ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዘጸአት ነዉ ለሕዝቡ

ዘጸአት ነዉ ለሕዝቡ
በደም ታስሯል ወጀቡ
ፅኑ ክብርን ያየነዉ
ኢየሱስን ይዘን ነዉ ክርስቶሰን ለብሰን ነዉ

የግብፁ ፈረኦን በግፍ ሲያስጨንቀን
ክቡደመዘአረት ሙሴ ተነሳና ከራምሴ
መንጋዉን ይዞ ወጣ እየቀናበ ቃዱስ በሲና
ያመንፈሳዊ መጠጥ ያመንፈሳዊ መብል
ክርስቶስ ነበረ እኛን የሚከተል

አዝ

በራፍሊም እንዳንቀር ተወልን ምስክር
በኢያሱ ወልደ ነዌ እያዳነን ከአርዌ
ከነአን ሄደ ከፊት እየመራ
ስሙ መድሀኒት ሆነን
እሰራኤል ዘነፍስ ነን ድል ባደረገዉ ጌታ
ኢያሪኮ ሲኦል ፈረሷል በእልልታ
አዝ

በፋርስ ነገስታት ወድቆብን ባርነት
በኤርሚያስ የለወዝ በትር
እየታየን በምስጢር
እንደ ብረት አምድ ቅጥር አድረጎን
የእሳቱን ወጀብ አለፍን
በምልክት በራዕይ ተስሎ በሰማይ
ማምለጫችን ሆነ በጎልጎታ ላይ
አዝ

ከጥላታችን መዳፍ መከራ ቢወነጨፍ
የጠበቅነዉ መሲህ ደርሷል
ሸክማችንም ተራግፏል.
የመቤጀት ቀን ቀርቦ ዘፅአት
ጠቅልለንወጣን ከሞት
በደሙ አጊጠናል እርስቱን እንወርሳለን
በጽዮን ተራራ ለበጉ እየዘመርን

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆች እኮ ነን
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ እናት ልጆች እኮ ነን
ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነዉ ግዛቱ አብረን እንወርሳለን

የተካፈልኩትን ንብረት አትፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል ብዙ ነዉ የእርሱ መንግስት
አይክፋህ እባክህ ወንድሜ ፍቅር ይበልጣል ከሀብት

አዝ

ፊትህ በሀዘን አይጥቆር ድንጋዩን ጣለዉ ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ የአንተም መስዋዕት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነዉ መታዘዝ ንጉስ ያደርጋል
አዝ

ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም
አዝ

ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ደጅ ጠናሁ

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔንን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሁኝኝ ቀሪዉ ዘመኔን /2/

የመከራዉ ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንችን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንችም ደግነት
ባርያሽን ሰወረኝ ከአስጨናቂዉ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ

አዝ

ልቤ በአንች ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጥላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ

እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክራቸዉ ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸዉ
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸዉ
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ
አዝ

ከአዉደ ምህረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችኝ ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለዉ
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነዉ
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንች እየታበሰ ሰላም ለኪ

ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ንሴብሆ

ንሴብሆ/2/ ለእግዚአብሔር/2/
ስቡሃ ዘተሰብሃ/2/
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/
ምስጉን ነው የተመሰገነ/2/

አዝ

ባሕሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍጹም ነጻ ወጣን
ህይወት የሚሆነን መና ነው ምግባችን
አዝ

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
አዝ

ከዓለት ላይ ውሀ ፈልቆልን ጠጣን
ይህን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግን
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆኗል
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
አዝ

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አረሳት ኢትዮጵያን

አረሳት ኢትዮጲያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በ ሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ

ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠር ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ

አዝ

ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
አዝ

ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት
አዝ

ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዚህ ስም የሚጠራ Bot በዝማሬ ዳዊት እና በሌሎች መንፈሳዊ ግሩፕ ላይ የሚለቃቸውን ከመንፈሳዊ ይዘት ውጭ የሆኑ ነገሮች ብናጠፋ፣ ብሎክ ብናደርገውም ልንቆጣጠረው አልቻልንም። በመሆኑም ጉዳዩን እስክንፈታው ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በቤተ መቅደስህ ያሳደከኝ

በቤተ መቅደስህ ያሳደከኝ
ለአፌ ጥበብን ያስተማርከኝ
የልጅነቴ አምላክ ወዴት አለህ
በዚህ ዓለም ሀሳብ ክንዴ ዛለ

አዝ

የአሸዋ ላይ ህንፃ ሆኗል ቤቴ
ያረገርጋል መሰረቴ
ጠላት ሰልጥኖብኝ ደክምያለሁ
ዛሬ ብቻዬን ቀርቻለሁ
አዝ

አባካኝ ሆኛለሁ አመጸኛ
ለዚህ ዓለም ሀጢአት የማልተኛ
ነፍሴ ተንገላታች በመከራ
ማን ያገናኛት ካንተ ጋራ
አዝ

ሰላሜ ነህ አንተ ትዝታዬ
ጽፌ ያኖርኩህ በእንባዬ
አለም ወስዳኛለች በዘፈኗ
እባክህ ስራኝ እንደገና
አዝ

አመጸኞች ሁሉ ቤትህ ገቡ
ምሕረት ፍቅርህን እያሰቡ
እጅህን ዘርግተህ አቀፍካቸው
ባንተ ቀለጠ ልቦናቸው

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለቤሩታዊት የደረሰ

ለቤሩታዊት የደረሰ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ገሰገሰ
ፈጥኖ ሊያወጣኝ ከመከራ
ቆሟል ከጎኔ ከእኔ ጋራ

ስጋው ሲመተር አልፈራም እሱ
ሰባት አክሊላት ጭኗል በእራሱ
በደብረ ይድራስ በዛ ተራራ
የልዳው ፀሐይ ተብሎ ተጠራ

አዝ

ዓለምን ስትዞር በነጭ ፈረስ
አንድ ግዜ እርዳኝ ጊዮርጊስ ድረስ
ስሙን ለጠራ አምላከ ጊዮርጊስ
ሲደርስ ይፈጥናል ከአውሎ ንፋስ
አዝ

ለእሳት ለግለት ስጋውን ሲሰጥ
ፍርሃት የለበት ወይም መደንገጥ
ኡዲያኖስ አፋሮ ጣኦት ወደቀ
በጊዮርጊስ ጽናት ጌታ ታወቀ
አዝ

ከሹመት ይልቅ መርጠህ መከራ
ወንጌሉን ሰበክ አንዳች ሳትፈራ
በጭንቀት ሆነ ላንተ ንግስና
ብድራትህን አይተሃልና
አዝ

መስተጋድል ነህ ሃያል ገናና
መክብበ ሰማይት የእምነት ጀግና
ስምክን ስጠራ ከቤትህ ቆሜ
ይቀልልኛል የኃጢአት ሸክሜ

ዘማሪት መቅደስ ማርዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አለ ለእኔ የተሻለ ነገረ

አለ ለእኔ የተሻለ ነገር /2/
ዛሬን ባዝን ለጊዜው ብቸገር
አለ ለእኔ የተሻለ ነገር

በእጄ የጨበጥኩት በድንገት ቢበተን
ዙርያዬን ቢከበኝ ያላሰብኩት ሀዘን
እንባዬ በደስታ መቀየሩ አይቀርም
እተማመናለው በጌታዬ አላፍርም

አዝ

ሀብቴን ልጄን ባጣ እርሱ እንደወደደ
የእዮብ መከራ በእኔም ከወረደ
እራቁቴን መጣው እንዲሁ ሄዳለው
ከዚህ የላቀውን ከእርሱ እጠብቃለው
አዝ

መከራው ቢከብደኝ ከዙፋን ወርጄ
ከርስቴ ብሰደድ በአቤሰሎም ልጄ
ቀኑ እስከሚነጋ አልፈራም ጨለማ
ዳግም እለብሳለው የጽዮንን ግርማ
አዝ

አሳዳጄ ቢያይል ጉልበቱ ቢፀና
ተግዳሮቱ በዝቶ ወደ እኔ ቢያቀና
የከበረው ድንጋይ አለ በወንጭፌ
እቋቋመዋለው እርሱን ተደግፌ
አዝ

በናባው ተራራ ቢሆን መቃብሬ
ከነዓን ባልገባ ከህዝቡ ጋር አብሬ
አለኝ በሰማይ ቤት እጅግ የከበረች
በጆሮ ያልተሰማች በአይንም ያልታየች

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መልአከ ሰላምነ

መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ዑራኤል /2/
ሰዐል ወጸሊ በእንቲአነ አእርግ ጸሎተነ
ቅድመ መንበሩ ለመድኃኒዓለም /2/

ጸበልህ የሚፈውስ የዋህ መልዐክ/2/
የምህረት ዝናብህን ፍጥረት ሁሉ ያደነቀው
ጸጋህ ልብስ ሆኖን እዲያስጌጠን
በረድኤት በፍቅር እባክህን አትለየን
አዝ
መራኄ ብርሃን ዑራኤል ሆይ አትለየን /2/
በምልጃ ብርሃንህ በረድኤት ጥላ ስር ነን
ፈጣን ንስር ሆይ ለምሕረት ሰውን ለማዳን/2/ የማይዘገይ/2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስምሽን ጠርቼ

ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ
ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ
የምጽናናበት ስምሽ ነውና
ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና

ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር
ለዘመናትም ስረገጥ ስኖር
ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ
የዓለሙን መድን ወለድሽልኝ
ከአባቶቼ ርስት ከሀገር ወጥቼ
በአሕዛብ አገር ስኖር ተሸጬ
ደርሰሽ አጽናንተሽ አከበርሽኝ
ብቸኝነቴን አስረሳሽኝ

አዝ

ድንኳኑ ሞልቶ ሰዉ ታድሞ
አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ
ምን አቀርባለሁ ብዬ ስቸገር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር
ያሰብኩት ሐሳብ ደመና ሆኖ
ቢበተንብኝ እንደ ጉም ተኖ
ይሆናል ያልኩት ሳይሆን ቢቀርም
በእመ አምላክ እኔስ ተስፋ አልቆርጥም
አዝ

እናት አባቴ ባያስታውሱኝ
ይህች ዓለም ንቃ ገፍታ ብትተወኝ
አንቺ ካለሽኝ ምን እሆናለሁ
አውሎ ነፋሱን ባሕሩን አልፋለሁ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝ
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም
አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝና
አዝ

ክፉዎች ደርሰው ቢዝቱብኝ
አንቺን መውደዴን አያስተውኝ
በአሕዛብ መሐል ስምሽን ስጠራ
መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም
አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝና

ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳፩ /21/


በዚችም ቀን የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ።

ይህም የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር ስለ ክርስቶስም በኢየሩሳሌም መኖርና ማስተማር ትንቢት ተናገረ። ደግሞም ስለ መከራው በሐዋርያትና በሰባ ሁለቱ አርድእት በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ።

"ከዚህ በኋላ በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ።" ሁለተኛም እንዲህ አለ ያን ጊዜ ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል።

ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት እንዲህ አለ ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ የከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል። የትንቢቱንም ወራት አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሐሜት

ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?!

የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ደግሞ ሔዋን ነበረች፡፡ (ዘፍ 3፥1-5)

የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር አደረገ። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል?

ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡ በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር።

ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።

ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው "ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።"

ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ ይቻለን ነበር።

"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።

ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።

ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።

"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15


ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳ /20/


ዳግመኛም በዚህች ቀን የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ የታላቅ ነቢይ የኤልሳዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

እርሱም አሜሁላ ከሚባል አገር ከይሳኮር ነገድ ነው ብዙ ትንቢትን ተናግሮአል ብዙ ተአምራትንም አድርጓል። የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን "ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት" ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት ።

ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ "እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት" አለ አላቸው።

ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ። የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል። በኋላም የትንቢቱን ወራት ፈጽሞ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ገብርኤል መልዐከ ራማ

ገብርኤል/2/ መልዐከ ራማ/2/
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እንስማ

ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰውን መሆን ለዓለሙ ሰበክ /2/

አዝ

ከውኃ እና ከእሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለው ሞትና መከራ /2/

አዝ

የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና/2/

አዝ

አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ
ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳተ ነህ ገብርኤል ነበልባል አስወጋጅ
የአምላክ መወለድ ለዓለም የምታውጅ /2/


ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክበብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳፮/26/

በዚች ቀን ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞች ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ።

ይህ ቅዱስ የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከሐዋርያት ጋር ከተቀበለ በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ተሾመ።

በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ:: በውስጧም ሃይማኖትን አስተማረ ከዮናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው።

የዚያች አገር ገዢም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​የሰው ልጅ ከውድቀት በኋላ

የሰው ልጅ ፍጹም የተለወጠው በእግዚአብሔር ላይ ሲያምፅ ነው። ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተለየው፤ ያን ጊዜ የክብር ልብሱ ተወሰደበት፤ ያን ጊዜ ሐፍረትና ውርደት አገኘው፤ ያን ጊዜ ከመላእክት ሕይወት ወርዶ የዚህ ዓለም ጭንቀት የሚገዛው ፣ ጥሮ ግሮ የሚበላ፣ ልብሱ ከእንስሳት የተገኘ ቆዳ፣ እጅግ ብርቱ የኾኑ  ፍትወታትና ሥጋዊ መሻቶች የሚጸኑበት፣ የሚርበው፣ የሚጠማው፣ የሚደክምና የሚሞት ኾነ።

እግዚአብሔርን መስሎ የሚያድግበት አቅም በውስጡ የነበረ ቢኾንም፥ የሰይጣንን ምክር ሰምቶ በአቋራጭ ያልተገባ ክብርን በመሻቱ ምክንያት፥ ያን ጊዜ የማያድግ ይልቁንስ ቁልቁል የሚወርድ ኾነ። እንደ እንስሳት የሚኖር አላዋቂ ኾነ። እንደ እንስሳት መኖርም የሰው ልጅ የመጨረሻ የውርደት መገለጫ ነበር።

የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሮ ሳለ እንደ እንስሳት ሲኖር ማየት በእውነት ጥንቱን እንስሳ ኾኖ በተፈጠረ በተሻለው ነበር የሚያስብል ኾነ። ከጌታ በታች ገዢ ሲኾን ይህን ባለማወቁና ከዕፀ በለስ ሰርቆ በመብላቱ በፍቃዱ ራሱን አዋርዷልና፥ ባሪያ ኾኖ ጌቶች ያልኾኑት የሚገዙት ኾኗልና እጅግ አሳዛኝ ፍጥረት ኾነ። በኃጢአት ብዛት ጠቁሮ በሰማያውያን አምሳል መኖር ተሳነው።

ቅዱስ ኤፍሬምም ይህንን ሲያይ፡-

"አዳም ከንግሥና ወርዶ ከእንስሳት መኖሪያ ሲያየው እንዴት እንደ ወደቀ እያሰበ ዳዊት አለቀሰለት (መዝ.48፡13)። ሸሽቶ ከዱር እንደ ተደበቀ የዱር እንስሳትን መሰለ። ከወደቀበት መርገም የተነሣም ከእንስሳት ጋር ሣርና ሥራሥር በላ፤ ጓደኛቸው ኾኖም እንደ እነርሱ ሞተ አለ።

ስለዚህም እውነተኛ ሰው መኾን ተሳነው። ሰውን ሰው የሚያስብለው የሰው መልክ ዓይን፣ አፍንጫ፣ አፍ ስላለው አይደለምና። እነዚህ የሰውነት ብልቶች ናቸውና። ሰው ብለን ልንጠራው የሚገባን የሰው ልጅን ጠባይ መገለጫ ገንዘብ አድርጎ ሲገኝ ነውና፤ እርሱም ማሰብ መቻሉና በዚያ መሠረት የቅድስና ሕይወትን መያዝ ነው።

ቀድሞ ይገዛቸው ይነዳቸው የነበሩት ብዙ እንስሳት በእርሱ ላይ የሚነሣሡበት ኾኑ። ምንም እንኳን ቀድሞ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ የተገኘ ኾኖ ሳለ እንደ መላእክት ይኖር የነበረ ቢኾንም፥ ሲወድቅ ግን ወደ እርሱ የሚመለስ ኾነ። መንፈስ ቅዱስ የማይመራው የማይነዳው ኾነ። ቀድሞ የነበረው እጅግ አስደናቂ ዐዋቂነትን አጥቶ በድንግዝግዝ የሚጓዝ ኾነ። ሞት ሙስና፣ ክፋት የአዳም አዲሶቹ መገለጫዎቹ ኾኑ።

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ፥ አዳም ከእግዚአብሔር ጋር አፍ ለአፍ የማይነጋገር ኾነ። በእርሱና በእግዚአብሔር መካከል ኃጢአት እንደ ግድግዳ ኾኖ ቆመ። በዚህ ኹኔታ ውስጥ ላየውም ከላይ እንደ ተገለፀው አዳም እጅግ የሚያሳዝን ፍጥረት ኾነ። ሰውነቱ በኃጢአት ለመጠቃት እጅግ ተጋለጠ። ሞት ከተፈረደበት በኋላ ፍትወታት ወደ ባሕርዩ ዘልቀው ስለ ገቡ ደግ ሥራን ለመሥራት ከባድ ኾነበት። ልጓም የሌላት ፈረስ እንዲሁ እንደምትላተምና እንደምትወድቅ፥ ሰውም እንደዚህ ኾነ። ከምንም በላይ ደግሞ የአዳምና የሔዋን አንድነት ወደ መፍረስ ተቃረበ። በዲያብሎስ ምክር ምክንያት አዳምና ሔዋን እየተካሰሱና አንዳቸው በአንዳቸው ላይ እያመካኙ ወደ መለያየት የተቃረቡ ኾኑ።

ሲወድቅ የሚጠቅሙት (መንሻ የሚኾኑት)፥ ግን ደግሞ የውድቀቱ ማሳያ የኾኑ መገለጫዎች ወደ ባሕርዩ ዘልቀው ገቡ። ምክንያቱም ፍርሐት ሲመጣበት ስለ ኃጢአት፣ ኀዘን ሲመጣበት ስለ ኃጢአት፡ ሞት ሲመጣበት ስለ ኃጢአት እንዲያስብ እንጂ እርሱን ለመጉዳት የመጡ አይደሉምና። እግዚአብሔር እነዚህን ኹሉ የሰጠው በበደል ላይ በደል እየጨመረ እንዳይጠፋ ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ትንሿ ቤተክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳፭/25/


በዚች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው። በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው። አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው።

ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በዚያንም ጊዜ እጅግ ለመስማት የሚዘገንን መከራ እና ስቃይ በህፃኑ ላይ አደረሰበት የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው።

ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚለይበት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ወርዶ ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት በደረቱም ላይ አድርጎ ወደ አየር አወጣው። የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አጌጥንበት ስምህን

አጌጥንበት ስምህን
ተዋብንበት ፍቅርህን
ሞገሳችን ሆነሃል
የጽድቅ ልብሳችን አማኑኤል /2/

ተዋህዶ የአዳምን ሥጋ
አማኑኤል ሆነ ከእኛጋ
በግርግም በቤተልሔም
ተወልዶ ሆነልን ሰላም

አዝ

ብንጠግብ በልተን ጠጥተን
ብንገባ በሰላም ወጥተን
ልጆችን ወልደንም ብንስም
ጠርተን ነው ጌታ ያንተን ስም
አዝ

ቢያምርብን ቢሞቀን ለብሰን
ብንረሳ ለቅሶና ሀዘን
ፍቅርህ ነው ዛሬን ያሳየን
ተመስገን እንልሃለን
አዝ

በባዕድ ሀገር ብንኖር
ቢገጥመን መከራ ችግር
ነጩን ልብስ ለብሰን ታይተናል
መስቀሉን ከማህተቡ ጋር

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳፬ /24/


በዚች ቀን መስተጋድል መነኰስ አባ አብላርዮስ አረፈ።

ይህም ቅዱስ ጋዛ ከሚባል አገር ነው። ወላጆቹም አረማውያን ናቸው የዮናናውያንንም ትምህርታቸውንና ፍልስፍናቸውን አስተማሩት ሰውነቱ ለጥበብ ማደሪያዋ እስከሆነ ድረስ በዕውቀቱ ከጓደኞቹ በላይ ሆነ።

ከዚህም በኋላ ከሀገሩ የሌለ መልካም የሆነ ጥበብን ከውጭ አገር መማርን ወዶ ተነሥቶ ወደ እስክንድርያ ሀገር ሔደ መምህራንም ሁሉ ከሚኖሩበት ቦታ ገብቶ ከእሳቸው ዘንድ ብዙ ትምህርትን ተማረ በዚያንም ጊዜ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ለመማር ተነሣሥቶ ቸኰለ የቤተክርስቲያንንም መጻሕፍት ብዙዎቹን  አነበበ የእስክንድርያ ሊቀጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስም ይተረጒምለትና ያስረዳው ነበር።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በምንኵስና ሕግ ጸንቶ ገድልን ተጋደለ ወደ አባ እንጦንዮስም ሔዶ መንፈሳዊ የሆነ ጥምቀት ተጠመቀ ከዚያም መንኵሶ የትሩፋትን ሥራ እየተማረ በእርሱ ዘንድ ብዙ ወራት ኖረ።

ወላጆቹም እንደሞቱ በሰማ ጊዜ ሒዶ የተዉለትን ገንዘባቸውን ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች መጸወተ ከዚህም በኋላ ከሶርያ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባ በዚያም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት በመትጋት ፍጹም ገድልን ተጋደለ በየሰባት ቀን እስኪመገብ ድረስ ምግቡም የዱር ሣር ነበር።

እግዚአብሔርም ሀብተ ትንቢትን ሰጥቶት ልቡናው ብሩህ ሆነ ድንቆች ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ ኤጲፋንዮስንም ያመነኰሰውና ለደሴተ ቆጵሮስም ኤጲስቆጶስ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረለት እርሱ ነው። ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም ካገለገለ በኋላ በሰላም አረፈ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የጥቅምት ፳፬ ማኅሌተ ጽጌ🌹
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳፫ /23/


በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኀምሳ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ አረፈ።

ይህም አባት ከመኑፍ አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን ነው ወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ያላቸው ነበሩ ታናሽም ሁኖ ሳለ አባትና እናቱ ትተውት ሲሞቱ ድኃ አደግ ሆነ አንድ እግዚአብሔርንም የሚወድ ሰው አሳደገው።

አድጎ በጐለመሰም ጊዜ የወላጆቹን ገንዘብ ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጥቶ ከአንድ ጻድቅ ሽማግሌ ሰው አባት ዘንድ መነኰሰ በበጎ ገድል ሁሉ እየተጋደለ ኖረ።

ይህም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መናፍቃንን የሚገሥጻቸው ሆነ ሕዝቡንም ከአባቶቻቸው፤ በተቀበሏት በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አስተማራቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ለእነርሱም  ሥውር የሆነውን ተርጕሞ ያስረዳቸዋል ያስገነዝባቸዋልም በትምህርቱና በጸሎቱም እንዲህ ጠበቃቸው ጌታችንም በእጆቹ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ያማረች ገድሉንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም  በፍቅር አረፈ።

መላ የሕይወቱም ዘመን ሰባ ስምንት ነው ከምንኵስና በፊት ሃያ ዓመት በምንኵስና ተጋድሎ ሠላሳ ዘጠኝ ዓመት በሊቀ ጵጵስና ሹመት ዓሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት

እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥረው እንደ መላእክት አድርጎ ነው። ቅዱስት መላእክት ለባውያን፡ ሥጋዊ መሻት የሌለባቸው ከኃጢአት የነጹ እንደ ኾኑ ሁሉ የሰው ልጅም ሲፈጠር ምንም እንኳን ሥጋን የለበሰ ቢኾንም እንዲህ ኾኖ ነበር። የሰው ልጅ ያልተለመደ ዓይነት መልአክ ኾኖ የተፈጠረ ነው። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ አዳምንና ሔዋንን ኹለት መላእክት" የሚላቸውም ለዚህ ነው። ከቅዱሳን መላእክት ጋር ኾኖ ከአምላክ ጋር አንድነት የነበረው፡

ዲያብሎስና እርሱን የተከተሉት መላእክት እንዲቀኑ ያደረጋቸው የሰው ልጅ ሕይወት ነበር። ምንም እንኳን ሥጋን የለበሰ ቢኾንም እንደ ረቂቃኑ” መላእክት መኖሩ፣ በአንድ ጊዜ ረቂቅና ግዙፍ ፍጥረት መኾኑ ነበር ያስቀናቸው::

ይህ ሰው ለሞት የተፈጠረ አልነበረም። ምንም እንኳን ካለ መኖር ወደ መኖር የተፈጠረ እንደ መኾኑ በባሕርዩ ሊሞት የሚችል ማለት ሞት የሚስማማው ገና የተፈጠረ ቢኾንም፥ ሕያው ባሕርይ በኾነው በራሱ በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠረ በመኾኑ ሕጉን በመጠበቅና ፈጣሪውን በማወቅ ይህንን አርአያ እግዚአብሔርን ቢጠብቅ ግን አይሞትም ነበር። እግዚአብሔር ሕያው የምታደርገውን ነፍስ የሰጠው ስለ ኾነ ብሩህ፡ ውብ፡ ለባዊ፡ መልካም ሥራዎችን ለመሥራት ዓቅም ያለው የተፈጠረ ነው፥ ይሀ በርግጥም ልዩ ክብር እንደ ነበረ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘቡል) ሲገልፀውም፡-

ከዚህ ክብር የሚበልጥ ምን ክብር አለ? ከዚህ ትምክሕት የሚበልጥ ምን
የሚያስመካ ነገር አለ?..
. ሰውን በእርሱ አምሳል እንደ ፈጠረው እንዲመሰክር ከመኾን የበለጠ የሚያስመካ ምን ነገር አለ?" ይላል ።"
ሙስና፡ ሞት፡ ሕማምና ድካም የመጡበት ከዚህ በኤደን ገነት ውስጥ ይኖርበት ከነበረው የንጽሕናና የድንግልና ሕይወት ፈቀቅ ሲል ነው። ሞት የሚስማማው ኾኖ የተፈጠረ ቢኾንም፥ በገዛ ፈቃዱ እንዳይሞት ማድረግ ይችል የነበረው የሰው ልጅ መዋቲ የኾነው ከበደለ በኋላ ነው።

ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ የተፈጠረ ቢኾንም፥ ክብሩ ግን ሰማያዊ ነበር። አፈርና ትቢያ የኾነው፡ እግዚአብሔር የነገረውን ባለ ማመን ብሎም ባለመታዘዝ ሲበድል ነው። ጥንቱን ከትቢያ የተፈጠረ ቢኾንም እስኪወድቅ ድረስ ክብሩ እፍ ተብላ ከተሰጠችው ነፍሱ የተነሣ ከፍ ያለ ነበር። ስለዚህም እንደ መላእክት ስለሚበላው፡ ስለሚጠጣው፣ ስለሚለብሰው፡ ስለ እንቅልፍ፣ ወጥቶ ወርዶ ስለ መሥራት፣ በአጠቃላይ ስለዚህ ዓለም ኑሮ የሚጨነቅ አልነበረም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይህን ግልፅ አድርጎ ሲነግረንም እንዲህ ይላል፡-

ምንም እንኳን በዚህ ምድር ላይ ሥጋ ለብሶ ቢኖርም ፍትወተ ሥጋ ሳይኖርበት እንደ ሰማያውያን መላእክት ኾኖ ይኖር ነበር። በትረ መንግሥቱን ይዞ የንግሥና ዘውዱን ጭኖ፡ ሐምራዊ መጎናጸፍያውን አድርጎ እንዳጌጠ ንጉሥ በነጻነትና በፍጹም ደስታ ይኖር ነበር። አንድም ነገር ሳይጐድልበት እጅግ ባለጸጋ ኾኖ በገነት ይኖር ነበር።"


ይበላ የነበረ ቢኾንም፤ በአንድ መልኩ ጥሮ ግሮ የሚበላ አልነበረም፡ በሌላ መልኩ ደግሞ አሁን የምናውቀው ዓይነት ረሃብና ጥም ስለ ነበረበት አይደለም። መላእክት እንደማይርባቸውና እንደማይጠማቸው ኹሉ፥ ሰውም እንደዚህ ነበር። ሰውስ ይቅርና ዛሬ ሥጋ በል የምንላቸው እንስሳትም ከውድቀት በፊት ምግባቸው ማር እንጂ ሥጋ እንዳልነበረ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ይነግረናል።'

በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምንም እንኳን ሥጋ የለበሰ የነበረ ቢኾንም፥ በሥጋው ብቻ የታጠረ ግን አልነበረም። መላእክት ሥጋዊ ፍላጎት እንደ ሌለባቸው ኹሉ' ሰውም ይህ ኣልነበረበትም። መላእክት ልብስ እንደማያሻቸው ኹሉ' ሰውም ልብስ የሚያስፈልገው አልነበረም። ልብሱ፣ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ እንደሚነግረን የክብር ልብስ ነበር ይህን የክብር ልብስ ለብሶ እያለ' እስራኤላውያን ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፊቱን ሳይሽፍን ማየት የማይቻላቸው እንደ ኾኑ፥ የምድር ፍጥረታትም አዳምንና ሔዋንን ማየት አይቻላቸውም ነበር። አዳም ለእንስሳቱ ስም ሲያወጣላቸውና በፊቱ ሲያልፉ እንኳን ቀና ብለው ማየት ሳይቻላቸው አጎንብሰው ነበር። አዳም ለብሶት የነበረውን የክብር ልብስ ማየት አይቻላቸውም ነበር።' እንስሳቱስ ይቅሩና ዲያብሎስ ይህን የአዳም ክብር በግልፅ ማየት አይቻለውም ነበር።" አዳም ይህን የክብር ልብስ ለብሶ ሲኖር ከግዙፍ ልብስ ዕራቁቱ እንደ ኾነ እንኳን አያውቅም ነበር። ስለዚህ አሁን የምናውቀው ዓይነት ልብስ ለሰው ልጅ የተሰጠው "ለዚያ አጊጠዉበት ለነበረው የብርሃን ልብስና ከሥጋ መሻቶች ነጻ ኾነው ለኖሩበት ሕይወት ያልተገቡ ኾነው በመገኘታቸው ነው።'' የቆዳ ልብስ የተሰጣቸው ለዚያ የክብር ልብስ ያልተገቡ ኾነው በመገኘታቸው ብቻ ሳይኾን ላለማመናቸውና ላለመታዘዛቸው ማዘከሪያ እንዲኾን ነው።

ዳግመኛም የሰው ልጅ በራሱ ላይ ብቻ ሳይኾን በሌሎች በሚታዩ ፍጥረታት ላይ ንጉሥ ኾኖ ይኖር የነበረ ነው። መጨረሻ ላይ መፈጠሩ፣ ሌሎቹ ፍጥረታት ኹሉ እርሱ እንዲጠቀምባቸው መዘጋጀታቸው በገነት ውስጥ ያለ ጣር መኖሩ፡ እንስሳቱ ኹሉ ስም እንዲያወጣላቸው ወደ እርሱ መምጣታቸውም ይህን ንግሥናውን በግልፅ የሚያስረዱ ናቸው። ፍርሐትና መንቀጥቀጥ የመጣበት ከበደለ በኋላ ነው፤ ሔዋን ከእባብ ጋር ያለ ፍርሐት መነጋገርዋ ይህን የሚያሳይ ነው።

የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት እጅግ ዐዋቂና ጠቢብም ጭምር ነበር። ይህም ሳይሳሳትና ሳይደግም ለእንስሳቱ ስም በማውጣቱ ታውቆአል።

ነጻነትም ነበረው። ከመበደሉ በፊት የሚያሻውን በጎ ነገር ለማድረግ አያቅተውም ነበር። በጎ ማድረግን አስቦ ማድረግ ያቃተው ሲበድል ነው።

ከእግዚአብሔር ጋር እንደ ባልንጀራ አፍ ለአፍ የሚነጋገር ነበር። አባት ለልጁ ኹሉን ነገር እንደሚያስተምረው፥ እግዚአብሔርም ለአዳም ኹሉን ነገር ያስተምረው ነበር። በኋላ ሲወድቅ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠውም የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ስለ ራቀ ነው። አጠገብ ላለ ወዳጅ ደብዳቤ አይጻፍምና።በጎውንና ክፉውን የሚያውቅ መለየት የሚችል ነበር። መለየት የማይችል ቢኾን ኖሮ ባልተጠየቀ ነበርና።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ትንሿ ቤተክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት፳፪ /22/


በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ።

ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።

በኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።

ንጉሥ ኔሮንም እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ።

ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ጥቅምት 21 ቀን እመቤታችን ሐዋርያው ማትያስን ከእስር ያስፈታችበት ቀን ነው!

በዛሬው እለት ማለትም ጥቅምት 21 ቀን እመቤታችን ለሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ አስገራሚ ተአምር አድርጋለታለች፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ቅዱስ ወንጌል እንዲያስተምሩ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ሰዎችን ወደሚበሉ ሀገር ዕጣ ደረሰው፡፡ ቅዱስ ማትያስም ወንጌልን እሰብካለሁ ብሎ ሀገራቸው ገባ፡፡

በዚያች ሀገር የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ አንድ ሰይጣናዊ ልማድ ነበራቸው። ይኸውም አንድ ሰው ሀገራቸው ከመጣ ይዘውት ሁለቱንም ዓይኑን በማውጣት ለ30 ቀን እንደ ከብት ሣር እያበሉት በእስር ቤት ያቆዩታል፡፡ በ 30ኛው ቀንም ከእስር ቤት አውጥተው አርደው ይበሉታል። ታዲያ እነዚህ ሰው በላ ሰዎች ቅዱስ ማትያስንም ይዘው ሁለቱን ዓይኖቹን አወጡ በእስር ቤትም አስቀመጡት፡፡

ቅዱስ ማትያስም በእስር ቤት በጭንቅ ሆኖ ወደ እመቤታችን መማጸን ጀመረ፡፡ እመቤታችንም ቅዱስ ማትያስ የሚበላበት ሠላሳኛው ቀን ሳይደርስ በጸሎቷ ኃይል ከእስር ቤት አስወጣችው በተአምራትም ከሰው በላ ሰዎች አስመለጠችው፡፡

እመቤታችን በመዓዛ መለኮት በጣፈጠ ጥዑም አንደበቷ ከችግራችን፣ ከሕመማችን፣ ከእሥራታችን ትፍታን፡፡

ቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዝማሬ ዳዊት ትክክለኛው የቲክቶክ ገጽ ይህ ነው።

በቅርቡ አዳዲስ ስራዎች ይዘን ስለምንቀርብ ቲክቶክ የምትጠቀሙ ቤተሰቦቻችን Follow እና ሼር በማድረግ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ያስፉ።

https://vm.tiktok.com/ZMhQPn89c/
https://vm.tiktok.com/ZMhQ5DW1f/

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ማርያም ማርያም ብዬ

ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወልደኝ/2/

ገና በማህጸን በእናቴ የምጥ ቀን
ደጋግሜ ሰማሁ ሲጠሩ ስምሽን
በሰከንዳት እድሜ የማውቃት አንዲት ቃል
ልቤ ላይ ያለው ስም ማርያም ማርያም ይላል/2/
ማርያም ማርያም

አዝ

ሔዋን ምጧ ቀሎ ልጆቿን ታቀፈች
በአማላጅነትሽ እናቴም ታመነች
በተወለድኩበት በመጀመሪያው ቀን
ስምሽን እየሰማሁ ወጣሁ ከማህጸን /2/
ማርያም ማርያም
አዝ

ከቃልኪዳን ስም ጋር አደግኩኝ አብሬ
ምልጃሽ ሳይለየኝ አለሁ እስከ ዛሬ
የህይወቴን ፊደል ካንቺ ላይ ቆጠርኩኝ
በልጅሽ አምኜ ዳግም ተወለድኩኝ /2/
ማርያም ማርያም
አዝ

የክፉ ቀን ስንቄ ያዘልኩሽ በልቤ
የህይወቴ ምግብ የእንጀራ መሶቤ
እንደ ትላንትናው ዛሬም እጠራሻለሁ
የመስቀል ስር ክብሬን እንዴት እረሳለሁ
የመስቀል ስር ክብሬን እንዴት እተዋለሁ/2/
ማርያም ማርያም

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከሰማዩ ከፍታ

ከሰማዩ ከፍታ ከፍ ብላ ጽዮን
በሰገነት ላይ ተቀምጣ
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ /2/

አይን ከሞላባቸው ከኪሩቤል
ክንፋቸው ከበዛ ከሱራፌል
ከሊቃናቱ ሁሉ ትበልጣለች
እሳተ መለኮትን በሆዱዋ ስለተሸከመች

አዝ

ከንጉሱ በስተቀኝ ከዙፋኑ
ንግስቲቱ ቆማለች በየቀኑ
የቃል ኪዳን ቀሚሷን ተጐናጽፋ
የምትማልድልን ድንግል ናት የሁላችን ተስፉ
አዝ

በብርሀን ወንበር ላይ ተቀምጣለች
ጨረቃን ከእግሯ በታች ተጫምታለች
የቅድስናን ውበት ተሸልማ
የምታብረቀርቀው እርሷ ናት የልዑል ከተማ
አዝ

ከዕብራውያን ሴቶች ተለይታ
ከሔዋን ዘሮች ሁሉ ታየች ጐልታ
ሰባቱን መቅረዝ ልጇ ያበራል
ስጋዋን ተዋህዶ በፍቅር እኛኑ መስሏል

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሞገድ ሲመታኝ

ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉ ተችሎ ላንተ ጌታ /2/

በአንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅር ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው ባንተ ሞት
ይህው አቆምከኝ በህይወት/2/

አዝ

ደጅህ ስጠና ስማጸንህ
መቼ ጨከነ ጌታ ልብህ
እንደ ቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ጸጋህ በእጅህ ለበስኩ/2/
አዝ

ዘወትር እልል ብል ብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተ ፍቅር
ጌታ ብጠራው ስምህን
ለውጠኸው ነው ታሪኬን /2/
አዝ

አይኖቼ አያዩም ካንተ በቀር
የምትወደድ የምትፈቀር
ዘመድ ወገኔ ሆነኸኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል /2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፱ /19/


በዚች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ።

እኚህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው፤ ክርስቲያኖችም እንደሆኑ፤ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው፤ መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ።

መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал