ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፪ /2/


የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ መጣ።

የከኀዲው ንጉስ ዮስጥያኖስ ሚስት በሃይማኖቷ የቀናች ነበረች። ቅዱስ አባ ሳዊሮስንም ትወደው ታከብረውም ነበር። በዚሕም ንጉሱ ሊገድለው እንደሆነ በአወቀች ጊዜ ለአባ ሳዊሮስ እንዲሸሽ ነገረችው፤ አባታችንም እኔ ስለ ክርስቶስ ለሞት የተዘጋጀው ነኝ አለ። ንግሥቲቱና ምዕመናኑም በለመኑት ጊዜ ወደ ግብፅ አገር ተሰደደ። የንጉሱ ወታደሮችም በመካከላቸው ሆኖ ሲጓዝ አላገኙትም ነበር፤ ጌታችን ይሠውረው ነበርና።

በአንዲት ቀንም በአስቄጥስ ገዳም በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን በመጻተኛ መነኩሴ አምሳል ገባ። በዚያም ቄሱ ዕጣኑንና ቁርባኑን ሊያሳርግ ጀመረ ሁሉንም ሥርዓት ፈጽሞ እጆቹን ታጥቦ ማኅፈዱን በገለጠው ጊዜ በጻሕሉ ውስጥ የቁርባኑን ኅብስት አላገኘውም፤ ደንግጦም አለቀሰ ለሕዝቡም ወንድሞቼ ይሕ የሆነ በእኔ ኃጢያት ወይም በእናንተ ኃጢያት እንደሆነ አላወቅሁም አላቸው።

መልአክም ተገልጦ ይህ የሆነ በኃጢአትሕ ወይም በሕዝቡ ኃጢአት አይደለም ሊቀጳጳሳት አባ ሳዊሮስ እያለ መሥዋዕትን ለማሳረግ በመድፈርሕ ነው አለው። ቄሱም መልሶ ሊቀጳጳሳት መኖሩን አላወቅሁም አለው፤ መልአኩም አባታችን ወደ ቆመበት ቦታ አመለከተው። ቄሱም ከአባታችን ከእግሩ በታች ሰግዶ ቡራኬ ተቀበለ። ወደ ቤተመቅደስም ገባ፤ በኋላም ቄሱ የቁርባኑን ኅብስት በጻሕሉ ውስጥ አገኘው ካሕናቱና ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ የቁርባኑም ሥርዓት ተፈጸመ።

ከዚያም ወጥቶ ወደ ሀገረ ስሐ ሄደ ምዕመናንንም በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው እስከሚያርፍባት የካቲት ወር ዐሥራ አራት ቀን ኖረ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​መጽሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በአንድ ጥራዝ የሚገኝ የብዙ መጻሕፍት ስብስብ የሆነ የተለየ፣ የተቀደሰ ጽሑፍ ማለት ነው። በውስጡም ከኢየሱስ ክርስቶስ በፊት የተጻፈ ብሉይ ኪዳንና ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ የተጻፈው ሐዲስ ኪዳን ተብለው የተከፈሉ መጻሕፍትን የያዘ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ የተባለበት ምክንያት ከሌሎች መጻሐፍት የተለየ  በመሆኑ ነው፡፡ የተለየ የሆነው በሚከተለው ምክንያቶች ነው ፡- 

. በመጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ የሚገኙት ጽሑፎች ከቅዱሱ ከእግዚአብሔር  የተገኙ እና የእግዚአብሔርን ቃል የያዙ ስለሆኑ፡፡
. መጽሐፉ ቅድስና ምን እንደሆነ፣ ሰዎች ቅዱሱን እግዚአብሔርን በቅድስና እንዲመስሉ የሚመክሩ የሚያስተምሩ ታሪኮችን እና ምክሮችን የያዘ መጽሐፍ በመሆኑ።
፫. መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነቡትን፣ የሚሰሙትን፣ የሚያምኑበትና  የተሳለሙትን ሁሉ የሚቀድስ፣ የሚባርክ ስለሆነ ቅዱስ ተብሏል።
፬. ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ።
፭. የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ሁነት እና ወደፊት  የሚፈጸሙትን በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ።

መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በተለያዩ ጊዜ እና ቦታ በነበሩ ከተለያዩ የሥራ መስክ በተሰማሩ ከ፵ በላይ በሚሆኑ ቅዱሳን ሰዎች ሲሆን፤ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ ያደረጋቸው እግዚአብሔር ነው፡፡

እግዚአብሔር መጽሐፍቱን እንዲጽፉ ያደረገበት ምክንያትም ሰዎች በእግዚአብሔር እንዲያምኑና ሕጉን እና ትእዛዙን አክብረው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው፡፡

በሌላ በኩልም መጽሐፍ ቅዱስ የጻፉትን ሰዎች የመረጣቸው እርሱ እግዚአብሔር ነው ሲመርጣቸውም የተለያዩ ሙያ የነበራቸው ሰዎችን ነው፡፡ እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፉት መካከል የተወስኑት እንመለከት፦ 

ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ፦

ኤርሚያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዘካሪያስ ካህናት ሲሆኑ ኢሳይያስ፣ ዳንኤልና ሆሴዕ ደግሞ ከነቢያነት ቅዱስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን ደግሞ ከነገሥነት ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው አሞፅ ደግሞ ከእረኛነት ነበረ።

ከሐዲስ ኪዳን ጽሐፊዎች ደግሞ 

ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ የሐንስ፣ ቅዱስ ያዕቆብ እና ቅዱስ እንድርያስ ከአሳ አጥማጅነት፣ ማቴዎስ (ሌዊ) ከቀራጭነት በመመረጥ መጽሐፍትን እንዲጽፉ አድርጓቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ መቼ ተጻፈ?

እግዚአብሔር ዘላለም የሚኖር አምላክ በመሆኑ በተለያዩ ዘመናት የነበሩ ሰዎች በመምረጥ ያጻፈው መጽሐፍ ነው። በመሆኑም መጽሐፉን የጻፉት ሰዎች የኖሩበት ዘመን የተለያየ እንደመሆኑ መጽሐፍቱም የተጻበት ዘመን እንዲሁ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ለመመለከት ያህል፦

እንደ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በመጀመሪያ የተጻፈው  መጽሐፈ ሄኖክ ነው። መጽሐፈ ሄኖክ ዓለም ከተፈጠረ በ፲፬፹፮ ዓ.ዓ ጌታችን አምላካችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ በፊት ፵፻፲፬ ቅ.ል.ክ ገደማ ተጽፏል፡፡ ከዚህም ቀጥሎ ሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሐፍት ከ፲፭፻ ዓ.ዓ-፫፻ ዓ.ዓ (ዓመተ ዓለም) ጌታችን  አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ በፊት ያለው ጊዜ እና አሁን ያለንበት ዓመት ማለት ነው።

ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐርገ በኋላ ከ፵፭ ዓ.ም- ፻ ዓ.ም፤ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጽፏል።

ምንጭ:- መጽሐፍ ቅዱስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምህር ቸሬ አበበ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደ እኛ

ሃናና ኢያቄም ወለዱ ሰማይ
አዲሷም ሰማይ አስገኘች ፀሐይ
ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛ
ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደ እኛ
/2/

አዝ

ተጨነቀ አዳም በመከራ
በእርግማን ቀን ለቅሶ እየዘራ
በልጅሽ ሞት ዓለም ተቀደሰ
የፍጥረቱ እንባ በመስቀል ታበሰ
/2/
አዝ

የሕያዋን እናታቸው ሆነሽ
ለቀደመችዋ ሔዋን ጠበቃ ሆንሽ
ደስተኛዋ ደስ ይበልሽ ማርያም
ከአንቺ ወጣ የዓለሙ ሰላም
/2/
አዝ

ፅዕኑ ገመድ በአንቺ ተቆረጠ
የፍዳ ዓመት ይኸው ተለወጠ
በሃና ልጅ በኢያቄም ፍሬ
ደስታ ሆነ ቅኔና ዝማሬ
/2/
አዝ

በወለዱሽ በሃና በኢያቄም
ተማፅነናል ድንግል ማርያም
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ልጆችሽን ጠብቂ ከጥፋት
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ኢትዮጲያን ጠብቂ ከጥፋት

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እውነት ነው አዎ እውነት ነው

እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው

ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
አንድያ ልጁን የምናምንበት
የህይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
የባህሪ አምላክ ብለን ስናምነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የአማልክት አምላክ ነው


በማርያም ስጋ የተገለጠው
ወልድን ስናውቅ ነው አብን ያወቅነው
አብ በእርሱ እንዳለ እርሱም በአብ አለ
በኃይል በሥልጣን የተካከለ
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ እርሱ ጌታ ነው


ሥጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍሶ
ህይወት የሰጠን በደልን ክሶ
እኛም ዳሰስነው በላን ጠጣነው
በዝግ ቤት ሳለን ገብቶ ያየነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው


ፈቅዶ ቢወሰን በአጭር ቁመት
ረቂቁ ቢገዝፍ በጠባብ ደረት
መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል
በዓለም ሊፈርድ ዳግም ይመጣል
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው


ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ

ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ ወጣሁት ዳገቱን
ድንግል ባንች ምልጃ አለፍኩት ወጥመዱን
ድንግል ማርያም በአንቺ ምልጃ ሰበርኩት ወጥመዱን

አዝ

አምላክ ቀድሶሻል ከሁሉም አብልጦ
ከአንቺ ይወለድ ዘንድ በሥጋ ተገልጦ
ለዓለሙ መዳን ምክንያት የሆንሽ
ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም አንቺ ነሽ
አዝ

ወጀቡን ልሻገር ባንቺ ተደግፌ
ድካሜ ይወገድ ከጥላሽ ሥር አርፌ
ያላንቺ መድኃኒት ከቶ የለምና
ባንቺ ተመገብኩት የሰማዩን መና
አዝ

ይመስገን ፈጣሪ የነዳዊት አባት
ቤቴን ሞልቶልኛል ባንቺ አማላጅነት
አንቺን የተጠጋ በነፍስም በሥጋ
ከልጅሽ ይወርሳል የሰማዩን ዋጋ
አዝ

ዳግም እንዳልራብ ነፍሴ እንዳትጠማ
ከማይደርቀው ምንጭሽ አጠጭኝ እማማ
ከቤትሽ ገብቼ እረፍት አግኝቻለሁ
እድፌ ተወግዶ አዲስ ለብሻለሁ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምን ሰማህ ዮሐንስ

ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ /2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2/

አዝ

ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር    
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /2/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ    
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /2/
አዝ

በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት  
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት /2/ 
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ  
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ /2/
አዝ

ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም    
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም /2/      
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ      
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ /2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በድንግል ትህትና

በድንግል ትህትና በዓለም ተደነቀ /2/
እዉነተኛ መጠጥ ከሆዷ ፈለቀ /2/
ሰዉ የሚድንበት ሮማንና ገዉዝ /2/
ከሆዷ ፈለቀ እንደ ምንጭ እንደ ወንዝ /2/

አዝ

ፀጋን ስላደላት የመዉለድ ስጦታ/2/
በፍቅር ሳበችው የፍጥረትን ጌታ /2/
ሰማያዊዉ አካል ከእርሷ ሥጋን ነሳ /2/
ፀሐይ ስለወጣ ቀረልን አበሳ /2/
አዝ

እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ስንከብር /2/
ታላላቅ አንስት እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ እርሷን አያህሉም /2/
አዝ

እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ስንከብር /2/
ታላላቅ አንስት እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ ድንግልን አይቀድሙም /2/
አዝ

እግዚአብሔር ምድርን አየና በሞላ /2/
ማርያምን አገኛት ከቤተ-መቅደሱ ከደጁ ተጥላ /2/
ከመላዕክቱ ጋር እየተጫወተች /2/
የሰማዩን መና እየተመገበች /2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት፤
ዘተወልደ እምማርያም ቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ
የማይሞት የማይለወጥ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ
ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስን የተዋሀደ
የሰዉ ልጅ ነው በምድር የተመላለሰ
አምላክም ነው በደልን የደመሰሰ

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ፣ ወተሰቅለ ዲበ ዕጸ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ
የማይሞት የማይለወጥ በማዕዶተ ዮርዳኖስ የተጠመቀ
የተቀበረውን የዕዳ ደብዳቤ ወዶ የፋቀ
በዕጸ መስቀል ቤዛ መድኃኒት የሆነ
በይቅርታ በምሕረት የተለመነ

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተንሥአ እምሙታን አመ ሣልስት ዕለት
ዐረገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ
በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት
ይኮንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ

የማይሞት የማይለወጥ በሦስተኛው ቀን ተነስቶ ሞትን የሻረ
ወደ አባቱ ቀኝ በኃይል ያረገ የተከበረ
በምስጋና ዳግም ለፍርድ የሚመጣው
አምላካችን ከሀሊ ስሙም ቅዱስ ነው

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፳፰ (28)

በዚች ቀን ቅድስት ሶስና አረፈች

ይህችውም ቅድስት የባዕለ ጸጋ ኢዮአቄም ሚስት የኾነች፣ የቅዱስ ሙሴን ሕግ የተማረችና ደጋግ የኾኑን አባትና እናቷም በመልካም ያሳደጓት፣ የኦሪትንም ሕግ ያስተማሯት አስተዋይ ቅድስት ናት።

በዚያም በባልዋ ቤት ብዙ እስራኤላውያን ይመጡ ነበርና የዚያም፡ቤት ቤተኛ ከኾኑት ኹለት የአይሁድ ረበናት ይገኙበታል። እኒህም ኹለት ግብዞች ደጋግመው ሶስናን አዩአት በዚህም ጸላኤ ሰናያት በልቡናቸው አደረና ዐይናቸው ኹሉ ግልብጥብጥ ብሎ በክፉ ሥራ ፈቀዷት።

አንድ እለት ከአትክልት ሥፍራ ዘግታ ስትታጠብ አገልጋዮቿን መልእክት ልካቸው እንደወጡ እኒህ ኹለት ክፉዎች ከተደበቁበት ወጥተው ፈቃዳችንን ፈጽሚ ካልፈጸምሽ ስታመነዝር ይዘናታል ብለን እንከስሻለን አሏት። እርሷም ከእጃቸው ማምለጥ አትችልምና ወደ ሰማይ አንጋጣ ቸሩን አምላክ በጽኑዕ ያድናት ዘንድ ተማጸነች።

እርሷም ፈቃዳቸውን ብፈጽምም ኾነ ባልፈጽም እሞታለሁ፣ ከፈጸምኹ ግን ከነርኲሰት ነውና የምሞተው ብላ አስባ እንደማትፈጽም ነገረቻቸው። ሦስቱም ሲጮኹ ሕዝብ ሲሰበሰብ ስታመነዝር አገኘናት አሉና ከሰሷት። እርሷም እንዲህ ያለ ነውር ተሰምቶባት አይታወቅምና ዘመዶቿ አፈሩ። በኋላም ለፍርድ በአደባባይ አቀረቧትና አየን ያሉትን ተናገሩ።

ሊወግሯትም ብለው ሲኼዱ ታላቁ ነብይ ቅዱስ ዳንኤል ቆይ እኔ ልመርምራቸው ብሎ አራርቆ ቢመረምራቸው አንዱ ከኮክ ዛፍ ሥር ነው ያየኋት፣ አንዱ ደግሞ ከሮማን ዛፍ ሥር ነው አለ። በዚህም ተለያይተዋልና ሕዝቡ እኒህን ኹለት ግብዝ ክፉ ሰዎች ገደሏቸው፣ ቅድስት ሶስናም በቸሩ አምላክ ታላቅ ነቢይ እርዳታ ዳነች።

በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​የበገና አካል ክፍሎች መንፈሳዊ ምሳሌ

1. ቀንበር (ጋድም)- የአኀዜ ኩሉ እግዚአብሔር ምሳሌ ሲሆን የሁሉ የበላይ መሆኑን ያጠይቃል።

2. ጌጥ (መስቀል)- እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ፍፁም ፍቅሩን የገለጸበት።

3. መቃኛ- የመቃኛ ምድራዊ ሕይወታቸውን በቅድስና፣ በሰማዕትነት፤ አሸንፈው ሰማያዊውን ድል በተቀዳጁ የቤተ ክረስቲያን ሰማያዊ አካል በጻድቃን ይመስላል።

4. የቀኝ ምሰሶ - የፍቅረ እግዚአብሔር፣ የብሉይ ኪዳን፣ የመጋቤ ብሉይ የቅዱስ ሚካኤል ምሳሌ።

5. የግራ ምሰሶ - የፍቅረ ቢፅ/ሰው/፣ የሐዲስ ከዳን፤ የመጋቤ ሐዲስ የቅዱስ ገብርኤል ምሳሌ ነው።

6. አውታር - በቁጥር አስር ሲሆኑ የአስርቱ ትዕዛዛት ምሳሌ ናቸው።

7. የድምጽ ሳጥን (ገበቴ)፦ የእመቤታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ፤ ከድምጽ ሳጥኑ (ገበቴው) የበገናው ድምጽ እንደሚገኝ ከእመቤታችንም አካላዊ ቃል ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷል፡፡

8. ብርኩማ - የደብረ ሲና ተራራ ምሳሌ።

9. እንዚራ - በተጋድሎ ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ይመሰላል።

10 መወጠሪያ፦ የሰዎች መኖሪያ /ምድር/ ይመሰላል።

11. ድህንጻ - የክርስቶስ ምሳሌ ነው። በክርስቶስ መመሰሉም፤ ጌታችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ በኦሪት ለሰዎች የሰጣቸውን ዐሥሩን ትእዛዛት ደግሞ በሐዲስ ቃኝቷቸዋልና፤ ይበልጥ አጥብቋቸዋልና ነው።

ከድምጽ ሳጥኑ (ገበቴ) ጀርባ (ኋላ) ላይ የመስቀል ቅርጽ ምልክት አለ፡፡ ይህ የመስቀል ምልክት ቅዱስ ዳዊት ከሳኦል ጦር የዳነበት ምልክት ሲሆን መስቀል በሐዲስ ኪዳን ከዲያብሎስ ፍላፃ የዳነበት /የምንድንበት/ ምልክታችን በመሆኑ ይህ ምልክት ተደርጓል::

በገና የሚሠራበት ቁስ (ማቴሪያል)

በገና ከእንስሳትና ከእጽዋት ተዋጽኦ የሚሠራ የዜማ መሳሪያ ነው፡፡ ቁመቱ ከ90 ሳ.ሜ. እስከ 140 ሳ.ሜ ይደርሳል፡፡ ነገር ግን እንደ ሠሪውና እንደ አሠሪው ፍላጎት ሊጨምር /ሊቀንስ/ ይችላል፡፡

ከእንስሳት ተዋጽኦ :-

1.አውታር(ጅማት):- ከበግ አንጀት ከበሬ ከላም ጅማት።
2. ቆዳ:- የድምጽ ሳጥኑ የሚለብሰው እና
መወጠሪያውን የሚያስረው ከበሬ፣ ከላም፤ ከበግ፣ ከፍየል ቆዳ
3. እንዚራ:- ከበሬ (ከላም) ቆዳ
4. ድህንፃ:-ከበሬ (ከላም) ቀንድ

ከእጽዋት ተዋጽኦ

ከእጽዋት ተዋጽኦ ማለትም ከዋንዛ፣ ከቀረሮ፣ ከዝግባ፣ ከጽድ ወ.ዘ.ተ. የሚሠሩ የበገና ክፍሎች ቀንበሩ(ጋድም)፣ ምሰሶዎቹ የድምጽ ሳጥኑ፣ ብርኩማው፣ መቃኛው፣ ጌጡ እና መወጠሪያው ናቸው።

ይህ የዜማ ዕቃ ቁሶቹን ከማለዘብ፣ ከማለስለስ፣ ጌጥ ከመቅረጽ፣ ለአያያዝ እንዲመች ከማድረግና ውበት ከመስጠት ውጪ ከተፈጥሮ ከተገኙ ቁሶች የሚሠራ ነው፡፡ በመሆኑም የሚያወጣው ድምጽ፣ የሚሰጠውም ዜማ ተፈጥሮአዊ ነውና መንፈስን ይማርካል፣ ነፍስን ያስደስታል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- የበገና መማሪያ መጽሐፍት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፳፯ (27)


በዚህችም ቀን ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት የሆነች ቅድስት ጤቅላ አረፈች።

የዚህች ቅድስት ወላጆቿ ከመቄዶንያ ሰዎች ውስጥ ባለጸጎች ናቸው እርሷንም እንደ ሀገራቸው ባህል በተግሣጽ በምክር አሳደጓት እነርሱ ግን ጣዖትን የሚያመልኩ ነበሩ። ሐዋርያው ጳውሎስም ወደዚህች አገር በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አምስትን ሊያስተምር ጀመረ ዐውቀው ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት ለእነርሱ ናትና።

ይህንን በሰማች ጊዜ ያለ መብልና መጠጥ ሦስት ቀን ኖረች። ከዚህም በኋላ ወደ ሐዋርያው ጳውሎስ ሔደች። እርሱም በደስታ ተቀብሎ የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራት። በማግሥቱም እናቷ ከቅዱስ ጳውሎስ ዘንድ አብራ ተቀምጣ አገኘቻት ከዚያም ወደ መኰንን ሒዳ ልጇን ክርስቲያን እንደሆነች ነገረችው። መኰንኑም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋራ እንዲያመጧት አዘዘ አስቀድመው ቅዱስ ጳውሎስን ወደ እሳት እንዲወረውሩት አዘዘ እግዚአብሔርም አዳነው።

መኰንኑም ቅድስት ጤቅላን ወደ እሳት እንዲወረውሩዋት አዘዘ። በዚያን ጊዜ በክርስቶስ ማዕተብ ራሷን አማትባ ራስዋን በራስዋ ወደ እሳት ወረወረች ማንም ያያት ሳይኖር ከእሳት ውስጥ ወጥታ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሔደች የራስዋን ጠጒር ቆርጣ ወገቧንም ታጥቃ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተለችው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ አንበሳና ድብ ከሚያድርበት ጨመራት እነርሱም ሰገዱላትና የእግሮቿን ትቢያ ላሱ። መኰንኑና ወገኖቹ ይህን አይተው በእግዚአብሔር አመኑ ቅድስት ጤቅላም ቅዱስ ጳውሎስን አገልግላ በሰላም አረፈች።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንዴት ወጣሁ ብዬ

እንዴት ወጣሁ ብዬ ከቶ አልደነቅም
አምንሀለሁና ትተኸኝ አታውቅም
ያ ሁሉም አለፈ ቀረ ወደ ኋላ
ማልቀስ ማንባት ይብቃኝ ከእንግዲህ በኋላ

አዝ

ከእንግዲ አይመጣም ያ ቀን ተመልሶ
ላያዳግም ሄዷል እንባዬን አፍስሶ
በመስቀል ላይ ሆነህ ችንካርህ ታይቶኛል
ያ ሁሉ መከራ ባንተ አልፎልኛል
አዝ

እንደምን ተነሳ አላዛር አትበሉ
ይችላል እግዚአብሄር ይችላል ሀያሉ
ታሪክ ሆኖ አልፏል ያኔ ያስጨነቀኝ
ስንቱን ተሻግረናል ጌታ እየጠበቀን
አዝ

ከአሳ አንበሪው መዳፍ ከጥልቁ ወጥቼ
ዘምርለታለሁ ዳግም ተሰርቼ
የሽቶዬን ብልቃጥ ሰበርኩት በፊቱ
በፅድቅ እንዲያስበኝ ጌታ በምህረቱ
አዝ

ቁስሌን ቆሰልክልኝ ጥሜንም ተጠማህ
መቼ ገባኝና የመስቀሉ አላማ
ለካ ስለፍቅር የማይሆኑት የለም
አሳየኸኝ ጌታ ታላቅ ነህ ዘላለም

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፳፮ (26)


በዚህች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ወደ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ልኮት መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ስለ መወለዱ አበሰረው።

ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና።

ልመናውንም ሰማ በቤተመቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በንጉስ ክርስቶስ ፊት እንደሚሄድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሰረው።

ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃው ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጀ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና መልአኩን ተከራከረው መልአኩም እኔ ይህን ልነግርህ ከእግዚአብሔር ወደ አንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠርም ባልተገባ ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል ብሎ ገሰጸው። ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበትጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ።

በሚገረዝበት ቀንም የሕፃኑን አባት  ዘካርያስን የሕፃኑን ስሙን ማን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም
እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሄድ ትንቢት ተናገረ።


በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ላመስግንህ የኔ ጌታ

ላመስግንህ የኔ ጌታ ላመስግንህ
ልቀኝልህ የኔ ጌታ ልቀኝልህ
ህይወቴ ነው ዝማሬዬ ትሩፋቴ
የሰጠኸኝ እንዳከብርህ አንተ አባቴ/2/

አዝ

ከኔ የሆነ የምሰጥህ ባይኖረኝም
ከሰጠኸኝ የአንተን መስጠት አይከብደኝም
ጥበቤ ነህ የምስጋና መሰረቴ
ዝማሬዬን ያፈሰስከው በህይወቴ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና/2/
አዝ

ባዶ እኮ ነኝ የኔ ጌታ ምን ልቅዳልህ
በእጄ ላይ አንዳች የለኝ የምሰጥህ
ላንተ ክብር የሚመጥን ህይወት የለኝ
ዝማሬዬን በቸርነት ተቀበለኝ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና/2/
አዝ

ከምድር ላይ ከአፈር ስትፈጥረኝ
ከምስጋና የተለየ ምን ሥራ አለኝ
ቀን እና ሌት በመቅደስህ እቆማለሁ
አምላኬ ሆይ ሳወድስህ እኖራለሁ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና/2/.
አዝ

ዕዝራ ስጠኝ የከበረ መሰንቆህን
ዳዊት ስጠኝ የሚፈውስ በገናህን
መዝሙር ቅኔ ተምርያለሁ ከአባቶቼ
ዘምራለሁ ባንተ ፍቅር ተነክቼ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና/2/

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፳፭


በዚች ቀን ታላቅ ነቢይ ዮናስ አረፈ።

ስሙ ከፍ ከፍ ያለና የተመሰገነ እግዚአብሔር ወደ ነነዌ ሀገር ሂደህ ሀገራችሁ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ትጠፋለች ብለህ አስተምር ብሎ አዘዘው። ዮናስም በልቡ እግዚአብሔር መሀሪ ነው በኋላ ሲምራቸው እኔ ሀሰተኛ ነቢይ እባላለው እንዳይገድሉኝም እፈራለው፤ ወደዚያች ሀገርም ሄጄ እንዳላስተምር ከእግዚአብሔር ፊት ብኮበልል ይሻለኛል ብሎ አሰበ።

ዮናስም እግዚአብሔርን ሽሽት ወደ ተርሴስ ሊሄድ በመርከብ ላይ ወጣ። እግዚአብሔርም ታላቁን ነፋስ ወደ ባህር አመጣ መርከባቸውም ሊሰበር ቀረበ በመርከቧም የነበሩ ፈርተው ይህች መከራ ያገኘችን ስለማናችን ኃጢአት እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ኑ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣበት።

ዮናስም ማዕበሉ እንዲቆም አንሥታቹ ወደ ባህር ጣሉኝ ይተዋችኋል ይህ ታላቅ ሞገድ የመጣው በእኔ ምክንያት ነው አላቸው። እነርሱም የጻድቅ ሰው ደም አታድርግብን ብለው ዮናስን አንስተው ወደ ባህር ጣሉት። በባህርም ታላቅ አሳ አንበሪ ዋጠው በሆዱ ውስጥም ሦስት ቀንና ሦስት ለሊት ቆየ። ከዛም ዮናስ ወደ ከተማ ሊገባ የአንድ ቀን መንገድ ሲቀረው ነነዌ እስከ ሦስት ቀን ትጠፋለች ብሎ አስተማረ።

የነነዌ ሰዎችም የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ ሁሉም ሰው ጾምን እንጹም ብለው አወጁ ንጉሳቸውም ህዝቡም ልብሳቸውን አውልቀው ማቅ ትቢያ ለበሱ። እግዚአብሔርም ንሰሐቸውን ተቀብሎ ከቁጣው ተመለሰ። ዮናስም ነቢየ ሀሰት እየተባልኩ ከምኖር ሞት ይሻለኛልና አቤቱ አሁን ነፍሴን ከሥጋዬ ለያት አለ። ከዚህም በኋላ ዮናስ ተነስቶ ወደ ሀገሩ ተመልሶ በሰላም አረፈ መላ ዕድሜውም መቶ ሰባ ነው።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ

ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ከእኔ ጋር ስለሆንሽ  እመቤቴ አወድስሻለሁ
ምስጋናሽን ይዤ ጠዋት ማታ  ፊትሽ እቆማለሁ
ምስጋናሽን ይዤ እመቤቴ ፊትሽ እቆማለሁ

አዝ

ሀዘን ትካዜዬ በአንቺ ተወግዷል
ልመና ፀሎቴ ሀሳቤ ተሟልቷል
ያጣሁትን ሁሉ አግኝቼብሻለው
በእናትነትሽ ዘውትር እመካለሁ
አዝ

በአንቺ ደስ ይለኛል ያርፋል ልቦናዬ
ሰአሊ ለነ ብዬ ተቃና ጉዞዬ
አልፈራም እንግዲህ ገደል እንቅፋቱን
ይዘሽኛልና ድንግል አዛኚቱ
አዝ

የተስፋ መብራቴ አጠፊም ከፊቴ
መድኃኒቴ አንቺ ነሽ ለብቸኝነቴ
ይህቺ አለም ብትከፋ ፊቷን ብትመልስ
ጨክነሽ አታውቂም እናቴ በእኔስ
አዝ

ምስክር አልሻም ከእንግዲህ በኋላ
ነፍሴ ትጮሃለች አማላጄ ብላ
አወድስሻለሁ እናቴ እመቤቴ
በኑሮዬ ሁሉ እስከ እለተ ሞቴ

ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሠናይ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼በአዲስ አመት በገና፣ክራር ከበሮ መማር ይፈልጋሉ?🌼

መመዝገብ ለምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን

በ0956861468
በ0912085085 ደውለው ይመዝገቡ

እንዲሁም በቴሌግራም ለመመዝገብ ለምትፈልጉ
@Orthodoxtewahed0

በእዚህ ሊንክ በውስጥ ማውራት ትችላላችሁ

✝ያለው ቀሪ ቦታ ውስን ስለሆነ ቶሎ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን✝

መማሪያ ሰዓቶች
ከሰኞ-አርብ 11:00-1:00

ቅዳሜ እና እሑድ
3:00-5:00
6:00-8:00
9:00-11:00

ክፍያ የ6ወሩ በወር 700ብር
        የ3ወሩ በወር 1000ብር ነው ሁለቱም ዋጋቸው እኩል ነው አጠቃላይ 3000ብር ነው የሚመጣው። መመዝገቢያ 200ብር ይጨምራል።


✝ ከበሮ አለን የ1 ወር እና የ1 ሳምንት
የ1 ሳምንቱ ሙሉ ሳምንት ሲሆን
ከ8:00-10:00 እና 9:00-11:00 አለ
የአንድ ወሩ ከሆነ በሳምንት 2 ቀን ነው የምትማሩት። ሁለቱም ክፍያቸው ተመሳሳይ ነው 1100ብር ነው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፩ /1/


በዚህችም ቀን ቅድስት አንስጣሲያ በሰማዕትነት አረፈች። ይህችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርአት አሳደጓት።

በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቡአት ፈለጉ እርሷ ግን በሥውር በሮሜ ከሚገኙ ወደ አንዱ ገዳማት ሂዳ የምንኩስና ልብስን በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ ሥጋዋን አደከመች በቀኑ ርዝመት ትጾማለች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በጌታችን ጾም ግን ያለ ሰንበታት ቀን አትመገብም።

ከዚሕም በኋላ የንጉስ ዳኬዎስ ወታደሮች ክርስቲያኖችን አሥረው በቁጣ ሲጎትቷቸው አይታ ልቧ በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው
የእውነት ፈጣሪን የካዳቹ ልባቹ የደነዘዘ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለ እነርሱም ነፍሱን አሳልፎ በሰጣቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላቹ።


ወታደሮቹም ይሕን ሲሰሙ ተቆጡ ይዘውም ወደ መኮንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስቲያን ነሽን እርሷም ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለው ብላ መለሰችለት።

በዚያን ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ ከዛም ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም አጤሱባት ከሃይማኖቷም ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ትክክለኛው የዝማሬ ዳዊት የቲክቶክ ገጽ ይህ ነው።
https://vm.tiktok.com/ZMhDY21ox/
https://vm.tiktok.com/ZMhDY21ox/

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፴ /30/


በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በከበረና በተመሰገነ በአባ አትናቴዎስ ላይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም ሁለተኛም ቁስጠንጢኖስ ወደ ረከሰች የአርዮስ ሃይማኖት በገባ ጊዜ የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስን አሳድዶ ከሀዲውን ጊዮርጊስን በእስክንድርያ መንበር ላይ ሾመው።

ቅዱስ አትናቴዎስም በተሰደደበት ስድስት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሡ ሔዶ እንዲህ አለው ወደ ተሾምኩበት መንበሬ ትመልሰኝ እንደሆነ መልሰኝ ይህ ካልሆነ የምስክርነት አክሊልን እንድቀበል ግደለኝ አለው። ንጉሱም እርሱን ቢገድለው እንደሚበጠበጥ አውቆ በብልሐት ሊያጠፋው ወሰነ።

በመርከብ አድርጎ ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም ቀዛፊ በሌለበት በሜድትራኒያን ባሕሪ ላይ ጣለው። መለዕክትም እየመገቡት እና መርከቡን እየቀዘፉለት እስክንድሪያ አደረሱቱ። የምእመናን ወገኖችም ደግ ጠባቂያቸው እንደ ደረሰ በሰሙ ጊዜ በታላቅ ደስታ እየዘመሩ ተቀብለውታል፡

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አሰራር ሥርዓት

እግዚአብሔር በባሕርይ ምልዓቱ የተነሳ የሌለበት ቦታ ባይኖርም  ውስን ፍጥረታት እኛ ለሕሊናችን በሚስማማ ሁኔታ በውሱን ቦታ  እንድናመልከው አዝዞናል፡፡ ይህም ለእኛ መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን እርሱም በእኛ በረድኤትና በጸጋ ላለመለየቱ የቃል ኪዳን ቦታ መሆኑ  ነው። እስራኤልን

‹‹በመካከላችሁ አድር ዘንድ መቅደስን ሥሩልኝ›› ያላቸው ለዚህ ነው፡፡ ዘጸ ፳፤፱

ሰዎችም ምሕረትና ይቅርታ ረድኤትና  በረከት ሲፈልጉ ወደዚህ ቦታ ይመጣሉ። የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንም ያለሥርዓት አትተከልም ቅዱስ ጳውሎስ  ‹‹ ... የኩነኔ አገልግሎት በክብር ከሆነ የጽድቅ አገልግሎት በክብር  አብዝቶ ይበልጣልና ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚሁ ነገር ክብሩን አጥቷልና ያ ይሻል የነበረው በክብር ከሆነ ጸንቶ  የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ይሆናል፡፡›› ብሎ እንደተናገረው  በሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የምትተካው ቤተመቅደስ ይህን ያህል ሥርዓት ከነበራት በሌላ የማትተካው በክርስቶስ ደም የተመሠረተችው ቤተክርስቲያን ይልቁንም እጅጉን ትከብራለችና በሥርዓት ትተከላለች ፪ቆሮ ፫፤፯-፲፩ ማንኛውም ቤተክርስቲያን በተለያየ ቅርጽ ቢሠራም 
ሦስት ክፍል አለው፡፡ ይኸውም በሰሎሞን ቤተመቅደስ አምሳል ነው። ምክንያቱም ለብዙ ክርስትና እምነት ሥርዓት መሠረቱና ምሳሌው የብሉይ ኪዳን ሥርዓት ነውና፡፡

ሀ. ቅኔ ማኅሌት፡- ስያሜው ከግብሩ የተወረሰ ነው፡፡ ይህ ክፍል በቤተ  ክርስቲያን ከውጪ ወደ ውስጥ ስንገባ በመጀመሪያ የምናገኘው ክፍል ነው፡፡ መዘምራን ስብሐተ እግዚአብሔር ማኅሌተ እግዚአብሔር የሚዘምሩበት ነውና። በዚሁ ክፍል ሰሜን ምስራቅ በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት በመንፈቀ ሌሊትና በነግህ ሰዓታት ይቆሙበታል፡፡ በምዕራብ አቅጣጫ መዘምራን የሚዘምሩበት፣ ቅኔ የሚቀኙበት፣ ማኅሌት ቆመው የሚያስቀድሱ ሲሆን ንፍቅ ዲያቆናት፣  አናጉንስጢስና መዘምራን በዚህ ሥፍራ ያስቀድሳሉ፡፡ በዚሁ ክፍል ደቡብ ምስራቅ በኩል የሚገኘው ቦታ የሴቶች  መቆሚያ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ወንድና ሴት አብረው መቆም ስለማይችሉ በመጋረጃ ይጋረዳል፡፡ በምሥራቅ የካህናት፤ በሰሜን የወንዶች፤ በደቡብ የሴቶች መግቢያ ይሆናል፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ በአራቱ ማዕዘናት አቅጣጫዎች አራት ወይም ሦስት በሮች አሉት፡፡

ለ. ቅድስት፡- ቅድስት ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ የተመረጠ፤ የተለየ  ማለት ነው፡፡ ይህ ክፍል የሚገኘው በቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ቦታ ነው፡፡ በምዕራብ በኩል ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ቆሞሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ሲሆኑ በሰሜን በኩል ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ደግሞ መነኮሳት፣ የሚቆርቡ ወንዶች ምእመናን ናቸው፡፡ በስተደቡብ በኩል  ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ደግሞ ንጽሕ ጠብቀው የኖሩ ደናግል  መነኮሳት እንዲሁም መአረገ ክህነት ያላቸው ቀሳውስትና ዲያቆናት  ምዕመናን ናቸው፡፡

በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያኑ በአራቱ ማዕዘናት አቅጣጫ አራት በሮች አሉት። በቅዳሴ ጊዜ በስብከተ ወንጌል ሰዓት መምህራን ቆመው የሚያስተምሩበት  ክፍልም ነው፡፡ ካህናት በድርገት ጊዜ ምዕመናንን የሚያቆርቡበት ቦታ ነው፡፡ በተክሊልና በቁርባን ለሚጋቡ ሙሽሮች ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸምበት ነው፡፡

በስቅለት ዕለት ሥርዓተ ጸሎት ይፈጸምበታል፡፡ ካህናት ኪዳን ዘነግህ ያደርሱበታል፡፡ የማይቆርቡ ምዕመናን በዚህ ቦታ ቆመው ማስቀደስ አይችሉም፡፡

ሐ. መቅደስ፡- መቅደስ ስያሜው ከብሉይ ኪዳን ‹ቅድስተ ቅዱሳን› አሰያየም ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን በዚህ ውስጥ ኅብስቱ ወደ አማናዊ ሥጋ መለኮት ወይኑም ወደ አማናዊ ደመ መለኮት በጸሎተ ቅዳሴ የሚለወጥበት ሥርዓተ ቅዳሴው የሚመራበት ቅዱስ ሥጋውና  ክቡር ደሙ የሚፈተትበት ነው። መንበረ ታቦቱና ሌሎችም ንዋያተ ቅድሳት በዚህ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ክፍል ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ያስቀድሱበታል፤ ቀሳውስትና ዲያቆናትን ጨምሮ በዚህ ክፍል ሥጋ ወደሙንም ይቀበሉበታል፡፡ ወደዚህ ክፍል ለመግባት የሚችሉት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ፣ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት፡ ቀሳውስትና ዲያቆናት ብቻ ናቸው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:-ሥራዓተ ቤተክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፳፱


በዚህች ዕለት ቅድስት አርሴማ እና አብረዋት የነበሩ ደናግሎች ሰማዕት ሆኑ።

ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ የቅድስት አርሴማን ሥዕሏንም ሥለው ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።

ደናግልሉም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው ወደ አርማንያ በሥውር ሸሹ። ከእርሷ ጋርም ሰባ አምስት ወንዶችና ሠላሳ ዘጠኝ ሴቶች ነበሩ።

ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን ወታደር ወደ እኔ አምጣት ብሎ አዘዘው። እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወሰዷት።

ድርጣድስም እናቷ አጋታን እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው።

ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ። በዚህች ዕለትም ሰማዕትነትን ተቀበሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አማኑኤል ይቅር ባይ ነው ፍቅር

አማኑኤል ይቅር ባይ ነው ፍቅር
ምህረት ከቦት በሰማያት ሚኖር
እያመመው አባቱን እየጠራ
አይቻለሁ ለሚገድሉት ሲራራ

አይምረኝም አትበሉ ጨካኝ ንጉስ አይደለም
ደሙ ብቻ ያነጻናል ከኃጢአታችን ዘለዓለም
እንደሞላ ጅረት ፈሶ ምድራችንን አጥለቅልቋል
የእርሱ ምህረት ኃያል ሆኖት ስንቱ ከሞት አፈትልኳል
መድኃኔዓለም ይቅር ባይ ነው ፍቅር
ምህረት ከቦት በሰማያት ሚኖር
እያመመው አባቱን እየጠራ
አይቻለሁ ለሚገድሉት ሲራራ

የጨለመው እየነጋ የተሻለ ቀን ይመጣል
በፍቅሩ ጦር ሳይወጋ ማን ከሞት ፊት ሮጦ ያመልጣል
ያን ክፉ ቀን በድል አልፈን እንደዋርካ የሰፋነው
ነውርን ሁሉ በሚከድን በሞተልን በኢየሱስ ነው
ጌታ ኢየሱስ ይቅር ባይ ነው ፍቅር
ምህረት ከቦት በሰማያት ሚኖር
እያመመው አባቱን እየጠራ
አይቻለሁ ለሚገድሉት ሲራራ

የእርሱን ፍቅር የሚያሸንፍ አንዳች ኃጢአት የለምና
ወደ ጌታ ለመመለስ አንዳች እንኳን እንዳትፈራ
ሃገራችን በሰማይ ነው የሚወድቅ የለም የሚረሳ
ሰማያትን እንወርሳለን በበጉ ደም የተነሳ
ጌታ ኢየሱስ ይቅር ባይ ነው ፍቅር
ምህረት ከቦት በሰማያት ሚኖር
እያመመው አባቱን እየጠራ
አይቻለሁ ለሚገድሉት ሲራራ

ወዳጅ አለን አንድ ብቻ በሰማይም በምድር
ስሙ ኢየሱስ የተባለ ሰውን ሁሉ የሚያፈቅር
ከመቃብር በላይ ሆኖ ፍቅሩ ዓለምን አስገረመ
ይህን ሁሉ ጎስቋል ሰው በትከሻው ተሸከመ
ጌታ ኢየሱስ ይቅር ባይ ነው ፍቅር
ምህረት ከቦት በሰማያት ሚኖር
እያመመው አባቱን እየጠራ
አይቻለሁ ለሚገድሉት ሲራራ

ዘማሪ ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አክሊለ ጽጌ ማርያም

አክሊለ ጽጌ ማርያም አክሊለ ጽጌ/2/
አክሊለ ጽጌ ማርያም አክሊለ ጽጌ/2/
ቀጸላ መንግስቱ መንግስቱ ለጊዮርጊስ
ቀጸላ መንግስቱ መንግስቱ ለጊዮርጊስ
ክበበ ጌራ ወርቅ
ክበበ ጌራ ወርቅ
አክሊለ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ
ክበበ ጌራ ወርቅ
አክሊለ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ
ክበበ ጌራ ወርቅ
አክሊለ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ
ክበበ ጌራ ወርቅ
አክሊለ ጽጌ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መድኃኔዓለም ሥምህ ገናና

በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል
ክብርህም በምድር ይነገራል
ዘመን የሚዋጅ አለን ምስጋና
መድኃኔዓለም ሥምህ ገናና /2/

አዝ

እልፍ አዕላፍ መላዕክት
ቢቆሙ ካንተ ፊት
አያርፉም ይተጋሉ
ሥሉስ ቅዱስ እያሉ
ያለና የሚኖር /2/
አንተ ነህ እግዚአብሔር
አዝ

ሊቃናት ይጮሃሉ
በጉ ድል ነሳህ እያሉ
የወርቅ ጽንሐ የያዙ
ምስጋናህን አበዙ
ያለና የሚኖር /2/
አንተ ነህ እግዚአብሔር
አዝ

በደምህ የታተሙ
ኃይልህን ተሸከሙ
የቅኔ ዑደት ሆነ
ክብርህ በዓለም ገነነ
ያለና የሚኖር /2/
አንተ ነህ እግዚአብሔር
አዝ

በዙፋኑ ሥር ካሉት
ከሰባቱ መናፍስት
ከታመነው ምስክር
አዲስ ውዳሴ መዝሙር
ያለና የሚኖር /2/
አንተ ነህ እግዚአብሔር

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በብርሃን ጸዳል

በብርሃን ጸዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የጽጌውን ዜማ ስዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ ሲሰማኝ እርካታ

አዝ

እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ሕልሜ የቀን ምኞቴ ነው
አዝ

እሩህሩህ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህሊናዬ ረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ሕሊናዬ ይትጋ
አዝ

ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ሕሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይጻፍብኝ በልዩ ሕብር

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አጋጣሚ_አይደለም

አጋጣሚ አይደለም መትረፌ መዳኔ
የጌታ ተአምር ነው አረ ይገርማል የኔ
ሞት እንቅልፍ ሆነልኝ ጭንቀቴ ቀለለ
የረዳኝ ጌታ ነው ውዴ እየተከተለ

አዝ

ማነው በዛ በረሀ ያበላኝ መና ያጠጣኝ ውሀ
ማነው የደገፈኝ ጥልቁን ሸለቆ ያሻገረኝ
አንተ ነህ ለኔ እናት አባቴ
ፍፁም ወዳጄ ስጋና አጥንቴ
አይኔ አይነቀል ከዙፋንህ
ፊት አያዞርም ፍቅር አይንህ
አዝ

ወሮኝ ድቅድቅ ጨለማ ተስፋዬ መክኖ ልቤ ሲደማ
አይቶ ሲፈስ እንባዬ ደመና ጠቅሶ መጣ ጌታዬ
ፀሐይ ነውና የብርሀን አምዴ
ኢየሱስ ለኔ ህይወት መንገዴ
አልተሸነፍኩም ውዴ አግዞኛል
መቃብር ከፍቶ ህይወት ሰቶኛል፤
አዝ

ሲለይ ነፍስ ከስጋ በጨለማ ቀን በክፉ አደጋ፤
ዳንኩኝ ሞት እያየኝ የንስሀ እድሜ ጨመረልኝ፤
በፅድቄ አይደለም የተረፍኩት
በሱ ፍቅር ነው በሱ ምህረት
ብቻዬን ሆኜ ሁሌ ማለቅሰው
እየበደልኩት ስላዳነኝ ነው፤
አዝ

ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ
ብሎ ጥሎሀል እየታገለ
ሲኦል ድል መግዛትህ
ባዶ ቀርተሀል ተበዝብዘህ
በእራሱ መንግስት ፈጥሮኝ በአላማ
የልጁን ህይወት ማንም አይቀማ
መቃብር ያልፋል በአገልግሎቴ
ተከፍቶልኛል ደጁ የአባቴ

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ፆመ ፅጌ / የፅጌ ፆም

የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ።

ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡

በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡

ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡

እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”

የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡

ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡

ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የአካኮ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ተዐምር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መሐረኒ ድንግል

መሐረኒ ድንግል ወተሰሐለኒ በበዘመኑ /2/
ለእመ መሐርከኒ /3/ አንቲ ዘይኮንነኒ መኑ
ኩናኔ ሥጋ ወነፍስ /2/ ወልድኪ አኮኑ

አዝ

ይጠሩሻል ካህናቱ
ንኢ ይሉሻል በሰዓታቱ
ለለመነሽ የማትቀሪ
በልቤ ውስጥ ፀንተሽ ኑሪ
የሥጋና የነፍስ ፈራጅ /3/
ልጅሽ አይደለም ወይ
መሐርኒ ድንግል ወተሰሐለኒ በበዘመኑ /2/
ለእመ መሐርከኒ /3/አንቲ ዘይኮንነኒ መኑ
አዝ

የአዲስ ኪዳን ኪሩብ የሆንሽ
ለምኝልን ከአንዱ ልጅሽ
እርግብየ ሰናይትየ
ነይ ወደኔ ነይ ወልድየ
ኩናኔ ሥጋ ወነፍስ /3/ ወልድኪ አኮኑ
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ/2/
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ
እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ
ልጅሽ አይፈርድብኝ
አዝ

በዓለም መኖር ሰልችቶኛል
መልካም መስራት አቅቶኛል
እጄን ይዘሽ ድንግል ምሪኝ
አዛኝቷ አትለይኝ
የሥጋና የነፍስ ፈራጅ /3/
ልጅሽ አይደለም  ወይ
መሐርኒ ድንግል ወተሰሐለኒ በበዘመኑ /2/
ለእመ መሐርከኒ/3/ አንቲ ዘይኮንነኒ መኑ
አዝ

እበላለሁ ብዬ ማርያም
እመካለሁ ባንቺ አላፍርም
ካንቺ ወዴት እሄዳለሁ
ስምሽን ልጥራው እጽናናለሁ
ኩናኔ ሥጋ ወነፍስ/3/ ወልድኪ አኮኑ
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ/2/
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ 
እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ
ልጅሽ አይፈርድብኝ

ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал