ነነዌን ሊያቃጥል
ነነዌን ሊያቃጥል የወረደው እሳት (፪)
ተመልሶ ዐረገ(፪) በሀዘን በጸሎት (፪)
ስለሆነ ከልብ የሀዘናቸው ምንጩ (፪)
ነበር እንደ ራሔል (፪)እንባን እየረጩ (፪)
ለነነዌ ሰዎች ደስታን ያበሰረ (፪)
ጋሻ እና ጦራቸው(፪)ጾም ጸሎት ነበረ (፪)
እንኳን የሰው ልጆች እንስሳት ሳይቀሩ(፪)
በዮናስ ስብከት (፪)ፆም ጸሎት ተማሩ(፪)
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡
በጾመ ነነዌ የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡
የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡
በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።
ኦሮሚያን የኦርቶዶክሳውያን እስርቤት ማድረጉ ቀጥሏል።
በአዲስ አበባ አጎራባች ዞኖች በይበልጠጥም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሰበታ መሥመር የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በአፈሳ መልክ መጋዙ ቀጥሏል። በጅማ እና ሻሸመኔ በምዕራብ አርሲ ወረዳዎች በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ የወረዳ ሊቃነ ካህናት አባቶች ቀሳውስት ዲያቆናት በጅምላ እየታሠሩ መሆኑ መረጃዎች እየደረሱን ነው።
ትላንት የታሰሩ ምእመናን ምግብና ውሃ እንዳያገኙ ተደርገዋል። የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እስካሁን ዝምታን መርጠዋል።
ምንጭ: EOTC TV
በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት በዳሰነችኛ ቋንቋ ቅዱስ ወንጌልን ሲማሩ ከነበሩ ወገኖች መካከል 1182 አዳዲስ አማንያን ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ብጹዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድንና እስካንዲናቪያን ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ በተገኙበት በኦሞ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት በማግኘት የቤተ ክርስቲያን አባላት ሆነዋል፡፡
Читать полностью…አብይ ሽማግሌ ልኳል
ዛሬ አሁን ከመሽ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ የሚመራ ሽማግሌዎች ከአራት ኪሎ ከጠቅላዩ ወደ ቤተክህነት መጥተው አባቶች እግር ወድቀው እባካችሁ እርቅና ሰላም ያስፈልጋል ስለዚህ አሁን ተነሱ ወደ ቤተመንግሥት መሄድ አለብን ብለው ሲማፀኖ አምሽተዋል
የእኛ አባቶች ደግሞ አሁን በአሁን የሚሆን ነገር የለም ዛሬ ይሄ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ብዙ ለምነን ተማፅኖ አቅርበናል ስለዚህ ዛሬ አይሆንም ቋሚ ሲኖዶስ ይምከርበት ሲኖዶሱ ይነጋገርበትና ያኔ መልስ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል!
በአሰበ ተፈሪ/ጭሮ/ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእመናን እየወረወሩና ተኩስ መጀመራቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጹ።
ምእመናን ከጠዋት ጀምረው ቤተ ክርስቲያኗን ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን የዞኑ የጸጥታ ኃይል "በሁለታችሁ አንገባም" በማለት ገለልተኛ ለመሆን ሞክሮ ውሏል።
ነገር ግን ከመሼ ከክልል የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የክልሉ ልዩ ኃይልን ጨምሮ ተኩስ በመክፈት አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእምናን እየወረወረ መሆኑን ምእምናን በስልክ ገልጸውልናል።
መረጃውን ያደረሱን ምእመናን አክለውም የጸጥታ ኃይሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከቦ እየተኮሰና እያወከበ ቢሆንም ምእመኑ ግን ከግቢ አልወጣም ብሏል።
መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡
ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤
2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ
4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በእልልታ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
አሰላ
የከተማው ህዝብ በሌለበት ከበቆጂ የሌላ እምነት ተከታዮችን በአይሱዚ በማምጣት መንበረ ጵጵስናውን ሰብረው ገብተዋል። ስድስት ፓትሮል መኪና ያጀባቸው የክልሉ ልዩ ኃይል ሲሆን ከገቡ በኋላ በተሿሚው የገዳሟን ምዷየ ምጽዋት በመሥበር ለአጃቢዎቹ የፀጥታ ሰዎች ሕገ ወጥ ተሿሚው ገንዘቡን አድለዋል። የከተማው ፖሊስ ሊቀ ጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ያሬድን አፍኖ ምሽት ከከተማው ማስወጣቱ ይታወቃል።
ምንጭ eotc tv
👉🏼 አስቸኳይ
ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በስናይፐር የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል።
የጸጥታ ኃይሉ ፎቅ ላይ በመሆን በቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ወዳሉት ምእመናን በስናይፐር እየተኮሰ ሲሆን በዚህም አንዲት ሴት ተገድላለች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናንና ምእመናት ቆስለዋል።
ከውጪ በኩልም ሕገ ወጡ ቡድን ብር በመክፈል ያደራጃቸው ቡድኖች ድንጋይ በመወርወር ላይ ናቸው በዚህም የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብረውታል።
"አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?" -ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን አስመልክቶ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤተ ክርስቲያን እና በክርስቲያኖችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የማሳደድ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል::
በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ እናስከብራለን በሚል በትግራይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው በማለት ገልጸዋል።
በሻሸመኔ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው ግፍ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት ከሚደረግ የዘር ጭፍጨፋ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።
አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?
በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት ደረሰ!
በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት የደረሰ ሲሆን በአራቱ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።
አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ በቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የጸጥታ ኃይል አባላት በዱላ እያባረሩ ይገኛሉ።
የከተማዋ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አካላት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ውጪ ላሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ነጠላ በማደል ሻሸመኔ ስታዲዮም ተገኝተው ሕገ ወጡን ቡድን እንዲቀበሉ እያስተባበሩ ያሉ ሲሆን በመኪና ከተማውን እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
በዚህ ሰዓት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ ድረስ ያለውን ቦታ ተቆጣጥሯል።
ምንጭ: ተሚማ
✝ሰበር ዜና✝
ዛሬ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት የፌደራል አካላት በመምጣት ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ምዕመናን ላይ ጭፍጨፋ እያደረጉ ይገኛሉ በእዚህ ሰዓት
አንድ ኦርቶዶክስ በዚህ ሰዓት ሞቷል።
✝ሁላችንም ኦርቶዶክሳዊያን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ነቅተን የአባቶችን አዋጅጨመጠበቅ ይኖርብናል በየትኛው ሰዓት ኢንተርኔት ሊዘጋ ስለሚችል ቤተክርስቲያን ጥሪ ስታደርግ ሁላችንም በአንድነት መነሳት አለብን✝
እግዚአብሔር የደረሰብንን ሁሉ ይመልከት
https://youtube.com/shorts/MFwTyvXFCs8?feature=share
🤲ቅዳሴ ተምረው ከምዕመናን ጋር እኩል ቅዳሴ ተሰጥኦውን መመለስ ይፈልጋሉ?🤲
👉ስለ ቅዳሴ በቂ እውቀት የምታገኙበትን ፕሮግራም ይዘን ወደ እናንተ መጥተናል።
👉በየቀኑ የ2 ደቂቃ የቅዳሴ ክፍል እየተለማመድን ከ1-2ወር ውስጥ የቅዳሴ ተሰጥኦውን ተምረን እንጨርስ።
✝በዚህ ሊንክ ወደ ዩቲዩብ ቻናላችን በመግባት Susbcribe ያድርጉ ቅዳሴም እንማር✝
ጾመ ሰብአ ነነዌ
በርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል
ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡
ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት 7 ቀን ትጀመራለች፡፡
‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡
ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡
ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡
እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡
እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡
እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡
ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡
እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡
የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡
ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡
ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡
ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አስቸኳይ መረጃ፡፡
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ/አሰበ ተፈሪ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾሙት አካላት በጥር 27/2015 ዓ/ም እንደሚመጡ በቂ መረጃ ለሕቡ ሰለደረሰ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን ከሕገ ወጦች ወረራ በንቃት እንዲጠብቁ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት በከተማው የሚገኙትን 4 አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እየጠበቀ መዋሉ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል፡፡
ከቀኑ 11፡45 ስዓት ላይ የመጡት ሕገወጥ ቡድን ለመንግሥት አካል እንደማይመለሱ ሲነግሩት ሙሉ ወጪ ችሎ እንዲያድሩ አድርጓል። በዚህ መሀል 10 የማይሞሉ ዱላ ይዘው እየዘፈኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ እነሱን ትቶ ቤተክርስቲያ እየጠበቁ ባሉት ላይ ተኩስ ተከፈተ።
በተኩስና አስለቃሽ ጭስ እስከ 2ስዓት ምዕመናን ሲያዋክብም አምሽቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ ከበው ህዝቡን በተኩስ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ በዱላ እያሰቃዩ ሙሉ ህዝቡን እንዳስወጡና የሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ አንዳንድ የመምሪያ ሓላፊዎች ሞታችን በልደታ ብለው ግቢ ውስጥ ቀርተዋል፡፡
እስከምሽቱ 4ስዓት ላይም ቤተክርስቲያን ማን እንደሚገባ መመሪያ ከመንግስት እንጠብቃለን ብለው ከቆዩ በኋላ እና 5 ሰዓት ላይ ከሆቴል ጠርተው ሕገወጡን ቡድን አስገብተዋል፡፡ የጸጥታ እና የመንግስት አካላት ዛሬ እሑድ 4ስዓት ተደራደሩ ወይም ለሕገ ወጡ ቡድን ንብረት አስረክቡ ብለው አባቶችን እያስገደዱ ይገኛሉ።
አባቶች ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የምንመራ እንጂ በግል ምንወስነው አይደለም ብለዋል።
የጸጥታ ኃይሎች ተደራድረው ገብተዋል ለማለት ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ የመምሪያ ኃላፊዎችን አስገድደው ፎቶ ለማንሳት ሲሞክሩ እንደነበረ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መረጃውን ያደረሱን ገልጸዋል።
"የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
የሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ እንዲሁም የምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ምሽት የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሻሸመኔ አብያተክርስቲያናትን በመሥበር ምእመናንን በግፍ በማሠርና በመደብደብ ከየአካባቢው ባመጧቸው ቡድኖች አብያተክርስቲያናት ተቆጣጥረዋል ሲሉ ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በስልክ ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ "የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?" ያሉ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሰጡትን መግለጫ ምእመናን እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
በ13 ወረዳዎች ሊቃነ ካህናት በግፍ መታሠራቸውን ገልጸዋል።
የብፁዕነታቸውን መልእክት በዩቲዩብ ገጻችን ይከታተሉ።
ምንጭ: EOTC TV
ሰበር ዜና
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡
#መከራው_ክርስትናዬን_አጣፈጠው ✞
መከራው ክርስትናዬን አጣፈጠው
ስደቱ ማህተቤን አጠበቀው
በሞት መንደር በሀዘን ውስጥ በመከራ
አየውት እግዚአብሔርን ከኔ ጋራ
ክርስትያን ተብለን በክርስቶስ ስም የተጠራነው
በጥልቁ ውስጥም በእግዚአብሔር እንድናምን ነው
ለጥቂት ግዜ ቢበረታብን ስደት ሀዘኑ
አምላክ ግን መውጫ ያዘጋጃል በዚህ ተፅናኑ
#አዝ
በስደት ሳለን ካፋችን ቢደርቅ የፅዮን ዜማ
ከወንዙ አጠገብ ቁጭ ብለን ሰለን ድምፁን ሳንሰማ
በእግዚአብሔር ጊዜ ከባቢሎን ምድር እንለቃለን
መሰንቆአችንን ከአርያም ዛፍ ላይ እናወርዳለን
#አዝ
ደካሞች ሲሉን በስሙ ያን ጊዜ እንበረታለን
ድሆች ስንባል ባለጠጎች እናደርጋለን
በምድር ቅዱስ ህዝብ አድርጎ ለእርሱ ለየን
ጨለማው አልፎ በቸርነቱ ብርሀን አሳየን
#አዝ
ከፀጋ በላይ እንዳንፈተን ይከልለናል
በቁስላችን ላይ የፈውስን ዘይት ያፈስልናል
በጊዜም ቢሆን ያለ ጊዜውም በእርሱ እንፅና
እንኳን ስደቱን ሞቱን ሊገታው ይችላልና
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በሻሸመኔ እና በመላው ምዕራብ አርሲ የምትገኙ ጠንካራ ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በሙሉ ይህንን ከዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ያልተናነሰ ዘመን በጠንካራ መሠረት ላይ በታነፀው የሃይማኖታችሁ ጥንካሬ በጸሎት ፣ በጾም እና በፍፁም ክርስቲያናዊ ጥንካሬ ራሳችሁን ፣ ቤተ ክርስቲያናችሁን እና ሀገራችሁን እንድጠብቁ ሲሉም ጠይቀዋል።
በመሆኑም ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል በማስተዋል የፌደራል መንግስትና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወገንተኝነታቸውን በማቆም እግዚአብሔር ፍርድ ከመስጠቱ በፊት ንስሐ በመግባት በግፍ የሚፈሰውን የንፁሐን ኦርቶዶክሳውያንን ደም እንዲያስቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ውይይት ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንዲመለስ በከተማው የመጣ እንግዳ የለም የሚል ከፖሊሶቹ ሃሳብ የቀረበ ቢሆንም ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች ሕገ ወጦቹ ግለሰቦች በአንድ ሆቴል ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከቅዱስ ሲኖዶስና ከአባቶቻችን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ግቢያችን ውስጥ ሆነን እየዘመርን እና ወንጌል እየተማርን ቤተ ክርስቲያናችን እንጠብቃለን፡፡
ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት የመጡት ሕገ ወጥ ግለሰቦች ወደ መጡበት ቦታ ካልተመለሱ ሕዝቡን ማሰናበት አንችልም፣ ሕዝቡም እሺ አይለንም በሚል ለመንግሥት የጸጥታ አካላት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
ከመንግሥት የመጡ አካላትም ሕዝቡ ከስሜተኝነት እንዲወጣ የሃይማኖት አባቶች እንዲያረጋጉት መመሪያ ሰጥተው መመለሳቸውን ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በንቃት ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቀ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ የማረጋጊያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው።
በሻሸመኔ አንድ ወጣት ኦርቶዶክሳዊ ከመንግሥት አካላት በተተኮሰ ጥይት ሰማዕትነትን ተቀብሏል።
ተሿሚዎቹ በእነዚህ ንፁሀን ሰማዕታት ደም ላይ ተረማምደው ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር መነሳታቸውን ስናስብ ሃይማኖት አልባነታቸውን እንረዳለን። ሰማዕትነታችሁ የከበረ ነው።
ምንጭ፡- ኢኦተቤ ቴቪ
"ምዕመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት በምእመናን ላይ ስጋት መፍጠሩን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማምሻውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አሳወቁ።
ከሰሞኑን የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ለሚመለከተው የዞን ፀጥታ አካል ለማሳወቅና ጥበቃ እንዲያደርጉ ብንደውልም፣ መልእክት ብንጽፍም ሊመልሱልን አልቻሉም ብለዋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኦሮምያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ጥበቃና ከለላን በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስቀድሞ ደብዳቤ ቢጻፍም ምንም አይነት የቃልም ሆነ የተግባር መልስ እንዳልተሰጣቸውም ተናግረዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም መንግሥት በሕገ ወጡ ቡድን የሚደረገውን ድርጊት ማስቆም ካልቻለ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል ብለዋል።
በመጨረሻም ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ምንጭ:- የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኅን አግልግሎት ሥርጭት ድርጅት
"ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን"- ቅዱስ ሲኖዶስ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ!
ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል።
በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ
"ራሱን ሲኖዶስ ብሎ የሰየመው ቡድን ደጋፊዎች ዓላማቸው አባቶችን ማስፈራራትና ሐሰተኛ አሉባልታዎችን መንዛት መሆኑን ታዝበናል" የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጴጥሮሳዊያን ሕብረት
የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብር እና መብት አስጠባቂ ኅብረት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫውም ራሱን ሲኖዶስ ብሎ የሰየመዉ ቡድን ደጋፊዎች ዓላማቸዉ አባቶችን ማስፈራራትና ሐሰተኛ አሉባልታዎችን መንዛት መሆኑን ታዝበናል ሲል አስነብቧል::