ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
28 сентября 2024 06:00
መስከረም ፲፰
በዚች ቀን አባታችን ኤዎስጣቴዎስ አረፈ።
በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት የተወለደው ኤዎስጣቴዎስ ገና በልጅነቱ
የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍትን ተማረ። ከዚህም በኋላ ወላጆቹ አጎቱ ወዳለበት የመነኰሳት ገዳም ወሰዱት።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚካኤልና ከገብርኤል ጋር ተገለጠለትና ሰላምታ ሰጠው፤ እንዲህም አለው ከኢትዮጵያ እስከ አርመንያ ድረስ መምህር አደረግሁህ አንተን የሰማ እኔን ሰማ አንተን ያልሰማ እኔን አልሰማም ጌታችንም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ በክብር ዐረገ። ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስም ቅስና ተሹሞ የወንጌልን ሃይማኖት ይሰብክ ጀመረ።
ተጉዘዉ ባሕረ ኢያሪኮ ሲደርሱ የሚሻገሩበት መርከብ አጡ። አባታችን በእምነት አጽፋቸውን (ኩታቸውን) አውልቀው ባሕሩ ላይ ጣሉት። በላዩ ላይም በትእምርተ
መስቀል አማትበው ተቀመጡበት። ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ባሕሩ ላይ በተነጠፈው ኩታ ላይ ከበው ተቀመጡ።
ከሰማይም ጌታ ወርዶ በመካከላቸው ቆመአባታችን፤ ሚካኤል በቀኝ ገብርኤልም በግራ ቆሙ። ጻድቁም ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው ገቡ። ከመካከል ግን አንዱ በመጠራጠሩ እርሱ የተቀመጠባት ብቻ ተቀዳ ሰጠመ። በኋላ ግን ጻድቁ ተመልሰው አውጥተው ከሞት አስነስተውታል። በዚህም ምክንያት
ማዕበልን የተሻገረ ይባላሉ።
ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳንን ሰጠው። በአረፈም ጊዜ ጳጳሳትና ካህናት በታላቅ ክብር ገንዘው በሰማዕቱ በቅዱስ መርምህናም
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገለጡ።
በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
27 сентября 2024 20:27
ቤተ ክርስቲያን
ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?
በቀጥተኛ ትርጉም ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ቤተ እና ክርስቲያን ከሚሉት ሁለት የግእዝ ቃላት የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቲያኖች መኖሪያ /ቤት/ ማለት ነው፡፡ ይህም የክርስቶስ ቤት፣ የክርስቲያኖች መሰባሰቢያ ቤት የሚል ትርጉም አለው፡፡
በግሪክ አቅሌስያ ትባላለች፤ የምርጦች ጉባዔ ማለት ነው፡፡ ይህች የምርጦች ጉባዔ የእግዚአብሔር ሕዝብ የነበሩት ጉባዔ እስራኤልን ያመለክታል፡፡
በዘይቤያዊ ፍቺ ቤተ ክርስቲያን ስንል ሦስት ትርጉም አለው ፡-
፩. ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን:- ተሰባስበን የምናስቀድስባት፣ የምንማርባትና ሌሎች ምሥጢራትን የምንፈጽምባት ናት፡፡ ይኽችም ቤት ጌታችን ኢየሱስ ቤቴ ስላላት የክርስቶስ ቤት እንላታለን፡፡
ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤ እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው።” ሉቃ. ፲፱ ፥ ፲፮
በዘመነ ሐዲስ የማርቆስ እናት የማርያም ቤት የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ ሐዋርያት በዚያች ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው ይጸልዩ ነበር፡፡
ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቃ ታደረግ ነበር። የሐዋ.፲፪፥፭
፪.
የክርስቲያኖችን ስብስብ፡- በክርስቶስ አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖች ሁለትና ከዚያ በላይ የሚኖራቸው ስብስብ ቤተ ክርስቲያን ይባላል፡፡ ምክንያቱም በዚያ የእምነት አንድነት ውስጥ እግዚአብሔር አለና፡፡
“ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።” ማቴ. ፲፰ ፥ ፳ እንደተባለ፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበደለንን መክረን አልሰማ ቢለን ለቤተ ክርስቲያን ንገራት ያለን ለዚህች የአባቶች ካህናት እና የምእመናን ስብስብ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ማቴ. ፲፰ ፥ ፲፯ ስለዚህች ቤተ ክርስቲያን በተለይም በሐዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ ተጽፏል፡፡ የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ የሐዋ. ፲፩፥፳፪፣ ፲፫፥፩፣ ሮሜ.፲፮፥፩፣ ፩ኛ.ቆሮ.፲፮፥፲፱፣ ፊልሞ.፩፥፪፣ ፩ኛ.ጴጥ. ፭፥፲፫
፫.
እያንዳንዱ ክርስቲያን ፡- በእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች፣ የክርስቶስ አካላት ናቸውና ቤተ መቅደስ ይባላሉ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ
“የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?” ፩ኛ.ቆሮ.፫፥ ፲፮ ብሎ የተናገረው፡፡
እንዲሁም በሌላ ቦታ “ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣኦት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና ፪ኛ ቆሮ. ፮ ፥ ፲፮ እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።” እንደተባለ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ማደሪያ ነንና ቤተ ክርስቲያን ተብለን እንጠራለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- ሥራዓተ ቤተክርስቲያን
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
27 сентября 2024 18:07
መስቀል ነው ኃይላችን
መስቀል ነው ኃይላችን
ሞገስ ነው መመኪያችን
ላመነው መስቀል ለእኛ
አርማ ነው የመዳኛ
አዝ
የክርስቶስ ዙፋኑ
ቀራንዮ መካኑ
መስቀል ብርሃን ነው
በአንገታችን ያሰርነው
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)
አዝ
ጠላትን መመከቻ
ፍቅርን መመስረቻ
ከጦር ከቀስት ያመለጥነው
መስቀሉን ጋሻ አርገን ነው
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)
አዝ
ለማያምኑት ሞኝነት
ለታመንበት ሕይወት
መስቀሉ ነው ምልክት
የለንም ትምክህት
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)
አዝ
የደከሙት ማረፊያ
የስደተኞች መኖሪያ
መስቀል ድልድይ ነው
እሳቱን የሚያሻግረው
በመስቀል(2)አገኘን ሰላም(4)
ዘማሪ ዲያቆን አቤኔዘር ፍቃዱ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
27 сентября 2024 10:47
መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ
መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ (2)
ይኩነነ ቤዛ ይኩነነ ቤዛ (2)
መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ
አዝ
የድኅነት አርማችን የክብር ጌጣችን
ፍቅርን ያየንበት ነው መታረቂያችን
የክርስቲያን ትምክህት የመዳን ምልክት
እርሱን ለምንፈራ ያደለን በረከት
አዝ
እሌኒ አገኘችው ከዓመታት በኃላ
በደመራውም ጢስ ወጣ ከተራራ
የአይሁድ ክፋታቸው በዛው ያላስቀረው
ለምናምን ለእኛ መስቀል ኃይላችን ነው
አዝ
እግሮቹ የቆሙበት በክብር ለሰዓታት
እፀ መስቀሉ ነው የመዳን ምክንያት
እንሰግዳለን እኛም ይህንን ይዘን
በአበው ትውፊት ትምህርት ጸንተን
አዝ
ለእለ ይፈርሁከ ለምንፈራው ለእኛ
የሰጠን ምልክት መስቀል ነው መዳኛ
ነገሩ ገብቶናል ሞኝነት አደለም
ከሚድኑት ተርታ እንቁም ዘለዓለም
አዝ
መድኃኒተ ነፍስ ለኩሉ ፍጥረት
ሰላምን ያደለን የእርቅ ምክንያት
ዛሬም እንድናለን በእፀ መስቀሉ
በእርሱ የሚባርኩ ካህናት ስላሉ
ዘማሪት ፍሬ ተስፋዬ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
27 сентября 2024 09:03
እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።
📍 አ.አ መስቀል አደባባይ
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
27 сентября 2024 08:42
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በዓል 🙏 🙏 🙏
📍 ሰሚት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/አርሴማ ቤ/ክ
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
27 сентября 2024 05:43
እፀ መስቀል
እፀ መስቀል የክብር መውረሻ
ሞትን ድል መንሻ (2)
አዝ
የክብር ባለቤት
እፀ መስቀልየተሰዋበት
እፀ መስቀልእፀ መስቀሉ ነው
እፀ መስቀልየእኛ መድኃኒት
እፀ መስቀልአዝ
እንደእሌኒ ንግስት
እፀ መስቀልፍፁም አክብራችሁ
እፀ መስቀልሁላችሁ ገስግሱ
እፀ መስቀልመስቀሉን ይዛችሁ
እፀ መስቀልአዝ
ያለኃይለ መስቀል
እፀ መስቀልየሰላም አርማችን
እፀ መስቀልሊጠፋ አይችልም
እፀ መስቀልሰይጣን ጠላታችን
እፀ መስቀልአዝ
እሳተ መለኮት
እፀ መስቀልዙፋኑ የሆነ
እፀ መስቀልሰይጣንን የሚያነድ
እፀ መስቀልእፀ መስቀሉ ነው
እፀ መስቀልአዝ
እንደተባረከ
እፀ መስቀልቆስጠንጢኖስ ንጉሥ
እፀ መስቀልበመስቀል ብርሃን
እፀ መስቀልወደ ሕይወት እንገስግስ
እፀ መስቀልአዝ
የተዋህዶ ልጆች
እፀ መስቀልገስግሱ በተስፋ
እፀ መስቀልእፀ መስቀል ያዙ
እፀ መስቀልጠላት እንዲጠፋ
እፀ መስቀልዘማሪ በሱፍቃድ እንዳርጋቸው💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
27 сентября 2024 00:53
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን
📍 ወሊሶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
26 сентября 2024 20:43
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ🙏
ደቡብ ምዕራብ ~ ከፋ ክልል ~በቦንጋ ከተማ የመስቀል በዓል አከባበር
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
26 сентября 2024 20:40
እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንላችሁ ።
📍 ባህርዳር
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
26 сентября 2024 19:12
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
"ደስ ይበለን እልል በሉ፣
አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ፣
በብርሃን መላት ዓለምን በሙሉ"
በዓሉ የደስታ፣ የሰላም የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን፡፡
🌼🌼🌼
የአስኮ መካነ ሕይወት ቅዱስ አማኑኤል እና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
26 сентября 2024 18:02
መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ መስቀል አበራ ሰማይም በከዋክብት ደመቀ።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን! አሜን🙏
📍 ጌቴሴማኒ ቅድስት ኪዳነምህረት> ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
አያት ደራርቱ አደባባይ
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
26 сентября 2024 17:18
እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይጠብቅ።
📍 በወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከትና ባሕታ ለማርያም ቤተክርስቲያንን
ትንሽ ስለቦታው :-
እኔ እንግዳ ነኝ ከአ.አ ለስራ ሄጄ ነው ቦታው በተወሰኑ ግለስቦች (ኢ-አማንያን) በሆኑ ሰዎች በልማት አሳበው ደብሯን ለተወሰነ ግዜ ቦታ ተቀይሮ ነው ያለው ህዝቡም ተበታትኖ በዚህ መልኩ ሲያከብሩ እንዲው ድምፅ ከሆናችኋቸው በማለት ነው!! ፈጣሪ ያክብርልኝ መልካም በዓል
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
26 сентября 2024 16:59
እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
📍 ፈረንሳይ ለጋሲዮን አደባባይ
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
26 сентября 2024 15:07
የደመራ ዓመት
መስቀል የከበረው ትናንት መስሏቸው
ያዩ ተገረሙ ክብሩ አስደንቋቸው
ትናንትና አይደለም የበራው ደመራ
ዘንድሮ ዓመት ፈጀ የመስቀሉ ሥራ
ስንት አይሁድ ተነሥተው መስቀሉን ቀበሩ?
ስንትስ እሌኒዎች ሊያወጡት ቆፈሩ?
ጅጅጋ ሲዳማ ውጡ ተናገሩ
ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ደመራ
በእሳት ተለኩሳ ደምቃ ስታበራ
ካህናት ምእመናን እንደ ችቦ ነድደው
ስንቴ አከበሩት ለመስቀሉ ታርደው?
ስንት ጊዜ አፏጨ ዲያቢሎስ ተቆጣ
ስንት ሟርት ተሰማ ስንት ቁጣ መጣ?
በዕጣን ያልተገኘ ጌታ ያልሞተበት
ቅርፁ መስቀል ሆኖ መዳን የሌለበት
የወንበዴው መስቀል መስቀሉ መስሏቸው
ስንቶች ትተው ሔዱ ከእሌኒ እናታቸው?
ዓለም የዳነበት መስቀሉን ጨብጦ
ስለዘር የሚሰብክ እጅግ ተመስጦ
የተቃጠለውን መቅደስዋን እያየ
"ራስሽን አድኝ" ሲል ሲስቅ የታየ
ዘንድሮ አይደለም ወይ አይሁዱ የለየ?
ዘንድሮ ከበረ ለአንድ ዓመት ደመራ
በማያቆም ጥቃት በማያቆም ሴራ
ቅድስት ተዋሕዶ በጭንቅ ተወጥራ
አባቶችዋን ከፊት እንደ ጦር ሰድራ
በልጆችዋ ጩኸት በገና ደርድራ
በሰማዕታትዋ ደም ተረጭታና ርሳ
በየአደባባዩ ምሕላን አድርሳ
በፓትርያርክዋ ዓይን በምሬት አልቅሳ
እንደ ራሔል ለአምላክ ዕንባዋን አፍስሳ
ለመስቀሉ ቀን ግን ነጭ ልብስዋን ለብሳ
እንደ ቆስጠንጢኖስ በድል ልትነሣ
አምላክዋን ከፍ አድርጋ ኀዘንዋን ልትረሳ
ተስፋ ያደረገችው በመስቀል ታድሳ
ዘንድሮ ነው በዓል ዘንድሮ ደመራ
በዚህ ዓመት ተገኘን ከመስቀሉ ሥፍራ!!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌመስከረም 17 2012 ዓ.ም.
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…