#ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን
ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን /2/
ድንበር የሚጠብቁትን /2/
ጠብቅ እግዚአብሔር ሠራዊቷን /4/
የደም መሬት አትሁን ደም አይፍሰስባት
ካንተ የመነጨ ሰላም ይስፈንባት
አሽናፊ እንድትሆን ለስምህ ተገዝታ
አይንህን ሳትመልስ እያት ጠዋት ማታ
#አዝ
ሰንሰለት ሲፀና ለመከራ ፈርቶ
ኢትዮጲያዊ መልኩን አይቀይርም ከቶ
ድንቁን ብርሃን ያያል ወቶ ከጨለማ
በመንገዱ ሁሉ አዳኝ ቀኝ ቀድማ
#አዝ
እጅግ የፈተናት ተነቅሎላት መርዙ
ከእግሮቿ በታች ጠላቶች ይገዙ
ደጅ ስትጠና እጆቿን ዘርግታ
ጠብቅ ሠራዊቿን ዱሩ እንዳይፈታ
#አዝ
ከራሳቸው ይልቅ ኢትዮጵያን ወደዱ
ደም ከፍለው ሊያቆዮት በዱር ተሰደዱ
በሃሩር በውርጩ የሆኗትን አጥር
በማይፋቅ ቀለም ፃፋቸው ለክብር
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#በድንግል_ትህትና
በድንግል ትህትና አለምተደነቀ /2/
እዉነተኛ መጠጥ ከሆዷ ፈለቀ /2/
ሰዉ የሚድንበት ሮማንና ገዉዝ /2/
ከሆዷ ፈለቀ እንደ ምንጭ እንደወንዝ /2/
#አዝ
ፀጋን ስላደላት የመዉለድ ስጦታ/2/
በፍቅር ሳበችው የፍጥረቱን ጌታ /2/
ሰማያዊዉ አምላክ ከእርሷ ሥጋንነሳ /2/
ፀሐይ ስለወጣ ቀረልን አበሣ /2/
#አዝ
እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ እርሷን አያህሉም /2/
#አዝ
እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ ድንግልን አይቀድሙም /2/
#አዝ
እግዚአብሔር ምድርን አየና በመላ /2/
ማርያምን አገኛት ከቤተ-መቅደሱ ከቤቱ ተጥላ
ከመላዕክቱ ጋር እየተጫወተች /2/
የሰማዩን መና እየተመገበች /2/
ሙሉ ዜማው በዚሁ ይወርዳል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም"
"እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰነዋለሁ በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ"
ሥላሴ ትትረመም
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር (፪)
ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ
ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ
ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ
ፍጥረትን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ
አዝ
ልበል ሃሌ ሉያ ኪሩቤልን ልምሰል
በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል
ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል
ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል
አዝ
በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል
በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል
ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት
በባሕሪይ እና ደግሞም በመንግሥት
አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት
አዝ
በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ
ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ
ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ጸንቶ(፪)
አዝ
ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር
የአምላክ ጌትነት የሥላሴን ክብር
ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ
መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ
ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ነይ_አርሴማ_ቅድስት
ነይ አርሴማ ቅድስት ነይ አርሴማ
ነይ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት
አርሴማ (፪) ነይ አርሴማ
አርሴማ ስልሽ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አንድታማልጂኝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካምላክ ፈጣሪሽ ።።።።።።።
በደሌን ጭንቀቴን።።።።።።።።
ልናዘዝልሽ ።።።።።።።።።።።።
ምሪኝ አርሴማ ሆይ።።።።።።።።
እጆቼን ይዘሽ ።።።።።።።።።።።።
ወልዲያ ሲሪንቃ ።።።።።።።።።።።
ልምጣ ከደጅሽ።።።።።።።።።።።።።
#አዝ
እንድታማልጂኝ ነይ አርሴማ
ከንጉስ ከራማ ።።።።።።።።።
ትለምንሻለች ።።።።።።።።።።።
ነብሴ ደጅሽ ቆማ ።።።።።።።።
ወልዲያ ሲሪንቃ ።።።።።።።።።።
ኤዶ ያየሽማ ።።።።።።።።።።።።
ቅዱሱ ዝናሽን ።።።።።።።።።።።።
ገድልሽን የሰማ ።።።።።።።።።።
ጠበልሽ ፈውስ ነው።።።።።።።።
እናቴ አርሴማ።።።።።።።።።።።።
#አዝ
በጉብዝና ወራት ነይ አርሴማ
ፈጣሪህን አስብ።።።።።።።።።
ብሎ እንዳስተማረ።።።።።።።።
በመፃፈ መክብብ።።።።።።።።
ስለ ጌታ እየሱስ።።።።።።።።።
ሰለ አለም መዳኒት።።።።።።።
ስለ ተዋህዶ።።።።።።።።።።።
ስለ ፀናች ዕምነት።።።።።።።።
መከራን ተቀበልሽ።።።።።።።።
በጉብዝናሽ ወራት።።።።።።።።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#በዙሪያችን_ካሉ
በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከፀኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት/2/
ሀብትና ንብረቷን ውበቷን የናቀች
ንግስት መባልን በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ምስክር
የቅድስት አርሴማ ልዩ ነው የሷ ክብር/2/
#አዝ
እግዚአብሄር ፅናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅፅሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሀን ለዓለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለኛ አማላጅ ነች/2/
#አዝ
ይሔው በዚ ዘመን እግዚአብሄር ገለጣት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አደረጋት
አክሊል ተጎናጽፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር/2/
#አዝ
እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ/2/
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ስለ 81 መጽሐፍ ቅዱስ በመረጣችሁት ርዕስ መሠረት። ዛሬ ትምህርታችንን ጀምረናል።
👉ሁላችሁም ትምህርተ ተዋሕዶ አፕሊኬሽኑን ስልካችሁ ላይ ጭናችሁ እየተከታተላችሁን እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን።
ትምህርታችንን ነገ የምንጀምር ስለሆነ ለእህት ወንድሞቻችን ኦርቶዶክሳዊያን የእዚህን ግሩፕ ሊንክ በመላክ እንዲቀላቀሉ እና እንዲማሩ እናድርግ! ዛሬ ማታ በትንሹ 10,000 ሰው ግሩፓችን ውስጥ ገብቶ ትምህርት እንዲማር እናድርግ ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
/channel/+SoivjLkD4oUfYh7H
/channel/+SoivjLkD4oUfYh7H
🎬 🛑 በ2 ደቂቃ አጠር ብሎ የተዘጋጀ "ውርጃ - Abortion" - በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/X0uKajkKzM4
https://youtu.be/X0uKajkKzM4
ታኅሣሥ ፩ (1)
እንኳን ለታላቁ ነቢይ "ቅዱስ ኤልያስ" :
"ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ" እና "ቅድስት ቤርሳቤህ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#ታላቁ_ቅዱስ_ኤልያስ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ቀጥላ ቅዱስ ኤልያስን ታከብራለች:: "ርዕሰ ነቢያት - የነቢያት ራስም" ትለዋለች:: እርሱ ሰማይን የለጐመ: እሳትን ያዘነመ: ፍጥረትንም በቃሉ ያዘዘ አባት ነውና:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቅዱሱ ትውልዱ (ነገዱ) ኢዮርብዓም ነጥሎ ከወሰዳቸው እሥራኤል (10ሩ ነገድ) ሲሆን አባቱ "ኢያስኑዩ" : እናቱ ደግሞ "ቶና (ቶናህ)" ይባላሉ:: በጐ አምልኮ ነበራቸውና እግዚአብሔር ማሕጸነ ቶናህን ቀድሶ ይህንን ቅዱስ ፍሬ ፈጠረ::
ቅዱስ ኤልያስ በተወለደ ቀን በቤታቸው ብርሃን ተሞልቶ ታይቷል:: ብርሃን የለበሱ 4 ሰዎች (መላእክት) መጥተውም በእሳት ሰፋድል (መጐናጸፊያ) ሲጠቀልሉት ወላጆቹ በማየታቸው ደንግጠው ለነቢያትና ለካህናት ነገሯቸው::
ካህናቱ ግን ነገሩ ቢረቅባቸው "ምን ዓይነት ፍጥረት ይሆን? በእሥራኤል ይነግሥ ይሆን! ወይስ ነቢይ ይሆን?" ብለውም አድንቀዋል:: ቅዱስ ኤልያስ ከልጅነቱ ጀምሮ ኮስታራ: ቁም ነገረኛ: ንጽሕናንም የሚወድ እሥራኤላዊ ነው::
ወቅቱ (ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት) ሕዝቡና ነገሥታቱ የከፉበት: እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት የሚመለክበት ነበር:: ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት ጣዖታት (ዳጐንና ቤል) በዚያ ዘመን ወደ እሥራኤል ገብተው ነበር::
ቅዱስ ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ: የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር::
በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው:: እርሱም "እሺ" ብሎ ታዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ ተቀበለ::
ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል: ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር አደረገ::
+በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር:: በዚህ ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ:-
1. ለድንግልና (ድንግል ነበርና)
2. ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና)
3. ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን የጣለ ነቢይ ይባላል::
መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን: በዘመነ ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን: በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ አልነበረም:: በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ ክፉ ባልና ሚስት በእሥራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን ጣዖት አስመለኩት::
ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሃሰት ምስክር ደሙን አፈሰሱት:: ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም: አልለውጥም::" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::
ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ ዠ አክአብና ኤልዛቤል ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም:: የአንቺንም ደም ውሻ ይልሰዋል" አላቸው:: በዚህ ምክንያትም ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም::
በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች:: 900ው ሲታረዱ አንድ መቶውን ግን ቅዱስ አብድዩ በዋሻ ውስጥ ደብቆ እየመገበ አተረፋቸው:: በእሥራኤል ውስጥ ግን ዓመጻና ኃጢአት እየተስፋፋ ሔደ:: የእግዚአብሔርን ስጦታ እየተመገበ ሕዝቡ ለቤል (ለበዓል) ሰገደ::
ይህን ጊዜ ግን ቅዱስ ኤልያስ እንዲህ አለ:- "ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ በቃለ አፉየ::" ብሎ ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ ከለከለ::
ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት ተከለከለ::
ሕዝቡ በኃጢአቱ ምክንያት ተጐዳ:: እርሱን ቁራ ይመግበው: ምንጭ ፈልቆለት ይጠጣ ነበር:: ይሔው ቢቀርበት ጸለየ:: እግዚአብሔርም ከፈለገ ኮራት ወደ ሰራፕታ እንዲወርድ አዘዘው:: በዚያም የነቢዩ ዮናስ እናት እንጐቻ ጋግራ ብታበላው ቤቷ በበረከት ተሞላ::
ልጇ ሕጻኑ ዮናስ ቢሞትም በጸሎቱ አስነሳላት:: ቀጥሎም 7 ጊዜ በትጋት ጸልዮ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የዘጋውን ሰማይ ከፍቶታል:: ሕዝቡም ዕለቱኑ ከበረከቱ ቀምሰዋል::
ከዚያ አስቀድሞ ግን ከኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖት ጋር ተወዳድሮ አሸንፏቸዋል:: መስዋዕት ሰውተው የእርሱን ብቻ እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታለታለችና ሕዝቡ 850ውን ሐሰተኛ ነቢያት በወንዝ ዳር በሰይፍ መትተዋቸዋል::
ይሕንን የሰማች ኤልዛቤልም ትገድለው ዘንድ አሳደደችው:: "አቤቱ ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ! ብቻየን ቀርቻለሁና" ብሎ ቢጸልይ እግዚአብሔር ለጣዖት ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን እንዳተረፈ: እርሱንም ወደ ብሔረ ሕያዋን እንደሚወስደው ብሥራትን ነገረው::
ደክሞት ተኝቶ ሳለም ቅዱስ መልአክ (ሚካኤል) ቀስቅሶ ታየው:: እንጐቻ ባገልግል: ውሃ በመንቀል አቅርቦ "ብላ! ጠጣ!" አለው:: በላ: ጠጣ: ተኛ:: እንደ ገና ቀስቅሶ አበላው:: በ3ኛው ግን "ብላዕ እስከ ትጸግብ እስመ ርሑቅ ፍኖትከ - ጐዳናህ ሩቅ ነውና እስክትጠግብ ብላ" አለው::
ኤልያስም ለ40 ቀናት ያለ ምግብ ተጉዟል:: ከዚያ በሁዋላም ምድራዊ ሕብስትን አልተመገበም:: እግዚአብሔር አክአብና ኤልዛቤልን ከተበቀላቸው በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስ በክፋተኞች ላይ 2 ጊዜ እሳትን አዝንሟል::
የሚያርግበት ጊዜ ሲደርስም ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን "የምትሻውን ለምነኝ" ቢለው "እጥፍ መንፈስህን" አለው:: 3 ጊዜ ሊያስመልሰው ሞከረ:: ቅዱስ ኤልሳዕ ግን በብርታት ተከተለው:: ዮርዳኖስን ከፍለው ከተሻገሩ በሁዋላ ግን ቅዱስ ኤልያስን ሠረገላ እሳት ወርዶ ነጠቀው:: ለኤልሳዕም እኩሉን ግምጃውን ጣለለት::
ዛሬ ቅዱስ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለ ሲሆን በዘመነ ሐሳዌ መሲሕ መጥቶ በሰማዕትነት ከቅዱስ ሔኖክ ጋር ያርፋል:: (ራዕይ)
¤ ለተጨማሪ ንባብ ( ከ1ነገ. 17-2ነገ. 2, እና ዕርገተ ኤልያስን ያንብቡ::)
<<ነቢዩ ኤልያስ በእውነት ታላቅ ነው!>>
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ሰማዕት
ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት (የሰማዕታት መጨረሻ)" በሚለው ስሙ ነው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ጴጥሮስ" አለችው::
ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ጴጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::
ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::
አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ጵጵስናው ላይ አልተቀመጠም:: በኋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::
ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ጴጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::
ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ? አሜን የቅዱሳን አምላክ የእግዚአብሔር ስም የተከበረና የተመሰገነ ይሁን! እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ተከታታይ ትምህርት ልንሰጥ አስበናል በመሆኑም መማር የምትፈልጉትን ትምህርት በእናንተ ፍላጎት እንዲሆን ምርጫውን ለእናንተው ትተናል። ከስር ከተዘረዘሩት የትምህርት ርዕስ አንዱን ይምረጡ። አምላከ ቅዱሳን በምሕረቱ ይቅረበን።
anonymous poll
81 መጽሐፍ ቅዱስ – 798
👍👍👍👍👍👍👍 38%
አምስቱ አእማደ ምሥጢራት – 423
👍👍👍👍 20%
ነገረ ማርያም – 379
👍👍👍 18%
ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን – 269
👍👍 13%
ነገረ ቅዱሳን – 133
👍 6%
ነገረ መላእክት – 108
👍 5%
👥 2110 people voted so far.
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
#ኅዳር ፳፮
#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ_ዘሐይቅ
እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::
እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::
ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::
አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት: የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::
በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::
በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::
ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::
በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::
ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::
ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::
እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::
ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል::
<<ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው!!>>
ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰንበት
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡
ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10)፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡
ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-
👉 እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
👉 ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
👉 ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
👉 የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያገኙባት ዕለት
👉 ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት(1ኛ ቆሮ 16፤1)
👉 የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7 በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት
ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡
ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር። (ራዕ 1፡10)
በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)
ከሰንበት ረድኤት በረከት ይካፍለን!
ሌሎች እህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🎬 🛑 |ክፍል 1| ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66??? እጃችን ላይ የያዝነውስ ባለ ስንቱን ነው??? ልታደምጡት ይገባል
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/Iggo8ws7quM
https://youtu.be/Iggo8ws7quM
በመጽሐፍ ቅዱስ ዙርያ በተማማርነው መሰረት ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት የጥያቄ እና መልስ ፕሮግራም ይሆረናል። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን!
Читать полностью…ቅድስት ሥላሴ
ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው?
◉ አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም።
◉ አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ።
◉ አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ።
ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ በማለት ያመሰጥራል። ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን።
◉ አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም ቅድስት ይባላሉ።
◎ አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም። ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ።
◎ ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት እንላቸዋለን።
◉ አኔድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ ቅድስት ይባላሉ ።
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን!
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#ተባረኩኝ_ጠራኝ_ጸሎቷ
ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ
ልሳለማት ልሂድ እቤቷ
ፍቅሯ ልዩነው ደግነቷ
እናቴ አርሴማ ሰማእቷ
እግሩ ያነከሰ ክንዱ የዛለበት
ደስታ የራቀው ሰው ህመም የጸናበት
ልቡ የደከመ መንገድ የጠፋበት
አፍሮ አይመለስም ደጅሽ የመጣለት
#አዝ ------
ያንሁሉ ቁልቁለት ያንሁሉ ጋራ
እንዴት ልጓዝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ድረሽልኝ ብዬ ላንቺ ስናገር
እንደእንቦሳ ጥጃ እዘለው ጀመር
#አዝ ------
ላይድን መችይመጣል ላይለቀው ችግሩ
አንቺስ መችልጠሪው ሲነሳ ከክብሩ
አቤት ቃል-ኪዳንሽ እንዴት ይገለፃል
አምኖ የመጣ ሰው ድኖ ተመልሶል
#አዝ ------
የውስጥ ደዌውን ህመሙን ደብቆ
ገስግሶ የመጣ ካለሽበት ዘልቆ
ድኖ ተመለሰ ዝናሽን አሰማ
ሰማቷ እናቴ እያለሽ አርሴማ
#አዝ ------
አንደበትን ስጪኝ እመሰክራለው
በሶስት ፍሬቆሎ ስታድኚ እያየው
ነግሬሽ ነበረ ችግሬን በሙሉ
አላሳፈርሽኝም ተፈታልኝ ሁሉም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ታህሳስ 6
ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)
✝እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።
✝መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና።"(ማቴ. ፭፥፲፩) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት። ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት።
ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦ ፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት ፪.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት ፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት። ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት።
✝መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር። ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስን ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ። በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ። በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም።
ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው። ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ፤ አይሆንም።" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዓይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው። አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፣ አሰቃያት፣ ዓይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት። ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው።
✝የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራእይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም።" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት። ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም።
ለአሥራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው። የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል። ለዚህም ነው ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት።
✝በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ ስባ ውስጥ የሚገኝ ነው።) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና። ነገር ግን ወንድሞቼና እኅቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ። የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን። አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና።" (መዝ. ፸፭፥፭) በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል። ይህች እናት እመ ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጐኗም ትቆምላት ነበር።
✝ ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች። ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ያጋሩ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝
🌹የዝማሬ ዳዊት ቻናል ተከታታይ ትምህርት መርኀ ግብራት እና መመሪያ ህግ🌹
መንፈሳዊ ሠላምታችንን በቅድሚያ እያቀረብን እንደ አምላካችን መልካም በእዚህ ሳምንት እናንተ በመረጣችሁት ርዕስ ለተከታታይ ሳምንታት መንፈሳዊ ትምህርት የምንማር ሲሆን የተመረጡት ርዕሶች በቅደም ተከተል፦
👉81 መጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ
👉አምስቱ አእማደ ምሥጢራት
👉ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን
👉ነገረ ማርያም
👉ነገረ መላእክት
👉ነገረ ቅዱሳን እነዚህ ሲሆን
👉ቅዳሴ
🤲ትምህርታችንን የምንማርበት ቀናት (ሰኞ፣እሮብ እና አርብ) ናቸው።
በእነዚህ የትምህርት ቀናት ከቻናሉ አባላት ምን ይጠበቃል
1. ትምህርተ ተዋሕዶ የሚባል አፕሊኬሽን ስላለ እርሱን ስልካችን ላይ መጫን።
2. የምንልክላችሁን የትምህርት ርዕሶች እኛ ማብራሪያ ከመስጠታችን በፊት አፕሊኬሽኑ ላይ በመግባት አንብባችሁ ትጠብቁናላችሁ።
3. ስልካችሁ Android ያልሆነ እና Iphone የሆነ ካለ አፕሊኬሽኑ ስለማይሰራላችሁ ፎቶ አንስተን እንልካለን።
4. ካነበባችሁ በኋላ ጽሑፉን እኛ ማጠቃለያ የምንሰጥ ሲሆን ጥያቄ ካላችሁ በእዚህ የቻናላችን Bot በመግባት ጥያቄ ወይም አስተያየት መስጠት @zmaredawit_messengerbot
5. የተመረጡትን ርዕሶች እንደ ጨረስን ፈተና የሚኖር ሲሆን ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ እንድትፈተኑ ይጠበቃል።
መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልን ምሥጢር ሰማያዊን ቸሩ አምላክ ይግለጽልን
ታህሳስ 3
በአታ ለማርያም እመቤታችን በሶስት አመቷ ቤተመቅደስ የገባችበት ቀን
ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም።" በሚል ይናቁ ነበር። ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት - ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ።
እነርሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም። የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን፣ እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች። ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ።
በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ። እርሱ፦ ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ በማኅጸኗ ስትደርስ አየ። እርሷ ደግሞ፦ የኢያቄም በትር አብቦ፣ አፍርቶ፣ ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን።" አሉ። ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ።
በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ ፯) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ። "ዓለም የሚድንባት የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ።" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች።
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ..... ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም።" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም)
"ለጽንሰትኪ በከርሥ እንበለ አበሳ ወርኩስ ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ..... ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው። የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።....." (መጽሐፈ ሰዓታት ፣ ኢሳ. ፩፥፱)
"ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ። ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን። ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን፤ (ወለደች - አስገኘችልን።)" የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል፤ ተመስግነዋል። ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኳ መሆን የማይችል የሰማይና የምድር ንግሥት የእግዚአብሔርን እናት እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን። ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ። ቅዱሳኑ እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ጸልየዋል።
ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል። እመቤታችን ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን ተወልዳለች። ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች።
(ኢሳ. ፩፥፱) የእመቤታችን የዘር ሐረግ፦ አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ በእናቷ፦ ሌዊ- ቀዓት- እንበረም- አሮን- ቴክታና በጥሪቃ- ሔኤሜን- ዴርዴን- ቶና- ሲካር- ሔርሜላና ማጣት- ሐና።
በአባቷ በኩል፦ ይሁዳ- ፋሬስ- ሰልሞን- ቦኤዝ- እሴይ- ዳዊት- ሰሎሞን- ሕዝቅያስ- ዘሩባቤል- አልዓዛር- ቅስራ- ኢያቄም ይሆናል። ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች።
ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ድንግል እመ ብርሃንን ከወለዱ በኋላ ለሦስት ዓመታት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ፣ ነዳያንንም ሲጠግኑ ኖሩ። በእነዚህ ዓመታትም ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከእቅፏ አውርዳት አታውቅም። ቅዱሳን መላእክትም ዘወትር እየመጡ ያጫውቷት ይንከባከቧትም ነበር።
ሦስት ዓመት በሞላት ጊዜም በቅድስት ሐና አሳሳቢነት ብጽዓታቸውን (ስዕለታቸውን) ይፈጽሙ ዘንድ ተዘጋጁ። እንደ ሥርዓቱ የሚዘጋጀውን (መባውን) ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሲደርሱ አበው ካህናትና የመቅደሱ አገልጋዮች ሁሉ ሊቀበሏቸው ወጡ። ሕዝቡ፣ ሊቃነ ካህናት ቅዱሳን ዘካርያስና ስምዖን፣ ኢያቄም ወሐና ከድንግል ማርያም ጋር ቆመው ሳሉም ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ከሰማይ ወርዶ ረቦ ታየ።
ከቅዱስ ዘካርያስ ጀምሮ ሁሉም ሰው ሕብስትና ጽዋዑን ለመቀበል ቀረበ፤ ግን መልአኩ ራቀ። ድንግል ማርያም በቀረበች ጊዜ ግን ከመሬት አፈፍ አድርጐ አንስቶ ክንፉን ጋርዶ ሰማያዊውን ማዕድ መገባት። በዚህ ደስ የተሰኙ ካህናትና ሕዝቡ እየዘመሩ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል። አማናዊት መቅደሰ መለኮት ድንግል ማርያም ወደ ኦሪቱ ቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ጸሎታችን እንድትሰማን እንደ ሊቃውንቱ፦ "ማርያም አንቲ ሰዋስው ዘምድረ ሎዛ ዲቤኪ ትዕርግ ጸሎትየ ከመ ጼና ሠናይ መዓዛ ኀበ ለነፍስየ ታሰስል ትካዛ።" እንላለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ቅዱስ_ቀሌምንጦስ_ዘሮም
የዚህ ቅዱስ ሐዋርያ ስሙ እንደ ምን ያምር! እንደ ምንስ ይከብር! ለቤተ ክርስቲያን ትልቁ ድልድዩዋ ነውና:: ቅዱስ ቀሌምንጦስ የቅዱስ ቀውስጦስና የቅድስት አክሮስያ ልጅ ሲሆን ወንድምም ነበረው::
አባትና እናቱም የሮም መሳፍንት: በስብከተ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ያመኑ: ገንዘባቸውን በምጽዋት የጨረሱ የመጀመሪያዎቹ የሮም ክርስቲያኖች ናቸው:: ልጆቻቸው (ቀሌምንጦስና ወንድሙ) በመርዝ ቢሞቱባቸው በአምላከ ጴጥሮስ ተማጽነው ተነስተውላቸዋል::
አንድ ጊዜ ቀውስጦስ በሌለበት አንድ ሰው አክሮስያን ስላስቸገራት ልጆቿን ይዛ ተሰዳለች:: በመንገድም መርከባቸው ተሰብሮ ቅዱስ ቀሌምንጦስ በስባሪው ግብጽ ደርሷል:: በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስን አግኝቶት የሊቀ ሐዋርያት ደቀ መዝሙሩ ሆኗል::
ቅዱስ ጴጥሮስንም ተከትሎ ለአገልግሎት ብዙ አሕጉራትን ዙሯል:: ብዙ ምሥጢራትንም ተካፍሏል:: የቅዱሳን ሐዋርያትን ዜናም ከቅዱስ ሉቃስ (ግብረ ሐዋርያት) ቀጥሎ የጻፈ እርሱ ነው::
ቅዱሳን ሐዋርያት ሙሉ ቀኖናቸውን ለቅዱስ ቀሌምንጦስ ሲሰጡት ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ሰብአ ሰገል ለክርስቶስ ያመጡትን ወርቅ: እጣን: ከርቤውን አስረክቦታል:: በተለይ ሁሉም ሐዋርያት ባረፉ ጊዜ እርሱ ቤተ ክርስቲያንን ተረከበ:: በሮም ሁለተኛው ፓትርያርክ ሆነ::
በጊዜው መጽሐፈ ቅዳሴ ባለ መደራጀቱ ሥጋውን ደሙን ሲፈትቱ ፈጣሪ እንዳመለከታቸው ይጸልዩ ነበር:: ቅዱሱ ግን የጌታንና የሐዋርያትን ቅዳሴ ዛሬ በምናየው መንገድ አደራጅቶ ጽፎታል:: በስሙ የሚጠራና "ቀሌምንጦስ" የሚባል መጽሐፉም (8 ክፍሎች አሉት) ከ81ዱ (አሥራው) መጻሕፍት ተቆጥሮ ለታል::
ቅዱሱ ሐዋርያ እንዲህ ሲመላለስ ኖሮ በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በጠራብሎስ እጅ ወደቀ:: ንጉሡም "ክርስትናን አስተምረሃል" በሚል ብዙ አሰቃይቶ: ከትልቅ ድንጋይ ጋር አስሮ ባሕር ውስጥ አስጥሞታል:: በዚህም ዐርፏል::
ሁሌ ግን በዓመት በዓመት ባሕሩ እየተከፈለላቸው: ምዕመናን እየገቡ ከቅዱስ አካሉ ይባረካሉ:: ቅዱሱን ብዙ ጊዜ "ቀሌምንጦስ ዘሮም" የምንለው "ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ" የሚባል መናፍቅ ስላለ ከእርሱ ለመለየት ነው::
የቅዱሱ ክብር በእውነት ታላቅ ነው!
አምላከ ሐዋርያት ወሰማዕት በመከራቸው ከመከራ ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
#ኅዳር 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን ሰማዕታተ ክርስቶስ (ሁሉም)
2.ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
3.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ (ዘሮም)
#ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
2.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
3.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊት
4.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
5.ቅድስት አርሴማ ድንግል
"አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ::
የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ::
ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት::
የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች አደረጉ::
የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት::
ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ::
የሚቀብራቸውም አጡ::"
(መዝ. ፸፰፥፩)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለአእላፍ ሰማዕታት: ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
#ቅዱሳን_ሰማዕታት
ቤተ ክርስቲያን ዛሬ (ኅዳር 29) የሁሉንም ሰማዕታት በዓል ታከብራለች:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቅዱሱ ሊቅ) በመጽሐፈ ሰዓታት ሰማዕታትን:-
"መስተጋድላን ከዋክብት ብሩሃን::
ማኅትዊሃ ለቤተ ክርስቲያን::" ይላቸዋል::
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ:- ፋሲለደስ: ገላውዴዎስ: ፊቅጦር: መቃርስ: አባዲር: ቴዎድሮስ (ሦስቱም): አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::
ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ: ሶፍያ: ኢራኢ: ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ (ሞተ)::
የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::
በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪጳዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪጳዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::
ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::
ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ከሃዲውም ይህንን ሲያይ የልብ ልብ ተሰማው:: ከድሮ ያሰበውንና ክርስቲያኖችን የማጥፋቱን እቅድ ሊፈጽም ምክንያት አገኘ::
አባ አጋግዮስ በሚባል መነኩሴ ምክንያት "አብያተ ክርስቲያናት ይትዐጸዋ: አብያተ ጣዖታት ይትረኀዋ - ቤተ ክርስቲያኖች ይዘጉ: ቤተ ጣዖቶችም ይከፈቱ" አለ:: አጵሎን: አርዳሚስ የሚባሉ ጣዖቶችንም አቆመ::
በዚህ አዋጅ ምክንያትም የክርስቲያኖች ሰቆቃ ጀመረ::
ምድር በደም ታጠበች::
ቅዱሳኑ ቀባሪ አጡ::
እኩሉ ተገደለ:: እኩሉ ተቃጠለ:: እኩሉ ታሠረ:: እኩሉም ተሰደደ::
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተጻፈው በብራናና በብዕር አይደለም:: ይልቁኑ እንደ ቀለም የሰማዕታት ደማቸው: እንደ ብዕር አጥንታቸው: ቆዳቸው እንደ ብራና ሆኖ ተጽፏል እንጂ:: ሰማዕታት ለሃይማኖታቸው የከፈሉት ዋጋ እጅግ ታላቅ ነው::
ስለዚህም "ተጋዳዮች: የሚያበሩ ኮከቦች: የቤተ ክርስቲያን ሻማዎች" ተብለው: እነሱ እየቀለጡ አብርተዋል:: ሰማዕትነት በብሉይ ኪዳን የጀመረና እስከ ዳግም ምጽዐተ ክርስቶስም የሚቀጥል ቢሆንም "ዘመነ ሰማዕታት" የሚባለው ከ150 እስከ 312 ዓ/ም ድረስ ያለው ዘመን ነው::
በተለይ ግን ከ270ዎቹ እስከ 312 ዓ/ም ድረስ ያሉ ዓመታት እጅግ የከፉ ነበሩና: የአርባ ሰባት ሚሊየን (47,000,000) ክርስቲያኖች ደም በምድር ላይ ፈሷል:: የሰማዕታት ምሥጢራቸው ቃለ ወንጌል: የጌታ ስብከትና ሕይወት እንጂ ሌላ አይደለም:: (ማቴ. 10:16, ማር. 13:9, ሉቃ. 12:4, ዮሐ. 16:1, ሮሜ. 8:35, ራዕይ. 2:9)
የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳሳት ነው::
ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#አቡነ_ሃብተ_ማርያም_ጻድቅ
እኒህ ጻድቅ ደግሞ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::
ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ: እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ: ምጽዋትን ወዳጅ: ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::
ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::
ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::
የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::
ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::
ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::
በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)
በ40 ቀናት: ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)
ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ: ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::
በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን: መከፋትን አላሳደሩም::
በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::
"ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"
"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::
ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት::
#የናግራን_ሰማዕታት
በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ናግራን (የአሁኗ የመን) የክርስቲያኖች ሃገር ነበረች:: የሳባ ግዛትን የእኛ ነገሥታት ሲተዋት የተተካው ፊንሐስ ደግሞ ጨካኝ አይሁዳዊ ነበርና ናግራንን ሊያጠፋት ተመኘ:: ቀጥሎም "ሃገራችሁን ልጐብኝ" ብሎ በማታለል ገባ::
ወዲያውም ሕዝቡንና ካህናትን ሰብስቦ "ክርስቶስን ካዱ" አላቸው:: ጽኑ ክርስቲያኖች ግን "አይደረግም" አሉት:: እርሱም ሊያስፈራራቸው አስቦ 4,000 ያህል ካህናት: ዲያቆናትና ምሑራንን ጨፈጨፋቸው::
ይሕንን አድርጐ "አሁንሳ?" አላቸው:: ሕዝቡ ግን አሁንም "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን የለም" አሉት:: (ሮሜ. 8:5) ጨካኙ ፊንሐስም እንደ ገና ከሕዝቡ መካከል ከ4,100 በላይ የሚሆኑትን ጨፈጨፈ::
ታላቁን ቅዱስ ሒሩትንም (የሕዝቡ መሪ ነው) ብዙ አሰቃይቶ ሰየፈው:: ሚስቱን ቅድስት ድማሕንም 2 ሴት ልጆቿን ሰይፈው የልጆቿን ደም አጠጧት:: ከዚያም ሰየፏት:: ይሕንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ::
ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ40 ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል::
አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
#ኅዳር 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.አቡነ ሃብተ ማርያም ንጹሕ
3.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
4.ቅዱስ ሒሩት አረጋዊ
5.ቅዱሳን ቢላርያኖስ: ኪልቅያና ታቱስብያ (ሰማዕታት)
6.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘደሴተ ሰንሲላ
7.ቅድስት ዮስቴና ቡርክት
#ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" (መዝ. 36:28-31)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ባህር ዳር የት አከባቢ ነው የሚገኝው ሙሉ መረጃውን የሚነግረኝ።
ለጭንቅላት ዕጢ ጠበሉ ፈዋሽ ነው። በጣም ብዙ ሰው እየሄደ ይፈወሳል።
@BeGood16 ላይ አድረሱኝ ሙሉ መረጃውን። እግዚአብሔር ይስጥልኝ