ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይቺን ዓመት ተወኝ

ከአመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እንዳጎሳቆልኲኝ

አውቃለሁ አምላኬ ፍሬን ለመቀበል እንዳመላለስኩሁህ
ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅዬ ደርቄ ጠበኩህ
ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም
ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አለየኝም ከዓለም
አዝ
የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ
የኔን ክፋት ተወው መላክህን ሰምተህ ይቺን ዓመት ተወኝ
አዝ
አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር
ብዙ ጊዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር
ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይሔን ጊዜ ሰምተኸኝ ነበር
ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮዬ አልፎ በአዲስ ተቀየረ
አዝ
ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ
እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ
የቃልህን ውሃ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ
ወደ ልቤ ሳይሰርግ ሕይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈሶ ቀረ
አዝ
ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ
በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ
ብዙ ጥቅስ አገኘው ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ
ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁኝ በበደል ተኝቼ
አዝ
ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርፀኝ ተማሪ ብሆንም
ይቺን ዓመት ተወኝ ደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም
እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ
ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መዓዛ እንዲደርሰኝ
አዝ
የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሽከመኝ አትሰልቸኝ አደራ
ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት አይሰሩ ስሰራ
አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ
አዝ
ቦታስ የሚይዙ ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸዉ
ልክ እንደ ዘንባባ የተንዥረገገ ተጋድሎ ፅድቃቸው
ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው
አዝ
እኔ አይደለሁም ቦታስ የሞትይዘው ያንተው እናት ናት
ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት
ይቺን ዓመት ተወኝ ከስሯ ሆናለው ባፈራ ምናልባት
አዝ
ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት
ሺ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንት ናት
ይሔ ዓመት አልፎ ዳግም ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ
እባክህን ጌታ ይቺን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ

ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሚ ጸጋ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጷጉሜ 5


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ጷጉሜ አምስት በዚች ቀን ንፁሕ ድንግል አባት፤ የምስር ሀገር ኤጲስቆጶስ አባ ያዕቆብ አረፈ።

አባታችን ገና በታናሽነቱ የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ነፍሱ ወደደች ከሀገሩም ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደና በአባ ዮሐንስ ሐጺር በዓት ውስጥ በጽኑ ተጋድሎ ኖረ።

የደግነቱ የትሩፋቱና የቅድስናውም ዜና ተሰማ በእግዚአብሔር ፈቃድ በምስር ሀገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። በሹመቱ ወንበርም በተቀመጠ ጊዜ ጾምን ጸሎትን ተጋድሎውንም ጨመረ።

ስለ ሹመቱም ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ እንጂ ቸልም አላለም።


ሕዝቡንም ሁልጊዜ ያስተምራቸዋል ኃጢያትን በመስራት የሚኖሩትን ይገስጻቸዋል። በንስሐ እስኪመለሱም ሥጋውና ደሙን ከመቀበል ያግዳቸዋል።

በጎ ተጋድሎንም በፈጸመ ጊዜ ጥቂት ታመመ መንጋዎቹንም ጠርቶ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አዘዛቸው። ካህናቱንም ጠርቶ በጸሎትና
በአገልግሎት ጊዜ ቸል እንዳይሉ አዘዛቸው። በዚህች ዕለትም አረፈ።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​🌼 አበባ አየሽ ወይ 🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2)
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ጌቶች አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ዘመን መጣ ብለን

አበባ አየሽ ወይ           ለምለም(2)
ባልንጀሮቼ                        "
ግቡ በተራ                       "
በእግዚአብሔር መቅደስ     "  
በዚያች ተራራ                   "   
እንድታደንቁ                      "          
የአምላክን ሥራ                 "    
ህይወት ያገኛል                 "  
እርሱን የጠራ                    "      

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባ አየሽ ወይ          ለምለም (2)
ክረምት አለፈ                   "
ጨለማው ጠፋ                "   
የመስቀሉ ቃል                  "
ሆነልን ደስታ                    "   
እናገልግለው                   "  
ቤቱ ገብተን                     "     
ትንሽ ትልቁ                      "  
ተሰልፈን                         "        

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባ አየሽ ወይ     ለምለም(2)
ያንን ኩነኔ                    "
ዘመነ ፍዳ                    " 
የሞቱ በራፍ                 "
ያ ምድረበዳ                 "
ልክ አንደ ክረምት         "
ሄደ ተገፎ                    "
ፀሐይ ወጣልን             "
ጨለማው አልፎ           "

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ (2)

አበባ አየሽ ወይ         ለምለም(2)
ይኸው መስከረም           "
ይኸው ፀሐይ                 "    
ንጉሡ ወርዶ                  "       
ከላይ ሰማይ                  "        
አውደ ዓመት ሆነ            "
ደስታ ሰላም                   "
ፍቅር ሲገለጥ                "   
በአርያም                       "       

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባ አየሽ ወይ         ለምለም(2)
ይኸው አበባ                  "
ለምለም ቄጤማ             "
አዲሱ ዘመን                  "
አምጥቷልና                    "    
በሩን ክፈቱ                     "       
መኳንንቶቹ                     "       
የክብር ንጉሥ                 "    
ይግባ ቤታችሁ               " 

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባ አየሽ ወይ         ለምለም(2)
ቤታችሁ ይሙላ             "
ሰላም ደስታ                   "
ሰጥቷችሁ እርሱ            "
የሁሉ ጌታ                     "      
ከዘመን ዘመን                "     
ያሸጋግራችሁ                "      
የሽበትን ዘር                  "   
ይሸልማችሁ                 "      

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ

ይሸታል ዶሮ ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ

ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጎሳ ልብየ

ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ/2/
ወአነ አይድ ቅዳሴሃ ለማርያም/2/

እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለሁ
እንደ አባቴ ዳዊት በበገና እዘምራለሁ
ቀን ከሌሊት ሳልል ለምስጋና እተጋለሁ
የኃጢአቴ ቁስል እንዲፈወስ እጮሃለሁ
ምርኩዜ ነሽና እመቤቴ በአንቺ እመካለሁ

አዝ

ኦ...እመቤቴ በእውነት እንወድሻለን
የእውነተኛ መብል ክርስቶስን ወለድሽልን
ምክንያተ ድሂን ሆይ ድንግል ማርያም የአምላክ መገኛ
በአማላጅነትሽ በመታመን እንጮሃን እኛ
ምሕረትን አድይን ኪዳነምህረት የዓለም መዳኛ
አዝ

ስለ ቸርነትሽ እመቤቴ ለእኔ እናቴ ነሽ
ስለ ንግሥትነትሽ እመቤቴ ነሽ
ዝናባት ሳያጠጡት አየራት ሳያሳድጉት
ሰማያዊ እንጀራ የሰጠሸን ቤተልሔማዊት
ቅድስተ ቅዱሳን የኖህ መርከብ የአምላክ እናት
አዝ

ቃና ዘገሊላ በሰርጉ ቤት በዚያ ተገኝተሽ ሳለሽ
ውኃውን ወደ ወይን ባንቺ ምልጃ እዳስለወጥሽ
ዛሬም የእኔ ሕይወት ወይኑ አልቆ ባዶ ሆኖአልና
አንቺየአምላክ እናት ንጽሂትቅድስት ርኅሪሂተ ህሊና
ሕይወቴን አድሰሽ ቀድሰሽ ሙይው በምስጋና

ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጷጉሜ 4


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም፤ ጷጉሜ አራት በዚች ቀን ተጋዳይ አባ ባይሞን አረፈ። አባ ባይሞን የተባረኩ ስድስት ታላላቅ መነኮሳት ወንድሞች ያሉት ሲሆን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ከስድስቱ ቅዱሳን እርሱ የተለየ ነበር።

መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ሁሉም በአንድ ቀን መነኮሱ። ለእናታቸውም እንዳይቸግራት የሚያስፈልጋትን ሁሉ ካዘጋጁ በኋላ ይህን ዓለም ንቀው ወደ ገዳም ተጉዘው በአንዲት በዓት አረፉ።

አባ ባይሞን በአስቄጥስ ገዳም ፈተና፣ የሃይማኖት ጥርጥርና ደዌ ያገኘውን ሁሉ ይፈውስ፣ያረጋጋም ነበር። ስለ ምንኩስና ሕግ፣ስለ መጋደል እና ስለ አምልኮም ብዙ ድርሳናትን ደረሰ።

ዕድሜውንም በተጋድሎና በትሩፋት ሥራ ከፈጸመ በኋላ ወደ መልካም ዕርግና ደርሶ እግዚአብሔርን አገልግሎ አረፈ።

አባታችን እንዲም ይሉናል
እኛ የወንድማችንን በደል ብንሰውር እግዚአብሔርም በደላችንን ይሠውርልናል።


በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✞ ሩፋኤል ብዬ ✞

ሩፋኤል ብዬ ስጠራው ምስጢሬን ሁሉ ሳወራው
ትላንት የረዳኝ ጸሎትህ ዛሬም ይድረሰኝ ለልጅህ

ሩፋኤል ብዬ  አንደበቴ ለምዶት ስምህን
ሩፋኤል ብዬ  ልጅነቴ  ቀምሶት ፍቅርህን
ሩፋኤል ብዬ የህይወቴ ቅጥር ሲላላ
ነፍሴ ትጮሀለች ሩፋኤል ሩፋኤል ብላ አዝ
ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት
ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት
ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ
ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ
አዝ
ሩፋኤል ብዬ ህመሜ እንዳይጸና ክፋቱ
ሩፋኤል ብዬ መድሐኒት እንዲሆን ሀሞቱ
ሩፋኤል ብዬ  ካጠገቤ እንዳትርቅ ከጎኔ
ትዳሬ እንዲጸና ሩፋኤል እንዲበራ አይኔ
አዝ
ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት
ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት
ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ
ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ

ዘማሪ ሚኪያስ መንገሻ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ፈታሔ ማሕፀን

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ቅዱሳን መላእክት ምእመናን ለመርዳት ለማገልገል ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት አይደሉምን? ( ዕብ ፩÷፲፬) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም "የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ"( ራእዩ ለዮሐንስ ፰÷፬) በማለት ተናግሯል።

ቅዱሳን መላእክት ያለማያቋረጥ ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ለተልእኮ ይፋጠናሉ። የሰውን ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ምሕረት ወደ ሰው አድርሰው በእምነት ያጸናሉ። "በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው" (ራእ. ፰÷፪) የሚለው የሚያስረዳን ለተልእኮ መፋጠናቸውን ነው። ሄኖክም “በሰው ሰውነት ላይ የተሾሙ ከከበሩ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው” (ሄኖ.፮÷፩-፵፪) ብሏል።

የሰዎችን ልመና ወደ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና በረከት ወደ ሰው የሚወርድባት ዕለት"ርኅወተ ሰማይ” ትባላለች። ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች። እንዲህ የሚባለው በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት የሚያሳርጉበት፣ አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንጂ።

ቅዱስ ሩፋኤል ልቡናን ደስ የሚያሰኝ፣ ባለ መድኃኒት፣ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ ቍልፍ የተሰጠው፣ የሴቶችን ማሕጸን የሚፈታና ሳይጨነቁ እንዲወልዱ ምጥን የሚያቀል መልአክ ነው። "ለሰብእ ወለእንሰ ፈታሔ ማሕጸኖሙ አንተ" እንዲል። የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረና ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ መላእክት መካከል አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ "(ጦቢያ ፲፪÷፲፭) የሚለው የሚያስገነዝበው ተራዳኢነታቸውን፣ ባለሟልነታቸውን፣ አማላጅነታቸውን ነው።

ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ"(ሐዋ. ፲÷፬) የሚለው የመላእክትን አገልግሎት የሚገልጥ ነው። መላእክት ሰዎችን ይራዳሉ፣ የሰውን ጸሎት ያሳርጋሉ፣ ያማልዱሉ፣ ሰዎችን ከመከራ ነጥቀው ያወጣሉ። "የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህን ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ፣ እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው። ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ። ስበክ እንዲህም በል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል (ዘካ፣ ፩÷፲፪÷፲፬) የሚለው አማላጅነታቸውን የሚገልጥ የማጽናኛ ቃል ነው።

ጦቢያና መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱ ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው። መልአኩም ለጦቢያ አባትህ ከዘመዶችህ ወገን አግባ ያለህን ቃል አስብ አለው። ራጉኤልም ልጁ ሣራን ለጦቢያ አጋባት። ተመግበውም ከጨረሱ በኋላ ጦቢያን ወደ እርሷ አገቡት፤ ወደ እርሷም በገባ ጊዜ የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤልን ነገር አሰበ፤ የዕጣን እራሪ ወሰደ፤ ከዚያም ዓሣ ከልቡና ከጉበቱ ጨምሮ አጤሰው። ሽታውም ያን ጋኔን በሸተተው ጊዜ እስከ ላይኛው ግብፅ አውራጃ ድረስ ሸሸ። መልአኩም ጋኔኑን አሰረው( ጦቢ ፰÷፩) የተባለው የሚያስረዳን የመላእክትን ተራዳኢነት ነው።

ጦቢያ የሰርጉን በዓል በጨረሰ ጊዜ ወደ አባቱ ቤት ከሚስቱ ከሣራና ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር ተመለሱ። ሩፋኤልም አለው፥ "ያባትህ ዐይኖች እንዲበሩ አውቃለሁ፤ አንተ ግን ያን ሐሞት ያባትህ ዓይን ኳለው፤ በተኳለም ጊዜ ብልዙ ከአይኑ ይወጣል በደህናም ያያል። ጦቢያም የአባቱን አይን ኳለው ዓይኑም በራለት”( ጦቢ ፲፩÷፮) ተብሎ እንደተነገረው እግዚአብሔር ከዚህ ክፉ ወረርሽኝ ጠብቆን በሰላም በጤንነት ለሚመጣው ዓመት ያድርሰን። የጦቢትን ዓይን ያበራውን የቅዱስ ሩፋኤልን ዓመታዊ በዓል አክብረን በረከት ለማግኘት ያብቃን።አሜን!!

ዲ/ን ተመስገን ዘገየ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ጳጉሜን

ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡

ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡

በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡

የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡

ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡

ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🙏🙏ነገረ ማርያም ክፍል ፫🙏🙏
ምልጃ ወይም አማላጅነት ምን ማለት ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ነገረ ማርያም ክፍል ፪
እነሆ🤲🤲🤲


ክፍል ፩ ያላዳመጣችሁ ካላችሁ በኮመንት አሳውቁን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል" ሉቃ 1:48

🤲ክፍል ፭🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🙏አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ🙏
       

      🤲ትርጓሜ ክፍል ፫🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🤲ነገረ ማርያም መግቢያ🤲

📣ክፍል ፩📣

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉ስለ ድንግል ማርያም
👉ስለ ፍጹም ድንግልናዋ
👉አምላክን ስለመውለዷ
👉ስለ አማላጅነቷ እና ሌሎችም ጥያቄዎች መልስ ከፈለጋችሁ እነዚህን አዳምጧቸው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጳጉሜ 2


ከ72ቱ አርድእት የሆነ የከበረ ቅዱስ ቲቶ በዚች ዕለት አረፈ።

ቅዱሱ ባለፈ ሕይወቱ እግዚአብሔርን ባያመልክም በጠባዩ ግን እጅግ ቅንና ደግ ነበር። እግዚአብሔርም ይህን ቅን ሰው መልካም ስራውን ተመልክቶ በራዕይ ተገለጠለት።
ስለነፍስህ ተጋደል አለው።


ቅዱስ ቲቶም ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። ጌታችንም በሚያደርጋቸውን አምላከዊ ስራ ተመልክቶ ፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ። ሰማያዊና ዘላለማዊ ትምሕርቱን በሰማ ጊዜ  በራዕይ ''ስለ ነፍስህ ተጋደል።'' ያለው ምሥጢር አሁን ተገለፀለት። አምኖም ተከታዩ ሆነ።

ከዚህም በኋላ ከጌታችን እግር ለሦስት ዓመታት ተምሮ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በመላው እስያ ለስምንት ዓመታት ወንጌልን ሰብኳል። ዕድሜው በደረሰ ጊዜም በዚህች ዕለት አርፏል።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼ዘመን ተሰጠን🌼

ዘመን ተሰጠን ለምስጋና
ዘመን ተሰጠን ለውዳሴ
ተመስገን ሥላሴ

ቸርነትን ሰጠን ዘመን ለፍስሐ
ይቺም እድሜ ለእርቅነች ለንስሀ
ጥበባችን መቼ ሆነ እውቀታችን
ምሕረትህ በዝቶልን ነው መቆማችን

ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት

አዝ🌼

የለውም ጫፍ የለው ድንበር ያንተ ምህረት
በእድሜያችን ጨመርክልን ይህቺን እለት
ተደነቅን ተገረምን በአንተ ፀጋ
ቀንና ለሊት ሲፈራረቅ ክረምት በጋ

ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት
አዝ🌼

ምድር ረክታ በዝናቡ በሰማይ ጠል
በአበባ ደምቃ ታየች በሐመልማል
በእድሜያችን ላይ ከጨመርከው ይህን ዓመት
የንስሀ ይሁንልን የመጸጸት

ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት
አዝ🌼

የእርቅ ይሁን ዘመናችን የይቅርታ
ሰላም ትሁን ሀገራችን ፍቅር ተመልታ
መለያየት መጠላላት የሌለበት
አድርግልን ጌታችን ሆይ ይህን ዓመት

ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​🌼 አበባ አየሽ ወይ 🌼

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​​​🌼 መስከረም 1
ሃይማኖታዊ መሠረት

ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን ሲጽፍ «የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጅ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ» ተብሎ በኢሳይያስ እንደ ተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ  ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ላይ ተነሥቶ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ ለኃጢአት ሥርየት እየሰበከ መጣ ብሎ በዘመነ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ገልጾታል።

/የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፵፤ ትንቢተ ኢሳይያስምዕ ፵ ቁ ፫ - ፬/።

የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ ሆኖ መገኘቱን በመረዳት የቤተክርስቲያን አበው የበዓላቱን ድንጋጌ በወሰኑበት ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል የኢትዮጵያ ርዕሰ ዓውደ ዓመት በሚሆን መስከረም ፩ ቀን እንዲከበር በየዓመቱ የዘመኑ መጀመሪያ በእርሱ ስም እንዲጠራ አባቶች ደንግገዋል፡፡ / ድርሳነ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1ጠ 3/

ይህንንም በዓል አባቶቻችን በርእሰ ዓውደ ዓመት ማክበር እንደሚገባ አስበው ያደረጉት ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ሆኖ አይደለም፡፡ ለአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወይም ርእሰ ዓውደ ዓመት «ቅዱስ ዮሐንስ» ይባላል፡፡ 

መጽሐፈ ስንክሳር የዓመቱን መጀመሪያ /መስከረምን/ ሲያትት «ይህ የመስከረም ወር የተባረከ ነው እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው በማለት ያስረዳል፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከመስከረም አንድ ቀን ጀምሮ ቀኑ እየጎደለ ይሔዳል፡፡

👉 ከዚህ በመቀጠል በዓሉ በተለያየ ስያሜ ስለመጠራቱና ትርጓሜያቸውን እንመለከታለን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሰማይም የምድርም ጌታ

የሰማይም የምድርም ጌታ
በዝቶልናል እጅግ ስጦታ
በጎነትህ ቸርነትህ
እረድቶናል ክቡር ስምህ። (2)

አዝ

በማይዝሉ ጽኑ ክንዶችህ
ተደገፍን በቸርነትህ
የፍቅር አባት ላመኑህ ጥላ
ክርስቶስ ነህ የእኛ ከለላ።
አዝ

ፍፁም ቆምን በንጹህ ደምህ
ተፈወስን በቅዱስ ቃልህ
መዛል ድካም ከቶ አይነካንም
ኃይላችን ነው ሁሌም የአንተ ስም።
አዝ

ያጣው ሲጮኽ ፊትህ ተደፍቶ
ሲያማክርህ ምስጢሩን ገልጦ
አባት ለልጁ እንደሚራራ
አወጣህን ከሙታን ሥፍራ፡፡
አዝ

ምስክር ነን ለዓለም ሁሉ
ስላዳነን በሕያው ቃሉ
ለውለታው ምላሽ ባይኖርም
ከምስጋና ከቶ አንቦዝንም

ዘማሪ; ቸርነት ሰናይ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✞ ቅዱስ ሩፋኤል ✞


ምስጢረ መለኮት አድራሽ ነህ ለእስራኤል
መድኃኒት ነው ስምህ ቅዱስ ሩፋኤል (፪)

የሱሳኑ ነቢይ በእጆችህ ተዳስሶ
አይኖቹ በርተዋል ምህረትን ለብሶ
እኔ ራሴን ማየት ተስኖኛልና
ከኔ አልፎ አምላኬን ልየው በጽሞና
አዝ

እረፍትህ ምስጋና ነውና አታርፍም
ችግር የምትጋርድ በያዝከው በእሳት ፍም
በሳት ሰረገላ በሚፋጠን እግርህ
ፈጥነህ ድረስልኝ የልቤን ስነግርህ
አዝ

ከአህዛብ እርሾ ደግሜ እንዳልበላ
እንደ ጦቢት ጋርደኝ በክንፎችህ ጥላ
እግዚአብሔርን ላስብ በፍፁም ልቦና
አንተን እንደሚልክ አምነዋለሁና
አዝ

ሰናክሬም በክፋት ቆሞብኝ ከፊቴ
ናልኝ እልሃለሁ ሩፋኤል አባቴ
የሰራብኝን ግፍ በአንተ ረስቻለሁ
በመድኃኒት እጅህ ደስታን አግኝቻለሁ

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ

ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ። ጦቢት፲፪፥፲፭

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሩፋኤል ይቅር በለኝ

አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ
ከልጆች ጋር ተሯሩጬ
በጠበልህ እየታጠብኩ
የውኃ ጨው እየቀመስኩ

ሩፋኤል አሳድገኝ
እንደ ታላቆቼ አድርገኝ
ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ
ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ

ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ
ጠበል ሲወርድ  ተሸሸግሁኝ
ከበረከትህ ሸሸሁኝ
ከቡራኬህ አመለጥኩኝ
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ

ስላበቃ ልጅነቴ
በቆሸሸ ሰውነቴ
በረከሰ ማንነቴ
እንዳላረክስ ጠበልህን
ተጠለልኩት ጥምቀትህን

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጳጉሜ 3


ርኅወተ ሰማይ (ሰመይ የሚከፈትባት)

ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች ሰማይ የሚከፈትባት ቀን ትባላለች።

ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት

በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱስ መልአክ ሰው(አዛርያን) መስሎ ጦብያን ለትዳር አብቅቶ ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ የጦቢትን ዓይን አብርቷል።

ዳግመኛም ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ ናት።

ቅዱስ ሩፋኤል ልቦናን ደስ የሚያሰኝ: ባለ መድኃኒት ፈዋሽ: የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው በዙፋን ለይ በክብር ለሚቀመጡ መላእክት መሪ: የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ: (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) መላእክ ነው።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቀዋምያን

ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት 
ኡራኤል ወሩፋኤል/2/ 
ይትፌነዉ ለሣህል/2/
እምኀበ ልኡል/2/ 

ትርጉም
ለነፍሳት የቆሙ እነዚህ መላእክት 
ኡራኤልና ሩፋኤል/2/ 
ከልኡል ዘንድ ለይቅርታ/2/
ይላካሉ ከልኡል/2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ነገረ ማርያም ክፍል ፫
እነሆ🤲🤲🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📣የዛሬው ምሽት ስለ ነገረ ማርያም የነበረን ትምህርት በእዚህ ላይ እናበቃለን📣


ቅዳሜ ምሽትም በተመሳሳይ ሰዓት 2:00 ላይ ቀጣዩን ክፍል የምንቀጥል ይሆናል። ሁላችሁም ቅዳሜ 2:00 ላይ ጠብቁን።


👉እስከ አሁን የነበረውን ትምህርት ከወደዳችሁት በኮመንት ላይ አሳውቁን።

ከ8,000 ሰው በላይ ይሄንን ቻናል በአንድ ቀን ውስጥ እየተመለከተው ግን ለምትወዷቸው ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችሁ የእኛን ቻናል እንዲቀላቀሉ ለምን እንደማትልኩላቸው አላውቅም።


🤲እባካችሁ ድንግል ማርያምን አትወዷትም? ጓደኞቻችሁስ በደንብ ፍቅሯ እንዲያድርባቸው አትፈልጉም? ለምን አትልኩላቸውም?


አሁን ድንግል ማርያምን ከወደዳችኋት ለ20-30 ጓደኞቻችሁ አሁን በኃላፊነት የቻናላችንን ሊንክ ላኩላቸው አሁን። ከእዛም ከላካችሁ በኋላ ልከናል ብላችሁ ኮመንት አድርጉ🙏🙏🙏

ሊንኩ 👉 /channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"እነሆ የጌታ ባርያ" ሉቃ 1:38

       🤲ክፍል ፬🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የእመቤታችን የድንግል ማርያም ንጽሕና እና ቅድስና እንዴት ነው?🤔

📣ክፍል ፪📣

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🤲🤲🤲ስለ ነገረ ማርያም🤲🤲🤲


ዛሬ ማታ 2:00 ላይ ትምህርታችንን የምንጀምር ስለሚሆን ሁላችሁም 2:00 ላይ ተሰብስባችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን።

መምህር ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን

ይሄንን ትምህርት ጓደኞቻችሁ እንዲማሩ ይሄንን ማስታወቂያ ላኩላቸው ከታች ያለውን ሊንክ በመግባት ይቀላቀሉን።


🌙 የማታ ሰው ይበለን 🌙

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ድል አለ በስምህ
በስልክ የተቀዳ

ድል አለ በስምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኔዓለም ስልህ

ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውሀ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የጸና ስምህ ነው
አምላኬ የጸና ስምህ ነው
አዝ
በእልልታ ቢፈርስ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ካንተ ነው/2/
አዝ
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውሀ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ስለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ስለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
አዝ
የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነኸን ነው ክብርና ሞገስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዝማሬ ዳዊት ቻናል የምትለቋቸው መልዕክቶች እኛ ጋር Not supported ነው የሚለን ብላችሁ መልዕክት ለላካችሁልን ተከታታዮች በሙሉ፤ እባክዎ ከስር ባስቀመጥነው ሊንክ የቴሌግራም መተግበሪያዎን ያዘምኑት /Update/ ያድርጉት።

https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

Читать полностью…
Подписаться на канал