ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የማትረግፍ አበባ

የማትረግፍ አበባ የማትጠወልግ ዘወትር የምታብብ
መአዛ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ናት መድኃኒተ ሕዝብ

አዝ

የሲና ሐመልማል እሳት የተስማማት
መቃጠልን የማታውቅ የመለኮት ሌማት
የእርሷ ድንግልና ዘለዓለማዊ ነው
የማትረግፍ ሲላት ያሬድን አየነው
አዝ

ተቀጥፋ የቆየች የአቤሜሌክ ቅጠል
ስልሳ ስድስት ዓመት ደርቃ ሳትቃጠል
መስጠት ያላቆመች የልምላሜዋን ጠል
ፍሬዋ ክርስቶስ አበባ ናት ድንግል
አዝ

ከአሮን በትር ላይ አብባ የተገኘች
የደረቀን ዓለም ማለምለም ታውቃለች
አባ ጊዮርጊስም አላት ፈርከሊሳ
እዳትረሳ ኃጢያቱን ድል እንድትነሳ
አዝ

የምታሳሳ ናት ውብ ናት እንደ አበባ
በምልጃዋ የአመነ ስንቱ ገነት ገባ
አባ ጽጌ ድንግል ማበቧን ያወቀው
ማህሌቷን ታጥቆ ተመስጦ ነጠቀው
አዝ

በጽጌ ማህሌት ንኢ ንኢ እያልን
እኛም ከሊቁ ጋር እንጠራታለን
አበባ ነፍሳችን ጠውልጋ እንዳትረግፍ
የምልጃዋ ጥላ በእኛ ላይ ይረፍ

ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ግርማ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንዘ ትሐቅፊዮ

እንዘ ትሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ንኢ ማርያም(2)
ንኢ(3)ማርያም (2)

አዝ

የዋኖስ እናት ነሽ የእርግብ ወላዲቱ
ንኢ ሰናይትዬ ንኢ ናዛዚቱ
የእምነታችን ሙዳይ መንበር ለመስዋዕቱ
አዝ

ገብርኤልም ይምጣ የደስታው አብሳሪ
ነይ ከሚካኤል ጋር ጨለማውን አብሪ
የሕግ ታቦት ሆይ በእኛ መሃል ኑሪ
አዝ

ነጭ እና ቀይ ነው የአንቺ ፅጌሬዳ
የተዋህዶ አክሊል መለኮት ፀአዳ
በቀይ ስጋ ደሙ አራቀን ከፍዳ
አዝ

በሰቆቃው ሐዘን በማህሌት ደስታ
በአንድ የሚሰማብሽ ለቅሶ እና እልልታ
የፅጌ ምስጢር ነሽ የእጣኑ ሽታ

ዘማሪት ትዕግስት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፯ /7/


በዚች ዕለት ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።

ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ ባለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።

ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።

አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።

ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።

ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​አቡዬና አንበሳ

ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዜግነት ግብፃዊ ናቸው። በተጋድሎ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ቁጥራቸው ከባሕታዊያን እንደመሆኑና ተጋድሎአቸው በኢትዮጵያ እንደመሆኑ ግብፃውያን ጨርሶ አያውቁአቸውም። ስለ እርሳቸው ቅድስናም የሚሰሙት ከእኛ አንደበት ነው።

በአንጻሩ እኛም ስለ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንሰማው ከግብፃውያኑ አንደበት ነው። በእነርሱ አንደበት ኢትዮጵያዊው ሲባል ብንሰማም እኛ ግን በለመድንበት ጥቁሩ ሙሴ ብለን መጥራት ይቀናናል እንጂ ኢትዮጵያዊነቱን ብዙም አጉልተን አናነሳም። በዛሬይቱ ኤርትራ ሐማሴን የተወለደው ቅዱስ አብደል መሲህ አል ሐበሺንም እንዲሁ ግብፃውያን የሚያከብሩትን ያህል በኤርትራውያንና በኢትዮጵያውያን እምብዛም አይታወቅም። ቅዱሳኑ የዚህ ዓለም ስደተኞች መሆናቸውን ስለሚያስተውሉ መነኩሴ ሀገር የለውም ብለው የሔዱበት ሀገር አድርገው ይኖራሉ።

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዙሪያቸውን በአንበሳ እና በነብር ተከብበው የሚሔዱ አባት ነበሩ። አቡነ አረጋዊን ደግሞ ከዘንዶ ጋር  እናያቸዋለን። ይህ ነገር ምንድን ነው? ቅዱሳኑ ከአራዊት ጋር ምን አላቸው?

ነገሩ ወዲህ ነው ሰው በጥንተ ተፈጥሮ በቅድስና ይኖር በነበረበት በአዳምና ሔዋን ዘመን ከአራዊት ጋር ሰላም ነበረ። አራዊትን ሳይቀር ያዝዛቸው ያነጋግራቸው ነበረ። ሔዋን ከዕባብ ጋር በተነጋገረች ጊዜ ዕባብ አፍ አውጥቶ መናገሩ ብርቅ ያልሆነባት ለዚህ ነው:: ሰው ከእግዚአብሔር ሲጣላ ግን የሚፈሩትንና የሚታዘዙለት አራዊት መፍራት ጀመረ።

በሐዲስ ኪዳን የሰውን ክብር ወደ ቀድሞ ሥፍራው የመለሰው ሁለተኛው አዳም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ግን "በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ'' ማር10:13

እኔ ክርስቶስን እመስላለሁ ያለው ጳውሎስም የበረሃ ዕባብ ስትነድፈው ትንኝ እንደነካችው ያህል ምንም ሳይሆን ወደ እሳት አራግፎአት ቁጭ ብሎአል። በዙሪያው የነበሩ አሕዛብ ከባሕር አደጋ ተርፎ በዕባብ መነደፉን አይተው "ይኼስ ነፍሰ ገዳይ ነው ከባሕር ስንኳ በደህና ቢወጣ እግዚአብሔር በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም'' ብለው ከፈረዱበት በኁዋላ ተነድፎ ምንም እንዳልሆነ ሲያዩ ይህስ አምላክ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። ሐዋ 28:6

ወደ ጥንተ ተፈጥሮ አዳማዊ ቅድስናህ ስትመለስ አራዊት ይገዙልሃል። ክርስቶስን ስትመስል እንደ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሳ እና ነብር ይሰግዱልሃል።

አንበሳና ነብር ባታገኝ አውሬው ምላስህ አራዊት ምኞቶችህ ይታዘዙልሃል። ቅዱስ ላሊበላ በአት ላንጽልዎ እያለ እየተማጸናቸው እንቢ ብለዉ የዝቋላን በረሃ የመረጡት መናኝ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወደ ጥንተ ተፈጥሮ ቅድስና ተመልሰው ከውድቀት ወዲህ የመጣውን የቆዳና የቅጠል ልብስ ሳይሹ በጸጋ እግዚአብሔር በብሩህ ጠጉር ተሸፍነው ለሀገራችን ጸልየዋል። ጻድቁ አባታችን አራዊትን በገሰፁበት ጸሎት ዛሬም በሀገራችን የተሰማራውን የጥላቻና የመለያየት አራዊታዊ ጠባይ ይገሥጹልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- የግዮን ወንዝ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዙሪያችን ካሉ

በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከፀኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ሰማዕት

አዝ

ሀብት እና ንብረቷን ውበቷን የናቀች
ንግሥት መባልን በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ምስክር
የቅድስት አርሴማ እፁብ ነው የእርሷ ክብር (2)
አዝ

እግዚአብሔር ፅናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅፅሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሃን ለዓለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለእኛም አማላጅ ነች(2)
አዝ

ይሄው በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ገለፃት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አደረጋት
አክሊል ተጎናፅፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር
ዛሬም በልጆቿ በረከቷ ይደር
አዝ

እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ (2)

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ
እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ግእዝን የምንማማርበት ዝግጅታችን ተመልሷል።

📜 እርስዎም የግእዝ ቋንቋን ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናልና ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።

✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ከታች ባለው የቴሌግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ የመማማሪያ ቦታዎችን ያገኛሉ  ✅

ለመመዝገብ 👇
@Geez202
@Geez202
@Geez202 👈

ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ፤  ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።

📲 የበለጠ መረጃ በምዝገባው ሂደት ይደርስዎታል። ጥያቄ ሲኖር ከታች በተቀመጠው በስልክ ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

🌺 መሠረተ፡ግእዝ 🌺
@MesereteGeez - 0918026533
ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በአክብሮት እንጠይቃለን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ሰውነቴ በአንተ ፍቅር ተጠምዳለች
ውለታህን እያሰበች ታለቅሳለች
መከራው ተረሳ ትካዜም ቀረልኝ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፈጥነህ ደርሰህልኝ

አዝ

ደጅህን ለመርገጥ መንገድ ስጀምር
ተፈቶ አየዋለሁ የልቤ ችግር
ወዳጄ እና አባቴ ሚስጥሬ ተስፋዬ
ቀና እንድል አደረከኝ በነስፍ በስጋዬ
አዝ

በሚመጥን ፊደል በሚያምሩ ቃላት
ነፍሴ ትጠማለች ስምክን ለመጥራት
እንባዬ ይፈሳል አንደበት ያጥረኛል
ውለታህን ሳስብ ልቤ ይቀልጥብኛል
አዝ

ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊት ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረሕይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ
አዝ

ስለቴን ስትሰማ ሲጠብቀኝ ምልጃህ
ሳጉረመርምብህ ትታገሰኛለህ
የጭንቄ ማረፊያ የህመሜም ፈውስ
አርከ እግዚአብሔር ገብረ መንፈስ ቅዱስ
አዝ

ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረሕይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፭ /5/

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው።

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ፣ ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና) ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም የተቀበሉ አባት ናቸው።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም ለአእላፍ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው፤ ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው። ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላልና ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር እና ፍትሃ ነገስት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​እንኳን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!

አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል።

አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ።

አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ

ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው።

በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር።

በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል።

ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል።

ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል።

ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል።

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ።

ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14 
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ማርያም የሕይወቴ ውበት

የሕይወቴ ውበት የመኖሬ ቀመር
ማርያም ጥበቤ ነሽ ስለአንቺ ልናገር
የእድገቴ ውጥን ምርኩዝ ድጋፌ
ለስምሽ ምስጋና ቅኔ ያፍስስ አፌ

አዝ

ውበት ንፅህናሽን ወደደ ንጉሡ
አፌም አያቋርጥ አንቺን ማወደሱ
የነፍሴ ዜማ ነሽ የቀን ትውስታዬ
እርግቤ ማርያም ነሽ መደምደሚያዬ
አዝ

ፍቅርሽን ከልቤ ማንችሎ ያጠፋል
እናትነትሽን የቀመሰ ያውቃል
በምስጋናሽ ፍቅር ልቤ ተቃጠለ
ያመሰግንሻል ማርያም እያለ
አዝ

ሆኖ አገኘሁት መውደድ የተገባ
አዳም ወደ ቤቱ በአንቺ ነው የገባ
ይወቅ ያላወቀ ትልቅ ሱታፌሽን
ዓለም ለመዳኑ ምክንያት መሆንሽን
አዝ

በአንቺ የተደረገ የሚርቅ ጥበብ
ነፍሴ ትረካለች እሱን በማሰብ
ከጨረቃ የተዋብሽ
ከፀሐይ የጠራሽ
በቃል አይገለፅ ልዩነው ክብርሽ

ዘማሪ አዲስ መስፍን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በእንባ ሸለቆ

በእንባ ሸለቆ ያየሁሽ ተራራ
ለበረሃው ልቤ የፍቅር አዝመራ
ለምለሚቷ ምድር አንቺ ነሽ እናቴ
ሁሌ እወድሻለሁ ማርያም እመቤቴ

አዝ

ዛሬ ትላንትናን ሽሯል በጉልበቱ
ሁሉም ይለወጣል የለም በዓለም ብርቱ
እኔ ግን እግሮቼን በፅዮን ተክዬ
የነቀለኝ የለም ድንግል አንቺን ብዬ
አዝ

አስፈሪውን ጉዞ በድል ወጥቻለሁ
ወደ ሰዶም ላልዞር በቀኜ ምያለሁ
ማምለጫ ዋሻዬ የተሸሸኩብሽ
ሞቴን የሞተውን በአንቺ አገኘሁብሽ
አዝ

ጭንቅ የያዘው ድንኳን ሰላም ተነፈሰ
በእልፍኝ በጓዳዬ መውደድሽ ፈሰሰ
የልጅነት ውርሴ ስምሽ አብሮኝ አለ
እንቅፋት ያነሳ ወጥመዴን የጣለ
አዝ

በብዙ መከራ መተማመኛዬ
የመዳኔ አርማ ቀስተ ደመናዬ
አይኔ አይነቀልም እናቴ ከአንቺማ
አይሰለችም አፌ ይሰጥሻል ዜማ
አዝ

አስፈሪውን ጉዞ በድል ወጥቻለሁ
ወደ ሰዶም ላልዞር በቀኜ ምያለሁ
ማምለጫ ዋሻዬ የተሸሸኩብሽ
ሞቴን የሞተውን በአንቺ አገኘሁብሽ
አዝ

በብዙ መከራ መተማመኛዬ
የመዳኔ አርማ ቀስተ ደመናዬ
አይኔ አይነቀልም እናቴ ከአንቺማ
አይሰለችም አፌ ይሰጥሻል ዜማ

ዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሣሙኤል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ናታኔም ነኝ

ናታኔም ነኝ አገልግሎቴ
አይከፋኝም ታናሽነቴ
እጠርጋለሁ ደጅህን ጌታ
ዝቅ ብዬ ላንተ ውለታ

አዝ

ከነገደ ሌዊ ባልሆን
ባልሾምም እንደ አሮን
የዜማ እቃ ባልይዝ በገና
ላመስግንህ በትህትና
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተሰፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
አዝ

ከረኝነት ከታናሽ ስፍራ
ለንግሥና ምንም ብጠራ
ከቀንዲሉ ቀርቧል ሀሣቤ
ልቀኝለት ተነጥፎ ልቤ
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
አዝ

ሳይከብድኝ የአለም ዝና
ተንበርክኬ ልሥጥህ ምሥጋና
ምክንያት አለኝ ለማዘንበሌ
ናታኔም ነኝ ይቺ ናት ቃሌ
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
አዝ

እንኳን ልቆሞ በፍታን ለብሼ
አፍርሀለው እኔ አጎንብሼ
የትመክኸት ካባዬን ጥዬ
ከመቅደስህ ልግባ ጌታዬ
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼በአዲስ አመት በገና፣ክራር ከበሮ መማር ይፈልጋሉ?🌼

መመዝገብ ለምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን

በ0956861468
በ0912085085 ደውለው ይመዝገቡ

እንዲሁም በቴሌግራም ለመመዝገብ ለምትፈልጉ
@Orthodoxtewahed0

በእዚህ ሊንክ በውስጥ ማውራት ትችላላችሁ

✝ያለው ቀሪ ቦታ ውስን ስለሆነ ቶሎ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን✝

መማሪያ ሰዓቶች
ከሰኞ-አርብ 11:00-1:00

ቅዳሜ እና እሑድ
3:00-5:00
6:00-8:00
9:00-11:00

ክፍያ የ6ወሩ በወር 500ብር
        የ3ወሩ በወር 1000ብር ነው ሁለቱም ዋጋቸው እኩል ነው አጠቃላይ 3000ብር ነው የሚመጣው። መመዝገቢያ 100ብር ይጨምራል።


✝ ከበሮ አለን የ1 ወር እና የ1 ሳምንት
የ1 ሳምንቱ ሙሉ ሳምንት ሲሆን
ከ8:00-10:00 እና 9:00-11:00 አለ
የአንድ ወሩ ከሆነ በሳምንት 2 ቀን ነው የምትማሩት። ሁለቱም ክፍያቸው ተመሳሳይ ነው 1100ብር ነው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፪ /2/


የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ መጣ።

የከኀዲው ንጉስ ዮስጥያኖስ ሚስት በሃይማኖቷ የቀናች ነበረች። ቅዱስ አባ ሳዊሮስንም ትወደው ታከብረውም ነበር። በዚሕም ንጉሱ ሊገድለው እንደሆነ በአወቀች ጊዜ ለአባ ሳዊሮስ እንዲሸሽ ነገረችው፤ አባታችንም እኔ ስለ ክርስቶስ ለሞት የተዘጋጀው ነኝ አለ። ንግሥቲቱና ምዕመናኑም በለመኑት ጊዜ ወደ ግብፅ አገር ተሰደደ። የንጉሱ ወታደሮችም በመካከላቸው ሆኖ ሲጓዝ አላገኙትም ነበር፤ ጌታችን ይሠውረው ነበርና።

በአንዲት ቀንም በአስቄጥስ ገዳም በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን በመጻተኛ መነኩሴ አምሳል ገባ። በዚያም ቄሱ ዕጣኑንና ቁርባኑን ሊያሳርግ ጀመረ ሁሉንም ሥርዓት ፈጽሞ እጆቹን ታጥቦ ማኅፈዱን በገለጠው ጊዜ በጻሕሉ ውስጥ የቁርባኑን ኅብስት አላገኘውም፤ ደንግጦም አለቀሰ ለሕዝቡም ወንድሞቼ ይሕ የሆነ በእኔ ኃጢያት ወይም በእናንተ ኃጢያት እንደሆነ አላወቅሁም አላቸው።

መልአክም ተገልጦ ይህ የሆነ በኃጢአትሕ ወይም በሕዝቡ ኃጢአት አይደለም ሊቀጳጳሳት አባ ሳዊሮስ እያለ መሥዋዕትን ለማሳረግ በመድፈርሕ ነው አለው። ቄሱም መልሶ ሊቀጳጳሳት መኖሩን አላወቅሁም አለው፤ መልአኩም አባታችን ወደ ቆመበት ቦታ አመለከተው። ቄሱም ከአባታችን ከእግሩ በታች ሰግዶ ቡራኬ ተቀበለ። ወደ ቤተመቅደስም ገባ፤ በኋላም ቄሱ የቁርባኑን ኅብስት በጻሕሉ ውስጥ አገኘው ካሕናቱና ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ የቁርባኑም ሥርዓት ተፈጸመ።

ከዚያም ወጥቶ ወደ ሀገረ ስሐ ሄደ ምዕመናንንም በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው እስከሚያርፍባት የካቲት ወር ዐሥራ አራት ቀን ኖረ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​መጽሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በአንድ ጥራዝ የሚገኝ የብዙ መጻሕፍት ስብስብ የሆነ የተለየ፣ የተቀደሰ ጽሑፍ ማለት ነው። በውስጡም ከኢየሱስ ክርስቶስ በፊት የተጻፈ ብሉይ ኪዳንና ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ የተጻፈው ሐዲስ ኪዳን ተብለው የተከፈሉ መጻሕፍትን የያዘ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ የተባለበት ምክንያት ከሌሎች መጻሐፍት የተለየ  በመሆኑ ነው፡፡ የተለየ የሆነው በሚከተለው ምክንያቶች ነው ፡- 

. በመጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ የሚገኙት ጽሑፎች ከቅዱሱ ከእግዚአብሔር  የተገኙ እና የእግዚአብሔርን ቃል የያዙ ስለሆኑ፡፡
. መጽሐፉ ቅድስና ምን እንደሆነ፣ ሰዎች ቅዱሱን እግዚአብሔርን በቅድስና እንዲመስሉ የሚመክሩ የሚያስተምሩ ታሪኮችን እና ምክሮችን የያዘ መጽሐፍ በመሆኑ።
፫. መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነቡትን፣ የሚሰሙትን፣ የሚያምኑበትና  የተሳለሙትን ሁሉ የሚቀድስ፣ የሚባርክ ስለሆነ ቅዱስ ተብሏል።
፬. ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ።
፭. የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ሁነት እና ወደፊት  የሚፈጸሙትን በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ።

መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በተለያዩ ጊዜ እና ቦታ በነበሩ ከተለያዩ የሥራ መስክ በተሰማሩ ከ፵ በላይ በሚሆኑ ቅዱሳን ሰዎች ሲሆን፤ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ ያደረጋቸው እግዚአብሔር ነው፡፡

እግዚአብሔር መጽሐፍቱን እንዲጽፉ ያደረገበት ምክንያትም ሰዎች በእግዚአብሔር እንዲያምኑና ሕጉን እና ትእዛዙን አክብረው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው፡፡

በሌላ በኩልም መጽሐፍ ቅዱስ የጻፉትን ሰዎች የመረጣቸው እርሱ እግዚአብሔር ነው ሲመርጣቸውም የተለያዩ ሙያ የነበራቸው ሰዎችን ነው፡፡ እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፉት መካከል የተወስኑት እንመለከት፦ 

ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ፦

ኤርሚያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዘካሪያስ ካህናት ሲሆኑ ኢሳይያስ፣ ዳንኤልና ሆሴዕ ደግሞ ከነቢያነት ቅዱስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን ደግሞ ከነገሥነት ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው አሞፅ ደግሞ ከእረኛነት ነበረ።

ከሐዲስ ኪዳን ጽሐፊዎች ደግሞ 

ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ የሐንስ፣ ቅዱስ ያዕቆብ እና ቅዱስ እንድርያስ ከአሳ አጥማጅነት፣ ማቴዎስ (ሌዊ) ከቀራጭነት በመመረጥ መጽሐፍትን እንዲጽፉ አድርጓቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ መቼ ተጻፈ?

እግዚአብሔር ዘላለም የሚኖር አምላክ በመሆኑ በተለያዩ ዘመናት የነበሩ ሰዎች በመምረጥ ያጻፈው መጽሐፍ ነው። በመሆኑም መጽሐፉን የጻፉት ሰዎች የኖሩበት ዘመን የተለያየ እንደመሆኑ መጽሐፍቱም የተጻበት ዘመን እንዲሁ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ለመመለከት ያህል፦

እንደ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በመጀመሪያ የተጻፈው  መጽሐፈ ሄኖክ ነው። መጽሐፈ ሄኖክ ዓለም ከተፈጠረ በ፲፬፹፮ ዓ.ዓ ጌታችን አምላካችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ በፊት ፵፻፲፬ ቅ.ል.ክ ገደማ ተጽፏል፡፡ ከዚህም ቀጥሎ ሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሐፍት ከ፲፭፻ ዓ.ዓ-፫፻ ዓ.ዓ (ዓመተ ዓለም) ጌታችን  አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ በፊት ያለው ጊዜ እና አሁን ያለንበት ዓመት ማለት ነው።

ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐርገ በኋላ ከ፵፭ ዓ.ም- ፻ ዓ.ም፤ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጽፏል።

ምንጭ:- መጽሐፍ ቅዱስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምህር ቸሬ አበበ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፰ /8/


በዚህች ቀን ቅዱስ አባት መጥራ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ አገር አማኒ ክርስቲያን ነው። ከሀዲ ንጉሥ ዳኬዎስ በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቁሞ የክርስቲያንን ወገኖች አሠቃያቸው። ትእዛዙም ወደ እስክንድርያ አገር ደርሶ ሰዎቿን ሁሉንም አሠቃያቸው የብዙዎች ምእመናንንም ደማቸውን አፈሰሰ።

ያን ጊዜ ክርስቲያን እንደ ሆነ ቅዱስ መጥራን በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሉት መኰንኑም ወደርሱ አስቀረበው እርሱም ብቻውን እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም ለአማልክት ስገድ እኔም ብዙ ገንዘብን እሰጥሃለሁ ታላቅ ክብርንም አከብርሃለሁ አለው። እርሱም ቃል ኪዳኑን አልተቀበለም ኪዳንህና ገንዘብህ ካንተ ጋራ ወደ ጥፋት ይሒድ አለው እንጂ። መኰንኑም በእርሱ ላይ ተቆጥቶ ጽኑዕ ሥቃይ እቀጣሃለሁ አለው።

ለፈጠረ ለሕያው እግዚአብሔር እሰግዳለሁ። ለረከሱ ጣዖታት ከደንጊያና ከዕንጨት ለተሠሩ ለማያዩ ለማይሰሙ ለማይናገሩ ለማያሸቱ ለማይንቀሳቀሱ እንሰግድ ዘንድ እንዴት ይገባል አለው። መኰንኑም በሰማ ጊዜ አፈረ ጽኑ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ ከዚህም በኋላ በክንዱ ሰቀሉት በደረቀች ሽመልም ጎኖቹን ሠነጠቁ ቀደዱትም ክብር ይግባውና ጌታ ኢየሱስም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤንነት አስነሣው መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ከከተማውም አውጥተው የከበረች ራሱን ቆረጡ  የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅድስት ሥላሴ

ገፄን አማትቤ ልጀምር ውዳሴ
በትምህርተ መስቀል በስመ ሥላሴ
ይርቃል ከጎኔ ጠላት ዲያብሎስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

አዝ

ከትቢያ ከአፈር አንስቶ የሰራኝ
በአፉም እስትንፋስ ሕይወትን ያደለኝ
የሥላሴ ሥራ ድንቅ ነው ጥበቡ
ከአይምሮ በላይ ነው የእግዚአብሔር ሃሳቡ
አዝ

እክሕደከ ሰይጣን ጠላቴን ክጃለውሁ
ለዚህም ምስክር ማርያም ናት ብያለሁ
በቤተክርስቲያ ቆሜ በመቅደሱ
ለቅድስት ሥላሴ ዘመርኩ ለንጉሡ
አዝ

አልነበረም ዘመን እርሱ ያልነበረበት
ዳግመኛም አይኖርም እርሱ ማይኖርበት
የሕይወቴ ጣዕም ክብሬ እና ሞገሴ
የማይሾሙት ንጉስ ዘላለም ሥላሴ
አዝ

ኪሩቤል ሱራፌል ኃይላት ሊቃናት
መናብርት ስልጣናት ቆመው በአንድነት
ያለአንዳች ዝምታ ይሉታል በክብር
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሥላሴን አመስግኑ

ሥላሴን አመስግኑ(2)
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ

አዝ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይገባል ከጠዋት እስከ ማታ
አዝ

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት
መላእክት በሰማይ የሚዘምሩለት
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይም በምድር እንጠራሃለን
አዝ

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ሥላሴም አምባዬ ክብሬም ናቸው እና
ሁሌ ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና
አዝ

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ሥላሴም አምባዬ ክብሬም ናቸው እና
ሁሌ ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አስደሳች ዜና ለዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች

እግዚአብሔር ጸጋውን ሰጥቷችኋል፤ ስትዘምሩ ሰው ሁሉ ተመስጦ ነው የሚሰማችሁ። ሰውም ያለህን/ያለሽን ጸጋ ተመልክተው "አረ አንተ/ቺ ልጅማ ዘማሪ ነው የምትሆነው/የምትሆኚው" ይሏቹሃል!

እናንተም ጸጋው እንዳላችሁ ታውቃላችሁ ግን እንዴት ጸጋችሁን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ማዋል እንደምትችሉ አላወቃችሁም፤ ወይም ደግሞ ሞክራቹ መንገዱን የሚያሳያችሁ አላገኛችሁም። በተቃራኒው ደግሞ ጸጋቸው ሌላ ሆኖ ሳለ መድረኩን ስላገኙ ብቻ ዘማሪ የሆኑ ስንት አሉ መሰላችሁ፤ ጸጋው ተሰጥቷቸው ደግሞ መድረክ ያላገኙ በየቤታችን ብዙዎች አሉ።

"የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤" 1ኛ ቆሮ 12:4

ሁሉም ከእግዚአብሔር የተቀበለው ጸጋ አለ። ያንን አውጥቶ እግዚአብሄርን አለማገልገል ወይም ደግሞ ጸጋውን ላልተገባ ተግባር/ዘፈን/ ማዋል እንደዚያ መክሊቱን እንደቀበረው አገልጋይ ንፉግ ያሰኘናል።

የዝማሬ ዳዊት ገጽም ይህንን በማስተዋል ብዙ አዳዲስና ጸጋውን የተላበሱ ዘማርያንን ለማውጣት እየሰራ ይገኛል። ይህንን የምትመለከቱ በሙሉ፤ መልዕክቱ እናንተን ባይመለከትም እንኳን የምታውቋቸው፤ በየሚዲያው የምትመለከቷቸው የዝማሬ ጸጋ የተሰጣቸውን ወንድም እህቶቻችንን ወደኛ መጥተው ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲያገለግሉ መልዕክቱን እንድታስተላልፉ በክርስቶስ ፍቅር እንጠይቃለን።

በዚህም መሰረት በ @Zemaredawitadmin ላይ ስምስልክአድራሻ እንዲሁም ከሁለት ደቂቃ ያልበለጠ ከድምጻችሁ ጋር የሚጣጣም ዝማሬ በመላክ መቀላቀል ትችላላችሁ። መልሳችንን በአጭር ግዜ ውስጥ በዛው እናሳውቃቹሀለን።

መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ!
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፮ /6/


በዚች ዕለት ቅዱስ አባት አባ ጰንጠሌዎን የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

ታላቁ ጻድቅ፣ ሰባኬ ወንጌልና ገዳማዊ አባ ጰንጠሌዎን የተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን መሪ ናቸው። ጻድቁ ሃገረ ትውልዳቸው ሮም ቢሆንም ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮጵያ ነው። በገዳም ትምህርቱን ካጠነቀቁ በኋላ በዚያው ጠፍተው ወደ ግብጽ ወረዱ፤ በዚያም መነኮሱ። እድሜአቸው እየገፋ ሲሔድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስምንቱን ቅዱሳን ሰብስበው በአቡነ አረጋዊ  መሪነት ወደ ሃገራችን መጡ። በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ የነበረው ንጉሥ አልዓሜዳም በክብር ተቀብሎ አክሱም ውስጥ ''ቤተ ቀጢን” የሚባል ቦታን ሰጣቸው።

አባ ጰንጠሌዎን 'ጾማዕት' ወደ ሚባል ረዥም ተራራ ወጡ። በዚያም አስቀድመው ለወንጌል አገልግሎት እየተጉ ድውያንን ፈወሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣ አጋንንትን አሳደዱ። ብዙ ተአምራትንም አደረጉ። እንዲያውም አንድ ቀን ወይራውን በጧት ተክለው በሠርክ ትልቅ ዛፍ ሆነላቸው። ከዚያ ዘንጥፈው እሳቱን በቀሚሳቸው ላይ አፍመው ማዕጠንት አሳርገዋል። የሚገርመው ያ ዛፍ ዛሬም ድረስ ለምስክርነት ቁሟል። በመጨረሻ ዘመናቸው ግን ጻድቁ አምስት ክንድ ርዝመት ባላት ጾማዕት (በዓት) ውስጥ ገብተው ቆሙ።

ለአርባ አምስት ዓመታት ሳይቀመጡና ሳይተኙ በእንባ ቢጸልዩ ቅንድባቸው ተላጠ። አካላቸውም በአጥንቱ ብቻ ቀረ። በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት መድኃኔዓለም መጥቶ ''ወዳጄ! ስምህን የጠራ መታሰቢያህን በእምነት ያደረገውንም ሁሉ እምርልሃለሁ።'' አላቸው። ያን ጊዜ አጥንቶቻቸው ተወዛወዙና ነፍሳቸው በክብር ዐረገች።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በረከትሽ ብዙ

በረከትሽ ብዙ አምኖ ለጠራሽ
የጭንቅ ቀን ዋስ ነሽ ዛሬን ላሰበሽ
አርሴማ በምልጃሽ ለታመነብሽ

አዝ

ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬ ነው ብለሽ
የዓለም ክብር ሀብቷን ስለ ክብሩ ንቀሽ
በደምሽ መሰከርሽ ስለ ደሙ ዋጋ
ጌታም አከበረሽ በተለየ ፀጋ
አዝ

የጳውሎስ ሰይፍን የጴጥሮስ ሃሳብን
ተቀብለሽ አየን ሰማዕትነትን
የረድኤትሽ ባሮች በላዬ ይስፋፉ
ያስጨነቁኝ ሁሉ ከላዬ እንዲረግፉ
አዝ

የእናትነትሽን ፍቅርን ያልቀመሰ
በእውነት ያስቆጨዋል በአንቺ ያልተዳሰሰ
እኔ ምስክር ነኝ ከስንቱ እንዳዳንሽኝ
አርሴማ በምልጃስ ከሞት እንዳስጣልሽኝ
አዝ

እንዴት አይነት ዉበት ቢኖርሽ ነው ከቶ
ነገስታት ያጣላ ክብር ሁሉ አስትቶ
ውበት ሐሰት ብለሽ ቆምሽ በአደባባይ
እኔንም አስተምሪኝ ልውጣ ከመታበይ
አዝ

በዓለም ውጣ ውረድ የተጨነቃችሁ
ለችግሮቻችሁ መፍትሄን ያጣችሁ
ቅድስት አርሴማ ነይ ብላችሁ ደጅ ጥኗት
አምላኳን ተማፅና ታስምራለች በእውነት

ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የአምላክ ዐቃቤ ሕግ

ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ

አዝ

ፀሐይ(2)የምድራችን ፀሐይ
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ
የመላዕክት ወዳጅ(2)ገብረሕይወት ሰማይ
አዝ

መብረቅ(2)ሰረገላው መብረቅ
የቃልኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ
የፍጥረቱ ደስታ(2)ገብረሕይወት ፃድቅ
አዝ

ኮከብ(2)ክብረገድላን ኮከብ
ዓለምን የሚያስንቅ መዐዛው የሚስብ
አርከ ሥሉስ ቅዱስ(2)ገብረሕይወት ኪሩብ
አዝ

ስኂን(2)ፄና ልብሱ ስኂን
የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን
የሚነበብ መፃፍ(2)ገብረሕይወት ድርሳን
አዝ

መቅረዝ(2)የማኅቶት መቅረዝ
ምድረከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ
የዝጊቲው ፈዋሽ(2)ገብረሕይወት ምርኩዝ

ሕብረ ዝማሬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ቆሚያለሁ ሁሉንም አልፌ
በምልጃው ከሞት ተርፌ
ፀሎቱ ኃይል አደረገልኝ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረዳኝ (2)

አዝ

አበቃ ሲባል አልቆ ተስፋዬ
በሃዘን ብዛት ሲፈስ እንባዬ
ገብረ ሕይወት መጣ ፃድቁ አባቴ
ደዌዬ ተሻረ ፀና ጉልበቴ (2)
አዝ

የጭንቁን ዘመን እረስቻለሁ
ከሰዎች እኩል በእግር ቆሚያለሁ
እርሱ ባይቆምልኝ በእግዚአብሔር ፊት
አልቆምም ነበር ዛሬ በሕይወት
አልኖርም ነበር ዛሬ በሕይወት
አዝ

በፅድቅ ክንዱ እየደገፈ
ክፉን በምልጃው እያሳለፈ
ስለ ቃልኪዳኑ በስሙ ታምኜ
አልጠግብም ፃድቁን እርሱን አመስግኜ(2)
አዝ

በደዌ ኃጢያት የተጠቃችሁ
ሞትን በችግር ለጠበቃችሁ
ፃድቁን ጥሩት ይረዳችኋል
ከአፈር ከትቢያ ያነሳችኋል(2)

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ነገረ ቅዱሳን

ቅዱሳን የሚለው ቃል ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን፣ ትርጉሙም ንጹሕ ልዩ የከበረ ማለት ነው። ይህ ቃል ለእግዚአብሔር የባሕርይ መገለጫ ነው። እግዚአብሔር በባሕርዩ ቅዱስ ነውና። ቅዱሳን የሚለውም ቃል በባሕርዩ ቅዱስ የሆነውን አምላክ ለሚያገለግሉ መላእክትና ደጋግ ሰዎች የሚሰጥ ነው።

ቅዱሳን መላእክትን ቅዱሳን እንላቸዋለን። ከማንኛውም ክፉ ነገር የራቁ፣ ሥርዓታቸውን የጠበቁ፣ እግዚአብሔርን ያወቁ፤ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ ስለሆኑ ቅዱሳን ይባላሉ። ከመዓረገ መላእክት የደረሱ ደጋግ ሰዎችም በዚሁ የቅድስና ስም ይጠራሉ:: ራሱ እግዚአብሔር

«እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ብሏልና:: ዘሌ.19÷2፣ 1ኛጴጥ.1፥15-16


ቅዱሳን በገድል በሦስት ይከፈላሉ

1. ስለቀናች ሃይማኖታቸውና ስለፈጣሪያቸው ክብር ሲሉ በአላውያን / በማያምኑ/ ነገሥታት ፊት ስለ ክርስቶስ አምላክነት ሳያፍሩ፣ ሳይፈሩ መስክረው እስከ ደም ጠብታ ድረስ ለክርስቶስ የመሰከሩ፤ ቁልቁል የተሰቀሉ፣ ለአናብስት የተሰጡ፣ በሰይፍ የተቀሉ በመጋዝ የተሰነጠቁ፤ ወደ እቶን እሳት የተጣሉ፤ በድንጋይ የተወገሩ ሰማዕታት ናቸው። ሰማዕታት ማለት መስካሪዎች ማለት ነው። ራዕይ.12+11፣

ምሳሌ፦ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ቅዱስ ቂርቆስ፣ ሠለስቱ ደቂቅ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

2. በገደል፤ በዱር፣ በዋሻ ሆነው ከጣዕመ ዓለም ተለይተው ክርስቶስ ለሞተላት ለዚህ ዓለም ሲጸልዩ ግርማ ሌሊቱን ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብዓ አጋንንትን፣ የቀን ሐሩር፣ የሌሊት ቁር ታግሰው የሚኖሩ ጻድቃን ናቸው።

ምሳሌ:- ጻድቁ ተክለሃይማኖት፣ ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ... ናቸው።

3. መጽሐፍ አውጥተው፤ አንቀጽ ጠቅሰው፣ መናፍቃንን ተከራክረው የቤተክርስቲያንን ሕግዋን ያስከበሩ የቤተክርስቲያን ጠበቆች ናቸው፡፡

ምሳሌ:- ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ቄርሎስ፣ ጎርጎርዮስ፣ ባስልዮስ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ የመሳስሉት ናቸው፡፡

በዚህ መሠረት የእግዚአብሔር ወዳጆች ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፤ ሰማዕታት ሁሉ ለቅዱስ እግዚአብሔር ሲሉ ሕይወታቸውን መስዋዕት አድርገው ስለሰጡ ስለስሙ ስለመሰከሩ በተጋድሎአቸውና በትሩፋታቸው ስላገለገሉ የቅድስናና የብጽዕና ማዕረግ ተሰጥቶአቸዋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ ፦ ትምህርተ ሃይማኖት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፬ /4/


በዚህች ቀን ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያረፉበት ነው። አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት ጌታችን በተወለደባት ዕለት ነው። በታላቁ በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እየተማሩ አድገው በእሳቸው እጅ በ330 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ በእነርሱም ጊዜ አማናዊው ጥምቀትና ቁርባን መጣልን፡፡ በሀገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ሲያሰሩ 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡ በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዓርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡

ከዕለታት አንደኛው ቀን ጌታችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በአክሱም ‹‹ማይ ኰኩሐ›› በሚባል ተራራ ላይ ጠርቶ ‹‹በዚህች ቦታ ላይ ቤተ መቅደሴን አንጹልኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ቦታው ባህር ነው በየት እናንጽልህ?›› አሉት፡፡ ጌታችንም በጥበቡ ከገነት ጥቂት አፈር አምጥቶ በባሕሩ ላይ ቢበትንበት ባሕሩ ደርቆ ሜዳ ሆነ፡፡ ጌታችንም በቆመባት ዓለት ላይ የእግሩ ጫማ ቅርጽ እስከ አሁን ሳይጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ቦታውም ከዚያ ወዲህ መከየደ እግዚእ›› እየተባለ ይጠራል፡፡

ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ በእንዲህ ዓይነት ግብር ጸንተው በመኖር እግዚአብሔርን አገልግለው ለሀገራችንም ብርሃን አብርተው፤ ታላቁ አብርሃ በ364 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን፤ ታናሹ አጽብሃ ከ13 ዓመት በኋላ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን ዐረፉ፡፡ ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነው ዓመቱ ይለያይ እንጂ፡፡ የንግሥና ስማቸው ኢዛናና ሳይዛና ይባላል፡፡

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ነፍሴ ሆይ

ነፍሴ ሆይ /3/ እግዚአብሔርን ባርኪ
አጥንቶቼም ሁሉ /3/ የተቀደሰ ስሙን

በደስታ ዘምሪ በአዲስ ምስጋና
ጸጥታ እና ሰላም አድሎሻልና
መሠንቆውን አንሺ ቅኔ ተቀኚለት
ለውጦሻልና በደስታ ዘይት

አዝ

ሀሴትን አድርጊ ነፍሴ በእግዚአብሔር
ይሰጥሻልና በክብር ላይ ክብር
ደሴቶች ሲያወሩ በደስታ መንፈስ
እየተወያዩ ስለ ሥሉስ ቅዱስ
አዝ

ሰማያት ሲያወሩ ጽድቅን ሲወያዩ
ሲጠራው አድምጪ ቀላዩን ቀላዩ
ደመናው ጭጋጉ በዙሪያው ከበውት
ቅኔ ያቀርባሉ ለፍጥረታት አባት
አዝ

መብረቅም ይሰማል ሰማዩን ሰንጥቆ
ምስጋናውን ሊያቀርብ ጊዜውን ጠብቆ
በፊቱ ይነዳል እሳትም በግርማ
ምድር ተናወጠች ነጎድጓዱን ሰምታ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፫ /3/


በዚሕችም ቀን ሊቀ ጳጳሳት አባ ስምዖን አረፈ።

የዚሕ አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ ያደገ የቤተክርስቲያንንም ትምሕርት ተምሮ ያደገ ነው። ወደ አስቄጥስ ገዳም በሊቀ ጳጳሳት በአባ ያዕቆብ ገዳም የምንኩስናን ልብስ ለብሶ መነኮሰ ተጋድሎውንም በየጊዜው ጨመረ ሥጋውንም አያደከመ በእርሱ ዘንድ ኖረ። ስለ በጎ ተጋድሎውና ስለ አገልግሎቱ ዳግማዊ ሊቀ ጳጳስ አባ ማርቆስ ወደ አባ ያዕቆብ ወስዶት እያገለገለው ከእርሱ ጋር ኖረ።

አባ ያዕቆብ በአረፈ ጊዜም ካሕናትና ኤጲስቆጶሳት ትሩፋቱንና ያማረ ሥራውን ስለተመለከቱ አምላካዊ ፍቅር አነሳስቷቸዋልና በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።በሹመቱ ጸንቶ መልካምን ጉዞ ተጓዘ እግዚአብሔርንም እያገለገለ የሃይማኖትንም ሕግ በማስጠበቅ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ። በሹመቱ ወራትም ቤተ ክርስቲያን በጸጥታና በሰላም ኖረች።

ከዚሕም በኋላ እግሮቹን በጽኑዕ ደዌ ታመመ እግዚአብሔርንም ከዚሕ ደዌ ያሳርፈው ዘንድ ለመነው ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በሰላም በፍቅር በአንድነት አሳረፈው የሹመቱም ወራት አምስት ወር ከዐሥራምስት
ቀን ነው።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል

እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል
የተረሱትን ያስታውሳል
የተናቁትን ያከብራል

አንተ በክብር ላይ ክብርን ስትጨምር
እረኛው ይሾማል በንጉሱ ወንበር
ጌታ ትወዳለህ የተናቁትን
አንተ ልብን እንጂ አታይም ፊትን

አዝ

ሳሙኤልን ልከህ ጠርተህ ትቀባለህ
የአንበሶቹንም አፍ አንተ ትዘጋለህ
በጌርጌሴኖን በመቃብር ስፍራ
አየሁ ጌታዬ ለሰዎች ስትራራ
አዝ

ጠላታችን ደርሶ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከእስራት
አዝ

ይደግፋል ክንድህ የተናቁትን
ከሰው በታች ሆኖ የሚኖሩትን
ደስታም ትሰጣለህ ሃዘን አርቀህ
አይቀርም አልቅሶ አንተን ያመነህ
አዝ

ጠላታችን ደርሶ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከእስራት

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ

ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ከእኔ ጋር ስለሆንሽ  እመቤቴ አወድስሻለሁ
ምስጋናሽን ይዤ ጠዋት ማታ  ፊትሽ እቆማለሁ
ምስጋናሽን ይዤ እመቤቴ ፊትሽ እቆማለሁ

አዝ

ሀዘን ትካዜዬ በአንቺ ተወግዷል
ልመና ፀሎቴ ሀሳቤ ተሟልቷል
ያጣሁትን ሁሉ አግኝቼብሻለው
በእናትነትሽ ዘውትር እመካለሁ
አዝ

በአንቺ ደስ ይለኛል ያርፋል ልቦናዬ
ሰአሊ ለነ ብዬ ተቃና ጉዞዬ
አልፈራም እንግዲህ ገደል እንቅፋቱን
ይዘሽኛልና ድንግል አዛኚቱ
አዝ

የተስፋ መብራቴ አጠፊም ከፊቴ
መድኃኒቴ አንቺ ነሽ ለብቸኝነቴ
ይህቺ አለም ብትከፋ ፊቷን ብትመልስ
ጨክነሽ አታውቂም እናቴ በእኔስ
አዝ

ምስክር አልሻም ከእንግዲህ በኋላ
ነፍሴ ትጮሃለች አማላጄ ብላ
አወድስሻለሁ እናቴ እመቤቴ
በኑሮዬ ሁሉ እስከ እለተ ሞቴ

ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሠናይ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼በአዲስ አመት በገና፣ክራር ከበሮ መማር ይፈልጋሉ?🌼

መመዝገብ ለምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን

በ0956861468
በ0912085085 ደውለው ይመዝገቡ

እንዲሁም በቴሌግራም ለመመዝገብ ለምትፈልጉ
@Orthodoxtewahed0

በእዚህ ሊንክ በውስጥ ማውራት ትችላላችሁ

✝ያለው ቀሪ ቦታ ውስን ስለሆነ ቶሎ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን✝

መማሪያ ሰዓቶች
ከሰኞ-አርብ 11:00-1:00

ቅዳሜ እና እሑድ
3:00-5:00
6:00-8:00
9:00-11:00

ክፍያ የ6ወሩ በወር 700ብር
        የ3ወሩ በወር 1000ብር ነው ሁለቱም ዋጋቸው እኩል ነው አጠቃላይ 3000ብር ነው የሚመጣው። መመዝገቢያ 200ብር ይጨምራል።


✝ ከበሮ አለን የ1 ወር እና የ1 ሳምንት
የ1 ሳምንቱ ሙሉ ሳምንት ሲሆን
ከ8:00-10:00 እና 9:00-11:00 አለ
የአንድ ወሩ ከሆነ በሳምንት 2 ቀን ነው የምትማሩት። ሁለቱም ክፍያቸው ተመሳሳይ ነው 1100ብር ነው

Читать полностью…
Подписаться на канал