ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
ወዳጆቼ ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት አይደለም፡፡ ግን ኃጢአት የሚሆንበት ሂደት አለው፡፡ አንድ ሰው በሕልሙ ሕልመ ሌሊት ቢመታው በዚህም ከሰውነቱ አባለ ዘር ይፈሳል፡፡ የአባለ ዘር መፍሰስ ኃጢአት የሚሆነው በራስ ፍቃድ ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ወዶ እና ፈቅዶ ግለ ወሲብ ሲፈጽም፣ የወሲብ ፊልም በማየት ከሚመጣ የሰውነት ሙቀት ጋር ዘር ሲፈስ፣ ከተቃራኒ ጾና ጋር በሚደረግ አልባል ንክኪና መሳሳም ነው፡፡
ሕልመ ሌሊት እላፊ በልቶ እና ጠጥቶ ከሚመጣ የሥጋ ፈተና ከሆነ ኃጢአት ይሆንበታል፡፡ ቅድስናን የሚያጎድል በመሆኑ የኃጢአተኝነት ስሜት እንዲጫነን ያደርገናል፡፡ ግን አንድ ሰውን ሕልመ ሌሊት ቢመታው ኃጢአት የሚሆንበት ሂደት አለ፡፡ ይህም አንድን ሰው ሕልመ ሌሊት ሲመታው ማለትም አጋንንቱ በሚያውቃት ሴት ተመስሎ በተኛበት ተገናኝቶት ዘሩን ቢያስፈስሰው የዚህ ችግር ሰለባ የሆነው ሰው በተፈጠረው ነገር ለምሳሌ ሴቷን እያሰበ፣ በሕልሙ ያየውን እያሰበ የሚደሰት፣ በሕልሙ የተፈጠረውን ግንኙነት በምልሰት እያየ ደስታን ካጣጣመ ኃጢአት ነው፡፡
ምክንያቱም ይሁዳ በመልእክቱ ‹‹እያለሙ ሥጋቸውን ያስደስታሉ›› ብሏልና፡፡ /ይሁ 1÷8/ በሕልማችን የተፈጠረውን ሕልመ ሌሊት በምልሰት በማየት እና በማሰብ መደሰት ሳይሆን መጸጸት መቆጨት ካልተሰማን ኃጢአት ነው የሚሆንብን፡፡
ወዳጆቼ የአጋንንት የረከሰ ሐሳብ በሕልማችን እየተከሰተ ሕልመ ሌሊት ሲያጋጥመን የተፈጠረውን ክስተት በጸጸት አጋንንቱን ልናሳፍረው ይገባል እንጂ የሆነውን እንደ በጎ ነገር ልንቀበለው አይገባም፡፡ ይህ እሳቤያችን ከፈጣሪ መለኮታዊ እርዳታ እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ የማንቆጭ፣የማንጸጸት ከሆነ የዝንየት አጋንንት ይለምድና የሌሊት ደንበኛው ያደርገናል፡፡
እዚህ ላይ አንድ መረሳት የሌለበት ነገር አለ፡፡ አንዳንዴ ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በሰይጣን ፈተና ብቻ ላይከሰት ይችላል፡፡ ምናልባት ከምንጠቀማቸው ምግብና መጠጥ እንዲሁም ከሥጋ ባህርያችን ሊከሰት ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰውነታችን ሲስማማው በራሱ ጊዜ ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል፡፡
ይህ ደግሞ ተፈጥሮ ነው፤ ምንም ማድረግ አይቻልም በጸጋ መቀበል ነው፡፡ ለምሳሌ ማታ ትኩስ ነገር ሙቅ፣ ሻይ አብዝተን የምንጠጣ ከሆነ በዘር ከረጢጣችን ያለው አባለ ዘር በራሱ ጊዜ ሊፈስ ይችላል፡፡
ተወዳጆች ሆይ በተአምረ ማርያም ላይ እንደሰማችሁት በሕልመ ሌሊት የተፈተነው ወጣት መነኩሴ ሕልመ ሌሊት ሳይሆን በሥጋው ምክንያት ሞት የመጣበት ስለመሰለው ‹‹የፍትወትን ጣዕም ዛሬ ቀምሰሻልና ወዮልሽ›› በማለት አምርሮ እራሱን ጠልቶ ወደ እመቤታችን አንብቶ ቢማጸናት እመቤታችን ተገልጣ ፈተናውን አርቃለት፣ በእጆችዋም ምልክት አድርጋለት ከሕልመ ሌሊት ተላቆ በሰጠችው ሐብተ ፈውስ ብዙ ድንቆችን አድርጎ ነበር፡፡
እኛም ወለላይቱ እመ ብርሃን በሕልመ ሌሊት የሚፈትነንን አጋንንት በጸሎቷ እንድታስርልን፣ እንድታርቅልን ከተማጸናት በእውነትም ይህን ፈተና፣ይህን መናጢ ታርቅልናለች፡፡
በቀጣይ 👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ነሐሴ 9/12/2016 ዓ.ም
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን፦ ፊል 1÷12-24
ንፍቅ ደያቆን፦2 ዮሐ 1፥6-ፍ.ም
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 15÷19-ፍ.ም
#የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ 44 ÷ 10
ወትቀውም ንግስት በየማንከ።
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወሁብርት።
ስምኢ ወለትየ ወርእዩ- ወአጽምኢ እዝነኪ።
ወንጌል ፦ ዮሐ 10÷1-12
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?
ተወዳጆች ሆይ መቼም ሱባኤ አይደል! በድካም ውስጥ ሆኜ ስለጻፍኩ የሐሳብ መደጋገም ካለ እያረማችሁ አንብቡት፡፡ በዚህ በሱባኤ የአጋንንት ውጊያ የሚበረታበት፣ ሕልመ ሌሊት ደግሞ በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ነው፡፡ የበጎ ነገር ጠላት አጋንንት እኛን ከመንፈሳዊ አገልግሎት እና ተገልጎሎት ለማሰናከል እኛ ላይ ዓይኑን ፈጠጥ፣ ጥርሱን ገጠጥ የሚያደርግበት ጊዜ በአጽዋማት ወቅት ነው፡፡
ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) የሚባለው አንድ ሰው ተኝቶ በሕልሙ ወንድን በሴት፣ ሴትን በወንድ አምሳል እንደ ገሐዱ በሚመስል ሩካቤ ሥጋ የሚታየንና ከሰውነታችን ፈሳሽ የሚወጣበት ሂደት ነው፡፡ ዝንየት የሚባለው ደግሞ በሕልመ ሌሊት የሚፈታተነን አጋንንት ነው፡፡ ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ወንድና ሴት ሳይል በማንኛውም ሰው ላይ በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡
በሱባኤ ጊዜ ሕልመ ሌሊት ከመታን እለቱን ቤተ-ክርስትያን በተለይም ቤተ-መቅደስ መግባት፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበል፣ ጸበል መጠመቅና መጠጣት፣ አንችልም፡፡ በማግስቱ ግን ሰውነታችንን ታጥበን፣ልብሳችንን ቀይረን ቤተ-ክርስትያን መግባት፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበል፣ ጸበል መጠመቅና መጠጣት እንችላለ፡፡
እንደዚህ የምናደርገው አንደኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ ስለሆነ ነው፡፡ ሁለተኛ ቅድስት ለሆነችው እናት ቤተ-ክርስትያን ክብር ከመስጠት አንጻር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን በዘሌዋውያን ምዕራፍ 15÷2 ላይ ‹‹ማንም ሰው ከሥጋው ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፣ስለሚወጣው ነገር ርኩስ ነው›› ይልና እዛው ቁጥር 16 ላይ ‹‹ማንም ሰው ዘር ከእርሱ ቢወጣ፣ገላውን ሁሉ በውኃ ይታጠባል፣እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው›› ይላል፡፡ /ዘሌ 15÷16/
ተወዳጆች ሆይ ልብ በሉ ‹‹ማንም ሰው›› ነው እንጂ ወንድ ሴት፣ወጣት አዛውንት አይልም፡፡ ይህ የሚያሳየው ኦርቶዶክስ የሆነ በየትኛው ጾታ እና የእድሜ ክልል ያለ ሁሉ ሕልመ ሌሊት ከመታው እለቱን ሳይሆን ማግስቱን ነው ቤተ-ክርስትያን መግባት የሚችለው፡፡ ‹‹እስከ ማታ›› የሚለው ሕልመ ሌሊት ሲመታን ለአንድ ቀን ብቻ የተከለከልን መሆናችን ያስረዳል፡፡ መቼም ሕልመ ሌሊት የሚመታን ማታ ወይም ሌሊት ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ማታ ወይም ሌሊት ሕልመ ሌሊት ከመታው ቀኑን ውሎ እስከ ማታ ነው የሚረክሰው፡፡ ከማታ በኃላ ንፁህ ይሆናል፡፡
ወዳጆቼ አንዳንዶች ‹‹ሕልመ ሌሊት ከተመታችሁ እስከ ሦስት ቀን ቤተ-ክርስትያን መግባት አይቻልም›› ይላሉ፡፡ ይህንም ‹‹ማነው ያለው›› ስትሉ የፈረደባቸው ‹‹አባቶች›› ናቸው ይላሉ፡፡ ቅዱስ መጽሐፍም አባቶቻችንም የሚነግሩን እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቤተ-ክርስትያን የማንገበው ሩካቤ ሥጋ ስንፈጽም ብቻ ነው፡፡
ሕልመ ሌሊት መታን ማለት በቤት እና በቅጽረ ቤተ-ክርስትያን ሆኖ መጸለይ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡ በሱባኤም ሆነን ሕልመ ሌሊት ቢመታን ሰውነታችን ታጥበት ሱባኤው መቀጠል እንጂ ማፍረስ የለብንም፡፡
በቀጣይ👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#ነሃሴ_7
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ሊቀ_ሐዋርያት
ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ። በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ።
የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር። የዋሃን (ገና ምሥጢርን ያልተረዱ) ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ። ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን። ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት።
አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው። "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው። ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ።
ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ። "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው። እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ።
ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ። ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና። በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው። (ማቴ. 16:16)
ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት (መሠረት) ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ። ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ (ሥልጣን)" ተሰጠው።
ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ። ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ ማርያም: አካላዊ ቃል: ሥግው ቃል: ገባሬ ኩሉ: የሁሉ ፈጣሪ" ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም።
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ነሃሴ_7
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ቁጽረታ (ጽንሰታ)ለማርያም
ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል።
ስለ ምን ነው_ቢሉ :- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ።
"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" - "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።"
(መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)
ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል።
የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር።
ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም።
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች።
ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ።
እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ።
በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች።
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" - "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም)
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 ለሱባዔ እንቅፋት ንስሐ አለመግባት!
👉 እውን እመቤታችን በራዕይ ትታያለች?
👉 ሱባኤ እና ሕልም ምን ይመስላሉ?
🎤 በቀሲስ ሔኖክ ወ/ማርያም
#የመጨረሻው_ክፍል
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 ሱባዔ በቤታችን መግባት እንችላለን
👉 አርምሞ ማለት ምን ማለት ነው?
👉 አርምሞና ተአቅቦ ልዮነታቸው?
🎤 በቀሲስ ሔኖክ ወ/ማርያም
#ክፍል_ሁለት
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 ሱባኤ ምን ማለት ነው?
👉 አንድ ሱባኤ ስንት ቀን ነው?
👉 ሱባኤን ማን ጀመረው?
👉 ሱባኤ የምንገባበት አላማ?
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ፍልሰታ ምን ማለት ነው?
ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"
‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››
ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡
ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡››
ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡
በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡
ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡
እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡
የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?
የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡
ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
የጾም ሥርዓቱና ጥቅሙ
‹‹መላው ሕዋሳታችን ካልጾሙ የምግብና መጠጥ ጾም ብቻ ዋጋ የለውም። መጽሐፉም የሚለው ‹ወደ አፍ የሚገባ ሰውን አያረክስም፤ ከአፍ የሚወጣ እንጂ› ነው። ስለዚህ ዐይን ፣ ጆሮ፣ እግርና እጅ የመሳሰሉት የስሜት ሕዋሳታችን መጾም አለባቸው፡፡
ከምግብና መጠጥ ይልቅ የሚበልጡት እነዚህ ናቸው፡፡ ከምግብና መጠጥ የምንቆጠበው በራሱ ኃጢአት ስለኾነ ሳይኾን ምግብና መጠጥ ሥጋን አጥግቦ በገደል ስለሚጥል ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ስለሚጎትት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡
ስንጾምም ከሐሜት፣ ከአሉባልታ፣ ከዝሙትና በሐሰት ከመመስከር፣ ወዘተ. መቆጠብ አለብን ሲሉ ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡
የጾም መሠረቱ ሃይማኖት ነው፡፡ በሃይማኖት የተነሣ ለተወሰኑ ጊዜያት ከምግብና ከመጠጥ የምንከለከልበት ኹኔታ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ጾም ይህ ብቻ አይደለም፤ ሁለት ዓይነት መስመር አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአጽዋማት ወቅት ከምግበ ሥጋና ከኃጢአት ትከለክላለች፡፡
ከኃጢአት ዅልጊዜም እንከላከላለን፡፡ ከምግብ የምንከለከለው ምግብ ኃጢአት ስለኾነ ሳይኾን ከሃይማኖት የተነሣ ነው፡፡ ምግብ በልተን ፈቃደ ሥጋችንን ከምናደልብ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሥጋችንን ጎስመን ያለ ምግብና ያለ መጠጥ እግዚአብሔርን እያመሰገንን የምንኖርበትን ሰማያዊና ዘለዓለማዊ ሕይወት የምናስብብት መንገድ ነው›› የሚሉት ደግሞ ቀሲስ ስንታየሁ አባተ ናቸው፡፡
በቀጠይ 👉 በጾም አይነቶች እና ፍልሰታ ጾም
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ሱባኤ ለመግባት መደረግ ያለበት ዝግጅት
ክፍል ሦስት
ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት ኣስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት ኣስፈላጊ ነው፡፡
ቅድመ ዝግጅት
ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/ በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኣንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት ኣለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሓ ኣባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በኣባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ ኣባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኣንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሓ ኣባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡
ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ ኣቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው ኣንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዓቅምንና ችሎታን ኣገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡
ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በኣብዛኛው ሱባዔ የሚገባው ኣጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን ኣለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በኣጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሓራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በኣጽዋማት ወቅት ብዙ ኣባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከኣባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ ኣይያዝም» የሚል ኣቋም ለመያዝ ኣይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ካጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግልናል ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ ኣያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና ኣድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡
በክፍል 4 :- በሱባዔ ጊዜ ምን እናድርግ?
ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሱባዔና ሥርዓቱ
ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ
ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡
ሱባዔ ምንድን ነው?
ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡
ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ሱባዔ መቼ ተጀመረ?
ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ሲል ቃልን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ አራት/፡፡
#ይቀጥላል ....
በቀጣይ ሱባዔ ምንድን ነው ጥቅሙ?
ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰንበት
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡
ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10)፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡
ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-
👉 እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
👉 ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
👉 ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
👉 የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያገኙባት ዕለት
👉 ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት(1ኛ ቆሮ 16፤1)
👉 የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7 በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት
ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡
ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር። (ራዕ 1፡10)
በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)
ከሰንበት ረድኤት በረከት ይካፍለን!
ሌሎች እህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ማስታወሻ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን፣ ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ አበክሮ ይነግረናል፡፡
በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡
ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››
ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ነሐሴ 10/12/2016 ዓ.ም
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን፦ ዕብ 12÷22-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦1 ጴጥ 1፥6-13
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 4÷31-ፍ.ም
ምስባክ ፦ መዝ 73፥2-4
ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅድምከ ፈጢረ
ወአድኀንከ በትረ ርስትከ
ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ
ትርጉም ፦
አስቀድመህ የፈጠርካትን ማኅበርህን
የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር
በርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተኣኣ አስብ፡፡
ወንጌል ፦ ሉቃ 16÷9-19
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👉 የሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#አፄ_ናዖድ_ጻድቅ
ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት: ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯ። ከእነዚህ አንዱ ደግሞ አፄ ናዖድ ናቸው። ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ/ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል።
ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት (ሰላም ለኪ: እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .) የደረሷት እርሳቸው ናቸው። ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል። ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው።
የጻድቁ ንጉሥ ሚስት (ማርያም ክብራ): ልጆቻቸው (አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ) እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ። ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሳ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት።
እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው። ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ" አሏት። በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ/ም ሊገባ እርሳቸው #ነሐሴ_7 ቀን በ1499 ዓ/ም ዐርፈዋል::
ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖትና የአፄ ናዖድን በረከት ያሳድርብን።
👉 ነሐሴ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር
4.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
6.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ)
7.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት
👉 ወርኀዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
"መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው። ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል።
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::"
(መዝ. ፹፮፥፩-፮)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ነሐሴ 7/12/2016 ዓ.ም
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን :- ዕብራው - 9:1-11
ንፍቅ ዲያቆን :- 1ኛጴጥሮስ - 2:6-18
ንፍቅ ካህን :- የሐዋሥራ - 10:1-30
ምስባክ:- መዝ 93:12
ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ
ወዘመሀርኮ ሕገከ
ከመ ይትገሃሥ እመዋዕለ እኩያት፡፡
ትርጉም
አቤቱ አንተ የገሠጽኸው
ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ምስጉን ነው
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፡፡
ወንጌል:- ማቴዎስ16:13-24
ቅዳሴ፡ ዘእግዝእትነ(ጎሥዓ)
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 በሱባዔ ወቅት ምን ልጸልይ?
👉 እንዴትስ ልጸልይ?
👉 ሁለት ሦስት ግዜ ሱባዔ ገብተን መልስ ብናጣ ምን እናድርግ?
🎤 በቀሲስ ሔኖክ ወ/ማርያም
#ክፍል_ሦስት
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
👉 በጾመ ፍልሰታ ሱባዔ እንዴት ልያዝ?
👉 አመጋገብስ?
👉 ሱባዔ እንዴት ተጀመረ?
📜 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማብራሪያ
🎤 በቀሲስ ሔኖክ ወ/ማርያም
#ክፍል_አንድ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#ፍልሰታ_የሕፃናት_ደስታ
የፍቅር የሰላም የደስታ ፆማችን
ከጌታችን እናት በረከት ማግኛችን
ፍልሰታ መታለች እጅግ ደስ ይበለን
ለቅዳሴ እንሂድ ልጆች ተሰብስበን
ፍልሰታ (2) የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ
ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ
ከመቤታችን እጅ ሰበኗን አግኝቶ
የተደሰተባት የበረከት ፆም ወቅት
ፍልሰታ መታለች እንሂድ ለፀሎት
#አዝ
መንፈሳዊ ቅናት ሐዋርያት ቀንተው
እነሱም ለማየት ትንሣኤዋን ሽተው
በህብረት በመሆን ጠይቀው በእምነት
ትንሣኤዋን አዩ በፆምና ፀሎት
#አዝ
ሁል ግዜ በዓመት የምንናፍቃት
በፍቅር ምንፆማት ለማግኘት በረከት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንማርባት
ፍልሰታ መታለች ኑ እንቁረብባት
ፍልሰታ (2) የሕፃናት ደስታ
እንሂድ ቅዳሴ ከቅዱሱ ቦታ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የጾም ዓይነቶች
ጾም የግል ,የዐዋጅ (የሕግ) እና የፈቃድ ጾም በመባል በሦስት ይከፈላል፡፡ ወይም የግል ጾምን የንስሐና የፈቃድ ጾም ብለን በሁለት እንከፍለዋለን፡፡ የዐዋጅ (የሕግ) አጽዋማት ሰባት ናቸው፡፡ እነዚህም :-
1⃣ ዐቢይ ጾም
2⃣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)
3⃣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
4⃣ ጾመ ገሃድ
5⃣ ጾመ ነነዌ
6⃣ ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ) እና
7⃣ ጾመ ፍልሰታ ናቸው፡፡
የዚህ ጽሑፍ መነሻም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነው ጾመ ፍልሰታ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ወቅቱ የፍልሰታ ጾም ስለኾነ፡፡
የፍልሰታ ጾም
ከዚህ በመቀጠል ጾመ ፍልሰታን ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምን እንደ ኾነ እንመለከታለን፡፡ የፍልሰታን ጾም ሕፃን አዋቂው ሳይቀር በልዩ ሥነ ሥርዓትና በደመቀ ኹኔታ ይጾማል፡፡
አብዛኞቹ ምእመናን የዕረፍት ጊዜ በመውሰድ በገዳማትና በየአብያተ ክርስቲያናት ሱባዔ በመግባት ከነሐሴ አንድ ጀምሮ እስከ አሥራ አምስት ቀን ድረስ ጾም፣ ጸሎት በማድረግ ይቆያሉ፡፡ ጾም ጸሎት ሲያደርጉ ደግሞ በድሎት ሳይኾን በየዋሻው፣ በየመቃብር ቤቱና አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ እንጨት ረብርበውና ሳር ጎዝጉዘው ጥሬ እየበሉ ነው፡፡
በቀጣይ 👉 ፍልሰታ ምን ማለት ነው? የሚለውን እናያለን
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/
በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሓራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢኣቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡
ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/
ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡
ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማጸን መጽናት ይኖርብናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወንድም እህቶቻችን ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሱባዔ ለምን?
#ክፍል_ሁለት
የሰው ልጅ፤ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡
በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ.7.22-25፡፡
ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ /ሱባዔ/ ይገባል፡፡
እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡
ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው? በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡
ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡
አኃው ለተልእኮ በወጡበት አንዱን ድቀት አግኝቶት ያድሯል፡፡ በነጋው ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ አለው፡፡እኔም እንዲሁ አግኝቶኛል፤ ይልቁንስ ሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደ ቀደመው ኾነን እንኖራለን ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡
ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢገብረ እኁከል፤ ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡
ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባት ቀን/ እንደ ጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡
ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡
#ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል ሱባዔ ለመግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት?
ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ወደናንተ ልናቀርብ ካሰብናቸው መካከል
👉 የየዕለቱ ምስባክ
👉 ስለ ሱባዔ ትምህርት
👉 በሱባኤ መካከል ሊያጋጥሙን የሚችሉ ነገሮች
👉 ስለ አጿማትና ጾመ ፍልሰታ
👉 የየዕለቱ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
👉 የንስሐ መዝሙራት
👉 ሌሎችንም ወደናንተ ለማድረስ ተዘጋጅተናል።
በመሆኑም ሁላችንም የተዋህዶ ልጆች ይህን የዝማሬ ዳዊት ገጽ ለሌሎች እህት እና ወንድሞቻችን በማዳረስ አገልግሎቱን ተደራሽ እንድናደርግ በእግዚአብሔር ሥም እንጠይቃለን።
መልካም ጾመ ፍልሰታ መልካም ሱባዔ ይሁንልን።
👉 @ortodoxmezmur
ሐምሌ 26 በዚህች ዕለት መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ጻድቁ ዮሴፍ አረፈ።
በአረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደ እርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ላይ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃብር አኖሩት።
ምንጭ፡ መጽሐፈ ስንክሳር
በረከቱ ይደርብን!
@ortodoxmezmur
እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤልና አገልግሎቱ በጥቂቱ
✍ ዑራኤል የሚለው ስም "ዑር"እና ኤል ከሚለው ሁለት ቃላት የተመሰረተ ነው ። ትርጉሙም ብርሃነ ጌታ አምላክ ብርሃን ነው። ማለት ነው።
✍ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ መብረቅና ነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበቁ ነጓድጓድ ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። (መጽሐፈ ሄኖክ ፮፥፪)
✍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ እየመራ፤ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ከዚያም ከእመቤታችን ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው።
✍ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለበት ጊዜ፥ክቡር ደሙ በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን ነሳንስ የረጨው እሱ ነው።
✍ ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ልቦና ያጠጣው፥ጥበብን ማስተዋልን የሰጠው የጠፉ መጽሓፍት በቃሉ አስታውሶ እንደገና ያጻፈው የረዳው መልአክ ነው።(ዕዝ፲፫፥፴፱)
✍ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ትዕዛዝ ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ህይወት ስላጠጣቸው ነው።
✍ በዓላቱም በዓመት 3ናቸው።
፩...ጥር። 22 በዓለ ሲመቱ፤
፪....መጋቢት 27 የጌታችንን ደም በዓለም የረጨበት፤
፫...ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ።
✍ በጸሎቱ የተማጸነ ከእግዚአብሔር አምላክ በረከትን ፣ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ ጠባቂ ና የዋህ መልአክ ነው።በተለይም ህጻናትን የሚጠብቅ የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ ፥ኃጢአተኞች ካሉበት ቦታ እኔን ላከኝ እያለ አምላኩን የሚማጸን አዛኝ የዋህ መልአክ ነው።
✍ ይህ አለም በአማላጅነቱ አምኖ በእምነት ጸበሉን ቢጠጣ ፥ዝክሩንም ቢዘክር ከክፉ በሽታው እንደሚድን፤ እንደሚፈውሰው ቃል ኪዳን ተሰጥቶታል ።
✍ ቅዱሳን መላዕክት እግዚአብሔርን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራሉ ከመከራም ያድኑዋቸዋል።(መዝ ፴፫÷፯) የአባታችን የጠባቂያችን የአማላጃችን የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል ቃል ኪዳን አይለየን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤