ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ጥር 5

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር አምስት በዚህች ዕለት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ የለውጥ በዓል ነው።

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ጥር አምስት በዚህች ዕለት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ የለውጥ በዓል ነው፡፡ ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን  እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ አሏት።ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ።ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"።እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡

ቅድስት አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ "የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን"አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ዳግመኛም ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን" አለ፡፡

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ  በዓለ ልደት ታህሳስ 29 በጌታችን ልደት ነው:: ነገር ግን ዕለቱ ትልቅ ሚስጥር የያዘ ነውና አባቶቻችን የጌታ ልደት ዘምረው ጣዕሙ ሳያልቅ ቅዳሴ ይገባሉ:: ስለዚህ የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ከሚቀር ልደታቸው ጥር 5 እንዲከበር ስርዓት ሰርተዋልና በዓለ ልደታቸው በዚህች ቀን ተከብሮ ይውላል፡፡

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ዮሐንስኒ

ዮሐንስኒ ሃሎ ያጠምቅ/2/ 
በሄኖን በቅሩበ ሣሌም/4/ 

ትርጉም፡-
ዮሐንስ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ 
በዮርዳኖስ ያጠምቅ ነበር

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥምቀተ ባሕር

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2ጊዜ/
ሀሌ ሉያ /4ጊዜ/

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ሄደ ወደ ኋላ
አዝ - - - - -
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና
አዝ - - - - - -
ጌታችን ሲጠመቅ በ30 ዓመት
ባሕር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዛን ለታ
አዝ - - - - - - -
እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የጽድቅ መሰላል የድኅነታችን ለእኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የጥምቀት መዝሙር ስብስብ #1
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬  🛑 ልጆቻችንን ለታቦት እንስጥ ወይስ ለክርስትና እናት እና አባት? ከእናንተ ለተጠየቀው ጥያቄ የተሰጠ መልስ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ መልሱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/MGu9vE6vImw
https://youtu.be/MGu9vE6vImw

እናንተም ያላችሁን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በመጀመሪያ ቃለ ሕይወት ያሰማል።እንዲህ አይነት ተከታታይ ትምህርት መጀመሩ መልካም ነዉ።ወደ ጥያቄየ ስመጣ
1. ድህረ አለም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማሪያም መወለዱ አለምን ለማዳን ነዉ ግን ቅድመ አለም ከእግዚአብሔር አብ መወለዱ ለምን ነዉ?
2.ጌታችን በምድር ላይ ሳለ በተዋህዶ የመለኮትንም የስጋንም(ከሀጢያት በስተቀር) ባሕሪይ ይዞ ነበር ከትንሳኤ በኃላ የስጋ ባሕሪይ አለ ወይስ የለም? ማለት ለምሳሌ አልአዛር ሲሞት ሲሞት እንደ መለኮቱ አስነስቶታል በስጋዊ ባሕሪዉ ደሞ አልቅሶለት ነበር እና አሁን ላይ እነዚህ የሰዉ ባሕሪያት አሉ ወይ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እሽ እግዚአብሔር ይስጥለን
1. ቃል ከስጋ ጋር በግብር ተዋህዳል አልተዋኸደም ከተዋሀደስ እንዴት ነዉ የምናገናዝብ???
2. ብዙ ግዚ ቅብዐቶች የሚሉት ቅብዓት ማለት መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ለዚህም ማስረጃ መፅሀፈ አክሲማሮስ ዘእሁድ ክፍላ 4 እና ዘማክሰኞ ክፍል 2 እና ይኸ እንዴት ነው ግልጽ ቢሆን????

3. ክርስቶስ ማለት ምን ማለት ነዉ ምን ሲሆን የወጣለት ስም ነዉ አማኑኤልስ????

3. ጴጥሮስ ሉቃ 9:20 አንተ ከእግዚአብሔር የተቀባኸ ነህ ያለዉ ይኸ እንዴት ነዉ???

4.ሲወሀድም ሲቀባም ከመቅፅበት አይን ከአንድ ጊዜ ነዉ ማቴ አንድምታ 1:16 ይኽም ግልፅ ቢሆን???
እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቃል ከስጋ ጋር በግብር ተዋህዳል አልተዋኸደም ይኸም በቀጣይ ቢብራልን???
ቃለ ህይዎትን ያሰማልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እስቲ ግልፅ ያልሆነልኝ ጥያቄ ነበር እና
1 ተዋህዶ ምስጢር ወይስ ሀይማኖት???
2.ተዋህዶ ተብሎ የሀይማኖት ስያሜ መቼ ተሰጠ???ማን ሰየመዉ ???ለምን ለኢትዮጵያ ብቻ በኦርቶዶክስ ለይ ተዋህዶ ተብሎ ተቀጠለ???ሌሎችን አምስቱን ምስራቀ ቤተክርስቲያን ብንመለከት እነ ግብጽ ኦርቶዶክስ ነዉ የሚባሉት እና ለምን ተዋህዶ የሀይማኖት መጠርያ ለኢትዮጵያ ብቻ ሆነ??
እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!!!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📺 ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
መንፈሳዊ ፊልም
#ክፍል_ሁለት
💰package ከገዙ ወደ 14.90 ብር
💵 package ከሌለዎት ወደ 24.84 ብር ይፈጃል
📍WiFi ብትጠቀሙ ይመረጣል

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​#ቅዱስ_እስጢፋኖስ

በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
(የሐዋ.6፡8-ም.7፡53)

በሐዋርያት ስብከት ቤተ ክርስቲያን ስትስፋፋ በትምህርታቸውና በተዐምራታቸው ተስበው ወደ ክርስትና እምነት የተመለሱ ከአይሁድና ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖች መሬታቸውንና ጥሪታቸውን በመሸጥ  ያላቸውን ሀብት አንድነት በማድረግ በኢየሩሳሌም የአንድነት ኑሮን ይኖሩ ነበር፡፡ በሕብረትም የሐዋርያት ትምህርትን በመስማትና  በጸሎት ይተጉ እንዲሁም ማዕድን በመባረክ በጋራ ይመገቡ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም “አንድ ልብና አንዲትነፈስ አላቸው በማለት (የሐዋ.4፡32) ስለአንድነታቸው ፍጹምነት ይነግረናል፡፡

ነገር ግን በቁጥር እየበዙ ሲመጡ በመካከላቸው በማዕድ ምክንያት ልዩነት ተፈጠረ፡፡ ከይሁዲነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ክርስቲያኖች በምግብ ክፍፍል ወቅት ከግሪክ የመጡትን ይጸየፉዋቸው፣ በተለይ ባልቴቶቻቸውን ቸል ይሉባቸው ስለነበር በማኅበሩ መካከል አለመስማማት ተፈጠረ፡፡ ይህም በሐዋርያት ዘንድ ተሰማ፡፡

ሐዋርያትም “የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ አይደለም”የሐዋ.6፡2) በማለት ማዕዱንና በውስጥ ያለውን አገልግሎት ያስተናብሩ ዘንድ ሰባት ሰዎች እንዲመረጡ የክርስቲያኑን ኅብረት ጠየቁ፡፡ ምዕመናኑም በአሳቡ ደስ ተሰኝተው መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ክርስቲያኖችን መረጡ፡፡ ሐዋርያትም እጆቻቸውን ጭነው ረድእ ይሆኑአቸው ዘንድ ዲያቆናት አድርገው ሾሙአቸው፡፡

ከእነዚህም ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስቲያኖች ዓብነት የሆነው ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ይገኝበታል፡፡ እስጢፋኖስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “አክሊል” ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ግእዝ በኋላም ወደ አማርኛ የመለሱት አባቶች በቀጥታ የግሪኩን እስጢፋኖስ የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ምንም እንኳ ስሙ የግሪክ ስም ይሁን እንጂ በትውልዱ አይሁዳዊ ነው፡፡ ወላጆቹ ይህንን ስም ሊሰጡት የቻሉት በፍልስጤም ጠረፋማ ከተሞች ይኖሩ ስለነበር የግርክ ባሕልና ቋንቋ ተጽእኖ አድሮባቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ በሐዋርያት ጥበቃ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ከአምላክ ዘንድ ባገኘው የማስተማርና የፈውስ ሀብት ያገለግል ነበር፡፡ በእርሱም ታላላቅ ተኣምራት ይፈጸሙ ነበር፡፡ ስለዚህም ሕዝቡ ከፊት ይልቅ እጅግ እየበዛና በትምህርት እየጠነከረ መጣ፡፡ አይሁድም ይህን ተመልክተው በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ በቅናትና በጠላትነት ተነሡበት፡፡ ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ባገኘው ጥበብና ኃይል እነርሱን በቃልም በድርጊትም ይቃወማቸው ነበርና ሊረቱት አልተቻላቸውም፡፡ ስለዚህም እግዚአብርሔርን፣ ሙሴ ሲሳደብ ሰምተነዋል፣. ሙሴ የሠራልንን ሥርዐት ይለውጣል፣ በዚህ ቤተ መቅደስና በሕጉ ላይ የስድብን ቃል ይናገራል፣ ይህንንም ቤተ መቅደስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አፍርሱ ብሎአል እያለ ያስተምራል አያሉ፣ ሕዝቡን፣ ሽማግሌዎችንና ጸሐፍትን በማናደድ ይዘው ከሸንጎ ፊት አቆሙት፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስን በሸንጎ ፊት ባቆሙት ጊዜም ፊቱ ልክ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ በርቶ ነበር፡፡ እርሱም ለተከሰሰበት ነጥብ መልስ ሰጠ፡፡ ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ ለእነርሱ የተሰጣቸውን በረከት በመቃወማቸው ከተስፋ ቃል እርቀው እንደተወገዱ ገለጠላቸው፡፡ ክርስቶስንም ባለመቀበላቸው ወቀሳቸው፡፡ በዚህም ምክንያት በቁጣ ተነሣስተው ከከተማ ውጭ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ አይሁድ በድንጋይ እየወገሩት ሳለ ሰማያት ተከፍተው ክርስቶስን በአብ ቀኝ ቆሞ ተመለከተ፡፡ ይህንን ራእይ የክርስቶስን ትንሣኤን ለማይቀበሉት አይሁድ አሰምቶ ተናገረ፤ እነርሱ ከፊት ይልቅ በእርሱ ጨከኑ በድንጋይም ወገሩት፡፡ ነገር ግን ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታውን ክርስቶስን መስሎ ነበርና ልክ እንደ መምህሩ ክርስቶስ “አቤቱ ይህን ኀጢአት አትቁጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኾ  ነፍሱን ሰጠ፡፡ በቤተክርስቲያንም ታሪክ ስለክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ዲያቆን ሆኖአል፡፡

በደማስቆ መንገድ ላይ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ሳውል በኋላም ቅዱስ ጳውሎስ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ  ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ በሚወግሩበት ወቅት በእርሱ ሞት ተስማምቶና ድንጋይን በእስጢፋኖስ ላይ ያነሡትን የአይሁድ ልብስ ይጠብቅ የነበረ ብላቴና ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ከሆነ በኋላ የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች አጥምቆአቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ድንቅ ነው፡፡  ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ይህን ቅዱስ የመታሰቢያ ቀን በመስጠት  ጥቅምት 17 የድቁና ማዕረግን በአነብሮተ ዕድ በሐዋርያት የተቀበለበትን፥  ጥር 1 ደግሞ ዕረፍቱን ታስባለች፡፡

የቅዱሱ በረከት በሁላችንም ላይ ይደር!
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ልደተ_ክርስቶስ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ልደተ_ክርስቶስ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ሥላሴ ትምህርትን እዚህ ጋር ታገኙታላችሁ👆

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዓለምን በደል

የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ 
ዘጠና ዘጠኙን መላእክት ትቶ 
ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 
- - - - - - አዝ - - - - - -
የሰማያት ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ 
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ 
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 
- - - - - - አዝ - - - - - -
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ 
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ 
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 
- - - - - - አዝ - - - - -
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቀን ሲመሠርት 
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት 
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬  🛑 እግዚአብሔር አብ ከክርስቶስ ጋር በዕለተ አርብ አብሮ ተሰቅሏል? ከእናንተ ለተጠየቀው ጥያቄ የተሰጠ መልስ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ መልሱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/aI_Noe6fOAQ
https://youtu.be/aI_Noe6fOAQ

እናንተም ያላችሁን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ግነዩ_ለእግዚአብሔር

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር
እስመ ለአለም ምህረቱ/2/ 
#አዝ-------------- 
እናመስግናሽ የአምላክ እናት በዝማሬ/2/
የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ/4/ 
#አዝ ----------- 
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ/2/  
መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ /4/ 
#አዝ ----------- 
በድንግልና የወለድሽው ያንቺው ጽንስ/2/
የድኩማኖች ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ/4/ 
#አዝ ------------ 
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ/2/ 
በቸርነቱ ጠብቆ ከበደል አራቀን/4/ 
#አዝ ------------- 
ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም የዘከረ/2/
በመንግስተ ሰማይ ይኖራል እንደተከበረ/4/
#አዝ ---- 
እመቤታችን እናታችን ማርያም/2/
የተማጸነሽ ይድናል ለዘለዓለም/4/ 
#አዝ ---- 
ድንግልናሽ ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ/2/ 
የጌታችን እናት ማርያም ድንግል አንቺው ነሽ 
የጌታችን እናት ማርያም ንጽሕት አንቺ ነሽ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የጥምቀት መዝሙር ስብስብ #2
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#እንደበደሌ አልከፈልከኝም

እንደበደሌ አልከፈልከኝ 
ፍቅር ነህና እያለፍከኝ 
ምን እከፍላለሁ ላንተ የሚሆን
ታውቀው የለም ወይ ችሎታዬን
#አዝ
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል 
ታረገዋለህ የኔን በደል 
እንደምትወደኝ አዉቃለሁ እኔ 
ባስመርርህም እድሜ ዘመኔ 
#አዝ
ከሰው ሁሉ ጋር ብትፈራረድ 
የትኛዉ ይሆን ፀድቆ የሚሔድ 
ያለምን ሃጢያት ደምህ ሸፈነው 
የተፈወስኩት እኔም በእርሱ ነው
#አዝ
ዘመኔ እንደ ሳር መሆኑን አስብ 
እድሜዬ ታጥሯል በጊዜ ገደብ 
መልካም ሰርቼ እንዲያልፍ ወራቴ 
በጎውን አብዛ በሰውነቴ
#አዝ
የልጅነቴን አታስብብኝ 
መጨረሻዬን አሳምርልኝ 
በሩን አትዝጋው ያዳራሹን 
ዘይቴን ልሙላ የመቅረዙን 

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ጥር 2
ቅዱስ አቤል ጻድቅ


ጥር ሁለት በዚች ቀን ደሙ በግፍ የፈሰሰ ጻድቁ አቤል አረፈ እርሱም ወንድሙ ቃየል የገደለው የሙታን በኵር የሆነ ነው።

ምክንያቱም አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተላልፎ እንዳይበላው የታዘዘውን ዕፅ በላ ያን ጊዜ በእርሱና በልጆቹ ላይ ሞት ሠለጠነ ለኃጢአትም ተገዥ ሆነ። ሰይጣንም ሰውን ለማሳት ሠለጠነ ከዚህም  በኋላ አዳም ከገነት ወጥቶ ወደታችኛዋ ምድር ወረደ ስለ በደሉና የፈጣሪውንም ትእዛዝ በመተላለፉ ፈጽሞ እያዘነና እያለቀሰ መቶ ዓመት ኖረ።

ከዚህም በኋላ አዳም ሔዋንን በግብር አወቃት ፀንሳ ቃየልንና እኅቱን ኤልዩድን ወለደች ሁለተኛም ዐወቃት አቤልንና እኅቱን አቅሌማን ወለደቻቸው አዳምም ሔዋንን እነሆ ልጆችሽ አካለ መጠን አደረሱ ጐለመሱ ቃየል የአቤልን እኅት አቅሌማን ያግባት አቤልም የቃየልን እኅት ኤልዩድን ያግባት አለ።

ቃየልም እናቱን ሔዋንን እንዲህ አላት ለእኔ ከእኔ ጋር የተወለደች እኅቴን ማግባት ይገባኛል አቤልም ከእርሱ ጋር የተወለደች እኅቱን ያግባ ቃየል ከእርሷ ጋር የተወለደ ኤልዮድም እናቷ ሔዋንን የምትመስል እጅግ የምታምር መልከ መልካም ናትና።

አዳምም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ ጭንቅ ሆነበት ቃየልንም አብራህ የተወለደች እኅትህን ታገባት ዘንድ አይገባህም አለዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቅርቡና መሥዋዕቱን ለተቀበለው ይሁን አለው።

መሥዋዕትንም በአቀረቡ ጊዜ የአቤልን መሥዋዕት እግዚአብሔር ተቀበለ የቃየልን ግን አልተቀበለም ስለዚህም ቃየል ፈጽሞ አዘነ ሰይጣንም ተገናኘውና ምን ያሳዝንሃል አለው ቃየልም ለወንድሜ ለአቤል እኅቴን እተውለት ዘንድ አባቴ አዘዘኝ አለው። ሰይጣንም ምክርን ከኔ ስማ ወንድምህን ወደ ውኃ ምንጭ ይዘኸው ሒድ ውኃንም ሲጣጣ ራሱን በደንጊያ ምታው በሞተ ጊዜ ሁለቱንም ታገባቸዋለህ የሚከለክልህ ማነው አለው ለቃየልም የሰይጣን ምክር ደስ አሰኘው ልቡም በዝሙት እሳትነት ነደደ ሰይጣን እንዳስተማረውም ወንድሙን አቤልን ገደለው ለሴት ስለ መቅናትም ጻድቁ አቤል በወንድሙ እጅ ሞተ እንዲህም ሞት ወደ ዓለም ገባ።

እግዚአብሔርም ቃየልን ወንድምህ አቤል ወዴት ነው አለው። ቃየልም አላውቅም በውኑ እኔ የአቤል ጠባቂው ነኝን አለው። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው ቃየል ምን አድርገሃል የወንድምህ የአቤል ደም ጩኸት ከምድር ወደኔ ደርሷል። አሁንም በእጅህ የፈሰሰውን የወንድምህን ደም ትጠጣ ዘንድ አፍዋን የከፈተች ምድር የተረገመች ትሁን አንተ ታርሳታለህና በረከቷን ትሰጥህ ዘንድ አትጨምርም በምድር ላይ ፈሪ ተቅበዝባዥ ሁን።

ይህም መርገም ዘሩ በጥፋት ውኃ ከምድር ገጽ እስከ ሚደመሰስ በቃየል ላይ የበዛ ሆነ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ጸሐፍት ፈሪሳውያንን ሲዘልፋቸው እንዲህ አላቸው ስለዚህ ነቢያትን ሊቃውንትን ጥበበኞችን ወደናንተ እልካለሁ ከነርሱ የምትገድሉት አለ የምትሰቅሉትም አለ በምኵራባችሁ የምትገርፉት አለ ካንድ አገር ወዳንድ አገር ታሳድዷቸዋላችሁ።

ከጻድቁ ከአቤል ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በዓለም የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርስ ዘንድ።

ጳውሎስም አለ ቃየል ካቀረበው መሥዋዕት ይልቅ አቤል በሃይማኖት ለእግዚአብሔር ያቀረበው መሥዋዕት ተሻለ ስለ እርሱም ደግ እንደሆነ መሰከረለት መሥዋዕቱንም በመቀበሉ ምስክሩ እግዚአብሔር ነው ደግ እንደሆነም ከሞተ በኋላ ተናገረ።

ከዚህም በኋላ አዳም ልጁን በአጣው ጊዜ ወንድምህ አቤል ወዴት አለ ብሎ ቃየልን ጠየቀው ቃየልም በቁጣ አላውቅም እኔ የአቤል ጠባቂው ነውኝን ብሎ መለሰ አዳምም ልጁን ይፈልግ ዘንድ ወደ ዱር ሮጠ በወንዝ ዳርም በድኑን አገኘና አንገቱን አቅፎ ማን ገደለህ አለው ከበድኑም ወንድሜ ቃየል ገደለኝ የሚል ቃል ወጣ። አዳምና ሔዋንም በልጃቸው በአቤል ሞት ሃያ ስምንት ዓመት ያህል ሲያለቅሱ ኖሩ።

ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ አዳም መጥተው የዓለሙ ሁሉ አባቶች አባት አዳም የምሥራች እነሆ ልጅህ አቤል የገነትን ዛፎች ተሳለመ ነፍሱም እንደ ተወደደ መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ዐረገች አሉት።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እሺ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን እያልኩ ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ አብም በተገናዝቦ ተሰቅሏል ብለው አባቶች ያስተምራሉ፤ተገናዝቦ የሚለው ላይ ማብራሪያ ቢሰጠው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እኔም አንድ ነገር ያልገባኝ ነገር አለ አሁን ለምሳሌ ሴት ልጅ በ80ቀኗ ክርስትና ትነሳለች ወንድ ልጅም በ40ቀኑ ክርስትና ይነሳል አንዳንዶች ልጆቻቸውን ሲያስነሱ ለታቦት የሚሰጡ አለ ለማርያም ለሚካኤል :::::::::ማለት ነውአንዳንዶች ደግሞ ለሰው ይሰጣሉ ሴትም ለሴቷን ክርስትና እናት ትባላለች ወንድም ለወንዱክርስትና አባት ይሆና አሁን እኔ ያልገባኝ ነገር በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ማለት ከታቦት ከሚሰጡና ከሰው በጣም ግራ ይገባኛል እስኪ ብታብራሩልኝ ??? በተረፈ በርቱ ጸጋውን ያብዛላችሁ👏👏👏

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቃለ ህይዎትን ያሰማልን እስቲ ይኸም ቢብራራልን
1. እግዚአብሔር አብ ወልድን በስጋዉ የወለደዉ ልደት እንዴት ነዉ መዝ 2:7 አንተ ልጄ ነህ(ቅድመ ዓለም የተወለደዉ ልደት) እኔ ዛሬ ወለድኩህ( ወልድን በስጋዉ እንደወለደዉ) ይነግረናል ይኸም አብሮ ቢብራራልን???
እግዚአብሔር ይስጥልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝

👉የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች በምሥጢረ ሥላሴ እና ምሥጢረ ስጋዌ ዙሪያ የተጠየቁ ጥያቄዎች ነበሩ በእነርሱ ዙሪያ አሁን መልስ እንሰጣለን

ተከታተሉ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📺 ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
መንፈሳዊ ፊልም
#ክፍል_አንድ
💰package ከገዙ ወደ 6.48 ብር
💵 package ከሌለዎት ወደ 10.80 ብር ይፈጃል
📍WiFi ብትጠቀሙ ይመረጣል

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📌ሰብአ ሰገል ማናቸው?
📌ከየት መጡ?
📌ሀገራቸው የት ነው?
📌ስንት ናቸው?
📌ለምን ዕጣን፣ ከርቤ እና ወርቅ አመጡ?

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ልደተ_ክርስቶስ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርትን እዚህ ጋር ታገኙታላችሁ👆

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ማስታወቂያ✝

👉በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ።

በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርታችን ዙሪያ የተላኩ 4 ጥያቄዎች ነበሩ መልሶቻቸው እነዚህ ናቸው👇

1.መ (ሀ እና ለ)
2.መ ሁሉም
3.ሐ. ከ2 ባህርይ 1 ባህርይ፤ ከ2 አካል 1 አካል መሆን ማለት ነው
4.መ ሁሉም።

እነዚህን ይመስላሉ😊 በትክክል እንደመለሳችኋቸው ተስፋ አደርጋለሁ።

እስከ አሁን ምሥጢረ ሥላሴ እና ምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርትን በድምጽ ልከንላችሁ ስትማሩ ነበር እንደ ድንገት ያላዳመጣችሁ ወይም ያለፋችሁ ካላችሁ ወደ ላይ በመውጣት ታዳምጡ ዘንድ እንጠይቃለን።

ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ እነዚህን 5ቱን አእማደ ምሥጢራት ማወቅ አለበት የኦርቶዶክስነታችን መሠረት ስለሆነ። ስለዚህ ትምህርቱን ከታች እናስቀምጥላችኋለን ወደ ላይ ወጥታችሁ አዳምጡት።

👉 በሁለቱም ርዕሶች ዙሪያ የተጠየቁ ጥያቄዎች አሉ እነርሱን የጠየቃችሁ እህት ወንድሞች የአሁኑ ሰኞ 3:00 ላይ መልስ የምንሰጥበት ስለሆነ እንድታዳምጡ እንጠይቃለን።


መልካም በዓል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አንፈራፁ

አንፈራፁ ሰብዓሰገል /2/
ረኪቦሙ ህፃን /2/ ዘተወልደ ለነ /4/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал