በወይራ ዝንጣፊ መጠብጠብበሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ የስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናን በሰሙነ ሕማማት የሠሩትን ኃጢአት ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱም በወይራ ቅጠል ትከሻቸወን እየጠበጠቡ ቀን ከሰገዱት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሣጽ ምሳሌ ነው፡፡
••
ጥብጣብ የሚደረግለት ሰው በሕማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይንም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቍጥር ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡ ይህ በስቅለት ቀን የሚፈጸም ሥርዓት ሲሆን፣ ጠብጣቤ ማለት ቸብ ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዕለተ ስቅለት ሲሰግድ ፣ ሲጸልይ ፣ መጻሕፍትን ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ / የሕዝብ መሰነባበቻ / ከመሆኑ በፊት በወይራ ቅጠል የእያንዳንዱ ምእመን ጀርባ ቸብ ቸብ መደረጉ ፣ የጌታን ግርፋት ያስታውሳል፡፡
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ዕለተ ዓርብ
ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕለት ዕለተ ዓርብ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት ክርስቶስ ከተሰቀለበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ በክርስቲያኖች ዘንድ በጾምና በስግደት በየዓመቱ ይከበራል፡፡
በመጀመሪያ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተሰቀለው ትንቢቱን ለመፈጸም ነው፡፡ ሙሴ "ስቅልተ ትሬእያ እስራኤል ለሕይወትከ ቅድመ አዕይንቲከ ወኢትትአመና"
"እስራኤል ሆይ ሕይወትህ /ክርስቶስ/ በዓይኖችህ ፊት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ታየዋለህ፡፡ ግን አታምነውም፡፡" /ዘዳግ. 28/
ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስም "መጽአ ከመ በግዕ ይጠባሕ ወከመ በግዕ ዘኢይነብብ በቅድመ ዘይቀርጾ ከማሁኢከሠተ አፍሁ በሕማሙ በቅድመ እለ ይረግዝዎ፤ ወበ ኃጢአተ ሕዝብየ በጽሐ እስከ ለሞት፣ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ" አኮ በመልአክ ወአኮ በተንባል አላ ለሊሁ እግዚእ መጽአ ወአድኀነነ ተብሎ በሰፊው ተናግሯል፡፡ ጥቅሶቹ ብዙ ናቸው፡፡ ኢሳ. 53፡1-6
ነቢዩ ዳዊትም "አገቱኒ ከለባት ብዙኃን፣ ወአዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን" ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ ወኆ ለቁ ኵሎ አዕጽምትየ" "እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፡፡ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም" እንዳለው፡፡ 6666 ጊዜ በገረፉት ጊዜ አጥንቱ ተቆጥሮዋል፣ ይኸ አስቀድሞ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ነው፡፡ 6666 ጊዜ ለመገረፉ ግብረ ሕማማት ይገልጻል፡፡ መዝ. 21/22 ቁጥር 17-18
ክርስቶስ ለምን ሞቱ በመስቀል ሆነ? ከመስቀል በሌላ ማዳን አይችልም ነበር ወይ? ቢባል በዘመኑ የነበረው የበደለኛ አገዳደል ሥርዓት እንደየሀገሩ ሁኔታ የተለያየ ነበር፡፡
ለምሳሌ የሮማውያን ሥርዓታቸው መስቀል ነው፡፡ የአይሁድ "ውግረተ ዕብን" ነበር፡፡ የባቢሎናውያን እሳት አንድዶ እዚያ መክተት ነው፡፡ ፋርስ ለአንበሳ መጣል ነው፡፡ ጌታም በሮማውያንም ሥርዓት ተሰቅሎ ሞተ፣ ለዚህም ራሱ ጌታ ሞቱ በመስቀል እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ ዮሐ. 3፡14፡፡
ባይሰቀል፣ ጎኑ ባይወጋ ማይ ለሕጽበት፣ ደም ለጥምቀት ባልተገኘ ነበር፡፡ ብለው መምህራን ተርጉመዋል፡፡ አይ፣ በውግረትም ደሙን አይታጣም ብለው ትንቢትን ለመፈጸም ተሰቀለ ብሎ አስታርቀውታል እንጂ፡፡ የአይሁድ ሥርዓት በድንጋይ ወግሮ መግደል ነው፡፡ ጌታ የተሰቀለው በሮማውያን ሥርዓት ነው፡፡
"ኲሉ ሰቁል ዲበ ዕፀመስቀል ርጉም ውእቱ" "ሠርቶ ቀምቶ የተሰቀለ ሰው የተረገመ ነው" ትላለች ኦሪት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም "ወፆረ መርግማ ለኦሪት" አለ፡፡
ርጉም ተብሎ የአዳምን መርገም ለማጥፋት በአዳም የተፈረደው ሁሉ ተቀብሎ አዳምን ከመርገመ ነፍስ አዳነው፡፡ "ወሠዓረ መርገመ እምኔነ" ከእኛ መርገመ ኃጢአትን ደመሰሰ፣ አጠፋ ያለው ስለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ክርስቶስ ከተሰቀለ፤ ልጅነት ከተመለሰ ወዲህ ወደ ሲኦል መውረድ ቀርቷል፡፡ ይህም ዮሐንስ አፈወርቅ ገልጦታል፡፡ "እንከሰ ኢንወርድ ታሕተ አላ ፈድፋደ ንተልዎ ለዘፈጠረነ ወንበውእ ኀበ ቦአ ሐዋርያነ ህየ ንበውእ ኵልነ" ይላል፡፡ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፋልን የተባለው አምኖ፣ ተጠምቆ ፣ ጥሩ ሥራ ከሠራ ወደታች መውረድ የለም ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ነው፡፡
ቀድሞ በዘመነ ብሉይ መልካም ሥራ ቢሠሩም እነ አብርሃም ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ሁሉ በሲኦል ነበሩ፡፡ የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ አጠፋ የሚለው ስለዚህ ነው፡፡
"ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በሞትየ ወበመስቀልየ" ቀሌምንጦስ፤ "ወለትከ" የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ገድለ አዳም ገጽ 105፡125፡፡ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ገጽ 54፡8
ቀደም ብሎ እንደተገለጸው "ከመይሥዓር መርግማ ለኦሪት" በተባለው መሠረት አዳም ተርግሞ ነበር ወይ? ሲባል መልሱ አዎ ነው፡፡
ከገነት ሲኖር "ይችን ዕፅ የበላህ እንደሆነ ትመውት ሞተ" ሞትን ትሞታለህ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር ርደተ ሲኦል ያገኝሃል ነው ያለው፡፡
"ወአልበሶሙ አእዳለ ማዕስ" ያብርሃን የነበረው፣ እንደብርሌ፣ እንደ ብርጭቶ ንጹሕ የነበረው እሾኽ እማይወጋው፣ እንቅፋት የማይመታው፣ እማያደማው፣ ብርድ የሌለበት የነበር በኋላ መርገም ሲያድርብት እሾክ የሚወጋው፣ እንቅፋት የሚመታው፣ ብርድ የሚሰማው ልጅነት የሌለው ቁርበት አለበሰው፡፡
እሱ ባይረገም፣ ወደ ምድር ባይወርድ፣ በዘፍጥረት 1፡28 "ብዙ፣ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም" ብሎ ነበረ አዳም ባያጠፋ ኑሮ ሰው እንዴት ሊበዛ ይችል ነበረ ቢሉ? ይኸማ መጀመሪያ አዳም በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘ እንጂ ከሴት አልተገኘም፡፡
ሔዋንም ያለ ወንድ በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘች እንጂ ሴትና ወንድ ተገናኝተው አልተፈጠሩም፡፡ ባይበድሉ በሥልጣነ እግዚአብሔር ወንድም በአዳም አምሳል፣ ሴቱም በሔዋን አምሳል በሥልጣነ እግዚአብሔር እየተባዛ፣ ዕፀ ሕይወትን እየበላ ሺህ ዘመን ሲሞላው መንግሥተ ሰማያትን ሊገባ ተፈጥሮ ነበር፡፡
እንግዲህ ለአዳም ዕፅዋትን ሰጠው፤ አንዱ የሚመገበው በመዓዛው ይጠግባል ሁለተኛው ሕግ ሊጠብቅለት ይችን ዕፅ አትብላ ብሎ፤ ሦስተኛው ሺህ ዘመን ኑሮ ያን ሲበላ ተሐድሶ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ፈጥሮት ነበር፡፡
ይኸንንም ሰሎሞን ገልጦታል "እግዚአብሔርሰ ኢገብረ ሞተ አላ ረሲአን ሰብእ አምጽእዎ በቃሎሙ ወዓርከ አምስልዎ" እግዚአብሔር ጥንቱን ሲፈጥረው ሞት እንዲሞት እንዲቀበር ወደሲኦል እንዲወርድ አልፈጠረውም፡፡ ሕጉን እንዲጠበቅ ሺህ ዘመን በሕይወት እየተቀመጠ ወደ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ተፈቅዶ ነበር፡፡
"ኢትብልዑ እምዕፅ" ይችን እንጨት አትብሉ ያለውን የዘነጉ አዳምና ሔዋን ሞትን፣ መቃብርን፣ ስበው ጎትተው አመጡት፡፡ "ወአርከአምስልዎ" ወዳጅ አስመሰሉት አለ ወዳጅ እንዳይለይ እንዳይለይ አደረጉት፡፡ ቀጥሎ ልጆቻቸውን፣ ይህንም ቅዱስ ጳውሎስ ገልጦታል፡፡ "ወሶበ ኵነኔ ኃጢአት ወጽአ እምላዕለ አሐዱ ብእሲ ተቀሰፈ ባቲ ኩሉ ፍጥረት" ሮሜ. 5፡12፡፡
ከአንዱ አዳም የተገኘች ኃጢአት ሁሉን /መላውን/ አደረሰች፣ ከአንድ ዛፍ በተቈረጠ ጨንገር ብዙ ሕፃናት እንደሚገረፋ ኃጢአትም ከአዳም ተገኝታ ሁሉን ያዘች፡፡ መባዛት በዘር በሩካቤ የሆነው ከመርገም በኋላ ነው፡፡ በገነት ሳሉ ወንድና ሴት መሆናቸው አይተዋወቁም፡፡
አዳም እኔ ብቻ ነኝ ሲል ረዳት እንድትሆነው ፈጠረለት እንጂ በዘር በሩካቤ ሊገናኙ አይደለም፡፡ ለምን ተባዙ አለ በሥልጣኑ ያበዛቸዋል። እግዚአብሔር ሁሉን አንድ አንድ ጊዜ ነው የተናገረው "ለታብቁል ምድር" አለ ይኸ መሬት ሁል ጊዜ ታበቅላለች፡፡ "ለያብርኁ ብርሃናት" አለ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ፣ ከያለበት ሲያበሩ ይኖራሉ፡፡ "ለታውጽእ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት" ሲል አዞ፣ ጉማሬ አንድ ጊዜ ሲባዙ ይኖራሉ፡፡
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የምትወዱት ሰዎች አልቅሱለት
ብክይዎ ወላሕውዎ
እለ ታፈቅርዎ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ኤልማስ
ዘበ እደ አይሁድ ተአስረ
አመ ጸምአ ማይ ይሰቲ
ሀሞተ ወከርቤ መሪረ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
ጌታዬ አምላኬ በደል ሳይኖርበት ተገፋ
የአዳምን መርገም ሊያጠፋ
በአይሁድ እጅ ታሰረ
እንደ ወንጀለኛ ተቆጠረ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት
አዕንቃዕደ ወሰማየ
ኀበ አቡሁ ነጸረ
ሶበመንፈሱ ትወጽዕ
በላዕለ መስቀሉ ገአረ
ወይቤ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ
ውሃን የፈጠረ ተጠማ
ሀሞትን አጠጡት እየደማ
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀና አለ
መራራውን ጽዋ ተቀበለ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት
በእናቱ ፊት ሰቀሉት
በጥፊ እየመቱ ዘበቱበት
ሐዘኑንስ እንዴት ትቻለው
መተኪያ የሌለው ልጇ እኮ ነው
እውነት ወደ ምድር ቢመጣ
በሀሰት ዳኝነት ተመታ
በጀርባው ላይ ጅራፍ አረፈ
ደሙ እንደ ውሃ ጎረፈ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ሰለኔ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
ወይቤ ኤሎሄ ተፈጸመ ኲሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰሙነ ሕማማት
👉 ዓርብ
የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።
ዝርዝሩን - https://youtu.be/NMHnlH0YLEE
መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
ዝርዝሩን - https://youtu.be/NMHnlH0YLEE
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 32
👉 የምትወዱት አልቅሱለት
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 30
👉 የመከራ ጉዞ ወደ መከራ
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞•
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2)
በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2)
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
#አዝ•••
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው
እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ
#አዝ•••
በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ
ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ
#አዝ•••
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
#አዝ•••
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አክፍሎት
በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡
ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡
ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡
ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡
ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ።
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ።
አምንስቲቲ ሙዐግያ አንቲ ፋሲልያሱ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 21÷16
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ።
ወኋለቁ ኵሎ አዕፅምትየ።
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ6 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 34÷11
ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ።
ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ1 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።፥
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 28
👉 በርባን
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
📺 የስቅለት ሙሉ ፊልም
💰package ከገዙ ወደ 48.61 ብር
💵 package ከሌለዎት ወደ 81 ብር ይፈጃል
📍WiFi ብትጠቀሙ ይመረጣል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ዓርብ ሦስት ሰዓት
በዚህች ሰዓት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ጲላጦስ ፍርድ ወስደው አቁመውታል፤ ጲላጦስም በርባንን ፈትቶ ጌታችንን ገርፎት እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፣ ጌታችንንም ይዘውት ሊሰቅሉት ወስደውታል። “በየበዓሉም ከእስረኞች የመረጡትን አንዱን ይፈታላቸው ነበር። ከክፉ አድራጊዎችና ከነፍሰ ገዳዮች ጋር የታሰረ በርባን የሚባል አንድ ሰው ነበረ። ሕዝቡም ወጥተው እንደ አስለመደ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ለመኑ። ጲላጦስም መልሶ፥ “የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን?” አላቸው። የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። የካህናት አለቆች ግን በርባንን እንዲፈታላቸው ይለምኑት ዘንድ ሕዝቡን አነሣሡአቸው። ጲላጦስም መልሶ፥ “እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ?” አላቸው። እነርሱም እንደገና ‘ስቀለው’ እያሉ ጮኹ።” (ማር.፲፭÷፮-፲፫)
ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሄደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ /፪/
ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ጽናት
አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያጽናናት
ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ
እሕት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
መቅደላዊት ማርያም ሶሎሜ ዮሐና
ማርያምን አይዋት ጸንቶባት ሐዘኗ
በልቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው
ዕንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው
ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳ ነው
ያዕቆብም አልቅሷል በሌላ የሠው ደም
ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
ጠብቶ ስለአደገ የድንግልና ጡቷን
መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን
በደም ተሸፍኖ ብታየው ውበቱን
ለይልኝ አለችው ከሥጋዋ ነፍሷን
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሔደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ
በእንተ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
"ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት ፣ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።" ማቴ፳፯፥፩-፪
@ortodoxmezmur
ሕማማት ክፍል 32
👉 የኢየሱስን ልብስ ገፈፉት
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 31
👉 አለቅነትም በጫንቃው ላይ ነው
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 29
👉 ደምን የሚያወርሱ ወላጆች
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ምን ሰጡህ ይሁዳ
ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ
ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ
ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡
በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡
ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡- ስምዐ ተዋሕዶ (ልዩ ዕትም ዘሰሙነ ሕማማት)
እንበለ ደዌ ወሕማም፥
እንበለ ጻማ ወድካም፥
ያብፀሓነ አመ ከመ ዮም።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 68÷21
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ።
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ9 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 27÷17
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።
ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን።
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ3 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 27
👉 ቀሚስህ ስለምን ቀላ
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️