በእውነት የገባን
የእሌኒ ልጆች ተባልን ክርስቲያን
ተሸክመነዋል መስቀሉን አውጥተን
በአንገታችን አስረን በልባችን ቀርፀን

ዘማሪ ዲያቆን ሄኖክ ሞገስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ተመርኩዘን

መስቀል ተመርኩዘን ወንጌል ተጫምተን
ሃይማኖትን ሰበክን በክርስቶስ አምነን
ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያንን ክርስቶስ አለልን

አዝ

ንግሥቲቷ እሌኒ በጣም የታደለች
በእጣን ጢስ ተመርታ መስቀሉን አገኘች
መድኃኒት ስትፈልግ ኪራኮስን ይዛ
መስቀሉን አገኘች የዓለሙን ቤዛ
አዝ

ሙታንም ተነስተው ያመሰገኑት
ዕፀ መስቀሉ ነው የእኛ መድኃኒት
መስቀል ምርኩዛችን ጎዳና ወንጌል
ወደ ገነት እንጂ አንወርድም ሲኦል
አዝ

ንኡ ንወድሶ ለእፀ መስቀል
የተሸከመውን የአምላክን ቃል
ንኡ ንወድሳ ለማርያም ድንግል
አክሊለ ምዕመናን መካ ደናግል(2)

ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፲፬


በዚህች ዕለት ቅዱስ አባ አጋቶን ዘዓምድ አረፈ።

እኚህ አባት ዘዓምድ ይባላሉ። ምክንያቱም ለ50 ዓመታት አንድ ምሰሶ ላይ ያለ ዕረፍት ጸልየዋልና ነው። ገና ከልጅነታቸው መጻሕፍትን የተማሩ ሲሆኑ ምናኔን አጥብቀው ይፈልጓት ነበር። በዚህም ራሳቸውን በትሕርምት እየገዙ በዲቁና ማዕርጋቸውም እያገለገሉ እስከ 35ዓመታቸው ቆዩ። በዚህ ጊዜ ደግሞ ይገባሃል ብለው ቅስናን ሾሟቸው።

እኚህ አባት አብዝተው ምንኩስናን ይፈልጉ ነበርና አስፈላጊውን የምንኩስና ፈተና ካለፉ በኋላም ምንኩስናን ከአባቶች ተቀበሉ። በዚያው በገዳመ አስቄጥስ በጽኑ ገድል ተጠምደው ለ15 ዓመታት አገለገሉ። እድሜአቸውም 50 በሞላ ጊዜ በልቡናቸው እንደ አባ ስምዖን ዘዓምድ ለመጋደል ወሰኑ።

አባ አጋቶን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ ከገዳሙ ወጡ። ወደ ዓለም ሳይገቡ ከዓለምም በጣም ሳይርቁ አንድ ረዥም ምሰሶ አገኙና ከላዩ ላይ ወጡ። ለ50 ዓመታትም ከዚያች ዓምድ (ምሰሶ) ወርደው ለሥጋቸውም ዕረፍትን ሰጥተውት አያውቁም። ለአካባቢውም የብርሃን ምሰሶ ሆኑ። የታመመ ቢኖር ይፈውሱታል። የበደለውን በንስሃ ይመልሱታል። ሰይጣን የቋጠረውን ይፈቱታል።

ጻድቁ አባ አጋቶን ዘዓምድ ከእነዚህ የቅድስና ዘመናት በኋላ በተወለዱ በ100 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐረፉ።

በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ምሥጢረ ቁርባን

ቁርባን ፤ ማለት፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምኃ፣ መስዋዕት፣ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማለት ነው።

በብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ቁርባን (መስዋዕት) ምሳሌዎች

1. የመልከ ጼዴቅ መስዋዕት ዘፍ 14፥ 18። ዕብ 5 ፥6። ዕብ 6 ፥1። ህብስቱ የሥጋው፤ ወይኑ የደሙ ምሳሌ፤ መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ፤ አብርሐም የምዕመናን።
2. የእስራኤል ፋሲካ። ዘፀ 12፥ 1። ሞት የዲያብሎስ፤ እስራኤል የምዕመናን፤ በጉ ደግሞ የክርስቶስ ምሳሌ።
3. የእስራኤል መና። ዘፀ 16፥ 13። መና የጌታችን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም፤ እስራኤል የምዕመናን፤ ደመና የእመቤታችን

በብሉይ ኪዳን መስዋዕት ቁርባን ያቀረቡና በረከት ያገኙ አባቶች

1. አዳም አባታችን አዳም ባቀረበው መስዋዕት ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ቃል ገባለት። ዘፍ 3፥ 22። ገላ 4፥ 4።
2. ኖኅ ባቀረበው መስዋዕት ለኖኅና ለልጆቹ ምድርን ዳግም በመቅሰፍት እንደማያጠፋት በቀስተ ደመና ምልክት ቃል ገባላቸው። ዘፍ 9፥ 1። ዘፍ 9፥ 8።
3. አብርሐም ዘፍ 18፥ 3። አባታችን አብርሐም ባቀረበው መስዋዕት በዘርህ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ የሚለውን የተስፋ ቃል ሰማ፤ ያም ዘር የተባለው ለጊዜው ይስሐቅ ሲሆን፤ ፍጻሜው ግን ለጌታ ነበር።
4. መልከ ጼዴቅ ዘፍ 14 ፥ 17። መዝ 109፥ 4። ዕብ 5፥ 6። በእግዚአብሔር ፊት ባቀረበው መስዋዕት ክህነቱ ለዘለዓለም ተብሎለት የክርስቶስ ምሳሌ ሆነ። ዕብ 7፥ 1።
5. ዳዊት መዝ 131፥ 11። መስዋዕት ባቀረበበት ሠዓት ከአብራክህ የተገኘው ልጅህ በዙፋንህ ይነግሣል ተባለለት፤ ይህም ለጊዜው የተነገረው ለሰሎሞን ሲሆን ፍጻሜው ለክርስቶስ ነበር። መዝ 71 ፡1። ሌሎችም በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ መስዋዕታቸውን እያቀረቡ በረከት ተቀብለዋል።

ምሥጢረ ቁርባን በሐዲስ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን ዘመን ይቀርብ የነበረው የመስዋዕት ቁርባን፤ ከበግ፤ ከላምና፤ ከተለያዩ እንስሳት ነበር። በሐዲስ ኪዳን ግን እንስሳት በቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕት (ቁርባን) ሆነው አይቀርቡም መስዋዕት ሁሉ በክስቶስ ሥጋና ደም ተጠቃሏል። ይህንም የአዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተው ራሱ ጌታችን ሲሆን ፤ በጸሎተ ሐሙስ ማታ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እንዳሉ በመጀመሪያ መስዋዕተ ኦሪትን ሰርቶ ካሳለፈ በኋላ ኅብስቱና ወይኑን ባርኮ “ነገ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬና የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው ብሉ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው”። ማቴ 26፥ 26።

ዛሬ ካህኑ ኅብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ ጸሎተ ቅዳሴውን እየጸለየ ሲባርከው እንደዚያ ጊዜው ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑም ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል። ይህንም ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም በምንቀበልበት ጊዜ ለእኛ ሲል የተቀበለውን መከራና ስቃይ እያሰብን ራሳችንን በንስሓ ከኃጢአት ንጹህ አድርገን ከንስሓ የቀረውን በደላችንን እንደሚደመስስልን ፤ ከበደል እንደሚያነጻንና የዘለዓለም ሕይወት እንደሚሰጠን አምነን መሆን አለበት። በ1ቆሮ 11 ፥ 23 “ይህንም ለመታሰቢያዬ አድርጉት ”የሚለው ቃል ሥጋውንና ደሙን በምንቀበልበት ጊዜ ስለሰው ልጆች ሲል በቀራንዮ አደባባይ የተቀበለውን መከራና በልባችን ውስጥ የተሳለውን አምላካዊ ፍቅሩን እያስታወስን እንድንኖር ነው መታሰቢያ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይረሳ ነገርን ነውና። ገላ 3፥1

ጌታችን ይህን ምሥጢር ከማሳየቱ (ከመመስረቱ) በፊት በዮሐ 6 ፥ 25-8። “ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ (ሕይወትን የሚሰጥ) ነው ”በማለት ስለምሥጢረ ቁርባን በስፋት አስተምሯል። ክፍል ፪ ይቀጥላል

እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱስ ስጋው ከክቡር ደሙ እንድንሳተፍ መልካም ፍቃዱ ይሁንልን። አሜን!

ምንጭ:- የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት የተልኮ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ብርሃን ነው

መስቀል ብርሃን ነው ለመላው ዓለም
ፍቅርን የሚያድል የሚሰጥ ሰላም
መድኅን ክርስቶስ በደሙ ያከበረው
ለክርስቲያን መስቀል ትምክህት ነው

አዝ

መስቀል ብርሃን ነው ኢየሱስ ክርስቶስ
መስቀል ብርሃን ነው የነገሰበት
መስቀል ብርሃን ነው ከሳሹ ዲያብሎስ
መስቀል ብርሃን ነው የተጣለበት
መስቀል ብርሃን ነው ስሙን ለሚፈሩ
መስቀል ብርሃን ነው ምልክት የሆነ
መስቀል ብርሃን ነው የእኛ ምርኩዛችን
መስቀል ብርሃን ነው ቅዱስ መስቀሉ ነው
አዝ

መስቀል ብርሃን ነው ከቀስት እንድናመልጥ
መስቀል ብርሃን ነው የሆነን መከታ
መስቀል ብርሃን ነው ለቅዱስ መስቀሉ
መስቀል ብርሃን ነው ይገባል ሰላምታ
መስቀል ብርሃን ነው እንሰግድለታለን
መስቀል ብርሃን ነው እግሩ ለቆመበት
መስቀል ብርሃን ነው ለጌታችን ዙፋን
መስቀል ብርሃን ነው ሞት ለተረታበት
አዝ

መስቀል ብርሃን ነው ሥጋው ተቆርሶበት
መስቀል ብርሃን ነው ፈሶበታል ደሙ
መስቀል ብርሃን ነው በዛልን ይቅርታው
መስቀል ብርሃን ነው በዛልን ሰላሙ
መስቀል ብርሃን ነው በትምህርተ መስቀል
መስቀል ብርሃን ነው እናማትባለን
መስቀል ብርሃን ነው ሞትን አሸንፈን
መስቀል ብርሃን ነው ክፉን እናልፋለን
አዝ

መስቀል ብርሃን ነው የቤተክርስቲያን
መስቀል ብርሃን ነው መሰረቷ እርሱ ነው
መስቀል ብርሃን ነው ክብር እና ውበቷ
መስቀል ብርሃን ነው ጌጥ ጉልበቷ ነው
መስቀል ብርሃን ነው ተዐምርን የሚያደርግ
መስቀል ብርሃን ነው ድንቅን የሚሰራ
መስቀል ብርሃን ነው የሚገለጥበት
መስቀል ብርሃን ነው የአምላካችን ስራ

ዘማሪት ኢየሩሳሌም አለሙ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​መስከረም ፲፫

በዚች ቀን ታላቅና ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ባስልዮስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

በአንድ ወቅት አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው። አንድ ሰይጣንም መጥቶ ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። ዲያብሎስም ክርስቶስን ክጃለሁ ብለህ ፃፍ እና የምትፈልገውን አደርግልሀለው አለው። እርሱም የክህደቱን ቃል ጻፈለት።

በማግስቱ ጠዋት በሃገረ ገዥው ቤት ታላቅ ግርግር ሆነ። ልጃቸው "ያን አገልጋይ ካላጋባችሁኝ ራሴን አጠፋለሁ" አለች። ቢለምኗትም ልትሰማ አልቻለችም። ወላጆቿ ግራ ስለተጋቡ ከምትሞት ብለው እያዘኑ ልጃቸውን ከአጋንንት ጋር ለተዛመደ ሰው ሰጡ። እነርሱ ተጋብተው ኑሯቸውን ቀጠሉ። ወላጆች ግን ስለአንድ ልጃቸውን ይጾሙ ይጸልዩ ነበር። አንድ ቀንም ባሏን ጠርታ "ቤተ ክርስቲያን ተሳልመህ፤ ቆርበህ፤ ስመ እግዚአብሔር ጠርተህ፤ ታውቃለህ?" አለችው። እርሱም "በጭራሽ አላውቅም" አላት። "ለምን?" ብትለው የሆነውን ነገር ሁሉ ነገራት። ለረዥም ሰዓት አለቀሰች። ፈጥናም ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ሒዳ ከእግሩ ሥር ወድቃ አለቀሰች።

ቅዱሱም ያን ሰው "መዳን ትፈልጋለህ?" አለው። ሰውየው መልሶ "ያቺን ደብዳቤ መመለስ የሚቻል ቢሆንማ እፈልግ ነበር" አለው። ወደ ራሱ በዓት ወስዶ አስገባውና በ4 አቅጣጫ በመስቀል አተመው። "ከ3 ቀን በሁዋላ እመጣለሁ" ብሎት ሔደ። ቅዱሱ ያለ ዕረፍት ይጋደልም ጀመር። በ3ኛው ቀን መጥቶ "እንዴት ነህ?" አለው "አባቴ! አጋንንት አሰቃዩኝ" አለው፤ "አይዞህ!" ብሎት ወጣ። በ6ኛው ቀን መጥቶ "አሁንስ?" አለው:: "አባ! ስቃዩ ቀረልኝ: ግን ደብዳቤዋን እያሳዩ ያስፈራሩኛል" አለው:: "በርታ" ብሎት ሔደ።

እንዲህ በ3 በ3 ቀናት እየተመላለሰ ለ13 ጊዜ ጠየቀው። በ39ኛው ቀን መጥቶ "ዛሬ ምን አየህ" ቢለው "አባ! አጋንንትን ከእግርህ በታች ስትረግጣቸው አየሁ" አለው። ቅዱስ ባስልዮስ በ40ኛው ቀን ደወል ደውሎ መነኮሳት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ያን ሰው ከመሃል አቁሞ "እግዚኦ በሉ" አላቸው። ሲጨርሱም ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ ሁሉም ደስ ብሏቸው ምስጉን እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይህንን ቅዱስ አባት ባስልዮስን እያከበሩ ወደ ቤታቸው ገቡ።

በረከቱ ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብዙ ልጆች አሉት

ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለፍፁም ምልጃው ለኔግን ይለያል
መላአኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል

አዝ

ከመላእክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላክ የተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ
አዝ

ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
አዝ

በባህራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
አዝ

በጉዞ የረዳችሁ በባህር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ እንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
አዝ

ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፲፪


በዚህችም ቀን ደግሞ በኤፌሶን ከተማ የቅዱሳን፤ የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ ሆነ ይህም ለታላላቆች ጉባኤያት ሦስተኛ ነው።

በወቅቱ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው። ትምሕርቱም ክርስቶስን 2 አካል: ባሕርይ ነው (ሎቱ ስብሐት!) ማለትም እመቤታችንም የወለደችው ሰውን ነው ስለዚህ እመአምላክ አትባልም (ላቲ ስብሐት) ብሎ ነበር። ነገሩን ቅዱስ ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በቁስጥንጥንያ ንጉሥ ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ተደረገ።

አፈ ጉባዔው ቅዱስ ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው። ምላሽም አሳጣው። የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ። ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ።

በኋላም ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ
በድንግል ማርያም እመን። እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች

ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው። ያን ጊዜ ሊቁ ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ ብሎ ረገመው። ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ። እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሂዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች።

በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን።

መንፈሳዊ የዜማ ስቱዲዮ ያላችሁ ወንድም እህቶች በውስጥ በኩል መልዕክት ይላኩልን። የምታውቁም ካላችሁ ጠቁሙልን @Zimaredawitmessanger 📩

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፲፩


በዚህችም ቀን በእስክንድርያ አገር ትህትናን ገንዘብ ያደረገች ቅድስት ታዖድራ አረፈች።

ቅድስት ታዖድራ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ወላጆቿ ያመጡላትን ባል እሺ ብላ አገባች። በሥጋ ወደሙም ተወስነው ኖሩ። አንድ ቀን ግን ከቤተክርስቲያን ስትመለስ፤ በመልኳ ምክንያት ለኃጢአት ይፈልጋት የነበር አንድ ጎረምሳ ያዛት። በአቅምም አልቻለችውም፤ የሚፈልገውንም አድርጎ ከክብር አሳነሳት።

ታላቅ ኀዘን አዘነች፤ መሪር የሆነ ልቅሶንም አለቀሰች። የወንዶችንም ልብስ ለብሳ ወንድ መስላ ስሟንም ቴዎድሮስ በማለት በወቅቱ የሴቶች ገዳም አልነበረምና የወንዶች ገዳም ገባች። የምንኩስና ልብስንም ለበሰች። ሰይጣን ግን ፈተናውን አጸናባት።

በአንድ ወቅትም አንድ ወንድ ከአንዲት ብላቴና ጋር አመነዘረ፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። ወላጆቿም ድንግልናሽን ያጠፋው ማነው ብለው ጠየቋት። ሰይጣንም በእርሷ አድሮ፤ በገዳም ውስጥ የሚኖር አባ ቴዎድሮስ የሚባል ነው አለች። ወላጆቿም የተወለደውን ልጅ ወስደው ለገዳሙ አበምኔት የአባ ቴዎድሮስ ልጅ ነው ብለው ሰጡት።

አበምኔቱም ቅድስት ታዖድራን ልጁን አስይዘው ከገዳም አባረሯት። በበረሀም በብዙ ፈተና ሰባት አመት ኖረች። በኋላም ዳግመኛ ተቀብለው ወደ ገዳም አስገቧት። ጥቂት ቀንም ኖረች፤ መልካም ተጋድሎዋንም ፈጽማ በዚህች እለት አረፈች።

በረከቷ ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ንስሐ


ንስሐ ማለት ሐዘን፣ፀፀት፣ ቁጭት፣ ቀኖና፣ የኃጢአት ካሣ ማለት ነው፡፡ ንስሐ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መፀፀቱን ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው፡ ንስሐ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ደግሞ ንስሐ ማለት  ወደ እግዚአብሔር መመለስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ፣ ከኃጢአት መራቅ፣ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው።
 
ንስሐ ለመግባት ስናሳብ ከታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት አለብን፦
1. በአጥቢያችን ከሚገኝ ቤ/ክ  ክህነት ያላቸው በአገልግሎት ላይ ያሉ መልካም መንፈሳዊ ምግባር ያለቸውን አባቶች የንስሐ አባት መያዝ፤
2. የሰራነውን ኃጢአት ማመንእና በሰራነው ኃጢአት ከልብ አብዝተን መፀፀት፣ማዘንና ማልቀስ፤
3. እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በፍጹም ትህትና ራስን በማዋረድ መጠየቅ፤
4. ከእኛ ኃጢአት ይልቅ የእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅር ባይነት እንደሚበልጥ እና ይቅር እንደሚለን ያለጥርጥር ፍጹም ማመን፤
5. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን ንስሐ ለመግባት እና ቀኖናችንን ለመቀበል ማሰብ እና መወሰን፤
6. ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሰራናቸውን ኃጢአቶች ለማስታወስ መሞከር ከተቻለም ለማስታወስ ይረዳን ዘንድ በጽሑፍ መያዝ፤
7. ዳግም ወደ ሰራነው ኃጢአት እንደማንመለስ ለራሳችን ቃል መግባትና መወሰን፣ኃጢአትን መጸየፍ፤
8. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን የሰራነውን ኃጢአት ሳንደብቅ በግልፅ መናዘዝ።
9.የሚሰጠንን ቀኖና በትክክል መተግበር፤
10. ዳግም ወደ ኃጢአት እንዳንመለስ ራሳችንን በቃለ እግዚአብሔር ማነጽ፤
11. ዳግመኛ ለንስሐ መዘጋጀት።

ንስሐ ከሚደገሙ ምስጢራት መካከል አንዱ ነው። ሰዎች እንደመሆናችን በተደጋጋሚ በኃጢአት እንወድቃለን ስለዚህ በተደጋጋሚ ንስሐ ልንገባ ይገባናል ማለት ነው። ኃጢአት ለንስሐ አባት መናዘዝ ለምን አስፈለገ? ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘው ትዕዛዝ ስለሆነ ነው።
ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፡ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለመንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። ሉቃ.፭፥፲፬

ንስሐ ከገባን ቀኖናችንን በስርዓቱ ከፈፀምን በኋላ ንስሐችንን ፍፁም የሚያደርገው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ነው። ዮሐ 6፥33

ብዙዎቻችን መቁረብን እንደ ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ ለአዛውንቶች ብቻ አድርገን ስለምንቆጥር ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም። ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና። ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን። አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፲


በዚህች ዕለት ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል፤ ከሠሌዳዋም ቅባት የሚንጠፈጠፍባት የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ተዐምር ተገለጠ።

ይህችን ሥዕል የሳላት ቅዱስ ሉቃስ ነው። ወደ ጸዴንያ እንዴት መጣች ቢሉ፤ አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች በቤቷም እንግዳ ትቀበል ነበር። ድንግል ማርያምንም አብዝታ ትወዳት ነበር። በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ በእንግድነት መጣ። በማግስቱ ስትሸኘው ወዴት ነህ ብላ ጠየቀችው። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሆነ ነገራት። እርሷም ሲመለስ የእመቤታችንን ሥዕል አምጣልኝ አለችው።

ከዚህም በኋላ ከቦታው ደርሶ ሥዕሏን ሳይገዛ ተመለሰ፤ በመንገድም ሥዕሏን ለምን አልገዛህም? የሚል ድምጽ ሰምቶ ተመልሶ ገዛ። በጎዳናው እየተመለሰ ሳለም የሚያስፈሩ ወንበዴዎች፤ ኋላም አንበሳ ገጠመው፤ የያዛት ሥዕልም ቃል አውጥታ አዳነችው። አባ ቴዎድሮስም ይህን ድንቅ ተአምር ባየ ግዜ ሥዕሏን ወደ ሀገሩ ሊወስዳት ወደደ። በሌላ ከተማም አድርጎ ሊሄድ መርከብ ተሳፈረ።

በመርከቧ ሳለም ታላቅ ነፋስ ተነስቶ አቅጣጫውን አስቀይሮ ወደ ጸዴንያ ወሰደው። ኋላም ቢመሽበት ማርታ ቤት ሄደ እራሱን ግን አልገለጠም። በማግስቱም ተሰውሮ ከከተማው ሊወጣ ቢሞክር መውጫው ጠፍቶት ሲዞር ውሎ ተመለሰ። እንዲህም እያለ ሶስት ቀን ሆነው። ማርታም ይህን ተመልክታ ምን እንደሆነ ጠየቀችው። እርሱም ሁሉንም ነገራት።

በኋላም የመነኩሴውን እጅና እግር ስማ ሥዕሏን ተቀበለች። በታላቅ ክብርም አስቀመጠቻት። ያም መነኩሴ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ።

የእመቤታችን በረከት ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ቤዛነ

መስቀል ኃይልነ መስቀል ፅንዕነ
መስቀል ቤዛነ መድኃኒትነ
የዓለም ቤዛ (3) ለእኛ
ሰጠን መዳኛ (2)

አዝ

ከሰማያት (2) ወርዶ
ከድንግል ማርያም ተወልዶ
ጨለማውን ገፎ ብርሃን አሳይቶናል
የመስቀሉን ፍቅር ለእኛ ገልጦልናል
አዝ

እንደ ሄዋንማ እንደ አዳም ስህተት
ነበርን በግዞት ቤት ገሃነመ እሳት
የአዳምን እንባ ለቅሶ ተመልክቶ
ዓለምን አዳነ በመስቀል ላይ ሞቶ
አዝ

ፃድቃን ሰማዕታት የሰማይ መላእክት
ዘወትር በምስጋና ቅኔ የሚቀኙለት
አልፋ እና ኦሜጋ የሚኖር ዘለዓለም
የመስቀሉ ንጉስ ጌታ መድኃኔዓለም

ዘማሪ ሰሎሞን በዜ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እሰይ እልል በሉ

እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2)
እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2)

አዝ

የጥል ግድግዳ አበባ
የፈረሰበት አበባ
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር  አበባ
የታረቀበት አበባ
የእግዚአብሔር ልጅ አበባ   
የነገሰበት አበባ
የሞት አበጋዝ  አበባ      
የወደቀበት አበባ
አዝ

አይሁድ በቅናት አበባ         
መስቀሉን ቀብረው አበባ
ቢከድኑት እንኳን አበባ
በቆሻሻቸው አበባ
ጌታን መቃወም አበባ
ስለማይችሉ አበባ
ይኸው ተገኘ አበባ
ወጣ መስቀሉ አበባ
አዝ

ደጉ ኪራኮስ   አበባ      
ሽማግሌው  አበባ
እሌኒን መራ አበባ
በደመራው አበባ
ጌታ በእርሱ ላይ አበባ
በመሰቀሉ አበባ
ጭሱ ሰገደ አበባ
ወደ መስቀሉ አበባ      
አዝ

የእምነት ምልክት አበባ       
መስቀል ነውና  አበባ
ተራራው ሜዳ  አበባ
ሆነ እንደገና አበባ
እንደተነሳ አበባ
ጌታ እንደቃሉ  አበባ
ከጉድጓድ ወጣ አበባ
ዕፀ መስቀሉ አበባ 
አዝ

እኛም በመስቀል አበባ
እንመካለን  አበባ
በእግዚአብሔር ጥበብ አበባ
መቼ እናፍራለን አበባ
ሞኝነት እንኳን አበባ
ቢሆን ለዓለም አበባ
ኃይል ጸወን ነው አበባ
ለዘለዓለም አበባ
አዝ

ግድግዳው ፈርሷል  አበባ
የልዩነቱ አበባ                          
ምድርና ሰማይ አበባ                 
ሆኑ እንደ ጥንቱ  አበባ                
ነፍስና ስጋ አበባ                     
በእርሱ ታርቀዋል አበባ                
ሕዝብና አሕዛብ አበባ                  
ወንድም ሆነዋል አበባ                   

ዘማሪ ዲ/ን አበበ ታዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፲፭


በዚችም ቀን ጠራው ከሚባል አገር ለከበረ ጻድቅ አባት አባ ጴጥሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተሰጠ የስእለት ልጅ ነው። በአደገም ጊዜ ለታላቅ ተጋድሎ ከልቡ በቆራጥነት ተነሣ። በቀንና በሌሊትም በጾም በጸሎት ተወስኖ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሆነ።

ሰው የሚመገበውንም ምንም አይመገብም በዱር ያገኘውን ጥቂት ሣርን ይመገባል እንጂ። ደገኛው ምግቡ ግን ክብር ይግባውና የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ማመስገን ነበረ። በዚህም ምግባቸው የእግዚአብሔር ምስጋና የሆነ መላእክትን መሰላቸው።

አሎን በሚባል የወንዝ ውኃ ላይም ይመላለስ ዘንድ ውሀ ውስጥ የገቡት እግሮቹ አይርሱም ነበር ሥጋ እንደሌለው መንፈስ እስከሚሆን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከችግር ብዛትና ከሚለብሰው የብረት ልብስ ክብደት የተነሣ ሥጋው እጅግ ደርቆ የረቀቀም ሁኖ ነበርና በእንዲህ ያለ ተጋድሎም እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ በዚህች ቀን በክብር አርፏል።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀለ ኢየሱስ

የፀቡ ግድግዳ የፈረሰበት
አጋንንትም አፍረው የወደቁበት
ዕፀ መስቀሉ ነው የሰው ልጅ ሕይወት (2)

አዝ

መስቀል መሰረት ነው ለቤተክርስቲያን
ጋሻ እና ጦራቸው ለሰማእታት ለፃድቃን
ለእኛም ለምናምነው መስቀል ኃይላችን ነው
ከሞት የዳንበት ኃይሉ የእግዚአብሔር ነው
ኃይላችን ነው መስቀል ብርታታችን
ቤዛችን ነው መድኃኒታችን
(2)
አዝ

አይሁድ ቢቀብሩትም በክፋት ተነስተው
ቢያኖሩትም እንኳን ከምድር አርቀው
ነገርግን አልቻሉም መስቀሉን ለማጥፋት
ዳግመኛም ተገኘ ሊሆን ለእኛ ድኅነት
ኃይላችን ነው የምንድንበት የዳንበት
ጥንተ ጠላታችንን ድል የነሳንበት(2)
አዝ

ተቆፍሮ ሲገኝ መስቀሉ ለዓለም
በብርሃን ተመላች ኢየሩሳሌም
እናክብር መስቀሉን እንድናገኝ ፀጋ
መድኃኒት ነው እና ለነፍስም ለስጋ
ብርሃን ነው ለዓለሙ ሁሉ
እናምናለን እኛ በኃይለ መስቀሉ (2)

ዘማሪት ብሩክታዊት ተ/ ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ተገኘ መስቀሉ

ለእኛ ለምናምነው መስቀል ኃይላችን ነው
ጠላትን ድል መንሻ መስቀል አርማችን ነው
ተነሱ ዘምሩ ክርስቲያኖች ሁሉ
ተገኘ መስቀሉ እሰይ እልል በሉ (2)

አዝ

አይሁድ በክፋት መስቀሉን ቀበሩት
ተዓምር እንዳይሰራ ሸሽገው ቢያኖሩት
ለብዙ ዘመናት ቀብረው ቢያኖሩትም
ተዓምር ከመስራቱ ከቶ አላስቀሩትም
እሰይ እልል በሉ እንደ አይሁድ ክፋት
እሰይ እልል በሉ አልቀረም ተቀብሮ
እሰይ እልል በሉ በእሌኒ ንግሥት
እሰይ እልል በሉ ወጣ ተቆፍሮ
መስቀሉ ተቀብሮ ከቶ እንዳይረሳ
እሌኒም አገኘች ደመራ ለኩሳ
አዝ

የእሌኒ ንግሥት ፀሎቷ ተሰማ
መስቀል ለመፈለግ ጸናች በዓላማ
ደመራ ደምራ እጣኑን አጢሳ
አስገኘች መስቀሉን ተራራውን ምሳ
እሰይ እልል በሉ ክብራችን ነው ለእኛ
እሰይ እልል በሉ የሆነን መዳኛ
እሰይ እልል በሉ መስቀል ኃይላችን ነው
እሰይ እልል በሉ ለምናምነው ለእኛ
መስቀሉ ያበራል እንደ ፀሐይ ጮራ
ድውይ እየፈወሰ እውር እያበራ
አዝ

መስቀልን በመስቀል እንዳለ በቃሉ
አንብር መስቀልዬ በድበ መስቀሉ
በኢትዮጵያ ምድር ተዓምር እየሰራ
በቤቱ ከበረ በግሸን ተራራ
እሰይ እልል በሉ መስቀል ሞገሳችን
እሰይ እልል በሉ ምልክት አርማችን
እሰይ እልል በሉ ጠላትን ድል መንሻ
እሰይ እልል በሉ የእምነት ጋሻችን
በኢትዮጵያ ምድር በግሸን ተራራ
ግማደ መስቀሉ ዛሬም ተዓምር ሰራ

ዘማሪ ጥላሁን ፍቃዱ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ኃይላችን

መስቀል ኃይላችን መስቀል ተፈጥሮአችን
መስቀል(2) ይላል መላው አካላችን
ሞትን ድል ነስተናል በከበረው ስሙ
ቀድሶታል እና ክርስቶስ በደሙ(2)

አዝ

በአይሁድ አደባባይ ታየ በከፍታ
ጎባጣ እያቀና ሞትን እየረታ
ትንሹም ትልቁም ከአንገቱ የማይለየው
የእሌኒ ሞገስ መስቀል ቤዛችን ነው (2)
አዝ

የአምላክ ዙፋኑ ባለውለታችን
በአንተ የፈሰሰው ሆነ ሕይወታችን
አይሁድ አዋጅ ነግረው አመድ ሲደፉብህ
እሌኒ በጢሱ ፈልጋ አገኘችህ (2)
አዝ

እኛም አንተን ስንል ለሞት ብንሰጥም
ፍፁም ከአንገታችን ልንለይህ አንችልም
የፍቅር ፍፃሜ ሆነኸናልና
ከፅንፍ እስከ አፅናፍ ታብባለህ ገና
ከፅንፍ እስከ አፅናፍ ታበራለህ ገና
አዝ

በዕለተ ሠሉስ ለፈጠረህ ጌታ
ዙፋን ልትሆነው ወጣህ ጎልጎታ
አርብ ዕለት ተፈጥረው አርብ ዕለት ለዳኑት
ለአዳም እና ሄዋን ሆንካቸው መድኃኒት (2)

ዘማሪት ኤልሳቤጥ እያዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ

በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ኮነ ሕይወትነ
እንዘምር ሆነን በደስታ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ሆኖናል ከፍታ

አዝ

የፍቅሩ ዙፋን መስቀሉ
ተገልጦ በኛ ላይ ኃይሉ
በድል ነሺዎች ጎዳና
መራን መስቀሉ እንደገና
መስቀል ኃይልነ ዘምሩ መስቀል ኃይልነ
ተነሱ ዛሬ ለፍቅሩ መስቀል ኃይልነ
ቁሙ በፅናት በእውነቱ መስቀል ኃይልነ
ያዳነን ጌታ በሞቱ መስቀል ኃይልነ
አዝ

በጲላጦስ ፊት ተከሶ
የእሾህ አክሊልን ለብሶ
ከምድረ ፋይዳ አወጣን
መስቀሉ ኃይል አስታጠቀን
የቀሪናው ሰው ስምዖን መስቀል ኃይልነ
በእጁ እንደያዘ መስቀሉን መስቀል ኃይልነ
ደም ለጋረደው ለፊቱ መስቀል ኃይልነ
ምግባችን ሆነው አፅርቅቱ መስቀል ኃይልነ
አዝ

ፍኖተ መስቀል መከራ
ዜማ አስታጠቀን እንዚራ
ወርዶ መቃብር ንጉሡ
ጽድቃችን ሆነ ሞገሱ
የቆስጠንጢኖስ ራዕይ መስቀል ኃይልነ
ቃል አለው ጸፍጸፈ ሰማይ መስቀል ኃይልነ
ጠላት ይረታል በቃሉ መስቀል ኃይልነ
ላመነ መስቀል ነው ድሉ መስቀል ኃይልነ
አዝ

ተነሽ እሌኒ በደስታ
መስቀሉ ይታይ የጌታ
የእጣኑ ጢስ ከፍ ይበል
የክፋት ድልድይ ይነደል
ነካ ደመራው በሳ መስቀል ኃይልነ
ያለ እርሱ የለንም እረፍት መስቀል ኃይልነ
ምርኩዝ ነውና ለምድሩ መስቀል ኃይልነ
መስቀል ማርኮናል በፍቅሩ መስቀል ኃይልነ

ዘማሪ ዲያቆን ገዛኸኝ ኤርባ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ክብሬ ነው

ምልክቴ ነው ከቀስት ማምለጫዬ
መስቀል ክብሬ ነው ከክፉ መውጫዬ

አዝ

የእባቡ ራስ ሚቀጠቀጥበት
በመስቀል ቤዛነት መርገም ተሻረበት
ሰው በእጸ መስቀል ከእግዚአብሔር ታረቀ
የምሕረት ቀን ወጣ መከራው እራቀ
ኦ በመስቀል ጠላት ተቸገረ
ኦ በመስቀል ጨለማው ተሻረ
ኦ በመስቀል ደሙን አፈሰሰ
ኦ በመስቀል ሥጋውን ቆረሰ
አዝ

ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለሁ
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለሁ
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
ኦ በመስቀል ከሳሹ ተረታ
ኦ በመስቀል ሞትን ገደለልን
ኦ በመስቀል በሩን ከፈተልን
አዝ

የቤዛ ክርስቶስ የክብሩ ዙፋን ነው
በእምነት የሚያጸና በስሙ ላመነው
የቅድስና የሕይወት ማኅተም
መስቀል ትምክህት ነው እስከ ዘለዓለም
ኦ በመስቀል ፍቅሩን ገለጠልን
ኦ በመስቀል ነፍሱን ለእኛ ሰጠ
ኦ በመስቀል እምባችን ታበሰ
ኦ በመስቀል ጸጋ ተለበሰ
አዝ

ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለሁ
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለሁ
አይሁድ በምክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
ኦ በመስቀል ከሳሹ ተረታ
ኦ በመስቀል ሞትን ገደለልን
ኦ በመስቀል በሩን ከፈተልን

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ኃይላችን

መስቀል (2) ኃይላችን ጠላትን ማጥፊያችን (2)
በመስቀል እንመካለን እንድንበታለን (2)

አዝ

የክርስቲያን ጋሻ መስቀል ኃይላችን
የክርስቲያን ጦር መስቀል ኃይላችን
ዕፀ መስቀሉ ነው መስቀል ኃይላችን
የማያሳፍር መስቀል ኃይላችን
አዝ

መድኃኒት የሚሆን መስቀል ኃይላችን
ደሙ ፈሶበታል መስቀል ኃይላችን
መስቀሉን ጥግ አድርጉ መስቀል ኃይላችን
እርሱ ይፈውሳል መስቀል ኃይላችን
አዝ

ክርስቶስ በደሙ መስቀል ኃይላችን
ስለቀደሰው መስቀል ኃይላችን
መስቀል ላመነበት መስቀል ኃይላችን
ድል ማድረጊያ ነው መስቀል ኃይላችን
አዝ

የክርስቶስ ሥጋ መስቀል ኃይላችን
የተፈተተበት መስቀል ኃይላችን
መስቀል ኃይላችን ነው መስቀል ኃይላችን
የምንድንበት መስቀል ኃይላችን
አዝ

ሕይወትን ለማግኘት መስቀል ኃይላችን
ከሞት ለመዳን መስቀል ኃይላችን
መመኪያ ኃይላችን መስቀል ኃይላችን
መስቀል አለልልን መስቀል ኃይላችን

ዘማሪ ሚኪያስ ፀጋዬ
ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜፀጋ ዮሐንስ
ዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሣሙኤል
ዘማሪ አቤል ተስፋዬ
ዘማሪ በርሱፈቃድ አንዳርጋቸው

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን አደራችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን።

መንፈሳዊ የዜማ ስቱዲዮ ያላችሁ ወንድም እህቶች በውስጥ በኩል መልዕክት ይላኩልን። የምታውቁም ካላችሁ ጠቁሙልን @Zimaredawitmessanger 📩

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይለይብኛል

ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል /2/

አዝ

አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን
ሚካኤል  ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል   ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል መነሻዬ ሆነሀል
አዝ

እንዳይከፋኝ አንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳላፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል
ሚካኤል  ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል   ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤልእንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል አሳምረው ፍፃሜዬን
አዝ

ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ
ሚካኤል   እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል  ለኔ ኃይሌ ነው መከታዬ
ሚካኤል   የዘለዓለም ጠባቂዬ


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይላል አንደበቴ

ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው
ትናንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ
ትልሃለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ

አዝ

የትናንት ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው
ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው
ወደ እረፍቴ ወጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ
ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ (2)
አዝ

በጥልቁ በረሃ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ
መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ
በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ
ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ (2)
አዝ

የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል
ለእኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል
ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ
የጌታዬ ሃሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ (2)
አዝ

ትናንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ
የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ
በባሕርይው ቅዱስ የሌለው አምሳያ
ስሙ ወደቤ ነው መልህቄን መጣያ


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በብርሃን ፀዳል

በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የፅጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ ሲሰማኝ እርካታ/2/

አዝ

እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ሕልሜ የቀን ምኞቴ ነው/2/
አዝ

እሩሩህ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህሊናዬ እረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ሕሊናዬ ይትጋ/2/
አዝ

ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይጻፍብኝ በልዩ ሕብር/2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰባቱ መንጦላይት

ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት

አዝ

አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል   
አዝ

ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ

እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ
ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል     
አዝ

ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ
ከመሰወሪያው ዘንድ ከልጅሽም ሊደርስ
ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔርን አመስግኑት

እግዚአብሔርን አመስግኑት
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት/2/

አዝ

ሰማይን ያለምሰሶ
ምድርንም ያለ መሠረት
ያጸናው እርሱ ነው
ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ

የባሕርን ጥልቀት የመጠነ
ዳርቻዋን የወሰነ
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
አዝ

ማዕበል ነፋስ የሚገስጽ
ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ
ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት
እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ

ንጹሀ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ
የነገስታት ንጉሥ አልፋና ኦሜጋ
 ዘላለም እርሱ የማይለወጥ
እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ

 ጥበብን የሚገልጥ ጥበበኛ
ፍርድን የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ
 እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም
 እግዚአብሔር ግሩም ነው ዘለዓለም


ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал