አለ ለእኔ የተሻለ ነገረ
አለ ለእኔ የተሻለ ነገር /2/
ዛሬን ባዝን ለጊዜው ብቸገር
አለ ለእኔ የተሻለ ነገር
በእጄ የጨበጥኩት በድንገት ቢበተን
ዙርያዬን ቢከበኝ ያላሰብኩት ሀዘን
እንባዬ በደስታ መቀየሩ አይቀርም
እተማመናለው በጌታዬ አላፍርም
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
መልአከ ሰላምነ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ዑራኤል /2/
ሰዐል ወጸሊ በእንቲአነ አእርግ ጸሎተነ
ቅድመ መንበሩ ለመድኃኒዓለም /2/
ጸበልህ የሚፈውስ የዋህ መልዐክ/2/
የምህረት ዝናብህን ፍጥረት ሁሉ ያደነቀው
ጸጋህ ልብስ ሆኖን እዲያስጌጠን
በረድኤት በፍቅር እባክህን አትለየን
አዝ
መራኄ ብርሃን ዑራኤል ሆይ አትለየን /2/
በምልጃ ብርሃንህ በረድኤት ጥላ ስር ነን
ፈጣን ንስር ሆይ ለምሕረት ሰውን ለማዳን/2/ የማይዘገይ/2/
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ስምሽን ጠርቼ
ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ
ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ
የምጽናናበት ስምሽ ነውና
ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና
ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር
ለዘመናትም ስረገጥ ስኖር
ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ
የዓለሙን መድን ወለድሽልኝ
ከአባቶቼ ርስት ከሀገር ወጥቼ
በአሕዛብ አገር ስኖር ተሸጬ
ደርሰሽ አጽናንተሽ አከበርሽኝ
ብቸኝነቴን አስረሳሽኝ
አዝ
አዝ
አዝ
ጥቅምት ፳፩ /21/
ሐሜት
ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?!
የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ደግሞ ሔዋን ነበረች፡፡ (ዘፍ 3፥1-5)
የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር አደረገ። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል?
ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡ በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር።
ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።
ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው "ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።"
ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ ይቻለን ነበር።
"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።
ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።
ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።
"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15
ጥቅምት ፳ /20/
ገብርኤል መልዐከ ራማ
ገብርኤል/2/ መልዐከ ራማ/2/
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እንስማ
ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰውን መሆን ለዓለሙ ሰበክ /2/
አዝ
አዝ
አዝ
ገብርኤል ኃያል
ገብርኤል ኃያል መልዐከ ሰላም
መልዐከ ብስራት የምታወጣ
የእግዚአብሔርን ህዝብ ከሚነድ እሳት
ፍቅርህ ተስሏል በልባችን
ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን
የፅናታቸው ዝናው ሲሰማ
ከዚያች ባቢሎን ከሞት ከተማ
ህፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው
ቁመህ ተገኘህ መሀከላቸው
አዝ
አዝ
አዝ
ያዳነኝን አውቀዋለው
ያዳነኝን አውቀዋለው
የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው
ስጦታዬ ምስጋና ነው
ጨለማዬን አስወግዶ
ያበራልኝን አውቃለሁ
ሙሉ ሰው ነኝ ከእንግዲህስ
ስከተለው እኖራለሁ
የብርሃንን ልዩ ውበት
ፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁት
ፍቅሩ ማርኮኝ
በመቅደሱ ሰገድኩለት አመለኩት
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/
አዝ
አዝ
አዝ
እሰይ ነጋ
እሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው
አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው /2/
በበደሌ ሳትፈርድ ትጠብቀኛለህ
ከእኔ በላይ ለእኔ ታስብልኛለህ
የማታንቀላፋው ትጉህ እረኛዬ
ብርሃኑን ያየሁት ባንተ ነው ጌታዬ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ጥቅምት ፲፯ /17/
ኪዳነ ምህረት እናቴ
ኪዳነምህረት እናቴ ምስጢረኛዬ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ /2/
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ምስጢረኛዬ ነሽ
አውቀዋለሁ ደጅሽን የእረፍት ቦታዬን
ጽኑ ስላም ጸጥታ ማግኛዬን
የት እሄዳለሁ አልልም ሲከፋኝ
ኪዳነምሕረት አንቺ እያለሽልኝ/2/
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝላው ወረደች
አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ /2/
ስደተኛዋ የአምላክ እናት
ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
የሚጠብቀኝ አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም/2/
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ጥቅምት፳፪ /22/
ጥቅምት 21 ቀን እመቤታችን ሐዋርያው ማትያስን ከእስር ያስፈታችበት ቀን ነው!
በዛሬው እለት ማለትም ጥቅምት 21 ቀን እመቤታችን ለሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ አስገራሚ ተአምር አድርጋለታለች፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ቅዱስ ወንጌል እንዲያስተምሩ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ሰዎችን ወደሚበሉ ሀገር ዕጣ ደረሰው፡፡ ቅዱስ ማትያስም ወንጌልን እሰብካለሁ ብሎ ሀገራቸው ገባ፡፡
በዚያች ሀገር የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ አንድ ሰይጣናዊ ልማድ ነበራቸው። ይኸውም አንድ ሰው ሀገራቸው ከመጣ ይዘውት ሁለቱንም ዓይኑን በማውጣት ለ30 ቀን እንደ ከብት ሣር እያበሉት በእስር ቤት ያቆዩታል፡፡ በ 30ኛው ቀንም ከእስር ቤት አውጥተው አርደው ይበሉታል። ታዲያ እነዚህ ሰው በላ ሰዎች ቅዱስ ማትያስንም ይዘው ሁለቱን ዓይኖቹን አወጡ በእስር ቤትም አስቀመጡት፡፡
ቅዱስ ማትያስም በእስር ቤት በጭንቅ ሆኖ ወደ እመቤታችን መማጸን ጀመረ፡፡ እመቤታችንም ቅዱስ ማትያስ የሚበላበት ሠላሳኛው ቀን ሳይደርስ በጸሎቷ ኃይል ከእስር ቤት አስወጣችው በተአምራትም ከሰው በላ ሰዎች አስመለጠችው፡፡
እመቤታችን በመዓዛ መለኮት በጣፈጠ ጥዑም አንደበቷ ከችግራችን፣ ከሕመማችን፣ ከእሥራታችን ትፍታን፡፡
ቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
የዝማሬ ዳዊት ትክክለኛው የቲክቶክ ገጽ ይህ ነው።
በቅርቡ አዳዲስ ስራዎች ይዘን ስለምንቀርብ ቲክቶክ የምትጠቀሙ ቤተሰቦቻችን Follow እና ሼር በማድረግ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ያስፉ።
https://vm.tiktok.com/ZMhQPn89c/
https://vm.tiktok.com/ZMhQ5DW1f/
ማርያም ማርያም ብዬ
ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወልደኝ/2/
ገና በማህጸን በእናቴ የምጥ ቀን
ደጋግሜ ሰማሁ ሲጠሩ ስምሽን
በሰከንዳት እድሜ የማውቃት አንዲት ቃል
ልቤ ላይ ያለው ስም ማርያም ማርያም ይላል/2/
ማርያም ማርያም
አዝ
አዝ
አዝ
ከሰማዩ ከፍታ
ከሰማዩ ከፍታ ከፍ ብላ ጽዮን
በሰገነት ላይ ተቀምጣ
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ /2/
አይን ከሞላባቸው ከኪሩቤል
ክንፋቸው ከበዛ ከሱራፌል
ከሊቃናቱ ሁሉ ትበልጣለች
እሳተ መለኮትን በሆዱዋ ስለተሸከመች
አዝ
አዝ
አዝ
ሞገድ ሲመታኝ
ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉ ተችሎ ላንተ ጌታ /2/
በአንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅር ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው ባንተ ሞት
ይህው አቆምከኝ በህይወት/2/
አዝ
አዝ
አዝ
ጥቅምት ፲፱ /19/
ሥርዓተ ቅዳሴ
ቅዳሴ ማለት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ፣ ለየ፣ ለእግዚአብሔር መርጦ ሰጠ ማለት ነው። ሥርዓት ማለት ደግሞ ሠርዐ፡ ሠራ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው። ትርጉሙ ሕግ: ደንብ አሠራር ማለት ነው። በአንድ ላይ አድርገን ስናነበው የምሥጋና ሥርዓት ማለት ነው የሚመሰገነው ደግሞ እግዚአብሔር ነው።
ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡
ቅዳሴ፡-
• በሰማይ የሚገኘውን ሥርዓት በምድር መተግበር ነው።
• ቅዱስ ቁርባን የሚቀርብበት እግዚአብሔርን የምናመልክበት ሥርዓት ነው።
• በደስታ የምናከናውነው እግዚአብሔርን የምናመልክበት ጸሎት ነው።
• ቅዳሴ አባቶች ካህናት እና ምእመናን ያሳተፈ የምሥጋና ሥርዓት ነው። ስለዚህ ዘወትር ለቅዳሴና ለመንፈሳዊ ትምህርት ትኩረት ልትሰጡ ይገባል።
ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲቆናት በመቀደስ ምእመናን ደግሞ በማስቀደስ ይሳተፋሉ ከሁሉ በላይ አምላካችን የሚገኝበት እመቤታችን ቅድስት ማርያም የምትገኝበት መላእክት የሚገኙበት ሁሉም ቅዱሳን እንደተሰጣቸው ክብር የሚገኙበት ጸሎት ነው ስለዚህ ስናስቀድስ ብዙ በረከት እናገኝበታለን።
በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ መሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ፤ በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ተሟልተው ይገኙበታል። እዚህንም 5ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡
1. የቁርባን መስዋዕት፡-
በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ጸሎት ነው። ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል።
2. የከንፈር መስዋዕት፡-
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡
3. የመብራት መስዋዕት፡-
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጧፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሠጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ይህውም ጌታችን ጨለማ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡
4. የዕጣን መስዋዕት፡-
የዕጣን ጸሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል። ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ ወደ ሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል።
በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያለውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡
5. የሰውነት መስዋዕትነት፡-
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል። በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡
ይህ የጸሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦
1. የዝግጅት ክፍል
2. የንባብና የትምህርት ክፍል
3. ፍሬ ቅዳሴ፦ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው። እነዚህም፡-
3.1. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
3.2. ቅዳሴ እግዚእ
3.3. ቅዳሴ ማርያም
3.4. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
3.5. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
3.6. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
3.7. ቅዳሴ ባስልዮስ
3.8. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
3.9. ጎርጎርዮስ ካልእ
3.10. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
3.11. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
3.12. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
3.13. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
3.14. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
- የጌታችን በዓል ከሆነ (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጳጉሜ እሑድ ቀን ከዋለች ሰንበት (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጥቅምት ፲፰ /18/
ኑ በእግዚአብሔር
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/
ለታላቁ ክብር ለዚህ ያበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ለአሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ይበለን/2/
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
በርጠሚዮስ ነኝ
በርጠሚዬስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን
ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምፁ በግልፅ ይሰማኛል/2/
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ጥቅምት ፲፮ /16/
በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ዘጠነኛ የሆነ፤ ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ያቃቱ አረፈ።
ከርሱ በፊት የነበረ አባ ብንያሚን በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም ብዙ ችግር ደርሶበታል ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል አንድ መለካዊ ሰው ነበረ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ወደ ዘይድ ሒዶ ብዙ እጅ መንሻ ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሁኖ ተሾመ ። ይህንንም አባት አባ ያቃቱን ያስጨንቀው ጀመረ በየዓመቱ ግብር ሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከእርሱ እስከተቀበለ ድረስ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ ይህን አባት እንዲህ አሠቃየው ።
በአንዲት ሌሊትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዚህ አባት ተገለጸለት ፍዩም በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ ሰው መነኰስ እንዳለ ነገረው ። ሕዝብን በማስተማርና በመምከርም ይረዳው ዘንድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲአስመጣውም አዘዘው ሁለተኛም ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ገለጠለት ።
በዚያንም ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሥራውንም ሁሉ አስረከበው ይህንንም አባት ከብዙ ድካም የሚያሳርፈው ሆነ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አጋንንት
ርኩሳንና ረቂቅ መናፍስት የሚጠሩበት መጠሪያ ሲሆን በብዙ ቁጥር አጋንንት ሲባሉ ጋኔን የተናጠል ስያሜያቸው ነው:: የአለቃቸው መጠሪያ ሰይጣን ሲሆን እርሱን የሚከተሉ ሠራዊቱ አጋንንት ተብለው ይጠራሉ፡፡
አጋንንት እነማን ናቸው?
በዕለተ እሁድ እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ ሲፈጥራቸውም በብሩህ አእምሮ በረቂቅ ተፈጥሮ ፈጥሯቸው ነበርና በእምነት ይፈልጉኝ በአምልኮ ያቅርቡኝ በምስጋና ያክብሩኝ ተመራምረው ያግኙኝ እገለጽላቸዋለሁ ብሎ ተሰወረ፡፡ በዚህን ጊዜ ማን ፈጠረን? ከየት ተገኘን? የሚል ጥያቄ በመላእክት መካከል ተነስቶ ዓለመ መላእክት ተሸበረ፡፡
በመጀመሪያ ማዕረግ /በከፍታ ስፍራ/ ከዘጠና ዘጠኙ ነገድ በላይ የተቀመጠው ሳጥናኤል የተባለው አለቃ ከነሰራዊቱ ነበር ወደ እርሱ የሚደርሰውን ማን ፈጠረን? ከየት ተገኘን? የሚለውን ከታች ከዘጠና ዘጠኙ ነገድ የሚነሳውን ድምጽ በሰማ ጊዜ ከእርሱ በላይ በማዕረግ የተቀመጠ እንደሌለ አይቶ እኔ ፈጠርኋችሁ ልበላቸው ብሎ እሰበ አሰቦም አልቀረ እኔ ፈጠ ርኋችሁ አላቸው ኃጢአትን አደረገ ሐሰትንም ወለደ። /2ጴጥ2÷4/ ዮሐን 8፥44/ በዚህን ጊዜ የእርሱ ነገድ ሰራዊቱ ከሦስት ተከፋፈሉ፡፡
1ኛው - ከሰራዊቱ አንዱ እጅ አዎ ፈጠርከን ብሎ ተቀበለ ወድቆ ሰገደ
2ኛው -ከሰራዊቱ አንዱ እጅ ፈጥሮን ይሆን ሲለ ተጠራጠረ
3ኛው -ከሰራዊቱ አንዱ እጅ ምን አንተ ትፈጥረናለህ ስለምንበዛ እኛ ብንፈጥርህ እንጂ አሉ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ጨርሶ ሳያስክዳቸው ልገለጽላቸው አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የተባለውም አለቃ «ንቁም በበህላዊነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ» /የፈጠረንን እስክናውቅ ባለንበት እንጽና/ ብሎ በማወጅ የመላእክትን ዓለም አረጋጋ እግዚአብሔርም ከወደ ምስራቅ ብርሃን ገለፀላቸው /በብርሃን ጐርፍ ተገለፀላቸው/ ያን ጊዜ አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአበሔር እያሉ ጮኹ ከድምጽም የተነሳ መድረኩ ተንቀጠቀጠ የክብሩንም መቅደስ የጣኑ ጢስ ሞላው /ት.ኢሳ 6፥3/ የመላእክትም አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያመፀውን መልአክ ከነሰራዊቱ ሊዋጋ ለሰልፍ ወጣ በሰማይ ሰልፍ ሆነ / ራእ ዮሐ 12፥7/ የካዱትን መላእክት ተዋጋቸው ዲያብሎስም ድልን ተነስቶ ከነሰራዊቱ ወደ ምድር ተጣለ /ራእ ዮሐ 12፥9/
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮት ግን አጋንንት በብዙ ልዩ ልዩ መጠሪያ የሚጠሩ የወደቀው መልአክና ሠራዊቶቹ መሆናቸውን ያረጋግጥልናል፡፡ /ራእ 12፥9፣ ሕዝ. 28፥14፣ ኢሳ. 14፥12/ መልአካዊ ክብራቸውንና ሥልጣናቸውን ተገፈው የወደቁት መላእክት ስለመሆናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ከምናገኛቸው ብዙ ማስረጃዎች በስፋት የሚገልጹት ሁለቱን
1.አጋንንት በኃጢአት ምክንያት የወደቁት መላአክት ስስመሆናቸው
«እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉት መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሀነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው. . .» /2ጴጥ. 2፥4/ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይመሰክራል :: /ሉቃ 10÷8 ማቴ 13:29/
2.አጋንንት በትዕቢት ምክንያት የወደቁት መሳአክት ስስመሆናቸው
«አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ አሕዛብን ያዋረድህ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቆረጥህ፡፡ አንተም በልብህ ወደ ሰማይ አርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፡፡ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ከደመ ናዎች ከፍታ በላይ አርጋለሁ:: በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ፡፡» /ኢሳ. 14፥12/ ይላል::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-የአጋንንታዊ በሽታዎች ምስጢራዊነት እና በጠበል መፈወስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጥቅምት ፲፭ /15/
ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ለተራራው ፍቅር አደረባቸው፤ አለቀሱም፡፡ በዚህም ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ዳግመኛ መጥቶ ‹‹አረጋዊ ሆይ አይዞህ! አትፍራ ስልጣን ተሰጥቶሃልና፡፡ በሐረጓ በስተቀኝ በኩል ባለችው ቦታ ተቀመጥ፤ ወደ ተራራው ጫፍ ያወጣህ ዘንድ በገመድ ፋንታ ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ታላቅ ዘንዶ እግዚአብሔር ይልክልሃል›› አለው፡፡ ከዚያም በጾም በጸሎት ሁለት ሱባኤ ይዘው ፲፬ ቀን በዚያ ተቀመጡ፡፡ የታዘዘውም ዘንዶ በሦስት ሰዓት መጣ፤ በዘንዶው ጅራት ላይ ወጥቶ በቅጽበት ከተቀደሰው ተራራ ጫፍ ላይ ደረሰ፤ እንደደረሰም ሦስት ጊዜ ሰገደ። ወዲያው ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ›› እያለ አመሰገነ፡፡
ስለዚህም ቦታው ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሎ ተሠየመ፡፡ በመሸም ጊዜ አነስተኛ ዳቦ አንስቶ ባርኮ መብላት ጀመረ፡፡ ዳቦዋ ግማሽ ስትሆን ስለጠገበ የዳቦውን ግማሽ አምሳል ለኋለኛው ትውልድ ምልክት ትሆን ዘንድ እንጨት ጠርቦ/ቀርጾ/ አስቀመጠ፤ ይህች ምልክት እስከዛሬ ድረስ አለች፡፡
ደቀ መዛሙርቱም ከታች ወደ ላይ የሚወጡበትን መሰላል በሠሩ አባታችን አቡነ አረጋዊ ደግሞ መጠነኛ ቤት ሠራና ይዞት የመጣውን ታቦት በውስጡ አስገባ፡፡ እግዚአብሔርንም ስለቁርባኑ ወይም ስለመሥዋዕቱ ለመኑ፡፡ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ መላእክት ከሰማይ ይዘውላቸው ወረዱ፡፡ ለመኖሪያቸውም ትንሽ በአት አገኙ፡፡ ያለምንም መኝታ በጸሎትና በስግደት በመትጋት ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ተአምራትን አደረጉ፤ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሠቃዩትን በጸሎታቸው ኃይል ፈወሷቸው፤ ያላመኑትን ደግሞ እያስተማሩ አሳመኗቸው፤ ለዚያችም ሀገር ብርሃን አበሩላት።
አፄ ካሌብም ‹‹አባቴ ሆይ! በጸሎትህ አስበኝ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለች፤ ኃይልም ታሰጣለች፤ በጠላት ላይም ድልን ታቀዳጃለች›› ብሎ አቡነ አረጋዊን ለመኗቸው፤ ወደ ደቡብ በሄደም ጊዜ የመን ከሠራዊቱ ጋር ዘምተው አሸንፈው ተመለሱ። የአፄ ካሌብ ልጅ ገብረ መስቀል ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው። በውስጡም በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም የተሰየመች በወርቅና በብር ያጌጠች ታቦት አስገባ፡፡ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ከተራራው ላይ ሲወርድ ለቤተክርስቲያኑ ማሠሪያ የሆነውን መወጣጫ መሰላል ‹ላፍርሰው› ብሎ አባታችንን ጠየቀ፤ አባታችንም ‹‹አዎ! አፍርሰው፤ አትትወው፤ ነገር ግን ስለዘንዶው ጅራት ፈንታ ሰዎች ይወጡበት ዘንድ ገመድ አብጅ›› አለው፡፡ ንጉሡም አባታችን አቡነ አረጋዊ እንዳዘዘው አደረገ፤ያም ቦታ ደብረ ደኃምሞ ተብሎ ተሰየመ።
ከዚህ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ‹‹ከድካም ወደ ዕረፍት፣ ከኃዘን ደስታ ወዳለበት፣ ከኀሣር ወደ ክብር ቦታ በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ፡፡ የሞት ጥላ አያርፍብህም፤ መልአከ ሞትም ሊያስደነግጥህ አይችልም፤ እንደ ነቢያት ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ አረገ፡፡
አባታችን አቡነ አረጋዊ ማትያስ ለተባለው ደቀ መዛሙር ጌታችን ተገልጦ የሰጣቸውን ቃል ኪዳንና ይህ መጽሐፍ ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነገሩት፤ (መዝ ፻፲፩/፻፲፪፥፮) ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቶቹ በተሰበስቡበትም ሁሉንም ከአስተማሩ በኋላ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም›› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም በመሪር ኃዘን እግራቸው ሥር ወድቀው አለቀሱ፤ አባታችን አቡነ አረጋዊም አጽኗኗቸው፡፡ ጥቅምት ፲፬ ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በ፺፱ ዓመታቸው ተሰወሩ፤ በዚያም ከመቋሚያና ከመስቀል በስተቀር ምንም የተገኘ የለም፡፡
የአባታችን አብነ አረጋዊ ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር! አሜን
መምህር ሸዋገኘሁ ከበደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤