ደስ አለው ጌታ በሙሽሮች ደስ አለው ጌታ/2/
በቅዱስ ቁርባን ተወስነው ደስ አለው ጌታ
ደስ አላት ድንግል በሙሽሮች ደስ
አላት ድንግል/2/
በቅዱስ ቁርባን ተወስነው ደስ አላት ድንግል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕገ ሰብእናሁ ዐቀበ በተደንግሎ
ዘፈፀመ በወንጌል ዘሀሎ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መጻ መርዓዊ ፍስሐ ለኲሉ
በሰላም ጻኡ ተቀበሉ
መጣ ሙሽራው ደስታ ለሁሉ
በሰላም ውጡ ተቀበሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል።
ሁለተኛ ለምን ተገለጠ?
👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን
የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል።
ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።
👉 ሰንበትን ሊያጸናልን
የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ
👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ።
"ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ"
(ዮሐ20:29)
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ዮም_ፍስሐ_ኮነ
ዮም ፍስሐ ኮነ (፪)
በእንተ ልደታ ለማርያም
በባርነት ሳለን
ኃጢአት በአለም ነግሳ
በድንግል መወለድ
ቀረልን አበሳ
እግዚአብሔር መረጠሸ
ልትሆኚው እናቱ
ይኸው ተፈፀመ
የዳዊት ትንቢቱ
#አዝ
የሔዋን ተስፋዋ
የአዳም ዘር ህይወት
የኢያቄም የሐና
ፍሬ በረከት
ምክንያተ ድኂን
ኪዳነምህረት
ድንግል ተወለደች
የጌታዬ እናት
#አዝ
በሔዋን ምክንያት
ያጣነውን ሰላም
ዛሬ አገኘነው
በድንግል ማርያም
የምስራች እንበል
ሀዘናችን ይጥፋ
ተወልዳለችና
የአለም ሁሉ ተስፋ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ልደታ ለማርያም
👉 የማርያም ልደት ምን ይመስላል?
💵 በpackage 0.32 ብር
💵 በካርድ 0.54 ብር
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የመዝሙር ስብስብ
👉 የድንግል ማርያም መዝሙሮች
💵 በpackage 0.59 ብር
💵 በካርድ 0.98 ብር
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❖ ሚያዝያ ፴ ❖
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ሚያዝያን አስፈጸመን::
+ ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ:-
- ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::
- ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል (ሙተዋል)::
+ እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪዋን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::
" ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ "
በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል::
+ ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል::
+ የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ (20 ዓመት) እርሱ ነበር:: ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል::
በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና:: ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር::
ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ በዚህ ቀን በ60 ዓ/ም አካባቢ አረማውያን ገድለውታል::
ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል::
❖ ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ፡፡
❖ ቅድስት ማርያም (እናቱ)
- ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ:
- ጌታችንን ያገለገለች:
- ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::
+ ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::
❖ እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::
ሚያዝያ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)
ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
"+ . . . እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኩዋኩዋ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች::
+" (ሐዋ. 12:12-15)
ዝክረ ቅዱሳን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ክርስቶስ በኲር
ክርስቶስ በኲር ቀደመ ተንሥዖ
እምኲሎሙ ኲሎሙ ሙታን /2/
ወያርእዩ ብርሃነ ወያጸድቆ ለዘይትቀነይ
ለጽድቅ ወለሰናይ ወለብዙኃን
ኃጢአቶሙ ውእቱ ይደመስስ /2/
ትርጉም፡-
በኩር ክርስቶስ የብዙዎችን
ኀጢአት ይደመስስ ዘንድ
ለእውነትና ለመልካም ነገር የሚገዙትንም
ብርሃንን ያሳይ ዘንድ ከሙታን
ሁሉ ቀድሞ ተነሣ፡፡
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👉 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡
👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
⚡⚡⚡ማክሰኞ⚡⚡⚡
👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
⚡⚡⚡ረቡዕ⚡⚡⚡
👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
⚡⚡⚡ሐሙስ⚡⚡⚡
👉አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
⚡⚡⚡ዓርብ⚡⚡⚡
👉ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
⚡⚡⚡ቅዳሜ⚡⚡⚡
👉ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
⚡⚡⚡እሁድ⚡⚡⚡
👉ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ክብርህ ገነነ
ክብርህ ገነነ ቅዱስ ስምህ
አልተከደነም መልካም ስራህ
መቃብር ድንጋይ ያላስቀረህ
ኃያል ጌታ ነህ ሞት ማይገዛህ
የወይን ስካር እንደለቀቀው
እንደ ኃያል ሰው እንደታጠቀው
በዝግ መቃብር ጌታ ተነሳ
ጠላትን ጥሎ እኛን አነሳ
አዝ
የሞተልንን እንሰብካለን
የተነሳውን እናመልካለን
ኃያል ነው በእውነት ታላቅ ነው ጌታ
በራሱ ስልጣን ሞትን የረታ
አዝ
በኩር ነውና የትንሳኤያችን
ልባችን ጸና ሞላ ተስፋችን
ሞተን አንቀርም እንነሳለን
ጥልቁን ተሻግረን እንዘምራለን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ወምድርኒ
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ/2/
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ /4/
ምደር ጸዳች ሐሴት አደረገች /2/
በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች/4/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ክርስቶስ ሕያው ነው
ክርስቶስ ሕያው ነው
ሞት ይዞ ያላስቀረው
የለም ከመቃብር ተነሰቷል በክብር /2/
በገዛ ፈቃዱ ነፍሱን ስለሰጠ
የጨለመው ዓለም በብርሃን ተዋጠ
ሲኦል ድል መንሳቱ መውጊያውም ታጠፈ
የሞት ስልጣን በሞት ስለተሸነፈ
የጥሉ ግድግዳ በሞቱ ፈረሰ
የነፍሳችን ቁስል በእርሱ ተፈወሰ
ከቶ አላስቀረውም የመቃብር ድንጋይ
ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ኤልሻዳይ
ዓለሙን እንዲሁ እግዚአብሔር ወዶ
የሰው ልጅ ከበረ ዲያብሎስ ተዋርዶ
ይገዛን ይነዳን ያስጨንቀን ነበር
በሞት ላይ ተራመድን አምላካችን ይክበር
ሕይወት ይሰጠን ዘንድ ስለኛ የሞተው
ቤዛችን ክርስቶስ ሞትን ድል አረገው
የሞተው ተነስቷል በመቃብር የለም
ዳግመኛም ይመጣል ሊፈርድ በዓለም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ያስደስታል/3/ የእኛ እምነታችን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የጋብቻ ሥርዓታችን
ተፈፀመ/3/ ዛሬ ሰርጋችሁ ምስጋና ይግባው እንላለን/2/ ቸር አምላካችንን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ደስ አላት ቤተክርስቲያን በጣም ደስአላት/2/
ሙሽሪት ሙሽራው ልጆቿ/2/ በተክሊል በቍርባን አንድ ሆኑላት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እመቤታችን ተወለደች ማለት ጌታ ሊወለድ 15 ዓመት ቀረው ማለት ነው:: እግዚአብሔር ከሴት የተወለደ ልጁን ሊልክ የዘመኑ ፍጻሜ ቀረበ ማለት ነበር። እግዚአብሔር ሃና እና ኢያቄምን ሳይወልዱ ያዘገያቸውም ለዚህ ታላቅ ክብር እንዲበቁ ነበር።
ቀድመው ልጅ ቢወልዱ ኖሮ ይህችን የፍጥረት ደስታ የሆነች ልጅ አይወልዱም ነበር:: የእርስዋ የልደት ቀን የፍጥረት ደስታ ቀን ነው::
ክርስቶስ ፀሐይ ከሆነ የዛሬው ዕለት ሰማይዋ የተዘረጋችበት ዕለት ነው።
ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ከሆነ ዛሬ ምንጭዋ የፈለቀችበት ዕለት ነው።
ክርስቶስ መድኃኒት ከሆነ ዛሬ የመድኃኒቱ ሙዳይ የተገኘችበት ዕለት ነው::
ወንጌል በመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ይላል። በእመቤታችን መወለድ ምን ያህል ሰዎች ደስ ይላቸው ይሆን? የእመቤታችን ልደት በብዙ ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበራል።
እኛም በሊባኖስ ተራሮች (አድባረ ሊባኖስ) መወለድዋን በማሰብ ከደጅ ወጥተን ቅድም አያቶችዋ በጨረቃ ተመስላ በህልማቸው ያዩአትን የጨረቃችንን (በግሪኩ ሶልያና) ልደት ጨረቃን እያየን እናከብራለን። የልደትዋ ቀን ልደታችን ነው!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#መዝ. 86፥1
“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮችናቸው”
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም በእመቤታችን ልደት ምክንያትዛሬ ደስ ሆነ፡፡
በግንቦት 1 ቀን 5ሺ ከ5መቶ የመከራው ዘመን ሊያልቅ 15 ዓመታት ሲቀሩት/ ሊባኖስ በሚባል ተራራ ከፀሐይ የምታበራ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡
ይህቺውም ፍጥረት ሁሉ ደቂቀ አዳም ሁላቸው ተስፋ ሲያደርጓትና ሲጠባበቋት የነበረች የድኅነታቸው ምልክት እመቤታችን ናት፡፡
ሶሪያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም
“አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኀኒትነ፡፡ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል:- የመመኪያችን ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት በድንግል ማርያም ሆነልን” በማለት መናገሩ ስለዚህ ነው፡፡
አክሊል ምክሐነ አላት ይህም አክሊል የወዲህኛው፣ ምክሕ የወዲያኛው ነው። ከነገሥታት መካከል እንደ ዳዊት የከበረ የለም።
ምንም እንኳን ቅዱስ ዳዊት የከበረ ቢሆን የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም፡፡
ወቀዳሚተ መድኀኒትነ አላት፡- ቀዳሚተ የወዲህኛው መድኀኒት የወዲያኛው ነው፡፡ከመሳፍንት ወገን የሚሆን ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢሆን የደኅንነታ መሆን አልተቻለውም፡፡
ወመሠረተ ንጽሕነ አላት:- መሠረት የወዲህኛው፤ ንጽሕ የወዲያኛው ከነቢያተ እግዚአብሔር ወገን የሚሆን ኤልያስ በድንግልና በንጽሕና መኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡
ነገር ግን ምንም ንጹሕ ድንግል ቢባል የንጽሕናችንመሠረት መሆን አልተቻለው።
የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፤ የንጽሕናችን መሠረት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፤” በማለት ተናግሯል።
በእርሷ ምክንያትነት መድኀኒዓለም የሚፈጽምልንን ካሳነቢያትና የቀደሙ አበው ሁሉ
የእርሷን መወለድ በናፍቆት ሲጠባበቁ ነበር።
ከነቢያት አንዱ የሆነ ኢሳይያስም
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርዘርን ባያስቀርልን
ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ጎሞራም በመሰልነ ነበር፡፡” በማለት መናገሩ በእርሷ መገኘት ከጥፋት መዳናችንን ሲገልጽ ነው፡፡
#ኢሳ 1፥9
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የመዝሙር ስብስብ 2
👉 የድንግል ማርያም መዝሙሮች
💵 በpackage 0.62 ብር
💵 በካርድ 1.04 ብር
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ለመሆኑ ስለ ፋሲካ ምን ያህሎቻችን እናውቃለን
✍ የፋሲካ ትርጉም በእብራይስጥ <<ፖሳህ>> ሲሆን ትርጉሙ አለፈ ማለት ነው።
✍ እስራኤላውያን ከግብፅ ለመውጣት የቻሉት የፋሲካን በግ አርደው ስጋውን በመብላት ደሙን ደሞ እንደታዘዙት በጎበናቸው ላይ በመቀባት የሞት መላእክ ቤታቸው ሳይገባ በማለፉ ነበር።
✍ ክርስቶስም ታልፎ የተሠጠው በዚው ወቅት ስለነበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፍሲካችን ክርስቶስ ስለኛ ታርዶአል ብሎ የጻፈልን።
✍ ኢየሱስ ከሰማይ ሰማያት ወርዶ ሰው ተብሎ ክብሩን ጥሎ ስለእኛ የሞተው የፉሲካ በዓል ነው እያልን እንድንበላ፣ እንድንጠጣ፣ እንድንዝናና ነው ብዬ አላምንም።
✍ አልፎም አምሽቶ በወይን ጠጅ፣ በቢራ፣ በድራፍት እየተረጫጩ ማምሸት እንዲሁም ከሴት ጋር የመተኛት ቀን አይደለም።
✍ ይሄ ቀን የኃጢያታችን ዕዳ የተከፈለበት ቀን ነው።
ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የምስራች እንበል
የምስራች እንበል (፪) እናመስግን ጌታን
በመስቀል ላይ ውሎ ከኃጢአት ላነጻን
ሞትን ድል አድርጎ ለሰጠን ትንሳኤን
ታላቁ ጌታችን የዓለም መድኃኒት
አደረ በመቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት
#አዝ
ፈጣሪ ሆኖ ሳለ የፍጥረታት ጌታ
በሰው ፊት ተዋረደ በሰዎች ተንገላታ
#አዝ
አሳልፎ ሰጠ ስለኛ ራሱን
በመስቀል ተቸንክሮ መረጠ መሞትን
#አዝ
አይሁዶች ተሞኙ ትንሳኤን ሳያምኑ
ሳያምኑ መቃብሩን ወታደር አስጠበቁ
#አዝ
ዘቦችም ወደቁ ሞትም ተሸነፈ
ሰይጣንም ተዋረደ ስልጣኑ ተገፈፈ
#አዝ
በማለዳ ሄዳ ማርያም መግደላዊት
የጌታዋን ትንሳኤ መላዕክት አበሰሯት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👉 ትንሳኤ ክርስቶስ
🎤 በሊቃውንት አንደበት
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ትንሳኤከ
ትንሳኤከ ለእለ አመነ /2/
ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ/2/
ትንሣኤህን ለምናምን ለኛ /2/
ብርሃንህን ላክልን ወደኛ /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️