ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ሰበር የሀዘን ዜና✝

እዚህ ቪድዮ ላይ ተተኩሶበት መሬት ላይ ወድቆ ያያችሁት ወንድማችን ነፍሱ አርፋለች።

በረከቱ ይድረሰን። በሰማዕታት ጎን ያቁምልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በወለቴ ያለችው ቤተክርስቲያን ትጣራለች!
በሻሸመኔ የብዙ ንፁሀንን ደም ያፈሰሰው ሕገ ወጡ ቡድን በመንግስት በታጠቁ ኃይሎችን ወደ ቤተክርስቲያኗ እየተኮሰ ይገኛል !

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዶ/ር ወዳጄነህ መልዕክት

እኔማ የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን የማውቃት ይመስለኝ ነበር። ባለፉት ሶስት ቀናት እንደተረዳሁት ግን ስላንቺ የነገሩኝ ሰዎችና መጻህፍት ሁሉ ካለሽ ክብር፣ ሞገስና ዝና ከፊሉን እንኳን እንዳልነገሩኝ ነው። ተዋህዶ ሆይ! ንፁህ እምባ፣ ጥልቅ ትህትና፣ ብርቱ ትዕግስት፣ ታላቅ ጥበብ፣ ብዙ እውቀት፣ ሰፊ ማስተዋል፣ የሚያስፈራ ግርማ አየሁብሽና ተገረምኩኝ፣ ልቤ ተደነቀ፣ እጄን በአፌ ላይ ጫንኩኝ! የጸሎትና የምልጃሽ እጣን የልዑል እግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ሲያጥነው፣ ዙፋኑን ሲያውደው ማየት እንኳን እኔን ደካማውን ሰው ይቅርና ቅዱሳን መላዕክቱን ያስደንቃል። በነብዩ በዳንኤል መፅሃፍ እንደሚነበብ እጅ ያልነካው ድንጋይ ከሰማይ ወርዶ ሳይፈርስ ፣ ሳይከፈል፣ ሳይቆረስ ታላቅ ተራራ ሆኖ ጸንቶ እንደኖረ አንቺም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታላቅ ተራራ ሆነሽ ለአፍሪካ ትምክህት፣ ለመላው አለምም ክብር ሆነሽ ትኖሪያለሽ። ከእግዚአብሔር የተማሩት፣ ትሁታንና ብሩካን የሆኑት፣ ማቅ የለበሱልሽ የተወደዱ ልጆችሽ እንዴት የታደሉ ናቸው!

ከሩቅ እያየሽ የሚወድሽና የሚያከብርሽ
ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የፈረንሣይ ጉራራ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ሰብሳቢ ዲ/ን ታምራት ጥጋቡ እንዲሁም የደብሩ የአካባቢ ወጣቶች የሆኑ ዘካርያስ ዓለማየሁና ጸጋ ደምሴ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በትላንትናው ዕለት ታሥረዋል።

ወጣቶቹ በአሁኑ ሰዓት ሾላ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታሥረው የሚገኙ ሲሆን ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተገልጿል።

ወጣቶቹን ለእሥር ያበቃቸው ምክንያት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ወጣቶችን ታነሳሳላችሁ የሚል እንደሆነም ነው ለተ.ሚ.ማ የደረሰው መረጃ የሚያመለክተው።

ምንጭ፡ ተሚማ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

https://youtu.be/fsd2FVImZUI

😳ዘፈን ማቆም እና ልባችንን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ፈልገን አቅም አንሶናል?😞

👉 ሲኖዶሳችን ባስተላለፈው መልእክት መሠረት ጸሎት ጀምረን ነገር ግን ሀሳባችን እየተሰራረቀ ለጸሎት ተቸግረናል???

👉ዘፈን ለማቆም የሚረዱንን ትላልቅ ምሥጢሮች በእዚህ ቪድዮ ላይ ያገኛሉና ገብተው ትምህርቱን ያዳምጡት ለምትወዷቸውም ላኩላቸው። በእርግጠኝነት በእዚህ ወር ሰው አስገድዷችሁ ሳይሆን የክርስቶስ ፍቅር አሸንፏችሁ በመንፈሳዊ ደስታ ዘፈን ታቆማላችሁ።

✝የዩቲዩብ ቻናላችንን subscribe,like እና share አድርጉት✝

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ወጡን “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” እንደማትቀበልና ቤተ ክርስቲያንን የመክፈል ሙከራን እንደምታወግዝ አስታወቀች፡፡

ከስድስቱ ኦሬንታል እህት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ የሆነችው የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርኳ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አግናጢዎስ ኤፍሬም ፪ኛ በኩል ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጻፈችው ይፋዊ ደብዳቤ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ በለየው ሕገ ወጥ ቡድን የተፈጸመውን “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” በማውገዝ ከቅድስት ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጎን መቆሟን ገልጻለች፡፡

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ሕጋዊ እና ሐዋርያዊ ቅዱስ መሪነት ብቻ የምትቀበል መሆኑን በመግለጽ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲያልፍ በጸሎት እንደምትለምን ገልጻለች፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይነበብ🛑

ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች የዝማሬ ዳዊትን የዩቲዩብ ገጽ subscribe አድርጉ አገልግሎቱን አግዙ እያልን ብዙ ግዜ ብንናገርም በፍቅር ጥያቄያችንን ተግባራዊ ያደረጉ ጥቂት ብቻ ናቸው። ለምን ጥቂቶች ብቻ?

ምንም የማይጠቅመን ቦታ ስንርመሰመስ አይደል የምንውለው? መንፈሳዊ ተግባራትን ለመፈጸም እጃችን እሚታሰረው ስለምንድን ነው? መንፈሳዊ አገልግሎትን ልትደግፉ የምትችሉበት አንዱ እና ዋነኛው መንገድ ይህ እንደሆነ ጠፍቷችሁ ነው?

አሁንም ደግመን እንጠይቃለን እግዚአብሔር በፈቀደልን መልኩ መልካም አገልግሎት ወደናንተ ለማድረስ እየሰራን ነው። ከዚህ በብዙ መስራት እንድንችል ግን የእናንተም ድጋፍ ያስፈልገናል። ምን እናግዝ ካላችሁን ሁላችሁም ይህን ጽሁፍ የምታነብ በጠቅላላ ከስር ባስቀመጥነው አድራሻ በመግባት ዝማሬ ዳዊትን Subscribe እንድታደርጉ በቅዱስ ገብርኤል ስም እንጠይቃለን።

በተጨማሪም ይህን መልዕክት ለሁሉም ባለ ማዕተብ አድርሱልን። ለምትሰጡን መልካም ምላሽ እግዚአብሔር ያክብርልን።

https://bit.ly/2O1Z3d8
https://bit.ly/2O1Z3d8
ወይም
👉 https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አብይ አህመድ የዘመናችን ኔሮን ቄሳር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ተጨማሪ_የእስር_ዜና

ሕገወጡን ቡድን ትቃወማላችሁ በሚል መንግሥት በኦርቶዶክሳውያን ላይ እያደረሰ ያለው እስር እንደቀጠለ ሲሆን በትናንትናው ዕለት በማኅበረ ቅዱሳን የሻምቡ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ደረጄ ገለታ እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን የቡሌሆራ ማእክል አገልጋዮች ቀሲስ እሸቱ ታደሰ እና ቀሲስ መንግሥቱ መኮነን መታሰራቸው ታውቋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እናቴ ቤተክርስቲያን በኔ በኃጥያተኛው ልጇ በደል ጥቁር ለበሰች! የሕይወቴ ጥቁሩ ታሪክ

ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ ለብሳ እኔ ሌላ ልብስ አልለብስም። የአባቶቼን ትዕዛዝ እቀበላለው አከብራለው ጥቁር እለብሳለው እጾማለው እጸልያለው!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

፮. በመግለጫው የመጨረሻ አንቀጽ ላይ "..ችግሩን ለማባባስና በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ሀገርን ወደፈተና ለማስገባት በሚጥሩ አካላት ላይ መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንደሚሠራ በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል" በማለት ያስቀመጠውን በተመለከተ፡-

፮.፩. ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ከሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አንስቶ እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር አልፎም እስከ ተከታይ ምዕመኖቿ ድረስ የሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም የሕዝቧ አንድነት እና የሕግ የበላይነት ጉዳይ ለድርድር እንደማታቀርብ በድጋሚ እያስታወስን ስልጣንን ተገን በማድረግ የቤተ ክርስቲያንችንን ሕጋዊ ጥያቄ በግድያ፤ በእስር፤ በማዋከብ እና በማስፈራራት ሊፈታ የማይችል ይልቁንም መንግሥት የተጣለበትን መንግሥታዊ ኃላፊነት ያለ አድሎ መፈጸም ሲችል ብቻ መሆኑን ቤተ ክርስቲያናችን ዳግም በጽኑ ቃል ለማሳሰብ ትወዳለች፡፡

በመጨረሻም መንግሥት ይህንን መግለጫ ሲያወጣ በጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘ መሆኑን ስንመለከት የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል።

ስለሆነም መንግሥት ሕገ ወጥ አካላትን ድጋፍ ከመስጠት እና የእነርሱ ልሳን ሆኖ በመቅረብ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልእልና ከሚያንኳስስ ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታቀብ እያሳሰብን ሕገ ወጡ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊትም የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ እንዲያቆም እናሳስባለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ" በሚል ርዕስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ/ም የመንግስት ኮምዩኒኬሽን የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ።

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ እንዲሁም በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ ፲፱ ንኡስ አንቀጽ ፫ በተደነገገው መሠረት ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይማኖት፣ የቀኖና እና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስና እና መፈንቅለ ሲኖዶስ ሙከራ በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ አካል በኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡ ውሳኔዎች እና መልእክቶች ተከታታይ መድረኮች በማዘጋጀት ስለ ተፈጠረው የሃገራችን ሕግ እና የሕገ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በቂ ግንዛቤ ሕዝባችን እንዲያገኝ በተደጋጋሚ ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት መግለጫ እና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ይሁንና "በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ" በሚል ርእስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ፤ መግለጫው ያስቀመጣቸው ነጥቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ክብር፤ ታሪክ፤ እና እውነታ ቸል በማለት በጉዳዩ ላይ የተሟላ መረጃ የሌላቸው ወገኖች የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ የሚያስችል መግለጫ በመኾኑ በመግለጫው አንኳር ነጥቦች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ በሆነችው በደባርቅ ከተማ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ወደ አደባባይ በመውጣት የመንግሥት የጸጥታ አካላት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እያሳደሩ ያሉትን ተጽእኖ ተቃውመዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ተቀብለው ጥቁር በመልበስ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሄዱ ኦርቶዶክሳውያን በበደሌ፣ አሰላ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ ጨምሮ በአንዳንድ የኦሮምያ ክልል ከተሞች እንዲሁም በጂግጅጋ አንዳንድ አጥቢያዎች እንዳይገቡ እየተደረገ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል።

በተለይም በአዳማ በጸሎት ሰዓታት ደወል እንዳይደወል እየከለከሉ ሲሆን በበደሌ ጥቁር የለበሱት ተለይተው እየታሰሩ ነው ተብሏል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የጅግጅጋ ዬንቨርሲቲ ተማሪዎች የጋራ ጸሎት አታደርሱም ተብለው በልዩ ኃይሎች ሲመለሱ መንግስት ኦርቶዶክስ ላይ በደሉን ቀጥሏል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለሁሉም share አድርጉ
ይህ መረጃ እውነት ሆነም ውሸት መዘጋጀቱ አይከፋም። ለሁሉም ሙስሊም ወንድም እህቶቻችን አድርሱ።

ለግዜው እኛ ኦርቶዶክሳዊያን አባት እንጂ መንግስት የለንም የምንጠብቀውም የአባቶቻችንን ጥሪ ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰበር ዜና

አለምገና ሚካኤል የህገወጡ ቡድን መሪ የሆነው አካለወልድ በጣም ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ በሆኑ እና እጅግ በታጠቁ የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች  ታጅቦ ሰብሮ ገብቷል !!

ይሄንን ለመቃወም ከሰበታ እና ከተለያየ ቦታ የሚመጡ ወጣቶችን እያፈሱ እና እየበተኑ ይገኛሉ   !!!

በአሁን ሰዓት አለምገና ሚካኤል  በ ኦሮሚያ ልዩ ሀይል እገዛ በወንበዴዎች ተወሯል  ሁሉም ወንበዴዎች  ከአለምገና እስከ ሰበታ መንገዱ ተዘግቶ የአለምገና እና የሰበታ ህዝብ እንዳይቃወም በፖሊስ እየታፈሰ እና በመሳሪያ እየተበተነ ነው

ቤተክርስቲያኑ ጊቢ ውስጥ ከ 100 እና 200 የማይበልጡ የእነሱ  ደጋፊዎችን አስገብተው  ይገኛሉ።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በኦሮምያ ክልል ባሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየተደረገ ያለው ኦርቶዶክሳውያንን የማሰር ተግባር ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

ዛሬ ጠዋት ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰው መረጃ መሠረት የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት መቀመጫ በሆነችው አምቦ ከተማ የሀገረ ስብከቱ የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አባ ጴጥሮስ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ከሚገኘው ማረፊያቸው በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ታውቋል።

በተጨማሪም በወለቴ እና በዓለም ገና አካባቢዎች የጸጥታ አካላት በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ማዋከብ እና ድብደባ እያሳደሩ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የነነዌ 3ኛ ቀን ጸሎተ ምሕላ በተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ፍርድ ቤቱ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

የቤተክርስቲያናችንን የሕግ ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ በቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን ላይ የደረሰውን ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰትን አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያን ክስ መመስረቷን በማውሳት የክሱ ሂደት የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ክርክር የተከናወነ ሲሆን ለየካቲት 3/2015 ዓ.ም ተጨማሪ ቀጠሮ መያዙ ገልጿል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግስት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም !
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሻሸመኔ ከተማ በኦሮሚያ ክልል መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ኦርቶዶክሳውያንን ከክልሉ የማጽዳት ዘመቻ የሚመስል ኢሰብዓዊ እና ኢሕገመንግስታዊ ድርጊት መፈፀሙ መላው ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ድርጊት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አያይዘውም ለሕዝብ የተቋቋመው መንግስት የሕዝብን ሰብዓዊ መብት አለማክበሩ ሳያንስ በአንዳንድ አካባቢዎች ፣ ብሎም መንግስት በሚመራቸው ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ኦርቶዶክሳውያን መልበስ የምትችሉት እኔ የመረጥኩላችሁን ብቻ ነው በሚል ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን ቀኖናዊ ትዕዛዝ ምዕመናን እንዳይፈጽሙ ብሎም እንዲሸማቀቁ በማድረግ እያካሄደ ያለው አፈና ዲሞክራት ነኝ ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ፣ መብታችንን የረገጠ እና ከቀደሙ አፋኝ መንግሥታት ሥርዓት የተለየበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያዳግት ተግባር ነው ።

ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ከምን ጊዜውም በላይ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ እና አቅጣጫ ብቻ በመከተል የመብት ጥያቄያችን በተግባር እስከሚመለስ እና የመኖር መብታችንን እስከምናረጋግጥ ድረስ በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንድንቀጥል እያሳሰብን ፤ የጸጥታ አካላትም ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ጠባሳ ከመጣልና ሰላማዊ ክርስቲያኖችን ከማሳደድ እንድትቆጠቡ እንጠይቃለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጸሐፊ  ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ  ጋር በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችን ጉደይ ውይይት አደረጉ።

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኀን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ጥር ፳፭  ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ በሚገኘው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በመገኘት ከዋና ጸሐፊው ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ ጋር ውይይት አደረጉ። 

ብፁዕነታቸው  ዋና ጸሐፊው በቅርቡ ለዚህ ከፍተኛ ኃላፊነት በመመረጣቸው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ስም የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል።

ቤተ ክርስቲያን የምክር ቤቱ መስራችና ንቁ አባል በመሆን የበኩልዋን ሚና እየተወጣች መሆኑን አስታውሰው ይህ ግንኙነት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ወቅታዊ ሁኔታ ያብራሩላቸው ሲሆን የችግሩ ዋነኛ ምንጭ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና እና ሕግጋት የጣሱ ጥቂት አፈንጋጭ አካላት ድርጊታቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕልውና ላይ የሚያስከትለውን ታላቅ አደጋ በመገንዘብ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወገዙና የተለዩ ቢሆንም መንግሥት የሕግ የበላይነትንና የሕዝብን ሰላም የመጠበቅ ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ ሐዘንና ጭንቀት ፈጥሯል።

በዚህም ጳጳሳት እየተሳደዱ፣ ካህናት እየታሰሩ፣ ምዕመናን እየተደበደቡ ይገኛሉ። እንዲህም ሆኖ ሕግ የጣሱት አካላት በንስሐና በይቅርታ ቢመለሱ ቤተ ክርስቲያን በሯን ክፍት አድርጋ እየጠበቀች ትገኛለች። ምክር ቤቱ ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ልዕልና፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለሰላምና ለፍትሕ አጋርነቱን እንዲገልጽ ብፁዕነታቸው ጠይቀዋል።

ዋና ጸሐፊው  ለተደረገላችው ዝርዝር ማብራሪያ አመስግነው ይህች ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በወቅቱ የገጠማት ፈተና በእጅጉ አንደሚያሳስባቸውና ጉዳዩን በቅርበት መከታተላቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በብፁዕነታቸው በኩል ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ሰላምታና መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።  ከብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ጋር መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ሃይለ ጊዮርጊስ በስዊትዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የጄኔቫ አጥቢያ ሰበካ ጉባኤ አመራር ተወካዮች በውይይቱ ተሳትፈዋል።

ውይይቱን ተከትሎ ዋና ጸሐፊው በማግስቱ አጋርነታቸውን የሚያሳይ መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸው ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት የተመሰረተች፣ ሁልጊዜም ለአንድነትና ለሰላም የደም መስዋዕትነትም ጭምር ስትከፍል የኖረች ናት ብለዋል። አዲስ ሲኖዶስ ለመመስረት በሚደረገው ሙከራ ማዘናቸውን ገልጸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲጠበቅ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠይቀዋል። የሚመለከታቸው የፖለቲካ ኃይላት ሁሉ ሕጋዊ ሰውነት ያላት ቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይዋን በአላት መንፈሳዊ ቀኖና እና ሕግ ለመፍታት ብሎም የምዕመኗን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ: ኢኦተቤ ቴቪ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲ በማለት ኦርቶዶክሳዊያኑ ላይ ታላቅ በደል እያደረሱ ይገኛል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በጅማ የኦርቶዶክሳውያን እስር እንደቀጠለ ነው፡፡

ዛሬ ጠዋት የማኅበረ ቅዱሳን ጅማ ማእከል ሰብሳቢ እና የደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑትን አቶ ታዬ ደሳለኝ ታስረዋል፡፡

በተጨማሪም ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ማንም መንቀሳቀስ አይችልም መባሉን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ተመችቷችሁ ጥቁር ልብስም ኑሯችሁ እንዲሁ በቸልተኝነት የክት ልብሳችሁን ለብሳችሁ የዋለችሁ! የቤተክርስቲያንን የቅዱስ ሲኖዶስን አዋጅ አልቀበልም ነው? እህት እና ወንድሞቻችን ጥቁር በመልበሳቸው በተላያዩ ቦታዎች መከራን እየተቀበሉ ነው፤ የኛ ልብ ምን ያህል ቢደነድን ነው? የቤተክርስቲያን ሕመም ያላመመው ክርስቲያን እንዴት ክርስትያን ልንለው እንችላለን? እባኳችሁ ቢያንስ የተቀሩትን 2 ቀናቶች በጾም ጸሎት የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝ እንፈጽም።

ጥቁር ልብስ የማይለብስ አንዳችም ኦርቶዶክሳዊ እንዳይታይ
ቤተክርስቲያንናችን ሀዘን ላይ ናት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

፩. በመግለጫው የመጀመሪያ አንቀጽ ላይ "ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል" ያለውን በተመለከተ

፩.፩. እንደሚታወቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ መለያየት የለም። በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በአባልነታቸው የሚታወቁ እና የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ተብለው እውቅና የሚሰጣቸው ነገር ግን አለመግባባት የፈጠሩ ብፁዐን አባቶች የሉም።


የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የሰጠው መግለጫ፤ ብቸኛ ሕጋዊ ሰውነት ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ በታች የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በቀኖናው መሠረት አውግዞ የለያቸውን ግለሰቦች አሁንም ሕጋዊ አካላት እንደኾኑ እና እውቅናም እንደሚሰጣቸው የሚያስረዳ መግለጫ ኾኖ ስላገኘነው ተገቢነት የሌለው ነው ብላ ቤተ ክርስቲያን ስለምታምን በመንግሥት ኮምዩኒኬሽን የተሰጠውን መግለጫ አትቀበለውም፤

፩.፪. ሰላማዊት የኾነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው የበላይ አካል በኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በውስጣዊ መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ አሠራሩ የሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ መንግሥት ያወጣው መግለጫ አሁንም የማይቀበለው መኾኑን የሚያመለክት ኾኖ አግኝተነዋል።


፩.፫. በመንግሥት መገናኛ ብዙኅን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ በማፈን አንድም መግለጫዎቿን እንዳይተላለፉ ከተደረገ በኋላ ይህንን የመንግሥት መግለጫ በእነዚሁ መገናኛ ብዙኅን እንዲተላለፍ በማድረግ ብዙኅኑ አድማጭና ተመልካች የተዛባ አረዳድ እንዲኖረው የሚያደርግ ይዘት ያለው መግለጫ መኾኑን ቤተ ክርስቲያን ትገነዘባለች፡፡
፪. በመግለጫው ሁለተኛ አንቀጽ ላይ "...የተቋማቱን አንድነት የሚፈታተኑ ችግሮች ከውስጥ ሲነሱ በውይይትና በውስጣዊ አሠራር እንዲፈቱ ድጋፍ ሲያደርግ ነበር" ያለውን በተመለከተ

፪.፩. በመግለጫው ከተጠቀሰው በተቃራኒ ቤተ ክርስቲያናችን ሕገ ወጥ ካለቻቸው ግለሰቦች እና ቡድኖች ጋር መንግሥት ጥምረት ፈጥሮ በመንቀሳቀስ ላይ መኾኑን በጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ማሳወቁ የሚታወስ ሲኾን፤ መንግሥት ከዚህ ድርጊቱ አለመቆጠቡን የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል፤
፪.፪. መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በቃሉ የሚናገር ኾኖ ሳለ በተግባር ግን ይህ መግለጫ እስከ ተሰጠበት ሰዓት ድረስ መንግሥት የሕገ ወጦቹን ስብስቦች ድጋፍ ከመስጠት ድርጊቱ አለመቆጠቡ እና በምእመናን ላይ ግድያ እስከ መፈጸም፤ የቤተ ክርስቲያናቱን ቅጽር ተዳፍሮ ለሕገ ወጥ ቡድኖቹ በመሳሪያ የታጀበ ድጋፍ በመስጠት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ቁልፍ ሰብሮ በማስወረር ጭምር የሚፈጽመውን ፍጹም ያልተገባ እና ሕገ ወጥ የኾነ ድርጊት ለአድማጭ እና ለተመልካች ኹሉ ግልጽ ኾኖ ሳለ፤ መግለጫው ከዚህ ቀደም ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ከሰጡት እና ቅዱስ ሲኖዶስ መስመር በመስመር ነቅሶ ስህተቶቹን በመግለጽ እንዲታረም ካሳሰበው በተቃራኒ የክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን የተሳሳተ መግለጫ ቅጥያ ኾኖ አግኝተነዋል።
፫. በመግለጫው ፫ኛ አንቀጽ ላይ "የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ሁለቱን ወገኖች በማቀራረብ.." ሲል የገለጸውን በተመለከተ
፫.፩. ቅዱስ ሲኖዶስ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን በሰጠው ምላሽ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፤ መንግሥት ተወግዞ የተለየውን አካል ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እኩያ እና ትይዩ አድርጎ መመልከት መቀጠሉን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሁንም እየታዘበች ትገኛለች።

፫.፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጽሮቿ እየተደፈሩ እና ልዕልናዋ በመንግስት አጋዥነት እየተጣሰ ባለበት በዚህ ሰዓት መልስ ተሰጥቶበት የተዘጋውን የውስጥ አሠራር ጉዳይ ወደ ሽምግልና አውርዶ በማሳየት መግለጫውን ለሚሰሙ ኹሉ ግርታን የሚፈጥር ምሉዕ ምስል የማይሰጥና የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የተልዕኮ ምሰሶ በኾነው "ሽምግልና" በተባለ ክቡር ሃሳብ ላይ መዘባበት ኾኖ በማግኘታችን የተሰጠው መግለጫ ተገቢነት የሌለው ነው።

፬. በመግለጫው አራተኛ አንቀጽ ላይ ከተቀመጡ ሃሳቦች መሐል "...የጸጥታ አካላት የየአካባቢውን ሕዝብና የእምነት ተቋማት ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ግዴታቸው ነው" እንዲሁም "... የሚዲያ አካላት ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮችን ከማቅረብ መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል" በማለት የገለጻቸውን ፍሬ ሐሳቦች በተመለከተ፤
፬.፩. በመግለጫው የተጠቀሰው ሀሳብ ልክነት ያለው ቢሆንም በተጨባጭ እየታየ ያለው ተግባር ግን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው መንግሥት ለሕጋዊቷ ቤተ ክርስቲያን የሕግ ጥበቃ እና ከለላ ከመስጠት ይልቅ በተቃራኒው ለሕገ ወጥ ቡድኖች በተግባር እየሰጠ ባለው ወገንተኝነት የምእመናንን ሕይወት እየነጠቀ እና የቤተ ክርስቲያናችንን ቅጽር በተደራጀ የጸጥታ ኃይል አጀብ እየደፈረ እና እያስደፈረ መኾኑን የካደ መግለጫ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን በፍጹም ሐሳቧ ትረዳለች።

፬.፪. የመንግሥት መገናኛ ብዙኅን የቤተ ክርስቲያኒቱን የበላይ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጣቸውን መግለጫዎች እንዳይዘግቡ በተግባር እቀባ ያደረገው መንግሥታችን ሕሊናዊ እና ሕጋዊ ተግባራቸውን እየፈጸሙ በሚገኙ የሚዲያ አካላት ላይ የማስፈራሪያ መግለጫ በመስጠት የቤተ ክርስቲያናችን ድምጽ ይበልጥኑ ለማፈን በመንቀሳቀስ ላይ መኾኑን በገሃድ ያመላከተ መግለጫ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ስለሆነም ፈጽሞ ተገቢነት የሌለው ተግባር ነው፡፡

፭. በመግለጫው ፭ኛ አንቀጽ ላይ "...ሀገር ለማፍረስ በተለያዩ መንገዶች ሞክረው ያልተሳካላቸው ኃይሎች፣ ችግሩ እንዲባባስና እንዳይፈታ ለማድረግ እየሠሩ መሆኑ ተደርሶበታል።" በማለት የተገለጸውን ፍሬ ሐሳብ በተመለከተ፡-
፭.፩. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በማንኛውም ሁኔታ ሀገር የሚያፈርሱ ተግባራትን የምትጸየፍ፤ ዋነኛ ተልእኮዋም የሀገርን ሕልውና ማስቀጠል መኾኑን በተለያዩ የጦር ሜዳ ዐውዶች ላይ ታቦተ ሕጓን በማክበር ምእመናቶቿን ለትግል በመጥራት ጭምር የሀገርን ሕልውና ያስጠበቀች እና እያስጠበቀች ያለች መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን መንግሥት በመግለጫው የገለጸው ዓይነት ተግባር ቢፈጸም የመጀመሪያ ተቃዋሚ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መሆኗን በድጋሚ ማስታወስ ትወዳለች። ለዚህም ማሳያዋ እያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ ፍጹም ሰላማዊ እና የሕግ አግባብ እና መሠረትን ብቻ ተከትላ እየፈጸመች መገኘቷ ነው፡፡
፭.፪. ችግሩ እንዳይፈታና እንዲባባስ የሚፈልጉት ሀገር አፍራሽ ኃይሎች ሕገ ወጥ ቡድኖች መሆናቸውን መንግሥት ጠንቅቆ የሚያውቀውና ልዩ ድጋፍም የሚሰጠው መሆኑን ቤተ ክርስቲያን እያሳወቀች መንግሥትም ሕገ ወጦችን ከመደገፍ እና ከማገዝ ተግባሩ እንዲቆጠብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በድጋሚ ታሳስባለች።
፭.፫. እንደ መግለጫው ከሆነ ችግሩ የሚፈታው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕልውናዋን፣ ሕጋዊነቷን፣ ተቋማዊ ነጻነቷን እና ከመንግሥት ልታገኝ የሚገባውን የሕግ ከለላ አጥታ ከሕገ ወጥ አካላት እኩል ስትታይ መሆኑን መግለጫው በግልጽ ቋንቋ ያስቀመጠ መሆኑን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጽኑ የምታወግዘው እና የምትቃወመው መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​#አትንኩን ✞

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል(፪)
የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን(፪

ጥቂቶች ሆነን ተነስተን ነው
እንዲሁ ምድርን የመላነው
ልጣል ከውሃ ከእሳት
ጽኑ ነው የያዝነው እምነት

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል(፪)
የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን(፪)

ድሆች ስንባል ባለጸጋ
ሁሉን የያዘ ነው ከእኛ ጋ
ብርቱውን ጎልያድ የጣለ
በወንጭፋችን ጠጠር አለ

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል
የክርስቶስ ሰምራ የአርሴማ ልጆች ነን

በሕይወት በቃል አስተማረን
አምላካችን ነው የነገረን
የዚህ ዓለም ጨው ተብለናል
አልጫውንም አጣፍጠናል

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል
የቅዱስ መርቆሬዎስ የማርቆስ ልጆች ነን

እንደ ደመና የከበቡን
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩን
ስላሉን ብዙ ምስክሮች
ደካሞች ሲሉን ነን ኃይለኞች

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል
የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን
የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን

ቤተክርቲያን እማማ
ዝናሽ በዓለም ይሰማ

"እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ
ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን
ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር
ድረስ አቤቱ አትተወኝ"

ሊቀ መዘምራን ዲያቆን
ቴዎድሮስ ዮሴፍ

"አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር"
ሐዋ ፲፮፥፭

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በመንግሥት የጸጥታ ኃይል በግፍ የተገደሉት የሻሸመኔ ሰማዕታት ጸሎተ ፍትሐት እየተደረገላቸው ይገኛል!

ምንጭ፡ ተሚማ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጮህን ጮህን

ሰማዕታት እንጂ አንቆጥርም እሬሳ
አምነው የሞቱትን ስለማንረሳ

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ዘማሪ ቀሲስ ወነዶሰን በላይ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#መሐረነ_አብ_ሙሉ_ፀሎቱ

✴️ ሼር በማድረግ ማታ ማታ ከአባቶች ጋር በጋራ እንጸልይ

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал