#የልደት_ወረብ
#አንፈርዓፁ
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል /2/
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ /2/
"ቅኝት ዜማ"
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 🛑 ጻድቃን ላይ ለሚዘባበቱ መናፍቃን እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጥልን! የጻድቁ ተክለሃይማኖት አጭር ታሪክ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/6geWAZ_doak
https://youtu.be/6geWAZ_doak
ተክለሃይማኖት ባህታዊ
ተክለሃይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
በአደባባዩ ተተክለሀል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሀል
አዝ
ቃልኪዳን አለህ የገነነ
ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውኃ አጠጥተን
ዋጋችን በዝቷል አባታችን
አዝ
እኛም ሆነናል ልጆችህ
ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ
በምልጃህ ጸሎት ትሩፋት
ቤታችን መላ በረከት
አዝ
ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሀል
አዝ
ተሰባበሩ ጣኦታቱ
አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ከአፍህ ወጥቶ
የአምላክ አድርጓል ሁሉን ገዝቶ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አረሳት ኢትዮጵያን
አረሳት ኢትዮጲያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በ ሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ
ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠ ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ
አዝ
ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
አዝ
ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት
አዝ
ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ታኅሣሥ 23
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሃያ ሦስት በዚህች ዕለት ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ዐረፈ።
ታኅሣሥ ሃያ ሦስት በዚህች ዕለት ልበ አምላክ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ዐረፈ፡፡ ይህም ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት መልካም ጒዞን የተጓዘ ከእራኤልም ነገሥታት ሁሉ እውነተኛ ፍርድን ያደረገ ነው እርሱም አገሩ ቤተልሔም የሆነች ከይሁዳ ነገድ ነው ሳኦልም የእግዚአብሔር ትእዛዝ በተላለፈ ጊዜ ለእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ መረጠው ነቢይ ሳሙኤልንም ቅብዐ መንግሥትን የእሴይን ልጅ ይቀባ ዘንድ ላከው።
ሳሙኤልም ታላቁን ኤልያብን ተመለከተ መልኩ ያማረ አካሉም የጸና ነበርና እግዚአብሔር ግን አልመረጠውም። "የኤልያብ ፊቱን አትይ የመልኩንም ማማር አትመልከት እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ የሚያይ አይደለምና" አለው እንጂ "ሰው መልክ ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን" ያያል።
ከእሴይ ከሰባቱ ልጆች በኋላ ነቢይ ሳሙኤል ዳዊትን በእስራኤል ልጆች ላይ ይነግሥ ዘንድ ቀባው እግዚአብሔርም በሥራው ሁሉ ከእርሱ ጋር ሆነ። ከልቡናው ንጽሕና ከየዋህነቱም ብዛት የተነሣ ጠላቱን ሳኦልን ብዙ ጊዜ ሲያገኘው በላዩ ምንም ምን ክፉ ነገር አላደረገበትም። በአንዲትም ዕለት ሳኦል ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትን ከሰዎቹ ጋር ይፈልገው ዘንድ ዋሊያዎች ወደሚታደኑበት ሔዶ በጐዳና አጠገብ ያሉ ዘላኖችም ወደሚሠማሩበት ደረሰ በዚያም ዋሻ ነበር ሳኦልም ይናፈስ ዘንድ ወደዚያች ዋሻ ውስጥ ተቀምጠው ነበር። ዳዊትም ተነሥቶ ቀስ ብሎ ከልብሱ ጫፍ ቆረጠ። በሁለተኛም ጊዜ በድንክ አልጋ ላይ ተኝቶ ወዳለበት ከአቢሳ ጋር ገብቶ ከራስጌው ጦሩንና ውኃ ያለበትን ረዋቱን ይዞ ተመልሶ ሔደ ክፉ ነገርንም አላደረገበትም ሰዎቹም ጠላትህ ሳኦልን ግደለው በአሉት ጊዜ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን ልዘረጋ አይገባኝም ብሎ መለሰላቸው።
ስለ ሳኦልም መገደል አንድ ሰው በነገረው ጊዜ ዳዊትም "ያንን ሰው ማን ገደለው" አለው ሰውዬውም "እኔ ገደልሁት" አለው ዳዊትም እጅግ አዘነ ልብሱንም ቀደደ ያንንም ሳኦልን እኔ ገደልሁት ያለውን ሰው ገደለው። እግዚአብሔር በዚህ በጻድቅ ዳዊት ልብ ብዙ ትሩፋትን፣ ትሕትናን፣ የዋህነትን፣ ቅንነትን፣ ትዕግሥትን ፍቅርን አከማቸ ክብር ያለው ንጉሥ ሲሆን ራሱን ውሻ ትል እንስሳም አድርጎ ይጠራል ስለዚህም ከምድር ነገሥታት ሁሉ ከፍ ከፍ አደረገው እንዲህም ብሎ አመሰገነው "የእሴይን ልጅ ዳዊትን እንደ ልቤ ሆኖ አገኘሁት ፈቃዴን ሁሉ የሚያደርግ ታማኝ ሰው ነው"።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች ኢየሩሳሌምንም ስለ ዳዊት ደግነት ብዙ ጊዜ ጠበቃቸው እርሱ ካለፈ በኋላም በነቢያቶቹ አንደበት አከበረው ነገሥታትንም ከእርሱ ዘር አደረገ። እርሱም በሁሉ ዓለም የታወቀ የመዝሙሩን መጽሐፍ ደረሰ ይኸውም በሰይጣናት ላይ ጋሻና ጦር የሆነ መልካም ቃልንም የተመላ በሰማይና በምድርም ያሉ በእርሱ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ነው።
ቅዱስ ዳዊትም ፊቱ እንደ ሮማን ቀይ ነው ቁመቱም መካከለኛ የሆነ አካሉም የጸና ብርቱ ነበር ታናሽ ብላቴናም ሁኖ ሳለ እርሱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አንበሳ ወይም ተኵላ መጥቶ ከመንጋው ውስጥ በግ ነጥቆ በሚወስድ ጊዜ ተከትሎ ገድሎ ከአፉ ያስጥለው ነበር ሊጣላውም ቢነሣበት ጒረሮውን ይዞ ይሠነጥቅዋል። ከፍልስጥዔማውያንም ጋራ ሰልፍ በሆነ ጊዜ ብርቱ ሰው ስሙ ጎልያድ የሚባል ከጌት ሰዎች የተወለደ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ ከኢሎፍላውያን ሰፈር ወጣ። በራሱ ላይ የነሐስ በርቦርቴ ደፍቷል የነሐስ ጽሩርም ለብሷል በርሱ ላይ ያለ የብረቱና የነሐሱ ሁሉ ሚዛኑ አምስት ሽህ ወቄት ነበር።
በእግሮቹ ባቶችም ላይ የነሐስ ሰናፊል ታጥቆ ነበር በጫንቃውም መካከል የነሐስ እባቦች ነበሩ። የጦሩም ዛቢያ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ሁኖ በላዩ ሽቦ ነበረበት የጦሩም ብረት መጠን ስድስት መቶ ወቄት ነበር ጋሻ ጃግሬውም በፊቱ ይሔድ ነበር።
ቁሞም ወደ እስራኤል ሰፈር ይጮህ ነበር "ከእኛ ጋር ትዋጉ ለምን ወጣችሁ እኔ የኤሎፍላውያን ወገን ነኝ ከእናንተ የሳኦል ባሮች አይደላችሁምን ከእናንተ አንድ ሰው መርጣችሁ ወእኔ ይውረድ ከእኔ ጋር መዋጋት ችሎ ቢገድለኝ ባሮች እንሆናችኋለን እኔ ከርሱ ጋራ ችዬ ብገድለው እናንተ ባሮች ሁናችሁ ትገዙልናላችሁ" አላቸው። ያም ኢሎፍላዊ ለወገኖቹ "ዛሬ በዚች ቀን አንድ ሰው ስጡኝና ሁለታችን ለብቻችን እንደዋጋ ብሎ የእስራኤልን አርበኞች እነሆ ተገዳደርኳቸው" አላቸው። እስራኤል ሁሉና ሳኦልም ይህን የኢሎፍላዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ እጅግም ፈሩ የእራኤልንም ወገኖች እንዲህ እየተገዳደራቸውና እየተመካባቸው አርባ ቀኖች ያህል ኖረ ከእስራኤልም ወገን ወደርሱ ይወጣ ዘንድ የደፈረ የለም።
በዚያም ወራት ቅዱስ ዳዊት ወንድሞቹን ሊጐበኝ ወጣ ያንንም የኢሎፍሊ ወገን የሆነ ሰው የእግዚአብሔር ወገኖችን ሲገዳደራቸው በአየው ጊዜ አምላካዊ ቅናትን ቀና ሳኦልንም እንዲህ አለው "እኔ ሔጄ ይህን ያልተገረዘ ቈላፍ ገድዬ ዛሬ ከእስራኤል ሽሙጥን አርቃለሁ። ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔርን አርበኞች ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ቁም ነገር ነው ከድብ አፍና ከአንበሳ አፍ ያዳነኝ እርሱ እግዚአብሔር ከዚህ ካልተገረዘ ኢሎፍላዊ እጅ ያድነኛል"።
ሳኦል "ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ዳዊትም ወንጭፋን በእጁ ያዘ ከወንዝ መካከልም ሦስት ደንጊያዎችን መረጠና ወደዚያ ኢሎፍላዊ ሔደ። ጎልያድም ዳዊትን በአየው ጊዜ ናቀው እንዲህም አለው "ደንጊያና በትር ይዘህ ወደኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ውሻ ነኝን" ዳዊትም "ከውሻ የምትሻል አይደለህም ከውሻ ትብሳለህ እንጂ" ቈላፍ ጎልያድም ዳዊትን በጣዖቶቹ ስም ረገመው።
ያም ኢሎፍላዊ ዳዊትን "ወደ እኔ ና ሥጋህን ለሰማይ ወፎችና ለዱር አራዊት እሰጣሁ" አለው ዳዊትም ያንኑ ኢሎፍላዊ "አንተ ጦር ሰይፍና ጋሻ ይዘህ ወደኔ ትመጣለህ እኔ ግን አሸናፊ በሚሆን በእግዚአብሔር ስም ወዳንተ እመጣለሁ። ዛሬ የእስራኤልን አርበኞች የተገዳደርክ አንተን ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ይጥልሃል እገድልህምአለሁ ራስህንም እቆርጣለሁ የኢሎፍላውያን ሠራዊት ሬሳና ያንተን ሬሳ ዛሬ ለዱር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጣለሁ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ ሠራዊትም ሁሉ እግዚአብሔር በጦርና በሰይፍ የሚያድን እንዳይደለ ያውቃሉ ድል የእግዚአብሔር ገንዘብ ነውና"።
ቅዱስ ዳዊትም እጁን ወደ ድጉ ሰዶ አንዲት ደንጊያ አውጥቶ ወነጨፋት ያንንም ኢሎፍላዊ ግንባሩን ገመሰው ያቺም ደንጊያ ከግንባሩ ገብታ ናላውን በጠበጠችው በምድር ላይም በግንባሩ ተደፋ። ዳዊትም ሩጦ የገዛ ሰይፉን አንሥቶ ራሱን ቆረጠው ከእስራኤልም ልጀጆች ስድብን አራቀ። ቅዱስ ዳዊትም መላው ዕድሜው ሰባ ነው መንግሥትን ሳይዝ ሠላሳ ዓመት ኖረ ከያዘ በኋላ አርባ ዓመት ኖረ። የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመምጣቱ በፊት በሽህ አንድ መቶ ሃያ ዓመት ውስጥ ትንቢት የተናገረበት ዘመን ነው በሰላምም ዐረፈ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
✞ ይኩነኒ
ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ(፪)
አለች የእኛ እናት በትሕትና
በሥጋም በነፍስም ንጽሕት ናትና
አለች የእኛ እናት በትሕትና
ድንግል በክልኤ ንጽሕት ናትና
የአዳም ቃልኪዳን መፈጸሚያው ሲደርስ
ላከው ገብርኤልን ወደ ቤተ መቅደስ
በእግዚአብሔር ኅሊና ተስላ የነበረች
ከሠማይ የመጣ ቃሉን ተቀበለች
ዳግሚት ሠማይ አርያም ሆነች
ይደረግ ብላ በትሕትና ተቀበለች
አዝ
ማርያም ሆይ አትፍሪ ብሎ እያረጋጋት
ከአንቺ የሚወለደው መድኃኒት ነው አላት
ወንድ ሥለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል
ብላ ጠየቀችው ድንግልም ደንቋታል
ከሴቶች መሐል አንቺ ልዩ ነሽ
በሕግ ሣይሆን በድንግልና ትወልጃለሽ
አዝ
ሕይወት ሊቀዳባት አድሯል በማሕጸንዋ
አይኖርም ከእንግዲህ የሔዋን መርገሟ
በአዲሱ ኪዳን አዲስ ብስራታችን
ምክንያተ ድኅነት አለች እናታችን
ቃልሕ ይፈፀም ይደረግ ብላ
ተአምር ተሰማ ኢየሩሳሌም ናዝሬት ገሊላ
አዝ
እጅግ አስገረመን የገብርኤል ዜና
የእነ ዘካርያስ ከቶ አይደለምና
የተመረጠችው የደረሰው ብሥራት
ዓለምን ከመሞት ከመርገሟ ዋጃት
ከሴቶች መሐል አንቺ ልዩ ነሽ
በሕግ ሳይሆን በድንግልና ትጸንሻለሽ
ሉቃ፩፥፴፰
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
🎬 🛑 "ምስጢረ ሥላሴ በቡሉይ እና በሐዲስ ኪዳን" - አምስቱ አዕማደ ምስጢራት
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/rufT7ZRkgZ4
https://youtu.be/rufT7ZRkgZ4
አምላከ ተክለሃይማኖት ማረን
አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን 2×
አምላከ ቅዱሳን ታረቀን 2×
ስለቃልኪዳንህ በቁጣ አታጥፋን
አዝ
ሐዋርያው ቅዱስ ተክለሃይማኖት
የኢቲሳ አንበሳ የኔ አባት
ቁጣውን አብርደው ተክለሐይማኖት
ለምልጃ ተነሳ የኔ አባት
ከሰማይ ካህናት ተክለሐይማኖት
ቤተሰብ ሆነሃል የኔ አባት
የሥላሴን መንበር ተክለሐይማኖት
ለማጠን በቅተሀል የኔ አባት
አዝ
ከከርቤ ከሚያ ተክለሃይማኖት
ከሰሊክም በልጧል የኔ አባት
የፃድቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በእግዚአብሔር ፊት ሸቷል የኔ አባት
ስለቃልኪዳንህ ተክለሐይማኖት
አምላክ ይለመናል የኔ አባት
ፀሎትህ ሲደርስ ተክለሐይማኖት
እኛን ይታረቃል የኔ አባት
አዝ
ተማፅነንብሃል ተክለሃይማኖት
ጌታ ሆይ በስሙ የኔ አባት
በፃዲቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በሰባረ አፅሙ የኔ አባት
ኢትዮጲያን በሙሉ ተክለሐይማኖት
አስተምሮ ሲመለስ የኔ አባት
አፅመ ርስቱ ሆነች ተክለሐይማኖት
ደብረ ሊባኖስ የኔ አባት
አዝ
የፃዲቁ መንፈስ ተክለሃይማኖት
ከቅዱሳን ጋራ የኔ አባት
ከልባችን ገብተህ ተክለሐይማኖት
ብርሃንን አብራ የኔ አባት
በፀሎት ስቆም ተክለሐይማኖት
ስምህን ስጠራ የኔ አባት
ነፍሴ ተደሰተች ተክለሐይማኖት
ሲርቀኝ መከራ የኔ አባት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 🛑 "ምስጢረ ሥላሴ" - አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ክፍል አንድ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/cOQzGHpG-O4
https://youtu.be/cOQzGHpG-O4
#ሃያል_ነህ_አንተ
ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት
#አዝ
በዱራ ሜዳ ላይ - ገብርኤል
ጣኦት ተዘጋጅቶ - ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ - ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ - ገብርኤል
ሲድራቅ እና ሚሳቅ አብደናጎ ፀኑ፤
ጣኦቱን እረግጠው በእግዚያብሄር አመኑ
#አዝ
ተቆጣ ንጉሱ - ገብርኤል
በሶስቱ ህፃናት - ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ - ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት - ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ወረደ መላኩ፤
ከሞት አዳናቸው በሳት ሳይነኩ።
#አዝ
ከእቶኑ ስር ሆነው - ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ - ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው - ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ - ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር፤
አዩ መኩአንንቱ የእግዚአብሄርን ክብር።
#አዝ
ናቡከደነፆር - ገብርኤል
እጁን ባፉ ጫነ - ገብርኤል
ሰለስቱ ደቂቅን - ገብርኤል
ከእሳት ስለአዳነ - ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከ መላኩን፤
ሊአመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ይነበብ🛑
ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች የዝማሬ ዳዊትን የዩቲዩብ ገጽ subscribe አድርጉ አገልግሎቱን አግዙ እያልን ብዙ ግዜ ብንናገርም በፍቅር ጥያቄያችንን ተግባራዊ ያደረጉ ጥቂት ብቻ ናቸው። ለምን ጥቂቶች ብቻ?
ምንም የማይጠቅመን ቦታ ስንርመሰመስ አይደል የምንውለው? መንፈሳዊ ተግባራትን ለመፈጸም እጃችን እሚታሰረው ስለምንድን ነው? መንፈሳዊ አገልግሎትን ልትደግፉ የምትችሉበት አንዱ እና ዋነኛው መንገድ ይህ እንደሆነ ጠፍቷችሁ ነው?
አሁንም ደግመን እንጠይቃለን እግዚአብሔር በፈቀደልን መልኩ መልካም አገልግሎት ወደናንተ ለማድረስ እየሰራን ነው። ከዚህ በብዙ መስራት እንድንችል ግን የእናንተም ድጋፍ ያስፈልገናል። ምን እናግዝ ካላችሁን ሁላችሁም ይህን ጽሁፍ የምታነብ በጠቅላላ ከስር ባስቀመጥነው አድራሻ በመግባት ዝማሬ ዳዊትን Subscribe እንድታደርጉ በቅዱስ ገብርኤል ስም እንጠይቃለን።
በተጨማሪም ይህን መልዕክት ለሁሉም ባለ ማዕተብ አድርሱልን። ለምትሰጡን መልካም ምላሽ እግዚአብሔር ያክብርልን።
✝ https://bit.ly/2O1Z3d8
✝ https://bit.ly/2O1Z3d8
ወይም
👉 https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
ታህሳስ 19 ቀን በዚህ ቀን ሰለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው።
ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ነገሩ እንዲህ ነው። ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር ሰዎች የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሥም አይጣላልናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ነበሩ። ት/ዳንኤል 3፡1-30 ታሪኩ እንደሚግረን ንጉስ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሣት ውስጥ ብሎ አወጀ።
በዚህ መካከል ሰልስቱ ደቂቅ ነበሩ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር። የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻል?" ባላቸው ጊዜ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳን አንተ ለመታመልከው ጣኦት አንሰግድም አሉት።
በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሣት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሣቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠልስቱ ደቂቅን ግን መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው።
በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል እንዲያውም የአማልክትን ልጆች ይመስላል " አለ። የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ተብሎ የነበረው "ጉልበት ሁሉ ለሰልስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" ተባለ ይህን ሁሉ ታህሳስ 19 ቀን ሆነ በዚህም ምክንያት በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን!
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የመላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየን አሜን!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
📺 ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
መንፈሳዊ ፊልም
#ክፍል_ሁለት
💰package ከገዙ ወደ 14.90 ብር
💵 package ከሌለዎት ወደ 24.84 ብር ይፈጃል
📍WiFi ብትጠቀሙ ይመረጣል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 🛑 እስቲ ይችን እንኳን ከጉንዳን እንማር! - የሰው ልጅ ካስተዋለ የእያንዳንዱ ፍጥረት ሕይወት አስተማሪ ነው
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/Sp7KN-bKMc8
https://youtu.be/Sp7KN-bKMc8
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝
ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች?
እስከ አሁን ድረስ ምሥጢረ ሥላሴ እና ምሥጢረ ሥጋዌን ያየን ሲሆን በእነዚህ ርዕሶች ላይ ጥያቄዎች ካላችሁ አሁን መጠየቅ ትችላላችሁ። ሰብስበን መልስ እንሰጣለን።
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/
አዝ
በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና
ተክለሃይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ
ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#ልደት
መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።
#ዕድገት
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።
#መጠራት
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።
#አገልግሎት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት።
1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።
2ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::
#ገዳማዊ ሕይወት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።
እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል።
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል።
#ስድስት_ክንፍ
ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው።
#በዚያም :-
-የብርሃን ዐይን ተቀብለው
-6 ክንፍ አብቅለው
-የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
-ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
-ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
-ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።
#ተአምራት
የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
ሙት አንስተዋል
ድውያንን ፈውሰዋል
አጋንንትን አሳደዋል
እሳትን ጨብጠዋል
በክንፍ በረዋል
ደመናን ዙፋን አድርገዋል።
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::
#ዕረፍት
ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል።
ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አባ አባ ተክለሃይማኖት
አባ አባ ተክለሃይማኖት አቡዬ /2/
በለኒ በለኒ ወልድየ /2/
አዝ
አባ አባ - - - እንኳን ሰው ምድሪቱን
አባ አባ - - - ጦም አያሳድርም
አባ አባ - - - አምላከ ተክልዬ
አባ አባ - - - ብዬ አፍሬ አላውቅም
አባ አባ - - - ምድራዊ መልዓክ ነህ
አባ አባ - - - የእቲሳ አምበሳ
አባ አባ - - - ለደብረ ሊባኖስ
አባ አባ - - - አንተ ነህ ሞገሷ
አዝ
አባ አባ - - - ስማኒ ብያለው
አባ አባ - - - ሳለ በሰማይ
አባ አባ - - - ከኪሩቤል ተርታ
አባ አባ - - - ሆነህ ስትታይ
አባ አባ - - - ስምህም ሲጠራ
አባ አባ - - - ገድልህ ሲነገር
አባ አባ - - - እፁብ ድንቅ ያሰኛል
አባ አባ - - - የተሰጠህ ክብር
አዝ
አባ አባ - - - አባቴ እልሃለው
አባ አባ - - - ልጄ ሆይ በለኝ
አባ አባ - - - የአባትና የልጅ
አባ አባ - - - ፍቅርህ ይጽናልኝ
አባ አባ - - - ንፍሮ ውሃ ጠጥቼ
አባ አባ - - - ታምር አይቻለሁ
አባ አባ - - - እባብና ጊንጡን
አባ አባ - - - ተረማምጃለሁ
አዝ
አባ አባ - - - እለት በለት ሄጄ
አባ አባ - - - ደጅ ስጠናው
አባ አባ - - - ይሰማል ተክልዬ
አባ አባ - - - ዛሬም ህያው ነው
አባ አባ - - - እንቆቅልሽ ፈቶ
አባ አባ - - - ደስ አሰኝቶኛል
አባ አባ - - - የተክለሃይማኖት
አባ አባ - - - ቡራኬው ደርሶኛል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
✞ ጥሩልኝ ዳዊትን
ጥሩልኝ ዳዊትን በገናውን ያምጣ
መንፈስ አስጨንቆት ሳኦል ስለመጣ (፪)
ምድር ግብሯን ትታ ሕግ እያፈረሰች
የሳኦልን መንገድ ስለ ተከተለች
ከህልም አለም ቅዠት እንድትረጋጋ
ያን ዳዊትን ጥሩት ይደርድር በገና
አዝ
የእርኩሰትን ሥራ ዓለም ስላበዛች
ያልተፈቀደውን ምርኮን ስለያዘች
በዝማሬው ጸጋ ፈውስን እንድታገኝ
ጥሩልኝ ዳዊትን በበገና ይቃኝ
አዝ
የአባቶቹን ትዕዛዝ መንገድ ስለሳተ
ጸያፍ የሆነውን ሕጉን ስለሻተ
ለንስሐ ደርሶ መንግስት እንዲቀና
ጥሩልኝ ያን ዳዊት ይደርድር በገና
አዝ
መለያየት በዝቶ ፍቅር ስለራቃት
ስላቀረቀረች መንገድ ስለጠፋት
በጥልቁ ዝማሬ ምሕረትን እንድታይ
ዳዊት ይነሳና በበገና እንጸልይ
ዳዊት ይነሳና በበገና ትቃኝ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ቅዱስ ገብርኤል
በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ዳህና በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራችበት ተአምራትም ያሳየበትና በዚች ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ የከበረችበት ነው የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ አርኬላዎስ ምስክር የሆነበት ነው።
ይህም መልአክ ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር የታመነ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተላከ "የደስታ መገኛ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ" አላት።
ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድም ካህኑን ዘካርያስን ያበሠረው እርሱ ነው ይህ መልአክ እጅግ የከበረ የተመረጠ ገናና የሆነ ነውና ስለ እኛ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ዘንድ ልባችንን አንጽተን ወደዚህ የከበረ መልአክ እየለመንን መታሰቢያውን ልናደርግ ይገባል።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ታኅሣሥ 22
ብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል
ታኅሣሥ ሃያ ሁለት በዚህች ዕለት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ያበሰረበት መታሰቢያ ነው፡፡ ይኸውም ‹‹ልዑል እግዚአብሔር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ‹ሂድና ለጽዮን ልጅ ለድንግል የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ወደአንቺ መጥቶ ኃይለ ልዑል ወልድ ሥጋሽን ለብሶ ሰው ይሆናል፤ ይኸውም ካንቺ የሚወለደው ጽኑዕ ነው ብለህ ንገራት› አለው፡፡ ‹ደንቆሮዎች የሚሰሙበት፣ ድዳዎቸ የሚናገሩበት፣ ዕውራንም የሚያዩበት፣ ሙታን የሚነሡበት፣ ለምጻሞች የሚነጹበት፣ ሐንካሳዎች የሚሄዱበት፣ በጨለማ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ብርሃን የሚያዩበት ጊዜ እነሆ ደረሰ ብለህ ንገራት› አለው፡፡
ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ በግንባሩ ተደፍቶ ልዑል እግዚአብሔርን ‹ጌታ ሆይ! የምትነግረኝ ይደረግ ዘንድ እንደምን ይሆናል?› አለው፡፡ ጌታም ‹የጀመርኩትን ቸርነት ፈጸምኩ፣ የወይን ግንድ ይቆረጣል (ወልደ እግዚአብሔር ይሞታል)፣ ወይራም ከበለስ ጋር ይተከላል (መስቀል ይተከላል)፣ ቅጽሮችም ይቀጸራሉ (ምግባር ከሃይማኖት ጋር ይሠራል)፣ የኤልፍና የሌሚ ወገን ይነሣል፡፡ ገብርኤል ሆይ! ሄደህ ለዳዊት ልጅ ‹እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ› ብለህ አብሥራት› አለው፡፡ ‹ለዘለዓለም ነግሦ የሚኖረውን እነሆ ትፀንሳለሽ በላት› አለው፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ሰገደ፡፡ ልብሱንም በላዩ ይዞ በመስቀል ቀኝ ይወርድ ዘንድ ወደደ፡፡ ጌታም ‹መግባትህና መውጣትህ በፍቅር አንድነት ይሁን› አለው፡፡ ‹ዘካርያስን ረግመህ አንደበቱን እንዳሰርህ እርሷን እንዳታሳዝናት ይልቁንም አብዝተህ ደስ አሰኛት አንጂ› አለው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ፈጽሞ ደስ እያለው ሊባኖስ ከሚባል ተራራ እስኪሰማ ድረስ ክንፉን እያማታ ወረደ፡፡
በዚህም ጊዜ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ‹ይህ የምንሰማው ምንድነው?› ይሉ ነበር፡፡ የተደረገበትንም ቦታ አላወቁትም ነበር፡፡››
እመቤታችንን በ3 ዓመቷ እናትና አባቷ ብፅዓት አድርገው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋታልና ካህናትም በቤተ መቅደስ ከመካነ ደናግል አስገብተዋት በመልአኩ በቅዱስ ፋኑኤል አማካኝነት ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመጣላት ያንን እየተመገበች ቅዱሳን መላእክት እየጎበኟት 12 ዓመት ኖራለች፡፡ በ15 ዓመቷ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታችንን እንደምትወልድ በዚህች ዕለት አብሥሯታል፡፡ በመጀመሪያ እመቤታችን ውኃ ቀድታ ስትመለስ የጠተማ ውሻ እያለከለከ ሲመጣ ብታየው ለፍጥረት ሁሉ የምትራራ ናትና በወርቅ ጫማዋ ለዛ ለተጠማው ውሻ ውኃ ስታጠጣ አብሯት የነበሩ ሴቶች ‹‹ማድጋሽን አጎደልሺው፣ ቀድቼ እሞለዋለሁ እንዳትይ ጉድጓዱ ጥልቅ ነው መቅጃም የለሽም›› አሏት፡፡
ክብርት እመቤታችንም ‹‹ውሃ የሚገኘው ከወደላይ ነው እንጂ ከወደታች ነውን? ፍጥረቱን ያጠጣ ጌታ ይሞላልኛል›› አለቻቸው፡፡ ማድጋዋም በተአምራት ሞልቶ ተገኘ፡፡ ሴቶቹም ዳግመኛ ‹‹በዚህ ዘመን አምላክ ከድንግል ይወለዳል ይላሉ ካንቺ ይሆን?›› እያሉ ሲዘብቱባት ወዲያው ከወደኋላዋ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ዞር ብትል የተናገራትን አጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ ‹‹አባቴን አዳምን እናቴን ሔዋንን ያሳተ ጠላት ይሆናል›› ብላ ሄደች፡፡
ዳግመኛም እመቤታችን ከቤት ደርሳ ማድጋዋን ስታስቀምጥ መልአኩ አሁንም በድምፅ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹ምነው ይህስ ነገር ደጋገመኝ እንዲህ ያለውን ነገር ቤተ መቅደስ ሄደው ሊረዱት ይገባል›› ብላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዳ ወርቅና ሐር እያስማማች ስትፈት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እሁድ ቀን በ3 ሰዓት በገሃድ ተገለጸላትና እጅ እየነሳ እየሰገደ አበሠራት፡፡
‹‹የዕውነተኛ ንጉሥ እናቱ እመቤታችን ላንቺ ፍቅር አንድነት ይባል›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹አንቺ ከሴቶች ይልቅ ተለይተሸ ንዕድ ክብርት ነሽ›› አላት፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናቸ ክብርት እመቤታችንም የብርሃናዊውን መአልክ የቅዱስ ገብርኤልን ቃል በሰማች ጊዜ ‹‹እንዲህ ያለውን ሰላምታ እንደምን ይቀበሏል! እንዴትስ መቀበል ይቻላል? እንጃ›› አለችው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ‹‹ማርያም ሆይ! መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፣ ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳልና አይዞሽ አትፍሪ›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ይህ ካንቺ የሚወለደው ጽኑ ከሃሊ ነው፡፡ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ፣ እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፣ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፣ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፣ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም›› አላት፡፡
እመቤታችንም መልአኩን ‹‹ምድር ያለ ዘር ፍሬን አትሰጥምና እኔ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?›› አለችው፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ እርሷ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፡፡ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፣ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› አለችው፡፡ መልአኩም ከእርሷ ዘንድ ሄዶ ተሠወረ፡፡ አካላዊ ቃልም በማኅፀኗ አደረ፡፡ በዚያችም ቅጽበት የእመቤታችን የፊቷ መልክ ተለወጠ፣ እንደፀሐይም አሸበረቀ፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ ረድኤትና በረከቷ አይለየን አሜን!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝሙረ ዳዊት Psalms 1
1፤ምስጉን፡ነው፡በክፉዎች፡ምክር፡ያልኼደ፥በኀጢአተኛዎችም፡መንገድ፡ያልቆመ፥በዋዘኛዎችም፡ወንበር፡
ያልተቀመጠ።
2፤ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ሕግ፡ደስ፡ይለዋል፥ሕጉንም፡በቀንና፡በሌሊት፡ያስባል።
3፤ርሱም፡በውሃ፡ፈሳሾች፡ዳር፡እንደ፡ተተከለች፥ፍሬዋን፡በየጊዜዋ፡እንደምትሰጥ፥ቅጠሏም፡እንደማይረግፍ፡
ዛፍ፡ይኾናል፤የሚሠራውም፡ዅሉ፡ይከናወንለታል።
4፤ክፉዎች፡እንዲህ፡አይደሉም፥ነገር፡ግን፥ነፋስ፡ጠርጎ፡እንደሚወስደው፡ትቢያ፡ናቸው።
5፤ስለዚህ፥ክፉዎች
፡በፍርድ፥ኀጢአተኛዎችም፡በጻድቃን፡ማኅበር፡አይቆሙም።
6፤እግዚአብሔር፡የጻድቃንን፡መንገድ፡ያውቃልና፥የክፉዎች፡መንገድ፡ግን፡ትጠፋለች።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ታህሳስ 24
በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።
ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።
በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።
ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።
ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አብሰራ ገብርኤል
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
ወይቤላ /2/ ትወልዲ ወልድ
ሚካኤል መላዕክ በክነፍ ፆራ
መንጦላዕት ደመና ሰወራ
ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ተወልደ ወልድ እምኔሐ
ገብርኤል ማርያምን አበሰራት አበሰራት
ወንድ ልጅም ትወልጃለሺ አላት
ሚካኤል መላዕክ በክንፋ ከለላት
የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ
አዳም በጥፋቱ ከገነት ሲባረር
በሚካኤል ክንፎች ቀድሞ አይቶሽ ነበር
ሔዋንን ሲጠራት ሕይወቴ ነሽ አላት
እንደሚድን አውቆ ድንግል በአንች ምክንያት
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ
እግዚአብሔር የላከው የከበረው መላዕክ
ድንግል ሆይ ለክብርሽ ዐየን ሲንበረከክ
በፍቅር በትህትና በፍፁም ሰላምታ
የጌታ ሰው መሆን የነገረሽ በደስታ
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ
ደስተኛዬቷ ሆይ ደስ ይበልሽ ድንግል
የአብ ቃል ክርስቶስ ሥጋሽን ይለብሳል
አንቺም ትይዋለሽ ስሙን ኢየሱስ
መድኋኒት ነውና ለሥጋ ወነፍስ
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ
አንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ
አንደ ዘኬርያስ ሳትጠራጠሪ
ይሁነኒ ብለሽ ቃልን ተቀበልሽ
ከፍጥረት ማነው አንቺ የሚመስልሽ
ንፅህት ናትና በድንግልና /2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ለጣዖት_አንሰግድም
ለጣዖት አንሰግድም ብለው
ሶስቱ ህፃናት እምቢ አሉ
የምናመልከው አምላክ
ከእሣት ያወጣል እያሉ
#አዝ
በንጉሱ ቁጣ ልባቸው ሳይርድ
አንዳችም ሣይፈሩ በእሣቱ መንደድ
በእምነት በርትተው መከራን ታገሱ
የታመኑት ጌታ ፈረደ ለነሱ
#አዝ
በመካከል ታየ ከእነሱ ጋር
መላኩ ገብርኤል ታዞ ከእግዚአብሔር
በእሳቱ መካከል ምስጋናን ጀመሩ
ስቡህኒ ብለው ለስሙ ዘመሩ
#አዝ
የእሳቱን ነበልባል ውሀ እያደረገ
የእግዚአብሔር መላክ ነብሳቱን ታደገ
አንዳች ሳይነኩ ከእሳቱ ወጡ
የእግዚአብሔርን ክብር ለዓለም ገለጡ
#አዝ
ተመላልሰው ታዩ በእሳቱ መሀል
ከራሳቸው ፀጉር አንዲቶአ ሳትጎል
የከለዳውያን የእሳት ምድጃቸው
ህፃናቱን ትቶ እነሱን በላቸው
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡
፤
ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡
፤
የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእጠሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡
፤
የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡
፤
የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 🛑 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት - የቤተክርስቲያንን ዶግማ ትምህርቶችን ማወቅ የአንድ ክርስቲያን ግዴታ ነው
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/_sl3kylwGq8
https://youtu.be/_sl3kylwGq8
📺 ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
መንፈሳዊ ፊልም
#ክፍል_አንድ
💰package ከገዙ ወደ 6.48 ብር
💵 package ከሌለዎት ወደ 10.80 ብር ይፈጃል
📍WiFi ብትጠቀሙ ይመረጣል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 |ክፍል 2| ✝ መጽሐፍ ቅዱስ 81 ስለመሆኑ ማስረጃ❓- Evidence that the Bible is 81?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/3pVnv5o4JMc
https://youtu.be/3pVnv5o4JMc