ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 11:56
በዙሪያችን ካሉ
በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከፀኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ሰማዕት
አዝ
ሀብት እና ንብረቷን ውበቷን የናቀች
ንግሥት መባልን በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ምስክር
የቅድስት አርሴማ እፁብ ነው የእርሷ ክብር (2)
አዝ
እግዚአብሔር ፅናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅፅሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሃን ለዓለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለእኛም አማላጅ ነች(2)
አዝ
ይሄው በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ገለፃት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አደረጋት
አክሊል ተጎናፅፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር
ዛሬም በልጆቿ በረከቷ ይደር
አዝ
እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ (2)
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 05:30
🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ
እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ግእዝን የምንማማርበት ዝግጅታችን ተመልሷል።
📜 እርስዎም የግእዝ ቋንቋን ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናልና ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።
✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ከታች ባለው የቴሌግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ የመማማሪያ ቦታዎችን ያገኛሉ ✅
ለመመዝገብ 👇
@
@
@ 👈
ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ፤ ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።
📲 የበለጠ መረጃ በምዝገባው ሂደት ይደርስዎታል። ጥያቄ ሲኖር ከታች በተቀመጠው በስልክ ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።
🌺 መሠረተ፡ግእዝ 🌺
@ - 0918026533
ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በአክብሮት እንጠይቃለን።
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 октября 2024 13:54
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰውነቴ በአንተ ፍቅር ተጠምዳለች
ውለታህን እያሰበች ታለቅሳለች
መከራው ተረሳ ትካዜም ቀረልኝ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፈጥነህ ደርሰህልኝ
አዝ
ደጅህን ለመርገጥ መንገድ ስጀምር
ተፈቶ አየዋለሁ የልቤ ችግር
ወዳጄ እና አባቴ ሚስጥሬ ተስፋዬ
ቀና እንድል አደረከኝ በነስፍ በስጋዬ
አዝ
በሚመጥን ፊደል በሚያምሩ ቃላት
ነፍሴ ትጠማለች ስምክን ለመጥራት
እንባዬ ይፈሳል አንደበት ያጥረኛል
ውለታህን ሳስብ ልቤ ይቀልጥብኛል
አዝ
ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊት ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረሕይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ
አዝ
ስለቴን ስትሰማ ሲጠብቀኝ ምልጃህ
ሳጉረመርምብህ ትታገሰኛለህ
የጭንቄ ማረፊያ የህመሜም ፈውስ
አርከ እግዚአብሔር ገብረ መንፈስ ቅዱስ
አዝ
ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረሕይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 октября 2024 06:01
ጥቅምት ፭ /5/
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው።
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ፣ ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና) ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም የተቀበሉ አባት ናቸው።
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም ለአእላፍ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው፤ ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው። ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላልና ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር እና ፍትሃ ነገስት💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 октября 2024 20:53
እንኳን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!
አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል።
አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ።
አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ
ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።
ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው።
በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር።
በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል።
ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል።
ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል።
ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል።
ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ።
ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 октября 2024 13:57
ማርያም የሕይወቴ ውበት
የሕይወቴ ውበት የመኖሬ ቀመር
ማርያም ጥበቤ ነሽ ስለአንቺ ልናገር
የእድገቴ ውጥን ምርኩዝ ድጋፌ
ለስምሽ ምስጋና ቅኔ ያፍስስ አፌ
አዝ
ውበት ንፅህናሽን ወደደ ንጉሡ
አፌም አያቋርጥ አንቺን ማወደሱ
የነፍሴ ዜማ ነሽ የቀን ትውስታዬ
እርግቤ ማርያም ነሽ መደምደሚያዬ
አዝ
ፍቅርሽን ከልቤ ማንችሎ ያጠፋል
እናትነትሽን የቀመሰ ያውቃል
በምስጋናሽ ፍቅር ልቤ ተቃጠለ
ያመሰግንሻል ማርያም እያለ
አዝ
ሆኖ አገኘሁት መውደድ የተገባ
አዳም ወደ ቤቱ በአንቺ ነው የገባ
ይወቅ ያላወቀ ትልቅ ሱታፌሽን
ዓለም ለመዳኑ ምክንያት መሆንሽን
አዝ
በአንቺ የተደረገ የሚርቅ ጥበብ
ነፍሴ ትረካለች እሱን በማሰብ
ከጨረቃ የተዋብሽ
ከፀሐይ የጠራሽ
በቃል አይገለፅ ልዩነው ክብርሽ
ዘማሪ አዲስ መስፍን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 октября 2024 05:14
በእንባ ሸለቆ
በእንባ ሸለቆ ያየሁሽ ተራራ
ለበረሃው ልቤ የፍቅር አዝመራ
ለምለሚቷ ምድር አንቺ ነሽ እናቴ
ሁሌ እወድሻለሁ ማርያም እመቤቴ
አዝ
ዛሬ ትላንትናን ሽሯል በጉልበቱ
ሁሉም ይለወጣል የለም በዓለም ብርቱ
እኔ ግን እግሮቼን በፅዮን ተክዬ
የነቀለኝ የለም ድንግል አንቺን ብዬ
አዝ
አስፈሪውን ጉዞ በድል ወጥቻለሁ
ወደ ሰዶም ላልዞር በቀኜ ምያለሁ
ማምለጫ ዋሻዬ የተሸሸኩብሽ
ሞቴን የሞተውን በአንቺ አገኘሁብሽ
አዝ
ጭንቅ የያዘው ድንኳን ሰላም ተነፈሰ
በእልፍኝ በጓዳዬ መውደድሽ ፈሰሰ
የልጅነት ውርሴ ስምሽ አብሮኝ አለ
እንቅፋት ያነሳ ወጥመዴን የጣለ
አዝ
በብዙ መከራ መተማመኛዬ
የመዳኔ አርማ ቀስተ ደመናዬ
አይኔ አይነቀልም እናቴ ከአንቺማ
አይሰለችም አፌ ይሰጥሻል ዜማ
አዝ
አስፈሪውን ጉዞ በድል ወጥቻለሁ
ወደ ሰዶም ላልዞር በቀኜ ምያለሁ
ማምለጫ ዋሻዬ የተሸሸኩብሽ
ሞቴን የሞተውን በአንቺ አገኘሁብሽ
አዝ
በብዙ መከራ መተማመኛዬ
የመዳኔ አርማ ቀስተ ደመናዬ
አይኔ አይነቀልም እናቴ ከአንቺማ
አይሰለችም አፌ ይሰጥሻል ዜማ
ዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሣሙኤል 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
13 октября 2024 12:05
ናታኔም ነኝ
ናታኔም ነኝ አገልግሎቴ
አይከፋኝም ታናሽነቴ
እጠርጋለሁ ደጅህን ጌታ
ዝቅ ብዬ ላንተ ውለታ
አዝ
ከነገደ ሌዊ ባልሆን
ባልሾምም እንደ አሮን
የዜማ እቃ ባልይዝ በገና
ላመስግንህ በትህትና
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተሰፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
አዝ
ከረኝነት ከታናሽ ስፍራ
ለንግሥና ምንም ብጠራ
ከቀንዲሉ ቀርቧል ሀሣቤ
ልቀኝለት ተነጥፎ ልቤ
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
አዝ
ሳይከብድኝ የአለም ዝና
ተንበርክኬ ልሥጥህ ምሥጋና
ምክንያት አለኝ ለማዘንበሌ
ናታኔም ነኝ ይቺ ናት ቃሌ
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
አዝ
እንኳን ልቆሞ በፍታን ለብሼ
አፍርሀለው እኔ አጎንብሼ
የትመክኸት ካባዬን ጥዬ
ከመቅደስህ ልግባ ጌታዬ
ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
12 октября 2024 18:13
🌼በአዲስ አመት በገና፣ክራር ከበሮ መማር ይፈልጋሉ?🌼
መመዝገብ ለምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን
በ0956861468
በ0912085085 ደውለው ይመዝገቡ
እንዲሁም በቴሌግራም ለመመዝገብ ለምትፈልጉ
@
በእዚህ ሊንክ በውስጥ ማውራት ትችላላችሁ
✝ያለው ቀሪ ቦታ ውስን ስለሆነ ቶሎ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን✝
መማሪያ ሰዓቶች
ከሰኞ-አርብ 11:00-1:00
ቅዳሜ እና እሑድ
3:00-5:00
6:00-8:00
9:00-11:00
ክፍያ የ6ወሩ በወር 500ብር
የ3ወሩ በወር 1000ብር ነው ሁለቱም ዋጋቸው እኩል ነው አጠቃላይ 3000ብር ነው የሚመጣው። መመዝገቢያ 100ብር ይጨምራል።
✝ ከበሮ አለን የ1 ወር እና የ1 ሳምንት
የ1 ሳምንቱ ሙሉ ሳምንት ሲሆን
ከ8:00-10:00 እና 9:00-11:00 አለ
የአንድ ወሩ ከሆነ በሳምንት 2 ቀን ነው የምትማሩት። ሁለቱም ክፍያቸው ተመሳሳይ ነው 1100ብር ነው
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
12 октября 2024 06:06
ጥቅምት ፪ /2/
የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ መጣ።
የከኀዲው ንጉስ ዮስጥያኖስ ሚስት በሃይማኖቷ የቀናች ነበረች። ቅዱስ አባ ሳዊሮስንም ትወደው ታከብረውም ነበር። በዚሕም ንጉሱ ሊገድለው እንደሆነ በአወቀች ጊዜ ለአባ ሳዊሮስ እንዲሸሽ ነገረችው፤ አባታችንም
እኔ ስለ ክርስቶስ ለሞት የተዘጋጀው ነኝ አለ። ንግሥቲቱና ምዕመናኑም በለመኑት ጊዜ ወደ ግብፅ አገር ተሰደደ። የንጉሱ ወታደሮችም በመካከላቸው ሆኖ ሲጓዝ አላገኙትም ነበር፤ ጌታችን ይሠውረው ነበርና።
በአንዲት ቀንም በአስቄጥስ ገዳም በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን በመጻተኛ መነኩሴ አምሳል ገባ። በዚያም ቄሱ ዕጣኑንና ቁርባኑን ሊያሳርግ ጀመረ ሁሉንም ሥርዓት ፈጽሞ እጆቹን ታጥቦ ማኅፈዱን በገለጠው ጊዜ በጻሕሉ ውስጥ የቁርባኑን ኅብስት አላገኘውም፤ ደንግጦም አለቀሰ ለሕዝቡም ወንድሞቼ ይሕ የሆነ በእኔ ኃጢያት ወይም በእናንተ ኃጢያት እንደሆነ አላወቅሁም አላቸው።
መልአክም ተገልጦ ይህ የሆነ በኃጢአትሕ ወይም በሕዝቡ ኃጢአት አይደለም ሊቀጳጳሳት አባ ሳዊሮስ እያለ መሥዋዕትን ለማሳረግ በመድፈርሕ ነው አለው። ቄሱም መልሶ ሊቀጳጳሳት መኖሩን አላወቅሁም አለው፤ መልአኩም አባታችን ወደ ቆመበት ቦታ አመለከተው። ቄሱም ከአባታችን ከእግሩ በታች ሰግዶ ቡራኬ ተቀበለ። ወደ ቤተመቅደስም ገባ፤ በኋላም ቄሱ የቁርባኑን ኅብስት በጻሕሉ ውስጥ አገኘው ካሕናቱና ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ የቁርባኑም ሥርዓት ተፈጸመ።
ከዚያም ወጥቶ ወደ ሀገረ ስሐ ሄደ ምዕመናንንም በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው እስከሚያርፍባት የካቲት ወር ዐሥራ አራት ቀን ኖረ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
11 октября 2024 19:48
መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በአንድ ጥራዝ የሚገኝ የብዙ መጻሕፍት ስብስብ የሆነ የተለየ፣ የተቀደሰ ጽሑፍ ማለት ነው። በውስጡም ከኢየሱስ ክርስቶስ በፊት የተጻፈ ብሉይ ኪዳንና ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ የተጻፈው ሐዲስ ኪዳን ተብለው የተከፈሉ መጻሕፍትን የያዘ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ የተባለበት ምክንያት ከሌሎች መጻሐፍት የተለየ በመሆኑ ነው፡፡ የተለየ የሆነው በሚከተለው ምክንያቶች ነው ፡-
፩. በመጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ የሚገኙት ጽሑፎች ከቅዱሱ ከእግዚአብሔር የተገኙ እና የእግዚአብሔርን ቃል የያዙ ስለሆኑ፡፡
፪. መጽሐፉ ቅድስና ምን እንደሆነ፣ ሰዎች ቅዱሱን እግዚአብሔርን በቅድስና እንዲመስሉ የሚመክሩ የሚያስተምሩ ታሪኮችን እና ምክሮችን የያዘ መጽሐፍ በመሆኑ።
፫. መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነቡትን፣ የሚሰሙትን፣ የሚያምኑበትና የተሳለሙትን ሁሉ የሚቀድስ፣ የሚባርክ ስለሆነ ቅዱስ ተብሏል።
፬. ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ።
፭. የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ሁነት እና ወደፊት የሚፈጸሙትን በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ።
መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በተለያዩ ጊዜ እና ቦታ በነበሩ ከተለያዩ የሥራ መስክ በተሰማሩ ከ፵ በላይ በሚሆኑ ቅዱሳን ሰዎች ሲሆን፤ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ ያደረጋቸው እግዚአብሔር ነው፡፡
እግዚአብሔር መጽሐፍቱን እንዲጽፉ ያደረገበት ምክንያትም ሰዎች በእግዚአብሔር እንዲያምኑና ሕጉን እና ትእዛዙን አክብረው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው፡፡
በሌላ በኩልም መጽሐፍ ቅዱስ የጻፉትን ሰዎች የመረጣቸው እርሱ እግዚአብሔር ነው ሲመርጣቸውም የተለያዩ ሙያ የነበራቸው ሰዎችን ነው፡፡ እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፉት መካከል የተወስኑት እንመለከት፦
ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ፦
ኤርሚያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዘካሪያስ ካህናት ሲሆኑ ኢሳይያስ፣ ዳንኤልና ሆሴዕ ደግሞ ከነቢያነት ቅዱስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን ደግሞ ከነገሥነት ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው አሞፅ ደግሞ ከእረኛነት ነበረ።
ከሐዲስ ኪዳን ጽሐፊዎች ደግሞ
ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ የሐንስ፣ ቅዱስ ያዕቆብ እና ቅዱስ እንድርያስ ከአሳ አጥማጅነት፣ ማቴዎስ (ሌዊ) ከቀራጭነት በመመረጥ መጽሐፍትን እንዲጽፉ አድርጓቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ መቼ ተጻፈ?
እግዚአብሔር ዘላለም የሚኖር አምላክ በመሆኑ በተለያዩ ዘመናት የነበሩ ሰዎች በመምረጥ ያጻፈው መጽሐፍ ነው። በመሆኑም መጽሐፉን የጻፉት ሰዎች የኖሩበት ዘመን የተለያየ እንደመሆኑ መጽሐፍቱም የተጻበት ዘመን እንዲሁ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ለመመለከት ያህል፦
እንደ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በመጀመሪያ የተጻፈው መጽሐፈ ሄኖክ ነው። መጽሐፈ ሄኖክ ዓለም ከተፈጠረ በ፲፬፹፮ ዓ.ዓ ጌታችን አምላካችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ በፊት ፵፻፲፬ ቅ.ል.ክ ገደማ ተጽፏል፡፡ ከዚህም ቀጥሎ ሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሐፍት ከ፲፭፻ ዓ.ዓ-፫፻ ዓ.ዓ (ዓመተ ዓለም) ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወልዱ በፊት ያለው ጊዜ እና አሁን ያለንበት ዓመት ማለት ነው።
ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐርገ በኋላ ከ፵፭ ዓ.ም- ፻ ዓ.ም፤ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጽፏል።
ምንጭ:- መጽሐፍ ቅዱስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምህር ቸሬ አበበ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
11 октября 2024 12:00
ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደ እኛ
ሃናና ኢያቄም ወለዱ ሰማይ
አዲሷም ሰማይ አስገኘች ፀሐይ
ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛ
ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደ እኛ /2/
አዝ
ተጨነቀ አዳም በመከራ
በእርግማን ቀን ለቅሶ እየዘራ
በልጅሽ ሞት ዓለም ተቀደሰ
የፍጥረቱ እንባ በመስቀል ታበሰ /2/
አዝ
የሕያዋን እናታቸው ሆነሽ
ለቀደመችዋ ሔዋን ጠበቃ ሆንሽ
ደስተኛዋ ደስ ይበልሽ ማርያም
ከአንቺ ወጣ የዓለሙ ሰላም /2/
አዝ
ፅዕኑ ገመድ በአንቺ ተቆረጠ
የፍዳ ዓመት ይኸው ተለወጠ
በሃና ልጅ በኢያቄም ፍሬ
ደስታ ሆነ ቅኔና ዝማሬ /2/
አዝ
በወለዱሽ በሃና በኢያቄም
ተማፅነናል ድንግል ማርያም
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ልጆችሽን ጠብቂ ከጥፋት
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ኢትዮጲያን ጠብቂ ከጥፋት
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
11 октября 2024 05:00
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው
ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
አንድያ ልጁን የምናምንበት
የህይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
የባህሪ አምላክ ብለን ስናምነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የአማልክት አምላክ ነው
በማርያም ስጋ የተገለጠው
ወልድን ስናውቅ ነው አብን ያወቅነው
አብ በእርሱ እንዳለ እርሱም በአብ አለ
በኃይል በሥልጣን የተካከለ
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ እርሱ ጌታ ነው
ሥጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍሶ
ህይወት የሰጠን በደልን ክሶ
እኛም ዳሰስነው በላን ጠጣነው
በዝግ ቤት ሳለን ገብቶ ያየነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው
ፈቅዶ ቢወሰን በአጭር ቁመት
ረቂቁ ቢገዝፍ በጠባብ ደረት
መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል
በዓለም ሊፈርድ ዳግም ይመጣል
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
10 октября 2024 12:00
ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ
ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ ወጣሁት ዳገቱን
ድንግል ባንች ምልጃ አለፍኩት ወጥመዱን
ድንግል ማርያም በአንቺ ምልጃ ሰበርኩት ወጥመዱን
አዝ
አምላክ ቀድሶሻል ከሁሉም አብልጦ
ከአንቺ ይወለድ ዘንድ በሥጋ ተገልጦ
ለዓለሙ መዳን ምክንያት የሆንሽ
ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም አንቺ ነሽ
አዝ
ወጀቡን ልሻገር ባንቺ ተደግፌ
ድካሜ ይወገድ ከጥላሽ ሥር አርፌ
ያላንቺ መድኃኒት ከቶ የለምና
ባንቺ ተመገብኩት የሰማዩን መና
አዝ
ይመስገን ፈጣሪ የነዳዊት አባት
ቤቴን ሞልቶልኛል ባንቺ አማላጅነት
አንቺን የተጠጋ በነፍስም በሥጋ
ከልጅሽ ይወርሳል የሰማዩን ዋጋ
አዝ
ዳግም እንዳልራብ ነፍሴ እንዳትጠማ
ከማይደርቀው ምንጭሽ አጠጭኝ እማማ
ከቤትሽ ገብቼ እረፍት አግኝቻለሁ
እድፌ ተወግዶ አዲስ ለብሻለሁ
ዘማሪ ዲያቆን አቤል ተስፋዬ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
10 октября 2024 05:00
ምን ሰማህ ዮሐንስ
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ /2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2/
አዝ
ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው
የእናታችን ፍቅር /2/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና
የሰላምታ ቃሏ /2/አዝ
በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ
እንዴት ያለ ብሥራት /2/ አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ
ጭራሽ ያልታሰበ /2/አዝ
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ
በህይወቱ ፍፁም /2/ ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ
የኪዳን ሰላምታ /2/
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 06:00
ጥቅምት ፮ /6/
በዚች ዕለት ቅዱስ አባት አባ ጰንጠሌዎን የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው።
ታላቁ ጻድቅ፣ ሰባኬ ወንጌልና ገዳማዊ አባ ጰንጠሌዎን የተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን መሪ ናቸው። ጻድቁ ሃገረ ትውልዳቸው ሮም ቢሆንም ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮጵያ ነው። በገዳም ትምህርቱን ካጠነቀቁ በኋላ በዚያው ጠፍተው ወደ ግብጽ ወረዱ፤ በዚያም መነኮሱ። እድሜአቸው እየገፋ ሲሔድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስምንቱን ቅዱሳን ሰብስበው በአቡነ አረጋዊ መሪነት ወደ ሃገራችን መጡ። በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ የነበረው ንጉሥ አልዓሜዳም በክብር ተቀብሎ አክሱም ውስጥ ''ቤተ ቀጢን” የሚባል ቦታን ሰጣቸው።
አባ ጰንጠሌዎን 'ጾማዕት' ወደ ሚባል ረዥም ተራራ ወጡ። በዚያም አስቀድመው ለወንጌል አገልግሎት እየተጉ ድውያንን ፈወሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣ አጋንንትን አሳደዱ። ብዙ ተአምራትንም አደረጉ። እንዲያውም አንድ ቀን ወይራውን በጧት ተክለው በሠርክ ትልቅ ዛፍ ሆነላቸው። ከዚያ ዘንጥፈው እሳቱን በቀሚሳቸው ላይ አፍመው ማዕጠንት አሳርገዋል። የሚገርመው ያ ዛፍ ዛሬም ድረስ ለምስክርነት ቁሟል። በመጨረሻ ዘመናቸው ግን ጻድቁ አምስት ክንድ ርዝመት ባላት ጾማዕት (በዓት) ውስጥ ገብተው ቆሙ።
ለአርባ አምስት ዓመታት ሳይቀመጡና ሳይተኙ በእንባ ቢጸልዩ ቅንድባቸው ተላጠ። አካላቸውም በአጥንቱ ብቻ ቀረ። በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት መድኃኔዓለም መጥቶ ''ወዳጄ! ስምህን የጠራ መታሰቢያህን በእምነት ያደረገውንም ሁሉ እምርልሃለሁ።'' አላቸው። ያን ጊዜ አጥንቶቻቸው ተወዛወዙና ነፍሳቸው በክብር ዐረገች።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 05:00
በረከትሽ ብዙ
በረከትሽ ብዙ አምኖ ለጠራሽ
የጭንቅ ቀን ዋስ ነሽ ዛሬን ላሰበሽ
አርሴማ በምልጃሽ ለታመነብሽ
አዝ
ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬ ነው ብለሽ
የዓለም ክብር ሀብቷን ስለ ክብሩ ንቀሽ
በደምሽ መሰከርሽ ስለ ደሙ ዋጋ
ጌታም አከበረሽ በተለየ ፀጋ
አዝ
የጳውሎስ ሰይፍን የጴጥሮስ ሃሳብን
ተቀብለሽ አየን ሰማዕትነትን
የረድኤትሽ ባሮች በላዬ ይስፋፉ
ያስጨነቁኝ ሁሉ ከላዬ እንዲረግፉ
አዝ
የእናትነትሽን ፍቅርን ያልቀመሰ
በእውነት ያስቆጨዋል በአንቺ ያልተዳሰሰ
እኔ ምስክር ነኝ ከስንቱ እንዳዳንሽኝ
አርሴማ በምልጃስ ከሞት እንዳስጣልሽኝ
አዝ
እንዴት አይነት ዉበት ቢኖርሽ ነው ከቶ
ነገስታት ያጣላ ክብር ሁሉ አስትቶ
ውበት ሐሰት ብለሽ ቆምሽ በአደባባይ
እኔንም አስተምሪኝ ልውጣ ከመታበይ
አዝ
በዓለም ውጣ ውረድ የተጨነቃችሁ
ለችግሮቻችሁ መፍትሄን ያጣችሁ
ቅድስት አርሴማ ነይ ብላችሁ ደጅ ጥኗት
አምላኳን ተማፅና ታስምራለች በእውነት
ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 октября 2024 10:59
የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ
አዝ
ፀሐይ(2)የምድራችን ፀሐይ
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ
የመላዕክት ወዳጅ(2)ገብረሕይወት ሰማይ
አዝ
መብረቅ(2)ሰረገላው መብረቅ
የቃልኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ
የፍጥረቱ ደስታ(2)ገብረሕይወት ፃድቅ
አዝ
ኮከብ(2)ክብረገድላን ኮከብ
ዓለምን የሚያስንቅ መዐዛው የሚስብ
አርከ ሥሉስ ቅዱስ(2)ገብረሕይወት ኪሩብ
አዝ
ስኂን(2)ፄና ልብሱ ስኂን
የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን
የሚነበብ መፃፍ(2)ገብረሕይወት ድርሳን
አዝ
መቅረዝ(2)የማኅቶት መቅረዝ
ምድረከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ
የዝጊቲው ፈዋሽ(2)ገብረሕይወት ምርኩዝ
ሕብረ ዝማሬ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
15 октября 2024 05:30
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ቆሚያለሁ ሁሉንም አልፌ
በምልጃው ከሞት ተርፌ
ፀሎቱ ኃይል አደረገልኝ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረዳኝ (2)
አዝ
አበቃ ሲባል አልቆ ተስፋዬ
በሃዘን ብዛት ሲፈስ እንባዬ
ገብረ ሕይወት መጣ ፃድቁ አባቴ
ደዌዬ ተሻረ ፀና ጉልበቴ (2)
አዝ
የጭንቁን ዘመን እረስቻለሁ
ከሰዎች እኩል በእግር ቆሚያለሁ
እርሱ ባይቆምልኝ በእግዚአብሔር ፊት
አልቆምም ነበር ዛሬ በሕይወት
አልኖርም ነበር ዛሬ በሕይወት
አዝ
በፅድቅ ክንዱ እየደገፈ
ክፉን በምልጃው እያሳለፈ
ስለ ቃልኪዳኑ በስሙ ታምኜ
አልጠግብም ፃድቁን እርሱን አመስግኜ(2)
አዝ
በደዌ ኃጢያት የተጠቃችሁ
ሞትን በችግር ለጠበቃችሁ
ፃድቁን ጥሩት ይረዳችኋል
ከአፈር ከትቢያ ያነሳችኋል(2)
ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 октября 2024 19:36
ነገረ ቅዱሳን
ቅዱሳን የሚለው ቃል ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን፣ ትርጉሙም ንጹሕ ልዩ የከበረ ማለት ነው። ይህ ቃል ለእግዚአብሔር የባሕርይ መገለጫ ነው። እግዚአብሔር በባሕርዩ ቅዱስ ነውና። ቅዱሳን የሚለውም ቃል በባሕርዩ ቅዱስ የሆነውን አምላክ ለሚያገለግሉ መላእክትና ደጋግ ሰዎች የሚሰጥ ነው።
ቅዱሳን መላእክትን ቅዱሳን እንላቸዋለን። ከማንኛውም ክፉ ነገር የራቁ፣ ሥርዓታቸውን የጠበቁ፣ እግዚአብሔርን ያወቁ፤ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ ስለሆኑ ቅዱሳን ይባላሉ። ከመዓረገ መላእክት የደረሱ ደጋግ ሰዎችም በዚሁ የቅድስና ስም ይጠራሉ:: ራሱ እግዚአብሔር
«እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ብሏልና:: ዘሌ.19÷2፣ 1ኛጴጥ.1፥15-16
ቅዱሳን በገድል በሦስት ይከፈላሉ1. ስለቀናች ሃይማኖታቸውና ስለፈጣሪያቸው ክብር ሲሉ በአላውያን / በማያምኑ/ ነገሥታት ፊት ስለ ክርስቶስ አምላክነት ሳያፍሩ፣ ሳይፈሩ መስክረው እስከ ደም ጠብታ ድረስ ለክርስቶስ የመሰከሩ፤ ቁልቁል የተሰቀሉ፣ ለአናብስት የተሰጡ፣ በሰይፍ የተቀሉ በመጋዝ የተሰነጠቁ፤ ወደ እቶን እሳት የተጣሉ፤ በድንጋይ የተወገሩ ሰማዕታት ናቸው። ሰማዕታት ማለት መስካሪዎች ማለት ነው። ራዕይ.12+11፣
ምሳሌ፦ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ቅዱስ ቂርቆስ፣ ሠለስቱ ደቂቅ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
2. በገደል፤ በዱር፣ በዋሻ ሆነው ከጣዕመ ዓለም ተለይተው ክርስቶስ ለሞተላት ለዚህ ዓለም ሲጸልዩ ግርማ ሌሊቱን ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብዓ አጋንንትን፣ የቀን ሐሩር፣ የሌሊት ቁር ታግሰው የሚኖሩ ጻድቃን ናቸው።
ምሳሌ:- ጻድቁ ተክለሃይማኖት፣ ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ... ናቸው።
3. መጽሐፍ አውጥተው፤ አንቀጽ ጠቅሰው፣ መናፍቃንን ተከራክረው የቤተክርስቲያንን ሕግዋን ያስከበሩ የቤተክርስቲያን ጠበቆች ናቸው፡፡
ምሳሌ:- ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ቄርሎስ፣ ጎርጎርዮስ፣ ባስልዮስ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ የመሳስሉት ናቸው፡፡
በዚህ መሠረት የእግዚአብሔር ወዳጆች ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፤ ሰማዕታት ሁሉ ለቅዱስ እግዚአብሔር ሲሉ ሕይወታቸውን መስዋዕት አድርገው ስለሰጡ ስለስሙ ስለመሰከሩ በተጋድሎአቸውና በትሩፋታቸው ስላገለገሉ የቅድስናና የብጽዕና ማዕረግ ተሰጥቶአቸዋል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ ፦ ትምህርተ ሃይማኖት
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
14 октября 2024 05:59
ጥቅምት ፬ /4/
በዚህች ቀን ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያረፉበት ነው። አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት ጌታችን በተወለደባት ዕለት ነው። በታላቁ በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እየተማሩ አድገው በእሳቸው እጅ በ330 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ በእነርሱም ጊዜ አማናዊው ጥምቀትና ቁርባን መጣልን፡፡ በሀገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ሲያሰሩ 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡ በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዓርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡
ከዕለታት አንደኛው ቀን ጌታችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በአክሱም ‹‹ማይ ኰኩሐ›› በሚባል ተራራ ላይ ጠርቶ ‹‹በዚህች ቦታ ላይ ቤተ መቅደሴን አንጹልኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ቦታው ባህር ነው በየት እናንጽልህ?›› አሉት፡፡ ጌታችንም በጥበቡ ከገነት ጥቂት አፈር አምጥቶ በባሕሩ ላይ ቢበትንበት ባሕሩ ደርቆ ሜዳ ሆነ፡፡ ጌታችንም በቆመባት ዓለት ላይ የእግሩ ጫማ ቅርጽ እስከ አሁን ሳይጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ቦታውም ከዚያ ወዲህ መከየደ እግዚእ›› እየተባለ ይጠራል፡፡
ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ በእንዲህ ዓይነት ግብር ጸንተው በመኖር እግዚአብሔርን አገልግለው ለሀገራችንም ብርሃን አብርተው፤ ታላቁ አብርሃ በ364 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን፤ ታናሹ አጽብሃ ከ13 ዓመት በኋላ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን ዐረፉ፡፡ ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነው ዓመቱ ይለያይ እንጂ፡፡ የንግሥና ስማቸው ኢዛናና ሳይዛና ይባላል፡፡
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
13 октября 2024 17:23
ነፍሴ ሆይ
ነፍሴ ሆይ /3/ እግዚአብሔርን ባርኪ
አጥንቶቼም ሁሉ /3/ የተቀደሰ ስሙን
በደስታ ዘምሪ በአዲስ ምስጋና
ጸጥታ እና ሰላም አድሎሻልና
መሠንቆውን አንሺ ቅኔ ተቀኚለት
ለውጦሻልና በደስታ ዘይት
አዝ
ሀሴትን አድርጊ ነፍሴ በእግዚአብሔር
ይሰጥሻልና በክብር ላይ ክብር
ደሴቶች ሲያወሩ በደስታ መንፈስ
እየተወያዩ ስለ ሥሉስ ቅዱስ
አዝ
ሰማያት ሲያወሩ ጽድቅን ሲወያዩ
ሲጠራው አድምጪ ቀላዩን ቀላዩ
ደመናው ጭጋጉ በዙሪያው ከበውት
ቅኔ ያቀርባሉ ለፍጥረታት አባት
አዝ
መብረቅም ይሰማል ሰማዩን ሰንጥቆ
ምስጋናውን ሊያቀርብ ጊዜውን ጠብቆ
በፊቱ ይነዳል እሳትም በግርማ
ምድር ተናወጠች ነጎድጓዱን ሰምታ
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
13 октября 2024 09:16
ጥቅምት ፫ /3/
በዚሕችም ቀን ሊቀ ጳጳሳት አባ ስምዖን አረፈ።
የዚሕ አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ ያደገ የቤተክርስቲያንንም ትምሕርት ተምሮ ያደገ ነው። ወደ አስቄጥስ ገዳም በሊቀ ጳጳሳት በአባ ያዕቆብ ገዳም የምንኩስናን ልብስ ለብሶ መነኮሰ ተጋድሎውንም በየጊዜው ጨመረ ሥጋውንም አያደከመ በእርሱ ዘንድ ኖረ። ስለ በጎ ተጋድሎውና ስለ አገልግሎቱ ዳግማዊ ሊቀ ጳጳስ አባ ማርቆስ ወደ አባ ያዕቆብ ወስዶት እያገለገለው ከእርሱ ጋር ኖረ።
አባ ያዕቆብ በአረፈ ጊዜም ካሕናትና ኤጲስቆጶሳት ትሩፋቱንና ያማረ ሥራውን ስለተመለከቱ አምላካዊ ፍቅር አነሳስቷቸዋልና በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።በሹመቱ ጸንቶ መልካምን ጉዞ ተጓዘ እግዚአብሔርንም እያገለገለ የሃይማኖትንም ሕግ በማስጠበቅ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ። በሹመቱ ወራትም ቤተ ክርስቲያን በጸጥታና በሰላም ኖረች።
ከዚሕም በኋላ እግሮቹን በጽኑዕ ደዌ ታመመ እግዚአብሔርንም ከዚሕ ደዌ ያሳርፈው ዘንድ ለመነው ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በሰላም በፍቅር በአንድነት አሳረፈው የሹመቱም ወራት አምስት ወር ከዐሥራምስት
ቀን ነው።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
12 октября 2024 12:00
እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል
እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል
የተረሱትን ያስታውሳል
የተናቁትን ያከብራል
አንተ በክብር ላይ ክብርን ስትጨምር
እረኛው ይሾማል በንጉሱ ወንበር
ጌታ ትወዳለህ የተናቁትን
አንተ ልብን እንጂ አታይም ፊትን
አዝ
ሳሙኤልን ልከህ ጠርተህ ትቀባለህ
የአንበሶቹንም አፍ አንተ ትዘጋለህ
በጌርጌሴኖን በመቃብር ስፍራ
አየሁ ጌታዬ ለሰዎች ስትራራ
አዝ
ጠላታችን ደርሶ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከእስራት
አዝ
ይደግፋል ክንድህ የተናቁትን
ከሰው በታች ሆኖ የሚኖሩትን
ደስታም ትሰጣለህ ሃዘን አርቀህ
አይቀርም አልቅሶ አንተን ያመነህ
አዝ
ጠላታችን ደርሶ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከእስራት
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
12 октября 2024 05:00
ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ስለረዳሽኝ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ከእኔ ጋር ስለሆንሽ እመቤቴ አወድስሻለሁ
ምስጋናሽን ይዤ ጠዋት ማታ ፊትሽ እቆማለሁ
ምስጋናሽን ይዤ እመቤቴ ፊትሽ እቆማለሁ
አዝ
ሀዘን ትካዜዬ በአንቺ ተወግዷል
ልመና ፀሎቴ ሀሳቤ ተሟልቷል
ያጣሁትን ሁሉ አግኝቼብሻለው
በእናትነትሽ ዘውትር እመካለሁ
አዝ
በአንቺ ደስ ይለኛል ያርፋል ልቦናዬ
ሰአሊ ለነ ብዬ ተቃና ጉዞዬ
አልፈራም እንግዲህ ገደል እንቅፋቱን
ይዘሽኛልና ድንግል አዛኚቱ
አዝ
የተስፋ መብራቴ አጠፊም ከፊቴ
መድኃኒቴ አንቺ ነሽ ለብቸኝነቴ
ይህቺ አለም ብትከፋ ፊቷን ብትመልስ
ጨክነሽ አታውቂም እናቴ በእኔስ
አዝ
ምስክር አልሻም ከእንግዲህ በኋላ
ነፍሴ ትጮሃለች አማላጄ ብላ
አወድስሻለሁ እናቴ እመቤቴ
በኑሮዬ ሁሉ እስከ እለተ ሞቴ
ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሠናይ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
11 октября 2024 19:38
🌼በአዲስ አመት በገና፣ክራር ከበሮ መማር ይፈልጋሉ?🌼
መመዝገብ ለምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን
በ0956861468
በ0912085085 ደውለው ይመዝገቡ
እንዲሁም በቴሌግራም ለመመዝገብ ለምትፈልጉ
@
በእዚህ ሊንክ በውስጥ ማውራት ትችላላችሁ
✝ያለው ቀሪ ቦታ ውስን ስለሆነ ቶሎ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን✝
መማሪያ ሰዓቶች
ከሰኞ-አርብ 11:00-1:00
ቅዳሜ እና እሑድ
3:00-5:00
6:00-8:00
9:00-11:00
ክፍያ የ6ወሩ በወር 700ብር
የ3ወሩ በወር 1000ብር ነው ሁለቱም ዋጋቸው እኩል ነው አጠቃላይ 3000ብር ነው የሚመጣው። መመዝገቢያ 200ብር ይጨምራል።
✝ ከበሮ አለን የ1 ወር እና የ1 ሳምንት
የ1 ሳምንቱ ሙሉ ሳምንት ሲሆን
ከ8:00-10:00 እና 9:00-11:00 አለ
የአንድ ወሩ ከሆነ በሳምንት 2 ቀን ነው የምትማሩት። ሁለቱም ክፍያቸው ተመሳሳይ ነው 1100ብር ነው
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
11 октября 2024 05:59
ጥቅምት ፩ /1/
በዚህችም ቀን ቅድስት አንስጣሲያ በሰማዕትነት አረፈች። ይህችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርአት አሳደጓት።
በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቡአት ፈለጉ እርሷ ግን በሥውር በሮሜ ከሚገኙ ወደ አንዱ ገዳማት ሂዳ የምንኩስና ልብስን በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ ሥጋዋን አደከመች በቀኑ ርዝመት ትጾማለች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በጌታችን ጾም ግን ያለ ሰንበታት ቀን አትመገብም።
ከዚሕም በኋላ የንጉስ ዳኬዎስ ወታደሮች ክርስቲያኖችን አሥረው በቁጣ ሲጎትቷቸው አይታ ልቧ በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው
የእውነት ፈጣሪን የካዳቹ ልባቹ የደነዘዘ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለ እነርሱም ነፍሱን አሳልፎ በሰጣቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላቹ።
ወታደሮቹም ይሕን ሲሰሙ ተቆጡ ይዘውም ወደ መኮንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስቲያን ነሽን እርሷም ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለው ብላ መለሰችለት።
በዚያን ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ ከዛም ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም አጤሱባት ከሃይማኖቷም ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
10 октября 2024 06:00
መስከረም ፴ /30/
በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በከበረና በተመሰገነ በአባ አትናቴዎስ ላይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም ሁለተኛም ቁስጠንጢኖስ ወደ ረከሰች የአርዮስ ሃይማኖት በገባ ጊዜ የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስን አሳድዶ ከሀዲውን ጊዮርጊስን በእስክንድርያ መንበር ላይ ሾመው።
ቅዱስ አትናቴዎስም በተሰደደበት ስድስት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሡ ሔዶ እንዲህ አለው ወደ ተሾምኩበት መንበሬ ትመልሰኝ እንደሆነ መልሰኝ ይህ ካልሆነ የምስክርነት አክሊልን እንድቀበል ግደለኝ አለው። ንጉሱም እርሱን ቢገድለው እንደሚበጠበጥ አውቆ በብልሐት ሊያጠፋው ወሰነ።
በመርከብ አድርጎ ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም ቀዛፊ በሌለበት በሜድትራኒያን ባሕሪ ላይ ጣለው። መለዕክትም እየመገቡት እና መርከቡን እየቀዘፉለት እስክንድሪያ አደረሱቱ። የምእመናን ወገኖችም ደግ ጠባቂያቸው እንደ ደረሰ በሰሙ ጊዜ በታላቅ ደስታ እየዘመሩ ተቀብለውታል፡
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
09 октября 2024 19:32
የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አሰራር ሥርዓት
እግዚአብሔር በባሕርይ ምልዓቱ የተነሳ የሌለበት ቦታ ባይኖርም ውስን ፍጥረታት እኛ ለሕሊናችን በሚስማማ ሁኔታ በውሱን ቦታ እንድናመልከው አዝዞናል፡፡ ይህም ለእኛ መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን እርሱም በእኛ በረድኤትና በጸጋ ላለመለየቱ የቃል ኪዳን ቦታ መሆኑ ነው። እስራኤልን
‹‹በመካከላችሁ አድር ዘንድ መቅደስን ሥሩልኝ›› ያላቸው ለዚህ ነው፡፡ ዘጸ ፳፤፱
ሰዎችም ምሕረትና ይቅርታ ረድኤትና በረከት ሲፈልጉ ወደዚህ ቦታ ይመጣሉ። የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንም ያለሥርዓት አትተከልም ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ ... የኩነኔ አገልግሎት በክብር ከሆነ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚሁ ነገር ክብሩን አጥቷልና ያ ይሻል የነበረው በክብር ከሆነ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ይሆናል፡፡›› ብሎ እንደተናገረው በሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የምትተካው ቤተመቅደስ ይህን ያህል ሥርዓት ከነበራት በሌላ የማትተካው በክርስቶስ ደም የተመሠረተችው ቤተክርስቲያን ይልቁንም እጅጉን ትከብራለችና በሥርዓት ትተከላለች ፪ቆሮ ፫፤፯-፲፩ ማንኛውም ቤተክርስቲያን በተለያየ ቅርጽ ቢሠራም
ሦስት ክፍል አለው፡፡ ይኸውም በሰሎሞን ቤተመቅደስ አምሳል ነው። ምክንያቱም ለብዙ ክርስትና እምነት ሥርዓት መሠረቱና ምሳሌው የብሉይ ኪዳን ሥርዓት ነውና፡፡
ሀ.
ቅኔ ማኅሌት፡- ስያሜው ከግብሩ የተወረሰ ነው፡፡ ይህ ክፍል በቤተ ክርስቲያን ከውጪ ወደ ውስጥ ስንገባ በመጀመሪያ የምናገኘው ክፍል ነው፡፡ መዘምራን ስብሐተ እግዚአብሔር ማኅሌተ እግዚአብሔር የሚዘምሩበት ነውና። በዚሁ ክፍል ሰሜን ምስራቅ በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት በመንፈቀ ሌሊትና በነግህ ሰዓታት ይቆሙበታል፡፡ በምዕራብ አቅጣጫ መዘምራን የሚዘምሩበት፣ ቅኔ የሚቀኙበት፣ ማኅሌት ቆመው የሚያስቀድሱ ሲሆን ንፍቅ ዲያቆናት፣ አናጉንስጢስና መዘምራን በዚህ ሥፍራ ያስቀድሳሉ፡፡ በዚሁ ክፍል ደቡብ ምስራቅ በኩል የሚገኘው ቦታ የሴቶች መቆሚያ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ወንድና ሴት አብረው መቆም ስለማይችሉ በመጋረጃ ይጋረዳል፡፡ በምሥራቅ የካህናት፤ በሰሜን የወንዶች፤ በደቡብ የሴቶች መግቢያ ይሆናል፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ በአራቱ ማዕዘናት አቅጣጫዎች አራት ወይም ሦስት በሮች አሉት፡፡
ለ.
ቅድስት፡- ቅድስት ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ የተመረጠ፤ የተለየ ማለት ነው፡፡ ይህ ክፍል የሚገኘው በቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ቦታ ነው፡፡ በምዕራብ በኩል ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ቆሞሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ሲሆኑ በሰሜን በኩል ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ደግሞ መነኮሳት፣ የሚቆርቡ ወንዶች ምእመናን ናቸው፡፡ በስተደቡብ በኩል ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ደግሞ ንጽሕ ጠብቀው የኖሩ ደናግል መነኮሳት እንዲሁም መአረገ ክህነት ያላቸው ቀሳውስትና ዲያቆናት ምዕመናን ናቸው፡፡
በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያኑ በአራቱ ማዕዘናት አቅጣጫ አራት በሮች አሉት። በቅዳሴ ጊዜ በስብከተ ወንጌል ሰዓት መምህራን ቆመው የሚያስተምሩበት ክፍልም ነው፡፡ ካህናት በድርገት ጊዜ ምዕመናንን የሚያቆርቡበት ቦታ ነው፡፡ በተክሊልና በቁርባን ለሚጋቡ ሙሽሮች ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸምበት ነው፡፡
በስቅለት ዕለት ሥርዓተ ጸሎት ይፈጸምበታል፡፡ ካህናት ኪዳን ዘነግህ ያደርሱበታል፡፡ የማይቆርቡ ምዕመናን በዚህ ቦታ ቆመው ማስቀደስ አይችሉም፡፡
ሐ.
መቅደስ፡- መቅደስ ስያሜው ከብሉይ ኪዳን ‹ቅድስተ ቅዱሳን› አሰያየም ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን በዚህ ውስጥ ኅብስቱ ወደ አማናዊ ሥጋ መለኮት ወይኑም ወደ አማናዊ ደመ መለኮት በጸሎተ ቅዳሴ የሚለወጥበት ሥርዓተ ቅዳሴው የሚመራበት ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት ነው። መንበረ ታቦቱና ሌሎችም ንዋያተ ቅድሳት በዚህ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ክፍል ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ያስቀድሱበታል፤ ቀሳውስትና ዲያቆናትን ጨምሮ በዚህ ክፍል ሥጋ ወደሙንም ይቀበሉበታል፡፡ ወደዚህ ክፍል ለመግባት የሚችሉት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ፣ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት፡ ቀሳውስትና ዲያቆናት ብቻ ናቸው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:-ሥራዓተ ቤተክርስቲያን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…