ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
05 октября 2024 05:01
መሐረኒ ድንግል
መሐረኒ ድንግል ወተሰሐለኒ በበዘመኑ /2/
ለእመ መሐርከኒ /3/ አንቲ ዘይኮንነኒ መኑ
ኩናኔ ሥጋ ወነፍስ /2/ ወልድኪ አኮኑ
አዝ
ይጠሩሻል ካህናቱ
ንኢ ይሉሻል በሰዓታቱ
ለለመነሽ የማትቀሪ
በልቤ ውስጥ ፀንተሽ ኑሪ
የሥጋና የነፍስ ፈራጅ /3/
ልጅሽ አይደለም ወይ
መሐርኒ ድንግል ወተሰሐለኒ በበዘመኑ /2/
ለእመ መሐርከኒ /3/አንቲ ዘይኮንነኒ መኑ
አዝ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ የሆንሽ
ለምኝልን ከአንዱ ልጅሽ
እርግብየ ሰናይትየ
ነይ ወደኔ ነይ ወልድየ
ኩናኔ ሥጋ ወነፍስ /3/ ወልድኪ አኮኑ
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ/2/
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ
እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ
ልጅሽ አይፈርድብኝ
አዝ
በዓለም መኖር ሰልችቶኛል
መልካም መስራት አቅቶኛል
እጄን ይዘሽ ድንግል ምሪኝ
አዛኝቷ አትለይኝ
የሥጋና የነፍስ ፈራጅ /3/
ልጅሽ አይደለም ወይ
መሐርኒ ድንግል ወተሰሐለኒ በበዘመኑ /2/
ለእመ መሐርከኒ/3/ አንቲ ዘይኮንነኒ መኑ
አዝ
እበላለሁ ብዬ ማርያም
እመካለሁ ባንቺ አላፍርም
ካንቺ ወዴት እሄዳለሁ
ስምሽን ልጥራው እጽናናለሁ
ኩናኔ ሥጋ ወነፍስ/3/ ወልድኪ አኮኑ
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ/2/
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ
እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ
ልጅሽ አይፈርድብኝ
ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 октября 2024 17:58
በተለይ ለኦርቶዶክሳውያን
አምልኮ/ምስጋና/ ማለት ክርስቶስ ራስ ለኾነላት ቤተ ክርስቲያን ለተባለችው አንዲት አካል ብልት ለመኾን የምንጋደልበት ሰማያዊ ሥርዓት ነው። ኦርቶዶክሳውያን በአምልኮ ጊዜ እርስ በእርሳችን ብቻ ሳይኾን ከመላእክትም ጋር ረቂቅ አንድነት አለን። "በሰላም ማሠሪያ (ይህን) የመንፈስ አንድነት ለመጠበቅ እንድንተጋም" ታዘናል። (ኤፌ.4÷3)።
ወደዚህ ሰማያዊ ኅብረት ይመጡ ዘንድም ለዓለም ኹሉ እንደ ሐዋርያቱ እንጮኃለን፤ "ወደ ክርስቶስ ኅብረት በሃይማኖት ኑ" እንላለን። "እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው " እንዲል ሐዋርያው።
(1ኛ ዮሐ. 1÷3)።
ይህን በማድረግ ፈንታ ግን በማይመች አካሔድ ከማያምኑ ጋር መሰለፍ በሃይማኖታችን አይፈቀድም። ስለዚህ ማንም ኦርቶዶክሳዊ በሌላ ማኅበረሰባዊ ጉዳይ እንጂ በሃይማኖት ከማያምኑ ጋር ቢተባበር ራሱን ለካህን ያሳይ፣ በንስሐ ይመለስ።
ወንጌላችንም የሚለው የሚከተለውን ነው:-
"ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?" (2ኛ ቆሮ. 6÷14-15)።
እኔም እላለሁ - ኦርቶዶክሳዊ ከኢሬቻ/ዋቄፈና ጋር ምን ኅብረት አለው?
+ የኢሬቻና የኢኩሜኒዝም አካሔድ መመሳሰል - ሌላው ሥጋት?
የዓለማዊነት (Secularism) አቀንቃኞች ከፖለቲካ ዲሞክራሲን ፣ ከምጣኔ ሀብት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ፣ ከሃይማኖት ፕሮቴስታንቲዝምን ይመርጣሉ፣ ይደግፋሉ። እነዚህ ሦስቱም በዓለማዊነት አቀንቃኞች መደገፋቸው: ለአንድ ማኅበረሰብ በኹሉም መልክ ለዘብተኝነትን ( Liberalism) ስለሚያለማምዱ ነው። አንድ ማኅበረሰብእ ለዘብተኛ ከኾነ ደግሞ ቸልተኝነቱ ይጨምርና ኹሉን ችላ በማለት በእነርሱ ቁጥጥር ሥር ለመዋል ምቹ ይኾናል። ስለዚህ ለዚህ አካሔድ ወግ አጥባቂ (Conservative) ኾነው የሚያስቸግሯቸው ኦርቶዶክሶች ኹሉ (Orthodox Christians, Orthodox Jews, Orthodox Muslims) ጥርስ ውስጥ የገቡ ናቸው። በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የመሰሉ በሥርዓትና በዜማ የደመቁ አብያተ ክርስቲያናትን ለዘብተኛ ለማድረግ በተሐድሶ እንቅስቃሴና በተለያዩ መንግሥታዊ ተጽዕኖዎችም ጭምር እንዲጎዱ ተደርጓል።
ለዚህ ለዓለማዊነት እንቅስቃሴ የተሸረበው ሌላው ሴራ ደግሞ (ምንም እንኳን ጠቃሚ ጎን ቢኖረውም) የኢኩሜኒዝም (Ecumenism) እንቅስቃሴ ነው። ይህን እንቅስቃሴ በቅርቡ እነ ዶክተር ወዳጄነህን የመሳሰሉት እንደሚከተሉት በግልጽ አስረድተው ነበር። በዚሁ እንቅስቃሴ ስም የሚንቀሳቀሱት አንዳንዶች ታዲያ "ከኹሉም ሃይማኖት ጥሩ ጥሩውን ፣ የጋራውን እንውሰድ" በሚል መርሕ ሌላ ዓይነት ፕሮቴስታንቲዝምን ይዘውና ሃይማኖትን በልካቸው አበጅተው ብቅ ብለዋል። ይህንን የሚደግፉት በዋናነት ግላዊነትን የሚያበረታቱት ፕሮቴስታንቶችና ዓለማውያን ናቸው።
ኢሬቻም የዚሁ ኮፒ እየኾነ ነው። በኦሮሞ ፕሮቴስታንቶችና በፕሮቴስታንታዊው ኦዲፒ ከሞላ ጎደል ካለ ምንም ማንገራገር ይደገፋል። ኢኩሜኒዝም በክርስትና ስም የሚንቀሳቀሱትን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ ኢሬቻ/ዋቄፈና ደግሞ ሙስሊሙንም፣ ኦርቶዶክሱንም ፣ ፕሮቴስታንቱንም ማዕከል አድርጓል። ይህም በተለይ ኦርቶዶክሱን በኦሮሙማ ስም ከኦርቶዶክሳዊነት ለማለዘብ የተነደፈ ሴራ ይመስላል።
"ምን ችግር አለው?" የሚል ለዘብተኛ ኦርቶዶክስ ደግሞ በስም እንጂ በግብር የቤተ ክርስቲያን ሊኾን አይችልም። ስለዚህ በተለይ የኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን ትልቅ አስተዋይነትን የሚጠይቅ ጊዜ ላይ እንዳላችሁ ልትገነዘቡት ይገባል። ከኦርቶዶክሳዊነትና በተወዳጅ ባሕል ስም ከመጣ ሌላ እምነት መካከል ያላችሁ የምትወስኑበት ጊዜ እንደኾነ ይሰማኛል።
ኹለቱንም መኾን አይቻልም። ወይ ከጊዜ በኋላ በቅርቡ የሚበርደውን የወቅቱን ሞቅታ መምረጥ ወይም ደግሞ ካለችበት ከፍታ ላይ ሳትወርድ ለዘመናት የኖረችውን ተዋሕዶን መምረጥ ያሻል።
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንንና ምዕመኖቿን፣ ሀገራችንንና ዜጎችን ይጠብቅልን። አሜን።
hilinabzehohite@gmail.com
©ዘሕሊና
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 октября 2024 12:10
አኑሮኛል ቸርነትህ
አኑሮኛል ቸርነትህ ልክ የሌለው ደግነትህ
እንዳንተ አይነት ከየት ይገኛል
ሁሉም ነገር ትዝ ይለኛል/2/
እዝ
ያቺ ፈዋሽ አዳኝ እጅህ
ዛሬም ለኔ ተዘርግታ
በሐጢያት ርቄ እንዳልጓዝ
አስረኸኛል በውለታ
ደግሞስ ህይወት ምርጫ ቢሆን
ካንተ ወደማን ይኬዳል
አባቴ ፍቅርህ እኮ
ጌታዬ ፍቅርህ እኮ
አለምን ያስክዳል
እዝ
ሞቼ ነበር ተቀብሬ
ጌታ ወደ እኔ ባትመጣ
አንተ ሞቴን ባትሞትልኝ
ወዴት ነበር የእኔ እጣ
ከንቱ ነበር ማንነቴ
ተሽናፊ ለዚች ዓለም
ግን አንተ የያዝከው
አባቴ የያዝከው
ይኖራል ዘላለም
እዝ
መቅደስህን ተጠግቼ
አይቻለሁ ብዙ ነገር
በልቤ ውስጥ ያስቀመጥኩት
እንዲህ ለሰው ማይነገር
ግን የሆነው ሁሉም ሆኖ
የለም ዛሬ ያላረፈ
የመከራው እሳት
የፈተናው እሳት
ባንተ እየታለፈ
እዝ
አይጠፋኝም ያ ፈገግታ
ልጄ ብለህ ያሳየህኝ
አመፀኛ መጥፎም ሆኜ
በትክሻህ ላይ ያኖርከኝ
እንዲህም አይነት ወዳጅ አለ
እየጠሉት የሚያፈቅር
ስሙም ኢየሱስ ነው/2/
የፅድቃችን ሚስጥር
እዝ
ስነፈርቅ ሳለቅስብህ
እሺ እያልከኝ ሁሉም ሆነ
ማይሆንለት ነገር የለም
ለካስ ባንተ የታመነ
መቸኮሌ መጣደፌ
አምላኬ ሆይ በከንቱ ነው
መፈፀሙ ላይቀር/2/
ጌታዬ አንተ ያልከው
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 октября 2024 05:01
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
ከደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ
አዝ
በእቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር
ተክለሐይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና
ተክለሐይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ ከሰማይ
አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ ተክለሐይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ
ሠላሳ ሥልሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስኮ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና
ተክለሐይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጀ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
03 октября 2024 05:58
መስከረም ፳፫
በዚሕች ቀን ቅዱሳን ጻድቃን መነኮሳት አውናብዮስና እንድርያስ አረፉ።
እኒህ ቅዱሳን ከልዳ ሀገር ከታላላቆቹ ተወላጆች ናቸው ከታናሽነታቸውም በአምላካዊ ምክር ተሰማምተው በሶርያ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ሂደው መነኮሳትን ሆኑ።
ከዚህም በኋላ ወደ ከበረ ወደ ተመሰገነ ወደ አባ መቃርስ ሔዱ ደቀመዛሙርቱም ሁነው ታዘዙለት ምክሩንም በመቀበል በጾም በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምደው የሚኖሩ ሆኑ በእንዲህ ያለ ስራም ሦስት አመት ኖሩ በጎ የሆነ የተጋድሎአቸውና የአገልግሎታቸው ዜና በተሰማ ጊዜ አውናብዮስን መርጠው ኤጲስቆጶስነት እንድርያስን ቅስና ሾሙአቸው በበጎ አጠባበቅም የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቁአቸው። ከዚሕም በኋላ ስጋቸውን ፈጽሞ እስከአደከሙ ድረስ ተጋድሎአቸውንና አገልግሎታቸውን እጅግ አበዙ።
ከሀዲ ንጉስ ዮልዮስም ስለ እርሳቸው በሰማ ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደ እርሱ አስቀርቦ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ወደ ረከሰች አምልኮቱ እንዲገቡ አዘዛቸው ያን ጊዜ እርሱንና የረከሱ ጣዖታትን ረገሙ እርሱም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ወደ ብዙ ክፍልም ቆራርጦ ከፋፈላቸውና ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ።
እያንዳንዳቸውም ሦስት ሦስት አክሊላትን ተቀበሉ። አንዱ በገድል ስለ መጠመድና ስለ ምንኵስና ዋጋ ሁለተኛውም ስለ ክህነት አገልግሎት ሦስተኛውም ደማቸውን ስለ ማፍሰሳቸው ነው።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 октября 2024 19:53
የክርስትና አባት ወይም እናት
የክርስትና አባት እና እናት ዋነኛ ዓላማ ተጠማቂው በዕድሜው ወይም በእምነቱ ያልጠነከረውን ሰው ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን ለማስተማር፣ አስተምሮ ለማሳመን፤ አሳምኖም በክርስትና ጸንቶ እንዲቆይ የትሩፋት ሥራዎችን እየሠራ በበረከተ እግዚአብሔር ፀንቶ እንዲቆይ ማበርታት መምከር በመሆኑ ግንኙነቱ ፍፁም የሆነ መቀራረብን የልብ ምክክር እና ወዳጅነትን እንዲሁም ብዙ ጊዜ አብሮ በመቆየት መመካከርን የሚጠይቅ በመሆኑ ወንዶች ሴቶችን ወይም ሴቶች ወንዶችን ክርስትና ቢያነሱ በዚህ ሂደት ሁለቱ ተቃራኒ ፆታዎች በሚኖራቸው መቀራረብ በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ዝምድና ወይም የአባትና የልጅነት የእናትነት የልጅነት! የወንድም እና እህትነት ዝምድና ላይ ሥጋዊ ፍላጎቶች ገብተው ታላቁን መንፈሳዊ ዝምድና እንዳይጎዱት
ወንዶች ሴቶችን፤ ሴቶችም ወንዶችን ክርስትና ማንሳት አይገባቸውም፡፡ በመሆኑም የክርስትና አባት ወይም እናት የሚሆነው ሰው ኃላፊነቱን ከመቀበሉ በፊት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በታቦተ እግዚአብሔር እና በመስቀሉ ፊት ቆሞ ቃለ መሀላ ወይም ቃል ኪዳን ይገባል፡፡ በመሆኑም ምዕመናን ለልጆቻቸው የክርስትና አባት ወይም እናት ሲመርጡ ሃብቱን ገንዘቡን መልክና ቁመናውን ወይም ሌሎች ሥጋዊ ነገሮችን መሠረት አድርገው ሊሆን አይገባም፤ ይልቁንም ዋነኛው ዓላማ የተመራጩ እምነት ሃይማኖት ሊሆን ይገባል፡፡
ህፃናት ለምን በለጋ ዕድሜያቸው ይጠመቃሉ ?
ከኦርቶዶክሳዊት እምነት ውጭ የሆኑ አንዳንዶች ቤተ ክርስቲያን ህፃናትን በአርባ እና ስማንያ ቀናቸው ማጥመቋን የሚቃወሙ አሉ፡፡ ለዚህም እንደ አብነት አድርገው የወንጌላዊው የቅዱስ ማርቆስ ትምህርት
ማር 16፥16 "ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡"
የሚለውን ጠቅሰው ሰው መጠመቅ ያለበት ለአቅመ አዳም እና ሔዋን ከደረሰ እና እምነቱን ማረጋገጥ ከቻለ በኋላ ነው ይላሉ፡፡ ይኽም ለመጠመቅ መጀመሪያ ማመን ቀጥሎ መጠመቅ የሚገባ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ይሁን እንጂ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ስንመለከት ደግሞ ዮሐ 3፥5. እውነት እውነት እልሀለው ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ደግሞ ጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት የግድ አስፈላጊ መሆኑን ያስተምረናል፡፡ ስለዚህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰው ሞቱ አይታወቅምና ህፃናት ሳይጠመቁ ቢሞቱ ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዳይለዩ ስትል ህፃናትን ለአቅመ አዳም እና ሔዋን እስኪደርሉ እምነታቸውን መመስከር እስከሚችሉ ሳትጠብቅ አስቀድማ ታጠምቃለች። ለዚህ ደግሞ አሁንም መጽሐፍ ቅዱስን አብነት ታደርጋለች፡፡
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው"
— ማቴዎስ 28፥19-20
በዚህ ትምህርት ደግሞ መጠመቅ ቀዳሚ ለጥቆ ደግሞ መማር እና ማመን እንደሚከተል እንረዳለን፡፡ በዚህም ቤተ ክርስቲያን ትምህርቷ እና ሥርዓቷ መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን እንረዳለን።
በአንዲት ጥምቀት እናምናለን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ሰ/ት/ቤት
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 октября 2024 06:17
መስከረም ፳፪
በዚህች ቀን የከበረ ዮልዮስ በሰማዕትነት
ያረፈበት መታሰቢያ ነው።
ይህ ቅዱስ አቅፋሐስ ከሚባል አገር ሲሆን ክብር ይግባውና ጌታችን ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ለሥጋቸው እንዲያስብ ገድላቸውንም እንዲጽፍ ሥጋቸውንም ገንዞ እየአንዳንዱን ወደ ሀገራቸው እንዲልክ ያቆመው ነው።
ጽሕፈትም የሚያውቁ ሦስት መቶ አገልጋዮች አሉት እነርሱም የሰማዕታትን ገድላቸውን እየተከተሉ ይጽፋሉ። በመሠቃየትም ሳሉ ሰማዕታትን ያገለግላቸዋል በቁስላቸውም ውስጥ መድኀኒት ያደርግላቸዋል እነርሱም ይመርቁታል። እንዲህም ብለው ትንቢት ይናገሩለት ነበር፦
ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ደምህ ይፈስ ዘንድ አለህ ከቅዱሳን ሰማዕታትም ጋራ ትቆጠራለህ።
ቅዱሳን ሰማዕታትም ትንቢት እንደተናገሩለት በመኰንኑ ፊት ስለከበረ ስሙ ይታመን ዘንድ ለግብፅ አገር ደቡብ ወደ ሆነች ወደ ገምኑዲ ወደ መኰንኑ አርማንዮስ እንዲሔድ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዘዘው። ወዲያውኑ ተነሥቶ ሔደ ከዚያም ደርሶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ታላቅ ሥቃይን አሰቃየው፤ እግዚአብሔርንም ያለጥፋት በጤና ያነሳው ነበር።
ከዚሕም በኋላ ቅዱስ ዮልዮስ ብዙ ድንቅ ተዓምራትን እያደረገ ጣዖታትን እያጠፋ መከራና ሥቃይንም እየተቀበለ በሚያደርጋቸው ተአምራቶችም ጣዖት አምላኪ የነበሩትን አህዛቦች መኮንኖችና ወታደሮችንም ክብር ይግባውና በጌታችን ስም እንዲያምኑ አደረገ።
በመጨረሻም ቅዱስ ዮልዮስና ከእርሱ ጋር አንድ ሺህ አምስት መቶ የሚሆኑ ሰማዕታት አንገታቸውን ተቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበሉ።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 октября 2024 12:11
አለፍኩኝ ድንግል
አለፍኩኝ ድንግል ማእበሉን
አለፍኩኝ ድንግል ውጣ ውረዱን
ምርኩዜ ስለሆንሽ ስጠራ ስምሽን
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል በእመቤቴ ምልጃ
አለፍኩኝ ድንግል ወንዙን ስሻገር
አለፍኩኝ ድንግል ያባረረኝ ጠላት
አለፍኩኝ ድንግል ቀረ ሰምጦ ባህር
አለፍኩኝ ድንግል ከበሮውን ላንሳ
አለፍኩኝ ድንግል እንደ ሙሴ እህት
አለፍኩኝ ድንግል ምስጋና ልሰዋ
አለፍኩኝ ድንግል ለዓለም እመቤት
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል ወንድሞች ቢሸጡኝ
አለፍኩኝ ድንግል አሳልፈውኝ
አለፍኩኝ ድንግል በባዕድ ከተማ
አለፍኩኝ ድንግል ድንግል ሾመችኝ
አለፍኩኝ ድንግል በቅን የማመልከው
አለፍኩኝ ድንግል ልጅሽ ክርስቶስ
አለፍኩኝ ድንግል ምልጃሽን አስቦ
አለፍኩኝ ድንግል ሰጥቶኛል ሞገስ
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል በስምጥ ሸለቆ
አለፍኩኝ ድንግል ሆኜ ባጣብቂኝ
አለፍኩኝ ድንግል የምደገፍበት
አለፍኩኝ ድንግል አንዳች ሳይኖረኝ
አለፍኩኝ ድንግል ባንቺ ተርፌአለሁ
አለፍኩኝ ድንግል ምርኩዝ ሆነሽኝ
አዝ
አለፍኩኝ ድንግል ሰው የለኝም እና
አለፍኩኝ ድንግል ድንግል አትራቂኝ
አለፍኩኝ ድንግል አንቺው ነሽ እናቴ
አለፍኩኝ ድንግል የማትሰለቺኝ
አለፍኩኝ ድንግል ውለታዋ ብዙ
አለፍኩኝ ድንግል የድንግል ማርያም
አለፍኩኝ ድንግል እርሷን ለእኔ የሰጠ
አለፍኩኝ ድንግል ይክበር ዘለዓለም
ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 октября 2024 09:20
📕 መጽሐፈ ጤፉት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም መቀመጡን እና ሌሎች ጥንታዊያን ታሪኮች የሚናገር መጽሐፍ ነው።
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 октября 2024 05:01
ውል ውል አለኝ ደጅሽ
ውል ውል አለኝ ደጅሽ /፪/
የአምላክ ፈቃድ ሆኖ እስክሳለምሽ
ውል ውል አለኝ ደጅሽ /፪/
አዝ
የልቤን ፍላጎት ግሸን ላይ ነግሬ
ደስታ ቤቴን ሞላው ተረሳ ችግሬ
የግሸኗ እመቤት ልኑር በፍቅርሽ
ከአመቱ ሳትለዪኝ ልቁም ከደጅሽ
ውል ውል አለኝ ደጅሽአዝ
ሚካኤል ገብርኤል በቀኝ በግራ
አንቺ ከመሀል ነሽ ከፍ ባለ ስፍራ
የግሸኗ ንግስት ይነገር ዝናሽ፤
ግማደ መስቀሉን በክብር ያኖርሽ
ውል ውል አለኝ ደጅሽግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ /፪/
ለመንግስተ ሰማይ ምሳሌ የሆነዉ
ግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ /፪/
አዝ
ጉልበቴ በረታ ዳገት ቁልቁለት፤
በምልጃሽ እንዲያገኝ የሀጢያት ስርየት፤
ይናፍቃል ልቤ ደጅሽ እስኪደርስ፤
ጠበልሽን ልጠጣ በእምነት ልታበስ፤
ግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ፤አዝ
የእግዚአብሔር ሀገሩ ግሸን ደብረ ከርቤ፤
እረካሁ ከጥሜ ጠገብኩኝ ከራቤ፤
ሀምሳለ ገነት ነሽ ኢየሩሳሌም፤
አምላክ አክብሮሻል እስከ ዘለአለም፤
ግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ፤አዝ
የመስቀል ቅርፅ ነው የተራራው ራስ፤
ሁሉም ይናፍቃል ደጅሽ እስኪደርስ፤
ተገልጾ የታየበት የክርስቶስ ፍቅር፤
የእግዚአብሄር አብ መቅደስ አለ በክብር፤
ውል ውል አለኝ ደጅሽነፍሴን አለሟን አሳየዋት /፪/
በአለማዊ ግብር ካላበላሸዋት
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
30 сентября 2024 12:58
እቴ ሙሽራዬ
እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ /2/
እኔም ልበልሽ እናቴ
እመ አምላክ ግቢ በቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ
ማርያም ግቢ በቤቴ
አዝ
ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ
የክብርን ሽልማት ራሱን ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባርያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ
ነይ በደመና /4/ እመቤታችን ርህርህተ ህሊና/2/
አዝ
ወርቀ ዘቦ ለብሰው ከቤቱ ከሞሉት
በሐርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ
ነይ በደመና /4/ እመቤታችን ርህርህተ ህሊና/2/
አዝ
አሳድጎሽ ሳለ መልአኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተዉቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መልአክ ጌታን ተሸከምሽው
ነይ በደመና /4/ እመቤታችን ርህርህተ ህሊና/2/
አዝ
የባርያውን ውርደት ተመልክቷልና
ለወለድሽው ንጉስ ይድረሰው ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጂ ከንቱውን አይደለም
ብጽዕት እንላለን እኛ ለዘላለም
ነይ በደመና /4/ እመቤታችን ርህርህተ ህሊና/2/
ዘማሪ ቀሲስ አሽናፊ ገ/ማርያም 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
30 сентября 2024 05:59
መስከረም ፳
በዚህች ቀን ለሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባት አትናቴዎስ አረፈ።
ይህም አባት አስቀድሞ የእስክንድርያ አገር ቤተክርስቲያን መጋቢ ነበር፤ ከእርሱም በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ሁሉም ኤጲስቆጶሳት መኳንንቱና ሊቃውንቱ ሕዝቡም በአንድ ምክር ተስማሙ።
በእግዚአብሔር ሕግ በመጽናት ያደረገው መልካም ተጋድሎውና ቅድስናው ስለእርሱ ስለተነገረ መንፈስ ቅዱስም እንደ አደረበት ስለ ተረዱ
ያለ ፈቃዱም ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በምክሩ፣ በትምህርቱ፣ በጸሎቱ ከዲያብሎስ ተኵላዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው እኒህም ሃይማኖትን የሚለውጡ መናፍቃን ናቸው። በሊቀ ጵጵስናውም ፯ ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
29 сентября 2024 17:26
ለዘማርያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ።
የዝማሬ ዳዊት የዩቲዩብ ገጽ ዝማሬዎቻችሁን ወደ ምእመናኑ ለማድረስ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።
በዚህም መሰረት ዝማሬ ሰርታችሁ ለምእመናኑ ሳይደርስ በቤታችሁ አስቀምጣችሁ ያስቀራችሁ፤ አዳዲስ ዝማሬ እየሰራችሁ ያላችሁ እና ለመስራት በመንገድ ላይ ያላችሁ በሙሉ፤ የዝማሬ ዳዊት ገጽ ስራችሁን ወደ ምእመናኑ ሊያደርሳችሁ ዝግጅቱን አጠናቋል።
በዚህም መሰረት ዝማሬዎቹን በዝማሬ ዳዊት የዩቲዩብ ገጽ ለማስተላለፍ መሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች በውስጥ መስመር የምናሳውቃችሁ ይሆናል። እኛን ማግኘት ለምትፈልጉ
📩 @
📩 @ ወይም
📞 +251703408851 ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። የምታውቁት ሰው ካለም እባክዎ ይህን ዕድል ይጠቁሙ።
በተጨማሪም ዘማሪ መሆን የምትፈልጉ እና ጸጋው ያላችሁ ወንድም እህቶቻችን እግዚአብሔር ከፈቀደልን ትልቅ ዕድል ይዘን እየመጣን ስለሆነ እራሳችሁን አዘጋጅታችሁ ጠብቁን። ጅማሬዎቻችን ሁሉ መልካም ፍጻሜ እንዲኖራቸው በጸሎታችሁ አስቡን።
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
29 сентября 2024 05:52
መስከረም ፲፱
በዚች ቀን ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ከዐዘቅት የወጣበት መታሰቢያው ነው።
ይህም በንጉሥ ድርጣድስ ዘመን በአርማንያ አገር ራሱን ባሪያ አድርጎ ይኖር ነበር። ንጉሡ ከሀዲ ነበርና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ጣዖቱን ዕጣን እንዲያጥን አዘዘው። ቅዱሱም የንጉሱን ትዕዛዝ ባለመስማቱም እጅግ በጣም አሰቃየውና ከጥልቅ ጉድጓድ ጣለው በዚያም ለ15 ዓመት ኖረ። በዚያም በጉድጓድ ሳለ
እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ምግቡን የምትወረውርለት አንዲት ሴት አዘጋጀለት።
በዚያም ወራት ይህ ንጉሥ ድርጣድስ ደናግሎችንና ቅድስት አርሴማን ገድሎ ሥጋቸውም በተራራ ላይ ተጣለ።
እግዚአብሔርም ከሰራው ክፋት የተነሳ የተፈጥሮ መልኩን ለውጦ እንስሳ አደረገው።
የንጉሡ እኅት ግን በራእይ "ጎርጎርዮስን ከጉድጓድ ውስጥ ካላወጣችሁት አትድኑም" የሚላት ሰውን አየች ለወገኖቿም ነገረቻቸውና እንርሱም ሒደው ቅዱስ ጎርጎርዮስን ከጎድጓድ አወጡት በዚያን ጊዜም ቅዱሳት ደናግልን ሥጋቸውን ገንዞ በመልካም ቦታ አኖራቸው ከዚያም በኃላ ንጉሡንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም ወደ ሰውነት መለሳቸው።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
28 сентября 2024 20:21
ለዘማርያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ።
የዝማሬ ዳዊት የዩቲዩብ ገጽ ዝማሬዎቻችሁን ወደ ምእመናኑ ለማድረስ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።
በዚህም መሰረት ዝማሬ ሰርታችሁ ለምእመናኑ ሳይደርስ በቤታችሁ አስቀምጣችሁ ያስቀራችሁ፤ አዳዲስ ዝማሬ እየሰራችሁ ያላችሁ እና ለመስራት በመንገድ ላይ ያላችሁ በሙሉ፤ የዝማሬ ዳዊት ገጽ ስራችሁን ወደ ምእመናኑ ሊያደርሳችሁ ዝግጅቱን አጠናቋል።
በዚህም መሰረት ዝማሬዎቹን በዝማሬ ዳዊት የዩቲዩብ ገጽ ለማስተላለፍ መሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች በውስጥ መስመር የምናሳውቃችሁ ይሆናል። እኛን ማግኘት ለምትፈልጉ
📩 @
📩 @ ወይም
📞 +251703408851 ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። የምታውቁት ሰው ካለም እባክዎ ይህን ዕድል ይጠቁሙ።
በተጨማሪም ዘማሪ መሆን የምትፈልጉ እና ጸጋው ያላችሁ ወንድም እህቶቻችን እግዚአብሔር ከፈቀደልን ትልቅ ዕድል ይዘን እየመጣን ስለሆነ እራሳችሁን አዘጋጅታችሁ ጠብቁን። ጅማሬዎቻችን ሁሉ መልካም ፍጻሜ እንዲኖራቸው በጸሎታችሁ አስቡን።
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 октября 2024 19:41
በገና
“በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት“መዝ.፻፶፥፫ (150፥3)
አባታችን ቅዱስ ዳዊት አምላካችንን በበገናና በመሰንቆ በጠቀስናቸው የመዝሙር ዕቃዎች ሁሉ ያመሰግን እንደነበር ሌሎችም አባቶቻችን እና እናቶቻችን እንደርሱ ለእግዚአብሔር ይዘምሩ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ከምስጋናው ተጨማሪ በዚህ ዓይነት ዝማሬ አጋንንትና ርኩሳን መናፍስት ደዌና ሕማም ሁሉ ከሰው ልጆች ይርቁ እንደነበር ዛሬም እንደሚርቁ ተጽፎልናል። ቅዱስ ዳዊት አባታችንን ባሰብን ጊዜ ሁሉ በገናው አብሮ ይታሰበናል።
አባታችን ነቢዩ መዝሙረኛው ዳዊት በገና እየመታ የእግዚአብሔርን ስም ከማመስገን ጋራ በነቢዩ ሳሙኤል በተቀባ ጊዜ ከተሰጡት ከሰባቱ ሀብታት አንዱ ሀብተ ፈውስ ስለሆነ ንጉሥ ሳኦል የሚያስጨንቅ ርኩስ መንፈስ ሲያሠቃየው በበገናው ዝማሬ ይፈውሰው ነበር። “
እንዲህም ሆነ … ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር። ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር ክፉ መንፈስም ከርሱ ይርቅ ነበር።” ፩ ሳሙ. ፲፮ ፥፳፫ (16:23)
ቅዱስ ዳዊት ለእግዚአብሔር በሚዘምርበት ጊዜ በሙሉ ኃይሉና ክብሩ ነበር። ያልታደለች ሜልኮል እስከምትቀልድበት ድረስ ለእግዚአብሔር ታቦት ካባው ከላዩ እስኪወድቅ በተመሰጦ ይዘምር ነበር። 2ኛ ሳሙ.6
ዛሬም እንደ ሜልኮል ሰዎች እንዳይዳፈሩ የታቦቱንም ዝማሬ እንዳይንቁ ቢንቁ ግን የሚደርስባቸውን ቀድመው እንዲያውቁት እግዚአብሔር ነግሮናል። ሜልኮል የዳዊትን በእግዚአብሔር ፊት መዘመር በናቀች ጊዜ እግዚአብሔር ማህፀኗን ዘጋ። ቅዱስ ዳዊት ግን አሁን ከሆንኩት በላይ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ በሰው ፊትም አከብረዋለሁ አለ። ዘወትርም እንዲህ እያለ ያመሰግን ነበር። ”
በገና ሆይ ተነሥ መሰንቆም እኔም ማልጄ እነሣለሁ” አቤቱ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ። መዝ(107:2)
ሰኞ ምሽት ስለ በገና አሠራሩና ምሳሌነቱ እንመለከታለን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ ፦ መጽሐፈ አሚን ወስርዓት
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 октября 2024 17:33
ኢሬቻ/ዋቄፈና/ ለክርስቲያን ምኑ ነው?
(በዲ/ን ሕሊና በለጠ)
ቤተ ክርስቲያን በባሕርይዋ የአንድ ማኅበረሰብን ባሕል ንቃም ኾነ ተቃውማ አታውቅም። በተቻላት መጠን ማኅበረሰቡ ከነ ባሕሉ ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ሃይማኖቷንና ሥርዓቷን አስተምራ ታስተናግደዋለች እንጂ። ከእርሷ አምልኮ በተቃራኒው የሚያመልክ የአንድን ተገዳዳሪ የእምነት ተቋም አምልኮም በማይገባ መልኩ ተችታና አኮስሳ አታውቅም፤ እውነተኛውን መንገድ ግን በተገቢው መልኩ በጥብዓት ታስተምራለች። የዚያ የእምነት ተቋም አምልኮና እምነት ስሕተት ከኾነ ሰዎች ኹሉ ይድኑ ዘንድ እውነትን ትሰብካለች፤ ወደ እውነት ትመራለች፣ ታደርሳለች።
ኢሬቻ ምንድን ነው? ባሕል ነውን?
መልካም፣ ባሕልስ ከኾነ ቤተ ክርስቲያን የባሕሉን አክባሪ ባሕሉን ሳይዘነጋ ይቀበላት ዘንድ አይገዳትም። እርሷም ከነ ባሕሉ ዐቅፋና ደግፋ ትቀበለዋለች።
ግን ኢሬቻ ባሕል ነው?
አይመስለኝም። ሰሞንኛ ተናጋሪዎችን እንዘንጋቸውና እስኪ እንዴት እንደተከበረ እንመርምር። የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች ውኃ ውስጥ ሣር እየነከሩ ወይም ዛፍን ቅቤ እየቀቡ ፈጣሪን ሲያመሰግኑ የሚያሳዩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ስናይ ነበር። ስለዚህ ይህ በዓል:-
#1ኛ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ነው (ይህም ተደጋግሞ በአክባሪዎቹ እየተነገረ ነው)። በፈጣሪ መኖር ማመን ደግሞ: ለሃይማኖት ህልውና የመጀመሪያው መስፈርት መኾኑን ልብ ይሏል። ስለዚህ ኢሬቻ/ዋቄፈና/ ለሃይማኖትነት ትልቁን መሥፈርት አሟልቷል ማለት እንችላለን።
#2ኛ የታወቀ የምስጋና (አምልኮ?) ሥርዓት (ለምሳሌ:- ሣር ውኃ ውስጥ መንከር፣ ቅቤ መቀባት ...) አለው። ይህም እስልምናም ኾነ ክርስትና የታወቀ የአምልኮ ሥርዓት እንዳላቸው ማለት ነው።
#3ኛ እስልምና መስጊድ፣ ክርስትናም ቤተ ክርስቲያን እንዳላቸው ኹሉ: ኢሬቻም /ዋቄፈናም/ ይህ ሥርዓት የሚፈጸምበት ቦታ (Sacred Place, ለምሳሌ:- ውኃና ዛፍ ያለበት ሥፍራ) አሉት።
#4ኛ ሃይማኖታዊ የአምልኮ ሥርዓት በካህናት እንደሚመራ: ክብረ በዓሉን የሚመሩ የሥርዓት መሪዎች (አባ ገዳዎች?) አሉት።
ስለዚህ ወይ አምልኮ ነው፣ ወይም ደግሞ ከቆይታ ብዛት ወደ ባሕልነት የተቀየረ አምልኮ ነው።
#ዐቢይነጥብ - ከላይ ከጠቀስናቸው ከዐራቱ ለጊዜው አንዱን ብቻ እንምረጥ -
-ፈጣሪ የሚመሰገንበት መኾኑ
ይህ ብቻ "ባሕል ነው" ለሚሉት ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያስገድድ ምክንያት ነው።
ፈጣሪን ማመስገን የሚቻለው በእምነት ነው። በመጀመሪያ ይህን ፈጣሪ ማመንና በጥቂቱም ቢኾን በእምነት ማወቅ ይገባል። ቢያንስ ፈጣሪ መኾኑን በእምነት መረዳት ያሻል። ከዚያም እርሱ በሚፈልገው ሥርዓት እርሱን ማመስገን/ማምለክ ይከተላል። እርሱን ማምለኪያ ውሱን ሥርዓት የለም ቢባል እንኳን: የማመስገኛ ሥርዓቱ "ሥርዓት የለሽ በመኾን" ይገለጻል፤ (non-religiousness is my religion) እንዲል አንድ የፍልስፍና መምህር /ፈላስፋ ላለማለት ነው/)።
ሙስሊሙ ፈጣሪን የሚያመሰግንበት ሥርዓትና ቦታ አለው፤ ሳምንታዊ(ጁምዓ) እና ዓመታዊ (ኢድ አል ፈጥር፣ ኢድ አልአድሃ) የበዓላት ዕለታትም አሉት። ክርስቲያኑም እንዲሁ ከሳምንታዊ ሰንበትን፣ ከዓመታዊ ልደትና ትንሣኤን የመሰሉ (ዕለታዊና ወርኃዊውን ጨምሮ) ብዙ በዓላት አሉት። ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በየበዓላቱና በየታወቀ ሥርዓቱ ፈጣሪን ያመሰግናሉ፣ ያመልካሉ። ነገር ግን ክርስቲያኑ ኢሬቻ የሚል ፈጣሪን የማመስገኛ በዓል በዚቁ (liturgical Calendar) ውስጥ የለም። ሙስሊሙም እንደዚያ።
ሌላው ነጥብ: ኹሉም እምነት ፈጣሪን የተመለከተ መሠረተ-ትምህርቱ (Doctrine/Creed) ከሞላ ጎደል ይለያያል። ሙስሊሙም (ካልተሳሳትኩ) "ላ ኢላህ ኢለላህ መሐመዱር ረሱለላህ" የሚል ሸሀዳ (Creed) አለው። ይህንን አዘውትሮ ያደርሳል። ፕሮቴስታንቱ "ክርስቶስ አማላጄ" (ሎቱ ስብሃት) ይላል። እኛ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ "ኹሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚኾን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን" ከሚለው ጀምሮ የክርስቶስንና የመንፈስ ቅዱስን አንድ የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ጋር መተካከል፣ የቤተ ክርስቲያንን ኲላዊነት፣ አንድነት፣ ቅድስናና ሐዋርያዊነት፣ የጥምቀትን የኃጢአት ማስተሥሪያነት፣ የትንሣኤ ሙታንን ተስፋነት የምንመሠክርበት የዘወትር ጸሎተ ሃይማኖት (Creed) አለን።
እነዚህ እምነቶች ይለያያሉ ብቻም ሳይሆን ይቃረናሉ። እንዴት በአንድነት ምስጋናቸውን ለአምላክ ያደርሳሉ?
እኔ አምላክ የምለውን ክርስቶስን አንዱ ከአጠገቤ "አማላጄ" እያለው እንዴት አንድነት ይኖረኛል? አንዱስ "ነቢይ" እያለው እንዴት አብረን እናመሰግናለን? የኔን አምላክ አማላጅም ፣ ነቢይም ማለት እርሱን ማሳነስ ለእኔም ንቀት ነው።
ሙስሊሙም አላህን አምላክ ይላል። ኢሳን ነቢይ ይላል። እኔ ከጎኑ ቆሜ ኢየሱስ ክርስቶስን "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ስል እንዴት ይዋጥለታል?
አብረን ቡና የምንጠጣ፣ አብረን ኳስ የምንጫወት፣ በንግድ የምንተባበር ሙስሊሞችና ፕሮቴስታንቶች ይኖራሉ። በጣም የምንዋደድ ጓደኛሞችና የሥራ ባልደረቦች ልንሆን እንችላለን። ግን ለአምልኮ ሙስሊሙም መስጊድ፣ ፕሮቴስታንቱም "ቸርች" እኛም ቤተ ክርስቲያን እንሔዳለን እንጂ ፈጣሪን ለማመስገን መስጊድ ወይም ቤተ ክርስቲያን በአንድነት አንሔድም።
አንድ የምንኾንበትንና የማንኾንበትን እንለይ እንጂ! በኢትዮጵያዊነት አንድ ነን፤ በባሕል እንተባበራለን፤ በልማት አንድ መኾን እንችላለን፤ እንኳን በሀገር በቤተ ዘመድም በሃይማኖት መለያየት ይገጥመናል፤ ዝምድናን ጨምሮ ግን ብዙ አንድ የሚያደርጉን ጉዳዮች አሉን። ኾኖም በሃይማኖት አንድ ካልኾንን ከእናቴም ጋር ለጸሎትና ለምስጋና አልቆምም።
እንኳን ከሙስሊምና ከፕሮቴስታንት ጋር ይቅርና በብሉይ ኪዳን በሃይማኖት አንድ ከነበርነው ከይሁዲውም ጋር ፈጣሪን ለማመስገን በአንድነት አንቆምም። የይሁዲው መሠረተ ሃይማኖት ( ሸማ፣ Creed) በእኛው ብሉይ ኪዳን ላይ ዘዳ.6÷4-9 ያለው ንባብ ነው። ይሁዲዎች ይህንን በእጃቸው ያሥሩታል (Teffilin)። በበራቸውም ይጽፉታል (Mezzuzah)። ንባቡ እኛም የምናምንበትና የምናነበው ነው። ነገር ግን ምንም ያኽል ብንወዳቸው ክርስቶስን ከማያምኑት ከይሁዲ እምነት (Judaism) ተከታዮች ጋር የሃይማኖት ኅብረት የለንም።
ወንጌላችንም ያዘናልና "ቢቻለንስ በእኛ በኩል ከሰው ኹሉ ጋር በሰላም መኖርና ሰላምን መከታተል" የክርስትና መርሐችን ነው። (ሮሜ 12÷18፣ ዕብ. 12÷14)። ኾኖም ፈጣሪን የምናመሰግንበት የሃይማኖት ኅብረት የሚኖረን ግን ከተጠመቁት ጋር ብቻ ነው።
#ይቀጥላል
#ሼር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
04 октября 2024 06:01
መስከረም ፳፬
በዚህች ቀን ቅዱስ አባት መነኰስ ጎርጎርዮስ አረፈ።
የዚሕም ቅዱስና የተመሰገነ ጎርጎርዮስ ወላጆቹ ደጎች እና ባለጸጎች ነበሩ ይህን ልጃቸውን ጎርጎርዮስንም የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ሁሉ ሥጋዊም የሆነ ጥበብንና ቋንቋንም አስተማሩት። የሀገራቸው ኤጲስቆጶስ አባ ይስሐቅ እጁን ጭኖ አናጒንስጢስነት ሾመው ዳግመኛም ወደ ጳጳስ ወስደው ዲቁናን ተሾመ።
ከወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ወስዶ ወደ አባ ጳኵሚስም ቀርቦ ለሕንጻ ለቤተክርስቲያን፣ በገዳማቱ ለሚሰሩ ስራዎችና ለመነኮሳት ቤት መሥሪያ ተሳትፎ አደረገለት። ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኵሚስም ገዳም ሄዶ የምንኩስናን ልብስ ለብሶ በጾም በጸሎት በመትጋት በመስገድ ከትሕትና ከቅንነት ከፍቅር ጋር ይጋደል ጀመረ።
ፈሪሃ እግዚአብሔርን ከእርሱ ተምረው አመንዝራዎች ንስሐ ገብተው ንጹሐንም እስከሆኑ ድረስ ተጋደሉ። ከአባ ጳኵሚስም ዘንድ ዐሥራ ሦስት አመት ኖረ። ዳግመኛም በአስቄጥስ ገዳም ከአባ መቃርስ ጋር ብዙ ዘመናት ኖረ። ከዚሕም በኋላ በዋሻ ውስጥ ሰባት አመት ኖረ።
አባ መቃርስም በከበረ በጌታችን የልደት በዓል እና የክብር ባለቤት ጌታችን በተነሳበት በትንሣኤ በዓል ቀን ይጎበኘው ነበር ከእርሱ ጋርም ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ይመለስ ነበር። ሃያ ሁለት ዓመታት በተጋድሎ ፈጸመ j እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ከሦስት ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ወጥተህ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትገባለህ አለው። ከሦስት ቀንም በኋላ አርፎ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ገባ።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
03 октября 2024 11:58
ፈተና ወጀብ ቢበዛ
ፈተና ወጀብ ቢበዛ
አይተናል ሕዝቡን ሲያበዛ
በሕይወት አንዴ ጠርቶናል
እግዚአብሔር መች ይተወናል/2/
አዝ
ፍቅር ነዉ የናርዶስ ሽቶ
ወደደን ተሰቅሎ ሞቶ
ነጎድጓድ መብረቅ ቢሆንም
በህይወት አለን አሁንም/2/
አዝ
መኳንንት ደጁን ክፈቱ
የፀጋዉ ፈልቷል ዘይቱ
ተራግፏል ሸክማችን
ምህረቱ ቢፈስልን/2/
አዝ
ተጽናንቷል አርፏል ልባችን
በእሳት ታጥሮአል ቅጥራችን
አንወድቅም አንሸነፍም
ይዞናል የአምላካችን ስም/2/
አዝ
ሕይወት ነህ የፅድቅ ጥላ
ያውቅሐል ቃል የተመላ
ነህ አንተ ጣፋጭ ምግባችን
እግዚአብሔር ቸሩ አምላካችን/2/
ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
03 октября 2024 05:00
ሰማዕተ ኢየሱስ
ሰማዕተ ኢየሱስ የእውነት ምስክር
ሕያው ነው በሰማይ ብፁዕ ነው በምድር
ደራጎንን በጦር ወግቶ ገደለና
ከሞት አፍ አዳነኝ ጊዮርጊስ ደረሰና/2/
አዝ
የኀዘን ማዕበል እንዳያንገላታኝ
ተዓምር ሰሪው ሰማዕት ፈጥኖ አረጋጋኝ
በእግዚአብሔር ጣዕም በፍቅሩ ተጠምዷል
ይህን ዓለም ንቆ በክብር አጊጧል
ኦ ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ንፋስ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት አገሬን ከገጠማት ትካዝ
አዝ
እርሱን ለምጠራው ሲመሽም ሲነጋ
ዋስ ጠበቃዬ ነው በነፍስም በሥጋ
ድንቅን የሚፈጽም ኃያል ሰማዕት ነው
በቅድመ እግዚአብሔር ለእኔ የሚቆመው
ኦ ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ንፋስ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት አገሬን ከገጠማት ትካዝ
አዝ
የምስጋናን አውታር የታጠቀ ሰማዕት
ስሙን ተሸክሞ የታመነ እስከ ሞት
ሙታን የሚያስነሳ ስልጣን ተቀብሏል
በአባቱ መንግስት እንደ ፀሀይ ደምቋል
ኦ ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ንፋስ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት አገሬን ከገጠማት ትካዝ
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 октября 2024 12:00
ቀስተ ደመና
ቀስተ ደመና
የኖህ ቃል ኪዳን መተማመኛ
ቃል ገብቷል ባንቺ
እንዳያጠፍን በሞት ዳግመኛ
መድኅኒት ወልደሽ
ለጠፍው ዓለም ደስታ የሆንሽ
ሰንደቃችን ነሽ ለዓለም እንጠቁምሽ
አዝ
ጌታ ምልክት ይሰጣችኋል
የድንግል ፍሬ ያድናችኋል
የአዳም ታሪክ ተገለበጠ
ሞት በልጅሽ ሞት ስለተዋጠ /2/
አዝ
አሰልፎናል ለክብርሽ ዜማ
የመማፀኛ የድል ከተማ
ሞልቶ ይፈሳል ፀጋ ምልጃሽ
ክብራችን በዝቷል ስናከብርሽ /2/
አዝ
መልዐክ ነገረን ታላቁን ነገር
እንደምቶልጂው ያለ ወንድ ዘር
ጌታ በልቡ ስለሳለሽ
የሁሉ ፍጥረት ብጽእት አለሽ /2/
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
02 октября 2024 05:00
ባለ ውለታዬ
ባለውለታዬ /2/
ከአመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ
አዝ
በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ
ዝቅ አደርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘ ጌታዬ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ /2/
አዝ
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራዬ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታዬ
መዓረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ /2/
አዝ
ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ
ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ
ፈረደችባቸው ኃጢአትም በእነርሱ
በሠላም ሂድ ብሎ ምሮኛል ንጉሱ /2/
አዝ
የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ
በሰራልኝ ሥራ በእድሜ በዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ /2/
ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 октября 2024 09:24
እንኳን ለግሸን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ግሸን ደብረ ከርቤ
ሃገራችን ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል። (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው። የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም። "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች። ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም።"
ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው። ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን። ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል።
በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን። ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ።
የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው። እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል።
አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል። አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል።
አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው። ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል።
በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል። ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት በመዳብ በናስ በብር በወርቅ ለብጦ ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል።
በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል። ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል። መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው። ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው።
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
01 октября 2024 06:09
መስከረም ፳፩
በዚችም ቀን ቅዱስ ቆጵርያኖስና፤ ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት አረፉ።
ቅዱስ ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሃዲና ሥራየኛ ነበር። በሥራዩም የሚበልጠው ካለ ሊማር ከሌለ ግን በእነርሱ ላይ ሊመካባቸው ወደ አንጾኪያ አገር ሔደ። በዚያም አንድ ጎልማሳ ነበረ። ላይዋ የሚያምር አንዲትን ድንግል ብላቴና ወደ ቤተ ክርስቲያን በምትሄድ ግዜ እያያት በእርሷ ፍቅር ልቡ እንደ እሳት ተቃጠለ በገንዘብ፣ በማስፈራራት፣ በስራይ ስራም ሊያገኛት አልተቻለውም።
ጎልማሳውም ለቆጵርያኖስ ነገረው እርሱም ዮስቴናን እንዲያመጡለት አጋንንትን ላካቸው ከጸሎቷ የተነሳ ወደእርሱ ሊያመጧት አልቻሉም። ቆጵርያኖስም አጋንንቱን ድንግል ዮስቴናን ካላመጣችሁልኝ ክርስቲያን እሆናለው አላቸው። በዚሕም ጊዜ አንዱ ሰይጣን ዮስቴናን ተመስሎ ለቆጵርያኖስ ታየው።
ቆጵርያኖስም እውነት መስሎት በደስታ የሴቶች እመቤት ዮስቴና መምጣትሽ መልካም ሆነ አለ። ስሟን በጠራ ጊዜም በእርሷ አምሳል የተመሰለው ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ። በዚሕ ጊዜ በልቡ ስሟን በጠሩበት ቦታ እንደጢስ የሚበተኑ ከሆነ በፊቷ ሊቆሙ እንዴት ይቻላቸዋል ብሎ ወዲያውኑ የጥንቆላ መጻሕፍቶቹን አቃጠለ።
ከዚሕም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ተጠምቆ የምንኩስና ልብስን ለበሰ። ዲቁና ዳግመኛም ቅስና ተሾመ። ቅድስት ዮስቴናንም ወስዶ ለደናግል ገዳም እመ ምኔት አደረጋት። በኋላም ከሀዲው ንጉስ ዳኬዎስ ስለእነርሱ ሰማ፤ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖቶቹ እንዲሰግዱ አዘዛቸው ትዕዛዙን ባልሰሙ ጊዜ ብዙ ሥቃይን አሠቃያቸው። በኋላም የቅዱስ ቆጵርያኖስን የቅድስት ዮስቴናን እራሳቸውን አስቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
30 сентября 2024 19:39
ማማተብ
ጸሎት በምንጀምርበት ጊዜና በምንፈጽምበት፣ በምንሰግድበትና በምንሳለምበት፣ አንዲሁም
መስቀልን የሚያነሳ ቃልን በምንጸልይበት ጊዜ የሚያስደነግጥ ነገርን በምንሰማበትና በምናይበት ጊዜ
በመስቀል አምሳል ገጻችንን እናማትባለን። ጸሎት በምንጀምርበት ጊዜ በማማተብ ይህንን ቃል እንላለን፡-
ይህን በምንልበት ጊዜ
ፊታችንን ከግንባራችን ጀምረን ወደታች ወደ ደረት እንወርድና ከዚያ ወደ ግራ ሔደን ወደ ቀኝ እንመለሳለን። በዚህ ጊዜ መስቀል እንሠራለን። ይህም በጣታችን የመስቀል ምልክት በመሥራት ነው። በዚህ ጊዜ የሰይጣን መንፈስ ይርቃል መንፈስ ቅዱስ ይቀርባል። በጣታችንም የምናማትብበት ምሥጢሩ ይህ ነው፡፡
“እኔ ግን
በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ አንግዲህ
የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።” ሉቃ11፥ 20
በማማተብ ያለ ምሥጢር
በመጀመሪያ በቀኝ እጅ ጣታችን
የመስቀል ምልክት እንሠራለን። ይህም
መስቀል ምልክታችንና ዓርማችን አንደሆነ እንመሰክራለን። ከዚያም ገጻችንን እናማትባለን። በዚህም ጊዜ የምናስበውና የምንመሰክረው ምሥጢር በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ኃይል ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገራችንን ነው።
ከግንባር ጀምረን ከላይ ወደ ደረት ወደታች በምንወርድበት ጊዜ አምላካችን እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ስለእኛ በዚህ ምድር ሞትን ቀምሶ እኛን የማዳኑን ነገር እናስባለን።
በመቀጠልም ወደ ግራ አድርገን ወደቀኝ ተመልሰን ማማተባችን በኃጢአታችን ምክንያት ያመጣነውን ሞት አጥፍቶ ከግራ ቁመት፤ ከነፍስ ስደት አውጥቶ ወደ ቀኝ ቁመት ገነት መንግሥተ ሰማያት እንደመለሰንና እንዳስገባን አምነን የምናስብበት ነው። እንደገናም በኃጢአት ብንወድቅ በንስሐ አጥቦ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ በቀኝ ከሚቆሙት ቅዱሳን ጋር እንዲቆጥረን እንማጸናለን።
ድኅነታችንን ሁልጊዜ ከማሰብ ጋራ በምናማትብበት ጊዜ የሰይጣንን መንፈስ የምናርቅበት ኃይላችን የሆነ
መስቀልን እንደምንመካበት እንገልጻለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ ፦ መጽሐፈ አሚን ወስርዓት
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
30 сентября 2024 06:20
አዲሱን የዝማሬ ዳዊት የቲክቶክ ገጽ ይከተሉ!
https://vm.tiktok.com/ZMhMKp9NY/
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
30 сентября 2024 05:02
ማረኝ
ማረኝ /3/ መመኪያዬ
አርጅቻለሁ እና በኃጢያት ጎስቁዬ/2/
አዝ
ከፊቴ ናትና ኃጢያቴ ሁል ጊዜ
ተዉጫለሁ እኔስ
በሐዘን በትካዜ/2/
በፊትህ ክፋትን አድርጌያለሁ እኔ
ምንም ጽድቅ አልሰራሁ
በሕይወት ዘመኔ/2/
አዝ
ከፊትህ መቅበዝበዝ መሰደድ ፈለኩኝ
ኃጢያት ከኋላዬ
እያሳደደችኝ/2/
ወዴት እሄዳለሁ መሸሸጊያም የለኝ
ምህረትህ መጠጊያ
ዋሻ ካልሆነችኝ/2/
አዝ
የተሰባበረዉ አጥንቴ እንዲጠገን
በምህረት እና
በቸርነት ዳሰኝ /2/
የቀና መንፈስን አድስ በልቤ ዉስጥ
ነፍሴ በእሽታ
በተስፋ ትለወጥ /2/
አዝ
ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትዉሰድ
በንስሐ ድኜ በተስፋ እንድራመድ
አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ እና
በደስታ ልስገድ
በፍቅርህ ልፅናና/2/
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
29 сентября 2024 11:51
አለና ሚካኤል
አለና ሚካኤል አምላኩን ማለደው
ዘወትር ስለ እኛ መለመን ስራው ነው
አዝ
ሕፃናት በረሃብ ሲረግፉ አይቻለሁ
ስለዚህ አምላኬ ልማልድህ መጣሁ
ምድር ብረምጣድ ሆና ተቃጥላለች
እናት ለልጆቿ የምትሰጠው አጣች
አዝ
የሻገተ እንጀራ ፍርፋሪ ጠፋ
ምድር በውሃ ጥም በርሃብ ተቀፅፋ
ስለዚህ ታረቀው ይቅር በለው አለ
ሚካኤል በሰማይ ከአምላኩ ፊት ሳለ
አዝ
አይቻለሁ አለ ሰባ ዓመት ሲቆጣ
የምሕረት ፀሐይ በኢትዮጵያ ይውጣ
ሜዳው አረጓንዴ አበባ ይሞላ
ደመናው ይመለስ የምሕረት ጥላ
አዝ
ሚካኤል አምላኩን ማለደው በብርቱ
ዳግም እንድታበቅል አዝርዕት መሬቱ
ጠላትም እንዲያፍር ሕዝቡም እንዲፅናና
እግዚአብሔር በምሕረት በረድኤትህና
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
29 сентября 2024 04:48
ስሙ ገብርኤል ነው
የዘለዓለም ወንጌል በእጁ የተያዘ
በጠላቶች መኃል ሰይፍን የመዘዘ
ዘወትር ስለእኔ በአምላክ ፊት የሚቆመው
የሚረዳኝ መልዐክ ስሙ ገብርኤል ነው
አዝ
በሰርክ መስዋዕት ጊዜ የዳሰሰኝ
ጥበብ ክርስቶስን ገልጦ ያስተማረኝ
ክብሩ እያበራ በሌሊቱ ግርማ
የጌታን መወለድ ምስራች አሰማ(2)
አዝ
የአምላክ ስም ያለበት ክንፉን የዘረጋ
ሕዝቡን የታደገ ከጠላት መንጋጋ
የተሰጠው ግርማ እጅጉን ታላቅ ነው
በእሳቱ መካከል ሲበር እንዳየነው (2)
አዝ
የእየሉጣ ረዳት የቂርቆስ አዳኙ
የዳንኤል መምህር የጠላት በታኙ
ዛሬም ለልጆቹ የጌታን ፊት ያያል
ለታናናሾቹ በምልጃው ይቆማል(2)
አዝ
የአምላክ ስም ያለበት ክንፉን የዘረጋ
ሕዝቡን የታደገ ከጠላት መንጋጋ
የተሰጠው ግርማ እጅጉን ታላቅ ነው
በእሳቱ መካከል ሲበር እንዳየነው(2)
ዘማሪ ዲያቆን እንዳለ ደረጀ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
28 сентября 2024 12:00
በድንኳኔ እልልታ ሙሉ ነው
በድንኳኔ እልልታ ሙሉ ነው
በድንኳኔ ዝማሬ ሙሉ ነው
በማንነቴ ላይ እግዚአብሔር ታላቅ ነው
አዝ
ፍላፃውን የጠላቴን ቁጣ
መከተልኝ ወደ እኔ እየመጣ
በራራልኝ በእርሱ በወዳጄ
ሰላም ሰፍኗል በጓዳ በደጄ
አዝ
የመንገዴን ጥርጊያውን አቅንቶ
የሰለለ ጉልበቴን አፅንቶ
ከፊት ለፊት በድል ቀድሞልኛል
በምስጋናው ከኋላ ስቦኛል
አዝ
ስላልተወኝ አንዳች አጣህ ብሎ
ሙሉ ሰው ነኝ የለኝም ጎዶሎ
በከፍታ ብኖር በዝቅታ
ደስተኛ ነኝ ሁልጊዜ በጌታ
አዝ
ማማረርን ማጉረምረም ትቻለሁ
አንደበቴን ቅኔ ሞልቻለሁ
ቢፈራረቅ ብርሃን ጨለማ
ከቶ አልወርድም ከምስጋና ማማ (2)
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…