ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት

እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥረው እንደ መላእክት አድርጎ ነው። ቅዱስት መላእክት ለባውያን፡ ሥጋዊ መሻት የሌለባቸው ከኃጢአት የነጹ እንደ ኾኑ ሁሉ የሰው ልጅም ሲፈጠር ምንም እንኳን ሥጋን የለበሰ ቢኾንም እንዲህ ኾኖ ነበር። የሰው ልጅ ያልተለመደ ዓይነት መልአክ ኾኖ የተፈጠረ ነው። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ አዳምንና ሔዋንን ኹለት መላእክት" የሚላቸውም ለዚህ ነው። ከቅዱሳን መላእክት ጋር ኾኖ ከአምላክ ጋር አንድነት የነበረው፡

ዲያብሎስና እርሱን የተከተሉት መላእክት እንዲቀኑ ያደረጋቸው የሰው ልጅ ሕይወት ነበር። ምንም እንኳን ሥጋን የለበሰ ቢኾንም እንደ ረቂቃኑ” መላእክት መኖሩ፣ በአንድ ጊዜ ረቂቅና ግዙፍ ፍጥረት መኾኑ ነበር ያስቀናቸው::

ይህ ሰው ለሞት የተፈጠረ አልነበረም። ምንም እንኳን ካለ መኖር ወደ መኖር የተፈጠረ እንደ መኾኑ በባሕርዩ ሊሞት የሚችል ማለት ሞት የሚስማማው ገና የተፈጠረ ቢኾንም፥ ሕያው ባሕርይ በኾነው በራሱ በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠረ በመኾኑ ሕጉን በመጠበቅና ፈጣሪውን በማወቅ ይህንን አርአያ እግዚአብሔርን ቢጠብቅ ግን አይሞትም ነበር። እግዚአብሔር ሕያው የምታደርገውን ነፍስ የሰጠው ስለ ኾነ ብሩህ፡ ውብ፡ ለባዊ፡ መልካም ሥራዎችን ለመሥራት ዓቅም ያለው የተፈጠረ ነው፥ ይሀ በርግጥም ልዩ ክብር እንደ ነበረ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘቡል) ሲገልፀውም፡-

ከዚህ ክብር የሚበልጥ ምን ክብር አለ? ከዚህ ትምክሕት የሚበልጥ ምን
የሚያስመካ ነገር አለ?..
. ሰውን በእርሱ አምሳል እንደ ፈጠረው እንዲመሰክር ከመኾን የበለጠ የሚያስመካ ምን ነገር አለ?" ይላል ።"
ሙስና፡ ሞት፡ ሕማምና ድካም የመጡበት ከዚህ በኤደን ገነት ውስጥ ይኖርበት ከነበረው የንጽሕናና የድንግልና ሕይወት ፈቀቅ ሲል ነው። ሞት የሚስማማው ኾኖ የተፈጠረ ቢኾንም፥ በገዛ ፈቃዱ እንዳይሞት ማድረግ ይችል የነበረው የሰው ልጅ መዋቲ የኾነው ከበደለ በኋላ ነው።

ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ የተፈጠረ ቢኾንም፥ ክብሩ ግን ሰማያዊ ነበር። አፈርና ትቢያ የኾነው፡ እግዚአብሔር የነገረውን ባለ ማመን ብሎም ባለመታዘዝ ሲበድል ነው። ጥንቱን ከትቢያ የተፈጠረ ቢኾንም እስኪወድቅ ድረስ ክብሩ እፍ ተብላ ከተሰጠችው ነፍሱ የተነሣ ከፍ ያለ ነበር። ስለዚህም እንደ መላእክት ስለሚበላው፡ ስለሚጠጣው፣ ስለሚለብሰው፡ ስለ እንቅልፍ፣ ወጥቶ ወርዶ ስለ መሥራት፣ በአጠቃላይ ስለዚህ ዓለም ኑሮ የሚጨነቅ አልነበረም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይህን ግልፅ አድርጎ ሲነግረንም እንዲህ ይላል፡-

ምንም እንኳን በዚህ ምድር ላይ ሥጋ ለብሶ ቢኖርም ፍትወተ ሥጋ ሳይኖርበት እንደ ሰማያውያን መላእክት ኾኖ ይኖር ነበር። በትረ መንግሥቱን ይዞ የንግሥና ዘውዱን ጭኖ፡ ሐምራዊ መጎናጸፍያውን አድርጎ እንዳጌጠ ንጉሥ በነጻነትና በፍጹም ደስታ ይኖር ነበር። አንድም ነገር ሳይጐድልበት እጅግ ባለጸጋ ኾኖ በገነት ይኖር ነበር።"


ይበላ የነበረ ቢኾንም፤ በአንድ መልኩ ጥሮ ግሮ የሚበላ አልነበረም፡ በሌላ መልኩ ደግሞ አሁን የምናውቀው ዓይነት ረሃብና ጥም ስለ ነበረበት አይደለም። መላእክት እንደማይርባቸውና እንደማይጠማቸው ኹሉ፥ ሰውም እንደዚህ ነበር። ሰውስ ይቅርና ዛሬ ሥጋ በል የምንላቸው እንስሳትም ከውድቀት በፊት ምግባቸው ማር እንጂ ሥጋ እንዳልነበረ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ይነግረናል።'

በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምንም እንኳን ሥጋ የለበሰ የነበረ ቢኾንም፥ በሥጋው ብቻ የታጠረ ግን አልነበረም። መላእክት ሥጋዊ ፍላጎት እንደ ሌለባቸው ኹሉ' ሰውም ይህ ኣልነበረበትም። መላእክት ልብስ እንደማያሻቸው ኹሉ' ሰውም ልብስ የሚያስፈልገው አልነበረም። ልብሱ፣ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ እንደሚነግረን የክብር ልብስ ነበር ይህን የክብር ልብስ ለብሶ እያለ' እስራኤላውያን ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፊቱን ሳይሽፍን ማየት የማይቻላቸው እንደ ኾኑ፥ የምድር ፍጥረታትም አዳምንና ሔዋንን ማየት አይቻላቸውም ነበር። አዳም ለእንስሳቱ ስም ሲያወጣላቸውና በፊቱ ሲያልፉ እንኳን ቀና ብለው ማየት ሳይቻላቸው አጎንብሰው ነበር። አዳም ለብሶት የነበረውን የክብር ልብስ ማየት አይቻላቸውም ነበር።' እንስሳቱስ ይቅሩና ዲያብሎስ ይህን የአዳም ክብር በግልፅ ማየት አይቻለውም ነበር።" አዳም ይህን የክብር ልብስ ለብሶ ሲኖር ከግዙፍ ልብስ ዕራቁቱ እንደ ኾነ እንኳን አያውቅም ነበር። ስለዚህ አሁን የምናውቀው ዓይነት ልብስ ለሰው ልጅ የተሰጠው "ለዚያ አጊጠዉበት ለነበረው የብርሃን ልብስና ከሥጋ መሻቶች ነጻ ኾነው ለኖሩበት ሕይወት ያልተገቡ ኾነው በመገኘታቸው ነው።'' የቆዳ ልብስ የተሰጣቸው ለዚያ የክብር ልብስ ያልተገቡ ኾነው በመገኘታቸው ብቻ ሳይኾን ላለማመናቸውና ላለመታዘዛቸው ማዘከሪያ እንዲኾን ነው።

ዳግመኛም የሰው ልጅ በራሱ ላይ ብቻ ሳይኾን በሌሎች በሚታዩ ፍጥረታት ላይ ንጉሥ ኾኖ ይኖር የነበረ ነው። መጨረሻ ላይ መፈጠሩ፣ ሌሎቹ ፍጥረታት ኹሉ እርሱ እንዲጠቀምባቸው መዘጋጀታቸው በገነት ውስጥ ያለ ጣር መኖሩ፡ እንስሳቱ ኹሉ ስም እንዲያወጣላቸው ወደ እርሱ መምጣታቸውም ይህን ንግሥናውን በግልፅ የሚያስረዱ ናቸው። ፍርሐትና መንቀጥቀጥ የመጣበት ከበደለ በኋላ ነው፤ ሔዋን ከእባብ ጋር ያለ ፍርሐት መነጋገርዋ ይህን የሚያሳይ ነው።

የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት እጅግ ዐዋቂና ጠቢብም ጭምር ነበር። ይህም ሳይሳሳትና ሳይደግም ለእንስሳቱ ስም በማውጣቱ ታውቆአል።

ነጻነትም ነበረው። ከመበደሉ በፊት የሚያሻውን በጎ ነገር ለማድረግ አያቅተውም ነበር። በጎ ማድረግን አስቦ ማድረግ ያቃተው ሲበድል ነው።

ከእግዚአብሔር ጋር እንደ ባልንጀራ አፍ ለአፍ የሚነጋገር ነበር። አባት ለልጁ ኹሉን ነገር እንደሚያስተምረው፥ እግዚአብሔርም ለአዳም ኹሉን ነገር ያስተምረው ነበር። በኋላ ሲወድቅ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠውም የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ስለ ራቀ ነው። አጠገብ ላለ ወዳጅ ደብዳቤ አይጻፍምና።በጎውንና ክፉውን የሚያውቅ መለየት የሚችል ነበር። መለየት የማይችል ቢኾን ኖሮ ባልተጠየቀ ነበርና።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ትንሿ ቤተክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት፳፪ /22/


በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ።

ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።

በኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።

ንጉሥ ኔሮንም እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ።

ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ጥቅምት 21 ቀን እመቤታችን ሐዋርያው ማትያስን ከእስር ያስፈታችበት ቀን ነው!

በዛሬው እለት ማለትም ጥቅምት 21 ቀን እመቤታችን ለሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ አስገራሚ ተአምር አድርጋለታለች፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ቅዱስ ወንጌል እንዲያስተምሩ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ሰዎችን ወደሚበሉ ሀገር ዕጣ ደረሰው፡፡ ቅዱስ ማትያስም ወንጌልን እሰብካለሁ ብሎ ሀገራቸው ገባ፡፡

በዚያች ሀገር የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ አንድ ሰይጣናዊ ልማድ ነበራቸው። ይኸውም አንድ ሰው ሀገራቸው ከመጣ ይዘውት ሁለቱንም ዓይኑን በማውጣት ለ30 ቀን እንደ ከብት ሣር እያበሉት በእስር ቤት ያቆዩታል፡፡ በ 30ኛው ቀንም ከእስር ቤት አውጥተው አርደው ይበሉታል። ታዲያ እነዚህ ሰው በላ ሰዎች ቅዱስ ማትያስንም ይዘው ሁለቱን ዓይኖቹን አወጡ በእስር ቤትም አስቀመጡት፡፡

ቅዱስ ማትያስም በእስር ቤት በጭንቅ ሆኖ ወደ እመቤታችን መማጸን ጀመረ፡፡ እመቤታችንም ቅዱስ ማትያስ የሚበላበት ሠላሳኛው ቀን ሳይደርስ በጸሎቷ ኃይል ከእስር ቤት አስወጣችው በተአምራትም ከሰው በላ ሰዎች አስመለጠችው፡፡

እመቤታችን በመዓዛ መለኮት በጣፈጠ ጥዑም አንደበቷ ከችግራችን፣ ከሕመማችን፣ ከእሥራታችን ትፍታን፡፡

ቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዝማሬ ዳዊት ትክክለኛው የቲክቶክ ገጽ ይህ ነው።

በቅርቡ አዳዲስ ስራዎች ይዘን ስለምንቀርብ ቲክቶክ የምትጠቀሙ ቤተሰቦቻችን Follow እና ሼር በማድረግ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ያስፉ።

https://vm.tiktok.com/ZMhQPn89c/
https://vm.tiktok.com/ZMhQ5DW1f/

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ማርያም ማርያም ብዬ

ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወልደኝ/2/

ገና በማህጸን በእናቴ የምጥ ቀን
ደጋግሜ ሰማሁ ሲጠሩ ስምሽን
በሰከንዳት እድሜ የማውቃት አንዲት ቃል
ልቤ ላይ ያለው ስም ማርያም ማርያም ይላል/2/
ማርያም ማርያም

አዝ

ሔዋን ምጧ ቀሎ ልጆቿን ታቀፈች
በአማላጅነትሽ እናቴም ታመነች
በተወለድኩበት በመጀመሪያው ቀን
ስምሽን እየሰማሁ ወጣሁ ከማህጸን /2/
ማርያም ማርያም
አዝ

ከቃልኪዳን ስም ጋር አደግኩኝ አብሬ
ምልጃሽ ሳይለየኝ አለሁ እስከ ዛሬ
የህይወቴን ፊደል ካንቺ ላይ ቆጠርኩኝ
በልጅሽ አምኜ ዳግም ተወለድኩኝ /2/
ማርያም ማርያም
አዝ

የክፉ ቀን ስንቄ ያዘልኩሽ በልቤ
የህይወቴ ምግብ የእንጀራ መሶቤ
እንደ ትላንትናው ዛሬም እጠራሻለሁ
የመስቀል ስር ክብሬን እንዴት እረሳለሁ
የመስቀል ስር ክብሬን እንዴት እተዋለሁ/2/
ማርያም ማርያም

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከሰማዩ ከፍታ

ከሰማዩ ከፍታ ከፍ ብላ ጽዮን
በሰገነት ላይ ተቀምጣ
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ /2/

አይን ከሞላባቸው ከኪሩቤል
ክንፋቸው ከበዛ ከሱራፌል
ከሊቃናቱ ሁሉ ትበልጣለች
እሳተ መለኮትን በሆዱዋ ስለተሸከመች

አዝ

ከንጉሱ በስተቀኝ ከዙፋኑ
ንግስቲቱ ቆማለች በየቀኑ
የቃል ኪዳን ቀሚሷን ተጐናጽፋ
የምትማልድልን ድንግል ናት የሁላችን ተስፉ
አዝ

በብርሀን ወንበር ላይ ተቀምጣለች
ጨረቃን ከእግሯ በታች ተጫምታለች
የቅድስናን ውበት ተሸልማ
የምታብረቀርቀው እርሷ ናት የልዑል ከተማ
አዝ

ከዕብራውያን ሴቶች ተለይታ
ከሔዋን ዘሮች ሁሉ ታየች ጐልታ
ሰባቱን መቅረዝ ልጇ ያበራል
ስጋዋን ተዋህዶ በፍቅር እኛኑ መስሏል

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሞገድ ሲመታኝ

ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉ ተችሎ ላንተ ጌታ /2/

በአንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅር ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው ባንተ ሞት
ይህው አቆምከኝ በህይወት/2/

አዝ

ደጅህ ስጠና ስማጸንህ
መቼ ጨከነ ጌታ ልብህ
እንደ ቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ጸጋህ በእጅህ ለበስኩ/2/
አዝ

ዘወትር እልል ብል ብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተ ፍቅር
ጌታ ብጠራው ስምህን
ለውጠኸው ነው ታሪኬን /2/
አዝ

አይኖቼ አያዩም ካንተ በቀር
የምትወደድ የምትፈቀር
ዘመድ ወገኔ ሆነኸኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል /2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፱ /19/


በዚች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ።

እኚህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው፤ ክርስቲያኖችም እንደሆኑ፤ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው፤ መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ።

መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሥርዓተ ቅዳሴ

ቅዳሴ ማለት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ፣ ለየ፣ ለእግዚአብሔር መርጦ ሰጠ ማለት ነው። ሥርዓት ማለት ደግሞ ሠርዐ፡ ሠራ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው። ትርጉሙ ሕግ: ደንብ አሠራር ማለት ነው። በአንድ ላይ አድርገን ስናነበው የምሥጋና ሥርዓት ማለት ነው የሚመሰገነው  ደግሞ እግዚአብሔር ነው።

ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡

ቅዳሴ፡-
• በሰማይ የሚገኘውን ሥርዓት በምድር መተግበር ነው።
• ቅዱስ ቁርባን የሚቀርብበት እግዚአብሔርን የምናመልክበት ሥርዓት ነው።
• በደስታ የምናከናውነው እግዚአብሔርን የምናመልክበት ጸሎት ነው።
• ቅዳሴ አባቶች ካህናት እና ምእመናን ያሳተፈ የምሥጋና ሥርዓት ነው። ስለዚህ ዘወትር ለቅዳሴና ለመንፈሳዊ ትምህርት ትኩረት ልትሰጡ ይገባል።

ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲቆናት በመቀደስ ምእመናን ደግሞ በማስቀደስ  ይሳተፋሉ ከሁሉ በላይ አምላካችን የሚገኝበት እመቤታችን ቅድስት ማርያም የምትገኝበት መላእክት የሚገኙበት ሁሉም ቅዱሳን እንደተሰጣቸው ክብር የሚገኙበት ጸሎት ነው ስለዚህ ስናስቀድስ ብዙ በረከት እናገኝበታለን።

በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ መሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?

አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ፤ በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ተሟልተው ይገኙበታል። እዚህንም 5ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡

1. የቁርባን መስዋዕት፡-
በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ጸሎት ነው። ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል።

2. የከንፈር መስዋዕት፡-
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡

3. የመብራት መስዋዕት፡-
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጧፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሠጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ይህውም ጌታችን ጨለማ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡

4. የዕጣን መስዋዕት፡-
የዕጣን ጸሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል። ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ ወደ ሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል።

በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያለውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡

5. የሰውነት መስዋዕትነት፡-
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል። በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡

ይህ የጸሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦
1. የዝግጅት ክፍል
2. የንባብና የትምህርት ክፍል
3. ፍሬ ቅዳሴ፦ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው። እነዚህም፡-
3.1. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
3.2. ቅዳሴ እግዚእ
3.3. ቅዳሴ ማርያም
3.4. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
3.5. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
3.6. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
3.7. ቅዳሴ ባስልዮስ
3.8. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
3.9. ጎርጎርዮስ ካልእ
3.10. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
3.11. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
3.12. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
3.13. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
3.14. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ

- የጌታችን በዓል ከሆነ (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጳጉሜ እሑድ ቀን ከዋለች ሰንበት (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፰ /18/


በዚህች ቀን የከበረ ቅዱስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው።

አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን? አለው ቅዱሱም የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን ክርስቶስ ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ።

በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው "እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ፤እውነት ነገርን ብታውቅ ለእግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ ይገባ እንደሆነ ወይም ለአማልክት እንዲነግረን ሕፃን ልጅ እንዲአመጡ እዘዝ" መኰንኑም ታናሽ ሕፃንን እንዲአመጡ አዘዘ መኰንኑም ሕፃኑን ስግደት ለማን እንዲገባ ዕውነቱን ንገረን አለው። ሕፃኑም በአንዲት ቃል ዓለሙን ሁሉ ለፈጠረ ለሕያው እግዚአብሔር ስግደትና አምልኮ እንዲገባ አታውቅምን አለው።  በዚያንም ጊዜ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ።

ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ፤ ወታደሩንም ጠርቶ ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው አለው ወታደሩም የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ አለው አምጥተውለትም አየ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኑ በእግዚአብሔር

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/
ለታላቁ ክብር ለዚህ ያበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ለአሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ይበለን/2/

አዝ

የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምሥጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
አዝ

ከዓለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልኝ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግን ከጧት እስከ ማታ
አዝ

በቃዴስ በረሃ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍጹም እምኑት
አዝ

በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
አዝ

የሐና የእያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
የእያቄም ስእለት የሐና እምነት
ለምኝልን ለእኛ ኪዳነ ምሕረት

ዘማሪት አዜብ ከበደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በርጠሚዮስ ነኝ

በርጠሚዬስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን
ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምፁ በግልፅ ይሰማኛል/2/

አዝ

የልቦናዬ አይን ፈፅሞ ታውሯል
አይኔን ፈውስልኝ በርጠሚዮስ ይላል
አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በውስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ/2/
አዝ

አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙዎች
በኅጥያት ሰንሰለት ታስረሃል አቅተዎች
ስለዚህ አትልፋ ሲኦልን ጠብቃት
እንደዚህ ቢሉኝም እጮሀለው ሳልታክት/2/
አዝ

የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ
ስለእኔ የሞተው ኢየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል/2/
አዝ

አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልፅ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በውስጤ በደልስ ህይወቴ ዝላለች
በአምላኬ ቸርነት ህይወት ካላገኘች/2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፮ /16/

በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ዘጠነኛ የሆነ፤ ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ያቃቱ አረፈ።

ከርሱ በፊት የነበረ አባ ብንያሚን በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም ብዙ ችግር ደርሶበታል ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል አንድ መለካዊ ሰው ነበረ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ወደ ዘይድ ሒዶ ብዙ እጅ መንሻ ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሁኖ ተሾመ ። ይህንንም አባት አባ ያቃቱን ያስጨንቀው ጀመረ በየዓመቱ ግብር ሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከእርሱ እስከተቀበለ ድረስ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ ይህን አባት እንዲህ አሠቃየው ።

በአንዲት ሌሊትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዚህ አባት ተገለጸለት ፍዩም በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ ሰው መነኰስ እንዳለ ነገረው ። ሕዝብን በማስተማርና በመምከርም ይረዳው ዘንድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲአስመጣውም አዘዘው ሁለተኛም ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ገለጠለት ።

በዚያንም ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሥራውንም ሁሉ አስረከበው ይህንንም አባት ከብዙ ድካም የሚያሳርፈው ሆነ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​አጋንንት

ርኩሳንና ረቂቅ መናፍስት የሚጠሩበት መጠሪያ ሲሆን በብዙ ቁጥር አጋንንት ሲባሉ ጋኔን የተናጠል ስያሜያቸው ነው:: የአለቃቸው መጠሪያ ሰይጣን ሲሆን እርሱን የሚከተሉ ሠራዊቱ አጋንንት ተብለው ይጠራሉ፡፡

አጋንንት እነማን ናቸው?

በዕለተ እሁድ እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ ሲፈጥራቸውም በብሩህ አእምሮ በረቂቅ ተፈጥሮ ፈጥሯቸው ነበርና በእምነት ይፈልጉኝ በአምልኮ ያቅርቡኝ በምስጋና ያክብሩኝ ተመራምረው ያግኙኝ እገለጽላቸዋለሁ ብሎ ተሰወረ፡፡ በዚህን ጊዜ ማን ፈጠረን? ከየት ተገኘን? የሚል ጥያቄ በመላእክት መካከል ተነስቶ ዓለመ መላእክት ተሸበረ፡፡

በመጀመሪያ ማዕረግ /በከፍታ ስፍራ/ ከዘጠና ዘጠኙ ነገድ በላይ የተቀመጠው ሳጥናኤል የተባለው አለቃ ከነሰራዊቱ ነበር ወደ እርሱ የሚደርሰውን ማን ፈጠረን? ከየት ተገኘን? የሚለውን ከታች ከዘጠና ዘጠኙ ነገድ የሚነሳውን ድምጽ በሰማ ጊዜ ከእርሱ በላይ በማዕረግ የተቀመጠ እንደሌለ አይቶ እኔ ፈጠርኋችሁ ልበላቸው ብሎ እሰበ አሰቦም አልቀረ እኔ ፈጠ ርኋችሁ አላቸው ኃጢአትን አደረገ ሐሰትንም ወለደ። /2ጴጥ2÷4/ ዮሐን 8፥44/ በዚህን ጊዜ የእርሱ ነገድ  ሰራዊቱ ከሦስት ተከፋፈሉ፡፡

1ኛው - ከሰራዊቱ አንዱ እጅ አዎ ፈጠርከን ብሎ ተቀበለ ወድቆ ሰገደ
2ኛው -ከሰራዊቱ አንዱ እጅ ፈጥሮን ይሆን ሲለ ተጠራጠረ
3ኛው -ከሰራዊቱ አንዱ እጅ ምን አንተ ትፈጥረናለህ ስለምንበዛ እኛ ብንፈጥርህ እንጂ አሉ።

ከዚህ በኋላ  እግዚአብሔር አምላክ ጨርሶ ሳያስክዳቸው ልገለጽላቸው አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የተባለውም አለቃ «ንቁም በበህላዊነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ» /የፈጠረንን እስክናውቅ ባለንበት እንጽና/ ብሎ በማወጅ የመላእክትን ዓለም አረጋጋ እግዚአብሔርም ከወደ ምስራቅ ብርሃን ገለፀላቸው /በብርሃን ጐርፍ ተገለፀላቸው/ ያን ጊዜ አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአበሔር እያሉ ጮኹ ከድምጽም የተነሳ መድረኩ ተንቀጠቀጠ የክብሩንም መቅደስ የጣኑ ጢስ ሞላው /ት.ኢሳ 6፥3/ የመላእክትም አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያመፀውን መልአክ ከነሰራዊቱ ሊዋጋ ለሰልፍ ወጣ በሰማይ ሰልፍ ሆነ / ራእ ዮሐ 12፥7/ የካዱትን መላእክት ተዋጋቸው ዲያብሎስም  ድልን ተነስቶ ከነሰራዊቱ ወደ ምድር ተጣለ /ራእ ዮሐ 12፥9/

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮት ግን አጋንንት በብዙ ልዩ ልዩ መጠሪያ የሚጠሩ የወደቀው መልአክና ሠራዊቶቹ መሆናቸውን ያረጋግጥልናል፡፡ /ራእ 12፥9፣ ሕዝ. 28፥14፣ ኢሳ. 14፥12/ መልአካዊ ክብራቸውንና ሥልጣናቸውን ተገፈው የወደቁት መላእክት ስለመሆናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ከምናገኛቸው ብዙ ማስረጃዎች በስፋት የሚገልጹት ሁለቱን

1.አጋንንት በኃጢአት ምክንያት የወደቁት መላአክት ስስመሆናቸው
«እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉት መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሀነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው. . .» /2ጴጥ. 2፥4/ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይመሰክራል :: /ሉቃ 10÷8  ማቴ 13:29/

2.አጋንንት በትዕቢት ምክንያት የወደቁት መሳአክት ስስመሆናቸው
«አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ አሕዛብን ያዋረድህ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቆረጥህ፡፡ አንተም በልብህ ወደ ሰማይ አርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፡፡ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ከደመ ናዎች ከፍታ በላይ አርጋለሁ:: በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ፡፡» /ኢሳ. 14፥12/ ይላል::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-የአጋንንታዊ በሽታዎች ምስጢራዊነት እና በጠበል መፈወስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፭ /15/


በዚህች ቀን ከኒቆምድያ አገር ቅዱስ ቢላሞን በሰማዕትነት አረፈ።

የዚህም ቅዱስ አባቱ ጣዖት አምላኪ ነው እናቱ ግን ክርስቲያን ናት ጥበብንም አስተማሩት ከዚህም በኋላ ስሙ አርማላስ ከሚባል ቄስ ጋር ተገናኘ። ዠ እርሱም ስለቀናች ሃይማኖት አስተምሮ አጠመቀው።

በትንሽ ጊዜም ከጸጋ ደርሶ ድውያንን ይፈውስ ገባ። ብዙ አህዛብንም እያስተማረ ከደዌአቸው እየፈወሰ ወደ ክርስትና መለሳቸው። አንድ ቀንም ዓይነ ስውር አብርተሃል በሚል ተከሶ ከንጉሱ ፊት ቀረበ።

ንጉሱም ስለ ሃይማኖቱ በጠየቀው ጊዜ እርሱም ክርስቲያን ነኝ ብሎ በፊቱ ታመነ ንጉሡም ብዙ ሽንገላን በመሸንገል አባበለው። ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት ባልሰማውም ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጥቶ  ካልሰማኸኝ እኔ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይሃለሁ አለው። ቅዱስ ቢላሞንም እኔ ከሥቃይህ የተነሣ ፈርቼ ሃይማኖቴን ለውጬ ፈጣሪዬን አልክድም አለው።

ከዚያችም ቀን ጀምሮ በብዙ አይነት ሥቃይ አሰቃየው። ከመገደሉ በፊትም ጌታችን ከሰማይ ወርዶ ወዳጄ ቢለው ወታደሮቹ ሰሙ። በዚህም ምክንያት አምነው በዚህች ቀን ቁጥራቸው መቶ ኀምሣ ስምንት ወታደሮች አብረውት ተሰይፈዋል::

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አለ ለእኔ የተሻለ ነገረ

አለ ለእኔ የተሻለ ነገር /2/
ዛሬን ባዝን ለጊዜው ብቸገር
አለ ለእኔ የተሻለ ነገር

በእጄ የጨበጥኩት በድንገት ቢበተን
ዙርያዬን ቢከበኝ ያላሰብኩት ሀዘን
እንባዬ በደስታ መቀየሩ አይቀርም
እተማመናለው በጌታዬ አላፍርም

አዝ

ሀብቴን ልጄን ባጣ እርሱ እንደወደደ
የእዮብ መከራ በእኔም ከወረደ
እራቁቴን መጣው እንዲሁ ሄዳለው
ከዚህ የላቀውን ከእርሱ እጠብቃለው
አዝ

መከራው ቢከብደኝ ከዙፋን ወርጄ
ከርስቴ ብሰደድ በአቤሰሎም ልጄ
ቀኑ እስከሚነጋ አልፈራም ጨለማ
ዳግም እለብሳለው የጽዮንን ግርማ
አዝ

አሳዳጄ ቢያይል ጉልበቱ ቢፀና
ተግዳሮቱ በዝቶ ወደ እኔ ቢያቀና
የከበረው ድንጋይ አለ በወንጭፌ
እቋቋመዋለው እርሱን ተደግፌ
አዝ

በናባው ተራራ ቢሆን መቃብሬ
ከነዓን ባልገባ ከህዝቡ ጋር አብሬ
አለኝ በሰማይ ቤት እጅግ የከበረች
በጆሮ ያልተሰማች በአይንም ያልታየች

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መልአከ ሰላምነ

መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ዑራኤል /2/
ሰዐል ወጸሊ በእንቲአነ አእርግ ጸሎተነ
ቅድመ መንበሩ ለመድኃኒዓለም /2/

ጸበልህ የሚፈውስ የዋህ መልዐክ/2/
የምህረት ዝናብህን ፍጥረት ሁሉ ያደነቀው
ጸጋህ ልብስ ሆኖን እዲያስጌጠን
በረድኤት በፍቅር እባክህን አትለየን
አዝ
መራኄ ብርሃን ዑራኤል ሆይ አትለየን /2/
በምልጃ ብርሃንህ በረድኤት ጥላ ስር ነን
ፈጣን ንስር ሆይ ለምሕረት ሰውን ለማዳን/2/ የማይዘገይ/2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስምሽን ጠርቼ

ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ
ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ
የምጽናናበት ስምሽ ነውና
ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና

ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር
ለዘመናትም ስረገጥ ስኖር
ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ
የዓለሙን መድን ወለድሽልኝ
ከአባቶቼ ርስት ከሀገር ወጥቼ
በአሕዛብ አገር ስኖር ተሸጬ
ደርሰሽ አጽናንተሽ አከበርሽኝ
ብቸኝነቴን አስረሳሽኝ

አዝ

ድንኳኑ ሞልቶ ሰዉ ታድሞ
አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ
ምን አቀርባለሁ ብዬ ስቸገር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር
ያሰብኩት ሐሳብ ደመና ሆኖ
ቢበተንብኝ እንደ ጉም ተኖ
ይሆናል ያልኩት ሳይሆን ቢቀርም
በእመ አምላክ እኔስ ተስፋ አልቆርጥም
አዝ

እናት አባቴ ባያስታውሱኝ
ይህች ዓለም ንቃ ገፍታ ብትተወኝ
አንቺ ካለሽኝ ምን እሆናለሁ
አውሎ ነፋሱን ባሕሩን አልፋለሁ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝ
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም
አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝና
አዝ

ክፉዎች ደርሰው ቢዝቱብኝ
አንቺን መውደዴን አያስተውኝ
በአሕዛብ መሐል ስምሽን ስጠራ
መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም
አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝና

ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳፩ /21/


በዚችም ቀን የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ።

ይህም የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር ስለ ክርስቶስም በኢየሩሳሌም መኖርና ማስተማር ትንቢት ተናገረ። ደግሞም ስለ መከራው በሐዋርያትና በሰባ ሁለቱ አርድእት በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ።

"ከዚህ በኋላ በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ።" ሁለተኛም እንዲህ አለ ያን ጊዜ ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል።

ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት እንዲህ አለ ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ የከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል። የትንቢቱንም ወራት አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሐሜት

ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?!

የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ደግሞ ሔዋን ነበረች፡፡ (ዘፍ 3፥1-5)

የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር አደረገ። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል?

ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡ በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር።

ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።

ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው "ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።"

ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ ይቻለን ነበር።

"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።

ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።

ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።

"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15


ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፳ /20/


ዳግመኛም በዚህች ቀን የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ የታላቅ ነቢይ የኤልሳዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

እርሱም አሜሁላ ከሚባል አገር ከይሳኮር ነገድ ነው ብዙ ትንቢትን ተናግሮአል ብዙ ተአምራትንም አድርጓል። የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን "ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት" ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት ።

ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ "እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት" አለ አላቸው።

ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ። የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል። በኋላም የትንቢቱን ወራት ፈጽሞ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ገብርኤል መልዐከ ራማ

ገብርኤል/2/ መልዐከ ራማ/2/
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እንስማ

ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰውን መሆን ለዓለሙ ሰበክ /2/

አዝ

ከውኃ እና ከእሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለው ሞትና መከራ /2/

አዝ

የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና/2/

አዝ

አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ
ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳተ ነህ ገብርኤል ነበልባል አስወጋጅ
የአምላክ መወለድ ለዓለም የምታውጅ /2/


ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክበብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ገብርኤል ኃያል

ገብርኤል ኃያል መልዐከ ሰላም
መልዐከ ብስራት የምታወጣ
የእግዚአብሔርን ህዝብ ከሚነድ እሳት
ፍቅርህ ተስሏል በልባችን
ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን

የፅናታቸው ዝናው ሲሰማ
ከዚያች ባቢሎን ከሞት ከተማ
ህፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው
ቁመህ ተገኘህ መሀከላቸው

አዝ

ውሀው ሲዘልል ቢያስደነግጥም
በጋኖቹም ውስጥ ቢነዋወጥም
ፀንተው ዘመሩ ልጅና እናቱ
አንተ ስትደርስ ከዚያ ከእሳቱ
አዝ

ቂርቆስም ፀና ሞትን ሳይፈራ
አንተ ስላለህ ከእነርሱ ጋራ
አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ
አምነው ድል ነሱት ያንን መከራ
አዝ

እኔም አምናለው አድነኝ ብዬ
ቆመህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ
ክፉውን ዘመን የማልፍበት
ፅናትን ስጠኝ ድል ልንሳበት

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ያዳነኝን አውቀዋለው

ያዳነኝን አውቀዋለው
የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው
ስጦታዬ ምስጋና ነው

ጨለማዬን አስወግዶ
ያበራልኝን አውቃለሁ
ሙሉ ሰው ነኝ ከእንግዲህስ
ስከተለው እኖራለሁ
የብርሃንን ልዩ ውበት
ፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁት
ፍቅሩ ማርኮኝ
በመቅደሱ ሰገድኩለት አመለኩት
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/

አዝ

አሳደረኝ በእቅፉ
መጠውለጌን አለምልሞ
በመስቀል ላይ ተሰቀለ
ዳንኩኝ እኔ እርሱ ታሞ
በማይዝለው ክንዶቹ ላይ
እኔን በክብር እያኖረ
እንዲመቸኝ ዝቅ ብሎ
በበረት ውስጥ እርሱ አደረ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/
አዝ

ቅኔ ባፈስ ምን ይደንቃል
ደሙን በመስቀል አፍስሶ
ስለ ልጁ መዳን ብሎ
ነፍሱን ሳይቀር ለኔ ክሶ
ፍቅሬ ይዞት ከጸባኦት
በትትና መቶ ወርዶ
ተቀደስኩኝ በነጩ በግ
ቀራንዮ ጌታ ታርዶ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/
አዝ

አክሊለ ሶክ አጠለቀ
ግርማ ክብሩን ሁሉ ትቶ
አሻገረኝ ወደ ክብሬ
በቅዱስ ደም እኔን ዋጅቶ
አጎንብሶ ቀና አረገኝ
ፊቴን በጽድቅ እያበራ
እኖራለሁ ለዘለአለም
ካከበረኝ ጌታ ጋራ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እሰይ ነጋ

እሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው
አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው /2/

በበደሌ ሳትፈርድ ትጠብቀኛለህ
ከእኔ በላይ ለእኔ ታስብልኛለህ
የማታንቀላፋው ትጉህ እረኛዬ
ብርሃኑን ያየሁት ባንተ ነው ጌታዬ

አዝ

ቀናቶቼን ሰጠሁ ላንተው አሳልፌ
በሰላም እተኛለሁ በክንድህ አርፌ
ተመስገን ማለትን በብርሃን ጨለማ
ታስተምረኛለህ በወፎቹ ዜማ
አዝ

ትናንትናን ታልፎ ስላየሁ አዲስ ቀን
ከእንቅልፌ ስነቃ እላለሁ ተመስገን
አንተ ባታነጋው የጨለመውን
አልኖርም ነበረ ዛሬ ባልኩት ቀን
አዝ

ሁሉም የሚሆነው እንደየ ስርዐቱ
በአንተ ብቻ እኮ ነው መጨለም መንጋቱ
ስለ አደረክልኝ ምኔን ልክፈልህ
ተመስገን ብቻ ነው ሥላሴ ዋጋህ
አዝ

በብርሃን ተተካ አስፈሪው ጨለማ
እንደኔማ ሳይሆን ምህረትህ ቀድማ
የእኔ ያልኳት ዛሬ ነግታ የምትመሸው
በጥበቤ አይደለም በበጎነትህ ነው

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፯ /17/


በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮስቆሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

ይህም አባት በዘመኑ ካሉ ትውልድ እርሱን የሚመስል ያልተገኘ በጠባዩ ቅን የዋህ በእውቀቱ አስተዋይ በበጎ ሥራው ፍጹም የሆነ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ስለ ምስጢረ ሥላሴ እና ስለ ምስጢረ ሥጋዌ አርቅቆ መልእክትን ጽፎ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጰሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ላካት። መልእክቱም ወደ ቅዱስ አባት ሳዊሮስ በደረሰች ጊዜ አነበባትና ፈጽሞ ደስ ተሰኘባት ለአንጾኪያም ሕዝብ አስተማረባት ሁሉም ደስ አለቸው።

ከዚህም በኋላ አባ ሳዊሮስ ለአባ ዲዮስቆሮስ የመልእክቱን መልስ እንዲህ ብሎ ጻፈ። ቤተ ክርስቲያንን እንድትጠብቅ ለዚች ለከበረች አገልግሎት የመረጠህ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። ዳግመኛም ሕዝቡ እንዲጸኑ ሁል ጊዜ ስለቀናች ሃይማኖት አስተምራቸው አለው።

የአባ ሳዊሮስም መልእክት ወደ አባ ዲዮስቆሮስ በደረሰች ጊዜ ደስ ተሰኘባት በሁሉ ቦታም እንዲአስተምሩባት አዘዘ። ይህም አባት ሁል ጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸዋል ኤጲስቆጶሳቱንና ካህናቱንም መንጋዎቻቸውን ስለ መጠበቅ ያዛቸዋል፤ መልካም አገልግሎቱንም አድርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አረፈ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኪዳነ ምህረት እናቴ

ኪዳነምህረት እናቴ ምስጢረኛዬ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ /2/

አዝ

አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ ባንቺ ታበሰ /2/
አዝ

ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልረሳሽም እናቴ /2/
አዝ

አልልም መቼ ነው ቀኑ
የእኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደሚፈፀም አምናለሁ
ሁሉን በጊዜው አያለው /2/
አዝ

የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂ /2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምስጢረኛዬ ነሽ

አውቀዋለሁ ደጅሽን የእረፍት ቦታዬን
ጽኑ ስላም ጸጥታ ማግኛዬን
የት እሄዳለሁ አልልም ሲከፋኝ
ኪዳነምሕረት አንቺ እያለሽልኝ/2/

አዝ

ከአጸደ መቅደስሽ ከስዕልሽ ስር
እረፍቴ በዚያ ነው በቅዱሱ ደብር
ከተራራው አናት ከደጅሽ መጥቼ
ሰምሮልኛል ስምሽን ጠርቼ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

የሮማን አበባ መዓዛሽ ተወዳጅ
በረከትን ልቅሰም ሳልለይ ካንቺ ደጅ
አስራትሽ አድርጊኝ ጠቅልይኝ እናቴ
ታብብልኝ ትፍካልኝ ሕይወቴ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

አጠገቤ ጎኔ በዙሪያዬ እንዳለሽ
እንደርሱ ነው ልቤ እማ የሚያወራሽ
አልቅሼ ሲቀለኝ ነግሬሽ የውስጤን
አትዘገይም ስትሠሪልኝ ቤቴን
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

የእንጦጦዋ እናቴ እምዬ የምልሽ
ኪዳንኪ ደጓ የልብን ሰሚ ነሽ
በሄድኩበት አለሽ ተከትለሽኛል
ስላለሽኝ ሰላም ይሰማኛል
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አዝላው ወረደች

አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ /2/
ስደተኛዋ የአምላክ እናት
ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት

አዝ

ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
አዝ

የክብርን ጌታ ተሸክማ
ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ
የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ
ሰው ተዘከራት ተቸግራ
አዝ

በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ አጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች
አዝ

ግና መላእክት በሰማያት
ሃሌ ሉያ አሉ በፍርሃት
ወልድን በአብ ቀኝ ከላይ አይተው
ደግሞም በምድር ከድንግል ክንድ
ከላይም ሳይጎድል ተመልክተው /2/
አዝ

ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
አዝ

የክብርን ጌታ ተሸክማ
ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ
የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ
ሰው ተዘከራት ተቸግራ
አዝ

በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሚጠብቀኝ አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም/2/

አዝ

ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ሌሊት ከእኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ
አዝ

መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ኃይል አያስፈራኝም
አዝ

ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
አዝ

የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ
አዝ

እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал