ሰላም የእግዚሃብሔር ቤተሰቦች የኔ ጥያቄ
1.በሌላ እምነት የነበረ ሰው የስላሴን ልጅነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባዋል
2.አንድ ሴት የወር አበባ ላይ ሆና የቅዳሴ ፀበል መጠጣት ይቻላል ወይ
መልስ👇👇👇
ሰላም የእግዚሃብሔር ቤተሰቦች የኔ ጥያቄ
1.በሌላ እምነት የነበረ ሰው የስላሴን ልጅነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባዋል
2.አንድ ሴት የወር አበባ ላይ ሆና የቅዳሴ ፀበል መጠጣት ይቻላል ወይ
🎬 🛑 ትክክለኛው የቅዱስ ሚካኤል ስዕል የቱ ነው? ይህኛውስ ስህተቱ ምንድን ነው?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/L4RFDc6-W5c
https://youtu.be/L4RFDc6-W5c
📯📯📯 ታላቅ የንግስ ጉዞ #ቁልቢ_ገብርኤል 📯📯📯
#ቁልቢ_ገብርኤል_ገዳም
ቁልቢ ገብርኤል ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461
ኪ/ሜ. ርቀት ላይ በምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጋራ
ሙለታ የሚገኝ ከተመሰረተ ጀምሮ ብዙዎቹን እንቆቅልሸ የፈታ ታላቅ ገዳም ነው።
በዘጠነኛው መ/ክ/ዘ. ዮዲት ጉዲት ተነሥታ አብያተ
ክርስቲያናትን ስትመዘብር፣ ክርስቲያኖችን ስትገድልና
መጻሕፍትን ስትቆነጻጽል ንጉሥ አንበሣ ውድም በአክሱምና
በአከባቢዋ የነበሩ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን በመያዝ ወደ
ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡
ከ40 ዓመታት ስደት በኋላ አንበሣ ውድም ወደ አኵሱም ሲመለስና የንዋያተ ቅዱሳት ቆጠራ ሲደረግ ታቦተ
ቅዱስ ገብርኤል በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ፡፡ ከኤርትራ ደብረ
ሲና ማርያም የመጡና አባ ሌዊ የተባሉ አባት ታቦቱን
ለማምጣት ከንጉሡ አስፈቅደው ወደ ዝዋይ መጡ፡፡
አባ ሌዊ ከሰባት ቀን ሱባኤ በኋላ ታቦተ ቅዱስ
ገብርኤልን ይዘው ወደ አኵሱም ሲጓዙ ቅዱስ ገብርኤል
ተገልጦ “#እኔ_ወደ_ማሳይህ_ቦታ_ታቦቱን_ይዘህ_ሂድ” አላቸው፡፡ታቦቱንም ይዘው ተከተሉት፡፡ በመጨረሻም #ቁልቢ
ደረሱ፡፡
ለአባ ሌዊም የተፈቀደላቸው ቦታ ይሄ መሆኑን
#ታቦቱም_በኋላ_ዘመን_ለሕዝቡ_ድንቅ_ሥራ_እንደሚሠራ ቅዱስ ገብርኤል ነግሯቸው ተሠወረ፡፡ አባ ሌዊ በቦታው ለ130
ዓመታት ያህል አገልግለው በንጉሥ ግርማ ሥዩም ዘመነ
መንግሥት ታኅሳስ 14 ቀን ዐርፈዋል፡፡
ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን ሲወርር ብዙ ካህናት ከሰሜን ኢትዮጵያ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን ይዘው ሲጓዙ
ቁልቢ ደረሱ፡፡ 3 ካህናት ከተነጠፈ ድንጋይ ላይ
የተጻፈ ነገር ያገኛሉ፡፡ ጽሑፉም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል ሥዉር መቀመጡን፣ ልዩ ልዩ ተአምራት እንደሚሰራ፣ ወደ ፊትም ታላቅ መቅደስ እንደ ሚሠራበት፣ እንዴት አባ ሌዊ ታቦቱን ወደ ዚህ ቦታ እንዳመጡት የሚገልጽ ነበር፡፡ እነርሱም ይህን ታሪክ ይዘውት በነበረው መጽሐፈቀሌሜንጦስ ሕዳግ ላይ ጻፉት፡፡
ወደ ዝዋይ ደሴት ሲደርሱም መጽሐፉን በዚያ አኖሩት፡፡
ልዑል ራስ መኰንን ከዝዋይ ደሴት መጽሐፈ
ቀሌሜንጦስን አስመጥተው ሲያነቡ #የቁልቢ\ገብርኤልን ታሪክ በማግኘታቸው የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ተነሡ፡፡
ልዑል ራስ መኰንን በአከባቢው የአየር ንብረት ተማርከው በሥፍራው ቤት ሠርተው ነበር፡፡
ልዑል ራስ መኰንን የቁልቢ ገብርኤልን ታቦት በዚሁ ስፍራ አስተከሉ። የካቲት 21 ቀን 1884 ዓ.ም ታቦቱ
ቁልቢ ገባ፡፡
ቅዳሴ ቤቱ የተከበረው ሐምሌ 19 ቀን 1884 ዓ.ም ነው፡፡
በዚሁ ዕለት የዋናው ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ሥራ የመሠረቱ
ድንጋይ ተጥሎ ታኅሳስ 19 ቀን 1888 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተፈጸመ።
ያኔ ቦታው የተገዛው በአርባ የቁም ከብት ነበር፡፡
ወደዚሕ ታላቅ ገዳም ቅዳሴ ቤቱን እንዲሁም በዓለ ንግሱን ለማክበር ቤተ-ኤጲፋንዮስ ከ16-11-2015 እስከ 20-11-2015ዓ,ም ድረስ ጉዞ ያደርጋል።
ከአዲስ አበባ 🙏 ፒያሳ ጊዮርጊስ
መነሻ ቦታዎቻችን ሲሆ
#በ_+251986677077
#በ_0907748876 ላይ በመደወል መመዝገብ የምትችሉ የጉዞውን ሁኔታ ማጣራት ቸምትችሉ ሲሆን።
ለጉዞ የተዘጋጃችሁ ህዝበ ክርስቲያን ግን ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ በባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ እና ደረሰኙን እንደትኬት በመያዝ ቦታ ማስያዝ እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
ትኬቱን መቁረጥ ትችላላችሁ።
#የጉዞ_ዋጋ_2500ብር_ነው።
➛🏦 #በ1000529190167 #CBE_ባንክ ዳንኤል ተስፋ
🤳 #በ +251986677077
ገቢ አድርገው በቴሌግራም ቢልኩልን ዲጂታል ትኬት በእጅ ስልክዎ ከነወንበር ቁጥርዎ ይደርስዎታል።
#በጉዞአችን_ድሬዳዋ የምንገባ ሲሆን እና የጉዞው ዋጋ የአንድ ቀን ትራንስፖርትን እና #ማደሪያ_ቦታን እንደሚያጠቃልል ለመግለጽ እንወዳለን።
አድራሻችን:➛ፓያሣ ጊዮርጊስ ሕንፃ ማዕዶት ህትመት ቤት እና ዮቶር ህትመት ቤት
አዘጋጅ :-#ማዕዶት መንፈሳዊ ጉዞ ማኅበር
የቴሌግራም ቻናላችን :➛
/channel/ENATEZ
🎬 ፀበል ስንጠመቅ እርቃናችንን መሆን አለብን ወይስ በልብስ? ፈጣሪ ምን ሰራህ እንጂ ምን በላህ አይልም ይላሉ?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/vpcA0p5ScOM
https://youtu.be/vpcA0p5ScOM
፮- ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ተብለው ተሠይመው በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
፯- ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተብለው ተሠይመው በሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት
፰- ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተብለው ተሠይመው በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፱- ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ተብለው ተሠይመው በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል።
ምንጭ: ሕዝብ ግንኘነት መምሪያ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን
❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ
ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም
ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ
→ መነሻ ሐምሌ 16
→ መመለሻ ሐምሌ 20
→ የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2300 ብር
ለበለጠ መረጃ☎️ 0986677077
☎️ 0907748876
☎️ 0941747170
ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን
ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ
🎬 🛑 አንዲት ሴት ከወለደች በኋላ ልጇን ክርስትና ሳታስነሳ ብትሞት ፍታት ይደረግላታል ወይ? 1ኛጢሞ 3፥1 ኤጲስ ቆጶስ አንድ ሚስት እንድትኖረው ይናገራል፤ በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት ደግሞ ጳጳስ(ኤጲስ ቆጶስ) የሚሆነው ድንግል ነው ይህ እንዴት ነው?
የሚሉት ጥያቄዎች የተመለሱበት ነው አዳምጡት
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/LRXMjQ0E15Q
https://youtu.be/LRXMjQ0E15Q
🎬 🛑 አንዲት ሴት ከወለደች በኋላ ልጇን ክርስትና ሳታስነሳ ብትሞት ፍታት ይደረግላታል ወይ? 1ኛጢሞ 3፥1 ኤጲስ ቆጶስ አንድ ሚስት እንድትኖረው ይናገራል፤ በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት ደግሞ ጳጳስ(ኤጲስ ቆጶስ) የሚሆነው ድንግል ነው ይህ እንዴት ነው?
የሚሉት ጥያቄዎች የተመለሱበት ነው አዳምጡት
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ
⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/LRXMjQ0E15Q
https://youtu.be/LRXMjQ0E15Q
እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም አባ_ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ሥሉስ ቅዱስ
በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ :ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::
ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::
አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች::
እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው::
ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::
ሐምሌ 7 ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም የተገለጠለት በቤቱም የተስተናገዱበት ዕለት ነው።
©ዝክረ ቅዱሳን
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለችግሩ መፈታት ባላት ቁርጠኝነት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የሰላም ልዑክ ወደ ክልሉ በመላክ በክልሉ ለደረሰው ጉዳት ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ብር20,000,000.00(ሃያ ሚሊየን ብር) ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያስረከበች ሲሆን በዚህም ወቅት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ለተደረገው የከበረ አቀባበል ቅዱስ ሲኖዶስ አመስግኗል፡፡
ይሁን እንጁ የሰላም ልዑኩ ዋና ተልእኮ የሆነውን በክልሉ ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር ለመወያየት የተያዘውን አጀንዳ በተመለከተ በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የተመራው የሰላም ልዑክ በመቀሌ ሀገረ ስብከት በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የተገኘ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን በመዘጋቱ ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ በእጅጉ አዝኗል፡፡
በመሆኑም የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 13 የሕግ ድንጋጌ መሠረት ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡
በትግራይ ክልል ሐምሌ 9 ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያንና አንቀጽ 37 እና 38 ያላከበረና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ይገልጻል፡፡
በመሆኑም ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙልን ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹልን ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሐምሌ 6 ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
begena siderder lamendenw ba gera eji yahonew gera eji yalelaw sew kale be kegu me metate yechelal way ??
Читать полностью…በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን
❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ
ደርሶ መልስ
ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም
ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ
→ መነሻ ሐምሌ 16
→ መመለሻ ሐምሌ 20
→ የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2500 ብር
ለበለጠ መረጃ☎️ +251986677077
☎️ +251907748876
☎️ +251941747170
ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን
ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን
❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ
ደርሶ መልስ
ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም
ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ
→ መነሻ ሐምሌ 16
→ መመለሻ ሐምሌ 20
→ የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2500 ብር
ለበለጠ መረጃ☎️ +251986677077
☎️ +251907748876
☎️ +251941747170
ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን
ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ
ለሥልጣነ ክህነቱ የማይገባ' ካህን ብትመለከት፥ [በደፈናው] ክህነትን አትንቀፍ፡፡ ደገኛ የኾነውን የክህነት ሥልጣን ይዞ ያልተገባ ሥራን ሲሠራ በማየቱ ምክንያት፥ ከዚህ ተነሥቶ ሥልጣነ ክህነትን የሚነቅፍ አንድ ሰውስ እንኳን አይኑር፡፡
የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁዳ እንዲህ በማድረጉ ግን ሐዋርያነት የሚነቀፍ ስለ ኾነ አይደለም፤ የይሁዳ የገዛ ነጻ ፈቃድ ችግር ነው እንጂ፡፡ የሚተቸውም ክህነቱ አይደለም፤ ጠማማው ነጻ ፈቃዱ ነው እንጂ፡፡
ስለዚህ አንተም ክህነትን አትንቀፍ፤ ክህነቱን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ካህኑን እንጂ፡፡ ...
ሐኪም ሳይኾኑ ሐኪም ነን ያሉት ስንት ናቸው? በዚሁ ምክንያት በመድኃኒት ፈንታ መርዝ የሰጡትስ ስንት ናቸው? እየነቀፍኩ ያለሁት ሙያውን አይደለም፤ ሙያውን በአግባቡ የማይተገብሩትን ነው እንጂ፡፡
መርከቦች እንዲሰምጡ ያደረጉ መርከበኞችስ ስንት ናቸው? ነገር ግን ችግሩ የባሕር ላይ ጉዞ አይደለም፤ ሙያውን እንደሚገባ የማይተገብሩት ሰዎች ችግር ነው እንጂ፡፡
ስለዚህ አንተም አንድ ክፉ ክርስቲያን ብትመለከት በደፈናው የክርስትና ትምህርትን ወይም ሥልጣነ ክህነትን አትንቀፍ፤ ደገኛውን ሥልጣን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ነው እንጂ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ትንቢተ ኢሳይያስን በተረጎመበት ፬ኛ ድርሳን ላይ ከተናገረው የተወሰደ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን
❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ
ደርሶ መልስ
ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም
ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ
→ መነሻ ሐምሌ 16
→ መመለሻ ሐምሌ 20
→ የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2300 ብር
ለበለጠ መረጃ☎️ +251986677077
☎️ +251907748876
☎️ +251941747170
ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን
ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ
የኢኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች።
ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለዘጠኝ አህጉረ ስብከት የተመረጡት ፱ ቆሞሳት ዛሬ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተፈጸመ ሥርዓት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመዋል።
ከሌሊቱ ፱ ስዓት ጀምሮ በተከናወነው ሥርዓተ ሢመት ላይ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች።፣ ግብዣ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የመጡ ሊቃውንት፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ምእመናን ተገኝተዋል።
በዚህም መሠረት የሚከተሉት አባቶች በቅድስት ቤተክርስቲያን የተሰጣቸውን ሥያሜ ይዘው ለተጠቀሱት አህጉረ ስብከት ተመድበዋል።
፩- ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተክለማርያም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተብለው ተሠይመው ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት
፪- ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተብለው ተሠይመው ለምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት
፫- ቆሞስ አባ ስብሐትለአብ ኃይለማርያም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተብለው ተሠይመው ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት
፬- ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተብለው ተሠይመው ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፭- ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስም ተብለው ተሠይመው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን
❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ
ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም
በሐረርና ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ
→ መነሻ ሐምሌ 16
→ መመለሻ ሐምሌ 20
→ የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2500 ብር
ለበለጠ መረጃ☎️ 0986677077
☎️ 0907748876
☎️ 0941747170
ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን
ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም"
"እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰነዋለሁ በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ"
ሥላሴ ትትረመም
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር (፪)
ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ
ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ
ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ
ፍጥረትን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ
አዝ
ልበል ሃሌ ሉያ ኪሩቤልን ልምሰል
በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል
ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል
ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል
አዝ
በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል
በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል
ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት
በባሕሪይ እና ደግሞም በመንግሥት
አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት
አዝ
በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ
ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ
ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ጸንቶ(፪)
አዝ
ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር
የአምላክ ጌትነት የሥላሴን ክብር
ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ
መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ
ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
༒ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ሥላሴ ༒
እንኳን ለቅደስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የሌሊቱን ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ ለማመስገን ይረዳን ዘንድ በዕለቱ የሚደርሰው ቃለ እግዚአብሔር እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
፩. ነግሥ / ሰላም ለአብ /
ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ፤
ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም ለባሲ፤
ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ፤
ኃይልየ ሥላሴ ወፀወንየ ሥላሴ፤
በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ።
ዚቅ፦
አምላክነሰ ኃይልነ ፨ አምላክነሰ ፀወንነ ፨ አምላከ አሕዛብ ዕብነ ወዕፀ ኪነት ኢኮነ።
፪. ለአጽፋረ እግርከ / መልክአ ሚካኤል /
ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ፤ ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ፤
ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ፤ ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ፤
አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ፡፡
ዚቅ፦
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘይሴባሕ እምትጉሃን ፨ ወይትቄደስ እምቅዱሳን ፡፡
፫. ተፈሥሒ ማርያም / ማኅሌተ ጽጌ /
ተፈሥሒ ማርያም እንተ ዘተአምሪ ብእሴ፤
ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ ሥላሴ፤
እንዘ እዘብጥ ከበሮ ቅድመ አእላፈ ኤፍሬም ወምናሴ፤ ለተአምርኪ እነግር ውዳሴ፡
ማርያም እኅቱ ለሙሴ።
ወረብ፦
ተፈሥሂ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ ተፈሥሂ ማርያም
ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ ሥላሴ ዘጸገይኪ ለነ።
ዚቅ ፦
ይሴብሑኪ ወይገንዩ ለስምኪ ፨ ዘእምሥሉስ ቅዱስ ቃል ኃደረ ላዕሌኪ ፨ ወትሰመዪ ማኅደረ መለኮት ።
፬. ለህላዌክሙ / መልክአ ሥላሴ /
ሰላም ለህላዌክሙ ዘይመውዕ ህላዌያተ፤
ለረኪበ ስሙ ኅቡእ አመ ወጠንኩ ተምኔተ፤ እምግብርክሙ #ሥላሴ ሶበ ረከብኩ አስማተ፤
መለኮተ ለለአሐዱ ዘዚኣክሙ ገጻተ፤
እንበለ ትድምርት እሰሚ ወእሁብ ትድምርተ።
ዚቅ፦
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ አአትብ ወእትነሣእ ፨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፨ሠለስተ አሥማተ ነሢእየ እትመረጐዝ ፨ እመኒ ወደቁ እትነሣእ፨ ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት ፨ እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ በእግዚአብሔር ተወከልኩ ፡፡
አመላለስ ዘዚቅ ፦
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሃሌ ሉያ።
፭ . ለሕጽንክሙ / መልክአ ሥላሴ /
ሰላም ለሕጽንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤
ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤
እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤
ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤
ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ ።
ዚቅ፦
በአፍዓኒ አንትሙ ፨ ወበውሣጤኒ አንትሙ ፨ በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለዘርዓ ያዕቆብ (ለኢያሱ) አንትሙ ፡፡
ወረብ፦
በአፍአኒ አንትሙ ወበውሣጤኒ አንትሙ/፪/
በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለኢያሱ ንጉሠ ነገሥት/፪/
፮. ለሕሊናክሙ / መልክአ ሥላሴ /
ሰላም ለሕሊናክሙ በከዊነ ኄር ዘተሐምየ፤ እምከላውዴዎን አብርሃም ዘምድረ ካራን ኀረየ፤ ሥላሴክሙ ሥላሴ ሶበ ይኔጽር ዕሩየ፤
፫ተ ዕደወ ሊሉያነ ውስተ ርእሰ ኀይምት ርእየ፤
ወለ፩ዱ ነገሮ ረሰየ።
ዚቅ፦
ወጽአ አብርሃም እምድረ ካራን ፨ ወቦአ ብሔረ ከነዓን፨ ተአመነ አብርሃም በእግዚአብሔር ፨ እንበይነዝ ጽድቀ
ኮኖ ፡፡
ወረብ፦
ወጽአ እምድረ ካራን ወቦአ ብሔረ ከነዓን፤
ተአመነ አብርሃም አብርሃም በእግዚአብሔር/፪/
፯. ለሐቌክሙ / መልክአ ሥላሴ /
ሰላም ለሐቌክሙ ዘቅናተ ኂሩት ቅናቱ፤
ሊሉያነ ፆታ ሥላሴ እምአምላከ በለዓም ከንቱ፤
ኀበ መስፈርትክሙ ጽድቅ እስመ ያበጽሕ ትእምርቱ፤ ተደለዉ ከመ ይሑሩ ምሕዋረ ዕለታት ሠለስቱ፤
በዓለ መሥዋዕት አብርሃም ወይስሐቅ መሥዋዕቱ።
ዚቅ፦
አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ ፨ አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ ፨ እኁዝ አቅርንቲሁ በዕፀ ሳቤቅ ፨ ዕፀ ሳቤቅ ብሂል ዕፀ ሥርየት መስቀል ፨ አብርሃምኒ ርእዮ በውስተ ምሥዋዕ ፨ ሕዝቅኤልኒ ርእዮ በልዑላን ፨ ሙሴኒ ርእዮ በዓምደ ደመና ፨ በነደ እሳት ፨ ፈያታዊኒ ርእዮ በዲበ ዕፀ መስቀል አምነ ፡፡
ወረብ፦
አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ፤
አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ ቤዛሁ በግዓ።
፰. ለዘበነጊድ / መልክአ ሥላሴ /
ለዘበነጊድ አቅረብኩ መካልየ ልሳን ስብሐታተ፤
መጠነ ራብዕ ዐሥር እንዘ አተሉ ስብዐተ፤
ህየንተ ፩ዱ ሥላሴ እለ ትፈድዩ ምእተ፤
ጸግዉኒ እምገጽክሙ ንዋየ ገጽ ትፍሥሕተ፤
ወዲበ ፲ቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ ።
ዚቅ፦
ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ፨ ስብሐት ለወልድ ለዘአክበራ ለማርያም ፨ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት።
ወረብ፦
ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ስብሐት ለወልድ ለገባሬ ኲሉ ዓለም፤
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት።
፲. ለሕሊናከ / መልክአ ተክለሃይማኖት /
ሰላም ለሕሊናከ ዘኮነ መምለኬ፤
ሥላሴ ዕሩየ እንበለ ውሳኬ፤
ተክለሃይማኖት ቄርሎስ ዘላፌ ረሲዓን እለ እውጣኬ፤ ባርከኒ አባ ለወልድቅዱስ፤ኬ፤
እስመ ልማዱ ለመምህር ቡራኬ።
ዚቅ፦
አንትሙሰ ከመ ዕብነ ሕይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ ፨ ወለክህነቱ ቅዱስ ፨ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ ወትንግሩ ሠናይቶ ለዘጸውዓክሙ ፨ አባ ባርከኒ ተክለሃይማኖት አባ ፨ ከመ ባረኮ አብርሃም ለይስሐቅ ወልዱ።
ወረብ፦
አንትሙሰ ዕብነ ህይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ፤
ወለክህነቱ ቅዱስ ታዕርጉ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ።
°༺༒༻° ምልጣን °༺༒༻°
ዕምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም ፤
መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም፤
እንዘ ይብሉ ይዜምሩ ፤
በልሳን ዘኢያረምም፤
አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም።
አመላለስ፦
አማን በአማን ፤
መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም።
°༺༒༻° እስመ ለዓለም ° ༺༒༻°
ሰአለ ሙሴ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ ፨ ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ፨ ወይቤሎ አብርሃም ንግሮ ለእግዚአብሔር ፨ እንዘ ትብል ተዘከር እግዚኦ ኪዳነከ ፨ አብርሃም ፍቊርከ ይስሐቅ ቊልዔከ ፨ ወያዕቆብሃ ዘአስተባዛሕከ ፨ ነሥአ ሙሴ ሠለስተ አስማተ ፨ ከመ ዘይወስድ አምኃ ለንጉሥ ፨ ወሰማዕትኒ ይጸውሩ ሥላሴ።
ወረብ ዘአመላለስ፦
ሰአለ ሙሴ ሰአለ ሙሴ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ፤
ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ።
°༺༒༻° አቡን በ ፫ °༺༒༻°
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ፤ እስመ በሥላሴ ትሄሉ በሰማይ ወበምድር ፤ (ሥ) ወሠናያቲሃ ይሰብክ ቃለ ኢያሱ ሐዋርያ ፍቅር ፤ ( ሥ ) ውስተ ሀገሩ ሐዳስ ደብረ ብርሃን ንግሥ አድባር ፣ ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ፤ ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ።
°༺༒༻° ሰላም °༺༒༻°
ሰላመ አብ ሰላመ ወልድ ወሰላመ መንፈስ ቅዱስ ኃይለ መስቀሉ እትመረጐዝ፤ የሃሉ ማእከሌክሙ እኃው።
+ °༺+ °༺+༻° ተፈጸመ °༺+ °༺+ °༺ +
ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪ አቀረበ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት በቤተ ክርስቲያናችን የበላይ መዋቅርና በክልል ትግራይ አህጉረ ስብከት መካከል የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ተቋርጦ መቆየቱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት ተፈቶ መዋቅራዊ አንድነታችን በድጋሚ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ሀገራዊ የሰላም እርቁ ከተፈጸመበት ማግስት ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ሲጠየቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ምንም እንኳን ቅዱስ ሲኖዶሱ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም በክልሉ ያሉት ብፁዓን አባቶችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተከፈተው የሰላምና የውይይት በር ከመጠቀም ይልቅ መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በመጣስ መንበረ ሰላም የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መሥርተናል በሚል ተገቢነት የሌለው መግለጫ ከመስጠትም አልፎ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸም አለበት የሚል ውሳኔ በማሳለፍ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዐ.ም. ለመሾም ፕሮግራም መያዙን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ በጦርነቱ ወቅት ለነበረው የመዋቅራዊ ግንኙነት ጉድለትና የሰብአዊ ድጋፍ እጥረት በይፋዊ መግለጫ ይቅርታ የተጠየቀ ቢሆንም ለይቅርታው አዎንታዊ ምላሽ አለመሰጠቱ በእጅጉ አሳዛኝ መሆኑ፤