#ገሊላ_እትዊ
እመቤቴ እሰከ መቼ
በባዕደ ሀገር ትኖርያለሽ /2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሐገርሽ ገሊላ ግቢ/2/
ገሊላ እትዊ/4/ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ
ሰደቱ ይበቃሽል ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቷልብሎ ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነገሮሽል ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰርገላ ገሊላ እትዊ
ዑራኤል ይመራሻል ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
የዝናቡን ጌታ ገሊላ እትዊ
እናቱ ሁነሽ ሳለ ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰው አድሮ ገሊላ እትዊ
ውሃ ጥም ጸንቶብሽ ገሊላ እትዊ
አፈሽ ደርቆ ዋለ ገሊላ እትዊ
ይበቃል እናቴ ገሊላ እትዊ
ረሀብ ጥማትሽ ገሊላ እትዊ
ሂጅ ወደ ገሊላ ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመድችሽ ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
የሰማዕታት አክሊል ገሊላ እትዊ
የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ
ባርከሽ ሰጠሻቸው ገሊላ እትዊ
መከራን ስድት ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደለን ገሊላ እትዊ
የአንቺው በረከት ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
ገጽሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ ገሊላ እትዊ
እግዝእትነ ማርያም ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ ገሊላ እትዊ
መከራ ስቃይ ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ /2/
ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/
ዘማሪ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በይስሐቅ ፈንታ
የበገና መዝሙር
በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2/
ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደ ሞት
ንፁህ ኢየሱስ በደል የሌለበት
በማመን ሲሸከም የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙ እየተዘራ
ለሚገርፋት ሁሉ ምህረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ
የሰማነውን ድምፅ ማን ሰው እኮ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጿል
ባየነው ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ
እጁ የታሰረው ይስሀቅ ተፈቶ
ኢየሱስ ቀረበ በሰው ልጆች ፈንታ
ንፁህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀሉን ተጭኖ
በእውነት ደዌያችንን እርሱ ተሰቀለ
በሰው ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነው እንደ ወንጀለኛ
ስለ እኛ ቢሰቀል ሰማያዊው ዳኛ
ለሰው ልጆች ህይወት የታሰበውን ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንፁህ በግ በአርምሞይነዳል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጥቅምት ፳፯ በዚህች ዕለት የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባ መባዓጽዮን መታሰቢያ ነው።
አቡነ መብዓጽዮን ለቸሩ አምላካችን ለመድኃኔ ዓለም ባላቸው ጽኑዕ ፍቅር የሚታወቁ ግሩም አባት ናቸው። ገና ልጅ እያሉ ሥዕለ አድኅኖ ተለይቷቸው አያውቅም። የመድኃኒታችንን ጽኑዕ መከራ በማሰብ በራሳቸው ላይ ያላደረጉት ምን አለ? ችንጋሮችን ራሳቸው ላይ ይቸነክሩ ነበር፣ ድንጋይ ተሸክመው ብዙ ይሰግዱና ከልቅሶ ጋር ይጸልዩ ነበር፣ ሥጋቸውንም በጽኑዕ ቅጣት ይቀጡት ነበር።
ጌታችንን ይወዱትም ስለነበር በቅዱስ ስሙ ዝክር ይዘክሩ ነበር። ዝክራቸውም በንጽሕና የኾነ ነበርና ከዚያ ዝክራቸው የቀመሰ ኹሉ ካለበት ደዌ ይፈወሳል።
ጌታችንም የሚያስደንቁ ቃልኪዳናትን የገባላቸውና በዚህች እለት ብዙ ነፍሳትን ከሲዖል ያወጡበትም እለት ነው።
ዕረፍታቸውም ከጌታችን ዕረፍት ጋራ አንድ እምደሚኾንላቸው ተነግሯቸው ነበር። ከጽኑዕ ገድልም በኋላ በዚህች ቡርክት ቀን ዐርፈዋል።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በአባታችን በአባ መባዓ ጽዮን ጸሎት ይማረን !
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ገሊላ_እትዊ
እመቤቴ እሰከ መቼ
በባዕደ ሀገር ትኖርያለሽ /2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሐገርሽ ገሊላ ግቢ/2/
ገሊላ እትዊ/4/ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ
ሰደቱ ይበቃሽል ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቱልብሉ ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነገሮሽል ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰርገላ ገሊላ እትዊ
ዑራኤል የምራሻል ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
የዝናቡን ጌታ ገሊላ እትዊ
እናቱ ሁነሽ ሳለ ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰው አደሩ ገሊላ እትዊ
ውሃ ጥም ፅንቶብሽ ገሊላ እትዊ
አፈሽ ደርቁ ዋል ገሊላ እትዊ
ይብቃል እናቴ ገሊላ እትዊ
ርሀብ ጥማትሽ ገሊላ እትዊ
ሂጅ ወደ ገሊላ ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመድችሽ ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
የሰማዕታት ገሊላ እትዊ
የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ
ባርክሽ ሰጠሽቸው ገሊላ እትዊ
መክራን ሰድት ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደገን ገሊላ እትዊ
የአንቺው ብርክት ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/
ገፃሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ ገሊላ እትዊ
እግዚትነ ማርያም ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ ገሊላ እትዊ
መክራ ስቃይ ገሊላ እትዊ
ሐገርኪ ገሊላ እትዊ /2/
ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/
ዘማሪ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
"እኔም ይመለከተኛል"
ታላቅ አገልግሎት የማስፋት ዘመቻ
እንደምን አላችሁ የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እና ተከታታዮች።
የዝማሬ ዳዊት ቻናላችን ለ5 ዓመታት ከእናንተ ጋር ሲያገለግል እና ቃለ እግዚአብሔርን ሲያስተላልፍ እንደነበር ይታወቃል።
ከቅርብ ግዜ ጀምሮ ደግሞ በዩቲዩብ ላይም ኦርቶዶክሳዊያንን ያማከለ ትምህርት በቪድዮ ስንሰጥ ቆይተናል።
አሁንም በእዚህ በጥቅምት ወር የዩቲዩብ ቻናሉን በአዳዲስ ርዕሶች ትምህርት ልንጀምር ስለሆነ ይህን አገልግሎት የማስፋት ዘመቻ መሳተፍ የእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የውዴታ ግዴታ ነው።
💻የዩቲዩብ ዘመቻ🖥
በሚል ርዕስ የዩቲዩባችንን አባላት ለማሳደግ እና ሰብስክራይበር ለመጨመር ሥራ ስለጀመርን።
ሁላችሁም ይህ ቻናላችን ወደ ተሻለ እድገት እንዲደርስ እና ቃለ እግዚአብሔርም በስፋት እንዲዳረስ አንድ አሻራ ሁላችንም እናሳርፍ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://bit.ly/2O1Z3d8
https://bit.ly/2O1Z3d8
https://bit.ly/2O1Z3d8
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ይህንን ሊንክ በመጫን ወደ ዩቲዩባችን ገጽ ትገባላችሁ ከእዛም ሰብስክራይብ(Subscribe) በማድረግ ቪድዮዎቹን እንድታዩ እና የዘመቻው አንድ አካል እንድትሆኑ እንጠይቃለን።
"እኔም ይመለከተኛል"
እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎታችንን ይባርክ✝
#የቀጠለ
ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ለተራራው ፍቅር አደረባቸው፤ አለቀሱም፡፡ በዚህም ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ዳግመኛ መጥቶ ‹‹አረጋዊ ሆይ አይዞህ! አትፍራ ስልጣን ተሰጥቶሃልና፡፡ በሐረጓ በስተቀኝ በኩል ባለችው ቦታ ተቀመጥ፤ ወደ ተራራው ጫፍ ያወጣህ ዘንድ በገመድ ፋንታ ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ታላቅ ዘንዶ እግዚአብሔር ይልክልሃል›› አለው፡፡ ከዚያም በጾም በጸሎት ሁለት ሱባኤ ይዘው ፲፬ ቀን በዚያ ተቀመጡ፡፡ የታዘዘውም ዘንዶ በሦስት ሰዓት መጣ፤ በዘንዶው ጅራት ላይ ወጥቶ በቅጽበት ከተቀደሰው ተራራ ጫፍ ላይ ደረሰ፤ እንደደረሰም ሦስት ጊዜ ሰገደ። ወዲያው ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ›› እያለ አመሰገነ፡፡ ስለዚህም ቦታው ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሎ ተሠየመ፡፡ በመሸም ጊዜ አነስተኛ ዳቦ አንስቶ ባርኮ መብላት ጀመረ፡፡ ዳቦዋ ግማሽ ስትሆን ስለጠገበ የዳቦውን ግማሽ አምሳል ለኋለኛው ትውልድ ምልክት ትሆን ዘንድ እንጨት ጠርቦ/ቀርጾ/ አስቀመጠ፤ ይህች ምልክት እስከዛሬ ድረስ አለች፡፡
ደቀ መዛሙርቱም ከታች ወደ ላይ የሚወጡበትን መሰላል በሠሩ አባታችን አቡነ አረጋዊ ደግሞ መጠነኛ ቤት ሠራና ይዞት የመጣውን ታቦት በውስጡ አስገባ፡፡ እግዚአብሔርንም ስለቁርባኑ ወይም ስለመሥዋዕቱ ለመኑ፡፡ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ መላእክት ከሰማይ ይዘውላቸው ወረዱ፡፡ ለመኖሪያቸውም ትንሽ በአት አገኙ፡፡ ያለምንም መኝታ በጸሎትና በስግደት በመትጋት ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ተአምራትን አደረጉ፤ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሠቃዩትን በጸሎታቸው ኃይል ፈወሷቸው፤ ያላመኑትን ደግሞ እያስተማሩ አሳመኗቸው፤ ለዚያችም ሀገር ብርሃን አበሩላት።
አፄ ካሌብም ‹‹አባቴ ሆይ! በጸሎትህ አስበኝ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለች፤ ኃይልም ታሰጣለች፤ በጠላት ላይም ድልን ታቀዳጃለች›› ብሎ አቡነ አረጋዊን ለመኗቸው፤ ወደ ደቡብ በሄደም ጊዜ የመን ከሠራዊቱ ጋር ዘምተው አሸንፈው ተመለሱ። የአፄ ካሌብ ልጅ ገብረ መስቀል ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው። በውስጡም በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም የተሰየመች በወርቅና በብር ያጌጠች ታቦት አስገባ፡፡ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ከተራራው ላይ ሲወርድ ለቤተክርስቲያኑ ማሠሪያ የሆነውን መወጣጫ መሰላል ‹ላፍርሰው› ብሎ አባታችንን ጠየቀ፤ አባታችንም ‹‹አዎ! አፍርሰው፤ አትትወው፤ ነገር ግን ስለዘንዶው ጅራት ፈንታ ሰዎች ይወጡበት ዘንድ ገመድ አብጅ›› አለው፡፡ ንጉሡም አባታችን አቡነ አረጋዊ እንዳዘዘው አደረገ፤ያም ቦታ ደብረ ደኃምሞ ተብሎ ተሰየመ።
ከዚህ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ‹‹ከድካም ወደ ዕረፍት፣ ከኃዘን ደስታ ወዳለበት፣ ከኀሣር ወደ ክብር ቦታ በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ፡፡ የሞት ጥላ አያርፍብህም፤ መልአከ ሞትም ሊያስደነግጥህ አይችልም፤ እንደ ነቢያት ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ አረገ፡፡
አባታችን አቡነ አረጋዊ ማትያስ ለተባለው ደቀ መዛሙር ጌታችን ተገልጦ የሰጣቸውን ቃል ኪዳንና ይህ መጽሐፍ ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነገሩት፤ (መዝ ፻፲፩/፻፲፪፥፮) ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቶቹ በተሰበስቡበትም ሁሉንም ከአስተማሩ በኋላ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም›› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም በመሪር ኃዘን እግራቸው ሥር ወድቀው አለቀሱ፤ አባታችን አቡነ አረጋዊም አጽኗኗቸው፡፡ ጥቅምት ፲፬ ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በ፺፱ ዓመታቸው ተሰወሩ፤ በዚያም ከመቋሚያና ከመስቀል በስተቀር ምንም የተገኘ የለም፡፡
የአባታችን አብነ አረጋዊ ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር! አሜን
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የበረከት ልጆች እንደምን ዋላችሁ።
የፊታችን ህዳር 12/03/15 ወደ አመጓ ጎዞ አዘጋጅተናል በዚህ የበረከት ጉዞ ላይ 4 ገዳማት አድባራትን እንሳለማለን ከነሱም ውስጥ አንደኛው አመጓ ደብረ ቆፕሮስ ኢየሱስ ዑራኤል ገዳም 2 ቀጭን አንባ ማርያም 3 ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም 4 አቡነ ሲኖዳ መቃብራቸው ያለበት ታላቅ የበረከት ቦታ ናቸው።
በዋነኝነት የጎዞው አላማ ቅዱስ ሚካኤል በዓልን እዛው ሰረርኩላ የማክበር ሀሳብ ነው።
ሌላ ደሞ ከእመጓ ወደ ሰረርኩላ ሚካኤል የሚያሻግር ድልድይ ለማሰራት አስበናል በክረምት ወደ ገዳሙ ለመሻገር የአካባቢውም ሰው እንዲሁም ምእመን በጣም ስለተቸገረ እነዚህን በታሪክ ብዙ ዘመን የተሻገሩ ገዳማትን በአንድ ለማገናኘት እንዲሁም የአካባቢው ህዝብ በጣም እየተቸገረ እረጅ መንገድ ተጉዞ ቦታው ላይ እየሄደ እየተሳለመ ስለሆነ የአካባቢውም ህዝብ ለመሳለም ሱባኤ ለመያዝ የሚመጣውም ምእመኑም አድካሚ የሆነውን መንገድ ሰውም ቅዱስ ዑራኤል ለመሳለም ሲመጣ በዛው ጌዜ ሳይወስድበት ተሳልሞ እንዲመለስ ጊዜውን ለማሳጠር ለመሳለም የመጣውም በረከት እንዲያገኝ እንዲሳለም መንገድዋን ተባብረን ብንሰራት እና የሚመጣውም ምእመን ቢያይልን ብለው አባቶች በጠየቁን መሰረት እኛም የልጅነታችንን በማሰብ ቦታው ላይ በዓለ ንግሱን አንግሰን ተባርከን ብንመለስ ብለን አስበናል። ሀሳቡን በማንሳት ጉዞውን ለማዘጋጀት እኛ አስበናል በመንገድ ስራ በኢንጂነሪንግ እውቀቱ ያላችሁ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል በረድኤት በበረከቱ የደረሰላቹ አብራችሁን ሄዳችሁ በአንድ ድንጋይ ሁለት እንዲሉ በረከቱን አግኝታችሁ ቦታውን አይተክ ወይ አይተሽ ይሄን ያህል ሲሚንቶ ብረት ይፈጃል ይሄ ያስፈልጋል ብላችሁ የበኩላችሁን እንድታደርጉልን በአምላከ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስም እንጠይቃለን ።
በተወሰነ ስለቦታው ለማብራራት ልሞክር
ሰረርኩላ ቅዱስ ሚካኤል
በ3 ቅዱሳን ናኦድ እያቄም ናትናኤል የተመሰረተ ታላቅ ቅዱስ ስፍራ ነው ቦታውን የረገጠ 12 ትውልድ ይማርለታል የበረከት ዋሻ አለ የቅዱሳኑን አፅም ለረጅም አመት በውስጡ የያዘ አሁን ወደ መቃኞ ገብቷል ቤተ ክርስትያኑም ተሰርቶ አልቋል ግንቦት 11 በሰላም ያድርሰን መንገዱንም ቤተክርስትያኑንም አንድላይ ለማስመረቅ። አምናለው እንደምንሰራው
ጥያቄ ያላችሁ በጉዞው መሄድ ያሰባችሁ
የጎዞው መነሻ ቀን ህዳር 11
12 ቅዱስ ሚካኤልን አንግሰን
በ 13 መመለሻ
የጎዞ ዋጋ 900 መስተንግዶን ማረፊያን ጨምሮ
መነሻ ሰአት 11 እሁድ
መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ
መገናኛ
አያት አደባባይ
+251991324844 እስጢፋኖስ @Estifo_17
+251921906085 ፍቅር
አዘነች ድንግል አለቀሰች
አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ/፪/
#አዝ
በመንጻቱ ወር በዓርባኛው ቀን
ሥምዖን አረጋዊ ታቀፈ እና ጌታን
ትንቢት ተናገረ ተገልጾለት ሞቱ
በነፍስሽ ሠይፍ ያልፋል አንቺም እናቲቱ
ይኽንን መከራ ሲሠማ ጆሮዋ
አምርራ አለቀሰች አልቆም አለ ዕንባዋ
#አዝ
በአሥራ ሁለት ዓመቱ ለማክበር በዓል
በኢየሩሳሌም ቢገኝ አማኑኤል
ሲጠይቅ ሲሠማ በቤተ መቅደሱ
የኦሪት ካኅናት ሲደነቁ በእርሱ
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብትልጣው ፈልጋ
ልቧ ተሠበረ በሐዘን አለንጋ
#አዝ
ጠዋት በማለዳ በጲላጦስ ደጅ
ሲጸናበት አይታ የጨካኞች እጅ
ርቃኑን አድርገው ያለ አንዳች ጥፋት
ከግንድ ጋር አስረው ጀርባውን ሲገርፉት
እንዴትስ አታለቅስ እንዴት አታነባ
ሲገርፉት ሲያዳፉት ልጇን እንደ ሌባ
#አዝ
የዓለሙን ፈጣሪ የዓለሙን ዳኛ
ንጹሑን ጌታ መሥሏቸው ቀማኛ
እጁን እና እግሮቹን በችንካር ወጥረው
በወንበዴ መሐል ሠቅለውን ብታየው
ድንግል አለቀሰች አልቻለች መጽናናት
ዕንባዋ ወረደ እንደ ክረምት ጅረት
#አዝ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአንድ ሲማከሩ
ቅዱሥ ሐያል ብለድ ገንዘው ሊቀብሩ
በአዲስ መቃብር በአሥራ አንደኛው ሠዓት
ሥጋውን አኑረው በድንጋይ ቢዘጉት
እያለች ዐነባች አንድ ልጄ እኮ ነው
ከእርሱ የሚቀድም ተከታይ የሌለው።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞
✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞
✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ
ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::
7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::
+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::
ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::
ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::
በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::
© ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ
ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ
ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለአባታችን አቡነ አረጋዊ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን! ጥቅምት 14
መምህር ሸዋገኘሁ ከበደ
አባታችን አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ናቸው። ትውልዳቸውም ከሮም ነገሥታት ወገን ሲሆን አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበር፤ እናታቸው እድና ትባላለች፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ የተባረከ ልጅም ወለዱ፤ በሕገ እግዚአብሔርና ቅዱሳት መጻሕፍትን እያነበበ አደጉ፡፡ ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ሚስት ቢታጭላቸውም ከነበራቸው የክርስቶስ ፍቅር የተነሳ ትዳር መመሥረትን ትተው ደውናስ ወደ ምትባል ገዳም ሔዱ፤ በዚያም አባ ጳኩሚስ ይኖሩ ነበር።
አበምኔቱ አባ ጳኩሚስን ልበሰ ምንኩስናን እንዲያለብሳቸው ጠየቁት። አባ ጳኩሚስም ‹ልጄ ሆይ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኩሰህ ለመኖር ይቻልሃልን?› አለው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹አባቴ ሆይ የምድር መንግሥት ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ነገር ግን የማታልፈውንና የማትጠፋውን ዘለዓለማዊት መንግሥት እወርስ ዘንድ እፈልጋለሁ›› አለው፡፡ እናም በ፲፬ ዓመታቸው በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናውን ልብስ ለበሱ፤ በገዳሙም እየተጉ ኖሩ፡፡
ከዚህ በኋላ የጻድቁ ዜና በሀገራቸው ሮም ውስጥ እንዲሁም በመላው ቦታ ተሰማ፡፡ በዚህም የተማረኩት ሰባት ቅዱሳን፤ አባ ሊቃኖስ ከቁስጥንጥንያ፣ አባ ይምአታ ከቆስያ፣ አባ ጽሕማ ከአንጾኪያ፣ አባ ጉባ ከቂልቅያ፣ አባ አፍፄ ከእስያ፣ አባ ጰንጠሌዎን ከሮም፣ አባ አሌፍ ከቂሳርያ እርሱ ወዳለበት ገዳም መጡ። አባ ጳኩሚስ ለብዙ ዓመታት ምንኩስናን ሥርዓተ ማኅበርን አስተማራቸው። እናቱ ንግሥት እድና የልጅዋን ዜና ሰምታ እርሱ ወዳለበት መጥታ መነኮሰች፡፡ በሴቶችም ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች፡፡ መነኮሳቱም አባ ዘሚካኤልን መሪያቸው አደረጉት፤ በአካለ ሥጋ ሕፃን ሆኖ ሳለ የአእምሮውን ብስለት ዐይተው የሕይወት መንገድ ስለመራህን አቡነ አረጋዊ መባል ይገባሃል አሉት፤ በዚህም አቡነ አረጋዊ ተብለው ተጠሩ፤ ብልህ አዋቂ ማለትም ነው፡፡
በገዳመ ዳውናስ ሰባት ዓመት ከቆዩ በኋላ ይስሐቅን (በኋላ አባ ገሪማን) ለመጠየቅ እና የሀገሩን ሰዎች ለማስተማር በአንድነት ሆነው ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ በዘመናቸው የካቶሊክ ሃይማኖት እንዲቀበሉ ጫና ቢደረግባቸውም… ‹‹እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት ማለት ተገቢ ነውና ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት ባሕርይ ነው ብሎ ማስተማር ክሕደት ነው››…. ብለው በድፍረት መቃወም ጀመሩ፡፡ ይሁን እንጂ በኃይል እና በገንዘብ ብዛት የምትመካው የሮማ ቫቲካን ቤተክርስቲያን ቅዱሱን ማሳደድ ጀመረች:: ቅዱሱ አባታችን አቡነ አረጋዊም ‹‹በአንዱ ቦታ መከራ ቢያጸኑባቸው ወደ ሌላው ሽሹ…›› የሚለውን የወንጌል ቃል አብነት በማድረግ እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያን ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር እንዲሆናት በቃል ኪዳን እንደሰጣት ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበቡ በኢትዮጵያ ፍቅር ተያዘ፤ ወደዚያውም መሄድ ፈለገ፡፡ ይህንንም ሁለት ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ለማንም ሳያሳውቅ ቅዱስ ሚካኤል እየመራው ንጉሡና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሰ፡፡
እዚያም ጥቂት ቀን ተቀምጦ ወደ ሮም ተመለሰ፡፡ ስለኢትዮጵያ በዐይኑ የተመለከተውን በጆሮ የሰማውን ሁሉ ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹እኛም ወደዚህች ሀገር መሄድ አለብን›› ተባባሉ፡፡ ያላቸውን የመገልገያ ዕቃ ይዘው ከታቦቶቻቸውና ከካህናቶቻቸው ጋር ንዋየ ቅድሳትና መጻሕፍችን ይዘው ከመሰል ወገኖቻቸው ጋር አባታችን ዘሚካኤል (በአቡነ አረጋዊ) እየመራቸው በአልዓሜዳ አምስተኛ የንግሥና ዓመት በ፬፻፹ ዓ.ም ንጉሡና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሱ፤ ስምንቱ ቅዱሳንም መጡ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ዘጠነኛው አቡነ ይስሓቅ (አቡነ ገሪማ) በሮም ከነገሠ ከሰባት ዓመት በኋላ መንግሥቱን ትቶ ወደ አክሱም መጣ፤ በዚያን ጊዜ እንደነሱ አመነኮሱት፤ ቍጥራቸውም ዘጠኝ ሆነ።
ለሁሉም አንድ የተለየ ማረፊያ ቦታ ቤተ ቀጢን የተባለው ተሰጥቷቸው በጸሎት ተጠምደው ይኖሩ ነበር፤ በአንዲት የጸሎት ቤት በአንድነት ሆነው ለጸሎት ፈጣሪያቸውን እየለመኑ፤ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረጉም ቆዩ፡፡ መላእክት ዘወትር ባለመለየት ያጽኗኗቸው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር ይገለጽላቸው ነበር፡፡ በእያንዳንዳቸውም ብዙ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ከእነርሱ መካከልም ተራራ ያፈለሱ፣ ባሕሩን ከፍለው ደረቅ መንገድ ያደረጉ፣ ስንዴ ዘርተው በቅጽበት ለዘጠኝ ሰዓት መሥዋዕተ ቁርባን ያደረሱ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምድር በእነዚህ የቅዱሳን ኪደተ እግር ተቀደሰች፡፡
በኋላም ንጉሥ አልዓሜዳ ከሞተ በኋላ በነገሠው በታዜና ስድስተኛ ‹‹የንግሥና ዓመት ላይ ተለያይተን እናስተምር›› ብለው ወስነው ተለያዩ። አቡነ ሊቃኖስ ደብረ ቆናጽል፣ አባ ጰንጠሌዎን ከእዚሁ ሁለት ምዕራፍ እልፍ ብሎ ከሚገኝ ኮረብታ፣ አቡነ ይስሐቅ መደራ፣ አቡነ ጉባ በእዚሁ በመደራ ትይዩ ሦስት ምዕራፍ እልፍ ብሎ፣ አባ ጽሕማ፣ አባ ይምዓታ ገርዓልታ፣ አባ አሌፍ አሕስዓ ብሕዛ በተባለችው፣ አባ አፍጼ ይሐ ተሠማሩ።
አባታችንም እናታቸው እና ማትያስ የተባለ ደቀ መዝሙራቸውን ይዘው ከሁሉም ርቀው ወደ መረጡት ቦታ ሲሄዱ ከዛፍ ጥላ ሥር አረፉ፤ እርስዋም እስከ ዛሬ ድረስ የቅዱሳን ማረፊያ ሆና ትገኛለች፡፡ አባታችንም ቅድስት ቦታ ዳሞን ባያት ጊዜ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ በተራራዋ ሥር ለመኖርም ወደደ፡፡ ነገር ግን ወደ ተራራዋ መውጫ አላገኘም፡፡ ተመልሶ ወደ ሌላ ተራራ ሄዶ አማረጠ፤ ሆኖም እንደ ደብረ ዳሞ የበረከት ቦታ ባላገኘ ጊዜ ተመልሰ፡፡ በዚያም የምንጭ ውኃ አገኘ፡፡ ውኃውን እየተንከባከበች የሴት መነኮሳቶችን ታስተዳድር ዘንድ እናቱ ቅድስት እድናን አስቀመጣት፤ ይህችንም ደብረ በአተልሞ አላት፤ ትርጓሜውም የእናቴ ማረፊያ ቤት ማለት ነው፡፡
ከዚያም ሲሄድ ጠፍጣፋ ድንጋይ አገኘና ከዚያ ላይ ትንሽ ምንጣፍ አነጠፈና ተቀመጠ፡፡ በትሩንም በድንጋይዋ ላይ አቆመ፡፡ በተነሳም ጊዜ ደቀ መዝሙሩ ማትያስ በትሩንና ምንጣፉን ሲያነሳው ያች ድንጋይ ቁመቷም ጎኗም ልክ በዚያች ምንጣፍ አይነት ቅርጽ አወጣች፡፡ የቀድሞ መልኳ ነጭ ሲሆን አሁን ግን የማይፋቅና የማይላጥ ቀይ ቀለም ሆኗል፡፡ ስለአባታችን አቡነ አረጋዊ ታላቅነቱና ስለክብሩ ከዚያ የደረሱ ሁሉ ይሳለሟታል፡፡
ከዕለታት በአንደኛው ቀን መንገድ ሲሄድ ውሎ ከተራራ አጠገብ ወደ ታች የተንዠረገገች ሐረግ/ገመድ/ አገኘና በሥሯ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ሲጸልይ ከቆየ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ‹‹እግዚአብሔር ያከበረህ ቅዱስ ሆይ ምን ያስጨንቅሃል?›› አለው፡፡ አባታችንም ‹‹ከዚህ ተራራ ላይ ወጥቼ ስለኃጢአቴ ይቅርታን እጠይቅህ ዘንድ እወዳለሁ›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹ወደ ተራራው የምትወጣበትን እግዚአብሔር እስኪልክልህ ድረስ ጥቂት ጊዜ ታገስ›› አለው፡፡
#ይቀጥላል
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤