📣የዛሬው ምሽት ስለ ነገረ ማርያም የነበረን ትምህርት በእዚህ ላይ እናበቃለን📣
ቅዳሜ ምሽትም በተመሳሳይ ሰዓት 2:00 ላይ ቀጣዩን ክፍል የምንቀጥል ይሆናል። ሁላችሁም ቅዳሜ 2:00 ላይ ጠብቁን።
👉እስከ አሁን የነበረውን ትምህርት ከወደዳችሁት በኮመንት ላይ አሳውቁን።
ከ8,000 ሰው በላይ ይሄንን ቻናል በአንድ ቀን ውስጥ እየተመለከተው ግን ለምትወዷቸው ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችሁ የእኛን ቻናል እንዲቀላቀሉ ለምን እንደማትልኩላቸው አላውቅም።
🤲እባካችሁ ድንግል ማርያምን አትወዷትም? ጓደኞቻችሁስ በደንብ ፍቅሯ እንዲያድርባቸው አትፈልጉም? ለምን አትልኩላቸውም?
አሁን ድንግል ማርያምን ከወደዳችኋት ለ20-30 ጓደኞቻችሁ አሁን በኃላፊነት የቻናላችንን ሊንክ ላኩላቸው አሁን። ከእዛም ከላካችሁ በኋላ ልከናል ብላችሁ ኮመንት አድርጉ🙏🙏🙏
ሊንኩ 👉 /channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
🤲🤲🤲ስለ ነገረ ማርያም🤲🤲🤲
ዛሬ ማታ 2:00 ላይ ትምህርታችንን የምንጀምር ስለሚሆን ሁላችሁም 2:00 ላይ ተሰብስባችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን።
መምህር ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን
ይሄንን ትምህርት ጓደኞቻችሁ እንዲማሩ ይሄንን ማስታወቂያ ላኩላቸው ከታች ያለውን ሊንክ በመግባት ይቀላቀሉን።
🌙 የማታ ሰው ይበለን 🌙
ድል አለ በስምህ
በስልክ የተቀዳ
ድል አለ በስምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኔዓለም ስልህ
ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውሀ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የጸና ስምህ ነው
አምላኬ የጸና ስምህ ነው
አዝ
በእልልታ ቢፈርስ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ካንተ ነው/2/
አዝ
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውሀ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ስለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ስለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
አዝ
የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነኸን ነው ክብርና ሞገስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በዝማሬ ዳዊት ቻናል የምትለቋቸው መልዕክቶች እኛ ጋር Not supported ነው የሚለን ብላችሁ መልዕክት ለላካችሁልን ተከታታዮች በሙሉ፤ እባክዎ ከስር ባስቀመጥነው ሊንክ የቴሌግራም መተግበሪያዎን ያዘምኑት /Update/ ያድርጉት።
https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger
ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ
ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጳጉሜ 1
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ጌታችን ኢየሱስ ለሕዝብ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ ምን ልታዮ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን...እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም...ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ተናገሩ። ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው። (ማቴ 11÷7-15)
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች በዝማሬ ዳዊት ገጽ የሚለቀቁትን ለወዳጅዎ ለማጋራት ካሰቡ ከታች ያስቀመጥነውን ቅደም ተከተል ተከተሉ።
1. ማጋራት የፈለጉትን መልዕክት ሲነኩ ከሚዘረዝርልዎ አማራጭ መካከል Copy link የሚለውን ይንኩት።
2. ለሚፈልጉት ሰው ወይም ማጋራት ወደሚፈለጉበት ቻናል ወይም ግሩፕ ላይ Copy ያደረጉትን ወስደው Past ማድረግ።
3. የዝማሬ ዳዊት ገጽን ከፍተው ሲገቡ ከስር UNMUTE የሚል ከሆነ የሚታይዎት ወደ MUTE መቀየርዎን አይዘንጉ።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን! አሜን።
✞ ዮሐንስ መጥምቅ ✞
መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ(፪)
ያስተፌስህ መላዕክተ ወሰብአ መዋቴ(፪)
ዘካርያስ አየ የገብርኤልን እውነት
በእርጅና ዘመንዋ ስትወልድ ኤልሳቤጥ
የልቦና መንገድ ከጥርጥር ጸድቶ
ዓለም ተደሰተ ልደትህን ሰምቶ
ዮሐንስ መልአክ ለእግዚአብሔር ቅሩቡ
ወርቀ ኪዳንከ ለነዳይ መዝገቡ
ዮሐንስ ዘኮንከ ደመና ሰማይ ኮናኔ
አዝንም መና አእምሮ ወህብስተ ወጥበበ መድኃኒት
ዮሐንስ ጠቢብ ሐመረ ክርሰቲያን አዳፊ
ኢይትዔየረከ በዕበይ በሰማይ ሱራፊ
ዮሐንስ አንተ ጽልመተ አበሳ ሰዳዴ
በአየረ ሰማይ ይጸርሕ ቃልከ ዓዋዲ
ዮሐንስ ልብ መዝገበ ጥበብ ወአእምሮ
ፍጹመ መነንከ አብያተ ዘውቅሮ
ነሐሴ 30
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትንቢተ ሚልክያስ 3:8
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ትንቢተ ሚልክያስ 3:10
ዘማሪ ዲ/ን ሱራፌል ስዩም አባክህን ይህን እየተመከትክ ከሆነ ወይም የምታውቁት ካላችሁ ከታሽ ባስቀመጥነው አድራሻ መልዕክት ይላክልን። አድራሻህ ከስልካችን ስለጠፋብን ነው።
📩 @Zimaredawitmessanger
ነሐሴ 29
ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው። ከዚያ አምጥተህ አብላኝ
ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው አላቸው።
ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን
አብርሃም አብርሃም
አብርሃም አብርሃም ደጉ ምዕመን
ተብለህ ተጠራህ አበ ብዙኃን
የልዑል ምሳሌ ለሆነው ካህን
አክብረህ ሰጠኸው ከአስር አንዱን
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ነሐሴ 28
👉ስለ ድንግል ማርያም
👉ስለ ፍጹም ድንግልናዋ
👉አምላክን ስለመውለዷ
👉ስለ አማላጅነቷ እና ሌሎችም ጥያቄዎች መልስ ከፈለጋችሁ እነዚህን አዳምጧቸው
ጳጉሜ 2
ስለነፍስህ ተጋደል አለው።
ቅዱሱ ጲላጦስ
ብዙዎቻችን መስፍኑን ጲላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን። የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል። የጲላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል። ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል።
ጲላጦስም ከሚስቱ አብሮቅላ ስለ እግዚአብሔር ገናንነት እየተጨዋወቱ ኹለቱም ስለ ትንሣኤው ሲነጋገሩ ከደመና ድምፅ ተሰማ።
ከደመናውም ጲላጦስ ሆይ በዚኽ ደመና ላይ በክብር ተቀምጠው ወደ ገነት የሚወስዷቸውን እነዚህን ነፍሳት ታያለህን፡፡ ይኽም የሄሮድስ ወታደሮች ከመቶ አለቃው ጋራ በመንገድ የገደሏቸው ናቸው፡፡ እንደዚሁም አንተንም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ምክንያት በሮም አንገትህን በሰይፍ ይቈርጡሃል፡፡
የአንተንና የሚስትህ አብሮቅላን ነፍስ በዚኹ ዐይነት ክብር በደመና ተሸክመው ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ያሳርጓችኋል፡፡ ጲላጦስ ሆይ ፈጣሪህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዕፀ ሕይወት ሥር ያኖርሃልና አይዞህ ጽና የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡
ድምፁም ይኽን ተናግሮ ከእነርሱ ዘንድ ተሠወረ፡፡ ጲላጦስም ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አንገቱን ይቈርጡት ዘንድም እጅግ ተደሰተ፡፡ በመጨረሻም በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል።
ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው። ጌታችንን ተከትላ ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፏለች።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ሰኔ 25 እና ላሐ ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አልረሳውም ያንን ዕለት
አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/
ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
አዝ
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
መቅረዜ ሲጨልም ስዋጥ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝም ብዬ አለቅሳለሁ
ግን እኔ አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
አዝ
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዊዋ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው ኧረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
አዝ
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ
ዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👉 ጳጉሜ ለምን እንጠመቃለን?
🎤 ቀሲስ ሄኖክ ወልደ ማርያም
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ጾመ ዮዲት
በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፡፡ የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣ ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በዓዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡
በዚያም ነዋሪዎችን በማስፈራራት የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበሉትን ሁሉ እያሳደደ ስላስጨነቃቸው ማቅ ለብሰው፣ አመድ ነስንሰውና ድንጋይ ተንተርሰው ወደ ፈጣሪያቸው በመጮህ መለመን ጀመሩ። በጭካኔ የተሞላው የጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስም ይበልጥ እጅግ እንዲሰቃዩ ውኃ የሚቀዱበትን ስፍራ ተቆጣጠረው፤ በግዴታ ማርኮም እጅ እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው በመጽሐፈ ዮዲት ፪፥፪ ላይ ተጽፏል፡፡
በአካባቢው ይኖር የነበረ ዖዝያን የተባለ አንድ ሰው የአባቶቻቸው አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸው ለአምስት ቀናት በትዕግሥት ይጾሙና ይጸልዩ ዘንድ ሕዝቡን መከራቸው፤ እነርሱም በትዕግሥት ሊጠብቁ ተስማሙ፡፡
የእስራኤል ልጆች የናቡከደነጾርን ጦር ብንችል ተዋግተን እንረታለን፤ ካልሆነም እጅ እንሰጣለን በማለት ይመካከሩ ጀመር።
በዚያን ጊዜ ባሏ የሞተባትና በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ዮዲት የተባለች ሴት ነበረች። (ዮዲት ፯፥፲)
እግዚአብሔርን የምትፈራ ብቸኛዋ ሴት እርሷ ነበረችና ምክክራቸውን ስትሰማ
ለምን እግዚአብሔር ያድነናል አትሉም ብላ ገሠጸቻቸው፡፡
«ይህችስ ለአለቃችን ትገባለች» ተባብለው ከጦር መሪያቸው ዘንድ ወሰዷት።
«ክቡር ጌታዬ ሆይ ርስት ተወስዶብኛል፤ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ ልጠና መጥቻለውና ርዳኝ፤ ትብብርህ አይለየኝ» አለችው፡፡
ከተጋረጠብን ችግር እግዚአብሔር ያድነናል
✞ ምን አለ ያጎደልክብኝ
ምን አለ ያጎደልክብኝ
ሳትነፍገኝ ሁሉን ሰጠኸኝ
ሁነኸኝ እናት እና አባት
አለፈ ብዙ ዘመናት (2)
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ
ኑ በብርሐኑ ተመላለሱ ተመላለሱ
ኑ በብርሐኑ በብርሐኑ ተመላለሱ
የፍቅርን ሕይወት እንድትለብሱ
ኑ በብርሐኑ ተመላለሱ/፪/
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
የማይጠፋው
የማይጠፋው የዘላለም ህይወት
የመይፈርሰው የፀና መሠረት
የእግዚአብሔር ቃልን በወለደችልን /2/
በድንግል ማርያም ተገኘልን /2/
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ቅዱስ አፈር
ቅዱስ አፈር ከሕመት (እምነት) ጋር ተመሳሳይ ሲሆን በቤተክርስቲያን ፣ በጠበል ቦታና በገዳማት ለቅዱሳን በተሰጣቸው ቃል ኪዳን መሰረት ምዕመናን የምንድንበት በረከት የምናገኝበት መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ቅዱስ አፈር ነው።
ይህንንም የሚያደርጉት የቦታውን ቅድስና በመረዳት ነው። በዚህም የተቀደሰ አፈር ብዙ ድንቅ ተአምራት በአምላካችን በአግዚአብሔርና በባለሟሎቹ በቅዱሳን ተደርጓል። ይደረጋልም። አንዳንድ ጊዜ የዚህ ምሥጢር ያልገባቸው ሰዎች ይህን ሲመከቱ እንደ ሞኝነት ሊያዩት ይችሉ ይሆናል። ዳሩ ግን ምሥጢሩ ረቂቅ ነው። ከእምነትም የሚመነጭ ነው። መሠረቱም ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
ከለምጽ ንዳድ በዮርዳኖስ ጠበል የተፈወሰው የሶሪያው የጦር ጀግና ንዕማን ከዳነ በኋላ ከእግዚብሔር ውጪ ሌላ አምላክ፣ አዳኝ እንደሌለ ተረድቷል፡ አምኗልም። እንዲህም ብሎ መስክሯል
እነሆ ከእስራኤል ዘንድ በምድር ሁሉ አምላክ እንደ ሌለ አወቅሁ።
ስለዚህም ኤልሳዕ የረገጠውን አፈር ለምኖ በበቅሎ ጭኖ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ ፪ነገ ፭፥፲፭-፲፱ (5፥15-19)
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሀይ ጠልቃ ነበር ከዛ እንደደረሰ
ከእራሱ በታች ድንጋይ ተንተራሰ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
🎬 🛑 ጻድቃን ላይ ለሚዘባበቱ መናፍቃን እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጥልን! የጻድቁ ተክለሃይማኖት አጭር ታሪክ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/6geWAZ_doak
https://youtu.be/6geWAZ_doak